Friday, January 15, 2016

የቤተክርስቲያኒቱ ኮሌጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁቤተክርስቲያን በሰጠችው ፈቃድ ውስጥ ከመብቱና ከሥልጣኑ ውጪ በሕገወጥና በአልታዛዝ ባይነት ከእኔ በቀር ለቤተክርስቲያኒቱ ማንም የለም በሚል የትእቢት መንፈስ እየተንቀሳቀሰና ብዙ ጥፋቶችን እያደረሰ ያለውን ሁከት ፈጣሪ ማኅበረ ቅዱሳንን የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድበት ሲሉ ጠየቁ፡፡ የቅድስት ሥላሴ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ እና  የከሣቴ ብርሃን ሰላማ ኮሌጆች ተማሪዎችና ኃላፊዎች ለቅዱስ ፓትርያርኩ ባቀረቡት አቤቱታ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ትልቅ አደጋ የጋረጠ በመሆኑ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ ፓትርያርኩም በማኅበሩ ሕገወጥ አካሄድ ላይ የጀመሩትን እንቅስቃሴ ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ አካላት ጋር በመሆን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡
ማኅበሩ ከኮሌጆቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከገባ የቆየ ቢሆንም ለአሁኑ ክስ መነሻ የሆነው ግን በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ 23ኛ ዓመት ቁጥር 5 ቅጽ 23 ቁጥር 333 ከኅዳር 16-30 ቀን 2008 ዓ.ም እና በዌብሳይቱ www.eotcmk.org ላይ በሦስቱ ኮሌጆች ላይ ከአንድ ለቤተክስቲያን ድጋፍ እሰጣለሁ ብሎ ከተደራጀ ማኅበር የማይጠበቅ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያለውን ከፍተኛ ንቀትና ኃላፊነት የጎደለው ጽሑፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሠራጭ በማድረጉ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቁጥር 532/05/04/08 በቀን 3/5/2008 ዓ.ም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረበውን ደብዳቤ እና ያወጣውን መግለጫ እንዳስሳለን፡፡ በቀጣይም የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስና የከሳቴ ብርሃን ሰላማ ደብዳቤዎችን ይዘት ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማኅበሩ ላይ ባቀረበው አቤቱታ ላይ እንደ ገለጸው፣ ማኅበሩ ስምዐ ሐሰት በሆነው ጋዜጣው ላይ ስም ለማጥፋት ከመቸኮሉ በፊት እውነተኛ ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ የቤተክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማት የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች እንዳይቀበሉትና ከኮሌጁ የወጡትን ሁሉ እንዲያገሉ ጥሪ ከማስተላለፍ ብሎም ምእመናንን ግራ ከማጋባት ይልቅ በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ለታወቁት ውሣኔ ሰጪ አካላት አቅርቦ የልጅነት ድርሻውን በተወጣ ነበር ይላል የክሱ ደብዳቤ፡፡ “በአንፃሩ ነገሮችን ለራስ በሚያመች መልኩ አቀናብሮ የሚዲያ ግብዓት ለማድረግ ብቻ የሚጥረው ይህ አካሄዳቸው ለአጽራረ ቤተክርስቲያን ትልቅ የድል ብሥራት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይህም የጽሑፎቹን አካሄድና አላማ በደንብ ለማጤን ትልቁን የመነሻ አሳብ የሚሰጥ ነው፡፡” በማለት ያትታል፡፡
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከክሱ ደብዳቤ ጋር ማኅበረ ቅዱሳን የተባለውን የጥፋት መልእክተኛ የሚያስቆም እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ተጨማሪ 13 ገጽ የኮሌጁን አቋም መግለጫ አባሪ አድርጎ ያቀረበ ሲሆን፣ በመግለጫውም ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ የፈጸመውን በደልና ግፍ፣ በመንፈሳዊ ኮሌጆቹ ላይ ያሳደረውን ጫናና ድብቅ ዓላማውን ለማራመድ ሲል በቤተክርስቲያን ላይ የጋረጠውን ቤተክርስቲያንን የመከፋፈልና ሥልጣኑን የመቆናጠጥ አደጋ በገሃድ አሳይቷል፡፡
