Tuesday, December 29, 2015

ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ልታቋቁም ባቀደችው የቴሌቪዥን ጣቢያ ገና ከጅምሩ ሊፈጸምበት የነበረው ሙስና መክሸፉ ተሰማቅዱስ ሲኖዶስ በዘንድሮው የጥቅምት ስብሳባ ላይ እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኒቱ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ማለትም የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ልትጀምር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው ጥናት ላይ መሠረት በማድረግ የአንድ ዓመት በጀት 12 ሚሊየን ብር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቋል፡፡ ይህን ፕሮጀክት የሚመራ ቦርድ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ሃላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ሐሳቡ በመጀመሪያ የመነጨውና እንቅስቃሴው የተጀመረው ጉዳዩ ግድ ከሚለው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሲሆን፣ የሰውን ሐሣብ በመንጠቅና የራስ አስመስሎ በማቅረብ በተግባር የተመሰከረላቸውና የሰዎችን ድርሰት በራሳቸው ስም በማሳተም ጭምር ቅሌት ውስጥ የገቡትና እስካሁን በሲኖዶስ ተጠያቂ ያልሆኑት አባ ሳሙኤል ይህን የስብከተ ወንጌልን ፕሮጀክት በመንጠቅ በሌላቸው ውክልና የራሳቸው አስመስለው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሐሳቡን ራሳቸው ያመነጩትና የጀመሩት ያህል በመቁጠር ስለጉዳዩ የማቅ ልሳናት ሆነው እያገለገሉ ባሉት እንደ አዲስ አድማስ ባሉ ጋዜጦች ላይ ጉዳዩን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ እንደነበር የጥቅምት 20/2008 አዲስ አድማስ ጋዜጣን መመልከት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም ከቦርዱ እውቅና ውጪ በስልት መንቀሳቀሳቸው ስለተደረሰበት የጉዳዩ ተዋናዮች ለነበሩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ከቤተክህነት አካባቢ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሊቋቋም የታቀደው የቴሌቪዥን ጣቢያ እስራኤል አገር ሲሆን፣ ባለፈው ሰሞን አባ ሳሙኤል ከዚህ ጋር ባልተያያዘ ለህክምና በሚል ፓትርያርኩን ፈቃድ ጠይቀውና ደብዳቤ አጽፈው፣ በጎን ደግሞ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ የአቡነ ማርቆስን ውክልና ወስደው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል  ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አባ ሃይለማርያም የፈረሙበትን ደብዳቤ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለመዋዋል ሙከራ አደርገው ነበር፡፡ ይህ የሆነው አባ ማቴዎስ ከሲኖዶሱ ስብሰባ በኋላ እምብዛም በቢሮ የማይገኙ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ 

Monday, December 28, 2015

ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳውያን ኮሌጆች ላይ በከፈተው የጽሑፍ ዘመቻ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነውራሱን ብቻ ትክክልና የቤተክርስቲያን ጠበቃ አድርጎ የሚመለከተውና ሌላውንና የእርሱን ተረት አልከተልም ያለውን፣ በአሰራር እንኳን ለእርሱ አልመች ያለውን ሁሉ መክሰስና ስሙን ማጥፋት ልማዱ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያወጣ ባለው ስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ሶስቱን አንጋፋ መንፈሳዊ ኮሌጆች ማለትም የቅድስት ሥላሴ፣ የመቀሌው ከሳቴ ብርሃንና ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆነዋል በማለቱ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡
ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን አለአቅሙ ሊዘልፋቸው የተነሳው እነዚህ ሦስቱ ኮሌጆች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የሚንቀሳቀሱና የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት የቤተክርስቲያኒቱን ራዕይ ያሳካሉ የተባሉ ኮሌጆች ናቸው፡፡ ኮሌጆቹን የመሠረትዋቸው ሰዎችን እንኳን ብንመለከት ለትምህርትና ለለውጥ ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ አባቶች ፍሬ መሆናቸውን እገነዘባለን፡፡ ለምሣሌ የቅድስት ሥላሴ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቴዎፍሎስ፣ የከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ መሥራች ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፣ የሰዋሰው ብርሃን ደግሞ የአጼ ኃ/ሥላሴ ምስረታ ውጤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤት እስከ ሚኒስቴር ደረጃ የደረሱ ደቀመዛሙርት ወጥተውባቸዋል፡፡ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን እንኳን ብንመለከት የቅ/ሥላሴ ኮሌጅ እንደ አይን ብሌን የሚያሳሳ ኮሌጅ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ይቅርና አሁን በሕይወት ያሉም የሌሉም አባቶች ሊቃውንት ወጥቶውበታል፡፡ ለመጥቀስ ያህል፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ፕሮፌሠር ሉሌ፣ ዶ/ር ሐዲስ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፣ አቶ እሱባለው፣ አቶ አእምሮ ወንድምአገኘሁ፣ አቶ ገ/ክርስቶስ መኮንን፣ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ስርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ፣ ፕ/ር ታደሰ ታምራት በመጀመሪያ የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ በየተሰማሩበት መስክ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ የተንቀሳቀሱና በጎ አሻራቸውን ያሳረፉ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡

