Wednesday, January 20, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የዛሬ 15 ዓመት ያሳተመውን የመዝሙር መጽሐፍ ፈቃድ ሳይጠይቅ በደስታ ጌታሁን ስም ማሳተሙ ውዝግብ አስነሣየሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ደራስያን የተደረሱ ዝማሬዎችን በመሰብሰብ የሰንበት ት/ቤቶች እንዲጠቀሙበት በሚል ያሳተመውን መጽሐፍ ማኅበረ ቀዱሳን ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በተባለው ቀሳጤ ድርሰት ስም ማሳተሙ ውዝግብ ማስነሣቱ ተሰማ፡፡ ዲ/ን ደስታ ጌታሁን ድርሰቱ የሌሎች መሆኑንና የመሰብሰቡን ስራ ሠርቶ “መዝሙረ ማኅሌት” በሚል ስም በ1993 ዓ.ም ያሳተመው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መሆኑን እያወቀ መጽሐፉ በታተመ በ15 ዓመቱ ራሱ እንደሰበሰበው ንቡረ እድ ኤልያስ እና መ/ር ዕንቆባሕርይ ተከሥተ ግጥሙንና ዜማውን እንዳስተማሩት በማስመሰል “ዋይ ዜማ” በሚል ስም በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት ሰሞኑን በ2008 ዓ.ም ያንኑ መዝሙር መልሶ አሳትሞታል፡፡ ከደስታ ይልቅ በአሳታሚነት ተሳታፊ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የመጽሐፉ ባለቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ ቢሆንም ማን ምን ያመጣል በሚል ትምክህት የማደራጃ መምሪያውን መጽሐፍ አሳትሞ እየቸበቸበ ይገኛል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ “ይህን የመዝሙር መጽሐፍ ሙሉ በሙሉ ዜማውንና ግጥሙን ላስተማሩኝ ለክቡር ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ፣ ለመምህር እንቈባሕርይ ተከሥተ ለመሪጌታ ሐዲስ አዱኛ እና በአሁኑ ሰዓት በሕይወት ለሌሉት መሪጌታ ጌራወርቅ ቀለመወርቅ” ምስጋና ያቀረበ መሆኑ ከስርቆቱ በላይ ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ሆኗል፡፡ እነዚህ በስም የተጠቀሱት ሰዎች በተለይም ንቡረ እድ ኤልያስ እና መምህር እንቈባሕርይ መቼ ነው በመዝሙር መጽሐፉ ውስጥ የሚገኙትን የመዝሙሮቹን ግጥምና ዜማ ሙሉ በሙሉ ያስተማሩት? የሚለው ከማነጋገሩም ባሻጋር በግለሰቦቹ በተለይም በመ/ር ዕንቆ ባሕርይ ዘንድ ቅሬታን እንዳሳደረ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ደስታ ይህን ያደረገው ምስጋና ካቀረብኩላቸው ምንም አይሉም ብሎ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በተሰረቀ ድርሰት ያላደረጉትን አስተማሩኝ ማለት መብታቸውን እንደመጋፋት የሚቆጠርና በሕግም ሊያስጠይቅ የሚችል ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም የስርቆቱ ተባባሪ እንደማድረግ የሚቆጠር ድርጊት ነውና፡፡ ይልቁንም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊው መ/ር ዕንቈ ባሕርይ በመምሪያው የታተመውን የመዝሙር መጽሐፍ ደስታ እንዲያሳትመው የተባበሩት ያስመስላልና፡፡

