Wednesday, January 27, 2016

ማቅ በስደተኛው ሲኖዶስ ላይ ጦርነት ሊከፍት ነውበዘንድሮው የጥምቀት በዓል በተሰበከው ወንጌል እጅግ የተቆጣው ሰይጣን ሰራዊቱን አሰባስቦ በሲኖዶሱ አባቶች ላይ ሊዘምት መሆኑን ምንጮች አረጋግጠዋል። በዳንኤል ግርማ የሚመራው የሁከት እንቅሥቃሴ ውስጥ ለውስጥ አዋኪዎችን እየመለመለ ሲሆን እነአባይነህ ካሴና እነዳንኤል ክብረት በቀስቃሽነት ተመድበዋል። እንደ ምክንያት የተወሰደው አቡነ መልከ ጼዴቅ በኦርጋን መዘመር ይቻላል ማለታቸውን ተከትሎ ቢሆንም አላማው ግን ቦታ እያየዘ የመጣውን የወንጌል ክብር ለመቃወም መሆኑ ግልጥ ነው።
 ኦርጋን መሣሪያ፣ እስከ አሁን ድረስ በአንዳድ የሲኖዶሱ አብያተ ክርስቲያናት እየተዘመረበት የቆየ ሲሆን በሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም ግን በማህበሩ የውስጥ እንቅሥቃሴ ታግዶ ቆይቶ እንደነበር ምንጮች ይጠቁማሉ። ማህበሩ በአንድ መነኩሴ አማካኘነት ሰንበት ተማሪዎችን በማሸፈት በቅድስት ማርያም ሰርጎ ለመግባት የሚያደርገውን እንቅሥቃሴ አስቀድመው ያወቁ ካህናትና የቦርድ አባላት ኦርጋኑ እንዲመለስ አድርገዋል። ይህን ያደረጉበት ምክንያት የማህበሩ አባላት የኦርጋን ድምጽ ሲሰሙና የኢየሱስ ስም ሲነሳ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መቆም ስለማይችሉ ነው ተብሏል። የማህበሩን አባላት ለማባረር የኢየሱስን ስም ደጋግሞ መጥራት እና ኦርጋን ማሰማት ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ካህናቱ ይናገራሉ። የአዲስ አበባው ቤተ ክህነትም ይህን ዘዴ ቢጠቀም ረፍት ሊያገኝ እደሚችል ብዙዎች ይመክራሉ። የማህበሩ አባላት ከኢየሱስ ስምና ከኦርጋን ጋር በተያያዘ በሚማሩት ትምህርት የሥነ ልቦና ችግር እንደገጠማቸው የሚናገሩ አሉ። በዘንድሮው ጥምቀት በዓል ላይ ኦርጋን ሲመታ ጆሯቸውን እየያዙ ሲሮጡ የታዩ የማህበሩ አባላት ነበሩ ተብሏል።

