Friday, January 1, 2016

በሚኒሶታ ስቴት በጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ፓትርያርኩ ታላቅ አቀባበል ተደረገ!


Read in PDF 
ከሚኒሶታ የፓትርያርኩን የአሜሪካ ጉዞና አቀባበል በዚያም የነበረውን ሁኔታ የተመለከተ ዘገባ ደርሶናል ቀጥሎ እናቀርበዋለን፡፡ ቀጣይ ዘገባዎችንም እንደደረሱን ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን፡፡
  
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓርትርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባለፈው ታኅሣሥ 11/2008 ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚኒሶታ የገቡ ሲሆን ታላቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከኤርፖርት ጀምሮ እስከ ቤተ ክርስቲያኑ ድረስ እጅግ በብዙ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ ያጀበ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞተረኞችም አጅበው እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። ልብሰ ተክህኖ የለበሱ በርካታ ካህናት የተገኙ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሊቃነ ጳጳሳት ታጅበው በሊሜዝን ሆነው የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና ሕዝቡ በዝማሬና በይባቤ ኢያሸበሸቡ ነበር ያጀቡአቸው። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አቀባበል በአሜሪካ ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም በዓይነቱና በይዘቱ ግን እጅግ የተለየ እንደነበረ ተገልጿል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን እንደ ደረሱ ጸሎተ ኪዳን ተደርሷል። የያሬድ ጣዕመ ዜማና ቅኔ ከተበረከተ በኋላ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። የቅዱስ ፓትርያርኩን ቃለ ምዕዳን ከዚህ ጽሑፍ ቀጥለን እናቀርባለን።

ሚኒሶታ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለይቶ የተቋቋመ ሲሆን ከተቋቋመ ሁለት ዓመት ያልሞላው አዲስ ቤተ ክርስቲያን ነው። የመቋቋሙ ምክንያትምበኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ እንመራ፤ የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ሥርዓት ከበር አለበትሲሉ ሌላው ወገን ደግሞ በገለልተኛነት መቀጠል አለብን በማለት የተፈጠረ ከፍተኛአለመግባባት ነበረ። ጉዳዩ በመጨረሻ ፍርድ ቤት ደርሶ አንደኛው ወገን እንደምንም የሰው ቁጥር በማብዛት በእጅ ብልጫ አስፈርዶ ቤተ ክርስቲያኑን ተረከበ። የቀረው ወገን በቁጭት ወጥቶ የራሱን ቤተ ክርስቲያን ገዝቶ ሚኖሶታ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ አሰኘ። አንዳንድ ጳጳሳት የገንዘብ ልመናን ተገን በማድረግ በሁለቱም መካከል ግጭቱን ወደተባባሰ ደረጃ ወስደውት የነበረ ሲሆን በዚህም የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ክፉኛ ያዘኑ መሆናቸው ይታወሳል። በዚያ ክፉ የፈተና ጊዜም ቅዱስነታቸው የማጽናናት መልእክታቸውን እንደአስተላለፉላቸው ተወስቷል። ያ ሁሉ የፈተናና የመከራ ጊዜ አልፎ ዛሬ ቅዱስ ፓትርያርኩ በአካል ተገኝተው ሲባርኩአቸው ደስታቸውን ዕፅብ ድርብ አድርጎታል። ስለዚህም አቀባበሉን ልዩ ያደረገው ይህ ሁሉ ተደማምሮ እንደሆነ ተገምቷል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አሜሪካ የሔዱት የተለየ ወቅታዊ ጉዳይ የነበራቸው ሲሆን እግረ መንገዳቸውን የሕክምና ምርምራ/ቼክአፕ/ አድርጓል። በምርመራውም ሙሉ ጤንነት ያላቸው ከመሆኑ ሌላ በጤናቸው ላይ ምንም እንከን አልተገኘም። ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ በአሜሪካ ከሚጎበኙአቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል የሚኒሶታው ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ አንዱ ሆነ። ይኽ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሞት የሚመኝ ማኅበረ ቅዱሳን/ማቅ ፍጹም እንደታመሙና ከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስመስሎ በሐራ ብሎጉ ማውጣቱ ይታወሳል። የማቅ ጥላቻ የተሠወረ ባይሆንም የቀድሞውን ፓትርያርክ ጳውሎስን በተዘዋዋሪ ማስገደሉ የሚታወቅ ነው።