መንፈሳዊ ኮሌጁ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለቤተክርስቲያን በርካታ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ምሁራንን በማፍራት በቤተክርቲያኒቱ ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እያስመዘገበ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ መሆኑን፣ እንዲሁም በሀገሪቱ አጠቃላይ በሚገኙ አህጉረ ስብከትና ከሀገሪቱ ውጪ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ በማምጣት ላይ የሚገኙ ምሁራንና ሰባኪያን ያስተማረና በማስተማር ላይ የሚገኝ ጥንታዊ ኮሌጅ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ ነገር ግን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሆኖ ግቢ ጉባኤያትን በማስተባበር ትውልዱን ትምህርተ ሃይማኖት በማስተማር በሥነ ምግባር አንድ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ትውልድ እንዲኖር ለማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ የሥራ ዝርዝር የተሰጠውና ከዚህ ከተሰጠው ሃላፊነትና ክልል ውጪ በሕገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በኮሌጆች ላይ በተደጋጋሚ የስም ማጥፋት ዘመቻና በምዕመናን ዘንድ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዲፈጠር በማድረግ ኮሌጆችን የማዳከም ስልት ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማኅበር መሆኑን አመልክቷል፡፡ ጉዳዩ የኮሌጆች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የቤተክርስቲኒቱ ጉዳይ ቢሆንም እንደ ኮሌጅ ደግሞ በኮሌጁ ስም በተፃፈው ጽሑፍ ላይ የጽሑፍ መግለጫ ለማውጣት መገደዱን ገልጿል፡፡
ኮሌጁ ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ሆኖ ሳለ እያስተማሩ ያሉ አንጋፋ መምህራንና ኮሌጁን እየመራ ያለውን የኮሌጁን አስተዳደር ምንም እንዳልሠሩና ምንም ሊሠሩ እንደማይችሉ፣ ለቤተክርስቲያንም እንደማይቆረቆሩ በማስመሰል “በሕዝቡ ዘንድ የጥርጣሬ እና የቀቢጸ ተስፋ ስሜት እንዲሰማቸው ለማድረግ ማህበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ብሎ በሰየመው ጋዜጣው ላይ የሐሰት ምስክር እየሰጠ እየፃፈ ይገኛል፡፡ ጽሑፉ በተለይ መደበኛ ደቀመዛሙርት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ የመደበኛ ደቀመዛሙርት ቢሆኑም ማህበሩ በልዩ ልዩ የሥራ ዘርፍ እየቀጠረ እንደማያሰራቸውና እንደሚገለገልባቸው ማንም ሊመሰክር ይችላል፡፡ ይህ የሚያሳየው ማሩን እየበሉ ንቡን አያስፈልግም እንደማለት ነው፡፡” ብሏል፡፡
ማኅበሩ ኮሌጁን መፈታተን የያዘውና በዓላማ ዕቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው በማታው መርሀ ግብር አባላቱን በገፍ ኮሌጁ ውስጥ እንዲማሩ በማድረግ ነው፡፡ ለመማር የተመዘገቡ የማኅበሩ አባላት የመማር ማስተማሩን ሂደት በተለያየ መንገድ ያውኩ ነበር፡፡ በተለይም ማኅበራቸው ሲግታቸው ከኖረው ተረት ጋር የሚጋጭ ትምህርት ሲሰጥ “ይህ የመናፍቃን ትምህርት ነው ለምን ይህን ታስተምረናለህ? … መማር ያለብን እንደዚህ ነው ወዘተ” በማለት መምህራንን ያሸማቅቁ ነበር፡፡ መቼም ሰው ወደ ኮሌጅ የሚገባው ሊማር ሊመራመር፣ እውነትን ሊያውቅ በተማረው ትምህርትም ራሱንና ቤተክርስቲያኑን ወደተሻለ ነገር ሊያመጣ እንጂ ባለህበት እርገጥ አካሄድን ሊከተል አይደለም፡፡ የማቅ አባላት ወደኮሌጅ የሚገቡት ግን ለዚህ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ወደኋላ ለመመለስ እንደሆነ ከፍሬያቸው ይታወቃል፡፡ ወደአድባራት ወርደን በምናይበት ጊዜም ከኮሌጆች ተመርቀው በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተመደቡትን ደቀመዛሙርት ለምን ይህን ታስተምራላችሁ? ይህን አስተምሩ እንጂ እያሉ በሌላቸው ሥልጣን አለቦታቸው ገብተው የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴን ያውካሉ፡፡ ብዙዎችንም በሐሰተኛ ውንጀላ በየደብሩ በሚገኙ አባሎቻቸው አማካይነት ከአገልግሎት እንዲታገዱ ሀገረ ስብከት ላይ እንዲከሰሱና ጉዳያቸው ወደሊቃውንት ጉባኤ እንዲላክ በማድረግ እዚያ በመለመሏቸውና የሃይማኖትን ምንነት ጠንቅቀው በማያውቁ ወኪሎቻቸው እውነተኞችን ጥፋተኛ ያሰኛሉ፡፡   
መግለጫው አክሎ “ማህበሩ ኃላፊነት በጎደለው አጻጻፍ ቤተክርቲያን መሪ ጠባቂ እንደሌላት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ስለ ቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚቆረቆር አካል እንደሌለ በማስመሰል ምዕመናንን በአንድ በኩል ተስፋ የሚያስቆርጥ በሌላ በኩል ሰው የለም ተነሱ ቤተክርስቲያን ጠባቂ የላትም የሚል መልዕክት ያለው ጽሑፍ በጋዜጣው ከገጽ 6 እስከ 7 በጠቅላላው 8 ዓምዶች የያዘ የውንጀላ እና ስም ማጥፋት ጽሑፍ ተጽፏል፡፡” ይላል፡፡
በተጨማሪም “ከውንጀላው መካከል መንፈሳዊ ኮሌጆች የካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች፣ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ የቤተክህነት መሥሪያ ቤቶች፣ የነገረ መለኮት ተማሪዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግሉ ቀሳውስትና ዲያቆናት፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ መናፍቃን ናቸው ስምዐ ጽድቅ ገጽ 6 በማለት በዝርዝር ስለ ታላላቆቹ ሦስቱ ኮሌጆች መሠረታዊ ችግር ብሎ በማብራራት ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በጅምላ የመናፍቃን መፈልፈያዎች ናቸው የሚል ግጭትንና ቅራኔን የሚፈጥር ጽሑፍ ይነበባል፡፡”
