Monday, November 9, 2015

የውጩ ሲኖዶስ በወንጌል ጉዳይ ላይ የተሻለ አቋም እየያዘ ነው፤ አዳዲስ ጳጳሳትንም ሊሾም ነው።

Read in PDF

በብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ስደተኛው ሲኖዶስ 42ኛ ሲኖዶሳዊ ጉባኤውን በኮሎምበስ ኦሐዮ ከጥቅምት 24 እስከ 26 2008 ዓ.ም ድረስ አካሂዷል። ሊሞቱ ነው እየተባለ ሁልጊዜ የሚወራባቸው ብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ገና እንደ ወጣት ሰው በማሰብ በመከራከር በማመን እና በማሳመን ሲኖዶሱን መርተዋል ቅዱስ ፓትርያርኩም በተሻለ ጤንነት ሆነው ጉባኤውን ተካፍለዋል። ጉባኤው በሰላም እና በአንድነት መንፈስ የተጠናቀቀ ሲሆን ጥሩ የሚባሉ አቋሞችን ይዞ ታይቷል።
 የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት በሦስት የተከፈሉ መሆናቸው ይታወቃል። እነርሱም በአገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚመሩ፣ በውጩ ሲኖዶስ የሚመሩና ገለልተኛ ማለት ከሁሉም ሲኖዶስ የወጡ ናቸው። ይሁን እንጂ የየራሳቸው ሕግ ያላቸው በመሆናቸው ለየትኛውም ሲኖዶስ መመሪያ አይገዙም። ሲኖዶሱ አንድ ወጥ የሆነ ሕግ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ለማቅረብ ካሰበ ረጅም ጊዜ ቢፈጅም በቅርቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ተስማምቷል።

 የኦርቶዶክስ አባል ቁጥር እየቀነሰ የሄደበትን ምክንያት አጀንዳ አድርጎ በተወያየበት ጊዜ የሚከተሉትን ምክንያቶች ጠቁሟል። አንደኛ መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እያደረገ ያለው ተጽእኖ ነው ብሏል። ሁለተኛ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ዘረኝነትና በልሹ አስተዳደር የሚለውን ምክንያት አምኖብታል። ሦስተኛ ወደ አረብ አገር የሚሄዱ ሰዎች በድኅነት ምክንያት እምነታቸውን ስለሚቀይሩ ነው ብሏል። አራተኛውና የመጨረሻው ምክንያት ግን የቤተ ክርስቲያንን አይናማ ሊቃውንት መናፍቃን እያልን በማሳደዳችን፤እና  ለሕዝቡ ትክክለኛውን ትምህርት ባለማስተማራችን ነው በሚሉት ምክንያቶች አምኖበታል። 