 የጥያቄው መንሥኤ ቅድስት ማርያም ውስጥ ኦርጋንን የሚቃወሙ የማህበሩ ምልምሎች በመገኘታቸው በዚህ ጉዳይ ላይ አቡነ መልከ ጸዴቅ ድንገተኛ ጥያቄ ሲጠየቁ የድሮ አቋማቸውን መልስ አድርገው መስጠታቸውን ተከትሎ ማህበሩ ነገሩን ያለ ልክ ከፍ እያደረገው ይገኛል። የውስጥ ምንጮች እንደሚያስረዱት ግን ይህ የኦርጋን ጥያቄ እንደ አዲስ እንዲጠየቅና የአቡነ መልከ ጼዴቅን መልስ መነሻ በማድረግ ፀረ ተሃድሶ እንቅሥቃሴ የሚባለው አካል ሲኖዶሱን ለመረበሽ አስቀድሞ ያቀደው መሆኑን ነው። ተረፈ ወርቁ የተባለው አባ ሰላማ ላይ አቡነ መልከ ጼዴቅን ወቅሶ የጻፈው ሰው የጥያቄውን መነሻ አላማውን የታሪኩን ሂደትና በውስጡ የተያዘውን የተንኮል እቅድ ስለማያውቅ ነው። አቡነ መልከ ጼዴቅ ስለ ኦርጋን ለመናገር እቅድ እንዳልነበራቸውና ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር አብረው የሰጡት መልስ መሆኑን ምንጮች ያስረዳሉ። ሌሎች ደግሞ ቅድስት ማርያም ውስጥ ለተነሣው የማህበሩ የተቃውሞ እንቅሥቃሴ አቡነ መልከ ጼዴቅ ቁርጡን እንዲነግሩላቸው ጥያቄውን ሆን ብለው አንስተውታል ይላሉ። የሲኖዶሱ ካህናትና ሰንበት ተማሪዎች ይህን እንቅሥቃሴ ለማክቸፍ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል ማህበሩ በሰሜን አሜሪካ የቆፈረው ጉድጓድ በርግጠኝነት እርሱ ሊገባበት እንደሚችል በርግጠኛነት ይናገራሉ።
 ኦርጋን በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የዝማሬ ዕቃ ሆኖ ማገልገሉን ባለሙያ በመጥፋቱ ቀዝቅዞ መቆየቱንና በንጉሥ አጼ ቴዎድሮስና ኃይለ ሥላሴ ዘመን እንደገና ይዘመርበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ከኦርጋን ማንኛውንም ድምጽ ከበሮንም ሆነ በገናን ማውጣት እየተቻለ ምዕራባውያንን በመጥላት ብቻ የሃይማኖት ጉዳይ አድርጎ መከራከር ምን ያህል ወደ ቁልቁለት እየሄድን እንደሆነ ያመለክታል። ስንዴያቸውን እየለመንን እየበላን ወደ ሃገራቸው ለመግባት አሳ እስኪበላን ድረስ እየሰጠምን፣ እነርሱ እንዲቀበሉን ስለት እየተሳልን፣ ነጻነት እንዲሰጡን በቤተ መንግሥታቸው በር ላይ እየተሰለፍን አሁንም እነርሱን መጥላታችን የበታችነት ስሜት ያጠቃን መሆኑን ያመለክታል እንጂ ኦርጋንስ ካሃገራቸው ካስገባናቸው ዕቃዎች አንዱ ነው። የማህበሩ አባላት ኦርጋን ሃይማኖትን እንደሚያስቀይር ያምናሉ፣ በኦርጋን ይዘምሩ የነበሩ ሰንበት ተማሪዎች ሁሉ ዛሬ ሙሉ ወንጌል ገብተዋል ይላሉ። ሰንበት ተማሪዎችን ወደ ሙሉ ወንጌል ያስገባችው ኦርጋን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱ ማለቂያ የሌለው የተረት ስብከትና የማህበረ ቅዱሳን ዱላ መሆኑ ማንም የሚስተው አይደለም። ዛሬ ኦርጋን ትተው እነ ምርትነሽ በክራር ሲዘምሩ ለምን መናፍቅ ተባሉ? ኦርጋን መናፍቅ የሚያደርግ ከሆነ ክራርም መናፍቅ ያደርጋል ማለት ነው? ጠባችሁ ከእውነት ጋር እንጂ ሌላ አለመሆኑን የታወቀ ነው። በሃያ አምስት ዓመት ውስጥ አሥር ሚሊዮን ሕዝብ ከኦርቶዶክስ ወጥቶ የሄደው በማህበሩ አማካኝነት በኦርጋን መዘመር ከቆመ በኋላ አይደለምን? ዶክተር መስፍን እና ቄስ ደጀኔ በፌስቡካቸው ኦርቶዶክስ ውስጥ ኦርጋን በመግባቱ ወጣቱ ወደ ፕሮቴስታንት ሄደ ብለው ጽፈዋል? ብዙ ሚሊዮን ቀነሰ የተባለው የናንተ ማሲንቆ ከጀመረ በኋላ አይደለምን? መሳሪያ ሰውን ሃይማኖት ያስቀይራል ብሎ የሚያስብ ትውልድ መኖሩ ሲታሰብ የኢትዮጵያ ዕዳ ገና ያላለቀ መሆኑን አመልካች ነው። ሰውን ከቤተ ክርስቲያን የሚያስወጣው ብልሹ አስተዳደር፣ እንዳይገለጥ የታገደው የወንጌል እውነት የኛ የአገልጋዮች አስመሳይነት ብቻ ነው።
  ለውሻ ከሮጡለት ይናከሳል ሞኝም ከሳቁለት ብዙ ያወራል እንደተባለው ለእንደዚህ ዓይነት የባለጌዎች ክፋት መንበርከክ ትልቅ ስሕተት ነውና የስደተኛው ሲኖዶስ አባቶች ከአቋማቸው እንደማይነቃነቁ እምነታችን ነው። የኦርጋን ጉዳይ ጉዳያችን ሆኖ ሳይሆን ትውልዱን በትክክለኛው መንገድ ለመምራት ግዴታ አቋም ያስፈልጋል ለማለት ነው። ብዙ ያልተፈታ ችግር እያለ ምንም ጥቅም የሌለውን የኦርጋንን ጉዳይ አንሥቶ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጣደፈውን ለማሳፈር በጥንቃቄ መጠበቅ ያስፈለጋል። ማህበሩ በከፈተው በዚህ አዲስ ጦርነት ላይ የሚያወጣቸውን እቅዶች ሁሉ እየተከታተልን መረጃ የምንሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናስታውቃለን።  ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ይበርቱ! ቡራኬዎ ይድረሰን! 