ይህ አካሄድ ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ተቀባይነት ለማግኘት የተንቀሳቀሰበት ስልቱ ነው፡፡ ገና ከመነሻው ቤተክህነት ውስጥ መደላደል የቻለው ራሱን የመናፍቃን ፖሊስ አድርጎ በመሰየም ሲሆን፣ በየጊዜው በመናፍቃን ላይ ዘመቻ ከፍቻለሁ ግንዛቤም አስጨብጣለሁ እያለ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ድጋፍና መድረኮችን መያዝ ችሏል፡፡ ይህን የሚለው እርሱ በብዙ የአስተምህሮ ችግር ውስጥ ተዘፍቆና ዋናው ማኅበረ መናፍቃን ሆኖ እያለ ነው፡፡ ከእርሱ አስተሳሰብ የራቁትንና ቤተክርስቲያን ውስጥ ወንጌልን የሚሰብኩትን “መናፍቃን” እያለ ስም ያጠፋል፡፡ በሌላም በኩል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁሉንም ነካክቶ ከሁሉም አካላት ጋር ግጭት ውስጥ በመግባቱ የትኩረት አቅጣጫውን ለማስቀየርና ተቀባይነቱን ቀድሞ ወደነበረበት ለመመለስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የስልት ለውጥ ያላደረገውና እንደ ሞኝ ዘፈን  ሁሌ “ተሐድሶ መናፍቃን” በማለቱ የገፋበት ማቅ በአሁኑ ወቅት በብዙኃኑ እየተተፋ ይገኛል፡፡
መግለጫው “ማኅበረ ቅዱሳን በሚዲያው ጠቅላላ በቤተክርስቲያኒቱ በዋናነት ደግሞ በሦስቱ ኮሌጆች ላይ እንዲህ ብሎ የጻፈበት ምክንያት ምንድነው? እውነት ስለቤተክርስቲያን ተቆርቁሮ ቤተክርስቲያን ውስጥ ችግር ስላለና ችግሩን ሊቀርፍ ወደሚችል የቤተክርስቲያኒቱ አካል ነው የተጻፈው? ማህበሩስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለ ኑፋቄ በጅምላ የጻፈው የሚመለከተው የቤተክርስቲያኒቱ አካል ነገሩን አጣርቶ በትክክል ችግሩ እንዳለ አረጋግጦ የተጠረጠሩ አካላትስ ተጠይቀው ይሆን? ማህበሩ ይህንን ጽሑፍ በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣው ሲያወጣ የሚመለከታቸው አካላት የጠቀሳቸው ክፍሎች ቀርቦ በመመካከር ደረጃ አናግሮ ይሆን?” የሚሉ ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን ለጥያቄዎቹ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ማህበሩ የተደራጀበት ዓላማ ግልጽ ሆኖ እያለ በተለያየ ጊዜ ከተሰጠው የሥራ ዝርዝር እና ዓላማ ውጪ ግጭትንና መለያየትን ቅራኔንና ጥላቻን የሚፈጥሩ ጽሑፎች የሚጽፈው ለምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄው በስምዐ ጽድቅ ኅዳር 16-30/2008 ዓ.ም. በኮሌጆች ላይ በተጻፈው ጽሑፍ ላይ ተመሥርቶ የኮሌጁ መግለጫ መልስ ሲሰጥ እንዲህ ብሏል፡፡  
1.    በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን የሥራ ድርሻ ያለማወቅ ችግር ነው፤
ማህበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠው የሥራ ድርሻ ካለመጠበቁ ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት የሚጻፉ ጽሑፎች በቤተክርስቲያን አካላት እና ተቋማት ግጭት ቅራኔ መለያየት ሲያስከትሉ እንመለከታለን፡፡ ማህበሩ የሥራ ድርሻው በግቢ ጉባኤያት ላይ በቂ ዝግጅት በማድረግ ትምህርተ ሃይማኖት እንዲያስተምር ትውልዱን በእምነት እንዲጠብቅ፣ በሥነምግባር እንዲያንጽ፣ ለቤተክርስቲያኒቱ ብሎም በሀገረ ደረጃ ብቁ ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ ነበር የተሰጠው የሥራ ድርሻ፡፡ ነገር ግን ማህበሩ የተሰጠውን የሥራ ድርሻ ወደጐን በመተው በኮሌጆች፣ በገዳማትና፣ በአብነት ትምህርት ቤቶች፣ በካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች፣ በቤተክህነት መዋቅር ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤክርስቲያን ድረስ የመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው ይመስል ኮሌጆች እንዲህ ናቸው፣ የቤተክህነት ሠራተኞች እስከ አጥቢያ ቤተክርቲያን ድረስ የሃይማኖት ችግር እንዳለ አስመስሎ በጽሑፍ የሚወነጅለው የስራ ድርሻውን ጠንቀቆ ካለማወቁ የተነሳ ሳይሆን በምን አለብኝነት ሕዝቡ በኮሌጆች ላይ በቤተክህነት መሥሪያ ቤቶች በካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች ጠቅላላ በአባቶች በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እምነት እንዲያጣ ተስፋ እንዲቆርጥ ብሎም የማህበሩ ጀሌና አጋፋሪ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም በመንፈሳዊ ኮሌጆች፣ በአብነት ትምህርት ቤቶች እና በካህናት ማሠልጠኛ ሥፍራዎች ላይ ሆን ብሎ በማይመለከተው ገብቶ የተለያዩ የውንጀላና የስም ማጥፋት ጽሑፎች የሚጽፈው ከእነዚህ ተቋማት የሚወጡ ምሁራን የቤተክርስቲያኒቱ ተረካቢ ትውልድ ስለሆኑና በትክክል ትምህርተ ሃይማኖቱን ስለሚያስተምሩ፣ የማህበሩን የተሳሳተ አካሄድም ስለማይደግፉና ስለሚቃወሙ ነው፡፡ በማህበሩ ላይ ጥያቄ የሚያነሳ አካል መናፍቅ ወይም ተሐድሶ በማለት የተቋማቱን ስም ማጥፋት አመኔታ እንዲያጡ ማድረግ፣ በሕዝቡ ዘንድ በጥርጥር መንፈስ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ማድረግ ማህበሩ እንደ ዓላማ አድርጎ ይዞታል፡፡
