Tuesday, January 12, 2016

ስለ ወንጌል እውነት መሞት እንጂ መግደል የክርስቲያኖች ተግባር አይደለምየማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ የሆነችው ሐራ ሰሞኑን አንድ ሊታመን የማይችል ወሬ አስነብባለች፡፡ ይኸውም ሁለት ማሊያ ለብሶ ለፖለቲካም ለሃይማኖትም በሚጫወተው በታደሰ ወርቁ ላይ ተሐድሶዎች የግድያ ሙከራ አደረጉበት የሚል ነው፡፡ በቅድሚያ ታደሰ ወርቁ ላይ ደረሰ የተባለው የግድያ ሙከራ ማንም ያድርሰው ማን እውነት ከሆነ ተገቢ አይደለም፡፡ ሐራ ግን ይህን ያደረጉት ተሐድሶዎች ናቸው ብላ ታደሰን አጽናንታዋለች፡፡ ምክንያቱም በህልሙም ሆነ በእውኑ የታደሰ ወርቁ ቅዠት ይህ ስለሆነ በተሐድሶ ላይ ማላከኳ እርሱ እንዲጽናና ካልሆነ በቀር ውሸት ለመሆኑ ዘገባው መለክታል፡፡ ለምን? ቢባል ታደሰ ወርቁ የግድያ ሙከራ ተቃጣበት ያለችው ቦታ ላይ ግድያን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎች የሚፈጸሙበት ስፍራ መሆኑን ያካባቢውን ነዋሪዎች አነጋግሬ ደርሼበታሁ ስትል ገልጻለች፡፡ ታደሰ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በተሐድሶዎች እጅ ነው የተፈጸመው መባሉ በየትኛው መንገድ ነው የተረጋገጠው? የሚለው ግን በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡
ሐራ ራሱን ታደሰን ጠቅሳ እንደጻፈችው ጥቃት አድራሾቹ ተሀድሶዎች ሲሆኑ “የእኛ የፀረ ተሐድሶ ገላጭ አሁን እስኪ ማህበሯ ታድንህ እንደሆነ እናያለን እንገድልሃለን” አሉኝ በማለት ሰዎቹ ተናገሩኝ ያለውን ጠቅሳለች፡፡ ለዚህ ግን ከእርሱ ውጪ ሌላ ምሰክር የለም፡፡ 

