Tuesday, December 15, 2015

ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ እንደ ገና ሊጤኑ ይገባልRead in PDF
ከዘሩባቤል
በቅድሚያ የጳጳሳት ጉባኤ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በግብረ ሐዋርያት እንደ ተጻፈው ሐዋርያትን አብነት አድርጎ የሚሰበሰብና ለቤተክርስቲያን (ለተቋሙ ወይም ለምድራዊ ድርጅቱ ሳይሆን ለማኅበረ ምእመናኑ) እድገትና መስፋፋት በዓለም ላይ ለሚኖራትም በጎ ተጽዕኖ የሚበጁ ውሳኔዎችን በመወሰን እንደ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ቢሠራ “እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናል” እስከማለት የደረሰ ሥልጣን እንዳለው መረዳቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህን ሥልጣኑን ከዚህ ውጪ የሚጠቀምበት ከሆነና ለእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ክብር፣ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ለራስ ወይም ለአንድ ማኅበር ጥቅም የሚበጁ ውሳኔዎችን የሚወስን ከሆነ ግን በውሳኔዎቹ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተባባሪ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ውሳኔዎቹ የሰዎቹ ብቻ ይሆናል፡፡ ውሳኔዎቹም የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን አያልፉም፣ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ክብደታቸው ይቀንሳል፣ ተቀባይነትም ያጣሉ፡፡ ባለፈው ጊዜ እንኳን ዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ስማችሁ የለም” በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እኛ ተነክተናልና መጽሐፉ በሊቃውንት ጉባኤ ይታይና ውሳኔ ያግኝ ተብሎ ከተወሰነ በኋላ ውሳኔው በገዛ እጁ ቀሊል ሆኖ ስለተገኘ  የትም እንዳልደረሰ ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ውሳኔው አጀንዳውን ያነሱት ጳጳሳት ለራሳቸው ክብር ከመጨነቅና ጉልበታቸውን ለማሳየት ከመፈለግ የወሰኑት እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ከማሰብ የቀረበና በሲኖዶስ መታየት የነበረበት ጉዳይ ባለመሆኑ ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስለኢየሱስ “አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ ምስክርነትን በሰጠ ጊዜ ኢየሱስ ይህን ሰማያዊ አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አልገለጠልህም ብሎ ብፁዕ መሆኑንና በእርሱ ምስክርነት ላይ ቤተክርስቲያን እንደምትመሠረት ተናገረለት (ማቴዎስ 16፡16-19)፡፡ እዚያው ምዕራፍ ላይ ዝቅ ብሎ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠላቸው ጊዜ ከሰማያዊው አባት የሰማውና ብፁዕ ነህ የተባለው ጴጥሮስ፣  እዚህ ላይ ከሰይጣን ሰምቶ ጌታን ወደ እርሱ ወስዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም” ብሎ ሊገሥጸው ሲጀምር ኢየሱስ ዘወር አለና ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” (ማቴዎስ 16፡21-23)፡፡ 

