Tuesday, December 20, 2016

የድርሳነ ሚካኤልና የድርሳነ ገብርኤል የታሪክ ሽሚያና መዘዙ

Read in PDF

“በደቡብ ሀገር መኖር መልካም ነበረ። ግን የደቡብ ሀገር ሰዎች ከእውነተኞቹ ሐሰተኞቹ ይበዛሉ።” እንዲህ ሲሉ የጻፉት ለአማርኛ ስነ ጽሑፍ መሠረት ተጥሏል ተብሎ በሚታመንበት ከ1900-1928 ዓ.ም ድረስ ባለው ዘመን  ተነሠተው  “የአማርኛን ስነ ጽሑፍ መሠረት ከጣሉና ካጠበቁ ደራስያን መሃል እውቁ የፖለቲካ ሰውና ዲፕሎማት ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ ናቸው፡፡” ከላይ የተጠቀሰው አረፍተ ነገር የሚገኘው ወዳጄ ልቤ በተሰኘው አሊጎሪያዊ ልቦለድ መጽሐፋቸው ውስጥ ገጽ 46 ላይ ነው። በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ “መሪ” ባሉት መግለጫ ውስጥ “ደቡብ ሲል አዋልድ መጻሕፍት ማለቱ ነው” የሚል ጠቋሚ አስቀምጠዋልና፥ ከአዋልድ መጻሕፍት መካከል ከእውነተኞቹ ይልቅ ሐሰተኞቹ ይበዛሉ የሚል ትዝብታቸውን የገሃዱ እውነታ ነጸብራቅ በሆነው ወዳጄ ልቤ መጽሐፍ ውስጥ አዋልድ መጻሕፍት በአብዛኛው ዋሾዎች መሆናቸውን መስክረዋል።
ሌሎች ግን ስለ አዋልድ መጻሕፍት ምስክርነት ሲሰጡ አዋልድ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩና ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጡ ወይም የተወለዱ ናቸው ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ አዋልድ መጻሕፍት በተለይም ድርሳናትና ገድላት ይዘዋል ከሚባለው እውነት ይልቅ እንደ ተባለው ውሸታቸው ይበዛል። አዋልድ መጻሕፍት በአብዛኛው በልቦለድ ታሪክና በተጋነኑ ገለጻዎች የተሞሉ ናቸው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚቃረኑ ብዙ የስሕተት ትምህርቶችንም በውስጣቸው ይዘዋል። አንዳንድ ጊዜም አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሠፈረ ታሪክ በመሻማት እርስ በእርሳቸው ይጣላሉ፡፡ በዚህ ጽሑፍ በድርሳነ ሚካኤልና በድርሳነ ገብርኤል መካከል ስላለው ውዝግብና የታሪክ ሽሚያ በታኅሳስ ድርሳን ላይ የተገለጸውን እንመልከት፡፡ 

Tuesday, December 13, 2016

ቤተ ክርስቲያንስ በጥልቀት መታደስ የለባትምን?ተሐድሶ የተሰኘው የግእዝ ቃል የቤተ ክርስቲያን ቃል ነው፡፡ ወይም ቤተ ክርስቲያን ስትጠቀምበት የነበረ ቃል ነው፡፡ “የነበረ” የተባለው ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ቃሉን እንዳትጠቀምበት ስለ ተደረገና ቤተ ክርስቲያን የጣለችውን ወንጌል ማንሳትና ወንጌልን መስበክ ስሕተቶቿንም ማረም አለባት ብለው ለተነሱ ልጆቿ ክፉ ስም አድርጋ በመስጠት በአሉታዊ መንገድ እየተጠቀመችበት ስለሆነ ነው፡፡ ተሐድሶ አሉታዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ፀረ ወንጌል ቡድኖች ላለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመዋል፡፡