እውነት ነው፡፡ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ የቤተክርስቲያን ልጆች ተሐድሶ መናፍቃን እየተባሉ ከእንጀራቸው የሚታገዱትና ስደት የሚታወጅባቸው ከማኅበሩ ጋር ስላልተስማሙ ብቻ ነው፡፡ ከማኅበሩ ጋር አለመስማማመት መብት ሳይሆን ተሐድሶነት ወይም መናፍቅነት እየሆነ ነው፡፡ በየደብሩ ያሉ የማኅበሩ ተላላኪዎች ማኅበሩ የጠላቸውን አገልጋዮች እንዲከሱና ከሥራቸው እንዲያግዱ ያደርጋል፡፡ እስከ ሊቃውንት ጉባኤ በዘረጋው ኔትወርክም የሃይማኖት ትምህርት እየታየ ያለው ቤተክርስቲያኒቱ በተመሰረተችበት ትምህርት ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን በሚፈልገው መንገድ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን ጥራት እስከዚህ ድረስ ያወረደው ማኅበረ ቅዱሳን ዝም ከተባለ ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ባሰ ቀውስ እንደምትገባና ፍልሰቱ እየጨመረ እንደሚሄድ አያጠራጥርም፡፡  
ኮሌጆች በቅዱስ ፓትርያርኩ የበላይ ጠባቂነት በቅዱስ ሲኖዶስ በጀት እየተበጀተላቸው የሚተዳደሩ በቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሊቀጳጳስ የሚመሩ ሆነው እያለ በማህበሩ አስተሳሰብ ግን በየኮሌጆቹ ያሉ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊቃነጳጳሳት ለኮሌጆቹ የማይቆረቆሩ ለሃይማኖታቸው የማያስቡ አድርጎ ስለሚቆጥራቸውና ራሱን ብቻ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተቆርቋሪ አድርጎ ስለሚቆጥር ቢያንስ እንኳን የኮሌጆቹን የበላይ ኃላፊዎች ሊቃነ ጳጳሳትን ብሎም የኮሌጆቹን አስተዳደር ማነጋገር እየቻለ ሳያነጋግር በስምዐጽድቅ ላይ ማውጣቱ ማኅበሩ ጽሑፉን የጻፈበትን ዓላማ ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ማህበሩ ችግሩ ስላለና ከተቋማቱ እንዲቀረፍ ወይም እንዲወገድ ስለሚፈልግ ሳይሆን ተቋማቱ እንዲዳከሙ፣ ጠንካራ ዝግጅት እንዳይኖራቸው ለማድረግ፣ ከየኮሌጆቹ እየተመረቁ የሚወጡ ምሩቃን በሕዝቡ ዘንድ ቦታ እንዳያገኙ ለማድረግ እና ማህበሩ ብቻ ሕዝቡን ይዞ የስምዐ ጽድቅና የሐመር መጽሔት ሽያጭ እንዲሰበስብ፣ ብሎም ማህበሩ ያለውን ድብቅ አጀንዳ ለማሳካት ይመስላል ብሏል፡፡
ማህበሩ ሁሌም ራሱን ትክክል ዐዋቂና ሃይማኖተኛ ሌላውን ሁሉ ደግሞ ስሕተተኛ ያልተማረና መናፍቅ አድርጎ ስለሚመለከት ኮሌጆቹን ከከሰሰባቸው ጉዳዮች አንዱ አህጉረ ስብከቶች ደቀመዛሙርትን የሚመለምሉባቸው መስፈርቶች በጥቅማ ጥቅም ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ኮሌጆቹም በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚሠራው ብሏል፡፡ እንዲህ ሲልም ደቀመዛሙርት ተመልምለው የሚላኩት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፊርማ እንደመሆኑ እነርሱንም በተዘዋዋሪ ተጠያቂ አድርጓል፡፡  
2.    በቅዱስ ሲኖዶስ አለመተማመን
ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱ ወሳኝ አካል፣ የቤተክርስቲያኒቱ ሕግ አውጪ፣ በሃይማኖትም ሆነ በአስተዳደር ዙሪያ ያሉ ችግሮች መፍትሔና ውሣኔ ሰጪ ሆኖ እያለ ማህበረ ቅዱሳን ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ የሚያስፈልገውን ጉዳይ ሳያስወስን ሕገ ቤተክርስቲያን እያፈረሰ ወይም እየጣሰ ይገኛል ያለው መግለጫው፣ ይህም ሁኔታ የሚያሳየው ማህበሩ ራሱን ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ አድርጎ እንደሚመለከት ነው ብሏል፡፡
ሌላው የማኅበሩ ችግር “ቅዱስ ሲኖዶስ ታላላቅ አባቶች ያሉበት በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ሆኖ እያለ በመንፈስ ቅዱስ ከሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ማህበሩ የሚያስበውና የሚያቅደው ብሎም ተቆርቃሪቱ የተሻለ ነው ብለው ማሰባቸው ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ዋናው እቅዱ ምእመናን በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አባቶች እምነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ፣ የቤተክርስቲያን አባቶችና መሪዎች በሕዝቡ ዘንድ ዋጋ እንዳይኖራቸው ለማድረግ፣ ከላይ እስከታች የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር በጥርጣሬ እንዲታይ በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር እንዳይጠበቅ፣ የማህበሩ ጀሌ አባል ብቻ እንዲበዛ ብሎም በማኅበሩ ሳንባ እንዲተነፍስ በማድረግ የማህበሩን የሕትመት ውጤቶች ብቻ እንዲገዛ ለማድረግ ነው፡፡