ከሰማያዊው አባት የሰማ ሰው፣ በራሱ መንገድ ከተጓዘ ከሰይጣን የመስማት ዕድል ይኖረዋል ማለት ነው፡፡  ሲኖዶስም እንደ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ሲሠራ ትክክል ከዚያ ውጪ ሲሠራ ደግሞ የተሳሳተ እንደሚሆን ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ “ብፁዕ” የተባለው ጴጥሮስ “አንተ ሰይጣን” ተብሏልና፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ ቢወስኑ ከውሳኔያቸው ጋር መንፈስ ቅዱስ እንደሚስማማ፣ ከዚህ ውጪ በተቃራኒው ቢሄዱ ግን ውሳኔው የራሳቸው ወይም የሰይጣን ሊሆን እንደሚችል ማወቁ አስፈላጊ ነው፡፡
በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ መጨረሻ ላይ የሲኖዶሱ አባላት ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ በተለይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 ላይ የሰፈሩት ነጥቦች በጣም አነጋጋሪና ቤተ ክርስቲያን በጥንቃቄ ካልያዘቻቸው ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሏት ናቸው፡፡ ለዛሬው የመጀመሪያውን እንመልከት፡፡ በተራ ቁጥር 7 የሰፈረው የመግለጫው ነጥብ እንዲህ የሚል ነው ቤተ ክርስቲያኒቱ በማታውቀው ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈቃድ ሳያገኙ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ትምህርታዊ ስብከት የሚያስተላልፉ ዝማሬ የሚያሰሙ መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች ልዩ ልዩ በራሪ ወረቀቶችን የሚያሳትሙ ሁሉ በአገሪቱ ሕግ መሠረት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ለሚመለከታቸውም የሚዲያ አካላት ማሳሰቢያ እንዲደርስ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡” ይህ የአቋም መግለጫ ነጥብ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ ነው፡፡
1.     በቅድሚያ ይህ አጀንዳ የማነው? ለቤተክርስቲያኒቱ ታስቦ ወይስ ቤተ ክርስቲያኒቱን መጥቀም ሳይሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ መጠቀም ያለብኝ እኔ ብቻ ነኝ በሚል ራስ ወዳድነት የቀረበ አጀንዳ ይሆን?   
2.    በሕግ እንዲጠየቁ አቋም የተወሰደባቸውና በቤተክርስቲያኒቱ ስም ትምህርታዊ ስብከት የሚያስተላልፉ ዝማሬ የሚያሰሙ መጻሕፍት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች ልዩ ልዩ በራሪ ወረቀቶችን የሚያሳትሙ የተባሉት እነማናቸው? እነማን መሆናቸው ታውቋል ወይ?
3.    ይህን ጉዳይ እንደ ስጋት ይዞ ሲከታተል የቆየው ማነው?
4.    ለክስ የሚያበቃቸው ወንጀልስ ምንድነው?
5.    በስሟ መጠቀማቸው ብቻ ነው? ወይስ ሌላ ለክስ የሚያበቃ ጥፋት ፈጽመዋል?
6.    መቼም በስሟ ለመጠቀም ድፍረት ያገኙት ኦርቶዶክሳውያን በመሆናቸው ነውና ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮች በኦርቶዶክስ ስም እንዳይጠቀሙ የሚከለክላቸው ምን አለ?
7.    በስሟ ለመጠቀም የሚያስችል ሕጋዊ አሠራርና መዋቅር በተገቢው ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርግታለች ወይ?
8.    ይህ አቋም የሚመለከተው ከዚህ ቀደም በስሟ የተባሉትን ነገሮች ያዘጋጁና ያሳተሙ ናቸው ወይስ ለወደፊቱ የሚያዘጋጁትንና የሚያሳትሙትን ነው የሚመለከተው?
9.    በሕግ እንዲጠየቁ አቋም ከመያዙ በፊት እነዚህን ሰዎች ጠርታ ለማነጋገርና በስሟ ለመጠቀም የሚያስችለውን መስፈርት እንዲያሟሉ ዕድሉን ሰጥታቸዋለች?
10.  ይህ አቋም ከዚህ ቀደም ያሳተሙትንና ያዘጋጁትን ከሆነ የሚመለከተው፣ ጉዳዩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዕውቅና በተገቢው መንገድ ሳያገኙና ባለቤታቸው ሳይታወቅ የታተሙትን ገድላትና ድርሳናት ጭምር ይመለከታል?
