Tuesday, December 29, 2015

ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ልታቋቁም ባቀደችው የቴሌቪዥን ጣቢያ ገና ከጅምሩ ሊፈጸምበት የነበረው ሙስና መክሸፉ ተሰማቅዱስ ሲኖዶስ በዘንድሮው የጥቅምት ስብሳባ ላይ እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኒቱ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ስርጭት ማለትም የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ልትጀምር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው ጥናት ላይ መሠረት በማድረግ የአንድ ዓመት በጀት 12 ሚሊየን ብር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቋል፡፡ ይህን ፕሮጀክት የሚመራ ቦርድ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ የስብከተ ወንጌል መምሪያ የበላይ ሃላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ሐሳቡ በመጀመሪያ የመነጨውና እንቅስቃሴው የተጀመረው ጉዳዩ ግድ ከሚለው የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሲሆን፣ የሰውን ሐሣብ በመንጠቅና የራስ አስመስሎ በማቅረብ በተግባር የተመሰከረላቸውና የሰዎችን ድርሰት በራሳቸው ስም በማሳተም ጭምር ቅሌት ውስጥ የገቡትና እስካሁን በሲኖዶስ ተጠያቂ ያልሆኑት አባ ሳሙኤል ይህን የስብከተ ወንጌልን ፕሮጀክት በመንጠቅ በሌላቸው ውክልና የራሳቸው አስመስለው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሐሳቡን ራሳቸው ያመነጩትና የጀመሩት ያህል በመቁጠር ስለጉዳዩ የማቅ ልሳናት ሆነው እያገለገሉ ባሉት እንደ አዲስ አድማስ ባሉ ጋዜጦች ላይ ጉዳዩን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ እንደነበር የጥቅምት 20/2008 አዲስ አድማስ ጋዜጣን መመልከት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ አባ ሳሙኤል ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም ከቦርዱ እውቅና ውጪ በስልት መንቀሳቀሳቸው ስለተደረሰበት የጉዳዩ ተዋናዮች ለነበሩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ከቤተክህነት አካባቢ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሊቋቋም የታቀደው የቴሌቪዥን ጣቢያ እስራኤል አገር ሲሆን፣ ባለፈው ሰሞን አባ ሳሙኤል ከዚህ ጋር ባልተያያዘ ለህክምና በሚል ፓትርያርኩን ፈቃድ ጠይቀውና ደብዳቤ አጽፈው፣ በጎን ደግሞ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ የአቡነ ማርቆስን ውክልና ወስደው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል  ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አባ ሃይለማርያም የፈረሙበትን ደብዳቤ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለመዋዋል ሙከራ አደርገው ነበር፡፡ ይህ የሆነው አባ ማቴዎስ ከሲኖዶሱ ስብሰባ በኋላ እምብዛም በቢሮ የማይገኙ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ውሉና ክፍያው የሚፈጸምበት መንገድ በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ እነርሱ ለመተዳደሪያ እንዲሆናቸው አዲስ አበባ ውስጥ ፎቅ ለማስገንባት ፕሮጄክት ነድፈዋልና የእነርሱ ፕሮጀክት አገር ውስጥ በብር እንዲሠራና እነርሱ ደግሞ ለቴሌቪዥን ጣቢያው በዶላር ክፍያውን እንዲፈጽሙ ነበር በአባ ሳሙኤል በኩል የታሰበው፡፡ ይሁን እንጂ ገዳሙ የሲኖዶስ ትእዛዝ እንዴት በአባ ኃይለማርያም ደብዳቤ ይወጣል? በማለት ጥርጣሬ ስለገባው እምቢ አለ፡፡ ጉዳዩም ፓትርያርኩ ጋ ስለደረሰ አቡነ ማርቆስ የሲኖዶስን ውክልና ከኮሚቴው ውጪ ለሆኑት ለአባ ሣሙኤል በመስጠታቸው፣ አባ ኃ/ማርያም ደግሞ ቀጥታ ፓትርያርኩን የሚመለከተውን ይህን ትልቅ ጉዳይ በሌላቸው ሥልጣን ደብዳቤ በመጻፋቸው ለአቡነ ማርቆስ በፓርያርኩ ለዶ/ር አባ ሀይለማርያም ደግሞ በአቡነ ማቴዎስ በተፃፈ ደብዳቤ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አባ ሳሙኤል ከተቋቋመው ኮሚቴ ውጪ የተደረጉ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች እርሳቸው ግን እዚህ ኮሚቴ ውስጥ የሚያስጠብቁት ጥቅም ስላላቸው ይሁን በሌላ ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም፣ ወደ እስራኤል ያለ ምክንያት ሄዱ እንዳይባሉ የህክምና ፈቃድ ደብዳቤ አጽፈው በስልት ነው የተንቀሳቀሱት፡፡ ሆኖም ገዳማቱ በያዙት ጠንካራ አቋም ምክንያት ለአሁኑ ሳይሳካላቸው ለአቡነ ማርቆስም ሆነ ለአባ ኃይለማያም ጦስ ሆነዋል፡፡ እስካሁን ያልታወቀው አቡነ ማርቆስ ለአባ ሳሙኤል ውክልናውን የሰጡት ከምን የተነሣ ነው የሚለው ነው፡፡ አባ ኃይለ ማርያም ደብዳቤውን የጻፉት ግን ከሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ በአብዛኛው ቢሮ ያልገቡትን አባ ማቴዎስን ተክተው በም/ስራ አስኪያጅነታቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ የአባ ማቴዎስ አለመኖር በፈጠረላቸው በዚህ አጋጣሚ አባ ሳሙኤልን ታዛዥ የሆኑት ግን ወደፊት ለጵጵስና ከታጩት አባቶች አንዱ እርሳቸው ስለ ሆኑ ኮሚቴው ውስጥ ሚና የሚጫወቱት አባ ሳሙኤል ምርጫውን ያለ ሳንካ እንዲያጠናቅቁላቸው አስቀድመው ውለታ ለመዋል ነው ሲሉ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ አባ ሀይለ ማርያም ከዚህ ቀደም እነ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው የሚያደርጉትን ጉባኤ ለማደናቀፍ አፍራሽ ደብዳቤ በመፃፍ ይታወቁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከራስ ጥቅም አንፃር የሲኖዶስን ውሣኔ ባልተገባ መንገድ ለማስፈጸም በማን አለብኝነት መንቀሳቀሳቸው እኚህ ሰው አሁን እንዲህ ካደረጉ ለወደፊቱ ጵጵስና ቢያገኙ ምን ሊያደርጉ ነው? የሚል ጥያቄ ፈጥሯል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሁለቱም በደብዳቤ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ተገቢ ነው፡፡ የኢየሩሳሌም ገዳማትም ያለ ሲኖዶስ ውሣኔ ቃለ ጉባኤ ሳይዙ ለመጡት አባ ሳሙኤል በአባ ኃይለማርያም ደብዳቤ ብቻ በዶላር ለጣቢያው አንከፍልም ማለታቸውም ተገቢ እርምጃ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የራስዋን የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈት በጐ ሐሳብ ቢሆንም ክፍተቱን በመሙላት ረገድ አስተዋፅኦ የነበራቸውን የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ለማስቆም ግን የተቸኮለ ይመስላል፡፡ የተቋቋመው ቦርድም ገና ከአሁኑ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ ስህተት ከሠራ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፣ ሩጫው ወደ ሥራው ሳይሆን ወደ ገንዘቡ ከሆነም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ገና ከመነሻው ፕሮጀክቱን በሰው ኃይል ከማደራጀት ባለሙያዎችን ከማሰማራትና ከመሳሰለው እርምጃ በፊት ገንዘብ ላይ አይን ከተጣለ ዋናው ጉዳይ ገደል መግባቱ ነው፡፡ “ወዴት እንደሚያደርስህ ሳታውቅ መንገድ አትጀምር” ይባላልና 24 ሠዓት በጣም ሰፊ ጊዜ በመሆኑ ዘመኑን የዋጀና ሕዝብ የሚፅናናበት አገልግሎት ለመስጠትና ያልተሸቃቀጠ ንጹሕ ወንጌል የሚሰበክበት አገልግሎት እንዲሆን ከወዲሁ በትኩረት መታሰብ አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም እንደታዩት አኮቴት እና የማኅበረ ቅዱሳን ፕሮግራሞች ገዳማትን ብቻ እናስጐበኛለን ተብሎ የአየር ሠዓትን በዚህ ለመሸፈን ታስቦ ከሆነ ሕዝቡን ከፍልሰት አይታደገውም፡፡ ሕዝቡ ወደሌላ እየፈለሰ ያለበት ዋናው ምክንያት የሚሰጠው ትምህርትና የሚሰበከው ልብን የሚያሳርፍ ወንጌል ባለመሆኑ ነው፡፡ስለዚህ ፕሮግራሞቹ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ ቀድሞ በብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ቤተክርስቲያኒቱ ታስተላለፍ የነበረውን ፕሮግራም ይዘትና ምንነት መፈተሽና ዘመኑ የሚጠይቀውን አገልግሎት መስጠት ተገቢ ነው፡፡ አሊያ ከጨዋታ ውጪ መሆንም አለ፡፡ የጣቢያውን አገልግሎት የራሳቸውን ዝና ለመገንባትና ግላዊ ጥቅም ለማግኘት የሚሯሯጡትን  ቅዱስ ሲኖዶስ ከወዲሁ ሊያስቆማቸው ይገባል እንላለን፡፡21 comments:

 1. It is wasting your time you are not preaching Bible but claiming MK this indicates that the blog stands for evil work by making conflict inside people so please stand and evaluate your self unless you have endless Christin will work for him self to get the promising land. GOD bless Ethiopia

  ReplyDelete
 2. Azenalehu Abune Samuel Btewahedo church yemesrut tenkol le girma wondemu begenzeb kihenet aberketu negade wondwosen getachew le tebale (Dukim) begenzeb USA selemehed ere ere sentu

  ReplyDelete
 3. No one preaching the true bible except Ethiopian Orthodox church.

  ReplyDelete
 4. አሁን ያለየሌለውን የሚያስቀባጥራችሁ እውነተኛው የቤተክርስትያን ትምህርት ቤተክርስትያን በምትቆጣጠረው ተቋም ሊተላለፍ ስለሆነ ነው አይደል፡፡እንግዲህ ምን ትሆኑ ቤተክርስትያን ከእንደናንተ አይነቱ አወናባጅ ልታርፍ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. እጅግ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ለነገሩ አባ ሳሙኤልም ሆነ አባ ሀይለማርያም ሁለቱም የዝሙት መንፈስ የነገሰባቸው ፣ በዝሙትም ሳቢያ ገንዘብ ማይበቃቸው የሚቀያይሯቸውን ኮረዳዎች ለማደሰት ጊዜየቸውን የሚያጠፉ ናቸው፡፡ ለማስረጃም ያህል ሁለቱም በመንፈሳዊ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በሚኖሩበት ሰዓት፤ ለሳሚ የመጣቸው አባ ሀይሌ ጋር እየገባች ኮረዳ ሲጠላለለፉ መኖራቸው ከኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የተሰወረ ድራማ አልነበረም፡፡ የተወሰኑ ተማሪዎች ከሴቶቻቸው ጋር በነበራቸው መቀራረብ የሁለቱን አባ ተብዬዎች ጓዳ እና ምስጢር ሰምተዋል፡፡ በሀብታቸው ረገድም የአባ ሳሙኤልን ያህል ባይሆንም አባ ሀ/ማርያም በንግድ ባንክ ብቻ በ12 ሚሌየን የሚቆጠር ሂሰብ ያለበት ደብተር በስሙ ነበረ፡፡ በወጋጋን ባንክ ደግሞ የ6 ሚሌየን ብር ደብተር ሴቶቹ አይተዋል፡፡
  አባ ሳሙኤል ገና የአ/አ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ እያሉ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ያለቸው ሲሆን ለሴቶች የሚሰጡ በርካታ ወርቅና ጌጣጌጦች በሎከራቸው ታይተዋል፡፡ እነኚህ መንፈሳዊነት የራቃቸው መነኮሳት በዝሙት ምከንያት ወጪያቸው ከፍተኛ ስለሆነ ገንዘብ ፍለጋ እንዲህ ያለ ቅሌት ውስጥ መግባታቸው የሚደንቅ አይደለም፡፡
  አባ ሳሙኤል ጳጳስ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዷትና የሚያዋርዷት ሳያንስ፤ ለግልገሉ አባ ሀ/ማርያምም ጵጵስና ከተሰጠ ለቤተ ክርስቲያን ሞት ነው፡፡ ነገር ግን እንደመላው ምእመናን ፍላጎት ከሆነ አዲስ ጳጳሳት ከመሾማቸው በፊት አሁን የሉት ጳጳሳት እየተገመገሙ የልጆች አባት ፣ የሀብት ባለቤት የሆኑት ፣በዝሙት የተጠመዱት፣ በአጠቃላይም መንፈሳዊነት የተለያቸው ጳጳሳት ወደ ገዳም ተልከው በጸሎት ቢኖሩ አይ ካም ከሚወዱት አለም ቆባቸውን ጥለው ቢቀላቀሉ ይሻል ነበር፡፡