  ወንጌል ያለምንም ገደብ እንዲሰበክ የሚለው የሲኖዶሱ ዋና መወያያ ነበር። በሲኖዶሱ ሥር የሚገኙ ሰባኪዎችን ተሐድሶ በማለት ከቤተ ክርስቲያን ለማስወጣት እየተደረገ ያለውን ሙከራ አጥብቆ የሚቃወመው መሆኑን የገለጠ ሲሆን ሕዝቡም ሰባኪዎቹን ከማነኛውም ጠላት እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል። አቶ ምርጫውና አቡነ መቃርዮስ ተሃድሶን እናውግዝ የሚል ሐሳብ አንስተው የነበረ ሲሆን በብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅ መጀመሪያ ተሐድሶ የተባልሁት እኔ ነኝ ይህ የጠላት ወሬ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ በማለት መልስ ሰጥተዋቸዋል። በሲኖዶሱ አባላት በግልም በጋራም በተደረገ ውይይት ወንጌል ሰባኪዎችን በሁሉም ነገር መደገፍ እንደሚገባ የታመነበት ሲሆን ራሳችን እያባረርን ቀነሰብን እያልን መጮህ የለብንም በማለት እጅግ ማስተዋል ያለበት አቋም ተይዟል። ይህ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደምም በማቅ የተገፉ ሰባክያንን በመደገፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረገ ታሪክ የማይረሳውን ሥራ ሰርቷል አሁንም በወንጌል እንዲህ ዓይነት አቋም ይዞ ከቀጠለ ትክክለኛው መንገድ ላይ ነው የሚል አስተያየት አለን። በሌላ በኩል ከዚህኛውና ከዚያኛው ሲኖዶስ እየተመላለሱ የሚያገለግሉ ካህናት በአንድ እንዲወሰኑ አሳስቧል። እዚያና እዚህ የሚረግጡ ሁሉ ከዚህ በኋላ እንደፈቀዱት አይሆኑም ወይ ወደዚያ ወይም ወደዚህ መጠቃለል አለባቸው ተብሏል።
የስያትሉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ የመምህር ልዑለ ቃልን ቤተ ክርስቲያን ተቀብለዋል በሊቀ ጳጳሱና በመምህር ልዑለ ቃል መካከልም እርቅ ተፈጽሟል። ስለዚህ የገብርኤልና የመድኃኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት በጋራ ሆነው ያገለግላሉ። የዳላስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንም በሲኖዶሱ ሥር እንዲጠቃለል ተወስኗል። ከዳላስ ሚካኤል የመጡ አቶ ሙሉዓለም የተባሉ ተወካይ የተቃወሙ ሲሆን ክብረ ነክ የሆኑ ቅላትን በመናገራቸው ብዙ አባቶች አዝነውባቸዋል። ቋሚ ሲኖዶሱ የሁለቱን አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት እንዲከታተልና በመካከላቸውን ያለውን ችግር እንዲፈታ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአትላንታ ቅድስት ማርያም የሚያገለግሉት አባ ኃይለ ሚካኤል አቡነ ያዕቆብን በተሃድሶነት ከሰው የነበረ መሆኑ ይታወቃል። ክሱ ከቅዳሴ በኋላ በመስቀል ይባርካሉ እና በወይን ይቀድሳሉ የሚሉት ይገኙበታል። ብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሁሉም ለክስ ለጠብና ለክርክር የሚያበቃ አይደለም ካሉ በኋላ ትክክለኛው ሥርዓት በወይን መቀደስ መሆኑን አስረግጠው አስረድተዋል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀር በዓለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በወይን ነው የሚቀድሱት ዘቢብ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለውም።
 በዚህ ጉባኤ ላይ ሌላው የተወሰነው አቢይ ጉዳይ የጳጳሳትን ሹመት ስለማጽደቅ ነው። ለአውሮፓ ለካናዳ ለአውስትራሊያና ለአፍሪካ አዳዲስ ጳጳሳት እንዲሾሙ ጉባኤው ያጸደቀ ሲሆን ይህን ጉዳይ የሚያስፈጽሙም ኮሚቴ ሰይሟል። በመጨረሻም የካልጋሪ ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁእ አቡነ ሚካኤልን ረዳት ጸሐፊ አድርጎ በመሾምና መግለጫ በማውጣት ገባኤው ተጠናቋል።
የግላችን ማሳሰቢያ
 ሁለቱም ሲኖዶሶች ወንጌልን እንስበክ የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ፣ ነገር ግን ከወንጌል ጋር እየተቀላቀለ የሚሰበከውን የተዳበለ ነገር በግልጥ ሲቃወሙት አይታዩም። ያለ ጊዜው ከሕዝብ ላለመጋጨት ጥንቃቄ እናድርግ ተብሎ ከሆነ እንስማማለን። አንዳድ አደገኛ ክህደቶች ሲሰበኩ ዝም ማለቱ ግን ለምን? ለምሳሌ ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም እያሉ የሚሰብኩ ሰባኪዎች ናቸውን? ይህን ልዩ ወንጌል የሚሰብኩ ሰዎች ባለ ዝና እና ባለብዙ ተከታይ ስለሆኑ ዝም ተብለዋል መዳን በኢየሱስ ነው የሚሉት ደግሞ መናፍቃን ተብለዋል። ሰባኪዎችን እናብዛ የሚለው ሐሳብ መልካም ቢሆንም ስለጥራቱ ግን ምንም ውይይት የለም። የሰው ኃይል በብዛት ማሰማራታችን ሳይሆን መታየበት ያለበት የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው ቅዱስ ወንጌል ያለምንም ሸቀጣ ሸቀጥ መሰበኩን ነው። ከዚህ ውጭ የተረት አባቶችን በብዛት አሰማርቶ ወንጌል እንሰብካለን ማለቱ እራስን ማታለል ነው። እንደ እኛ እምነት ብዙ ሕዝብ ከቤተ ክርስቲያን እየወጣ ወደሌላ እንዲገባ ያደረገው የተረት ስብከት ነው። ተረቱን ሲቃወም መናፍቅ ይባላል ዝም ብሎ እንዳይሰማ ሕይወት አይሆነውም ስለዚህ ብዙ አማራጭ ስላለው ትቶ ይሄዳል። እናም ብዛቱን ሳይሆን ጥራቱን ብንከታተል ያዋጣል የሚል ነው ማሳሰቢያችን።