11.    ይህን ክስ ያቀረበውና በአቋም መግለጫው ውስጥ እንዲካተት ያስደረገው እጀ ረጅሙ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለምና መግለጫው ማኅበሩ በቤተክርስቲያኗ ስም ያወጣቸውን መጽሐፎች፣ ጋዜጣና መጽሔት መዝሙሮች ስብከቶችና የመሳሰሉትንም ያጠቃልላል ወይስ ማኅበረ ቅዱሳንን አይመለከትም?
12.   ከዚህ ቀደም የሚያሳትማቸውን ጋዜጣና መጽሔት በሊቃውንት ጉባኤ እያስመረመረ እንዲያሳትም የተሰጠውን መመሪያ አላከበረምና በዚህ ላይስ የሚባል ነገር አለ ወይስ አሁንም ማኅበረ ቅዱሳንን አይመለከትም?
13.  ከዚህ ቀደም በስሟ የተሳሳተ ነገር ጽፎ ማለትም “ጽጌ ጾም” የተባለውን ጨምሮ 8 አጽዋማት እንዳሉ አስመስሎ በመጻፍ ላሰራጨው ጽሑፍ ማስተካከያ እንዲሰጥ በጠቅላይ ቤተክህነት ቢታዘዝም ያን እስካሁን አላስተካከለምና እነዚህን ሁኔታዎች ባለማስተካከሉ፣ ቤተ ክህነቱ እንዲስተካከል ያስተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ አልሆነምና አሁንስ ሲኖዶሱ የሚያወጣው ውሳኔ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ነው?    
እነዚህና ሌሎችም ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስም ከሲኖዶሱ የሚጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህን በጥሞና ማየትና ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን መወሰን ጥሩ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም እንደተላለፈው ውግዘት ዓይነት በስሜት በመገፋት የሚተላለፍ ውሳኔ መልሶ ቤተክርስቲያኒቱን ብዙ ዋጋ ሊያስከፍላት ይችላል፡፡ በእርግጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሁለት ቡድኖች መኖራቸው ሊካድ አይችልም፡፡ በአንድ ወገን ማኅበረ ቅዱሳንና ተከታዮቹ ሲገኙ በሌላው ወገን ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ስርዓት በተቃራኒ የቆሙ ውሉደ ወንጌል አሉ፡፡ ሲኖዶሱ ከራሱ አጀንዳ በተጨማሪ በእነዚህ ቡድኖች መካከል ካለው ትግል የሚመነጩ ጉዳዮችን አጀንዳው አድርጎ እንደሚነጋገር ግልጽ ነው፡፡ ይህ ሰባተኛው ነጥብም በዚህ መንገድ የተወሰደ አቋም ነው፡፡
ሲኖዶሱ ይህን ውሳኔ ሲወስን ጳጳሳቱ ወይም ቤተ ክርስቲያኗ እንደ ተቋም በውሳኔያቸው አቅጣጫ የሰሩት ሥራ አለ ወይ? ማለት የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም የሚፈለገውን ያህል ሕዝቡን አስተምረዋል ወይ? የሕዝቡን የአምልኮ ጥማት የሚያረኩ ዝማሬዎች እንዲዘጋጁ አድርገዋል ወይ? የተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶችን በሚፈለገው ዓይነት ጥራትና ይዘት አዘጋጅተው በማሳተም አሰራጭተዋል ወይ? ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ እነርሱ ይህን ቢሰሩ ኖሮ ክፍተቱ ተፈጥሮ እነዚህ አሁን እየተወነጀሉ ያሉ ወጣቶች ክፍተቱን ለመሙላት የራሳቸውን ጥረት ባላደረጉም ነበር፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱ ወይ ሥራ አልሠራ ወይ የሚሠሩትን አላሠራ ብሏል ማለት ነው፡፡ “ልርዳሽ ቢሏት መጇን ደበቀች” እንደ ተባለችው መሆኑ ነው፡፡