ለመሆኑ ታደሰ ወርቁ ማነው? ከዚህ ቀደም በአባ ጳውሎስ ዘመን በተደጋጋሚ በአንዳንድ የግል መጽሔቶች ላይ የሚያወጣቸውን ጽሑፎች ለተመለከተ ታደሰ ወርቁ በምድር ላይ ከሰይጣን በላይ የሚጠላው የቀድሞዎቹን ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊንና አቡነ ጳውሎስን እንደነበር ጽሑፎቹ ይመሰክራሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ አሁን ያሉትን ፓትርያርክ ጨምሮ ማንኛውንም የቤተ ክህነት አመራር ባገኘው አጋጣሚ በሻካራ ቃላት ሲወርፍ ኖሯል፡፡ ሁለት ማሊያ እንደመልበሱ የስምዓ ጽድቅ አዘጋጅ በነበረ ጊዜ ሃይማኖታዊ ጽሑፍ በጋዜጣው ላይ ሲጽፍ ፖለቲካዊ አመለካከቱን ደግሞ በተለይ በቋሚነት በተሰለፈበት ዕንቁ መጽሔት ላይ ሲያተላልፍ ኖሯል፡፡ በተለይ የጥምቀት ተመላሽ የተባለው የወጣት ክንፍ ለአመጽ የተሰናዳ ቅምጥ ኃይል መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ከዚህ የተነሣ ሁከት የሚያስነሱ ሰዎችን ማኅበረ ቅዱሳን አሳልፎ እንዲሰጥ ሲባል በዋነኛነት በወቅቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ የነበረው ተስፋዬ ውብሸት ከአባ ሳሙኤል ጋር በመሆን ስም ዝርዝራቸውን ከጠቀሷቸው ሁከት ፈጣሪዎች መካከል ከማንያዘዋል ቀጥሎ አንዱ ታደሰ ወርቁ ነበር፡፡ ማህበሩም ታደሰን ከማኅበሩ ሰራተኛነት በማስወጣት ከማኅበሩ ጋር ንክኪ ወዳለው ዮድ አቢሲኒያ የጉዞ ወኪል ውስጥ በአስጎብኚነት እንዲሰራ ተደርጓል፡፡
በሃይማኖታዊ ጽሑፎቹ ላይ ጭምር ፖለቲካዊነት የሚጫነው ታደሰ ወርቁ በቅርቡ በዲ/ን ምንዳዬ የመዝሙር ምርቃት ላይ ባልዋለበትና በማያውቀው ጉዳይ ውስጥ ገብቶ የዘመኑን መዝሙሮች ተችቶ የተናገረ ሲሆን፣ የአማርኛ መዝሙሮችን ታሪክ ባለፉት 20 ያህል ዓመታት ውስጥ ብቻ በመገደብ ለማህበሩ ቅርብ የሆኑ ዘማርያንን ብቻ ጠቅሶ አወድሶበታል፡፡ ከዚያ በፊት መዝሙር ሐዋዝ የመሪጌታ ጸሐይ ብርሃኑ እና ኪነጥበብ የታወቀባቸው እንደ ቸርነትህ የተሰኘውና ሌሎችም የዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ ዝማሬዎች ከኖታቸው ጋር የተዘጋጁትን መዝሙራት ታደሰ ወርቁ ስለማያውቃቸው ወይም ሊያውቃቸው ስለማይፈልግም አልጠቀሳቸውም፡፡
ታደሰን የሚያውቁት እንደሚናገሩት በማቅ አንዳንድ አመራሮች በኩል ድብቅ ዓላማችንን ፊት ለፊት አውጥቶ ያስጠቃንና በመንግሥት “ያስጠቆረን” እሱ ነው በማለት ይጠሉታል፡፡ በቤተ ክህነት ደግሞ አለሙያው መጋቤ ሥርዓት የሚል ማዕረግ ከተሸከመው ከደስታ ጌታሁን ውጪ ጰጳሳቱን ጨምሮ ሁሉም ሊያየው አይፈልግም፡፡ በሁሉም ዘንድ ዘርፈ ብዙ ጠብ ውስጥ የገባውና እዚያው እዘመዶቹ መካከል ብዙ ጠላቶችን ያፈራውን ታደሰ ወርቁን እንዴት ተሐድሶዎች  ደበደቡት ይባላል? የሚለው አነጋጋሪ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያምን መስቀሉን ነጥቀው በጥፊ ሲመቱት፣ ዘማሪት ምርትነሽንም ሴት ልጅ በመሆኗ እንኳን ርህራሄ ሳይሰማቸው በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥፊ ሲመቷት፣ በቅድስት ማርያም ግቢ ውስጥ ደግሞ ማቅ የቀጠራቸው ወሮበሎች ምስማር ባለው እንጨት ቀሲስ ዘማሪ ትዝታውን ሲፈነክቱት የቀድሞዋ ደጀሰላም የአሁኗ ሐራ ነገሩን ይበል ከማለት በቀር አልኮነነችውም ነበር፡፡ የታደሰ ወርቁን መደብደብ ግን ከተሐድሶ እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ አሳፋሪና ማንም ሊያምነው የማይችል ሐሰተኛ ዘገባ አውጣች፡፡ ታደሰንም ከሌላ ፕላኔት የመጣ በማስመሰል ደረሰበት ያለችውን ጥቃት ከሰማዕትነት እንዲቆጠርለት ዳር ዳር ብላለች፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ በወንጌል ምክንያት የተፈጸሙ ድብደባዎችን ይበል ስትል እንዳልነበር ከቤተክርስቲያን ውጪ ተፈጸመ ያለችውንና ምክንያቱና አድራሹ በውል ያልታወቀውን ጥቃት በተሐድሶዎች ላይ ማላከኳ ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥላት ነው፡፡