16 comments:

 1. Bemidir Sidetegna!!? Belayim Sidet? Papasum keneorganachew metifatachew new yasazinal!!!!!!

  ReplyDelete
 2. መቼ ነው በአቁዋማችሁ የምትቆሙት እናንተ እኮ የፕሮቴስታንቶች ተላላኪ ናችሁ። በፈጠራችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለማስጠላት ብላችሁ እራሳችሁን አታዋርዱ

  ReplyDelete
 3. የአይጥ ምስክር ድቢጥ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይጥ ማቅ፥ ድምቢጥ አንተ!

   Delete
 4. What are you saying, guys? It is not good to destruct the established tradition of the Ethiopian Orthodox Tewahido church. Please, don't act crazy.

  ReplyDelete
 5. Just full of trashes.

  ReplyDelete
 6. አንድ ትነቢት ልንገራችሁ በቅረብ ቀን ጠብቁ ሁሉም የዘራውን ያጨዳል ይህ የማይለወጥ እውነት ከማንም አይደለም ከእግዚአብሔር ነው ግዜው ሳይደርስ ንሰሀ መግባቱ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ የጌቶች ጌታ ፡ የንጉሶች ንጉስ፣ የአማልክት አምላክ የሆንከው ሰላማዊ ንጉስ ኢየሱስ ክርሰቶስ ሰላምህን አብዛልን ፍቅርህን አድለን በጨለማ ከመኖር በባርነት ከመገዛት ዋሽቶ ከማጣላት ለምነንህ ከማጣት የሃይማኖት አባት ሆኖ ስላምን ፍቅርን በሰዎች መካከል እንዲመጣ ከማድረግ ማራራቅ እኒህንና መሰል የዲያቢሎስ ስራዎችን ከመስራት ለሰማያዊ ሳይሆን ለምድራዊ በሬ ወለደ እያሉ ከሚጽፉ እንደ አባሰላማ ካሉ ብሎጎቸ ሩጫቸው ሁሉ የ666 ዘመን ለማፍጠን ከሚሰሩ የዲያቢሎስ ምረኮኞች ጠብቀህ የመንግስት ወራሾች አንተን ብቻ አወዳሾች እንድንሆን የቅድሰት ማርያም ምልጃ የቅዱሳን ተራዳይነት እና ጽሎት አይለየን ፡፡

  የአብረሃም የይሰሃቅ የያዕቆብ አምላክ ልቦናችንን ያብራልን
  አሜን !

  ReplyDelete
 7. ቀሲስ ፣ደጀኔ እኮ ቤቱን እንኳን በስርአት ያልመራ ሰው ነው ዲያቆን ተብየ ልጁ ሲጨፍር አድሮ ገብቶ የሚቀድስ።ሲጀመር እርሱና የሚየሚመራው ቤተክርስቲያን በ ኢትዪፂያው የሚመረሰው ሲኖዶስ ሊስት ውስጥ ስማቸው ስላልተገኘ ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ አለውቃችሁም ብለዋቸው ነው የተመለሱት።ቄስ ደጀነ ማህበረ ምናምንተን እንጂ የኢትዮፀጰያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይወክልም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ant gebz bwesthe yalewn satawta yelelawen yemtaye. Leb shewerara.
   Egziaber yerdahe.

