Friday, December 25, 2015

ማሙዬ በፎርጂድ ዲግሪ መቀጠሩ በመረጋገጡ ታሰረበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ የቆየውና ባልዋለበት ሙያ መጋቤ አእላፍ የሚል ማዕረግ የተሸከመው ማሙዬ እንደ ባልንጀራው ታዴዎስ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ቅሌት ሰሞኑን ለእስር መዳረጉ ተሰማ፡፡ ማሙዬ በሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ እንዳለው ተደርጎ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በነበራቸው የውስጥ ስምምነት የማቅን ተልእኮ ይፈጽማሉ ተብለው ከታሰቡትና በሀገረ ስብከቱ ቦታ ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ እስጢፋኖስ ሀገረ ስብከቱን ለማቅ ለማስረከብ ውስጥ ለውስጥ ሲሰሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ማሙዬ በደብረ ብርሃን ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬምን ከፖሊሶች ጋር ተመሳጥሮ በመኪና ሲሄዱ መሳሪያና የጥንቆላ መጽሐፍ ይዘዋል ብሎ ሊያሳስራቸው ሲሞክር ጉዳዩ ውሸት ስለሆነ ስራ አስኪያጅነቱ ተባርሮ የነበረ ቢሆንም የማቅ አባል ስለሆነና በመሰሪነቱ ለማቅ ስለሚጠቅም ግን አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀጠር መቻሉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

ከዚህ አልፎም የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ሆኖ በተሾመ ጊዜ ዛሬ ለምሳ እንመጣለን” እያለ ወደ አድባራት ስልክ በመደወል የአድባራቱን ካዝና በማራቆት ወደር ያልተገኘለት አጭበርባሪ ሆኖ ነበር፡፡ ጉቦ በመብላትና ብዙ የሰው ሀይል በመቀጠርም በየትኛውም ክፍለ ከተማ ሲታይ የማሙዬን ያህል የበዘበዘ ፈጽሞ አልተገኘም፡፡ በኋላም እንዳይነቃበት ከሥራ አስኪያጅነት ወደ ሀ/ስብከት በመሄድ ጠቅላላ አገልግሎት ሆኖ በመመደብ የቀሲስ በላይ ጉቦ አቀባይ በመሆን ስንቱን ሊቃውንት በመስደድና ዘረኝነትን በማስፋፋት አቻ አልተገኘለትም፡፡ ይህን ሁሉ ግፍና በደል ሲያደርስ የቆየው በተሳሳተ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥሮ መሆኑ ስለተረጋገጠ አሁን ለእስር ተዳርጓል፡፡ ማሙዬ ሳይገባው “መጋቤ አእላፍ” የሚል ማእረግ ተሸክሞ የቆየ ቢሆንም በዚህ ማእረግ ክፋትን ከማራመድ በቀር ምንም አልሰራበትም፡፡ እንዳይሰራበትም የቤተ ክርቲያን ትምህርት የለውም አይቀድስ አይወድስ፡፡ በዘመናዊውም ቢሆን ፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ እንጂ ያልተማረ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህ ሳያንስ ለማቅ ብሎግ ለሐራ የሌሎችን ስም ሲያጠፋ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ከሁሉ የሚገርመው ለቤተክርስቲያን አስባለሁ ከእኔ በላይ ተቆርቋሪ የለም ባዩ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክህነት ውስጥ የመለመላቸውና እየተጠቀመባቸው ያሉ ሰዎች በአብዛኛው እንደማሙዬ ያሉ መሃይምናንና የስነምግባር ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው ነው፡፡ ማቅ እነዚህን ሰዎች የሚጠቀመው ለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሳይሆን የራሱን ጥቅም በማስቀደም ነው፡፡ ለሊቃውንቱ ያለውንም ንቀት ለማሳየት ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን ቢያስብ ኖሮ እንዲህ ባለ ችግር ውስጥ ያሉትን ከዚህ ችግር ነጻ እንዲወጡ መርዳትና ሕይወታቸው እንዲስተካከል ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ማቅ ግን ዓላማው የራሱን አጀንዳ ማስፈጸም ስለሆነ ሊጠቀምባቸው የሚፈልጋቸው ሰዎች በሥነ ምግባር ችግር ውስጥ ያሉትን መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ ነው፡፡ የዚህ ጥቅሙ ግለሰቦቹ የማቅ አጀንዳ አስፈጻሚ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ከማቅ ጋር አንሰራም ቢሉ ማቅ ይዤባቸዋለሁ የሚለውን የስነምግባር ችግር ወይም ነውር ይፋ አወጣዋለሁ ብሎ በማስፈራራት ይጠቀምበታል፡፡ ለቤተክርስቲያን ያለውን ንቀትም እያሳየበት ነው፡፡ ሊቃውንቱን ለመምራት እየሞከረ ያለው እንደማሙዬ ባሉ መሃይምናን ነውና፡፡
ማቅ ለእርሱ ጠንቅ የሆኑትን ሰዎች ፈጥሮም ቢሆን ስም ለማጥፋት ማንም የማይቀድመውን ያህል የማሙዬንም ሆነ የሌሎቹን ወዳጆቹን ጥፋትና የስነምግባር ችግር እንዳላየ ነው የሚያልፈው፡፡ በዚህም ለቤተክርስቲያን እንዳልቆመ በተግባር እየመሰከረ ነው፡፡
   