ሐራ እንዳስነበበችው ታደሰ ወርቁ ላይ የደረሰውን ጥቃት የግድያ ሙከራ እና የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተጋድሎውን ከፍታና የእናድሳለን ባዮቹን ዝቅጠት አመልክቶናልበማለትየፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጥምረት” በማለት ራሱን የሚጠራው የድራፍት ቡድን መናገሩን ጠቅሳለች፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ወሬ በስተጀርባ የቡድኑ ሌላ ሴራ መኖሩ እየተነገረ ነው፡፡ አገር ውስጥ ያሉት የድራፍቱ ቡድን አባላት አሜሪካ ባሉት የቡድኑ አባላት በሱራፌልና በዳንኤል ግርማ አማካይነት በፀረ ተሐድሶ ዘመቻ ስም 500 ሺህ ብር ተልኮላቸዋል፡፡ በዚህም እርስ በርስ ንትርክ ጀምረዋል፡፡ እነርሱ እያሉ ያለው እነ ፌቨንን፣ እነ ደረጀ ዘወይንዬንና ሌሎችንም የምእመናን ወገኖች ከገንዘቡ መካፈል የለባቸውም በማለት ለእኛ ብቻ ባዮቹ እነ ጳውሎስ እና መኮንን ደስታ አንሰጥም እያሉ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታደሰም ተደብድቧልና በታክሲ እና በሰው መኪና ከሚመላለስ መኪና እንግዛለት እያሉ ነው፡፡ ለምን? ቢባል ተሐድሶን እንደ ያረጋል አበጋዝ በላፕቶፕ እየተዋጋልን ነውና፡፡ ስለዚህ ታደሰ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ መባሉ ነገሩ ወዲህ ነው አሰኝቷል፡፡ ይህም ወሬውን ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ ከቶታል፡፡
በመሠረቱ ሃይማኖትን በድብድብ ማስፋፋትም ሆነ መጠበቅ የክርስትና ጠባይ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን በታሪክ ክርስትናን በዚህ መንገድ በጦርነት ለማስፋፋት የሞከሩ ቢኖሩም የክርስትና መርህ ግን ፍቅር እንጂ ዱላ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች ስለጌታ በሌሎች ይደበደባሉ እንጂ እነርሱ ስለ ሃይማኖታቸው ሌሎችን አይደበድቡም፡፡ ክርስትና እንደ መሥራቹ እንደ ክርስቶስ በፍቅር የሚሰበክና ሰዎች ወደውና ፈቅደው የሚከተሉት የሕይወት መንገድ ነው እንጂ ዱላ የለበትም፡፡ ድብድብ የሥጋና የሰይጣን አሰራር ነው፡፡ ለሃይማኖታቸው በመቅናት ሃይማኖታቸውን በዱላ ወይም በሰይፍ ለማስፋፋት ወይም ከሌላው ለመከላከል የሚሞክሩ ሁሉ ከሰይጣን ወይም ከሥጋ ናቸው እንጂ ከእግዚአብሔር አይደሉም፡፡
በአገራችን ግን ይህን የክርስትና መርህ ሳይረዱ ሃይማኖታቸውን በዱላ ለማስፋፋት የሚሞክሩ ጥንትም ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፡፡ ቀደም ብሎ እንኳን ያለውን ብንጠቅስ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ልዩ ልዩ መከራና ስቃይ በማድረስ እነርሱን ከአምልኮተ እግዚአብሔር ለማስወጣትና እርሱ እያስፋፋ ወዳለው አዲስ አምልኮት ለማስገባት ሞክሯል፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም፤ በሥላሴ ላይ አራተኛ አልጨምርም ብለው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም መደብደብና ስለክርስቶስ መከራ መቀበል የክርስቲያን ጠባይና ዕጣ ፈንታው መሆኑን፣ ለሃይማኖት በመቅናት ስም በወንጌል ቃል መሰረት የሚያምኑትንና የሚመሰክሩትን መደብደብና ማሳደድ ደግሞ የሰይጣንና የግብር አበሮቹ ሥራ መሆኑ ታይቷል፡፡
ከዓመታት በፊት እንኳ መ/ር ግርማ በቀለና መ/ር ጽጌ ስጦታው በሃይማኖት ጉዳይ ተከሰው ሲኖዶስ ላይ ቀርበው ከተከራከሩና ከረቱ በኋላ እንዴት እንደፈራለን ባዮቹን አንዳንድ ጳጳሳትን ለማስደሰት ተብሎ ቀኖና ከተሰጣቸውና ደብረ ሊባኖስ ከወረዱ በኋላ ማቅ በአሰቃቂ ሁኔታ አስደብድቧቸው ሃይማኖቱን በዱላ ለመጠበቅ በመሞከር ማንነቱን አሳይቷል፡፡ አሁንም እያሳደዳቸው፣ እያገለላቸው፣ እያንገላታቸውና እያስደበደባቸው ያሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ ሃይማኖትን በዚህ መንገድ መከላከልም ሆነ ማስፋፋት የክርስትና መርህ አለመሆኑ ግን ክርስቲያን ከሆነ ሁሉ የተሰወረ አይደለም፡፡
በታደሰ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ የተባለው ወሬ የተረጋገጠ መሆን አለመሆኑ መጣራት ያለበት መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ይህን ድርጊት የፈጸሙት “ተሐድሶዎች ናቸው” ማለት ግን ለወንጌል ሰዎች አለስማቸው ስም መስጠት ይሆናል፡፡ እንዲህ የሚያደርጉ የወንጌል ሰዎች የሉም፡፡ እንዲህ የሚያደርጉ ወንጌልን የሚለውን ያልተረዱ፣ የግብር አባታቸው የነፍሰ ገዳዩ የዲያብሎስ ልጆች፣ የክርስትና መርህ ያልገባቸው የስም ክርስቲያኖች ናቸው፡፡