በተለያዩ ኦርቶዶክሳውያን በታተሙና በተሠራጩ ስብከቶችና ዝማሬዎች ላይ ሊነሣ የሚችለው ጥያቄ ምን ይሆን? ከሰበቡና ከምክንያቱ በስተጀርባ ያለው ትልቁ ጥያቄ ክርስቶስ ብቻ ለምን ይሰበካል? ለክርስቶስ ብቻ ለምን ይዘመራል? ነው፡፡ መሰበክ ያለበት ማነው? አዳኙ ኢየሱስና የእርሱ የማዳን ሥራ ብቻ አይደለምን? ሊዘመርለት የሚገባውስ ብቻውን አምላክ ጌታ እና አዳኝ የሆነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ብቻ አይደለምን? ስለመላእክትና ስለቅዱሳን ማንነት ስለሌላውም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን በትምህርት መልክ ማስተማር ይቻላል፡፡ በዐውደ ምሕረት ላይ ሊሰበክ የሚገባው ግን አዳኙ ኢየሱስና ተሰብኮ የማያልቀው ተነግሮ የማይዘለቀው ሁሌ አዲስ የሆነው የእርሱ ድንቅ ሥራ ብቻ ነው፡፡ ሐዋርያስ በዕብራውያን መልእክቱ የብሉይ ኪዳን የእምነት አርበኞችን ስም ዘርዝሮ ሲያበቃ “ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል” ያለው ለዚህ አይደለምን? (ዕብ. 11፡32)፡፡ በዚህ ውስጥ መላእክት ቅዱሳን ሊወሱ ይችላሉ፡፡ ቢወሱም በእነርሱ የሠራውን የእርሱን ድንቅ ሥራ ለማጉላት እንጂ እነርሱ እንደ አዳኝ እንዲሰበኩ አይደለም፡፡
ይሁን እንጂ ይህን ተከትለው የሚያገለግሉትን ሰባክያን ስለ ክርስቶስ ብቻ ነው የሚሰብኩት ስለማርያም አይሰብኩም ስቅዱሳን አይሰብኩም በሚል ዘወትር ይከሰሳሉ፡፡ ቤተክህነቱም ታዲያ ምን አጠፉ? በማለት ፈንታ ክሱን ተቀብሎ እንደተሳሳቱ በመቁጠር ከሥራ ያግዳል፤ ከቤተክርስቲያን ያባርራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከተለካ መናፍቅነት ክርስቶስን አለመስበክ ነው፡፡ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን እንዳለ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስቶስ ምትክ ሌላውን መስበክ አስቀድሞ ሐዋርያዊ ውግዘት የተላለፈበት መናፍቅነት ነውና በመናፍቅነት ሊያስከስስ፣ እንዲያውም ሊያስወግዝ ይገባል፡፡ “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” (ገላ. 1፡8-9) ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ ስለዚህ ሰው መናፍቅ መባል ያለበት ክርስቶስን ስለ ሰበከ ሳይሆን ክርስቶስን ወይም ወንጌልን ስላልሰበከ ወይም በእርሱ ምትክ ሌላውን አዳኝ አድርጎ ከሰበከ ነው፡፡
ከመዝሙር ጋር በተገናኘም እየቀረቡ ያሉት ክሶች በጥቅሉ የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1ኛ. መዝሙራቸው ስለክርስቶስ ብቻ ነው፤ ስለማርያም አይዘምሩም፡፡ 2ኛ. ዜማቸው ያሬዳዊ ዜማ ሳይሆን ወደ ዘፈን የቀረበ ነው፡፡ 3ኛ. ግጥሙም ኑፋቄ አለበት የሚሉና የመሳሰሉ ናቸው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉ ያሉ መዘምራንና መዘምራት እየተከሰሱ ያሉት ለምን ስለ ክርስቶስ ብቻ ይዘምራሉ? ስለማርያምም መዘመር አለባቸው በሚል ነው፡፡ ይህም ክስ መሰረተ ቢስ ነው፡፡ ምክንያቱም መዝሙር መቅረብ ያለበት ለፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ ለፍጡራን መዘመር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አይደለም፡፡ ልማዳዊና ሰው የሠራው ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ በልማድ ተመርቶና መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ጥሎ ለማርያም ካልዘመሩ መናፍቃን ናቸው ማለት ራሱ መናፍቅነት ነው፡፡ ይህን ክስ ለማስቀረት በሚል እነርሱም ዘጠኙን ስለክርስቶስና ሌላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ላይ የተመሰረተ ዝማሬ ካቀረቡ አንዱን ለማርያም መስጠታቸው አልቀረም፡፡ የሚያሳዝነው ግን እንዲህም አድርገው የሚያምናቸው አለመኖሩና ከመከሰስ አለመዳናቸው ነው፡፡ ከሁለት ያጣ ሆነዋል፡፡ ምናለበት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ቢያሰኙ!!
