Saturday, December 19, 2015

ግጭትና ጦርነት የማያስተምራት አገር

ስለራሳችን እንዲህ እንናገራለን ፦
-      እንግዳ ተቀባይ ሕዝቦች ነን ፤
-      ብዙ ብሔር ብሔረሶችና ሕዝቦች ተዋደው የሚኖሩባት አገር አለን ፤
-      ለቁጥር የሚታክት “ክርስቲያን” ፣ እልፍ አዕላፍ ገዳም ፣ መድረክ የሚያጨናንቁ አገልጋይ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናትና ዘማርያን አሉን ፤
-      ከእኛ ወዲህ ማን አለ አማኝ? ከእኛ በላይ ጸዳቂ ፤ ታማኝ አገር ወዳድ ወዴት አለ?! …
ስንታይ ግን፦
-      “ባዕድ እንግዳ” ለመቀበል ሆዳችንን እንደአገር ስናሰፋ ፥ ከጎረቤትና ከወገናችን ጋር ግን “ጠብ ያለሽ በዳቦ” በሚል መንፈስ የተያዝን ፤
-      አገልጋዮቻችን ጸንሰው ወልደው ፣ አሳድገው የሰጡን አንዱ መልክ ዘረኝነትና ልዩነት ነው ፤
-      ከእኛ በላይ ሁሌም ሰው የለም ብንልም ዘወትር ግን እየኖርን ያለነው ከሰው በታች ጅራት ሆነን ነው …
     ሰሞኑን በከፊል የአገራችን ክፍል ብጥብጥና ሁከት ፤ ደም ማፍሰስና ግድያ ነግሶ ነበር፡፡ ይህን ሁሉ አድራጊው ሌላ ወራሪ ወይም እንግዳ አሸባሪ መጥቶብን አይደለም ፤ ሟችም እኛው፥ ገዳይም ያው እኛው ኢትዮጲያውያን ፤ ንብረት አውዳሚም፥ ንብረት የሚወድምበትም ያው የአንድ አገር ዜጎች ፤ የአንድ ርስት ወሰንተኞች ፤ የአንድ ወንዝ ጠጪዎች እኛው ነን፡፡
 
      እስኪ አስተውሉ፥ አንድ መቶ ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በእኛና እኛ መካከል የተደረጉ ጦርነቶችን ብናነሳ፦ በ1909 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በንጉሥ ሚካኤል መካከል በሰገሌ ፣ በ1922 ዓ.ም በራስ ተፈሪና በራስ ጕግሳ በአንቺም ወይም በበጌምድር ፣ ከ1966-1983 ዓ.ም ወታደራዊው መንግሥት ደርግና ኢሕአዴግ በተለያየ ቦታ ያደረጉት አስቀያሚ ጦርነት ፣ በ1994 ዓ.ም ሁለቱ “ወንድማማች” ኢትዮጲያና ኤርትራ ያደረጉትን ጦርነት (ወታደራዊው መንግሥት በአንድ ጉድጓድ የፈጃቸው የንጉሡ ዘመን መሪዎችና ሌሎችም ሳይካተቱ) ይህን ሁሉ ስናነሳ ምን ይታወሰናል?!