በእነርሱ ተሐድሶ የተባሉትም ወገኖች ሳይታክቱ የተሐድሶን ትክክለኛ ምንነት ለማስረዳት ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዚህም ነው ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ የሚለውን ስም አዎንታዊነት ወደ መግለጽ የመጣው፡፡ በሐመረ ተዋሕዶ የጥር 2008 እትም ገጽ 120 ላይ ተሐድሶ ስለሚለው ቃል እንዲህ ብሏል “ስለ ተሐድሶ የቃል በቃል ትርጉም ነጋሪ አንፈልግም፡፡ ዕድሜ ለአባቶቻችን ዛሬ እናንተ የምታደናግሩበትን ግእዝ አምልተውና አስፍተው ጽፈውልን አልፈዋልና፡፡ ቃሉ አዎንታዊ ትርጉም እንዳለውም አላጣነውም፡፡ ስማችሁ “ተሐድሶ” ይባል አይባልም ለእኛ ጉዳያችን አይደለም፡፡ በእርግጥ ቃሉ ጤነኛ ቃል ስለሆነ ለእናንተ ግብር የሚስማማ አይደለም፡፡”

Sunday, November 13, 2016

በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ

1ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1
 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ፤ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው ይለናል ይህ ትዕዛዝ ሳሙኤል ለሳኦል እያለቀሰለት ያለ ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? ያለበት ጉዳይ ነው በመሆኑም ይህንን ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር ቢያስፈልግ ለሳሙኤል እጅግ ከባድ ነው እንደገናም ሳኦል ለእግዚአብሔር ሰገድኩ እያለ ነው ሳሙኤል ደግሞ ምንም እንኳ ሳኦልን አግኝቶ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ በማለት የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያስተላለፈለት ፣ ሳኦልንም እስከሞተበት ቀን ድረስ ዳግመኛ ለማየት ያልሄደበት ጉዳይ ቢሆንም የሳኦል ነገር ግን ከሳሙኤል ጨርሶ ያልቆረጠለትና ከልቡም ያልወጣለት ሰው በመሆኑ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተቀብሎና በቀንዱም ዘይቱን ሞልቶ ቅባልኝ ወደተባለው ሰው መሄድ ለሳሙኤል የሞት ያህል አዳጋች ነበር 
ለዚሁ ለእግዚአብሔር ትዕዛዝም ይሄው ሳሙኤል ምላሽ በመስጠት ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል ማለቱ አሁንም የሳኦል ነገር በሳሙኤል ሕይወት ውስጥ የሚያስከትለውን የስጋት ሃይልና የክብደት መጠን በጉልህ የሚያሳይ ነው ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ እያለ በመለማመጥ የልብስን ጫፍ ይዞ የሚቀድን ሰው ፣ አልፎም ሄዶ ለእግዚአብሔር ሰገደ የተባለን ሰውና የተለቀሰለትን ሰው ትቶ የተዘጋጀውን አዲስ ንጉሥ ለመቀባት በቀንድ ዘይትን ሞልቶ መሄድ ለሳሙኤል አሁንም ፍጹም የማይታሰብና ድንገተኛም ዱብዳ ነው ታድያ በዚህ ጉዳይ ላይ ሳሙኤል እንዲህ ከሚጨነቅ ይልቅ ይህንን ሁኔታ እግዚአብሔር ባየበት ዓይን ለማየት ዓይኑን ቢከፍት እንዲህ ባልተቸገረ ነበር ታድያ ይህንን በሳኦልና በሳሙኤል ዘመን የነበረን አጀንዳ ወደ እኛም ዘመን ስናመጣው ዛሬም በዘመናችን አቅም አግኝተው ንስሐን በሚመስሉ የማግባብያና የለበጣ ቃሎች ተውጠንጥነውና እና ተቀምመው እንደ ሳኦል ዘመን የቀጠሉ የሚመስሉ አምልኮዎች ፣ አገልግሎቶች ፣ የክህነት ሥራዎች እና ክህነቶችም ጭምር በእግዚአብሔር ዘንድ ያበቃላቸው ሆነው የተናቁና የተነወሩ ተቀባይነትም የሌላቸው ናቸው 

