Thursday, January 28, 2016

መንፈሳዊ ኮሌጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ላቀረቡት ክስ ፓትርያርኩ አንጀት አርስ መመሪያ ሰጡበሌለው ሥልጣን መንፈሳዊ ኮሌጆችን የመናፍቃን መፈልፈያዎች ናቸው ሲል በጅምላ በወነጀላቸውና ራሱን ከሕግ በላይ በማድረግ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እኩይ ሥራውን እየሠራ ባለው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ መንፈሳዊ ኮሌጆቹ ላቀረቡት ክስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከፍተኛ አድናቆት የተቸረውንና ተገቢና ጠንካራ አቋማቸው የተንጸባረቀበትን መመሪያ ሰጡ፡፡ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ይህን ድንቅ መመሪያ የሰጡት ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለሚገኙት ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲሁም መቀሌ ለሚገኘው ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻቸው በጻፉት ደብዳቤ ነው፡፡
ቅዱስነታቸው በደብዳቤያቸው እንደ ገለጹት “ማህበረ ቅዱሳን የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋትና ቤተክርስቲያንን በማተራመስ ቀኖና የለሽ ሥርዓት ሲከተል ይስተዋላል” ሲሉ የማኅበሩን የሚታይ ሕገወጥ አካሄድ ገልጸዋል፡፡ የሚያሳዝነው እስካሁን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያወጣው ደንብና መመሪያ በማኅበሩ በኩል በተደጋጋሚ እየተጣሰና እየፈረሰ ሳለ አንዳንድ ጳጳሳት በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ለወሰኑት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና መመሪያ ሳይሆን ለማኅበሩ መወገናቸው ማኅበሩ የልብ ልብ እንዲሰማው እንዳደረገ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ በቀጣይ ሊወሰድ የሚገባው እርምጃ የማያዳግምና በተደጋጋሚ ሲጣስና ሲፈርስ የነበረውን የሲኖዶስን ውሳኔ የሚያስከብር መሆን እንዳለበት የብዙዎች ተስፋ ነው፡፡ 