23 comments:

 1. ለመሆኑ ሁከት ፈጣሪዉ አንዱዓለም ዳግማዊ ሰብሰባው ላይ የለም ወይ?

  ReplyDelete
 2. Orthodox for JesusNovember 9, 2015 at 5:35 PM

  የ ኦርቶዶክስ አማኝ ቁጥር የቀነሰው አናንተ አባት ተበየዎች አባት መሆን ሰላልቻላችው ነው። ክርሰቶስ በሕይወታቸው ፈፅሞ የለም።
  " እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። "
  (ትንቢተ ኤርምያስ 10:21)
  " ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?"
  (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:17)
  ለመሆኑ እናንተስ ገዘረኝነት ንፁ ናችሁን? ጌታችን እየሱስ ከርስቶስ ልቦናችንን ያንፃልን!

  ReplyDelete
 3. ብዙ ሕዝብ ከቤተ ክርስቲያን እየወጣ ወደሌላ እንዲገባ ያደረገው የተረት ስብከት ነው። ተረቱን ሲቃወም መናፍቅ ይባላል ዝም ብሎ እንዳይሰማ ሕይወት አይሆነውም ስለዚህ ብዙ አማራጭ ስላለው ትቶ ይሄዳል። እናም ብዛቱን ሳይሆን ጥራቱን ብንከታተል ያዋጣል

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ab yaltekelew hulu yinekelal. Enkuan teret hone lemin atitewunim teret ketelachu? Hidu wede Getochachihua. Endee?

   Delete
 4. የቸገረው እርጉዝ ያገባል ይላል ያገሬ ሰው ያሉንም ፓፓሳቶቻችን ስረአቱን በጠበቁልን።እንደው መድሃኒያለም ልብ ይስጣችሁ የዝመኑ ፍጻሜ እየደረሰ ስለሁነ ይህን ልናይ ልንሰማ ግድ ይሆንብናል የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።እንደው ለናንተ ተረት ብላችሁ ያላችሁት ሃይማኖት አኮ መጀመሪኣውንም ፓፓሳት ስይሆን ማዘጋጀት ያለባችሁ እንደው ለይቶላችሁ እንደፕሮቴስታንት ሃይማኖት ፓስተሮችን ብትሉ መልካም ነው።እና እናንተ ኤትዮጵያዊ ነን ትላላችሁ ዘር አሰዳቢ ይሏችኋል እንደዝህ አይነቱ ነው። እግዚያብሄር ወደቀድሞዋ ሃይማኖታችን ይመልሰን የፓፓስ ብዛት ሳይሁን አሁን የውጩ ሲኖዶስ የሚኣያስፈልገው የሃይማኖት ጥራት ነው።የትሃድሶ ስረአት የሚያስፈጽም ፓፓሳት አያስፈልገንም።ህዝቡም ነቅቶባችኋልና ጥንቃቄ አድርጉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewunet new Tehadiso tenektobetal.