Wednesday, October 26, 2016

የአትላንታ የኖርዝ ካሎራይና እና የቴነሲ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ከአገልግሎት ተባረሩ። በአትላንታ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ረጅም ጊዜ አገልግለዋል። በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቀው በናዝሬት ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ ሆነው በርካታ መንፈሳዊ ሥራ የሰሩ አባት ናቸው። በባሕርያቸው እጅግ የዋህና ትሑት ክፋት የሌለባቸው ሲሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ከቅንነት ጋር ተጨምሮ መንፈሳዊ ውበት የሚታይባቸው መልካም ምሳሌ የሚሆኑ አባት ናቸው። ዓይናቸው ያልተገለጠ እና ሃይማኖትን በጥቅም በዘረኝነት በፖለቲካ ብቻ የሚተረጉሙ ጥቂት የቦርድ (በአሜሪካ ካህናት አጠራር የደርግ) አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል።
   በነዚህ የቦርድ አባላትና በማሕበረ ቅዱሳን ሴራ አባ ኃይለ ሚካኤል የሚባሉ ትቢተኛ መነኩሴ ከኢትዮጵያ ሄደው እንዲቀጠሩ ሆኖ ከአቡነ ያዕቆብና ሌሎች አገልጋዮች ጋር ጦርነት እንዲያደርጉ ተደርጎ ነበር። ፍየል ከመድረሷ ጎመን መቀንጠሷ እንዲሉ ይህ ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክስ አይመስልም እያሉ ወሬ መንዛት ጀመሩ። ከዚያም ግሪኮች እና ግብፆች በሚጠቀሙበት በሥርዓት በተዘጋጀ ወይን ይሰጥ የነበረውን የጌታ ደም ይህ ምንፍቅና ነው በማለት ወደ ወይን ጭማቂ እንዲመለስ አደረጉ። ንጹሑን ወንጌል ዘወር አድርገው በተረት የተሞሉ ገድላትን እና ልብ ወለድ ድርሳናትን መስበክ ጀመሩ። መነኩሴው ዜማ አዋቂና ብሉይ ኪዳን የተማሩ ናቸው ነገር ግን እውነት ከውሸት ጋር ተቀላቅሎባቸው ጠላና አረቄ ደባልቆ እንደጠጣ ሰው ነው ስብከታቸው። 

Friday, October 14, 2016

መጋቤ ሀዲስ እሸቱ እገዳ ተጣለባቸው።በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት እና በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ እየሰበኩ የሚገኙት  መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ባልተፈቀደላቸው ቦታ በመገኘት በሚል ሰበብ በሀገር ውስጥ ሲኖዶስ ስር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዳያገለግሉ እገዳ ተጣለባቸው።
እገዳው የተጣለው በብጹዕ አቡነ ዘካርያስ ፊርማ መሆኑም ታውቋል።

ደብዳቤውን ይመልከቱ

Thursday, September 29, 2016

ቤተ ክርስቲያን የማን ወኪል ናት?ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት አምባሳደር እንደ መሆኗ በዚህ ምድር ላይ ሳለች የምትወክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለችው የምትታየዋ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳን በዚህ ዓለም ጉዳይ ውስጥ በተለይም በፖለቲካ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ ባትሆንም ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ተከትሎ በአገር ላይ በሚፈጠሩ ችግሮች የማስታረቅና ሰላምን የመስበክ የማይተካ ሚና አላት፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን በመንግሥትና በሕዝብ መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶች ለመፍታት በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚናዋን መወጣት ተስኗት ታይታለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ በፓትርያርኩ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኩል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠችው መግለጫ ሲፈተሽ በተፈጠረው ችግር ተዋናይ የሆኑትን ሁሉ ሳይሆን አንድን ወገን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ ብቻ መሆኑ ሚዛናዊነት የሚጎድለውና ለመንግስት የወገነ ገጽታ ያለው ሆኖ አልፏል፡፡ ነሐሴ 3/2008 ዓ.ም. የወጣው መግለጫ በውስጡ የቤተ ክርስቲያኗን ሚና በተመለከተ “በአገር ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር አንዱን ከአንዱ ሳትለይና ሌላውን ሳታገል ሁሉንም በእኩልነትና በልጅነት መንፈስ በማየት ስትመክር ስታስተምርና ስታስማማ የነበረች አሁንም ያለች ለወደፊትም የምትኖር የቁርጥ ቀን እናት ቤተ ክርስቲያን ናት” ቢልም እዚያው ላይ ግን የሕዝብን ወገን እንጂ የግጭቱ አካል የሆነውን መንግስትን የሚገሥጽም ሆነ የሚመክር ቃል አልተጠቀሰበትም፡፡ ይህም ከላይ የተጠቀሰውንና ስለ ራሷ የሰጠችውን የራሷን ምስክርነት የሚቃረን ሐሳብ መስጠቷ ትዝብት ላይ እንድትወድቅ ከማድረጉም በላይ በተግባር የወገነችው ወደማን እንደሆነ አመላክቷል፡፡ በመግለጫው ውስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል ሁለቱን እንመልከት፡፡

Monday, September 26, 2016

የሚያድነው መስቀል የቱ ነው?