ሌላው ክስ ዜማቸው ያሬዳዊ አይደለም የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ ያሬዳዊ ዜማ ምን ዐይነት ነው? ጥንት በነበረበት ሁኔታ ዛሬ አለ ወይ? እየተሻሻለ አይደለምን ከእኛ ዘመን የደረሰው? ደግሞስ ኢትዮጵያዊው ዜማ ከያሬድ የዜማ ቅኝት ውጪ ነው ማለት ይቻላልን? ዛሬ እየተከሰሱ ያሉት ዘማርያንና ዘማርያት ከያሬዳዊ ቅኝት አልወጡም፡፡ ዜማቸው ለምእመናን ጆሮ የሚጥም ለአምልኮ የሚያነሣሣና የብዙ አድማጮችን ጆሮ የያዘ ነው፡፡ ይህን ማበረታታትና ቤተክርስቲያኗን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል፡፡ በዚህ ያልተደሰተውና እኔን ብቻ አድምጡኝ ያሬዳዊ ዜማ ያለው እኔ ዘንድ ብቻ ነው በሚል ትምክህት የተያዘው ማቅ በብዙ እንዲጠሉ ዘመቻ ቢከፍትባቸውም የእርሱ ዝማሬዎች በማኅበሩ አባላት ዘንድ ካልሆነ በቀር ተደማጭ አይደሉም፡፡ በብዙዎች እየተደመጡ ያሉትና ምድሩን የሸፈኑት “መዝሙራቸው ዘፈን ሆነ” እያለ ማቅ ዘወትር የሚከሳቸው፣ ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ ዘመኑን የዋጁት ዘማርያንና ዘማርያት ዝማሬዎች ናቸው፡፡
ማቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ሃይማኖታዊ ህጸጽ የተፈጠረ አስመስሎ ክሱን ቢያቀርበው ከበስተ ጀርባ ያለው ግን የእኔ ብቻ መዝሙር ይደመጥ የሚል የጥቅም ጥያቄ ያዘለ ነው፡፡ በዚህ ላይ የተመሠረተውን ይህን ጥላቻውን በቤተክህነቱም ላይ አጋብቶ ቤተክህነቱ ታሪክን አመሳክሮና ዘመኑንም ዋጅቶ በራሱ መስፈርት ነገሮችን መመዘን ሳይሆን በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ሥር በመውደቁና ማቅ ያቀረበውን ሁሉ ልክ ነው ብሎ መቀበሉ አስተዛዛቢ እየሆነ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህን አስተውሎና አመዛዝኖ በዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን የሚበጀው ምንድነው? የሚለውን ከማቅ ተጽዕኖ ነጻ ሆኖ ማሰብና መወሰን አለበት፡፡ ይህን እውነታ ባለማስተዋልና በማቅ በመመራት የመዘምራኑን የዝማሬ አገልግሎት ለማስቆም መሞከር አሁንም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው፡፡ በቋፍ ያለውን ምእመን ወደሌሎች እንዲፈልስ በር መክፈት ነው የሚሆነው፡፡     
ሦስተኛው ክስ ግጥማቸው ሃይማኖታዊ ሕጸጽ አለበት የሚል ነው፡፡ እነዚህ ዘማርያንና ዘማርያት እየዘመሩ ያለው በአብዛኛው በቅዱስ ቃሉ የተጻፈውን ነው፡፡ በቃሉ የተጻፈው እውነት በዝማሬም እየተገለጠ ስላለ የማቅ ተረት እየፈራረሰ መሄዱ አይቀርም፡፡ ከዚያ በፊት እነርሱን መዋጋት አለበትና ይህን ክስ ለማቅረብ ደፈረ፡፡ ለምሳሌ ሰሞኑን ዝማሬያቸውን ያስመረቁት አሥሩ ዘማርያን በኅብረት ያቀረቡት ዝማሬ ስም “መልእክተ ዮሐንስ” የሚል ነው፡፡ በዮሐንስ መልእክት ላይ የተመሠረቱት ዝማሬዎች ቃል በቃል የተወሰዱት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በቃሉ ላይ የተመሰረቱ ስላሆነ ዝማሬዎቹን ዘመን አይሽሬ ያደርጋቸዋል፡፡ ዝማሬዎቹ ልብን የሚነኩና አጥንትን የሚያለመልሙ ናቸው፡፡ የእነዚህን ዝማሬዎች ግጥሞች መተቸት ከባድ ነው፡፡ እንተችና እንንቀፍ ብንል በቀጥታ የተመሰረቱበት ቃሉ ልክ አይደለም ወደ ማለት ነው የምንገባው፡፡ በኋላ በስሙ የራሳቸውን ድርሰት በስርዋጽ አስገብተው የያሬድ ነው ያሰኙት ካልሆኑ በስተቀር የቅዱስ ያሬድ ዝማሬዎች ዘሩ (ንባቡ) በአብዛኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ቃሉን ከመዘመር የተሻለ ነገር የለም፡፡ ማቅ እያለ ያለው ግን ቃሉ ለምን ይዘመራል? አዋልድ መጻሕፍት ናቸው መዘመር ያለባቸው? ባይ ነው፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ቅኝት ውስጥ የገቡ መዘምራንና መዘምራት ቃሉን በመጠኑ ቢያነሱ ነው እንጂ አዋልድን ነው የሚዘምሩት፡፡
