Saturday, January 30, 2016

የመካነ ሕያዋን ጐፋ ገብርኤል ካቴድራል ታሪክ እያበላሹ ያሉትን ሰባኪዎች በመጋበዙ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

Read in PDF

በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ሥር ከወደቁት አድባራት መካከል አንዱ ለሆነው የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ከን/ስ/ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈ፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው ከአ/አ ሀገረ ስብከት እይታ ውጪ ለመሄድ ብሎም የቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ባልጠበቀ መልኩ ፈቃድ ሳይኖራቸውና የቤተክርስቲያንን መዋቅር ባልጠበቀና የቅዱስ ሲኖዶስን ትእዛዝ በመተላለፍ የማቅን አጀንዳ ለማስፈጸም ሌተቀን የሚተጉትን ያረጋል አበጋዝንና አባይነህ ካሴን ጋብዘው አባቶችን በተለመደው በላፕቶፕና በፕሮጀክተር ሲያሰድቡ በማምሸታቸው ነው፡፡ ደብዳቤው ከዚህ ቀደም መዋቅሩን ባልጠበቀ አሰራር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዳይሰጡ በቁጥር 1177/482/08 በቀን 27/3/08 ደብዳቤ ጽፎ የነበረ መሆኑን አስታውሶ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መመሪያው መጣሱን አመልክቷል፡፡ እነዚህ የማቅ አገልጋዮች በሌላቸው ሥልጣንና የስብከት ፈቃድ በሙስናና በሌላም ነውረኛ ሥራ ያንበረከኳቸውን የደብሩን አስተዳዳሪ መላከ ገነት አባ ገ/ሥላሴ ጠባይን በመጠቀም ነው ህገወጥ ድርጊቱን የፈጸሙት፡፡
ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው አባ ገ/ሥላሴ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጽሙ አለቆች አንዱ ቢሆኑም የማቅ ሚዲያ ሐራ ግን አንድም ጊዜ ስማቸውን አንሥቶ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም ለማኅበረ ቅዱሳን ጥቅም ሲል የሲኖዶስን ውሳኔ ጭምር እየጣሰ መድረኩን የሚያመቻችና ተገቢውን ድጋፍ ለማኅበሩ የሚያደርግ አለቃና ጸሐፊ ወይም መሰል ባለሥልጣን የቱንም ያህል በሙስና ቢነቅዝ የቱንም ያህል የስነምግባር ችግር ቢኖርበት በማቅ ዓይን እርሱ በሃይማኖቱ የጸና በምግባሩ የቀና ንጹሕ ነውና፡፡