   Delete
 8. ለመሆኑ በቅዳሴ ግዜ የፓትራርኩ እና የሊቀ ጳጳሱን ስም አለመጥራት የቅዳሴውን ስርዓት ማደስ አደለምን? የእነ ዶክተር ቀሲስ ዘበነ ለማና የማህበረ ቅዱሳን ገልለተኖች ቤተ ከርስቲያናት እነሆ በቅዳሴ ግዜ አይጠሩም። ይህ እምነቱም መቀየር አደለምን? ታድያስ ለምን ለኦርጋን መሳርያ ተዘመረበት ብለኝ ዘራፍ እንላለን። ለመሆኑ ለመላዊ የማህበረ ቅዱሳን አባላቱ ጥያቄ አለኝ ። የግብጽ ፤ የራሽያ ፤ የግርክ፤ የሶርያ አና የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ከርስትያን የምዘምሩት በኦርጋን እንጅ በከራርና በመሰንቆ አይደለም። ማቆች ዛሬ ህዝባችን ለማሞኘት ይፈጨረጨራሉ። የራሳቸው የቤተ ከርስቲያን ታሀድሶነት ሥራቸው ለራሳቸው ትክክል ነው። የሌላው ሰዉ መልካም ስራ ግን ሐጢአት ነው። በዘመናዊ መሳርያዎች መጠቀም ሐጢአት ነው ተብሎ በቅዱስ ቃሉ አልተጻፈም። ለምን በድምጽ ማጉያ እንጠቀማለን ? የፈረንጆች እንጅ የኦርቶዶክስ አባቶች በጥንት ግዜ አይጠቀሙትም ነበር።በኦርጋን መልካም ዝማረ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ሐጢአት ነው የምል ሰዉ ካለ በእውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃውን ለመላዉ ኦርቶዶክስ ያቅርብ ።

  ReplyDelete
 9. ere ene yenanten wushet mesmat astelagn

  ReplyDelete
 10. ክብር ለዕርሱ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሑን።አሜን፡የተረት መምህራንና ማቅ ምክንያት እና አዲስ ነገር እዬፈለጉ ሕዝብ ግራ ከማጋባት በሞት ጥላ ላለው ወገን እውነትን ስበኩ ፡ መኑ ጠቢብ ዘየሐስሶ ለእግዚአብሔር እኛም አዉቀናል ። አባ ሰላማን ያቆይልን፡

  ReplyDelete
 11. I am not sure we have a lot of issue we can or Abune can address instead of mentioning about this was not the right time with all do respect I think he has made a big mistake can we do something right instead of dividing us with a critical time we all can be prying together instead we are dividing with this idea it should it be the issue at this time. what about this Abatoch do something good before it is to late. May be this is new to most of us abune Melkesadik has seen may be 3 or 4 time when people are looking for small food and drink so they can have one more day in there life or someone they love dear like son and daughter but they are unable to give that special person small drink so she or he can live one more day. this is the subject we all need to get engaged called Rehabe Temate

  ReplyDelete
 12. ሕዝቅኤል ይከውነክሙ ትእምርተ(ነቢይ ምልክት(አብነት)ይሆናችኋል)እንደተባለው ቀደምት ሽማግሎች አልቀው አንድ አባት መልከ ጼዴቅ ብቻ ቢቀሩ አሁን ማን ይሙት እንዲህ ይባላል አይጣል ነው ይህ ጠማማ ትውልድ በጥመቱ ከፈጣሪ መለየቱን ጠንቅቆ ሳይረዳ አንዳንድ ጊዜ ኦርጋን በሌላ ጊዜ ካንጀት ሳይሆን ካንገት የሚጠራቸውን ጻድቃን በማሳበብ በየውሀን አባቶች ላይ የሽብር ፈጠራ ሲያራምድ ይታያል፤ መሣሪያ አንግበው አንገት እየቀነጠሱ ዐለምን ከንቱ(Demoralized)ካደርጉ ቡድኖች በምን ይለያል? ያው አንድ ነው ሥጋውያኑ ሥጋን መንፈሳውያኑ ነፍስን በማጥፋት ላይ ይገኛሉ እናም ከፊተኛው የኋለኛው የከፋ ይሆናልና በሽማግሎች ባትረግርሙ ይብጃችኋል ነስሑ ወእመኑ

  ReplyDelete
 13. Source: www.zenatewahedo.org (February 6/2016)
  የማኅበረ ቅዱሳን ክስ እና የልዩነታችን ምንጭ

  በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መልአኩ ባወቀ

  ReplyDelete
 14. https://www.youtube.com/watch?v=RFyJY5ytM1Q

  ReplyDelete