ሲኖዶሱ የወሰናቸውን አንዳንድ ውሳኔዎች ከሦስተኛ አካል ጋር የተያያዘ በመሆኑ ተፈጻሚ እየሆነ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በኢቢኤስ የሚተላለፉት መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እንዲታገዱ ተደርጓል፡፡ እገዳው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጨምር መሆኑ ደግሞ ቤተክህነቱ “ጥርስ አወጣ” አሰኝቷል፡፡ ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ አስቀድሞ ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ኦርቶዶክሳዊ አድርጎ ታኦሎጎስና ቃለ ዐዋዲ የቴሌሺዥን ፕሮግራሞችን ኦርቶዶክሳዊ አይደሉም በሚል ለማዘጋት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ እርሱ ከጀርባ ሆኖ የተለያዩ ለሃይማኖታችን የቀናን ነን የሚሉ ቡድኖችን በማደራጀት ፊርማ ከማሰባሰብ በሲኖዶስ ስብሰባ ዋዜማ አንዳንዶችን አሰልፎ እስከ መጠየቅ ደርሶ ነበር፡፡ እንደ ተመኘውም ይህ የአቋም መግለጫ ነጥብ ወጣ፡፡ ከዚያም ከእርሱ ውጪ ያሉት ሁለቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንደሚዘጉ በሰፊው አስወራ፡፡ እርሱ ግን እንደሚቀጥል ዓይነት ነበር ወሬው፡፡ ነገር ግን እርሱም ቢሆን ፈቃድ የላቸውም ከተባሉት ጋር ተቆጥሮ ታገደ፡፡ ማቅ በቆፈረው ጉድጓድ ለጊዜውም ቢሆን ገብቶበታል፡፡
ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለ ከማኅበረ ቅዱሳን በኩል ታኦሎጎስና ቃለ ዐዋዲ በስም ተለይተው አለመጠቀሳቸው ለኢቢኤስ ውሳኔ እንዳስቸገረና መዘጋት የሌለበት የማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራም አለአግባብ እንደተዘጋ ለመናገር ጥረት አደርጓል፡፡ ኢቢኤስ ፕሮግራሞቹ እንዲታገዱ በመደረጉና የአየር ሰዓቱ ለተወሰነ ጊዜ ክፍት ሆኖ እንደሚጠብቅና ካልሆነ በሌላ ፕሮግራም እንደሚሸፈን በመግለጹ በቢዝነሱ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋልና ቅር መሰኘቱና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ማቅ መሆኑን መቼም ሳያውቅ ይቀራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡
በተወሰደው እርምጃ የማኅበረ ቅዱሳን ወገኖች ታኦሎጎስና ቃለ ዓዋዲ በመታገዳቸው በአንድ ፊት ደስ ሲላቸው በሌላ በኩል ግን ማቅም ከመታደግ ስላልዳነና ከእነርሱ ጋር በመቆጠሩ ተበሳጭተዋል፡፡ የቃለ ዓዋዲና የታኦሎጎስ ወገኖች ደግሞ ፕሮግራሞቹ በመታገዳቸው በአንድ በኩል ሲያዝኑ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲዘጉ ያደረጋቸው ማኅበረ ቅዱሳንም ከመዘጋት ባለመትረፉ አልተጽናኑም ማለት አይቻልም፡፡ እገዳው ከተላለፈ በኋላ ሦስቱም ፈቃድ እንዲሰጣቸው ለጠቅላይ ቤተክህነት ያመለከቱ ሲሆን ከቤተ ክህነት አካባቢ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎች እንደሚያሳዩት እገዳው ላልተወሰነ ጊዜ ጸንቶ ይቆያል እንጂ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው ነው፡፡ ማቅ ይህን ውሳኔ እንዴት ያየው ይሆን? ልጇ ላይ ተኝታ በመግደሏ የሌላዋን ልጅ እንደወሰደችውና በኋላ ላይ ተካሰው ንጉስ ሰሎሞን ዘንድ ከቀረቡ በኋላ በአስደናቂ ፍርዱ ልጁን ከሁለት ቆርጬ ላካፍላችሁ ወይ? ባለ ጊዜ በሐሣቡ እንደተስማማችው ሴት እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ማለት ኢቢኤስ ለእኔም ለእነሱም አይሁን እንደሚል ግልጽ ነው፡፡ የታገለው እነርሱን ከኢቢኤስ ለማስወጣት ነውና ይህን ስላሳካ ደስተኛ ነው፡፡ የእርሱን መታገድ ግን እንደ ሽንፈት የሚወስደው ቢሆንም ከእነርሱ መታገድ ጋር ሲነጻጸር ግን ኢምንት እንደሚሆንበት መገመት ቀላል ነው፡፡