18 comments:

 1. ወሬኛ ሃራጥቃ።

  ReplyDelete
 2. ተሃድሶ ሰው እስከመግደል ሙከራ ያደርጋል አያደርግም የሚለው መከራከሪያ መቅረቡ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ምክንያቱም ከበረቱ እያወጡ ሰውን በዲያብሎስ የሐሰት ትምህርት ነፍሱን ከማጥፋት በላይ ምን ግድያ አለ?

  ReplyDelete
 3. Thank you very much

  ReplyDelete
 4. ታደሰ ወርቁ ማነው እንደዚህ ለግድያ የሚፈለገው ስለታሃድሶ ስበከ ጥሩ እንኩአን ሰበከ እንዲህ ግን ለግድያ ብሎ ወሬ ማስፋት በቲፎዞ ለማብዛት ጥቅማ ጥቅም ለማስገኘት ከሆነ ያሳዝናል ምክንቱም ተሀድሶን ባደባባይ የሚወቅሱ በነበሩና በቅዠት ሲጓዝ በደረሰበት ግን ውንጀላው ውሐ አይቋጥርም የሀሰት ውንጅላ ነው በሱ ላይ ደረሰ የተባለው የግድያ ሙከራ ማንም ያድርሰው ማን እውነት ከሆነ ተገቢ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 5. ስለ ወንጌል እውነት መሞት እንጂ መግደል የክርስቲያኖች ተግባር አይደለም

  ReplyDelete
 6. እናንተ የወንጌል ሰዎች ሌላው ፀረ ወንጌል ከየት የመጣ ክርስትና ነው

  ReplyDelete
 7. ዋሾዎች ትርኪምርኪ ማውራት አይሰለቻችሁም፡፡ ለወንድማችን መደብደቡ ክብር ነው ሥራችሁ ግን ተገድቧል፡፡ ዕቀብ ማኀበርነ ማኀበረ ቅዱሳን፡፡

  ReplyDelete
 8. ahun yihe hulu zuria timtim enkuan tedebedebe new? Zares betam telahuachihu.