     በእውኑ እኛ ነን ተቻችሎ አዳሪ? እኛ ነን ለእግዚአብሔር ቀናተኞች? ከእኛ በላይ አማኝ ፤ ከእኛም ወዲያ ክርስቲያን የሚባልልን በእውነት እኛ ነን?! እኔ የፖለቲካ ተንታኝ አይደለሁም፥ ዳሩ ይህን አምናለሁ ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግ ፣ ማኅተመ ጋንዲ ፣ ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ጦር ሳይመዙ ፣ የጥይት ባሩድ ሳያጤሱ ለሕዝቦቻቸው ነጻነትን ያጎናጸፉ ምርጥ የነጻነት ታጋይ ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ እኒህ መሪዎች ከሕዝባቸው እኩል መከራ ተቀብለዋል ፣ ተርበዋል ተጠምተዋል ፣ በእስር በግርፋት ተሰቃይተዋል ፤ በፍጻሜው ግን ዘረኞችን ድል አድርገዋል፡፡
      እኒህ የነጻነት ሰዎች ከንግግራቸው ይልቅ ከሕዝባቸው ጋር ያሳለፉት መከራና ሰቆቃ ረጅም ነው፡፡ ለወሬ የግል ተከታይና ደጋፊ የግል ቻናል አልከፈቱም ፤ ሕዝብ በአመጽ ለመቀስቀስ በስውር አልተመሳጠሩም ፣ ከሕዝቦቻቸው ርቀው በዲያስፖራነት እየተቀማጠሉ ኖረው፥ በየሚዲያው ተውበው አልቀረቡም ፣ እኩል የሕዝባቸውን መከራ በመቀበል ኖሩ እንጂ፡፡
     ወደአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ በአንድ መቶ ያሳለፍነው ጦርነት ምን አስተምሮናል? እርስ በእርስ ያን ያህል ተጋጭተን የት ደረስን? የገዛ ወንድማችንን ገድለን እርካታችን ምንድር ነው? … ገድለን ካልተማርንበት አሁንስ ለመግደል መነሳሳት ምን የሚሉት ድንዛዜ ነው? ነጻነት እፈልጋለሁ የሚል አካል ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ምን ያጣባዋል? አንድ ብሔር ወይም የተወሰኑ ብሔሮች ላች ላይ ችክ ማለትስ? የነጻነት ታጋይ ነን ካሉ ብዙ ሃይማኖትና ብዙ ብሔር ባለበት አገር ላይ ታች አንሶ አንድ ሃይማኖትና አንድ ብሔር ላይ ማቀንቀን በእውኑ የማስተዋል ውጤት ነውን?
      መጯጯህ ፣ አለመደማመጥ ፣ አለመከባበር ፣ ተቀራርቦ ከመወያየት ይልቅ መናናቅና መገፋፋት ፣ የትላንት ትውልድ የሠራውን ነውርና ዘረኛነት በግድና በብልሃት የዛሬው ትውልድ ላይ ቆልሎ በቂምና በበቀል ስሜት መነሳት ፣ ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን በብሔርና በሃይማኖት ከፍሎ ማየትና ማቅረብ ከትላንቱ ያልተማርንበት ከባዱ ስህተታችን ነው፡፡ ይህን የምለው መንግሥት ጉያ ውስጥ ሆነው ጠብ የሚጭሩና በሕዝብ መታመስ የሚረኩ ባለሥልጣናት ያሉትን ያህል፥ አንዲት የደም ጠብታ ምድርን እንዳይነካ የሚተጉ አገር ወዳድ ባለሥልጣናት መኖራቸውን ባለመዘንጋት ነው፡፡ ከዚህ እጅግ በሚልቅ ቁጥር ደግሞ “አገራችን ተበድላለች ፤ ብሔራችን ተጨቁኗል” በሚል ሽፋን የአንድን ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና በትውልድ ላይ ለመጫንና ዘረኝነት ፣ ግብረ ሰዶማዊነትንና ስድነትን በምድሪቱ ሊያመጡ የሚሠሩትን እጅግ እንቃወማለን፡፡