ቅዱስነታቸው በመመሪያቸው አክለው እንደተናገሩት “ማኅበረ ቅዱሳን ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖትና የሥርዓት ተፋልሶ ሳይፈተሽ በአንድ ወቅት ራሱ አርቆና አዘጋጅቶ ባቀረበው ደምብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ሕጋዊ ማኅበር ነኝ በማለት በቤተክርስቲያን መዋቅር ልክ ከላይ እስከ ታች መዋቅር ዘርግቶ ከቤተክርስቲያን አስተዳደር ውጪ የሆነ ሌላ ቤተክርስቲያን አከል ተቅዋም መሥርቶ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ነው” በማለት ማኅበሩ በግርግር ገብቶ ለቤተክርስቲያን አስተዳደር የማይገዛ፣ የቤተክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተንና የሚገዳደር ተቋም ሆኖ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ፓትርያርኩ በዚሁ ደብዳቤያቸው ላይ እንዳተቱት ማህበሩ “ከኦርቶዶክስ ቀኖና ውጪ በመዋቅር ለታቀፉ ስፍር ቁጥር የሌላቸውና የተበታተኑ ማህበራት እንዲፈጠሩና ከቅጽረ ቤተክርቲያን ውጪ በየመንደሩና በየአዳራሹ እንዲሰበሰቡ በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ባህልን እንዲለማመዱ፣ እንደዚሁም ከኦርቶዶክስ ቀኖና እንዲያፈነግጡ መጥፎ በር በመክፈት የነገይቱን ቤተክርስቲያን ሰው አልባ የሚያደርግ ሁኔታ ፈጥሯል” ሲሉ ማኅበሩ ራሱን ብቸኛ ኦርቶዶክሳዊ አድርጎ ለማቅረብ የሄደባቸው መንገዶች ከኦርቶዶክስ ቀኖና ያፈነገጡ ለትውልዱ መጥፎ አርኣያ የሚሆኑ ድርጊቶች መሆናቸውንና ቤተ ክርስቲያኗን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እያወካት እንዳለ የሚያሳዩትን የማኅበሩን ጉልሕ አስራ ሁለት ጥፋቶች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል በሌለው ሥልጣን ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጪ የጾም አዋጅን ማወጁ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች ስም ከፍተኛ ገንዘብ መሰብሰቡና ለድብቅ ዓለማው ማዋሉ፣ ከቤተክርስቲያን የሚሰጠውን አመራር አልቀበል ማለቱ፣ የቤተክርስቲያንን አመራር አካላት በመከፋፈልና የቤተክርስቲያንን አንድነት መፈታተኑና ራሱን ብቸኛና ጠንካራ አስመስሎ ማቅረቡ፣ በሃይማኖታዊ መርሕ ሳይሆን በረቀቀ የስለላ ሥራ የተሰማራ መሆኑና ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሊቃውንትና ካህናት ስም በማጥፋት ያለ ዕረፍት እየሠራ መሆኑ፣ በውጭ አገር በማኅበሩ ስም ቤተ ክርስቲያንን መትከሉና የማኅበር ቤተ ክርስቲያንን መፍጠሩ፣ ከቤተክርስቲያን መዋቅር ውጪ ወጣቱ ትውልድ በተበታተነ አደረጃጀት እንዲገኝ በማድረግ “የነገዋ ቤተ ክርስቲያን የተበታተነች አቅመ ደካማ ቤተክርስቲያን እንድትሆን በማድረግ በጣም ጎጂ ባህልን ማለማመዱን”፣ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ ያለ በቂ ትምህርትና ስሙ ተለይቶ ባልታወቀ ቤተክርስቲያን ለአባላቱ የጅምላ ክህነት እያሰጠ ለድብቅ ዓላመው እየተጠቀመበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡    
እንደ ግብር አባቱ እንደ ዲያብሎስ የወንድሞች ከሳሽ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ በከፍተኛ የሃይማኖት ሕጸጽ ውስጥ እየዳከረና ብዙዎችን በሐሰተኛና በልቦለድ ወንጌሉ እያሳተ ባለበት ሁኔታ ሌሎችን መናፍቅ ብሎ የመወንጀል ሞራልም ብቃትም የሌለው ስብስብ መሆኑ ቢታወቅም፣ እርሱ ግን ደረቱን ነፍቶ ኮሌጆቹን የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው ያለበት መንገድ በሌለው ሥልጣንና ትክክለኛውን መርሕ ባልተከተለ ሁኔታ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም “ማኅበሩ በቂ መረጃ ካለው ይህንን ቀኖናዊ ሕጋዊና ትክክለኛ አካሄድ የማይከተልበት ሁኔታ ምን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡” ካሉ በኋላ “የገበያ ግርግር …” እንደሚባለው በግርግር የኮሌጆቹን ስም አጥፍቶ “ያልተፈቀደውና በሆቴል ውስጥ ተመርቆ የተከፈተው ዕውቅና የለሽ የራሱ ት/ቤትን ለማስፋፋት ጥሩ ዘዴ መስሎ ስለታየው ይመስላል ከማለት ውጪ ሌላ ምክንያት ሊኖረው አይችልም” በማለት ገልጸዋል፡፡ በሆቴል ያስመረቀው የነጻ ትምህርት ዕድል ዜና በፊት ገጽ የኮሌጆቹን ስም ያጠፋበት ዘገባ ደግሞ በውስጥ ገጾች በአንድ ጋዜጣ ላይ መውጣታቸው አጋጣሚ ሳይሆን ታስቦ የተደረገ ለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡
በመጨረሻም “እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የመኖርና ያመኖር ጥያቄ ስለሆነ የኮሌጆቹን ቀጣይ ህልውና ዘላቂነት ለመጠበቅ የተጠናከረ የተደራጀና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት ማኅበሩ በቤተክርስቲያንና በት/ቤቶቿ ላይ የቀሰራቸውን የጥፋት ጣቶቹን መልሶ ወደኪሱ እስኪከትና ለቤተክርስቲያን ሉዓላዊ ሕግ ተገዢ እስኪሆን ድረስ የማያቋርጥ ትግል በማድረግ በንቃት መከታተል ይጠበቅባችኋል፡፡” በማለት የተጀመረው ማኅበረ ቅዱሳንን አደብ የማስገዛት እንቅስቃሴ አንድ ጊዜ ድምፅን በማሰማት የሚቆም መሆን እንደሌለበትና እስከመጨረሻው ትግሉ መቀጠል እንዳለበት መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ለዚህ እውን መሆን በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ከጎናቸው እንደምትሆን አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ይህን የፓትርያርኩን መመሪያ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ለንባብ የበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በስፋት የዘገበ ሲሆን ለወትሮው ቤተክርስቲያንን የተመለከተ የሰንደቅን ዘገባ እንዳለ በመለጠፍ የምትታወቀው ሐራ ይህን ዘገባ የሰንደቅን ዘገባ ትታ በራሷ መንገድ መመሪያውን በማጥላላትና ስለዘገባው ከመናገር ይልቅ እነእገሌ ናቸው ያዘጋጁት በማለት ስም በማጥፋት ማቅረቡን መርጣለች፡፡ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ተስፋዬ ቢሆነኝ ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጠው አስተያየት ውስጥም ቢሆን ራስን ከማጽደቅና ትክክለኛ አድርጎ ከማቅረብ ውጪ ቢያንስ እንኳ በኮሌጆቹ ላይ ማኅበሩ በጻፈው ስም አጥፊ ጽሑፍ ላይ ጥፋት እንደተፈጸመ ለማመንም ሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ አልደፈረም፡፡ ይህም የሚያሳየው ማኅበሩ ምን ያህል በትዕቢት እንዳበጠና ራሱን እንደማይሳሳት ፍጹም ተቋም አድርጎ እንደሚመለከት ነው፡፡
ደብዳቤው እነሆ!