  ReplyDelete
 9. ega yemenawekew nefese geday mahebere kidusan becha new

  ReplyDelete
 10. ማቅ በሌለበት ይህን ሠራ አደረገ እያላችሁ ስትከስሱት ምንም ያላፈራችሁ ዛሬ የናንተ ጉድ ሲገለጥ እንዲህ የሚያንጫጫችሁ ምን ይሆን፡፡ ወደዳችሁም ጠላችሁም እናንተ ጊዜ አልሰጥ ብሏችሁ እንጂ በትምህርት ሳይሆን በሰይፍም ተዋህዶን ለማጥፋት ወደኋላ እንደማትሉ በሀገራችን ክርስቲያኖች ላይ በዘመነ ሱስንዮስ፣ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ ዛሬም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቁጥር ባነሰባቸው አንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች እያደረሳችሁት ያላችሁት ዐይን ያወጣ ሥጋዊ ጫናና ማስፈራራት ድብደባም ግልፅ ማስረጃ ነው፡፡ ራስህን ቀይር እንጂ ቦታ አትቀይር በሚል የሞት ፍልስፍና በማታምኑባት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰርጋችሁ ለመግባትና በአባቶቻችን ፅናት እስካሁን የቆዩልንን ቤተመቅደሶቻችንን ለመቀማት የምታደርጉት የሽፍትነት ተግባር አንድን መምህር ከመደብበድና ከመግደል ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ ይመስላችኋል እንዴ፡፡ እናንተ በከፋት መንፈስ የጥፋት ሥራችሁን ለመሥራት ቀን ሌት ትሮጣላችሁ፤ ኦርቶዶክስ ተዋህዶም እስከ አለም ፍጻሜ ትጓዛለች ልታጠፏት የሚቻላችኁ አይደለምና፡፡ ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሎቹም ይጓዛሉ እንደተባለ የእናንተና የመሰሎቻችሁ ከንቱ ጩኸትና ድካም ቤተክርስቲያናችንን ከመልካም ሥራዋ አያስቆማትም ያፀናታል እንጂ፡፡ እናንተ ግን ታልፋላችሁ እሷትኖራለች፡፡ ይህ እውነት መሆኑን ለማመን ብትቸገሩም ይሆናል እስከዛሬም እያየነው ነው፤ የምናምነው መድኃኔአለም ቀድሞ ነግሮናል የነገረንም እየተፈጸመ ነውና አንደነግጥም፡፡

  ReplyDelete
 11. የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች።

  ReplyDelete
 12. Ye woshoch mahber .mahbere erkusan.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I AM TELLING YOU THIS GUYS RIGHT NOW NOW YOU ABA SELAMA REPRESENTING THE SO CALLED WEYANE/TPLF WCREATED YOU TO DIVDE THE EOTC IT IS VERY SAD AND SHAME

   Delete
 13. አባካችሁ ምን አለ መካሰሱን ትታችሁ ወንገልን ብቻ ብታስተምሩ ደግሞም ለወያኒ ባትስሩ

  ReplyDelete
 14. ይኼ የወሮበሎች ማህበር የሚሰራቸዉ ድራማዎች ማለቂያ የላቸዉም፡፡ እነ ምርትነሽ፣ትዝታዉ…..ወዘተ ሲደበደቡ ደብዳቢዎችን ለእምነታቸዉ ቀናኢ የሆኑ ጀግኖች አድርጎ ያቀርባል፣ የእሱ አፈቀላጤ ሲንዘላዘል በዱርዬ ስለተደበደበ ግን ሞንታርቦዉን ይነፋል፡፡
  ሰዉዬዉ መደብደቡን ባልደግፈዉም ደብዳቢዎቹ ተሀድሶዎች ናቸዉ መባሉ የሞኝ ዘፈን ሆኖብኛል፡፡ ተሀድሶ ይሰደዳል እንጅ ሌሎችን አያሳድድም፡፡

  ReplyDelete
 15. ሀራ ጥቃ አይሆንም ምርጥ እቃ ፍቅረ ንዋይ አንጎላችሁን ስላዞረው የሰማይ ቤታችሁን እረስታችሕል የመሀበረ ቅዱሳን መገለጫ ሀይማኖትን ከምግባር በስግብግብ ዘመን እውቀታቸውን ጉልበታቸውን ለቤተክርስቲያን የሰጡ የቤተክርስቲያኒቱ ቅን አገልጋዬች ናቸው። ምድረ ሀራ ጥቃ ተነቅቶባችሆል አስመሳይ ሁላ እግዚአብኤር ካልመረጠ ቤተክርስቲያንን ማገልገልም መገልገልም አትችሉም እርርርርርርርርርርርርርርርርርር በሉ እናንተ ገባር ወንዞች አበቃሁ።

  ReplyDelete
 16. ሀራጥቃ አይሆንም ምርጥ እቃ

  ReplyDelete
 17. Betam yemigermew enanete tehadiso mehonachihun eyanenachihu betekerestian wesete zarem yeleme yemilu mebezatachew new.

  ReplyDelete