    በእርግጥ ከገበሬው አንስቶ ተምሬያለሁ እስከሚለው ተማሪና አስተማሪ ይህን እውነት ምን ያህል እንዳስተዋለው አላውቅም፡፡ ልብንና ኩላሊትን ፤ ሃሳብንና የውስጥ ስውር ዕውቀትን የሚፈትነው አምላክና እውነተኛ ልጆቹ ይህ እውነት ግን አይጠፋቸውም፡፡ እግዚአብሔር ደም የሚያፈሱትን የእነርሱን ደማቸውን ያፈሳል፡፡ ኢትዮጲያ ትላንት ደም ላፈሰሰችበት ፤ በገዛ ልጆቿ ላይ ለፈጸመችው ግፍና እልቂት ፤ ምድሪቱን ላረከሰችበት የደም እንባና ጎርፍ ከልብ በሆነ እውነተኛ ንስሐ አላጸዳችውም፡፡ ከዚያ አንዳች ነገር ሳንማር ዛሬም የአገርን ልጅ ደም ለማፍሰስ ካራ ስለን ተነስተናል፡፡ እንኳን ከእግዚአብሔር፥ ከህሊና በታች ስለወረድን ፤ ስለተሸነፍንም ስለት አንስተን የሰው ደም እናፈሳለን ፤ ንብረት እናወድማለን እንጂ ሰብዐውያን ብንሆን ተወያይተን ፣ ተወቃቅሰን ፣ ተገሳስጸን ፣ አንዳችን ሌላችንን (ሌላውን) ተቆጥተን ወደመንገዳችን በተመለስን ፤ በመለስንም ነበር፡፡
     ቃየን ደም በማፍሰሱ ምክንያት ምድር ለእርሱ ትሰጥ የነበረ ኃይሏን ነፍጋዋለች ፤ እርሱ ደም በማፍሰሱም የእርሱን ደም ሌሎች አፍስሰውታል (ዘፍጥ.4፥23-24) ምድር የሰማይ ዝናም እንጂ የሰው ደም የተገባት አይደለም ፤ ቃየን የወንድሙን ደም በማፍሰሱ በምድር ሁሉ ፊት ኮብላይና ተቅበዝባዥ ሆነ፡፡ ወንድሙ አምላክን በፍቅርና በመታዘዝ ደስ እናዳሰኘ ቃየን ግን ስለተሳነው በጥላቻ ወንድሙን በድንጋይ መትቶ ገደለው፡፡
     ሰውን መሳደብ ፣ በጥላቻ መጥላት ፣ ደሙን ለማፍሰስ መቸኮልና ለመግደል መጣደፍ የመሸነፍና ከማስተዋል የመጉደል ትልቅ ምልክት ነው፡፡ አዎን! በሕይወት መስበክ ስላልቻልን በኃይልና በጥላቻ እንነሳሳለን፡፡  የመንግሥት ባለሥልጣናትም ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ፣ የመሃል ቤት ሰፋሪዎችም ትልቁ ችግራችን፦
1.     ከትላንቱ ታሪክ የተማርን አልመሰለኝም፡፡ የትላንቱን ነፍሰ ገዳነትና ዘረንነት በአፋችን ረገምነው እንጂ ከሃሳባችንና ከልባችን አልወጣም፡፡ ቀን ቢቀናልን ጎረቤታችንን ፣ ወዳጃችንን ለሞት የማንሰጥ እንኖር ይሆንን?
2.    ዛሬም የይቅርታ ጉልበት አልበዛልንም፡፡ አንዱ ብሔር ሌላውን ሊያፈቅር ፣ ሊቀበል ፣ በጋብቻ ሊዛመድ ፣ አቅርቦ ሊጎራበተው ... አቅም አጥቶ የትላንቱን ቂም በማሰብ የይቅርታ ጉልበታችንን አመናምነነዋል፡፡
3.    ልበ ሰፊዎች አይደለንም፡፡ ልበ ሰፊነት ሁሉን የመቀበል ደግሞም ሁሉን እንደቅዱስ ቃሉ የመመርመር ሃብት ነው፡፡ ጽንፈኝነትና ግትርነት ይህን ሃብት አስጥሎናል፡፡
     ኢትዮጲያ ዛሬም ከትላንቱ አልተማረችምና የልጆቿን ደም በማፍሰስ ተጠምዳለች ፤ የፍጡር ደም ደግሞ ጯኺና ከሳሽ ነው፡፡ (ዘፍጥ.4፥10 ፤ ዕብ.12፥24) ደም ደግሞ በደም እንዲጠራ እግዚአብሔር በልጁ ሞት ፤ በደሙ ሥርየትን ሰጥቶናል፡፡ (ዕብ.9፥22) የፈሰሰውን ደም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ማጥራት ((ዕብ.9፥14) ፤ በንስሐ መቋጨት የዛሬውን ቀን ሰላማዊ፥ የነገውን ደግሞ ብሩህ ፤ በተስፋ የተሞላም ያደርገዋል፡፡
      እንኪያስ “የሃይማኖት መሪዎች ወዴት ናችሁ? ፣ ቲዎሎጂያንስ ምነው ድምጻችሁ አይሰማም? የአገር ሽማግሌዎችስ የሰው መርገፍ አያሳስባችሁምን? በእውኑ አንድ ሰው ሲሞት አይገዳችሁምን? ስንት ሰው ሲሞት  ፤ አካሉ ሲጎድል ትነሱ ይሆን? … “የባሰ አታምጣ” ብለን የምናልፈው ነገር አይደለም ፤ ከዚህ የባሰ የለምና፡፡ በረሃብ የሚቆላውና አንጀቱ የተጣበቀው ወገን አሮ ፣ ከስሎ ፣ ደብኖ ፣ አንጀቱ ታጥፎ መሞቱ ሳያንስ የሌላውስ መጨመር በእውኑ ለምን አልገድ አለን?!  የምትጸልዩ ትጉ ፤ መፍትሔ ከፍጡር የምትፈልጉ ደግሞ ፍጹም የሆነ መፍትሔ ከአምላክ እንጂ ከፍጡር የለምና ንስሐ በመግባት  እጆቻችሁን ወደአዳኙና ታዳጊው ጌታ ዘርጉ፡፡