20 comments:

 1. እኔ የሚገርመኝ ነገር በቤተ ክርስቲያኒቱ ዉስጥ ትልቁን የአመራር ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ሆነዉ ሳለ የቀድሞዉም ሆነ የአሁኑ ፓትሪያሪክ በማቅ አባላትና ደጋፊዎች ለምን እንደሚብጠለጠሉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር በቀባዉ ላይ አፍክን አትክፈት የሚለዉን መለኮታዊ ትዕዛዝ እየጣሱ ሽብር መንዛትና የነሱን ዉንብድና የተቃወሙ አባቶችን መክሰስ ለወንበዴዉ ማህበርና ደጋፊዎች የት ያደርሳቸዉ ይሆን?

  ReplyDelete
 2. እንዲያው ሥለጮሃችሁ ማኅበሩ አይፈርስም እግዚአብሔር ካልፈቀደ ግን አንድም ቀን አያድርም ለነገሩ የእግዚአብሔርን መልካም ፈቃድ መቼ ታውቁና

  ReplyDelete
 3. የቤተ ክርሰቲያንን ውድቀቷንኗ ክፍፍሏን ለምትሹ ለናንተ/መናፍቃን/... በናንተው ቋንቋ ለተጻፈው ለዚህ ደብዳቤ እንኳን ደስ አላችሁ.....