Read in PDF

የእግዚአብሔር የእግሮቹ መቆሚያ ስፍራ
“ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን” (መዝ. 131/132፥7)
ክርስቶስ ስለ ተሰቀለበት መስቀል በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት የሚከታተል ሁሉ ይህ ቃል ለመስቀል ስለ መስገድ እንደሚጠቀስ ያውቃል፡፡ መስቀል ሦስት ፍቺ አለው፡፡
   የመጀመሪያው፥ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ የተሰቀለበት የተመሳቀለ ዕንጨት ሲኾን (ዮሐ. 19፥17፤ 1ጴጥ. 2፥24)
   ሁለተኛው ደግሞ፥ በዚህ የተመሳቀለ ዕንጨት ላይ ክርስቶስ የተቀበለው መከራና ሞት፥ በጥቅሉ የቤዛነቱ ሥራ ሁሉ መስቀል ይባላል (ኤፌ. 2፥16፤ ቆላ. 2፥14)፡፡
   ምእመናን ስለ ክርስቶስና ስለ ወንጌል የሚቀበሉት መከራም መስቀል ተብሎ ይጠራል (ማቴ. 10፥38፤ 16፥24፤ ማር. 8፥34፤ ሉቃ. 9፥26፤ 10፥21፤ 14፥27)፡፡
ዓለም ሁሉ በእምነት የሚድንበትና የሚመካበት መስቀል በሁለተኛው ፍቺ ውስጥ ነው የሚገኝው፡፡ በተለይ በአዲስ ኪዳን ክፍል ውስጥ ስለ መስቀል የተነገሩት ሁሉ የክርስቶስን ቤዛነት የሚያመለክቱ ናቸው (1ቆሮ. 1፥18፤ ገላ. 6፥14፤ ፊል. 3፥18)፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በቆሙ በብዙዎች ዘንድ ግን እነዚህ የተጠቀሱትና የቀሩት ሁሉ “መስቀል” የሚል ቃል ይዘው ስለ ተገኙ ብቻ፥ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀል ተሰጥተው ነው የሚተረጎሙት፡፡ ስለዚህ የብዙ ምእመናን ዐይኖች የመስቀልን ቅርጽ እንጂ የተሰቀለውን ክርስቶስን ለማየት አልታደሉም (ገላ. 3፥1)፡፡ እዚህ ላይ አንድ ወንድም ነገሮችን ሁሉ አስተውሎ በአንድ ወቅት፣ “ቤተ ክርስቲያናችን እየሰበከች ያለችው በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ነው” አለ፡፡