     አቤቱ ሕዝብህን አድን ፤ ርስትህንም ባርክ፡፡ ጌታ ሆይ! ሕዝባችንንና ምድራችንን ፈውስልን፡፡ አሜን፡፡

23 comments:

 1. ይህ ሰው በጣም አስተዋይ ጸሀፊ ነው። ጌታ ይባርክህ አቦ

  ReplyDelete
 2. This is a good message to Ethiopian government and any other people or groups,God Bless you so much my friend;

  ReplyDelete
 3. This is a good message to Ethiopian government and any other people or groups,God Bless you so much my friend;

  ReplyDelete
 4. ይህ መልዕክት ወቅቱን የጠበቀ መንግስትም እነ ጁሀር መሀመድንም የሚገስጽ ጽሁፍ ነው። መልእክቱን ገብቶን ለመፍትሔው እንንቀሳቀስ። ጸሀፊው የጌታ በረከት ይደርብህ

  ReplyDelete
 5. ABA SELAMA SIMACHIHUNA MIGBARACHIHU KETSIHUFACHIHU TEREDCHALEHU ENDIH YALEWIN HULUNIM YESWE LIJ YEMIYANITS LETEGTSTSIM LEMIKRM YEMIHON MELEKIKT METSAFACHIHU YEBELETE WEDEDKUACHIHU EGZIABHERN YIBARKACHIHU KALACHIHU BEFETARI FIT YISEMA MIHRET LEHEGERACHIN YIST LESELAM LEDGET LEKULNET EYETEGU LALALU MERIW OCH ACHING DIKAMACHEW KEAHUNU YEBELETE FRE AFRTO HIZBU SITE KEMETEW LEMAYET YABKAKACHEW NEGER SERIWOCH HIZBIN LEMAGELGEL SAYHON LEMEGELGEL SILTAN YEMIKAMTUTIN LIB YISATACHEW ENDE MAHBERE KIDUSAN YEMESASELU BEMENFSAWI SIM TETELILEW KIFU YEHONEW YEPOLETICA MENGE2 YEMIRAMEDUTIN POLETIKEVNOCH NEGER KEMIYABABS MILASACHEW INDIMELESU YADRGACHEW SELAMACHININA EDGETACHIN EGZIABHERN YASKETLILN

  ReplyDelete
 6. menafikan wushetam neh mejemeriya eminet yinurih yediyabilos lij man yisemahal? yaw yanite manfikan yisemuh
  Wuhibe D.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante gin min ayenet chinkelat new yeyazekew yehe chifen telacha new Ethiopian lezih yabekat "Egziabher libona yesteh yeker yebelih". Ewent sineger Amen beleh sima demom ye Ethiopia guday yemifetaw le Eyesus Chirstos sinegeza new.
   Emen enji atefera lehodeh ateder.

   Delete
  2. Wuy! endet yalehew mehayim neh yih tshuf yemaygebah? ende gari feres and aktacha bich tayalh.