አንዳንድ ቦታ ላይ በተደረገው ጥናት ማህበሩ ከቅዱስ ሲኖዶስና ከቤተክህነት በማወዳደር ራሱን ብቻ ያስተዋውቃል፡፡ ለምሳሌ ቤተክህነት የሚረዳቸው ይህንን ያህል ነው፣ ማህበሩ ግን ከዛ በላይ እገዛ እያደረገ ነው፡፡ ቤተክህነት ምንም የሚሠራጭ የሕትመት ውጤት የለውም፡፡ ማህበሩ ግን ስምዐ ጽድቅና ሐመር መጽሔት ያሠራጫል በማለት የቤተክህነት አሠራር በሕዝቡ የተናቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የራሱን ሲኖዶስ እንዲመሠረት የሚፈልግ በቤተክህነትም አሠራር ቤተክነቱን ተረክቦ ዓላማውን ለማሳካት እየተዘጋጀ ያለ ማህበር ነው፡፡ መዋቅሩም በቤተክህነት ዓይነት እንደሆነ ይነገራል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ የማህበሩ አባላት እነ እገሌ ናቸውና ጵጵስና ይመረጡ፣ ውሣኔ በዚህ መልኩ ይስተካከል በማለት ለቤተክርስቲያኒቱ መክፈል አይቀሬ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ በሚያዘጋጀው መድረክ የማህበሩ አባል ካልሆነ በስተቀር ሌላው ቀርቶ ሊቃነ ጳጳሳቱን እንኳን ብፁዕ አቡነ እገሌ የእኛ አይደሉም ብፁዕ አቡነ እገሌ የእኛ ስለሆኑ ይምጡልኝ እስከ ማለት ደርሶአል፡፡
ኮሌጁ እነዚህን ብቻ ጠቃቀሰ እንጂ ገና በጠዋቱ ራሱን ራሱን ከሲኖዶስ በላይ አድርጎ መመልከት የጀመረው ያሻሻላቸው ቀኖናዎች አሉት፡፡ አንዱ የጽጌን ጾም ስምንተኛ ጾም አድርጎ መቁጠሩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመላው ዓለም ለጳጉሜን አባላቱ እንዲጾሙ ጾም ያውጃል፡፡ ይህን ጉዳይ ሌሎች አድርገውት ቢሆን ጾም ማወጅ የሲኖዶስ ሥልጣን ነው ስለዚህ ቀኖና ተጣሰ አካኪ ዘራፍ ይል ነበር፡፡ እርሱ ሲጥሰው ግን ጽድቅ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ራሱን ከሲኖዶስ በላይ ነውና የሚያየው፡፡
ከእዚህ ውጪ ማኅበሩ እንዲያስተምር በተሰጠው በግቢ ጉባኤያት እንኳን ሁለት ዓበይት ጥፋቶችን ይፈፅማል ሲል ኮሌጁ ጽፏል፡፡ ይኸውም
1.     የብሔር ብሔረሰብ ተወላጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ወንጌል እንዲሰሙ አይፈልግም፡፡
ማኅበሩ መንፈሳዊነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ሰውን በሰውነቱ መቀበል የሚከብደውና ስለአንድ “ወንዝ” ብቻ የሚያስብ ዘረኛ ቡድን ነው፡፡ በማኅበሩ ውስጥ የተለያዩ ብሄር ሰዎች ያሉ ቢሆንም በአንደኛ ደረጃ የሚታዩት ግን የማኅበሩ የወንዝ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ ዘረኛ አስተሳሰቡ የወንዙን ጳጳሳት ከጎኑ አሰልፏል፡፡ በቤተክህነት ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የወንዙ ሰዎች በፎርጅድ የትምህርት መረጃ ጭምር ቁልፍ ቦታ እንዲይዙለት ያደረገበትና የተጋለጡበት ሁኔታ አለ፡፡          
2.    በአምሳሉ ከቀረፃቸው መምህራን በቀር ማንም የቤተክርስቲያኒቱ አባል የሆነ መምህር እንዲያስተምር አይፈቅድም፡፡
በመሆኑም “ራሱን የቻለ መዋቅራዊ አሠራር እየዘረጋ ስለሆነ ለቤተክርስቲያኒቱም ትልቅ ስጋት ሊሆን ስለሚችል ቅዱስ ሲኖዶስ ቆም ብሎ ሊያስብበት ይገባል፡፡ ሌሎች ሰዎች ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ ሳይሰጣቸው ተጠርጣሪ መናፍቃን በማለት የማህበሩ ጀሌዎች የሆኑ ንጹሐን የኦርቶዶክስ አባላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት እየፈጠሩ ይገኛል፡፡ ሌላው ቀርቶ በጣም ብዙ ጳጳሳት ከወጡበት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ኦርቶዶክስ ሆኖ መውጣት እንደተአምር ያህል እንደሚቆጠር ደፍረው ጽፈዋል፡፡ በየወቅቱ እየተጻፉ ያሉ ጽሑፎች በምዕመናን ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአሁኑ ጊዜ ምን ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ማህበሩ እየሠራው ያለው አፍራሽ ተግባር በትኩረት ሊጤን ይገባዋል፡፡” ሲል መግለጫው ያሳስባል፡፡
3.   የቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ አለማክበር
እንዲተዳደርበት በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠው ባለ 43 አንቀጽ መተዳደሪያ ደንብ እንደሚያሳየው ማህበሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ እንዲተዳደርና ስለሚያሳትማቸው የሕትመት ውጤቶች በተመለከተ፡-