  ReplyDelete
 4. ጸልዩ በእንተ አባ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘሀገሪትነ ኢትዮጵያ።
  ብለን በደግ እንነሳና ለምን ቢሉ ቅን መሆን ስለሚገባን ብሎም ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ስለሚያዘን አንድም ከፍ ብሎ ትችት ለመሰንዘር ታናሽነታችን ስለሚያስጨንቀን ከሁሉ በላይ ክፉን በደግ ማሸነፍ ከጌታችን ስለተማር አቤቱ ይቅር በለን እንላለን።ግን ሁሉም ክርስቲያን ለእምነቱ ጳጳስ(ጠባቂ በሚል ዐውድ) ነው በሚል ቅንዓተ ቤተክርስቲያን አገብሮን የተሰማንን ቅሬታ መግለጥ ይገባናል።ቅዱስነታቸው የተሰማቸውን ወይም የፈለጉትን ወይም ሌሎች መካሪዎቻቸው የፈለጉትን ሳይደብቁ ነግረውናል። በዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው ።ሳይነግሩን የፈለጉትን ለማድረግ በድብቅ መንቀሳቀስ ይችሉ ነበርና(እንደ አቡነ ጳውሎስ?)።
  ከምስጋና በመለስ ከቅዱስነታቸው ጀርባ ላሉ መካሪዎች ወይም “ልማታዊ” የቤተክህነቱ ሰዎች ማለት የሚገባንን ነገር ያለ ይመስለኛል። ማኅበረ ቅዱሳን እንዲፈርስ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜም ስትደክሙ ስትመክሩ ስታሴሩ አሳልፋችሁ ስትሰጡ አልነበረም ወይ?የሚቻል ነገር እንዳልሆነ አላያችሁትም ወይ ብለን እንጠይቃቸዋለን።ዛሬ ከትናንቱ ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል ሥርም ሰደዋል። እናንተም የምትከተሉት ስልት ደግሞ ደካማ ነው። ስቅሎ ስቅሎ ይፍረስ ይውደም ይታሰር በቁጥጥር ሥር ይዋል ብቻ!!።የምትከሱበት ምክንያት ራሱ ውሸት የሞላበት ሸፍጥ ያለበትና የቅናት እንደሆነ ከንግግራችሁ ይታወቃል።በአንጻሩ ማኅበሩ ደግሞ ልታፈርሱት ቀርቶ ልትጨብጡት በማትችሉት ደረጃ ከመዋቅርነት ወደ ሐሳብነት ተቀይሯል።በሥራው አሳምኗል።በመዋቅር ሰፍቷል።በእውቀት በስሏል።በፈተና እያለፈ ተምሯል። በቦታም አይወሰንም(በሁሉም የአገሪቱ ክልል፣በአገርም በውጭም፣ከአጥቢያ እስከ ሲኖዶስ፣ከወጣት እስከ አዛውንት፣ከምዕመን እስከ መነኮሳት፣ከደብር እስከ ገዳማት) ሥር ሰዷል ምኑን ነው የምታፈርሱት?ዛሬ ዛሬ በየአጥቢው በቁርጠኝነት ተሃድሶንና ሙሰኝነትን ለማስቆም የሚታገል ምዕመን “ማኅበረ ቅዱሳን” አባል ተደርጎ የሚቆጠረው ለምንድነው ስንል ከመዋቅሩ በላይ ሐሳቡ ገዢ ስለሆነ ነው።ይህ ሐሳብ ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ወካህናት ሐሳብ ነው።ሐሳቡም ቤተክርስቲያንን በገንዘብ በእውቀት በጊዜ በጉልበት ማገልገል ይባላል።ይህን ሐሳብ ታግላችሁ ታሸንፋላችሁ? ፍርድ የእግዚአብሔር ነውና አብረን እንጠብቅ።

  ReplyDelete
 5. ከፍተኛ አድናቆት የተቸረውንና ተገቢና ጠንካራ አቋማቸው የተንጸባረቀበትን መመሪያ ሰጡ!!!!!!!!!!!!!!!!!!! Maferiawoch! were agengachihu? indenante yewerede were!!!!!!!iwunetinet yeraqew were!

  ReplyDelete
 6. እንደ ግብር አባቱ እንደ ዲያብሎስ የወንድሞች ከሳሽ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ በከፍተኛ የሃይማኖት ሕጸጽ ውስጥ እየዳከረና ብዙዎችን በሐሰተኛና በልቦለድ ወንጌሉ እያሳተ ባለበት ሁኔታ ሌሎችን መናፍቅ ብሎ የመወንጀል ሞራልም ብቃትም የሌለው ስብስብ መሆኑ ቢታወቅም