   Delete
 7. ኢትዮጵያ የተባለች ሀገር የደም መሬት የገዛ ልጆቾ የሚባሉባት ሀገር ናት

  ReplyDelete
 8. ትክክል ብለሀል። እኔ የእናቴን የ ኦሮሞ የአባቴን የአማራ ዘር በዘላለማዊው የክርስቶስ ዘር ለውጫለው። ለሁላችን ልቦና ይስጠን። መፍትኤ ከክርስቶስ እንጂ ከሰው አይገኝም።

  ReplyDelete
 9. Enter your comment..yikirta wedaje eyetewera yalew sile hager new. degmo meleikitu enkuan lehayimanotegna hayimanot lelelewum bihon yemihon hageregna meliekit new. endew bechifin tilacha sewun metilatina yemitsifewunim mekawem agibab ayidelem. mastewal yasfeligal minalibat tsehafiwun ekawemalew bileh kehagerih gar endatitala. lehulachinim libona yisten.

  ReplyDelete
 10. ስድባም ህዝብ የተረገመ ህዝብ እግዚአብሄር በአፉ እንጂ በልቡ የሌለ ህዝብ ።ኢትዮጲያዊ መሆን ማለት መረገም ማለት ነው።ምቀኛ ሸረኛ በምድር ለይ ተንኮለኛ ህዝብ። ገና መአት ይመጣብናል በክፉ ልባችን ነምክንያት።ለእግዚአብሄፈርም ለሰውም የማይመች ዜጋ።

  ReplyDelete
 11. በዚህ ገጽ ጽሑፋቸው የሚቀርብላቸው ሰዎች ሁሉ ይገርሙኛል፡፡ወይ በቀጥታ ወይ በተዘዋዋሪ ስለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ወቀሳ ካልጻፉ የሚነበቡ አይመስላቸውም፡፡እዩት ይሄን ልጅ!
  ስለኛ አባቶች ደካማነት ለመጻፍና አማኙን ለማጣጣል ብዙ ይደክማል፡፡ስለሌሎች ቤተ እምነቶች እና አማንያኑ ግን ትንፍሽ አይልም፡፡የእኛ ሀገር በኦርቶዶክሳውያን አማኞች ምክንያት ለፈተና እንደተዳረገች ያስመስላል፡፡እንደ ርዋንዳ፣ቡሩንዲና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አይነት ሀገራት በጌታ ስም በሚምሉና በሚገዘቱ ሰዎች መካከል በሚጦፍ ግጭት ሲናጡ እንደኖሩ ግን አይናገርም፡፡ቤተክርስቲያን የተቻላትን በጾም፣በጸሎትና የሰላም ጥሪ በማቅረብ የተወጣቻቸውን የእርስ በርስ ግጭት የማስቀረት ኃላፊነቶች አይጠቅስም፡፡የአጼ ዮሐንስ የጎጃም ጥቃት የተገታው፣የአጼ ዮሐንስና አጼ ምኒልክ እርቅ የተፈጸመው በአባቶች ጣልቃ ገብነት ነው፡፡አንዳንድ ጊዜ ጉዳዩ የእርስ በርስ ስለሆነ በገለልተኛነት ለመዳኘት ሲሞከር ከባለጸቦች በኩል የሚመጣው ፍረጃም አስቸጋሪ መሆኑ አይረሳ፡፡
  ያስ ቢሆን የነ አቡነ ጴጥሮስ፣የነ አቡነ ቴዎፍሎስ ሰማዕትነት እንዴት ይድበሰበሳል፡፡በሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ያለው ተሳትፎ ለሀገሪቱ ድክመት ሲሆን አለመጠቀሱ ገራሚ ነው፡፡ቢያንስ በኦሮሚያ እስልምና ከኦርቶዶክስ የተሻለ ተከታይ አለው፡፡ፕሮቴስታንትም ቢሆን አብዛኛው የኦሮሞ ብሔርተኛ እምነት ነው፡፡ሆኖም እነዚህ ተቋማት በሰሞኑ አመጻ ሃላፊነታቸውን ባለመወጣት አይወቀሱም፡፡ሁሉም አፉን የሚፈታው በፈረደባት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ላይ ነው፡፡የሌላው ይሁን፤ዲያቆንና ቄስ የሚል መዐርግ አንግበው ልሳናቸውን ለተሳልቆ ቤተክርስቲያን ላይ የሚያላቅቁ ልብልብ እና ግልብልብ መጽሐፍ ጠቃሽ አፈ-ጻድቆችን ማየት ግን ያናድዳል፡፡
  የኛ ወገኞች በተሐድሶ ስም የምንቀሳቀሰው ቅዱሳን በጌታ ፈቃድ እየበዛን ነው ብላችሁ የለ! በከተማዋ 10 ቅዱሳን ካሉ መቅሰፍቱ እንደሚርቅ ስለተነገረ ጽድቃችሁን አትረፍርፋችሁ ሀገር አትርፉ እስኪ፡፡የአስራ ምናምን ሚሊዮን ጴንጤ ኤልዛቤላዊ ጩኸት ምን በላው! ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፤በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ›› እያልን እንዳንጸልይ ልትገስጸን የሞከርከው ቁንጽል ዲያቆን እስኪ ከቀሚስ ገላጮቹ ቅዱሳን ከነ ፓስተር ተከስተና ዳዊት ሞላልኝ ጋራ ሆነህ ሀገሪቷን በጸሎትህ ከመቅሰፍት አድናት፡፡ወገኛ ሁላ!በስንት ተጋድሎ በቆየች ሀገር ያለምንም መስዋዕትነት የሚሽን ፓንፕሌት እያነበነብክ ኦርቶዶክሳዊነትንና ሀገራዊ ታሪክን ታንቁዋሽሻለህ፡፡ለነገሩ መጽሐፉ ‹‹ወትገብእ አመጻሁ ዲበ ድማሁ›› እንዳለው ጸያፍ ቃልህ ወደራስህ ትመለሳለች እንጂ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማርከስ አቅም የላትም፡፡