Monday, September 5, 2016

የኢትዮጲያ “መካከለኞች” ወዴት ናቸው?ምንጭ፦ http://abenezerteklu.blogspot.com
ቺቸሮ “አለመግባባት መፍትሄ የሚያገኘው በሁለት መንገዶች በውይይት ወይም በኃይል ነው፡፡ የመጀመርያው የሰው ባሕርይ ሲሆን ሁለተኛው የአራዊት ነው” ይላል፡፡ ባለመታደል ሁላችንም ሁለተኛውን መረጥን፡፡ ማሸነፍ እንጂ መሸነፍን ያለመቀበል እንደባህል አድርገን በመያዛችንና በሃገሪቱ የፖለቲካ ልምድ ካለመኖር ጋር ተዳምሮ የኢትዮጲያ ተራማጆች ኃይልን መርጠው በመንቀሳቀሳቸው የደም መፋሰሱንና የጥፋቱን መጠን በማባባስ ለሃገር ግንባታ ይውል የነበረ ወጣት ለቅስፈት ተዳርጓል፡፡ (ሌ/ኰሎኔል ፍሥሐ ደስታ፤ አብዮቱና ትዝታዬ ፤ 2008 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት)
       ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም “እርምጃ እንዲወሰድ ከማዘዛቸው” በፊትም ሆነ በኋላ፥ የሕዝብ ኩርፊያ አሁንም ጋብ ያለ አይመስልም፡፡ ሕዝብ እንደሚናጠቅ የአንበሳ ደቦል “በገዛ ወገኑ” [እርስ በራሱ] ላይ ያደባ ይመስላል፤ “መንግሥት ሆይ!  ችግር አለብህ፤ ተስተካከል” ለማለት እየሄደበት ያለው አቅጣጫና አንዳንዶች እንደሚሉት ሕዝቡን የሚመራው “ሦስተኛው አካል” ዓላማና ግቡ ምንም እንደሆነ በትክክል አለመታወቁ ነገሮች የበለጠ እንዲወሳሰቡ ያደረገ ይመስላል፡፡
     እርግጥ ነው፥ የአብዛኛው ሰው ስሜት ሲደመጥ፥ “ይኼ መንግሥት በቃው፤ ይውረድ” ይመስላል፡፡  ይህ አካሄዱ ግን ፍጹም ኢ መንፈሳዊነት ብቻ ሳይሆን ኢ ሰብዓዊነት፣ ኢ ሥነ ምግባራዊነትና ኢ ሞራላዊነት የሰፈነበት መሆኑ ነገሩን አስጨናቂና እጅግ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ምንድር ነው አስጨናቂና አሳሳቢ የሚያደርገው ብንል፦
    1.     ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ምን ሆነው? በማን ላይ ነው እርምጃ እንዲወሰድ አዝዣለሁ ያሉት? ከእርምጃው በፊት ማወያየትና ማነጋገር አይቀድምም ወይ? ምክር አይፈለግም ወይ? እርምጃ የመጀመርያ ደረጃ መቀራረቢያና መግባቢያ መንገድ ነው ወይ? ሕዝብን ማድመጥና ፍላጐቱን መጠየቅ አይገባም ወይ? በደፈናው ከመፈረጅ ጥንተ ምክንያቱን ማጥናት፤ መረዳት አይገባም ወይ? ወይም ለምንድነዉ መንግስት በፖለቲካ አቅጠጫ ማሸነፍ የተሳነው? የሚሉና ሌሎች ብዙ ጥያቄዎችን መምዘዝ ይቻላል፡፡

Sunday, September 4, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ


Read in PDF
ከአሸናፊ በላይ
የመጨረሻ ክፍል
ከኑፋቄ ሁሉ የከፋ ኑፋቄ
ለጥምቀት (2007 ዓ.ም) የታተመውና በነፃ የተሠራጨው «በእርሱ አምሳል እንወለድ ዘንድ ስለ እኛ ተጠመቀ»የሚለው መጽሔት እጅግ አደገኛ ኑፋቄ ይዞ ወጥቶአል፡፡
«እመቤታችን ጥንቱን ሰው ሊፈጠር ንጽሕት ዘር ሆና ተወልዳለች፡፡ ጥንተ አብሶ የለባትም የልጇም ንጽሐ ባሕርይነት ከምንጩ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ፍጹም ንጽሕና የተነሣ ነው» ገጽ 36፡፡ ቀደም ብሎ በሁለት የሐመር መጽሔቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናና ቅድስና በአፅንኦት የተነገረን ለዚህ ለተሳሳተ ትምህርት መሠረት ይሆን ዘንድ እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እግዚአብሔር ወልድ (በጽሑፉ ልጃE የተበሰረው) በራሱ ንጽሐ ባሕርይ የሌለውና የባሕርይውን ንጽሕና ያገኘው ሰብአዊ ፍጡር ከሆነችው ከእናቱ ከድንግል ማርያም አይደለም፡፡ የባሕርይ ንጽሕናውን ከሰብአዊ ፍጡር አገኘ ማለት የወልድን የባሕርይ አምላክነት የሚያስክድ አጋንንታዊ ትምህርት ነው፡፡
ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይው እውነተኛ አምላክ በመሆኑ ቅዱስ ነው፡፡ የባሕርይ ንጽሕናውን ከሌላ ሰብአዊ ፍጡር የሚቀበል ፍጡር አይደለም፡፡ «እኔና አብ አንድ ነን» ብሎ የተናገረ ጌታ ከፍጡር ንጽሕናውን የሚበደር አምላክ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቅዳሴም አንዱ አብ ቅዱስ ነው÷ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው÷ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እየተባለ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ይመሰገናል፡፡» እርሱ ሕጸጹን የሚያሟላ ረዳት አያሻውም (ጎርጎርዮስ (አባ) የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ ገጽ 98)፡፡
በጣም የሚገርመው ይህ አጋንንታዊ ትምህርት  የያዘው መጽሔት በቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን አዘጋጅ መዘጋጀቱ÷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋም በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት መታተሙ÷ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታከብረው የጥምቀት በዓል ላይ በነፃ መታደሉ ነው፡፡ የበለጠ የሚያስገርመው ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤው በቸልታ ጉዳዩን ማየታቸው ነው፡፡ የኑፋቄው ጸሐፊ ብቻ ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን አለቆችም በልዑል እግዚአብሔር ፊት ይጠየቁበታል፤ በታሪክም ይወቀሱበታል፡፡ 