Friday, December 25, 2015

ማሙዬ በፎርጂድ ዲግሪ መቀጠሩ በመረጋገጡ ታሰረበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየውና ባልዋለበት ሙያ መጋቤ አእላፍ የሚል ማዕረግ የተሸከመው ማሙዬ እንደ ባልንጀራው ታዴዎስ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ቅሌት ሰሞኑን ለእስር መዳረጉ ተሰማ፡፡ ማሙዬ በሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ እንዳለው ተደርጎ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በነበራቸው የውስጥ ስምምነት የማቅን ተልእኮ ይፈጽማሉ ተብለው ከታሰቡትና በሀገረ ስብከቱ ቦታ ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ እስጢፋኖስ ሀገረ ስብከቱን ለማቅ ለማስረከብ ውስጥ ለውስጥ ሲሰሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ማሙዬ በደብረ ብርሃን ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬምን ከፖሊሶች ጋር ተመሳጥሮ በመኪና ሲሄዱ መሳሪያና የጥንቆላ መጽሐፍ ይዘዋል ብሎ ሊያሳስራቸው ሲሞክር ጉዳዩ ውሸት ስለሆነ ስራ አስኪያጅነቱ ተባርሮ የነበረ ቢሆንም የማቅ አባል ስለሆነና በመሰሪነቱ ለማቅ ስለሚጠቅም ግን አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀጠር መቻሉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

Saturday, December 19, 2015

ግጭትና ጦርነት የማያስተምራት አገር

ስለራሳችን እንዲህ እንናገራለን ፦
-      እንግዳ ተቀባይ ሕዝቦች ነን ፤
-      ብዙ ብሔር ብሔረሶችና ሕዝቦች ተዋደው የሚኖሩባት አገር አለን ፤
-      ለቁጥር የሚታክት “ክርስቲያን” ፣ እልፍ አዕላፍ ገዳም ፣ መድረክ የሚያጨናንቁ አገልጋይ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናትና ዘማርያን አሉን ፤
-      ከእኛ ወዲህ ማን አለ አማኝ? ከእኛ በላይ ጸዳቂ ፤ ታማኝ አገር ወዳድ ወዴት አለ?! …
ስንታይ ግን፦
-      “ባዕድ እንግዳ” ለመቀበል ሆዳችንን እንደአገር ስናሰፋ ፥ ከጎረቤትና ከወገናችን ጋር ግን “ጠብ ያለሽ በዳቦ” በሚል መንፈስ የተያዝን ፤
-      አገልጋዮቻችን ጸንሰው ወልደው ፣ አሳድገው የሰጡን አንዱ መልክ ዘረኝነትና ልዩነት ነው ፤
-      ከእኛ በላይ ሁሌም ሰው የለም ብንልም ዘወትር ግን እየኖርን ያለነው ከሰው በታች ጅራት ሆነን ነው …
     ሰሞኑን በከፊል የአገራችን ክፍል ብጥብጥና ሁከት ፤ ደም ማፍሰስና ግድያ ነግሶ ነበር፡፡ ይህን ሁሉ አድራጊው ሌላ ወራሪ ወይም እንግዳ አሸባሪ መጥቶብን አይደለም ፤ ሟችም እኛው፥ ገዳይም ያው እኛው ኢትዮጲያውያን ፤ ንብረት አውዳሚም፥ ንብረት የሚወድምበትም ያው የአንድ አገር ዜጎች ፤ የአንድ ርስት ወሰንተኞች ፤ የአንድ ወንዝ ጠጪዎች እኛው ነን፡፡
 