የአሁኑ ፓትርያርክ ማትያስ ለማቅ ቅሰጣዊ አካሔዱ ስላልተመቹት የክፉ ምኞት ዜማውን ኢያዜማ መቆየቱ ሐቅ ነው። በመሆኑም በምሉዕ ጤና ላይ የሚገኙትን ቅዱስ ፓትርያርክ ክርቲካል ሁኔታ ላይ ናቸው ብሎ መለፈፍ እብደት ቢሆንም በስተጀርባው ግን አንዱን ገድሎ ሌላውን ለማሾም ሌት ከቀን ደፋ ቀና የሚልለት ምኞቱ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ ማቅን ምን አደረጉ ብሎ የሚጠይቅ ጠያቂ መቼም አይጠፋም። ምክንያቱም ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁሉም ሰው የሚመሠክርላቸው ትግሥተኛ አባት፣ ቅድስናና የዋህነት፣ አርቆ አሳቢነትና የዓላማ ቁርጠኝነት ያላቸው ታላቅ አባት በማለት ነው። ወደ ማቅ ስንመጣ ግን የማቅ መሥፈርቱ ሌላ ስለሆነ ይኽ የቅዱስ ፓትርያርኩ ማንነት በፍጹም ሚዛን አልደፋም። ምክንያቱም ማቅ የሚፈልገው ፓትርያርክ እንደፈለገ የሚያሽከረክረው፤ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ቀርቶ የእርሱን ክስ ብቻ የሚያደምጥ፤ ማቅ ይባረር፤ ይሰቀል፤ ይገደል ያለ ሁሉ ያለምንም ፍርድ ተፈጻምነት እንዲኖረው የሚያደርግ ፓትርያርክ ነው። ፓትርያርክ ማትያስ ለዚህ ምኞቱ አልተመቹትም። ከዚህም አልፎ ህገ ወጥ ንግዱና ፖለቲካዊ አካሔዱ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና አሠራር ውጭ በመሆኑ ፓትርያርኩ የማቅ ደጋፊ ሆነው አልተገኙም። ቅዱስ ፓትርያርኩ ለእውነትና ለህሊናቸው ስለቆሙ ከማቅ ጋር ሳይገናኙ በመንገድ ተላለፉ።

በመሆኑም ይኽንና በመሳሰለው ሁሉ ማቅ በፓትርያርኩ ከመባረክ ይልቅ ክፉውን ሁሉ እየተመኘላቸው ይኖራል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለንሥሐ ያብቃው። ማቅ በቤተ ክህነት ውስጥ ሰግስጎ በአስቀመጣቸው ቅምጦቹ የተዛባ መረጃ እየተቀበለ፤ ቀጥተኛውንም ኢያዛባ የሰዎችን ንፁሕ ሕይወት ጥላሸት ይቀባል። የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ ያበላሻል። ለማቅ ወሬን የሚያቀብሉ፤ አይዞህ ባዮች ከቤተ ክህነት ውስጥ አንዳንድ ጳጳሳትና አንዳንድ መሰል ካህናት መሆናቸው ይታወቃል። እነዚህም በሁለተኛ ደረጃ ከማቅ ደሞዝ የሚከፈላቸው ናቸው። ማቅ በተለያየ መንገድ ከቤተ ክርስቲያን የሚያጋብሰውን ገንዘብ እነዚህን ወገኖች ይገዛበታል። እንደ ፈቃዱም ይታዘዙለታል። እነዚህ ወገኖች የሰውን ሕይወት ጥላሸት ለመቀባት፤ የቤተ ክርስቲያንን ገጽታ ለማበላሸት ህሊናቸውን የሸጡ እነማን ይሆኑ? የምንመለስበት ይሆናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

14 comments:

 1. ሰላም ለእናንተ ይሁን አባ ሰላማዎች! ስለ ቅዱስነታቸው የሚኒሶታ ጽርሐ አርያም ቅ/ሥላሴ ጉብኝት ከላይ ያላችሁትን ሳየው በወቅቱ የወንጌል ጉባኤ ለመካፈል ከሌላ ስቴት ሄጄ በቦታው ነበርኩ እና እውነቱን ላካፍላችሁ፦
  እንደተባለው አቀባበሉ እጅግ በጣም የተለየ ነበረ፣ የህዝቡ ስሜት፣ የሰ/ት ቤት ወጣቶች መዝሙር፣ በአጠቃላይ ለቅዱስነታቸው በሀገረ አሜሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ነው ብዬ ልለፈው፣ ግን "በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞተረኞች" የተባለው በሚቀጥለው ሲመጡ የተያዘ ዕቅድ ከሆነ ነው እንጂ የዛን ዕለት እንኳን ሞተር የሞተር ጭስም አልነበረም።
  እዚህ ላይ ማውሳት የምፈልገው የቅዱስነታቸውን ቆራጥነት ነው፣ ይኸውም ወደ ሚኒሶታ እንዳይመጡ በእነ አቡነ ፋኑኤል እና በማቅ ተላላኪ ወገኖች የተደረገባቸውን ከፍተኛ ጫና ወደ ጎን በመተው በተገፋው ምዕመን መካከል ተገኝተው ቀድሰው በማቁረብ ቦታውንም ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብለው በመሰየም ቃለ ምዕዳን መስጠታቸው ቆራጥ አባት መሆናቸውን ያስመሰከሩበት አጋጣሚ ነበረ። ማኅበረ ቅዱሳንማ ቅዱስነታቸው ሚኒሶታ እንዳይገኙ ያልፈነቀለው፣ ያላወራው በሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ አልነበረም፣ ምክንያቱም በእነ "ቀሲስ" ሱራፌልና በነ አባ ፊልጶስ የሚመራው ያለ አህጉረ ስብከቱ ፈቃድ ራሱን ፀረ ተሃድሶ ብሎ የሰየመው ቅርንጫፍ ቡድን በሚኒሶታ ጉባኤ ስለነበረው የቅዱስ ፓትርያርኩ ሚኒሶታ መገኘት ለማቅ አልተዋጠለትም ነበረ፣ እሱ ወደፊት ብዙ ዶላር ሊያጋብስበት ያሰበው የፀረ ተሃድሶ እንቅስቃሴን ሌሎች እውቅና እንዳያገኙበትና አጋጣሚውን እንዳይጠቀሙ ብዙ ዳክሮ ነበረ ግን አልሆነም ቅዱስነታቸውም ተገኙ ጉባኤውም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት ለሶስት ቀናት ተካሄደ የቅዱስነታቸው መኖርም ለጉባኤው ትልቅ ክብር ሆኖ አለፈ፣ ማቅም ከሰረ፣ አረረ!

  ReplyDelete
 2. ዛሬ ገና ያልሆነ ዘገባ አቀረባሁ "አባ" ማትያስና ማህበረ ቅዱሳን ወያኔ እንዳስታረቃቸው ያልሰማችሁ? ስላሴ ቤተ ክርስቲያን የማቅ እንደሆነ አታውቁም? እንዴት እንዴት ነገሩን ምታወሳስቡት

  ReplyDelete
  Replies
  1. aba kidan siyum ፦ የትኛውን ሥላሴ ነው የማኅበረ ቅዱሳን ነው ያሉት? ካላወቁ ልንገርዎት የሚኒሶታው ሥላሴ እዚህ ትልቅ ደረጃ የደረሰው የማቅ እጅ ስለሌለበት ነው። ለነገሩ አጋጣሚዋን ተጠቅሞ ባለቤት ለመምሰል አንዳንድ አባላቱ ውርውር ሲሉ ይስተዋላል ግን በፍፁም መኖራቸውም አይታወቅም የማቅ ቤተ ክርስቲያን ቢሆን ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ከኢትዮጵያ ይጋበዙ ነበረ፣ ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ ከአንዴም ሁለቴ ይጋበዝ ነበረ ብቻ ብዙ ማለት ይቻላል ግን ይቆየን……!

   Delete
  2. "አባ" ያጠለቁትን የሃራጥቃ ቆብ ያውልቁ፦የተኩላ እረኛ ከአነጋገሩ ያስታዉቃል ።

   Delete
 3. I commend you for covering the visit of the one and only Patriarch and holly father of the Ethiopian Orthodox Tewahdo CHURCH Abune Mathias' visit to the US. I also commend you for exposing the evil deeds and talks of the masked real enemies of the true Fathers of the Church.

  ReplyDelete
 4. Werada mahber begze yeraswan sinodos mesrata bitgenetel yishalatal.betecrstiyanwa cheresa kemetfatwa befit.