Sunday, August 28, 2016

ነጻነትነጻነት የሰው ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሰው ተፈጥሮውም ነው። ነጻነት ስለፈለግን አይደለም ስለ ነጻነት የምንጮኸው ነጻ ሆነን ስለተፈጠርን ነው። ያለተፈጥሯችን እንድንሆን የሚፈልጉ ሁሉ ተፈጥሮን ለማበላሸት የሚደክሙ ናቸው። እግዚአብሔር በነጻነት ውስጥ ያስቀመጠው ታላቅ ምሥጢር አለ ይህ የእግዚአብሔር ጥበብ እጅግ በጣም አስደናቂ ነው። ማነኛውም የሰው ልጅ እውቀትና ችሎታ በሥራ ላይ ውለው ለሰው ጥቅም የሚሰጡት በዚህ በነጻነት ምሥጢር ነው።
ነጻነት በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠ የሰው ማንነት ነው። ሰው ነጻ ፍጡር መሆኑን የሚያንጸባርቀው ገና ሲወለድ ጀምሮ ነው። ሕጻናት አቅም ካላነሳቸው በቀር ዝም ብለው መቀመጥ አይችሉም መሮጥ መጫወት ይፈልጋሉ እናት እና አባት እነርሱን ለመቆጣጠር ሲሞክሩ ተቃውሞአቸውን በለቅሶ ይገልጣሉ። ይህ ሁኔታ የነጻነት ፍላጎት በትምህርት ወይም በአካባቢ ሁኔታ የሚገኝ ሳይሆን በተፈጥሮ በውስጣችን ያለ የእግዚአብሔር ምሥጢር መሆኑን የሚያመለክት ነው። ነጻነትን በአግባቡ ማስተዳደር እንጂ መገደብ አደጋ አለው። ለመርከስም ሆነ ለመቀደስ ነጻነት አለን። ምርጫው የራሳችን ነው። እግዚአብሔር በጉልበት አይቀድሰንም። በኃይልና በግዴታ ቅድስና የለም። እግዚአብሔርን በመምረጥና ለቃሉ በመታዘዝ እንጂ። ይህን ሐሳብ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እናገኘዋለን።

Thursday, August 25, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ
ከአሸናፊ በላይ

ኑፋቄ ሁለት ፡- ማኅበሩ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ መንገዶች የክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ እየሠራበት እንደሆነ ወደፊት በዝርዝር ማስረዳት የሚቻል ቢሆንም ለዛሬው ጥቂት ሐሳቦችን ብቻ መጠቆም የማኅበሩን ምንነት የበለጠ ለመረዳት ይጠቅማል፡፡ ቀጥሎ የተጠቀሱት ጥቂት ነጥቦች ማኅበሩ የኢየሱስ ክርስቶስ ተቃዋሚ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡

«ኢየሱስ» የሚለውን ስም አጥብቆ መቃወሙ
ማኅበሩ በግልፅ ይህንን ስም መቃወሙን ባይናገርም የጌታን አዳኝነት የሚያሳየውን «ኢየሱስ» የሚለውን ስም የሚጠሩትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች «መናፍቃን ናቸው» ብሎ በክፉ ስማቸውን በማጥፋት እንዲሳደዱ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳ እንዳሰበው ባይሳካለትም የጌታ ስም እንዳይጠራ ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርጓል፡፡ አንዳንድ ዘማርያን
«ማልደራደርበት ማልቀብረው እውነት
አንገት የማያስደፋ የማላፍርበት
ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይኸው ነው»
በማለት ግሩም ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ኢየሱስ የሚለው ስም እንዳይጠራ ማኅበሩ መቃወሙ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ በግልፅ እየሠራበት መሆኑን ያመለክታል፤ (1ቆሮ 12÷3)፡፡

የጌታን የማዳን ሥራ ለፍጡራን መስጠቱ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛነትና ብቸኛ የአዳኝነት ሥራ ለፍጡራን በመስጠትና የተለያዩ የደኅንነት /የመዳን/ መንገዶች እንዳሉ በማስተማር ብዙዎች እንዳይድኑ ማኅበሩ እንቅፋት ሆኖአል፡፡ ከተጠቀሱት ሐመርና ዕንቁ መጽሔቶች አንዳንድ ሐሳቦችን እንመልከት፡፡

Tuesday, August 23, 2016

ግመሉን በዝምታ ትንኙን በጫጫታ


Read in PDF
ከአሸናፊ በላይ
ትንሹ ነገር ያለ ቅጥ ሲጐላና ሲጋነን ትልቁንና ዋናውን ነገር ይሸፍናል፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናውንና ትልቁን የእግዚአብሔርን እውነታ ቸል ብለውና ትተው ለማይረባውና ኢምንት ለሆነው በአንዳንድ ሁኔታም የእግዚአብሔርን ቃል ለሚቃረነው የወግና የሥርዓት ጉዳይ ብርቱ ጥረት ሲያደርጉ ለተመለከታቸው ግብዞች ፈሪሳውያን ፣ «እናንተ ዕውሮች መሪዎች፤ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ» በማለት በብርቱ ገስጾአቸዋል፤ ማቴ. 23÷24፡፡
ይህንን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለግብዞች ፈሪሳውያን የተናገረውን ትምህርት ያነሳሁት ማኅበረ ቅዱሳን ሊወቀስበትና ሊወገዝበት የሚገባው ዋናውና ትልቁ የኑፋቄ ሐሳብ እያለ ማኅበሩ ለሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ያለቅጥ ትኩረት በመስጠት ዋናውና ትልቁ ጉዳይ ቸል እንደተባለ ለማመልከት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን አለቆች (ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ) ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ዋናውን የኑፋቄ ጉዳይ ወደ ጐን ትተው /ቸል ብለው/ ማኅበሩ በሚፈጥራቸው አንዳንድ ችግሮች ላይ ወቀሳ ሲያሳሙ ቆይተዋል፡፡ ማኅበሩ በአስተዳደር ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ እንዳስቸገራቸው፤ በቤተ ክርስቲያን ደንብና ሥርዓት ላይ እንዳመፀ፤ ገንዘብ ያለ አግባብ ሰብስቦ እንደተጠቀመ፤ የቤተ ክርስቲያን አለቆችን አላሠራም እንዳለ ፈራ ተባ እያሉ ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ አንዳንዶችም «የታመነ ምስክር አይዋሸም»፤ ምሳሌ 14÷5 የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመተላለፍ ስለ መናፍቁ ማኅበር «የቤተ ክርስቲያን ልጅነት፤ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት» ሲለፍፉና ጥብቅና ሲቆሙ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሲቃወሙ ቆይተዋል፤ አልፈው ተርፈውም በተሰጣቸው ሥልጣን የእርሱን እኩይ ፈቃድ በማስፈጸም የማኅበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ 