17 comments:

 1. Behilmachihum bewunachihum yemitkazut sile Mahibere kidusan new aydel? kentuwoch nachihu.

  ReplyDelete
 2. ABET KLET ! ABET KLET ! BTROTA MEWCHA GIZEW FORGED DEGREE MIN LEMEHON FELGO NEW ENKLF TABEZI KENEBR GAR TFAZEZI ALU MENFKNETU YE.ENESU LEBNETU ENA FORGED YENESU AFKEFTEWNA ABZTEW FITACHEWN BE CHEW ATBEW LEWERE YEMAYKEDEMUT ENESU LEMANGNAW KIRSTIYAN YESEW KIFLU AYWEDMNA LEABA MATEWOSNA YEMAHBERE KIDISAN ALKLAKIWOCH EGZIABHERN TSINU TUN YISTACHIHU ABATACHIHU MENAFKU HAYLEGIYORGISM WENDMOCHIHIN ADERA ALEMAMDACHEW LEMALET NEW

  ReplyDelete
 3. አባ ሰላማዎች፣ ይህ ችግር እንደሀገርም ሊታሰብበት የሚገባ ችግር ይመስለኛል፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ ሰሞኑን ያነበብሁት የግጥም መጽሐፍ የሚያወሳው ይህንኑ ነው፡፡ አካል እና ጥላ በሚል ከደብረ ማርቆስ የተጻፈ መጽሐፍ አግንቼ ሳነበው የሚገርም ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይህንን ያነሳችሁትን ጉዳይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው-እንደሀገር፡፡ ብትችሉ ብታነቡትና የበለጠ ብትጽፉበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ምን ዓይነት በሽታ ነው የገባብን ባካችሁ! የቀድሞ አባቶቻችን ሙያው እና ሥነ ምግባሩ እያላቸው ሹመትን ይሸሹ ነበር፤ አሁን ደግሞ ሙያውም ምግባሩም ሳይኖር ለሹመት፡፡ ውይ! እስኪ ልብ ይስጠን፣ ጎበዝ!

  ReplyDelete
 4. ማሙዬ የሰራኽው በደል ገና አልተወራረደም በተለይ ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ላይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ሊቀ ጠበብት" ኤልያስ ላይ? ደግሞ እሱ ላይ በደል ቢፈፀም ማነው የሚቆረቆረው እውነተኛ ፈራጅ እግዚአብሔር አይደለም የኤልያስ ወዳጅ ሰይጣን እንኳን በሉት ነው የሚለው እሱ የሰራው ሥራ እንኳን እሱ ወደፊት እስከ 7 ትውልድ ተከፍሎ የሚያልቅ እንኳን አይደለም።

   Delete
 5. Ye-mahbere seytan gud malekiya yelewum good job AbaSelama

  ReplyDelete
 6. አብዛኛኛ ው የቤተ ክርስቲያን ሀላፊዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣የቢሮ ሰራተኞች ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የገቡት እና በቀንም ሆነ በማታ ትምህታቸውን አጠናቀዋል ተብለው የተመረቁት እኮ የ12 ኛ ክፍል ሰርተፊኬታቸው በፎርጂድ የተሰራ ነው፡፡ ከሁሉም የሚገርመው በፎርጂድ ሰርተፊኬት ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተመዝግበው በዲግሪ ተመርቀው ለማስትሬት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ነው፡፡
  አሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቅድስት ሥላሴ የመጡ እና በማስትሬት ፊሎሎጀ ወይንም በሌላ ትምህርት የሚማሩና ተምረው ፒኤችዲ ላይ ያሉትን በሙሉ ማጣራት ቢጀምር በእርግጠኝነት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 12ኛ ክፍል በፎርጂድ የገቡ ናቸው፡፡
  ይሄ አዲስ ነገር አይደለም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሞሉት አብዛኞቹ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ ከጳጳሳቱ ጀምሮ ፤ሲሾሙ በመንፈሳዊነታቸውና በእውቀታቸው ሳይሆን ፓትርያርክ ጳውሎስን በመደለል ጉቦ በመስጠት ወዘተ… ጳጳስ ሆነዋል አሁን ጀርባቸው ሲታይ የልጅ አባቶች፣ባለቪላቤቶች፣ዘመናዊ መኪናዎች ባለቤቶች፣ እቁባቶቻቸው ብዙ ፣የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ፣እረ ስንቱ … ታዲያ እናንተን እያየ ማን ጤነኛ ይሆናል ፤፤ ብቻ እግዚአብሄር ፍርድ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 7. የሰአሊተ ማርያሙ እለቃ አቡ (ሩፋኤል) ደፋሩ ቅ.ሥላሴ የተማረው በፎርጅድ ነው እኔ በተጨባጭ አውቃለው ካስፈለገ መልቀቅ ይቻላል