“በመመሪያው በኩል ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ አካላት ጋር በመነጋገር በማስፈቀድ ትምህርተ ወንጌል በተለያዩ ዘዴዎች በመጽሔቶች በጋዜጦች፣ በበራሪ ጽሑፎች፣ በካሴቶች፣ በኢንተርኔት፣ በኤሌክትሮኒክስ መገናኛና በመሳሰሉት እንዲስፋፋ ማድረግ፣ ወጣት ሰባክያንን ማበረታታት” ይላል (አንቀጽ 4 ቁጥር 6)፡፡
በ2003 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው ውሣኔ መሠረት ማህበሩ የሚያሳትማቸው ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔት እንዲሁም ማንኛውም የሕትመት ውጤት በሚመለከታቸው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሳይመለከቱዋቸውና ሳያርሙአቸው ስርጭት ላይ እንዳይውሉ ይልቁንም ልዩ ኮሚቴ ተቋቁም እንዲታይ ተብሎ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ቀደም ብሎም በ2002 ዓ.ም. ማህበሩ ከመተዳደሪያ ደንብ ውጪ ሥርጭት እያደረጉ እንደሆነ ተገልጾ ሕግ አክብሮ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገልጾ ነበር (ል/ጽ/ 55/2002 ቀን 27/01/2002 ዓ.ም)፡፡
ማህበሩ የሚያወጣቸው የሕትመት ውጤቶች የሚሠራጩት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ ስለማይገዛው ሕጋዊ ያልሆነ አካሄድና በመጽሔቶቹ ሆነ በጋዜጣው በሚያወጣው ጽሑፍ የዶግማም ሆነ የቀኖና ግድፈትና ስህተት ነቅሶ ማውጣት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ማህበሩ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ አክብሮ የማይሄድ ከሆነ ማህበሩ ሕጋዊ ያልሆነ አካሄድ እየሄደ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ለራሱ ሕግ እየጣሰ እየተንቀሳቀሰ ያለው ማህበር በምን ሞራልና በምን መልኩ ስለሕጋዊነት ሊናገርና ሊጽፍ ይችላል? በቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ መሠረት እና በወጣለት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ስላልሄደ፣ ከራሱ የግል ፍላጎት አንፃር እና ከድብቅ ዓላማ አኳያ ስለተፃፈ በቤተክርስቲያን ውስጥ መለያየት እንዲፈጠር እያደረገ ይገኛል፡፡
ቀደም ብሎም ማህበሩ የሚጽፋቸው ጽሑፎች በሚመለከታቸው የቤተክህነት ሊቃውንት የታዩና የታረሙ ስላልነበሩ የሚከተሉት አስተያየቶች በማኅበሩ ላይ መሰጠታቸውን ጠቅሷል፡፡
·        “በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና በሐመር መጽሔት የሚተላለፉ መልእክቶች መንግሥትንና ቤተክርስቲያንን መንግሥትንና ሕዝብን የሚያጋጩና ቅራኔን የሚፈጥሩ እየሆኑ ይስተዋላሉ፡፡ ስለዚህ መታረምና መስተካከል አለባቸው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ከቤተክርስቲያንና ከመንግሥት እይታ ውጪ እየሄደ ነው፡፡
·        “ማህበረ ሃይሠማኖትንና ፖለቲካን እያጣመረ የሚሄድ መሆኑን የሚያስገነዝብ መረጃ የተገኘበት ስለሆነ በፈፀመውና በሚፈጽመው ስህተት ሁሉ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ለሕግ አቅርቦ አስፈላጊውን ውሣኔ እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል፡፡
·        “ማህበሩ ማስተማር የነበረበት ስለ እምነቱ ነው የፖለቲካ ማህበር ነኝ የሚል ከሆነ የፖለቲካ የሥራ ፈቃድ መውጣት አለበት፡፡ ሃይማኖትንና ፖለቲካን ሁለቱን እያጠቀሱ መሄድ ግን አይቻልም፣ ስህተትን በስህተት ማረም የለብንም፣ የተፈፀመው ስህተት በሰላማዊ ምክክር መፍታት አለበት ከአሁን በኋላ በሚሰጠው ምክርና በቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ መሠረት መፈፀም አለበት፡፡ መንግሥትንና ሕዝብን ቤተ ክርቲያንንና መንግሥትን የሚያጋጭና የሚያለያይ አካሄድ መታረም ይኖርበታል በማለት አመራር ተሰጥቶት እንደነበረ መረዳት ይቻላል፡፡ (ል/ጽ 55/2002 ቀን 27 ዐ2 2002)፡፡
ማኅበሩ ከዚህ ቀደም እነዚህ ግድፈቶች እንዳሉበት ተጠቅሶ የማስተካከያ እርምጃ እንዲያደርግ መመሪያም ማስጠንቀቂያም ቢሰጠውም እርሱ ግን ወይ ፍንክች ብሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው ማኅበሩ ዓላማውን ለማሳካት ወደፊት በሕገወጥ እና በገንዘብ ኀይል የሚንቀሳቀስ ከመሆኑ ወጪ ምንም ለውጥና መሻሻል እንደማያመጣ ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሔው ማኅበሩ ላይ የማያዳግምና አስተማሪ እርምጃ መውሰድ እንጂ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን እንደሁ ያለ ማኅበረ ቅዱሳን ለብዙ ዘመናት ኖራለች፡፡ እንዲያውም በርካታ ምእመናን የፈለሱባት ብዙ የአስተምህሮና የሥነምግባር ችግሮች የበቀሉባት ማኅበረ ቅዱሳን የመናፍቃን ዘመቻ ከፍቼያለሁ ግንዛቤም እያስጨበጥኩ ነው እያለ ባለበት ወቅት ነውና በዚህ የማይለወጥና የቤተክርስቲያን ነቀርሳ በሆነው ማኅበር ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ቤተክርስቲያን በተሻለ መንገድ እንድትሄድ ይረዳል፡፡