  ReplyDelete
 12. nitsuhan lijochwan endebelach yemitinor hager, Ethiopia "Hgere Egziabher" dinkiem yegziabher hager

  ReplyDelete
 13. God bless you the writer of this massage,unless the holy spirit helps you you cant post it, hope every Ethiopian with open hearts listen it,leave on it , may God bless Ethiopia, and Ethiopia will rise hands to God!!!

  ReplyDelete
 14. እርስ በእርስ በዘረኝነት እና ቡድንተኝነት የሚደረገው መጨፋጨፍ እና አላስፈላጊ ማግለል በሰውም በእግዚአብሔርም ዘንድ ነውር ነው፡፡ ይህን በማለታችሁ ጥሩ አደረጋችሁ ስል ዘላችሁ ጳጳሳት፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ዘማርያን እያላችሁ አንድን ሃይማኖት ብቻ ለማጠልሸት ስትሞክሩ ማየት ደስ አያሰኝም፡፡ በኦሮሚያ እና የደቡቡ የሃገራችን ክፍል እኮ የፕሮቴስታንት ፓስተሮች የኦረቶዶክስ እምነት የአማራ እምነት ነው በማለት አማራ የኦሮሞ እና ደቡብ ህዝቦች ጠላት አድርጎ በማቅረብና የተሳሳተ ግንዛቤ በመፍጠር መንግስተ እግዚአብሔርን ሳይሆን የሰውን አስተሳሰብ በማራመድ እምነት ለማስቀየር ሲሞክሩ ነበር፡፡ ስለዚህ መረጫጨት ከተጀመረ ያንንም ወጣ አድርጉታ…ለማንኛውም ሁሉም ሰው አይሳሳትም የተወሰኑ ሊያጠፉ ይችላሉ…እግዚአብሔር ግን የበቀል አምላክ ነው እና ዘረኞችን ሙሰኞችን ወንጌልን ለፖለቲካ አላማ(ለነጮች የእጅ አዙር ገዢነት) ያመቻቹትን ፣ ከእምነት ይልቅ ሥጋዊ ሥራ ያየለባቸውን ሁሉ ይቀጣል፡፡ ለሁላችንም ማስተዋልን፣ ለሃገራችን እንዲሁም ለአለሙ ሁሉ ሰላምን ያድልልን፣ ለንስሃ ያብቃን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 15. በጣም ያሳዝናል አሁንም መከራውን ስቃዩን ያሚቀበለውን ህዝብ እረስተን እራሳችን ሃይማኖት አለን የምንል አሁንም ሰው ላይ እጃችን እንጠነቁላለን። እስኪ ይብቃን ስለ ፍቅር ጠላታችን ስለመውደድ እናስብ እስኪ አምላካችን ያዘዘንን እናድርግ የዚያም ሆነ የዚህ አባት እያልን አንመጻደቅ በአሁኑ ሰእት በየትኛውም በኩል ያሉ አብስቶች ስለራሳቸው ህልውና እንጅስለህዝቡ አንዳቸውም አይገዳቸውም የሚገዳቸው አባቶች ቢኖሩንማየኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም በሆነ ነበር።