Monday, December 28, 2015

ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳውያን ኮሌጆች ላይ በከፈተው የጽሑፍ ዘመቻ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነውራሱን ብቻ ትክክልና የቤተክርስቲያን ጠበቃ አድርጎ የሚመለከተውና ሌላውንና የእርሱን ተረት አልከተልም ያለውን፣ በአሰራር እንኳን ለእርሱ አልመች ያለውን ሁሉ መክሰስና ስሙን ማጥፋት ልማዱ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያወጣ ባለው ስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ሶስቱን አንጋፋ መንፈሳዊ ኮሌጆች ማለትም የቅድስት ሥላሴ፣ የመቀሌው ከሳቴ ብርሃንና ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆነዋል በማለቱ ተቃውሞ እየገጠመው ነው፡፡
ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን አለአቅሙ ሊዘልፋቸው የተነሳው እነዚህ ሦስቱ ኮሌጆች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው የሚንቀሳቀሱና የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት የቤተክርስቲያኒቱን ራዕይ ያሳካሉ የተባሉ ኮሌጆች ናቸው፡፡ ኮሌጆቹን የመሠረትዋቸው ሰዎችን እንኳን ብንመለከት ለትምህርትና ለለውጥ ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ አባቶች ፍሬ መሆናቸውን እገነዘባለን፡፡ ለምሣሌ የቅድስት ሥላሴ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ቴዎፍሎስ፣ የከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ መሥራች ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፣ የሰዋሰው ብርሃን ደግሞ የአጼ ኃ/ሥላሴ ምስረታ ውጤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ትምህርት ቤት እስከ ሚኒስቴር ደረጃ የደረሱ ደቀመዛሙርት ወጥተውባቸዋል፡፡ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን እንኳን ብንመለከት የቅ/ሥላሴ ኮሌጅ እንደ አይን ብሌን የሚያሳሳ ኮሌጅ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል፡፡ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ይቅርና አሁን በሕይወት ያሉም የሌሉም አባቶች ሊቃውንት ወጥቶውበታል፡፡ ለመጥቀስ ያህል፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ፕሮፌሠር ሉሌ፣ ዶ/ር ሐዲስ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ፣ አቶ እሱባለው፣ አቶ አእምሮ ወንድምአገኘሁ፣ አቶ ገ/ክርስቶስ መኮንን፣ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ስርግው ሐብለ ሥላሴ፣ ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ፣ ፕ/ር ታደሰ ታምራት በመጀመሪያ የዚህ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ በየተሰማሩበት መስክ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ የተንቀሳቀሱና በጎ አሻራቸውን ያሳረፉ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡

በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ አቶ የማነ ገብረ ማርያም፣ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ፣ ርእሰ ደብር መሐሪና ሌሎችም ወጥተዋል፡፡ ከመቀሌው ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅም በተመሳሳይ በርካታና ለቤተክርስቲያንና ለአገር የጠቀሙ ምሁራን ወጥተዋል፡፡ ለመማር ሳይሆን ኮሌጁን በማቅ አስተሳሰብ ለመምራትና ጫና መፍጠር በሚል ተልእኮ በርካታ የማቅ አባላትም በተለይ በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማታው መርሀ ግብር እየተማሩ ነው፡፡ እንዲህ የምንለው በሀሰት አይደለም በተጨባጭ እንደሚታየው ወደኮሌጅ የገቡት ለመማርና አዲስ ነገር ለማወቅና ለመለወጥ ሳይሆን በማህበሩ ውስጥ ሲጫኑና ሲጋቱ የኖሩትን ተረት ለማጽናት ነው፡፡ ወይም በትምህርት ሳይርሱና ሳይረሰርሱ በገቡበት ሁኔታ እንደዚያው እንዲወጡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ከእነርሱ አስተሳሰብ ውጪ የሆነ ነገር መምህራኑ ቢናገሩ ለክስና “ይህ የሌሎች ትምህርት ነው ለምን ይህን ታስተምራለህ?” እያሉ መምህራኑን በማሸማቀቅ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሲያውኩ ነው የኖሩት፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ኮሌጅ የመማሪያና የመመራመሪያ ስፍራ መሆኑ ቀርቶ የተለመደውን ነገር ተጭነው ያለአንዳች ለውጥ የሚወጡበት ቦታ እንዲሆን እያደረጉት ነው፡፡
ማቅ ስምአ ጽድቅ ብሎ በሰየመውና እውነት ሳይሆን ሐሰት በሚያወራበትና ተረት በሚተርትበት ጋዜጣው ላይ በጅምላ ስም ሲያጠፋ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት የገሃነም ደጆች ብሎ የብዙዎችን ስም አጥፍቷል፡፡ የጻፉትም በህግ የተጠየቁበት ሁኔታ አለ፡፡ ማቅ መቼ ይሆን ጋዜጣውን ቁምነገር የሚያስተላልፍበት? ስለተሐድሶ በተከታታይ እየጻፈ ያለው “ንቁ!” በሚል ርእስ ነው፡፡ “ንቁ!” አርዮሳውያን የሆኑት የይሆዋ ምስክሮች መጽሔት ስም ነው፡፡ መጽሔቱ ከስምአ ጽድቅ በፊት የነበረ ነው፡፡ ለእርሱ ሲሆን ርእስ ይሠርቃል፡፡ ሌላውን ግን በሐሰት ይከሳል፡፡ ለነገሩ “ንቁ” ሲል እኛም ነቅተናል የሚሉ በዝተዋል፤ የኮሌጆቹን ስም አጥፍቶ እኔ ጋ ተመዝገቡ እንዳለ መንቃታቸውን በመናገር፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማቅ ከጋዜጦቹ በአንደኛው ላይ አባ ሰላማ ብሎግን ጨምሮ ሌሎቹን ከእርሱ በአስተሳሰብ የተለዩትን ብሎጎች ስም በማጥፋት ጽፏል፡፡ ሲጽፍም ሌሎቹ የአባቶችን ስም በከንቱ እንደሚያጠፉ አስመስሎ ነው የጻፈው፡፡ ሐራ የተባለውን ብሎግ ግን ስሙን እንኳን አላነሳም፡፡ ለምን? ቢባል የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ነዋ! ባይሆንማ ኖሮ ቢያንስ ለማቅ ያልተመቹትን አባቶች ስምና ግብራቸውን እየጠቀሰ በማስፈራሪያነት የያዘባቸውን መረጃ እያወጣ እነርሱን ከማሳጣት ወደኋላ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ እውነተኛ ቢሆን ሐራንም መጥቀስ ነበረበት፡፡ ግን “ስምአ ጽድቅ” ጋዜጣ ስምአ ሐሰት በመሆኑ ለእውነት ሳይሆን ለግል ጥቅም የቆመ በመሆኑ እውቱን በሐቀኛነት አልመሰከረም ወደ ስም ማጥፋት ነው የገባው፡፡    
ከስህተቱ የማይማረው ስምአ ጽድቅ አሁንም የቤተክርስቲያኒቱን ኮሌጆች በተሐድሶነት በመፈረጅ ስማቸውን አጉድፏል፡፡ የአሁን የስም ማጥፋት ዘመቻ ለየት የሚያደርገው ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅ አመራሩን ጨምሮ 50 ከመቶ ተሐድሶ ነው፡፡ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅን በተአምር ካልሆነ በቀር ኦርቶዶክስ ሆኖ የማይወጣበት፣ የቅድስት ሥላሴን ኮሌጅ ደግሞ “መናፍቅ ሳልሆን አውጣኝ ተብሎ የሚጸለይበት ኮሌጅ ናቸው” በማለት መፈረጁ ነው፡፡ በተለይ በቅድስት ሥላሴ በማታው መርሐ ግብር አብዛኛው የማቅ አባላት ይማራሉና እንዲህ ከሆነ ታዲያ አባላቱ “መናፍቃን” አይሆኑበትም ወይ? በአንድ ወገን የኮሌጁን ስም እያጠፋ በሌላ በኩል ደግሞ ለዓላማው እየተጠቀመበት መሆኑ ማቅን ትልቅ ትዝብት ውስጥ ጥሎታል፡፡   
የአሁኑ የማቅ ፍላጎት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው አንድ እውነት አለ፡፡ በስምአ ሐሰት ጋዜጣው ከተሳደበ በኋላ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስም ለቤተክርስቲያን ሊቃውንት፣ ዲያቆናትና ቀሳውስት የነጻ ትምህርት ዕድል  የሚሰጥ ተቋም ከፍቻለሁ ብሎ አቡነ ሉቃስ በተገኙበት በሰሜን ሆቴል አስተዋውቋል፡፡ ብዙዎች እንደገመቱትም በዚህ ወቅት የኮሌጆቹን ስም ማጉደፍ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ሶስቱም ኮሌጆች ለቤተክርስቲያን አይበጁም ለቤተርክስቲያን ያለሁላት እኔ ብቻ ስለሆንኩ እኔ አሁን አዲስ ባቋቋምኩት ተቋም ገብታችሁ ተማሩ የሚል ነው መልእክቱ፡፡ ኮሌጆቹ የተሐድሶ መፈልፈያ ናቸው ንጹሕ ትምህርት ያለው አሁን በከፈትኩት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ት/ቤት ነው ብሏልና፡፡ ከዚህ ቀደም በዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ “ማኅበሩ ወደፊት ለእኔ ገድል ፃፉልኝ ፅላት ቅረጹልኝ ማለቱ አይቀርም” የሚለው ነገር የደረሠ ይመስላል፡፡ አሁን የቀረው የዚያኛው ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ትክክል አይደለም፣ ጽላት አቀራረጹ ልክ አይደለም እኔ ቀርጬ የምሰጣችሁን ተጠቀሙ ማለቱ አይቀርም፡፡
የማቅ የስም ማጥፋት ዘመቻ ኮሌጆቹ በዝምታ አልተመለከቱትም ሁሉም ለማቅ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተገቢውን ምላሽ  ለመስጠት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ማቅ በጻፈው ጽሑፍ ላይ የማስተካከያ ጽሑፍ እንዲያወጣ ደብዳቤ እንዲያወጣ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ የቅድስት መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የኮሌጁን ስምና መብቱን ለማስጠብቅ በየጊዜው እየወሰዱ ያለው ተገቢ እርምጃ የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ በቅርቡ እንኳ በቸሬ እና በዘሪሁን ሙላቱ ላይ የወሰዱት እርምጃ ከዚህ ቀደምም የማቅ አባል በነበረው አሜሪካዊ ዲን ላይ የወሰዷቸው አፋጣን እርምጃዎች ለዚህ ማሳያዎች ናቸው፡፡ አሁንም በማቅ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንደሚወስዱ እያሳዩ ነው፡፡ ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅም በስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ እያቀረበና በሕግ ለመጠየቅ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ በኩልም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡


19 comments:

 1. akerkariachihun yemisebir tsihuf mk awutitual malet new endih yancherecherachihu.

  ReplyDelete
 2. አብዛኛኛ ው የቤተ ክርስቲያን ሀላፊዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣የቢሮ ሰራተኞች ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የገቡት እና በቀንም ሆነ በማታ ትምህታቸውን አጠናቀዋል ተብለው የተመረቁት እኮ የ12 ኛ ክፍል ሰርተፊኬታቸው በፎርጂድ የተሰራ ነው፡፡ ከሁሉም የሚገርመው በፎርጂድ ሰርተፊኬት ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተመዝግበው በዲግሪ ተመርቀው ለማስትሬት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ነው፡፡
  አሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቅድስት ሥላሴ የመጡ እና በማስትሬት ፊሎሎጀ ወይንም በሌላ ትምህርት የሚማሩና ተምረው ፒኤችዲ ላይ ያሉትን በሙሉ ማጣራት ቢጀምር በእርግጠኝነት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 12ኛ ክፍል በፎርጂድ የገቡ ናቸው፡፡
  ይሄ አዲስ ነገር አይደለም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሞሉት አብዛኞቹ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ከጳጳሳቱ ጀምሮ ፤ሲሾሙ በመንፈሳዊነታቸውና በእውቀታቸው ሳይሆን ፓትርያርክ ጳውሎስን በመደለል ጉቦ በመስጠት ወዘተ… ጳጳስ ሆነዋል አሁን ጀርባቸው ሲታይ የልጅ አባቶች፣ባለቪላቤቶች፣ዘመናዊ መኪናዎች ባለቤቶች፣ እቁባቶቻቸው ብዙ ፣የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ፣እረ ስንቱ … ታዲያ እናንተን እያየ ማን ጤነኛ ይሆናል ፤፤ ብቻ እግዚአብሄር ፍርድ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 3. Yesewu belawu maheber gedgeda sichir yinoral enji Ashenafiwu Egziabher newu.!!!!!