እነዚህ ከላይ የተሰጡት አስተያየቶች ተግባራዊ ስላልሆኑ ግን አሁንም ማህበሩ ተመሳሳይ ድርጊት እየፈፀመ እንደሚገኝና ማህበሩ የሚያሳትማቸው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና ሐመር መጽሔት ሕግን ባልተከተለ መልኩ እንደሚታተሙና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ በተግባር ላይ አለመዋሉን መግለጫው አመልክቷል፡፡ ስለሆነም “በወጣላቸው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሚመለከታቸው የቤተ ክህነት ሊቃውንት ሳያርሙት የሚመለከተው ማዳራጃ መምሪያ ሳያየውና ሳያውቀው” ወደፊት የሊቃውንት ጉባኤን ይተካልኛል ብሎ ባደራጀው የኤዲቶሪያል ቦርድ በኩል ብቻ ታይቷል በሚል እየተሠራጨ ይገኛል፡፡ ስለሆነም “በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ህዳር 16 30 2008 ዓ.ም. የተፃፈው ጽሑፍ ስለ ኮሌጃችን በጠቀሰው ክፍል ላይ ሆን ብለው ኮሌጅን ለማዳከም፣ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማደናቀፍ፣ በአስተዳደርና በመምህራን በተማሪዎች በአስተዳደርና በተማሪዎች የኮሌጁ ማህበረሰብ እርስ በእርሱ የሚከፋፈል ኮሌጅንና ሕዝቡን ኮሌጁን አገልጋዮችንና ምዕመናንን የምዕመናንና ቤተክርስቲያንን ምዕመናንና የቤተክርቲያን መሪዎችን የሚያለያይ ግጭት የሚፈጥር፣ አለ መተማመንን የሚያነግሥ በሰላም እንዳይኖሩ የሚያደርግ፣ ያለ መተማመንንና የመፈራራትን ስሜት በመፍጠር የምዕመናንን አንድነት ብሎም የቤተ ክርስተያንን አንድነት የሚበትን ድርጊት ሆኖ ይታያል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምዕመናንን አገልጋዮችን ወይም የኮሌጅ ምሩቃንን እርስ በእርሳቸው እንዲጋጩ በማድረግ ሰላም የሚነሳ በሀገሪቱ ሰላምም ትልቅ ጠብ አጫሪ ተግባር ነው፡፡” ጽሑፉ ለሁሉ የተዳረሰ ቢሆንም የቤተክርሲቲያኒቱ አቋም ግን አይደለም ያለው መግለጫው፣ “የቤተክርቲያን አቋም መሆኑ ይቅርና ሕትመቱ በራሱ ሕጋዊ አካሄድ ያልተከተለ ጸረ አንድነት ጸረ ሰላም የሆነ ድርጊት ነው፡፡” ብሏል፡፡ ከዚህ የተነሣ ማህበሩ በየክፍለ ሀገሩ እያደረገው ያለውን ድርጊት ቅዱስ ሲኖዶስ በትኩረት ተመልክቶ እልባት ካልሰጠበት፣ የመንግሥት አካላትም ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሔ ካልወሰደበት አስጊ ሁኔታ ነው ብሏል፡፡
መግለጫው በማስከተልም “በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች በመዞር የመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን መልካም ገጽታ እያበላሸ ይገኛል፡፡ በስም ካህናት ስልጠና ሐዋርያዊ አገልግሎት እየተባለ በየቦታው የኮሌጁን ምሩቃን ባሉበት ቦታ ተፈጥሮኣዊና ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ማህበሩ በሃይማኖት ሽፋን መናፍቃን ናቸው ተብሎ ሳይጣራ ከመደረክ እንዲወርዱ፣ ደመወዛቸው ታግዶ ከሥራ እንዲባረሩ የተለያዩ ቅስቀሳዎች እያደረገ ይገኛል፡፡ ዜጐች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ታፍኖ እየተሸማቀቁ ይገኛሉ፡፡ በየአድባራቱ በሰንበት ትምህርት ቤቶች በየከተማው የተለያዩ ግጭቶች ይነሳሉ፡፡ የእነዚህ ግጭቶች መነሻው እንዲህ ዓይነቶቹ አስተሳሰቦች ናቸው፡፡” ብሏል፡፡ “ያጠፋ ሰው ካለ ለምን እርምጃ ይወሰድበታል? ለምን ይጋለጣል? ማለታችን ግን አይደለም” ያለው መግለጫው፣ ሁሉም ነገር በማስረጃ ተደግፎ የቤተ ክርስቲያን ሕግ በሚፈቅደው መልኩ መሆን አለበት ነው የሚለው፡፡
“ጫናው ውጫዊ ኃይል እንደሆነ ለማንም ሰው ግልጽ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ በትኩረትና ረጋ ባለ መንፈስ ለቤተክርስቲያን ጥቅም ተብሎ መፍትሄ ካላገኘ ነገ ቤተክርስቲያን አደጋ ላይ ትወድቃለች፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ቤተክርቲያን ልጆችዋን መምከር መገሠጽና መንከባከብ ዕለታዊ ተግባሯ ነው፡፡ ነገር ግን በግፊት የቤተክርስቲያን ልጆች እየተሰደዱ ነው፡፡ መንግሥትም ጉዳዩ በአጽንኦት ሊመለከተው ይገባል፡፡ ምክንያቱም የቤተክርስቲያኒቱን ሕግ ተከትለው ያልታተሙና ያልተሠራጩ ጋዜጦችና መጽሔቶች የሕዝቡን ሰላም እያደፈረሱ ግጭት እየፈጠሩ ስለሚገኙና የእነዚህ ሕትመቶች ባለቤት ያለቦታው ያለሥልጣኑ ገብቶ እየዘባረቀ የሚገኝ ማህበር ስለሆነ በትኩረት ተመልክቶ የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት መፍትሔ እንዲበጅለት እንጠይቃለን፡፡” ብሏል፡፡