በተደጋጋሚ እንደተባለው ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደ ተቋም በሕግ ፊት ያላትን መብት ተጠቅማ ፕሮግራሞቹን ማገድ ችላለች፡፡ ፕሮግራሞቹም ለጊዜው ከመታገድ ውጪ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ ይህ ግን እስከ መቼ ይቀጥላል? የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ጥንትም ቢሆን ወንጌል ተፈቅዶለት አይደለም እየተሰበከ ከእኛ የደረሰው፡፡ እየታገደና ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበትና ብዙ ክልከላ እየተደረገበት ነው የተስፋፋው፡፡ በመሆኑም የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን እንደ ቢዝነስ የያዘው ክፍል ይህ ቢዝነሱ ሲዘጋበት ቢዝነሱን በሌላ ቢዘነስ ሊተካው ይችላል፡፡ ፕሮግራሙን እንደ አገልግሎት የያዘው ወገን ግን ለጊዜው እንጂ ሌላ አማራጭ መውሰዱ አይቀርም የሚል ግምት ይኖራል፤ የወንጌሉ አገልግሎት እንዳይቆም ሌላ አማራጭ ይፈልጋልና፡፡
ታዲያ ሲኖዶሱ ከወሰደው ከዚህ እርምጃ ተጠቃሚ የሚሆነው ማነው? ቤተ ክርስቲያን? ወይስ ሌሎች? ውሳኔው ወንጌልን ማእከል ያላደረገ ነው፡፡ ወንጌልን ማእከል ያደረገ ቢሆን መርሐ ግብሮቹን ከማገድ ይልቅ ባሉበት ፈቃድ የሚያገኙበትንና በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ሆነው የሚሠሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት የተሻለ አማራጭ ነበር፡፡ አንድ እንኳ የራሷ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሳይኖራት እስካሁን ተኝታ ያለችው ቤተክርስቲያን  እነዚህ ፕሮግራሞች ክፍተቷን እንደሞሉላት በመቁጠር ልታበረታታቸው ይገባ ነበር እንጂ ታግዳችኋል ማለት አይጠበቅባትም ነበር፡፡ ሆኖም ለወንጌል መስፋፋት የሚያስቡ አባቶች ቁጥር እጅግ በመመናመኑ ውሳኔያቸው ግብታዊነት የተሞላና ወደፊት የሚከተለውን አደጋ ከግምት ያላስገባ ነው፡፡ በውሳኔው ቤተ ክርስቲያን ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ አትሆንም፡፡ ምናልባት በዚህ አጋጣሚ ብዙዎች ምእመናን አማራጭ ስለሌላቸው የፕሮቴስታንቶቹን ፐሮግራሞች ወደመመልከት መዞራቸው አይቀርም፡፡ ኣማራጭ ከሌለ ሊሆን የሚችለው ይህ ነው፡፡ አማራጭ ሳያስቀምጡ እንዲህ ዓይነት እርምጃ መውሰዱ አደገኛነት አለው፡፡ ይኸውም የኦርቶዶክስ ምእመናን ቁጥር እንዲቀንስ ሌላ በር ይከፍታልና፡፡
እንደ ተባለው ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷን የቴሌቪዥን ጣቢያ ልትከፍት ነው፡፡ ይህ እውን እስኪሆን ጊዜ መውሰዱና በመካከልም ብዙ ክፍተት መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ደግሞም ጣቢያውን መክፈት ብቻ ሳይሆን በሚከፈተው ጣቢያ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት መስጠት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቀላል ሥራ እንደማይሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል፡፡ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ሳይዙ ወደሜዳው መግባት ከጨዋታ ውጪ ወይም ተሸናፊ ማድረጉ ግን አይቀርም፡፡ ስለዚህ ሲኖዶሱ በጀት ከማጽደቅ በላይ ከዚህ ቀደም የነበሩትን ተሞክሮዎች በተለይም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥር የነበረው ሐዋርያዊ ድርጅት ይሠራው የነበረውን ውጤታማ ሥራ ዓይነትና ከዚያ የተሻለና ለዘመኑ የሚመጥን አሠራር መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ ካልሆነ ግን ተወዳዳሪ ሆኖ ጥሶ መውጣት አይቻልም፡፡ ይልቁንም በማኅበረ ቅዱሳን ቅኝት አሁን በተያዘው ከወንጌል ወደ ተረት ፈቀቅ የማለት አካሄድ ተባብሶ የሚቀጥል ከሆነ የትም አይደረስም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች መታሰብ አለባቸውና ሲኖዶሱ ውሳኔውን እንደ ገና ቢያጤነው ለወደፊቱም በሚወስናቸው ውሳኔዎች ላይ ብርቱ ጥንቃቄ ቢያደርግ መልካም ነው፡፡ የዛሬውን ጽሑፌን በሚከተለው “ሚ በዝኁ” ቅኔ ልደምድም