ለማህበረ ቅዱሳን ጥቅም ሲባል የሲኖዶስ መመሪያ የተጣሰበት የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ እጅግ ከሚጠላቸው አብያተ ክርስቲያናት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይህም የሆነበት አንዱ ምክንያት ሁለተኛው የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ በራሳቸው ገንዘብ ያሳነጹት በመሆ ነው፡፡ ታዲያ ይህን ከማቅ ጋር ምን ያገናኘዋል? ቢባል ቅዱስነታቸው በደርግ ክስ አዘጋጅቶ፣ ተፈራርሞ፣ አጨብጭቦ  ማስያዝ ጀምሮ እስከ ማስገደል በደም የታጠበ እጁ ያለበት የዛሬው የማህበረ ቅዱሳን አባቶች የቀድሞዎቹ የተሃድሶ ኮሚቴ ተብለው የተዋቀሩ ዘመዶቹ በግድያው እጃቸው ስላለበት ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የዜና ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅ የ60 ዓመቱ አዛውንት በ10 ዓመቱ ህፃን ዘለፈ በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ እንደገለፀው ማኅበረ ዱሳን አሁን የያዘውን ስም ክርስትና ወደ ዝዋይ ወረዶ ከማግኘቱ በፊት የሁለተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያንን ፓትርያርክ አባትነት ላለመቀበል የተቋቋመ ቡድን ነበር በማለት መግለጹ ይታወሳል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ መልኩ ብፁዕ ወቅዱስ ቡነ ቴዎፍሎስ ደም ያለበት ማህበር ስለሆነ የእሳቸው ታሪክ ያለበትን ማንኛውንም ነገር አይዘክርም ከማጥፋት ወደ ኋላ አይልም፡፡ ለዚህ ነው የስንት ጳጳሳትን ታሪክ በሐመር መጽሔትና በስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ወጣ እስካሁን ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰማዕት የተባሉትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎሎስን ታሪክ የሚዝለው፡፡ ከዚህ አንፃር አሁን መዘክራቸው ያለው ጐፋ መካነ ሕያዋን ገብርኤል ብቻ ስለሆነ ከዓመት በፊት ማቅ በአዲስ አበባ ብቸኛ ማዕከል ለማድረግ አስቦ በዚያ ባለ 5 ፎቅ ጽ/ቤት ለማሠራት ካቴድራሉን የተጠቀመው፡፡ ዕቅዱ ለጊዜው ቢከሽፍም ለዚህ መጠቀሚያ ያደረገው መላከ ገነት አባ ገ/ሥላሴ ጠባይን ነበር፡፡ የቀድሞ አለ አባ ኃይለ መለኮት ተጣጥረው ቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት የሚገኘውን አደባባይ አሠርተው ውልታቸውን ለማቆም ጫፍ ደርሰው የነበረ ሲሆን በዚህ እንቅልፍ ያጣውና ደም የለበሰው የማቅ አይን የወቅቱ ወዳጁን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን አባ ቀውስ ስን ተገን አድር ውልቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ እንዳይቆም አስደረገ፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሐውልት ቢቆም ሕያው ምስክር ሆኖ የሚከሰው በግድያቸው እጁን የነከረው ማቅ ስለሆነ ይህ እንዲሆን በፍጹም አይፈልግም፡፡
አሁን ያሉት አለቃ አባ ገ/ሥላሴ ጠባይ ምክትል የሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበሩ ይባቸዋለሁ ከሚለው ነውረኛ ሥራ የተነሳ ቦታውን የማቅ መጫወቻ እደረጉት ይገኛሉ፡፡ ይህ ግለሰብ አለቃውን አድርግ ያላቸውን ሁሉ ከማድረግ ወደ እንደማይሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ይናገራሉ፡፡ አባ ገ/ሥላሴ እንደ ቀድሞው አለቃ አባ ሃይ መለኮት ታሪክ መሠራት ሲችሉ የብፁዕ ወቅዱስ ቡነ ቴዎፍሎስ ታሪክ በመቅበሩ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ እየተወጡ በመሆኑ ብዙዎች ያዘኑ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ የሁለተኛውን ታሪክ ሠሪ ፓትርያርክ መታሰቢያ ሐውልት ማቆም ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሁም ከሀገረ ስብከቱ የሚጠበቅ ተግባር ነው እንላለን፡፡ በነውረኛ ሥራቸው ለማቅ እየገበሩና ቤተክርስቲያኒቱን ለማቅ እየሸጡ ያሉትን እንደ አባ ገ/ሥላሴ ያሉ ሙሰኞች ላይ ደግሞ ተገቢው የእርምት እርምጃ መውሰድ ይገባል፡፡

7 comments:

 1. wey gude yiche maheber min yisalatal? boteboteche eko.

  ReplyDelete
 2. ha ha you guys are so funny.. sew sitshewudu enkuan tinikake atadergum.....firmawun yeferemew sint sew new..ene endemitayegn 3 yeteleyaye feramiwoch nachew yeferemut...kiletamoch

  ReplyDelete
 3. Yemewgiawin betir bitikawem lante yibsal !!? Seif lay kamachual?