      እስኪ አስተውሉ፥ አንድ መቶ ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በእኛና እኛ መካከል የተደረጉ ጦርነቶችን ብናነሳ፦ በ1909 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በንጉሥ ሚካኤል መካከል በሰገሌ ፣ በ1922 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በራስ ጕግሳ በአንቺም ወይም በበጌምድር ፣ ከ1966-1983 ዓ.ም ወታደራዊው መንግሥት ደርግና ኢሕአዴግ በተለያየ ቦታ ያደረጉት አስቀያሚ ጦርነት ፣ በ1994 ዓ.ም ሁለቱ “ወንድማማች” ኢትዮጲያና ኤርትራ ያደረጉትን ጦርነት (ወታደራዊው መንግሥት በአንድ ጉድጓድ የፈጃቸው የንጉሡ ዘመን መሪዎችና ሌሎችም ሳይካተቱ) ይህን ሁሉ ስናነሳ ምን ይታወሰናል?!

     በእውኑ እኛ ነን ተቻችሎ አዳሪ? እኛ ነን ለእግዚአብሔር ቀናተኞች? ከእኛ በላይ አማኝ ፤ ከእኛም ወዲያ ክርስቲያን የሚባልልን በእውነት እኛ ነን?! እኔ የፖለቲካ ተንታኝ አይደለሁም፥ ዳሩ ይህን አምናለሁ ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግ ፣ ማኅተመ ጋንዲ ፣ ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጦር ሳይመዙ ፣ የጥይት ባሩድ ሳያጤሱ ለሕዝቦቻቸው ነጻነትን ያጎናጸፉ ምርጥ የነጻነት ታጋይ ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ እኒህ መሪዎች ከሕዝባቸው እኩል መከራ ተቀብለዋል ፣ ተርበዋል ተጠምተዋል ፣ በእስር በግርፋት ተሰቃይተዋል ፤ በፍጻሜው ግን ዘረኞችን ድል አድርገዋል፡፡

Tuesday, December 15, 2015

ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ እንደ ገና ሊጤኑ ይገባልRead in PDF
ከዘሩባቤል
በቅድሚያ የጳጳሳት ጉባኤ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በግብረ ሐዋርያት እንደ ተጻፈው ሐዋርያትን አብነት አድርጎ የሚሰበሰብና ለቤተክርስቲያን (ለተቋሙ ወይም ለምድራዊ ድርጅቱ ሳይሆን ለማኅበረ ምእመናኑ) እድገትና መስፋፋት በዓለም ላይ ለሚኖራትም በጎ ተጽዕኖ የሚበጁ ውሳኔዎችን በመወሰን እንደ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ቢሠራ “እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል” እስከማለት የደረሰ ሥልጣን እንዳለው መረዳቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህን ሥልጣኑን ከዚህ ውጪ የሚጠቀምበት ከሆነና ለእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ክብር፣ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ጥቅም የሚበጁ ውሳኔዎችን የሚወስን ከሆነ ግን በውሳኔዎቹ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተባባሪ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ውሳኔዎቹ የሰዎቹ ብቻ ይሆናል፡፡ ውሳኔዎቹም የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን አያልፉም፣ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ክብደታቸው ይቀንሳል፣ ተቀባይነትም ያጣሉ፡፡ ባለፈው ጊዜ እንኳን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ስማችሁ የለም” በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እኛ ተነክተናልና መጽሐፉ በሊቃውንት ጉባኤ ይታይና ውሳኔ ያግኝ ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ውሳኔው በገዛ እጁ ቀሊል ሆኖ ስለተገኘ  የትም እንዳልደረሰ ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ውሳኔው አጀንዳውን ያነሱት ጳጳሳት ለራሳቸው ክብር ከመጨነቅና ጉልበታቸውን ለማሳየት ከመፈለግ የወሰኑት እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ከማሰብ የቀረበና በሲኖዶስ መታየት የነበረበት ጉዳይ ባለመሆኑ ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስለኢየሱስ “አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ ምስክርነትን በሰጠ ጊዜ ኢየሱስ ይህን ሰማያዊ አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አልገለጠልህም ብሎ ብፁዕ መሆኑንና በእርሱ ምስክርነት ላይ ቤተክርስቲያን እንደምትመሠረት ተናገረለት (ማቴዎስ 16፡16-19)፡፡ እዚያው ምዕራፍ ላይ ዝቅ ብሎ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠላቸው ጊዜ ከሰማያዊው አባት የሰማውና ብፁዕ ነህ የተባለው ጴጥሮስ፣  እዚህ ላይ ከሰይጣን ሰምቶ ጌታን ወደ እርሱ ወስዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም” ብሎ ሊገሥጸው ሲጀምር ኢየሱስ ዘወር አለና ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” (ማቴዎስ 16፡21-23)፡፡ 