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች ምህረተ አባ የሚያሰተምረዉን የ ክህደት ትምህረት መልስ ሰጡበት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምልስ የሚሰጠው እውቀት ሲኖረ ነው ??????????????? የምህርት አብን መጀመርያ መልሱን ስማው ??? ከመናገር ማድመጥ ይቀድማል ስሙም ምህረት አብ ስብከት ነው ?? አስተውለው ማስተዋሉን ይስጥህ፣ አይነ ልቦናህን ያብራለህ፡፡

   Delete
 7. እናንተና ወያኔ አንድ ናችሁ ውሸት ከኪሳችሁ እያወጣችሁ የምትዘሩ የዘመኑ አውሬ /666/ ናችሁ

  ReplyDelete
 8. ወሬ ህይወት ቢሆን ስንት ወሬኞች ህይወት ባገኙ ነበር እናናተ ግን በወንጌል ስም የከፈታችሁትን ብሎግ ለአሉባልትና ተረት ተረት ከምታውሉት ምናለ ህይወት የሚሰጠውን ለሕግዚአብሔር ቃል ብታውሉት?? የሰውን ጉድፍ በማውጣት የከበረ የለም የራስን በማውጣት እንጂ ማንም ቢሆን ፍጹም የለም ስውን ፍጹም አደርጋችሁ አታስቡ ፍጹም አንድ እግዚአብሔር እንጂ ምንአልባት ፍጹምንን ብላቹ የምታስቡ ከሆነ እራሳችሁን መርምሩ ????????????????

  ReplyDelete
 9. ምህረተአብ ልክ ሚያሰገባዉ ጠፋ ማለት ነዉ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የተፈጠርክበት የማታውቅ በእግዚአብሔር ቃል የምትዘብት ዘባች ነህ። የተፈጠርከው ከአፈር መሆኑን እንደገና ዘፍጥረትን ገብተህ አንብብ።

   Delete
 10. ማነው? "ምህረተአብ" እድሜ ለአንጋፋውና ለታላቁ ሊቅ ለብፁዕ አቡነ ዘካርያስ! ስለ አሱ በአንድ መድረክ ላይ ተጠይቀው ሲያወሱ ማነው ያላችሁት ይሄ ዝመደ ብሎ የሚዘላብደው "መአተአብ" ብለው ሰይመውታል፣ እነሆ ስሙም ፍልፍሉ/መአተአብ ተብሎ ይስተካከል።

  ReplyDelete
 11. ኮሚዲ ምህረተ አብ በቤተ ክርስቲያኗ ፋነነባት
  አደብ አስገዙት

  ReplyDelete
 12. aba selama ,lisane zendo weseytan

  ReplyDelete
 13. To Anonymous December 29 this told to Hara blog YE mahbere seytan Afyehonew Yeharablog mechelen Timhrt setto yawkalu Lesidbnew yetekemet gin Hasabsetiteh atawkm ahun minancherecherh ahun abaselama Yeshewa gedil aytsifmengi wenjelma yisebekbeta werem mawrat sifelg Bemasreja new Tadewos a Mamuye Yingeruh

  ReplyDelete
 14. ስሙ ይስተካከል "መአተአብ" ነው!