  ReplyDelete
 8. እስመ ዘእኩይ ምግባሩ

  ReplyDelete
 9. ENE HAILU GUTETA TADWESNA DAWIT EYETEKATELACHIHU ENDEBEKOLO TIFEGALACHIU GIN EYARERACHIHU NEW KESEW SIHTET AYTEFAMNA LIKETEBEBTM TERA SIHTETET LINORACHEW YICHILALA GIN KENANTE GAR BEMINIM AYDEMERM MIKNYATUM ESU YEWEYRA ENCHET NEW ENANT BEKOSHAHA WIHHA YADEGACHIHU KETEMA OCH NACHIHU ESUN AMAKRACHIHU NEBERE ENDE FORGED YASEMACHIHU YESYTAN GILGRLOCH NACHHU ENANTE EKO SEW KENAKACHIHU KOYE YELELACHIHU YALACHIHIHU KEMENFESAWIM HONE KEZEMENAWI EWKKET YETELEYACHU BADOWOCH MAFERYA OCH DEMS DEGMO YE MEMHIR LIJMAGBAT MEMHIR AYADRGIM EMBIKALK YESERAHAWNIN ASTAWS TEW TEW

  ReplyDelete
 10. selesew sitaweru rasachihun mefetesha gize yatachihu esti kenante yalbedele yemjemryawin dingay yiwerwir

  ReplyDelete
 11. silesew sitaweru yeneseha gize atachihu silsew yawera weys hatyatun yetenazeze yemedinew silehaymanot bilachihu behon besemanachihu gin haymanot mech alachihu?

  ReplyDelete
 12. menafikan yediyabilos lijoch besiol keziyam begehanem esikemitiwereweru dires tenikejekejalachihu ai ye satan lijoch kekidist ager ke Ethiopia yatifachihu

  ReplyDelete
 13. MAK YEINE TADEWOS ENA MAMUYE SHEWA AFERA KILETNA ESRAT LEMSMAT GERO ANSOTNEW FORJIDU AKENABRO MENGED ENDITERGULET YELAKACHEW BE MEHONU AFRO NEW YEMIGERMEW HER A BETEBALE YESIDB BLOGU YALEMASEREJJA NTSIHOCHIN BEBHERACHEW AMAKAYNET SILETELACHEWNA DERGAWI ZARU SINESABET YEMISADEBUW BFORJED KLET YETASERUTNA YETEWAREDUTIN LEMESADEB AKM ATA DRONES TOLELE LAY YTEMESERETE TOLTAL MAHBERE LEBETEKRSTIYAN AASBO ASBO AYAWEKM LEGERU YEMAHBER KIDUSAN SEWOCH BADEBABAY HETIYAT YEMISERUT DEBERELIBANOS TEKEBERN ENETSEDKALEN BLOW SILEMIYAMNU NEW YEMITSEDKEW GIN (BEHASET YEMAYMESEKR BICHA NEW
  M=MAFIA
  H=HIGE ALBA MEDEDE
  B=BEKT RESSA
  R=REWADI ZERAFIWOCHIN
  K=KENT UWCH
  D=DOGMA AFRESH
  S=SEYTAN YELAKACHEW
  N=NISIHA YELELACHE SEDUKAWYAN NBLAE WENSTEY NEGDEW GIBR YEMAYKEFLU BETEKRSTIYAN LAY YETETEGU MEZGEROCH NACHEW MAKOCH ANDKEN AWNET MENAGAR BATCHLUM YETENEKABACHIHU POLETIKEGNOCH MOHONACHIH YE HAYMANOTE SHITAW YELELACHIHU YEBETEKIRSTIYAN METSAHFT EYASATEMACHU YEMTISHEYU YEGEBA BET YENGD BET YADERGACHIHU COPY RIGHT YALAKEBERACHIHU CIDINA ETAN TAF KITAB NEGADE OCH NACHIHU

  ReplyDelete
 14. Lets pray for these people working in this blog : our father God bring them out of this evil, take out of their sins of judging on others, cleanse their mind for truly blessing you, respect all EOTC members who believe in your son JESUS CHRIST, make their heart to incline for truth in the church, unite for one idea of salvation for which the church is running, respect church fathers, decline from insulting MK members for the MK respect and believe in your son Jesus..... Oh God please help people of this blog to serve you living in Harmony with the church!

  ReplyDelete