Monday, December 14, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ስምንት


Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
3.  ድህረ ውግዘት ልናደርገው የሚገባን ጥንቃ
3.1.አውግዞ መለየት በቂ አይደለም

“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ የበደለውን አውግዘህ ብትለየው በውጭ አትተወው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መልሰው እንጂ፡፡ የጠፋውንም ፈልግ፡፡ ስለኃጢአቱ ብዛት እድናለሁብሎ ተስፋ የማያደርገውን በሁሉ ጠፍቶ ይቀር ዘንድ አትተወው፡፡ እንዲህም ኤጲስ ቆጶስ የኃጥኡን ኃጢአት ሊሸከም ይገባዋል፡፡ እርሱም ፈጽሞ እንደበደለ
ያድርግለት፡፡ የበደለውንም “አንተ ተመለስ እኔም ስለእኔና ስለሁሉ በሞተው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምሳል ስለአንተ ሞትን እቀበላለሁ ይበለው፡፡”

(ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.122)

    ኃጢአትን በግልጥ በመሥራቱና ብዙዎችን ስለማሰናከሉ የተወገዘ ሰው፤ ፈጽሞ ሊጣልና ሊወረውር አይገባውም፡፡ ምንም እንኳ ቃሉ “እንደአረመኔና እንደቀራጭ ይሁንልህ”(ማቴ.18፥17) ቢልም፤ “ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ቢፈረድም” (1ቆሮ.5፥5) አውግዘን የለየውን “ወንድም” ዳግም ልንፈልገው፤ ከደጅ ወደ ቤቱ ልንመልሰው “የቀጣንህ ቅጣት ይበቃሐልና ፤ ከልክ ባለፈ ሐዘን አትዋጥ ይልቅ ተመለስና ተጽናና … በክርስቶስ ፊት ይቅር ብለንሐል፡፡”(2ቆሮ.2፥6-11)
   ጌታ ኢየሱስ በዱርና በጫካ የጠፋውን፤ የባዘነውን በግ አዳምን ሲፈልገው (ሉቃ 15፥3-7)ብዙ ዋጋ ከፍሎ ነው፡፡ “ኤጲስ ቆጶሳት ሆይ መድኃኒታችንን ንጉሳችንን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት ልታደርጉት ይገባችኋል፡፡ ጉበኞችም ልትሆኑ ይገባችኋል፡፡ እርሱንም ምሰሉት የምትራሩ ሰላምንም የምትፈልጉ ትሆኑ ዘንድ፡፡ … ኃጥእ ፩ ጊዜ ወይም ፪ ጊዜ ቢበድል ንቀህ ከአንድነት አትለየው፤ በምግብ ጊዜ ከእርሱ ጋር ተባበር አንጂ፡፡ንስሐውንም ተቀበል ፡፡ተጸጽቶ ወደአባቱ በተመለሰው ልጅ አምሳል (ሉቃ.15፥17-24) ልብስ አልብሳቸው፡፡ በጥምቀት ፈንታ እጅ በማኖር ባርካቸው፡፡ ንስሐ የሚገቡ ሰዎች በእጃችን በመባረክ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ያገኛሉና፡፡ ወደ ቀደመ ቦታቸውም መልሳቸው፡፡      (ፍትሐ ነገስት አን.5 ቁ.126፤132)
     እንግዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና የቤተ ክርስተያናችን ቀኖና ይህ ነው፡፡ አውግዞ መለየት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ መልሶ ማየትና መፈለግ፤ እድል መስጠት ይህን ሁሉ አድርገን በተመለሰ ጊዜ ይቅር ልንለው ይገባናል፡፡(ሉቃ.17፥3)