  ReplyDelete
 7. ማህበረ ቅዱሳን ቀልብ የሌለዉ ድርጅት ነዉ፤ከተመሰረተ ጀምሮ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ መዝናል፡፡ ሁሌም በክስላይ የተመሰረተ መሆኑ ደግሞ በጣም ያሳዝናል፤ከስምንት አመታት በፊት ለማህበሩ መረጃ አቀባይ ሆኜ ሰርቻለዉ፤ በጊዜዉ እንዲ ኣይነት ነገር ይቅር ተብሎ ተወስኖ ነበር፤ነገር ግን ያዉ ነገር ቀጥሎ ከተሃድሶ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባቱ ማሕበሩን ጎድቶታል አዉንስ ፈረቻለው መፍረሱ ነዉ መሰለኝ? ለዚ ሁሉ ምክንያት ግልጽ ራእይኛ ግብ ማህበሩ የለዉም ማለት ይቻላል፤ ሁሌ ግጭት በመፈጠር ቢቻ ጊዜዉን ኢያጠፋ ይገኛል፤ ሊታሰብበት የገባል እላለዉ ከቀድሞ አባል፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. keznb mar aytebekim!!!

   Delete
 8. ተሃድሶ ኢየገሰገሰ ኢየ ጨመረ ነዉ፤ መሓበረ ቅዱሳን ኢየ ኮሰመነ ዓላማ አልባ መሆኑ ኢየተጋለጠ ቀጥሏል……….

  ReplyDelete


 9. ማኅበረቅዱሳን ስለኮሌጆች ያወጣው ዘገባ መስመር ያለፈ ነበር፡፡ተሐድሶን መዋጋት ማለት ተቋማትን ማራከስ ማለት አይደለም፡፡ከኮሌጆቹ ለቀረበው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ያልደፈረው የማኅበሩ ጸሐፊ ለፌስቡክ፣ለብሎግና ለጋዜጣ ፕሮፖጋንዳ የሚሆን ጊዜ ግን በአያሌው ተትረፍርፎለታል፡፡ፓትርያርኩ ጋር መጀመሪያ አካባቢ የነበራችሁ መልካም ግንኙነት በሂደት የተበላሸው በዚሁ ግብዝ ‹‹እኔ ብቻ ሀቀኛ ኦርቶዶክሳዊ›› የሚል ስሑትና እጅግ አግላይ ጎዳና ነው፡፡አሁንም ችግሩን ማድፈንፈንና ስለራስ ስብስብ ብፅዕና ተሰባስቦ መደስኮር አይጠቅምም፡፡ፓትርያርኩን ለማነጋገር ጠይቃችሁ አለመፈቀዱን በጋዜጣ ሳይሆን በአካል ቅረቡና አረጋግጡ፡፡ፈቃደኛ ካልሆኑ የጠየቃችሁበትን ደብዳቤ አሳዩንና አብረናችሁ እንሰለፍ፡፡እድሜ ልክ ፓትርያርክና ተቋማትን በመገዳደር ከፍ ብሎ ካለኔ ንጹሕ የለም የሚል ጉዞ ከተመቻችሁ ቀጥሉበት፡፡

  ነገር ግን ራሳችሁን ከነዚህ በጅምላ ከምትፈርጇቸው አባቶችና ተቋማት ለሚመጣ አስተዳደራዊ ምላሽ ዝግጁ ማድረጉን አትዘንጉ፡፡ወሬና ልዩነት እያጋጋሉ ራስን ከመቆለል ሳይመሽ ተቀራርቦና ተመካክሮ ልዩነትን ለመፍታት እስከ ጥግ መሄድ ነው መፍትሄው፡፡ሺህ ቲፎዞ በሳይበርና በጋዜጣ ቢንጫጫ ጥቅም የለውም፡፡ነባሩም አባል፣ወጣኒውም ቲፎዞውም የራሱን ስብስብ እየቆለለ በየሚዲያው መሪና ተቋም ማራከሱ ውሃ ወቀጣ ነው፡፡ፓትርያርክ ማትያስን ሺህ ጊዜ ብታገላብጡዋቸው የሃይማኖት ህጸጽ አታገኙባቸውም፡፡ያለው የአስተዳደር ችግር ነው፡፡እሱ ደግሞ በሚዲያ ወከባና በቲፎዞ ጫጫታ ሳይሆን ተቀራርቦ እንደ አባትና ልጅ በመነጋገር ነው የሚፈታው፡፡‹‹እንደ ክርስቶስ ለእውነት ተሰቀልን፣እንደ ዮሐንስ ለቁርጥ ቀን ቀራንዮ ተገኘን›› እያሉ በእነዳንኤል ክብረት ጽሑፍ በመከለል የራስን አበሳ ሸፍኖ የሌላውን ብቻ ከማጉላት ተቀራርባችሁ በውይይት ፍቱት፡፡