   Delete
 5. እኔ በጣም የሚገርመኝ እናንተ ብቻ የወንጌል አስተማሪ አድርጋችሁ እራሳችሁ ታስቀምጣላችሁ፡፡ ይሁን እናንተ ወንጌላውያን ነን የምትሉ፡፡ እስኪ ገጻችሁን ተመልከቱት በእውነት አሳፊሪ ገጽ፤ ስድብ፣ነቀፋ፣ ትእቢት የሚያስተምር ገጽ ነው፡፡ አንድ እንኳን ደህና ተብሎ የሚለቀም ፍሬ ተበልቶ ሕይወት የማይሰጥ ገጽ ነው፡፡ የናንተ ወንጌል ስድብና ነቀፋ፣ ጥርጥር የሚሰብክ ገጽ እንዴት ነው እግዚአብሔር ይህንን ገጽ የሚጎበኘው????????????????? እናንተ ብሎ ለወንጌል ትምህርት ተቆርቋሪ፡፡ ወንጌል እኮ እራስህ ሳትበራ ሰው ልታበራ የምትችልበት መንገድ አይደለም፡፡ ጨለማ እንዴት ብርሀን ሊሰጥ ይችላል???????????????? ጨለማነቱን ተቀብሎ ከብርሀን ተበድሮ እንኳን ብርሀን መስጠት የማይችል፤ የሚበሩትን ብርሀናቸውን እያጠፋ በጨለማ የሚመላለስ ሰው እንዴት ሆኖ ነው ስለወንጌል ብርሃን ሊሰብክ የቻለው ይሁን???? ኧረ ኧረ ኧረ እኔ ኃጢያተኛዋ እንደዚህ ካሳዘነኝ ንጹሀን ክርስቶስ እንዴት ያዝን????????????????????????

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ene demo yemigermegn ewneten lemekebel hule Erasachenen yalemazegajetachen newe. Ebakachehu semi kale wengel endisebek enji Teret be geez endiwera be amaregna zeye Yeminageru ortodox lealaw tehadeso yemibalew eskemeche newe? Biyans be sebakiyan ley yemideregewn xelacha be krestenaw Ayn ayten sehetetm kale endiyastekakelu Be feker yemnekerbachew meche newe? Le lealaw wengelen lemesbek mejemeriya erasachen feker linoren yigebal.

   Delete
 6. ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀር በዓለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በወይን ነው የሚቀድሱት ዘቢብ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለውም። Is that true?

  ReplyDelete
 7. ሙሉዓለም የሚባለዉ የዳላስ ሚካኤል ተወካይ ሰዉየ አንዱአለም ዳግማዊ በአምሳሉ በክፉ ገብር የወለደው መሆኑን ስብሰባዉ ላይ በሚናገረዉ የልተገራ አንደበት በማየቴ አዝኛለሁ

  ReplyDelete
 8. This is the sign of the times!!!!! Where the likes of the Merchaw, Mulualem, Andualem, their chronies, etc. dictate how a synod should run its affairs, a Synod that rejects the instructions of a Patriarch, Arch Bishop that ignores and oppresses the rights of the flock. This is a Synod that has lost its zeal and responsibility to shepherd its flock, cannot enforce its teethless rules and regulations, comes together for formality once every six months and declare all the flowery positives. Where are the checks and balances? Are we all sitting on the sidelines and let Woyane infiltrate these power hungry self righteous zealots destroy our religion? This should behoove those that have attended this so called Synod meeting to report all they know and heard to the "christian" world that follows them so that everyone knows what and who they really are! and what they stand for! Then, Maybe! just Maybe! a change might dawn on this Synod for it to come out its Woyane Shell and teach and preach the GOSPEL OF JESUS CHRIST to us the hungry and distraught disciples.