  ReplyDelete
 4. ወይ ውረድ ወይ ፍረድ ።ክርስቶስን እንደሰቀሉት አይሁድ የእነርሱ ምሳሌ የሆነ ማህበር የዘመኑ አይሁድ የክርስቶስ ጠላት ማህበር።የቤተክርስቲያን የጀርባ ላይ እከክ በርባንነ ፍቱልነ እየሱስን ገርፋችሁ ስቀሉት የሚል ማህበር።ጌታ ሆይ ህዝብህን እና ቤተክርስቲያንክነ ከዚህ አንተን ከሚጠላ ማህበር ታደግ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባሰላማዋች ዛሬስ ሰይጣን ምን አቀበላችሁ ????? እንድታሰሙለት ሳስባችሁ ሰይጣን አጀንዳ ይሰጣችኋል እናንተ አስፍታችሁ ታቀርቡታላችሁ.
   አንተም የሰይጣን ተላላኪ ነህ..

   Delete
 5. አባ ጢሞቴዎስም ከቦታቸው ይነሳሉ፣ እውነተኛ አባት ይተካል። የሰይጣን ስብስብ አባ "ሰላማ"ወደ መቃብር ይወርዳል።

  ReplyDelete
 6. ደብዳቤው ለማኅበረቅዱሳን ስለተጻፈ ብቻ ዘላችሁ ኮሌጁ የእናንተ እንደሆነ አስመሰላችሁት፡፡ደብዳቤውን በጥሞና አንብቡት፡፡በማኅበረቅዱሳን ላይ ኮሌጁ ያቀረበው ቅሬታ ተሐድሶን በውስጤ እንዳይገባ አስፈላጊውን ማጣራት አደርጋለሁ፤ተጨባጭ መረጃ ሲቀርብ እርምጃ እወስዳለሁ የሚል ነው፡፡ደብዳቤው ሲጻፍም ማኅበረቅዱሳን የቤተክርስቲያን አካል መሆኑ ታምኖ እርምት እንዲያደርግ ነው፡፡እናንተ ግን ደብዳቤውን ይዘት ሳታጤኑ ማኅበረቅዱሳንን ያጠቃን መስሎአችሁ የራሳችሁን ፍላጎት አጉልታችሁ ታወራላችሁ፡፡ደብዳቤው ውዳሴ ማርያም ያልደገመ ሰው ኮሌጁ አይቀበልም እያለ እናንተ በተቃራኒው ተረት እያላችሁ ትቀባጥራላችሁ፡፡የእናንተ ዓመት እስከ ዓመት ሐሜትም ተረት አልተባለ እንኳንስ የወላዲተ አምላክ በምስጢረ ሥጋዌ ያጌጠ ውዳሴ ማርያም፡፡ዘወትር ከግርግር ለማትረፍ የምትሞክሩ ከለባት ሆናችሁ ቀራችሁ፡፡

  ReplyDelete
 7. አባ ሰላማዎች ለምታቀርቡልን መረጃ ትባረኩ፡፡ይህን ጉዳይ ወደ ፌስቡክ ላይ አውጡትና ሕዝቡ ይወያይበት፡፡ይህ ስም አጥፊና ከሳሽ ማኅበር ድካሙ መና እንደሚሆን ሲያውቅ በቀሩት አገልጋዮችና መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የድፍረት አፉን ከፍቶአል፡፡እንዴውም መንፈሳዊ ኮሌጆቹ ባይኖሩ የሕዝቡ ፍል ሰት እጅግ በጣም ይጨምር ነበር፡፡ወይ ማኅበረ ቅ.የምትገርሙ ጉዶች ናችሁ፡፡ሐዋርያት በዚህ ዘመን ቢኖሩ የመጀመሪያ ሰቃዮች እናንተ ነበር የምትሆኑት፡፡ሥልጣን የላችሁም እንጂ ቢሰጣችሁ እኮ በጌታ ቀኝ መቆም ያለብን እኛ እና የእኛ ደጋ ብቻ ነው ትሉ ነበረ…ጌታ የልባችሁን ጨለማነት ገልጦ የወንጌሉን ብርሃን ይሳልባችሁ፡፡