  ReplyDelete
 4. ehesa min tasebale sinodos hegihe lemaheberewa ayseram malet new

  ReplyDelete
 5. መረጃችሁ ሁልጊዜ ብስልና ጥሬ ነው፡፡ያለፈቃድ እየተዘዋወሩ መስበክ የተከለከለው ለማኅበረቅዱሳን አባላት ብቻ አይደለም፡፡ለሁሉም ሰባኪዎች ነው፡፡እነ በጋሻውን እና አሰግድንም ይጨምራል፡፡እርግጥ አንዳንድ የማኅበረቅዱሳን ሰዎች ሕገወጥ ሰባኪ ሲባል በጋሻውንና አሰግድን ብቻ የሚመለከት ይመስላቸዋል፡፡ሀቁ እንደሱ አይደለም፡፡ዳንኤል ክብረት፣ዓባይነህ ካሴ፣ብርሃኑ አድማስ፣ያረጋል አበጋዝ፣ዘበነ ለማ፣ዘላለም፣ታደሰ ወርቁ፣ሌሎች ስማቸው ያልተጠቀሰና በየትኛውም አጥቢያ በቋሚነት ሳይቀጠሩ ነጠላና ቀሚስ በሻንጣ ይዘው እየዞሩ መጠኑ በማይታወቅ ከስፖንሰር የሚገኝ የኪስ ገንዘብ የሚሰብኩትን ሁሉ ይመለከታል፡፡መመሪያው ያለምንም ልዩነት የወጣው ራሳቸውን በተዘዋዋሪ ሰባኪነት ሰይመው ያለቤተክህነት ፈቃድ እየዞሩ እንዳሻቸው መድረክ ላይ ተናግረው ለሚወርዱ ሁሉ ነው፡፡በተለይ አባቶችንና የቤተክሕነት ተቋማትን መዝለፍ እንደ ትልቅ ሙያ ቆጥረው በየሄዱበት የአፍ መፍቻ ላደረጉት አማተር ሰባክያን ማስተገሻ ነው መመሪያው የወጣው፡፡ለእገሌና ለእገሌ ወይም ለማኅበረቅዱሳን ሰባክያን ብቻ ተብሎ አይደለም፡፡
  ማኅበረቅዱሳንና የአቡነ ቴዎፍሎስን ኅልፈት ለማያያዝ መሞከራችሁ አሳፋሪ ነው፡፡እሳቸው ያለፉት በ1970 መጀመሪያ አካባቢ ነው፡፡ማኅበሩ የተመሰረተው በ1986 ዓ.ም ነው፡፡ምን አልባት አብዛኞቹ አባላት እሳቸው ሲገደሉ አልተወለዱም፡፡ጥላቻችሁን በልክ አድርጉት፡፡ሰው ምን ይለኛል ማለትም ጥሩ ነው፡፡የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ አንድ ጊዜ በመናፍቅነት ታውቀናል ብሎ የባጥ የቆጡን መቀባጠር ደግ አይደለም፡፡ኅሊናችሁን ተጠቀሙበት፡፡
  አባ ገብረሥላሴ የአቡነ ቴዎፍሎስን ሐውልት ቤተክርስቲያኑ በር ላይ አቁመዋል፡፡ምድረ ግቢውን አሳምረው ሰርተው በጽጌያት አስጊጠውታል፡፡ጉልላቱንና ቤተልሔሙን ጀምረው ወደ ማጠናቀቁ ናቸው፡፡ባልዋሉበት አታውሏቸው፡፡እርግጥ ነው በአስተዳደር ረገድ በተለይም ሠራተኞችን አንድ አድርጎ በመምራት ክፍተት አለባቸው፡፡ግላዊ ሕይወታቸውም ከአሶሳ እስከ ሐረር ከዚያም ከፉሪ ሥላሴ እስከ እግዚአብሔር አብ ከሐሜት የጸዳ አይደለም፡፡ምንኩስናቸው ላይ ሐሜቶች አሉ፡፡በዚህ የተነሳ የሰንበት ተማሪዎችና የማኅበረቅዱሳን ጥገኛ የመሆን አዝማሚያ አላቸው፡፡በገመናቸው ታስረዋል፡፡
  ለአረጋውያን የካቴድራሉ ሊቃውንት የሚሰጡት ክብር አስደሳች አይደለም፡፡በዓደባባይ ሊቃውንትን እያንጓጠጡ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሲካሰሱ ታይተዋል፡፡የደብሩን አንጋፋ ሊቃውንት ችላ ብለው በፓዎር ፖይንት የሚሰብክ ሰባኪ ነው የሚያስፈልገው የሚል ፈሊጥ አላቸው፡፡ያ ማለት የማኅበረቅዱሳን ሰባኪ ብቻ ነው የሚያስፈልገው ማለት ነው፡፡ይሄ ጎዳናቸው ለአንጋፋው ደብርና ለአንጋፎቹ የደብሩ ሊቃውንት ያላቸውን አነስተኛ ግምት ስለሚያሳይ ሁሉንም ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ቢያስተናግዱ መልካም ነው፡፡የሚያሳዩት እብሪት፣ጉልበተኛነት፣እልህ እና ገደብ ያለፈ የካሕናት ዘለፋ መስተካከል ያለበት ነው፡፡ታላቅ አባት ቦታ ላይ ተቀምጦ እንደ ትንሽ ሰው መሆን ጥሩ አይደለም፡፡ለአቡነ ቴዎፍሎስ ዝክረ ስምዕ ግን ከአባ ኃይለመለኮት ይልቅ እሳቸው የተሻለ መስራታቸው አይካድም፡፡ልማት ላይ ከተጠበቀው በላይ ሠርተዋል፡፡
  የእናንተ አንድ ደብዳቤ ባገኛችሁ ቁጥር ደብዳቤውን ከተጻፈበት ዐላማ ውጭ ለጥጦ መተርጎም፣የራሳችሁን ስሜት ቀላቅሎና ለውሶ ማቅረብ፣ግራ ቀኝ ሳያጣሩ የተገኘውን ሁሉ ለጥፎ ወሬ ማሟሟቅ አስተዋይ ኅሊና ለሌለው ሰው መስህት ነው፡፡ጥንተ ተፈጥሮአችሁን ለምናውቅ ግን አይገርመንም፡፡የአላማጂቱ ልጅ አእምሮዎን ለብዎውን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. አቦይ ገብረ ሥላሴ ሰላም ነው፡ ፡ገንዘብ እና ስስት አበዛችሁ ካካካካካ

  ReplyDelete