  ReplyDelete
 15. MK LEWSHET MANBLOT WENJEL FETFTO YEMIYSTMREWN YE ABA SELAMA BLOG KEHARATEWAHIDO BLOG YEMILEW BET BIZU NEGER ALE
  AND HARA LEBETEKRSTIYAN BILO SAYHON LEPOLETIKAW BLO GLESEWOCHIN BEBHERACHEW SLEMITELACHEW YEFETERWE WERE EYEFEBEREKE YEMIYATELESH AND KEN GIN MASREGA YEMAYKERB ABASELAMA GIN BEBIZAT HIYWET YEHONEW WENGEL YISEBKAL ALFOALFO YEGLESEBOCH SIMSIYANESA ENKA BEMASREJA ASDEGFO BE MEHONU YENE TADEWOSN GUD BEAYNUEYAYE MAN YIKDAL KEKEHADIW MAK GENA ENAYALEN GENA

  ReplyDelete
  Replies
  1. Menfeskidus Afihin kefto fitihin tsefto anagereh....WENJEL new yalkew...kikiki

   Delete
 16. YOU ARE THE VOICE OF DEVEL

  ReplyDelete
 17. He is not Bishop but misleading person because he went to mislead Ethiopian Monastery in Jerusalem and this is evil shame

  ReplyDelete
 18. እንዲሁ ሳያችሁ፣ ጽሑፋችሁን ሳነብ በጣም ትገርሙኛላችሁ፡፡ እንዴት ሰው ለውሸትና ቤተክርስቲያኒታን ለመበታተንና ለመቀራመት ብሎግ ይከፍታል? እንዳንድ ጊዜ የናንተን ጩኸት የማኅበረ ቅዱሳንን ዝምታ ስመለከት ቀራንዮ ያስታውሰኛል፡፡ በማኅበሩ በበርካታ መርሐ ግብሮቹ ተገኝቻለሁ፡፡ ያሉትንም ሚዲያዎች እከታተላለሁ፡፡ ሆኖም ግን አንድም ቀን ስለእናንተ ተነስቶ አያውቅም፡፡ እናንተ ግን በማኅበሩ ዝምታ የተደሰታችሁ አትመስሉም፡፡ ተንጨረጨራችሁ እኮ! ተንጨርጭራችሁ በጥቂት ጊዜ የምትሞቱም ይመስለኛል፡፡ ከተሳሳትኩ ይቅርታ፡፡ በጣም ይቅርታ፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ ይህን ለናንተ ስጽፍ ለመጻፍ ጊዜዬን እያጠፋሁ መሆኔን ሳስብ ደግሞ ይቆጨኛል፡፡ ወይ ጉድ ዝምታ እንዲኽ የሚያንጨረጭር ከሆነ እውነቴን ነው የምላችሁ ልሳኔ እስከወዲያኛው ጥርቅም ይበል! እንደዚህ አትንጨርጨሩ እሺ! ደም ግፊት፣ ስኳር እና ሌሎች ተያያዥ በሽታዎች መምጫቸው በዚህ ነው ብለውኛል፡፡
  ይቺ ቤተክርስቲያን እንደሆነች የፈለገ በጀት ከውጪና ከውስጥ ቢመድብ መሠረቷ እንደአፍሪቃ መንግሥታት በነውጥ የምትፈርስ አሸዋ ላይ የተሰራች አይደለችም፡፡ ሰማያዊ ነች! ታሪኳን ለምን አታነቡም፡፡ የዲያብሎስ ዝናሩ ሲያልቅ በነበረበት እንኳን እንደማይገኝ ታውቃላችሁ፡፡ አምላካችን እኮነው ያነጻት! እንዴት ይኽ ጠፋችሁ! አሁን እየደረሰባችሁ ያለውን መንኮታኮት መቀበል ነው! አማራጭ የላችሁም፡፡
  ከፊት ለፊት የፀረ ተሐድሶ ጥምረትን በኩል የሚያሯሩጧችሁን ብቻ አትመልከቱ! በየቦታው የቤተክርስቲያን ልጆች አሉ! አይኗ፣ ጆሮዋእኮ ነን እንዴት ይህ ይጠፋችኋል፡፡ እባካችሁ በንሰሐ ተመለሱ! የኋላ ታሪክን ቀያሪ አምላክ አለ፡፡ እንዲህ በየቦታው መንጨርጨር ምንድን ነው! እውነቴን ነው የምላችሁ፡፡
  እግዚአብሔር በጎ ነገርን ያሳስበን!

  ReplyDelete