  ReplyDelete
 8. ሐሰተኞች እግዚአብሔር ለቤተክርስትያን ያስነሳው በመሆኑ ማኀበረ ቅዱሳን እድሜው ይርዘምልን፡፡ የሉተር ተላላኪዎች መቼም አይሳካላችሁም ራሳችሁን ችላችሁ ወደ ባዶ መጋዘናችሁ መከማቸት ብቻ ነው ያላችሁ አማራጭ፡፡

  ReplyDelete
 9. Aworew tekulaw maq abet sentu sentu mekera deresebat Bete Kirstian benante ????????? For church isis geday aremene 1000%

  ReplyDelete
 10. ተሀድሶ ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ አሉ

  ReplyDelete
 11. ተሀድሶ ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ አሉ

  ReplyDelete
 12. Enante weregnoch ere neseha gibu lebetekirstyan man endekome hulum tenkiko yawkal mak seytanim behon lebetekirstyan endekomu yawkal yimesekiral minale yichi yekerachihun zemen ewnet bitinageru yealem gazetegnoch enkuan tekawmiwoch yeserutin melkam neger yinageralu enante "yemnet" sewoch tebilachihu and ewnet yelelachihu yedrow abireham endaymeslachihu ene yabelagnal beye bihed debedebegn yalew telat enante nachihu amlak lib yistachihu.

  ReplyDelete
 13. ጒበዝ ተሀድሶ ማህበረ ቅዱሳን ዉስጥ አለ ተወረናል
  ማንን እንመን

  ReplyDelete
 14. ደጀ በጥባጮች….እናንተ የሆነች ጉዳይ ላይ ስትንጫጩ ማየት ለኔ ልዩ ትርጉም ይሰጠኛል፤ ቤተ ክርስቲያን በሆነ ጉዳይ ድል አድርጋለች ማለት ነውና! ውጊያውን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር አስመሰላችሁት እንጂ የመውጊያውን ብረት እየረገጣችሁ እንደሆነ ውስጣችሁ ያውቀዋል፡፡ እናንተ ብትጮሁም ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የጻፈውን ጽፏል››! ገና ምን ታይቶ….በመረጃ ብቻ ሳይሆን በማስረጃ የተደገፉ ያልተነገሩ ብዙ ጉዶች ገና ይጻፋሉ፡፡ እናንተም የወዳጆቻችሁን ስም እንዲሁ ጻፉልን፤ ለክፉ ቀን ተመዝግቦ ይቀመጥ! ሃይማኖት እንዳትጠፋ የሚታገለውን፣ ሥርዐት የሚጠብቀውን፣ ቤተ ክርስቲያን አትታደስም የሚለውን ሁሉ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ነው›› እያላችሁ ብዙ አባላት እያፈራችሁለት ነው፤ ይህ ለእናንተ ያልተገለጠ የእግዚአብሔር እጅ ነው! ማኅበሩ ፎርም ካስሞላቸው አባላት በላይ እናንተ ያስሞላችሁለት በቁጥር ይበልጣሉ፡፡ ስለዚህም እናንተም ወሬአችሁን ቀጥሉ….ማኅበሩም ትጋቱን አያቆምም፤ እውነተኛ መድኃኔ ዓለም ደግሞ ምን ጊዜም ከእውነት ጋር ስለሆነ የእናንተ ወሬ ከትዝብት አያልፍም! ዛሬም ግን የምሕረት አምላክ ትመለሱ ዘንድ እጁን ዘርግቶ ይጠብቃችኋል፤ እምቢ ብትሉ፣ ብታምጹ ግን እናንተ ትጠፋላችሁ፤ ኦርቶዶክስ ግን ጠላቶቿን ሁሉ አሳልፋ ለዘላለም ትኖራለች!!!

  ReplyDelete
 15. yetbarek egziabhr amlak kulene mkn amlak yasfalen awrewome leb yestew!!
  ReplyDelete
 16. mkn amlak yasfalene awrewem yechuh!!

  ReplyDelete
 17. ኧረ ባክህ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም ምን ሆንኩ ብለው ነው ተቃውሞ ያሰሙት ምስጢራችን ወጣ ብለው ነው?????

  ReplyDelete
  Replies
  1. Luterawyan ketewahdo bet yemiteregubet gizew dersoal!!!?

   Delete