  ReplyDelete
 10. Yehamana Tehadso legizew medeset leholaw Merdokyos Desta New!!! Feraju fetahi betsidik Nigusu Kirstos Newna!!!

  ReplyDelete
 11. የግል አስተያየት
  (ሲኖዶሱን ማህበረ ቅዱሳን ይረከበው ወይ ሲኖዶሱ ማህበረቅዱሳንን ይውረሰው!!!!!!????)
  ትንታኔ ፡- እንዲህ ልል የቻልኩበት ምክንያት አለኝ፡፡
  በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የዕምነት ተቋማት በሀብታም በዕውቀትም በምዕመናን ብዛትም በማኔጅመንትም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን የሚያክል የለም፡፡ በአፍሪካ ኢትዮጵያ ደግሞ በምዕመናን ብዛትና በሀብት መጠን ኦርቶዶክስን የሚያክል የለም፡፡
  (ንጽጽር ))
  (1ኛ.ካቶሊክ ቤተክርስቲያን )ካህናቶቿን በዘመናዊና በመንፈሳዊ ዕውቀት ኮትኩታ በሚገባ አስተምራ ያላትን ሀብት በሚገባ ማኔጅ እያደረገች አገልጋዮቿን ቲዎሎጂ ከገቡ ጊዜ ጀምራ ደመዎዝ እየከፈለች አስመርቃ መኪና ከነ ቁልፋ አስረክባ በተማሩት መንፈሳዊ እና ዘመናዊ ዕውቀት ቤተክርስቲያናቸውን ሳይቸገሩ በዓለምአቀፍ ደረጃ እንዲያገለግሉ ታደርጋለች፡፡
  (2ኛ፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን )
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲጀመር ያሁኑን አያድርገውና ትምህርት ሚኒስቴርን የመሠረተች ቀደምት የዕውቀት ምንጭ እንደ ነበረች ሁላችንም እናውቃለን ፡፡
  አሁን የምትገኝ በት ሁኔታ እጅግ በጣም በሚያሳዝን ደረጃ ላይ ነው
  (ችግር 1:- አገልጋይ ካህናቶቿ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ እና ከዘመናዊ ትምህርት ጋራ 99% የማይተዋወቁ መሆናቸው
  (ችግር2:-) በመላ ኢትዮጵያ ከገጠር እስከ ከተማ ያላት ግዙፍ ሀብት /መሬት ሳይለማ በዕውቀት ችግር ብቻ ተዳፍኖ ካህናት በችግር መጠበሳቸው
  (ችግር 3) ፡- ያላትን ሀብት በዘመናዊ መልኩ መጠቀም ባለመቻሏ ለመንግት ጡረተኞች በሰበካ ጉባዔና ልማት ኮሚቴ ስም ማስመዝበሯ
  (ችግር4) ገንዘብ አውጥታ በዘመናዊ መልክ በ3ቱ ቲዎሎጂ ያስተማረቻቸውን ምሁራን በተገቢው ሁኔታ ቦታ ባለመስጠቷ ለመንግስት እና ለፕሮቴስታንት መዳረጓ
  (ችግር 5):- በዘመናዊ ትምህርት እየተዋጠ ያለውን መንፈሳዊ ትምህርት ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ዘመኑን የዋጀ መንፈሳዊ የትምህርት ፓሊሲ አለመቅረጿ ወዘተ......?
  እና የመሳሰለው ችግር እየታዬ ሲሆን
  የሲኖዶሱ 99%አባላት ከዘመኑ ትምህርት ጋር የማይተዋወቁ 1+1=2 እንኳን የማይሉ በመሆናቸው በራሳቸው ጥረት መንፈሳዊ ትምህርትንና ዘመናዊውን ተምህርት ተምረው ዘመኑን የዋጁ ሊቃውንትን ወደ ቢሮ የማያስገቡ ናቸው፡፡ ምኸክንያቱም ነገ የተማረ ከበዛ እንገፋለን ብለው ስለሚሰጉ የሚያስጠጉትና የሚቀጥሩት ደንቆሮውን ነው፡፡
  ይሔም በመሆኑ ከቤተክርስቲያኗ ጳጳሳት እንደ እነ አባጢሞቴዎስ አባ ገሪማ አባ ማትያስ ነፍሳቸውን ይማረውና አቡነ ጳውሎስን የመሣሠሉ ሁለቱን ትምህርት የተማሩትን ሊቃውንት አብዛኞች ጳጳሳት የተለያየ ስም በመስጠት ያንቋሽሿቸዋል፡፡ይሔም ያለማዎቅ ውጤት ነው፡፡