Tuesday, December 8, 2015

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሃይማኖት አልባውን ዘሪሁን ሙላቱን አባረረሃይማኖት የለሽ በመሆኑ የሚታወቀውና በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ጥናትና ምርምር ሥራ ላይ የተመደበው ዘሪሁን ሙላቱ ከሥራ ተባረረ፡፡ ላለፉት 4 ወራት በሥራ ላይ የቆየው ዘሪሁን የተባረረው ከ10 ገፅ በላይ የተሣሣተ መረጃ አዘጋጅቶ የኮሌጁ የበላይ ኀላፊ አቡነ ጢሞቴዎስና መምህር ግርማ ባቱ ኮሌጁን ለመናፍቃን አሳልፈው ሊሰጡ ነው በሚል ለአቡነ ማቴዎስ እና ለአቡነ ሉቃስ የተሳሳተና ስም የሚያጠፋ መረጃ በመስጠቱ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቸሬ አበበ የኮሌጁን ዌብሣይት ለግል ጥቅሙ በማዋል “ኦርቶዶክስ መልስ አላት” የሚለውን ሲዲ የኮሌጁ ልሳን አስመስሎ በዚያ ላይ ሲያስተዋውቅ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኦርቶዶክስ መልስ አላት የተሰኘው ሲዲ ዘሪሁን የእግዚአብሔርን ቃል እያጣመመና እየሸቃቀጠ ያቀረበበት ሲዲ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ ሳትወክለው የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን ሲያሳስትበት እንደ ነበረ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዘሪሁን ኮሌጁንና ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፅሁፎች በዌብሳይቱ ያወጣ የነበረ ሲሆን በዚህ ድርጊቱ የኮሌጁን ክብርና ምስጢር አልጠበቀም፡፡ በዚህ ድርጊቱ “ዘዳግም ቸሬ” ተብሎአል ቸሬ አበበ የተባረረበት አንዱ ምክንያት ይህ ነውና፡፡

Thursday, December 3, 2015

ውግዘትና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት - ክፍል ሰባት


Read in PDF 
በዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
ካለፈው የቀጠለ
2.   በውግዘት ጊዜ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ
     ነገሩ በምስክር ተረጋግጦ፤ ትምህርቱ ወይም ድርጊቱ ብዙዎችን ያሰናከለና እያሰናከለም ያለ እንደሆነ ቀድሞ በሚገባ ተጢኖ፥ ከተደመደመ በኋላ ወደውግዘት መሄድ የሚገባ ነገር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ፦
2.1. በንጹህ ህሊና መዳኘት

   የንጹህ ህሊና መገኛ መሠረቱ ዕውቀትና የራስ ጥበብ ሳይሆን ዛሬም ትኩስ ሆኖ በሰማያት ያለው የክርስቶስ ደም ነው፡፡ (ዕብ.9፥10 ፤ 14 ፤ 1ጴጥ.3፥21) በንጹና መልካም ህሊና ለመዳኘት በደሙ ህያውነት ቀድሞ መመላለስ ያሻል፡፡ የክርስቶስ ደሙ ለህይወታችን ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በሚገባ ከተረዳን፤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለተወጋዡም ያስፈልገዋልና በውግዘት ጊዜ ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያንን ብቻ እንድናስብና በእግዚአብሔር ፍርሃት ውስጥ እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ስለዚህ ምስክሮችን በቃሉ መሠረትነትና ሚዛንነት ላይ በማስቀመጥ በንጹህ ህሊና መዳኘት ያስችለናል፡፡
    በክርስቶስ ደም የተወቀረ ንጹህ ህሊና ከእግዚአብሔር ውጪ የሚፈራው ምንም ነገር የለውም፡፡  
v አድሎአዊነት ንጹህ ህሊናን ያሳጣል፡፡
v አድሎአዊነት ፍርድን ያዛባል፡፡
v አድሎአዊነት ደምን በእጅ ያስጨብጣል፡፡
v አድሎአዊነት ፍርድን በራስ ያስመልሳል፡፡
     ስለዚህ በማውገዝ ጊዜ በንጹህ ህሊና መሆን ከክፉ ጥፋት ያድናል፡፡ የጌታን ትምህርትና ቀኖናን እንጂ የሰዎችን ስሜት አለመከተል ከብዙ ነገር ይጠብቀናል፡፡ ይህን በተመለከተ በአንድ ወቅት ፓትርያርክ አቡነ ጳወሎስ በጻፉት ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፦