እና እኛ እንንቃ አንድነታችን የሚመጣበትን ህዝባችን ሰላም የሚያግርኝበትን ሁሉ እያሰብን ብርመተሳሰብ በመፈቃቀር እንተሳሰብ እናንተ እዝህ ቁጭ ብላችሁ የስድብ ናዳ ታወርዳላችሁ ከዚያም እንድሁ መሃከል ላይ ያለ ደግሞ እናንተን በለው በለው ይላል።እባካችሁ ጊዜው ዛሬ ነውን አንሞኝ ለንስሃ እንስ ለጽሎት እጃችን እንዘርጋ።መሰዳደብ የዲያብሎስ ይህ ዌብ ሳይት ሳየው በትትክክል የእውነተኛዋን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሚወክል አይደለም። እና እባካችሁ ሃይማኖታችንን አታሰድቡ መልካም ነገር አስተላልፉበት ቸሩ መድሃኒያለም ሁላችንም ለንስሃ ጊዚር ይስጠን!!!!!!!!!"

  ReplyDelete
 16. እግዚአብሄር ይባረካችሁ። ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻው ቀርቦዋል እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ። የጴጥ መል ም 4ቁ 7። በመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ ዘመን ፍጻመ ላይ መድረሉን በግልጽ አድርጎ ነግሮናል። እኛ ግን ማስተዋል አጥተን የድያብሎስ ማደረ ሆን እርስበርሳችን እንገዳደላሌን እንተራረዳለን። እጅግ በጣም የሚያሳዝነው በዚህ ክፉ ዘመን እያየነ ያለነው አስፈርው ነግር በእግዚአብሔር አምሳልና ምሳሌ አርአያ የተፈጠረውን ሰው ሥጋ አርዶ መመብላት የጅመረበት ሰዓት ላይ ነው ያለነው። የሰው አንገት በጭካነ እንደ ዶሮ አንገቱ በገዛ ወገኑ እየተቆረጠ ያለበት ወቅት ላይ ነው የምንገኙው።ኤረ ወገኖቼ ወደ እግዝአብሔር ሁላችን ተሰብስበን እንጮህ ከእሩሱ በቅር አዳኝ የለም። ሰው ለሰው ማዘን የቀረበት አስፈርዉ ዘመን ይህ ዘመናችን ነው። መንፈሳዊያን የሆኑት ሰዎች ሁሉ በግፍ የተሞሉ ሆነው እያየን ነው። እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል ታጠቡ ሰዉነታችሁንም አንጹ የሥራችሁን ክፋት ከአይኔ ፊት አስወግዱ ክፉ ማድረግን ተው መልካም መሥራትን ተማሩ ፍርድን ፈልጉ የተገፋውን አደኑ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት። ት ኢሳ ም 1 16። አባቶችን ለክርስትያኑ ነፊስ ደንታ የላቸው የእራሳቸው ፍላጎት ከተማላላቸው። እግዚአብሄር ግን የሚፈርድበት ቀን ሰዓት ይመጣል። ይልቁን ግዜው ሳያልፍ ንስሐ እንግባ። ስጋ ለባሹ ሁሉ እግዚብሄር እየበደለ ነው። እግዚአብሔር እምላክ ህዝባችንን ይጠብቅል የእመቤታችን የቅዱሳን ጸሎትና አይለየን አሜን።