Wednesday, August 17, 2016

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የምናከብራት እንዴት እና እስከ ምን ድረስ ነው?ክርስቲያኖች ሁሉ ድንግል ማርያምን ያከብሯታል፤ አለማክበር አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ጌታቸውን አምላካቸውንና መድኃኒታቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ የወለደች እርሷ ናትና፡፡ ይህ እርሷን ለማክበር ከበቂ በላይ ምክንያት ነው፡፡ ለነገሩ ክርስቲያን እንኳና የጌታን እናት ማንንም በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረን ሰው መጥላት አይችልም፡፡ ወንጌልም እኮ እንኳን ወዳጅን ጠላትን ውደዱ ነው የሚለው?
አሁን ጥያቄው ማርያምን የምናከብራት እንዴትና እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ ከባድ አይደለም፤ ቀላል ነው፡፡ ማርያምን ልናከብራት የሚገባው እኛ በመሰለንና በታየን መንገድ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል በሚለው መሠረት መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲባልም በእግዚአብሔር ቃል የታዘዘውን መሠረት አድርገን በተገቢው መንገድ ማክበር የሚገባ ሲሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከሚለው አልፈን በአክብሮት ስም ያልተገባ ነገር አለማድረግንም ያካትታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የዘንድሮውን ጾመ ፍልሰታ ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ መጀመሪያው ላይ ያስቀመጡት መርሕ ክርስቲያኖች ሁሉ የሚስማሙበት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗም አቋም ነው፡፡ ስለዚህ ማርያምን ስለማክበር መርሑ በተገቢው መንገድ መከበር አለበት፡፡ ቅዱስነታቸው ያስቀመጡት መርሕ እንዲህ የሚል ነው፡፡

Saturday, August 13, 2016

ሕይወት የሆነን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ብቻ ነው! ምንጭ፦ dejebirhan.blogspot.com
ቅዱሳንን ማክበር እንደሚገባ ምንም ጥያቄ የለንም። መታሰቢያን በተመለከተም የድርጊቶቻችን አፈፃፀም የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔርን ስምና ክብር እስካልጋረደና  እስካልተካ ድረስ የሚደገፍ ነው። ነገር ግን  «ጥቂት አሻሮ ይዞ፤ ዱቄት ወዳለው መጠጋት» የሚለውን ብሂል ለመተግበር መሞከር ግን አደገኛ ነገር ነው። በተለይም በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ወቅት ወንጌል እንደዚህ ስለሚል፤ እኔም እንደዚህ ብል ችግር የለውም የሚለውን ራስን መሸሸጊያ ምክንያት በማቅረብ ለመከለል መሞከር ፀረ ወንጌል ነው። በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ሥር ኑፋቄና ክህደትን ማስተማር በአምላክ ፊት ያስጠይቃል። እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ስለሚችል የኛን ተረት ሁሉ ይሰራልናል ማለት አይደለም። ብዙ ጥያቄዎች የሚነሱትና እነዚህ የመሳሰሉ የስህተት ችካሎች አልነቀል ያሉት በምክንያት ስር በመደበቃቸው ነው። ቅዱሳንን በማክበርና በመውደድ ሽፋን ወደአምልኮና ተገቢ ያልሆነ ሥፍራ ወደማስቀመጥ ያደገው መንፈሳዊ በሚመስል ማሳሳት ተሸፍኖ ነው።

ለክርስቲያኖች ድኅነት ዋናው ቁልፍ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው የማንም ሰው ሞትና ትንሣኤ ለመዳናችን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። አይጨምርልንም፣ አይቀንስልንም። ማዳን የእግዚአብሔር ነውና ኢሳይያስ 4311 "እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም"
ይህ የተሠጠን የቃሉ እውነት እንደተጠበቀ ሆኖ የጌታ እናት የድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ዘላለማዊ ድኅነት መስጠት ይችላል? ወይ ብለን ብንጠይቅ መልሱ አይችልም ነው። ታዲያ በድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ ላይ ጥንታዊያን የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት የተለየ ሃይማኖታዊ ትኩረት የሚሰጠው ለምንድነው? ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ትርጉምና ትረካ የሚገልፁበትስ ምክንያት ለምን ይሆን? እንኳን እኛ ጠያቂዎቹ ራሳቸው በትክክል ምክንያቱን የሚያውቁ አይመስለንም። የሆኖ ሆኖ ትርክታቸውን ለመዳሰስ እንሞክራለን።