ይህን ቅሰጣ ድርሰት ተከትሎ የመምሪያው የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና የመምሪያው ኃላፊ መ/ር ዕንቆባሕርይ ግለሰቡና አሳታሚው እንዲከሰሱ ለጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ለአባ ማቴዎስ ያመለከቱ ሲሆን ሥራ አስኪያጁ አባ ማቴዎስም በመጀመሪያ ተስማምተው የነበረ ሲሆን በኋላ ግን ማኅበራቸው የሚነካ ስለመሰላቸው ነገሩ በሽምግልና እንዲያልቅ እያግባቡ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡    
ደስታ ከዚህ ቀደም በመጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ የማቅ ጀሌዎች በተነሡበት ጊዜ እምነት የለሹ ዘሪሁን ሙላቱ ጽፎ የሰጠውንና “የሰባኪው ሕጸጽ” የተሰኘችውን ባለ ጥቂት ገጽ “መጽሐፍ” ጽፎ በመከሰሱ መጽሐፉ በፖሊስ እንዲሰበሰብ ተደርጎ የነበረና እርሱም ጥፋተኛ ተብሎ የፍርድ ውሳኔ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ባቀረበው የወንጀል ማቅለያ መሠረት በ2 ዓመት ገደብ መለቀቁ ይታወሳል፡፡ “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሁ አሁንም ከመጽሐፍ ጋር በተያያዘ የተቋምን ድርሰት በመቀሰጥና በመጽሐፉ ውስጥ የግለሰቦችን ስም ግጥምና ዜማውን አስተማሩኝ በማለት በሐሰት ምስጋና በማቅረብ ጥፋት ፈጽሟል፡፡ ግለሰቡ ምንም ዓይነት የትምህርት ዝግጅት ሳይኖረው የማቅን አጀንዳ የሚያስፈጽም ስለሆነ ብቻ ከዚህ ቀደም የክፍለ ከተማ ጸሐፊ እስከ መሆን ደርሶ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ በፋይሉ ውስጥ የሚገኘው የ3 ቀን ሥልጠና የምስክር ወረቀት ብቻ ሲሆን እርሱም የልማት ኮሚሽን ያዘጋጀውና በሴት ልጅ ግርዛት ዙሪያ “ጾታዊ ጥቃት በትዕማር ዘመቻ” በሚል ርእስ በተዘጋጀው ሥልጠና ተሳትፎ ያገኘው የምስክር ወረቀት ነው፡፡ ስለዚህ አለመማሩን የሸፈነ መስሎት ሰው በጻፈው ላይ ስሙን እያስገባ ራሱን ደራሲ ለማስመሰል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
የሰውን ድርሰት በራስ ስም ማሳተም እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን በማቅ ውስጥ ብዙ ድርሰቶች ቢፈተሹ ከዚህ ነጻ እንዳይደሉ ይነገራል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጽፈው አሳትሙልን ብለው የመጽሐፋቸውን ሶፍትኮፒ ለማቅ የኅትመት ክፍል ከሰጡ በኋላ፣ ክፍሉ ምክንያት ፈጥሮ መታተም እንደማይችል ይልጽላቸውና በኋላ ርእሱን ለወጥ አድርጎ እንደሚያትመው የዚህ ነገር ሰለባ የሆኑና ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ በቅርቡ ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ እና ከቄስ ማንስል መጽሐፎች ላይ አስቀነጫጭበውና የራሳቸው ድርሰት አስመስለው በስማቸው ያሳተሙት አባ ሳሙኤልም ቅስጣ ድርሰትን በተደጋጋሚ የፈጸሙ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ጳጳስ ከሕግ በላይ በሆነባት ቤተክርስቲያን ተጠያቂ መሆን አልቻሉም፡፡

10 comments:

 1. እንዲያው መቼ ይሆን ከጥላቻ የፀዳ ፅሑፍ የምትፅፉት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቆች እውነት የሚዋጥላችሁ መቼ ይሆን? አሁን ይህ ዜና ምን ሆነ? ይለቅ እውነታውን ለመሸፈን ባትሞክሩ ጥሩ ነው፡፡ ማቅ ስለዘረፈው የመዝሙር መጽሐፍ ብናወራ አይሻልም ወይ? ለምን ታደናግራላችሁ?

   Delete
  2. አሁን እውነት ለመናገር አንተ ጭንቅላት አለህ ??? የተሸከምከው ስላጠራጠረኝ ነው?? እንጂ
   ለሰይጣን ምስክር ፣
   ሀሰት በመናገር ፣
   መሆን ነበረብህ ፣
   የዕንቧይ ካብ ፤
   አስብ በአምሮህ ፣
   ሰው ሁንና ፣
   ለመኖር በጤና ፤

   ስለሁሉም ቸር ያናግርህ

   Delete
 2. Luterawiyan min agebachew? !!! Kkkkk?

  ReplyDelete
 3. Tehadisowech enaniten yegedele yitsedikal mikinyatum satan nachihu kezare jemiro Begashaw, Asegid, Ezira,yared etc megedel alebachew

  ReplyDelete
 4. አሁን እንዲህ ያለ የመንደር ወሬ የቱ ጋ ነዉ መንፈሳዊነቱ ? እስቲ ንገሩን፡፡

  ReplyDelete
 5. leba yetfa you are they are cheater

  ReplyDelete
 6. Please STOP such kind of baseless accusation. I will be STOP visiting your site. It seems that your agenda is not gospel but MK. SHAME ON YOU GUYS. You should be better.

  ReplyDelete
 7. It is not music like what your pastors are copying from musicians. As long as it is tewahido's mezmur, no problem. We can solve it internally without the involvement of you pastors and bastards.

  ReplyDelete
 8. only the way of heaven is Jesus
  Jesus is lord amen i am the side of Jesus
  Fikre from Mekelle

  ReplyDelete