  ReplyDelete
 17. ነበር ምን ዋጋ አለው!!! በነበር እንዲቀር ግን ይህች ቅድስት ሀገር ታሪኳን እንዳታሻገር ሰይጣን ምን ይሰራል???? ይኸው ሀገራችን የመሐመዳውያን አስተምሮ፣ የአውሮፓ ስኮላር፣ የሉተር የፍልስፍና የተኩላው ትምህርት አንድ ላይ ተቀናጅተው ይህን ድንቅ ታሪኳን ለትውልዱ እናዳታሻግር ከቅዱሳን ልጆቿ የተረከበችውን ቃል ኪዳኗን ከፈጣሪዋ እንዳትቀበል ለማጥፋት በሚያደርገው ትንቅንቅ እንደዚህ አይነት ትውልድ እንደፈጠር አድርጓል፡፡ የእፍኝት ልጅ፡፡ አባቱንና እናቱን ገድሎ እራሱ ብቻ እንዲኖር የሚሰራ ትውልድ፡፡ እስኪ ገጻችሁን ተመልከቱት፡፡ የአባቶችን ፎቶ ለጥፎ የሚሳደብ ትውልድ፣ በረከቱን ለውጪ ሰጥቶ ታሪኩን የሚሳደብ ትውልድ፡፡ እንደናንተ አይነቱ ትውልድ ይህች ምድር እያፈራች በየትኛው በኩል ትውልድ ይባረክ???? እግዚአብሔርና ኢትዮጰያ ለማለያየት ዲያቢሎስ መስራት የጀመረው በትንሹ 4ዐዐ ዓመት ሲሆን በፊርማ አረጋግጣ ከአምላኳ ከእግዚአብሔር ከተለያየች ደግሞ 42 ዓመት ሆናት፡፡ ካዲያ በየትኛው የበረከት ስራዋ ትባረክ???? የእናንተ አስተምሮ እንኳን ከገባ 1ዐዐ ዓመት ሆነው፡፡ እስኪ ሀገራችን ምን አተረፈች???????? ረሀብ ቢመጣ በዚሁ ዓመት የእርስ በርስ ጣርነት ቢነሳ በዚሁ ዘመን፣ ሀገራችን የሚሙቱላትን ማመስገን ትታ የሚገድሏትን የምታከብር ሀገር ሆነች፡፡ እሾህና አሜኬላ እንዲበዛ ያደረገው ሰይጣን ከሀገራችን እስካልወጣ ድረስ እንደዚህ ዓይነቱ ቅጣት ይቀጥላል፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጰያን ይባርክ!!! የእኛን ባዶነት ሳይሆን የቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎታቸውና ምልጃቸው በረከታቸውን ያድለን አይለየን፡፡ የድንግል ምልጃዋ አይለየን፡፡

  ReplyDelete
 18. ነፍሰ ገዳዩ ተሐድሶ ፕሮቴስታንት ይደምሰስ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. aye maru mirere yalke chelema eko nehe

   Delete
 19. ወይ ማሩ ተሀድሶ እንዳሆነ ይደምሰስ በማለት አይጠፋም ተሀድሶ በያንዳንዷ ቤተክርስቲያን አለ ባይገርምህ ማህበረ ቀረዱሳን ዉስጥም አለ ገና ይበዛል አንተም የጊዜ ጉዳይ ነ ዉ እንጅ ተሆናለህ
  ተባረክ

  ReplyDelete
 20. ባለፈው ግዜ ሀራ ብሎግ እንድ ሳምንት ብትዘገይ ሐራ ወሬ ጠሮባት አላችሁ እናንተ ምን ጠሮባችሁ ነው አሁን ከሳምንት በላይ የጥፋችሁት በአይናችሁ ወደ ውጭ ብቻ ሳይሆን ውደራሳችሁም እዩ

  ReplyDelete