  ReplyDelete
 9. አገር ቤትም ወጭም የላችው አባት ተብየዎች፦ biological አባት ሆናችው ሰለማታውቁ አባት ለተባላችውባቸው ልጆቻችው ምንም ግድ የላችውም። እናንተን ግድ የሚላችው ሆዳችውና ምቾታችው ብቻ ነው።ሕዝቡ በጥንቆላና በገድል የዘላለም ሕይወቱን ሲያጣ እናንተም አብራችው ወደ ሞት ፍርድ ሰትጓዙ ሳይ በጣሙን አዝናለው። " ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"
  (የዮሐንስ ወንጌል 14:6)

  " የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።"
  (የዮሐንስ ወንጌል 12:48)
  ያዋቂ አጥፊ በጣም ያስጠላል!

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are funny
   Do you want them to choose the way you already started .You way is only to meet your worldly matters.But, They belong to the spritual and angelic world.But I don#T mean getting married is a sin. I guess you are anti Orthodox Tewahedo church and anti monastic life wether they are real or false monks We must live to GOd for His judgement

   they shouldn't be biological fathers to lead the Church and serve properly.You are less educated , narrow minided and fanatic heretic. Please confess from this moment onward

   amen
   see u

   Delete
  2. The commentator wrote in his native language clearly. You can't throw a word that he is less educated. Let me tell you, you are less educated in English language. Your grammer and spelling errors are the indicator.

   Delete
  3. እንግሊዘኛህ ቢወለጋገድም መልክትህን አስተላልፈሀል። 'less educated' ያልካትን እራስህን ተመልከትበት። እኔ መንፈፅ ቅዱሰ እየሱስ ጌታ አንደሆነ ገልጦና አሰተምሮኝ ዳግም ምጣቱን አየጠበኩኝ እኖረለው። So, I am well educated and annoited by the Holy Spirit. I am a follower of Jesus of Nazareth, not human beings. Here is my little advice for you read a bible with out biased start from gospel of John, when you read don't read in to it , but from it. I ask Lord Jesus Christ to visit you, and touch you. Finally, I going to tell you that I am not anti Orthodox, but I am anti unorthodox. Jesus is the Lord!!!!!!!