  በዚህም ምክንያት የቤተክርስቲያን ታላላቅ ወሳኝ ምሁራንን እና የቲዎሎጂ ምሩቃንን በማራቅ
  በሙዝና በማንጎ እየተ ታለሉ እጅ ጠምዛዥ የሰንበት ተማሪ መሳይ የፖለቲካ አጀንዳ ያለው አደገኛ ማህበር እንዲመሠረት አድርገው ቤተክርስቲያኗን እያስበጠበጧት ይገኛሉ ፡፡
  አማራ ሲተርት(( ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆሞ ለማውረድ ይቸግራል ))
  እንዳለው
  ስለዚህ ይህ ማህበር የቤተክርስቲያኗን ሀብት እያጋበሰ ከሲኖዶሱ በልጦ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ህንጻ ገንብቶ ሲኖዶሱን ከላይ ሆኖ ቁልቁል እየተዘባበተበት ይገኛል፡፡
  ታዲያ ይህ ሲኖዶስ ወይ በማህበሩ ይወረስ
  ወይም ራሱን በዘመናዊ አሠራር አጠናክሮ ማህበራትን ይውረስ !!!.
  አስተያይት ስጡ መሳደብ የሰይጣን ሥራ ነው ፡፡ አሳማኝ ሀሳብ ካላችሁ እንወያይበት ፡፡  ReplyDelete
 12. ጴንጤው መናፍቅ እንኳን አንጀትህ ራሰ። አንድ ቀን እንኳን ሳይደርስ ለምን ተጠራርገህ ትባረራለህ?

  ReplyDelete
 13. Yezwayu Abune Gorgorios || Beatsede Nefis Sayawgzoachew yikeral ?? Gorgori Yedekemubet mahiber newna !!! Patriarku yihin Tarik yaweku alemeselegnm? Weyo ? Letehadsona hama?

  ReplyDelete
 14. "ግን ሁሉም ክርስቲያን ለእምነቱ ጳጳስ(ጠባቂ በሚል ዐውድ) ነው" = we don't need any papas; we are papas

  "በአንጻሩ ማኅበሩ ደግሞ ልታፈርሱት ቀርቶ ልትጨብጡት በማትችሉት ደረጃ ከመዋቅርነት ወደ ሐሳብነት ተቀይሯል" = we don't care if the church is destroyed as long as MK LIVES. and MK IS THE CURCH

  ReplyDelete
  Replies
  1. yihe new yemecheresah alamachu

   Delete
 15. Menafik mk መናፍቅ ማቅ።

  ReplyDelete
 16. እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ

  ReplyDelete
 17. The socalled mahibrekidusan is ceaselessly humilating the true church servants at the expense of its financial motifs and ambition to control the EOTC and privatize all what belongs to the church.To this end, this profitable organizations doing its best in scolding church servants and defaming them all the time since its establishment.

  ReplyDelete