  ReplyDelete
 5. ‹‹የቀድሞውን ፓትርያርክ ጳውሎስን በተዘዋዋሪ ማስገደሉ የሚታወቅ ነው›› ከአንድ የዕምነት ብሎገር የማይጠበቅ ተራና የወረደ አነጋገር... ይቅር ይበላችሁ...

  ReplyDelete
 6. It is a fair analysis. A little bit exaggerated but true.

  ReplyDelete
 7. እዜህ በማያገባህ አገር ያልተደረገውን ተደረገ ብለህ ከምትዘግብ እዛው ያለህበትን አገር የሕዝቡን እምባ አብሱ፤ወደታች ወርደው ችግርተኛውን ይባርኩት፣ የታሰሩ
  የሐይማኖት አባቶችን ይጎብኙ፣ ትክክለኛ ሕግ ባለበት አገር
  ለኛም ኦርቶዶክሶች ትክክለኛ ፍትህ ይጠይቁ በላቸው እንደው ያልተደረገውን ቸክችከህ በሳቸው ለመወደድ ይመስላል። የናንተ የተሀድሶ እና የማህበረ ቅዱሳን የቃላት
  ጦርነት እግዚአብሔር በጥበቡ አንድ መፍትሔ ይፍጠርላችሁ
  እኛ የተዋህዶ ልጆች የእናንተስ ጉዳይ ሰልችቶናል።

  ReplyDelete
 8. ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለዚህ ክብር የደረሰው በካህናተቱና በምእመናኑ ታላቅ ትግል እንዲሁም መሥዋዕት እንጂ በማቅ እንዳልሆነ ልታውቅ ይገባል። እግዚአብሔር ሁሉን አደርጓል። ወደር የሌለው አቀባበል ተደረገ የሚባለው ያስማማናል። ለኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክ ቢያንስ እንጂ አይበዛበትምና።
  "ጉዳዩ በመጨረሻ ፍርድ ቤት ደርሶ አንደኛው ወገን እንደምንም የሰው ቁጥር
  በማብዛት በእጅ ብልጫ አስፈርዶ ቤተ ክርስቲያኑን ተረከበ። የቀረው ወገን
  በቁጭት ወጥቶ የራሱን ቤተ ክርስቲያን ገዝቶ ሚኖሶታ ጽርሐ አርያም ቅድስት
  ሥላሴ አሰኘ።"

  ReplyDelete
 9. እስቲ አሉባልታውን ትታችሁ ወንጌልን ስበኩ፡፡ ነገረ ስራችሁ ሁሉ ክርስቲያን ክርስቲያን አይልም፡፡ ሰዎችን ከስህተታችው እንዲታረሙ ከመለምን ውድቀታቸውን በአደባባይ ማውጣት የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ክሚል ሰው አይጠበቅም፡፡

  ReplyDelete
 10. ZARE ADDIS NEGER ANEBEBIKU.YEMAHIBERE KIDUSANU TADESSE YEMIBALEW TEDEBEDEB YILAL YIHE FACEBOOK.YEEWUNET KEHONE EJIG BETAM NEWUR NEW.BEZIH LIDESET YEMICHILEW TELAT SEYITAN BICHA NEW.ENEN YEGEREMEGN CHIGIR BEDERESE KUTIR GUDAYU WEDETEHADISO MEZORU NEW.WEY GUD.LEGIZEW DEBIDABIWOCUNM HONE MIKINYATACHEWUN LEMAWEK BAYICHALIM....BAND BEKUL YEMAHIBERU EMINET YEMILEKABET FETENA SIHON BELELA BEKUL GIN SEW YEZERAWUN YACHIDALINA LEFETSEMUT GIF KELAY YEHONE KITAT NEW.DEGIMOS DIRGITU TIKIKIL BAYIHONM TENEKA BILO BURAKEREYU MIN MALET NEW.SILEKIRISTOS SIM YETEKEBELEW FETENA AYIDELEM.LEMANGNAWUM YESEW DULA YALIFAL.KELAY YEMIMETAW KITAT GIN YASIFERAL.GETA YEWENGELIN BIRHAN LEHIZIBACHN YABIRALIN.

  ReplyDelete
 11. ድንቄም አባ ሰላማ??

  ReplyDelete
 12. የሚኒሶታ ጽርህ አርያም ቅድስት ሥላሴ ለሃራጥቃዎች ቦታ የላትም በከንቱ አትድከሙ

  ReplyDelete