   Delete
 10. ኅዳር 1 ቀን 2008 ዓ.ም.
  እናንተ ደካሞች እናትን ጠልቶ ልጅን መውደድ እንዴት ይቻላል? ከነ ሉተርስ በምን ትለያላችሁ? ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት፣ አምላክ፣ ወልደ አምላክ ነው፡፡ ወዴት፣ ወዴት ጠጋ ነው? ከእግዚአብሔር ባለሟልነትን ያገኙ ቅዱሳን ደግሞ ያማልዳሉ፤ ቅዱሳት መጽሐፍት ከብሉያት እስከ ሐዲሳት ተባብረው የሚመሰክሩት ስለሆነ የሐሰት ቅርሻታችሁን የሚሰማ የለም፡፡ የማርያም ክብር ደግሞ ከቅዱሳን ሁሉ ክብር ስለሚበልጥና ምልዕተ ፀጋ ስለሆነች የማማለድ ፀጋ አላት፡፡ ስለሆነም ‘ቅድስት ሆይ ለምኝልን’ ብለን እንጠራታለን፡፡ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ፣ የምህረት ቃል ኪዳን ፍጻሜ-ኪዳነምህረት ብሎ የማያምን ትውልድ ክርስቲያን አይደለም፡፡ ስለሆነም መንግሥተ ሰማያትን አይወርስም፡፡ በነገራችን ላይ ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚጠላ ዲያብሎስና የግብር ልጆቹ ብቻ ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዴት እንዳሳደደና እንደ ወደቀ ከዘሯ የተረፉትን ልያሳድድ የባሕር አሸዋ ላይ እንደቆመ ይነግረናል፡፡ ራእይ 12፡፡ እንግዲህ የባሕር አሸዋ የተባለው የእንደ እናንተ ዓይነቶቹ የመናፍቃን ልቦና መሆኑ አይደለም ወይ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. I believe time has come, what you do doesn't matter any more you all are worried about the Money and how Memeher Lulekale will become rich and what is in it for you Abatoche (Yeweshet Abatoche) Please the people are wake now don't tell us we need more of the same Abunu Yakobe who is he? what has he done? other than making us fight one another, NOT TO TELL THE TRUTH, Every since he has been in our church not telling truth including when we bring Memeher Lulekal from Ethiopia he told everyone he was Kasse Untl he was on the flight to Atlanta then he said oh He is not Kasse Do you deny that Abune Yakobe? then I was shucked including Mesfin who was a secretory at the time. who is no longer with us because of this Abune Yakobe false story. Does this makes him Yetkeberu, so called synod. you can pass and say anything you want to say, one thing is true is people know what is the truth and we going to go forward with that. how come you think you are doing God work by dividing us you cant go to this church and that and you know the bible? yes Abune Yakobe don't have the ability to go to do anything other than what people don't have time to listen to his this and that story. as I was told he spend most of his time on the phone, how he can divide us. people want to know about bible and true orthodox believe who is Abune Melekesadik he was once want to go Ethiopia and want to be Mr. P but didn't work Yes who he think he is he might be damaging our religion more than any other one damaging it. " I was once were told I am Tehadeso" so what is the big deal "if he feet we must not Quit" we must tell him like it is or those who are around him will tell him the news may God tech him a listen and guide him to come to his full sense. for me not telling the truth is big fact knowing the Patric Abune Merkorios is unable to talk and do anything they pretend all is good and he gave a blessing and lead the meeting? that is not true he did not give any kind of Blessing why tell something it is not true? who are you tiring to mislead? Tell us the truth you are the worst of any human can be. I mean it. I have nothing to loss not even afraid of anyone of you because I am telling the truth. you all are hypocrite who say me me me you have forgot you are misleading so money Chastain who want to get blessing from Abune Markorious at any cost but you all are devil who are seating next to him for photo so you can mislead all of us. not working what we have to be carful is those who act and deny the facts like Abune Melkesadik. Aba Gebreselassia, Aba Woldetensye, Memeher Lulekale are a few to mention. I don't care what they believe but they need to tell the truth and do what they want but don't divide us while so money honest Christian are thinking you are as good as God because you mislead them with your mouth. you know as a Christian I have hurt come out of the box and let us forgive each other. it is not bad to do bad but doing it knowing you are misleading so money Christian is something you will face when you are alone you will not have pace to yourself and your family. those who have family like Memeher Lulekale or who knows some of you might have one and you have deny your family and pretend like Fetsume.