ኦርቶዶክሳዊት (ቤተክርስቲያን) ጽዮን አብርሂ እንከ በትፍሥሕት ወተዐግሦ
አምጣነ አልጸቀ ለኪ ንጉሠ ነገሥት (ንጉሥኪ) ተሐድሶ
በተጽዕኖ ዕዋል መጽሐፍ ለአማስኖ ገድላተ ጣኦታተ ግብጽ ሐንክሶ

ትርጉም
ጽዮን የተባልሽ ኦርቶዶክሳዊት (ቤተክርስቲያን) እንግዲህ በመታገስና በደስታ አብሪ
በውርንጭላ መጽሐፍ (ቅዱስ) ላይ ሆኖ የማንከስ የግብጽ ጣኦታት ገድላትን (አዋልድን) ለማስወገድ
ንጉሠ ነገሥት (ንጉስሽ) ተሐድሶ ደርሶልሻልና


ይቀጥላል፡፡

17 comments:

 1. menafkan nachu adel?????????????????/

  ReplyDelete
 2. "ሰው መናፍቅ መባል ያለበት ክርስቶስን ስለ ሰበከ ሳይሆን ክርስቶስን ወይም ወንጌልን ስላልሰበከ ወይም በእርሱ ምትክ ሌላውን አዳኝ አድርጎ ከሰበከ ነው፡፡"

  ReplyDelete
 3. "ይህን ክስ ለማስቀረት በሚል እነርሱም ዘጠኙን ስለክርስቶስና ሌላ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ላይ የተመሰረተ ዝማሬ ካቀረቡ አንዱን ለማርያም መስጠታቸው አልቀረም፡፡ የሚያሳዝነው ግን እንዲህም አድርገው የሚያምናቸው አለመኖሩና ከመከሰስ አለመዳናቸው ነው፡፡ ከሁለት ያጣ ሆነዋል፡፡ ምናለበት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ቢያሰኙ!!"

  ReplyDelete
 4. For your information there is an organization called Protestant who has the same way of belief, religion as you mention above only Jesus no Virgin Mary,no angels,no saints,no good doings only faith no Yaredawi zema etc etc etc .please go and join them in their ADARASh dance like rock and role and enjoy yourself and please please please live our Orthodox Tewahdo religion for US.Thank you

  ReplyDelete
 5. አትንጨርጨሩ

  ReplyDelete
 6. Yetabah ante menafrk!

  ReplyDelete
 7. አትጠራጠሩ
  በመስኮት የገቡ የኑፋቄ ትምህርቶችና የባልቴቶች ተረቶች ተወግደዉ የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. geta yekefetew yewengel ber besewoch midrawi hasab ayizegam. gena enibezalen

   Delete
 8. ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም.
  የቀናች የተረዳች የቅዱሳን አባቶቻችን ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት፡፡ አንድ ሃይማኖት አንድ ጌታ፣ አንዲት ጥምቀት ነውና ያለን፡፡ የናንተን ሰው ሰራሽ ዘባተሎ ፕሮቴስታንታዊ ተሐዲሶን ጨምሮ ብዙ ሰው ሰራሽ “ሃይማኖቶች” አሉ፡፡ ስለሆነም ምርጫችሁ በሰፊው እና በጥፋት መንገድ መጓዝ ከሆነ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ጋር ምን ግኑኝነት አላችሁ? መጽሐፉስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን መጋጠም አለው ብሎ የለም? በመጨረሻው ዘመን ሐሰተኞች መምህራን ይመጣሉ ተብሎ በወንጌል የተነገረው ለናንተ ዓይነቶቹ ነው፡፡ የመናፍቃንን እና የከሃዲያንን የሞት ትምህርት ቀምራችሁ እንደ አዲስ ግኝት ስትቀርቡ አለማፈራችሁ ይገርመኛል፡፡

  ReplyDelete
 9. minew ye Luther yediyabilos lijoch tenichachachihu sera fetoch min taderigu tifatu yenanite adelem minimsataku bebetekiristiyan yenayigebachihu kibir tesetachihu behulam kihedet jemerachihu enaniten menafikan minale bebetkiristyan atinegidu wutu egizr yatifachihu yediyabilos lijoch mechereshachihu tifat new
  yediyabilos lijoch

  wuhibe D.

  ReplyDelete
 10. Gambela and talak dildey ale bemengistu H/mariam gize yetesera tadya anatulay yemengisu foto nebere mengist sekeyer yesireatu aramajoch fotowin lemawred simokiru tewlaju ayhonem alachew lemin seluachew enantem siruna fotoachihun sikelu aluwachew zim bilachihu mak mak kemitilu enantem endenersu siruna simachihun besewu libona tsafu wey sira wey haimanot yelachihu zimbilo chuhet sewu silawekachihu gidyelem. ezaw zanigabachihu hiduna alazinu bet yetselot bet nat bilo yewnbwde washa endematihon negironal washachihun feligu wey atamiru wey atafiru ale yaegresew.

  ReplyDelete
 11. lemin yenen gambela bilo yemijemirewin alawetachihutim?altwatelachihum aydel ewnet lalamenebat timeralech

  ReplyDelete
 12. የምን ጣረሞት ማብዛት ነው ? እስኪ ዝም ብላችሁ ሙቱ !

  ReplyDelete
 13. ነፍሰ ገዳይ ተሐድሶ ፕሮቴስታንት መቀበሪያህ እየደረሰ ነው፣ እስከዚያው ፈንዳ።

  ReplyDelete