   Delete
  2. ስድቡን ምን አመጣው የድንግል ማርያም ልጅ እኮ ተሳዳቢ አይደለም!!የስድብ አፍ ተሰጠው የሚለው ዲያቢሎስን ነው ታዲያ ማነው የድንግል ማርያም ልጅ?ተሳዳቢው እርሶ ነዎት ወይስ ሌላው?አንዳንድ አበሻ የሚያምነው በስድብ ነው በማሳመን በንግግር አያምንም በጩኸት በዱላ በድብድብ መቼ ነው ከዚህ የምንላቀቀው??በሉ ሁሉን ተውትና ንስሐ ግቡ ስድብ ይቁም ሃሳብዎን በትህትና ቃል ይግለጹ!እንዳሉት ዓለም በሙሉ ከእርስዎና ከመሰሎችዎት በስተቀር ወደ ገሃነመ እሳት ይገባል አይደል?ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣውና መከራውን ያየውና መስቀል ላይ የተሰቃየው የተባለ ፍጡር በእመቤታችን ካላመነ ገሃነም እሳት ለመክተት ነው አይደል?የዋህ ነዎት እኮ እባክዎ! ለምን በትክክል በጽሞና መጽሐፍ ቅዱስን አያነቡም የተረጎሙት እኮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አባቶች ናቸው።ማን መስሎዎት ነው ወንድሜ?ደግሞ ጥቅስ ሲጠቅሱ በቦታው ቢሆን ያለቦታው የሚጠቀስ ጥቅስ ወጥ አድርገው እንዳላነበቡት ይታወቃል እኮ!ለመሆኑ እዚያ ቦታ ቅድስት ድንግል ማርያም የሚል አለ እንዴ?ታሪኩ የሚናገረው ስለእስራኤልና ስለመሢሁ ወይም ስለክርስቶስ አይመስልዎትምን?ለምን መሳቂያ ይሆናሉ?ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል የተባለው ቃል ይህ ይሆንን?እግዚአብሔር ማስተዋል ይስጥዎት!!
   ኒቆዲሞስ

   Delete
  3. Hold on guys! don't fight! we are making devil to be happy? he is our enemy. Please pray God to answer all your questions and puzzles in your life by Jesus name. Lord Jesus is Coming soon, probably in our time, we've seen all the signs of his second coming. The following is one of them , what I am figure out at this time:
   " ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።"
   (የማቴዎስ ወንጌል 24:12) The good news is we have Jesus , please! read a bible!

   " ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።"
   (የዮሐንስ ወንጌል 14:1)
   " ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።"
   (የዮሐንስ ወንጌል 14:14)
   " ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።"
   (የዮሐንስ ወንጌል 14:21)

   Delete
 11. ቃለ አዋዲ በስልክ ወንጌልን ይሰብካል ።ተወንጌል ጠላቶች ደግሞ ፀረ ተሀድሶ ብለው በስልክ ግሩፐ ክፍተው ሁከት ይነዛሉ።እኔስ ከነሱ መሰረተ ቢስ ከማይጠቅም ሁከታቸው ወንጌሉ ያንፀኛል።ይህነ ሁሉ ጊዜ ወስደዉ ከሚያውኩን ለምን ትምህርት አያስተምሩንም? ?ህዝቡ ተሳደቢ እና ስም አጥፊ የሆነው ወንጌል ካለማወቁ የተነሳ ነው።በዚህ ጉዳይ አበቶች ሆይ ፍርድ አለባችሁ።መንጋውን በለመለመ መስክ አላሰማራችሁምና ከፍርድ አታመልጡም።

  ReplyDelete
 12. Why don't write a new Scripture? I think you are living in dark.

  ReplyDelete
 13. Why Abune Yakobe this is not good, I know you didn't want to forgive and foget you must be very bad may God help you. Please Pry that will help. it won't make any difference whether this Seyn say this and that what matter is our hurt. and what you know. you know the fact more than anyone so let it be it.

  ReplyDelete
 14. I believe the Ethiopian Orthodox church is losing members because it is just preaching air not doing any tangible that is measurable. I lived in my city for over 25 years and I have been a member of two churches for a long time. The church leaders (priests, bishops) have never taken leadership to help our communities in times of hardship. There are many homeless, mentally sick, disoriented Ethiopians who need assistance from our church. But whenever the homeless or the sick and poor die, the priests step up their game of their nonsense Fetat Kedasse. Please change your game, serve your community that is paying your livlehood. Open the church to our homeless Ethiopians who are dying from loneliness and hunger, walk the street and talk to your community to find out about our youth who need guidance. Your once a week Kedase is so hollow and shallow that it does not hold water. No substance! No good deed! No members. I promise you, you may have the older generation but you sure have lost the youth. So my advice is change your game!!

  ReplyDelete