በመግለጫው የተነሣው ሌላው ጉዳይ ከእድሜ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለምሳሌ ፡- በቅርቡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ሥልጠና ላይ ሠልጣኞቹ ማህበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ከሰጡት መግለጫ መካከል የሚከተሉትን ጠቅሷል፡፡
·        “የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የሚሆኑት ከ30 ዓመት በታች ናቸው፡፡ በቃለ ዓዋዲ ሕግ መሠረት የማህበሩ አባላት ግን ከዚህ የዕድሜ ክልል ውጪ ሆነው በየአብያተ ክርስቲያኒቱ ዓመፅና ሁከት እየፈጠሩ ይገኛሉ”
·        “ማህበሩ አባላቱን ሲቀርፃቸው የማህበረ ደጋፊ ማህበሩ አንዳይነካ ማህበሩ እንዳይጐዳ ከሚለው አንፃር እንጂ ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንዲቆሙ አያደርጋቸውም፡፡ አንድ የማህበሩ ዋና ፀሐፊ የነበረው በአንድ ወቅት ስለማህበሩ አቋም እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር፡፡ ‘ማህበሩ ለቤተክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ቤተክርቲያን ለማህበሩ ጥቅም ወደሚል አስተሳሰብ እየዞረ ነው፡፡ ማንኛውም አካል በማህበሩ ፊት ከቆመ ማህበሩ የቤተክርስቲያን ጠላት አድርጎ ይፈርጀዋል፡፡ እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ የሃይማኖት ችግር ስላለበት አይደለም ማህበሩን የሚቃወም ከሆነ የሆነ ስም እንደሚሰጠው ወይም በሌላ አባባል መናፍቅ ወይም ተሐድሶ ሊባል ይችላል የሚል ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየን ማህበሩ አሁን የያዘው አቋም ተቋማዊ አካሄድ ነው፡፡ ስለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ስለማህበሩ ጥቅም ብቻ ነው የቆመው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ ፖለቲካዊ ድርጅት አባላት ማብዛት የገቢ ምንጭ አድርጎ ይዞታል፡፡ የማህበሩ አባላት አስራት በኩራት ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማህበሩ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ ዋናው ዓላማው በሀብት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በማድረስ በገንዘብ ብዛት ሁሉንም ለመቆጣጠር፣ ውሣኔ ለማስቀየር ስለሚታሰብ ነው፡፡ ብዙ አባላትን ማፍራት ለቤተክርቲያን ጥቅም፣ አገልግሎትና አንድነት ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ እንደምናየው በሆነ ምክንያት ብዙ ገቢ እንዲሰበሰብ ይደረግና ከተሰበሰበው ገቢ ለተሰበሰበበት ዓላማ ክፍፍል የሚደረገው ከ50 ፐርሰንት ያልበዛ ነው፡፡ ከዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ለትርፍ እየተንቀሳቀሰ ያለው ማህበር እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህንን እንቅስቃሴ በቁጥጥር ስር ካለዋለችው በጊዜ ሂደት ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ከባድ እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡” ብላል ኮሌጁ በመግለጫው፡፡

4.   የማህበሩ የሥልጣን ወሰን
የማህበሩ ሥልጣን ምንድነው? ማህበሩ መሥራት የሚገባው እና መሥራት የሌለበትስ ተግባር ምንድነው? ማህበሩ ለቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ፣ ሙያዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ እንደ መሆኑ መጠን በሥራው ሁሉ መንቀሳቀስ ያለበት በዚህ መልኩ ነበር፡፡ ማህበሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሃይማኖት ኮትኩቶ እንዲያሳድጋቸው ቤተክርስቲያን በሚያጋጥማት ሙያዊም ሆነ ኢኮኖሚዊ ክፍተት እንዲሠራ ነበር ፈቃድ የተሰጠው፡፡ እነዚህን ተግባራት ሲያከናውን በተቀመጠለት መተዳደሪያ ደንብ ብቻ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ በማህበሩ ውስጥ የቤተክርስቲያን እድገት የሚመኙ ገንዘባቸው ጉልበታቸው፣ እውቀታቸው በትክክል ለታለመለት ዓላማ የሚያውሉ፣ ስለማህበሩ ትክክለኛ የቤተክርስቲያኒቱ አቅጣጫ የሚከራከሩ የተሳሳተውን መንገድ የሚቃወሙ ትክክለኛና የቤተክርስቲያኒቱ ተቆርቆሪዎች እንዳሉ የማይካድ ሐቅ ነው፡፡ ነገር ግን ለማንም ያልተሰወረው የማህበሩ ሥልጣን እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ የማህበሩ ዋና ፀሐፊ የነበረው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትም ስለማህበሩ አቅጣጫ የወደፊት ራእዩ ስለ አመራሩ ሲናገር ማህበሩን የሚመራው ሥውር አመራር አለ ብሎ ጽፏል በብሎጉ፡፡ ስለዚህ ይህ ስውር አመራር ይሆን አቅጣጫው እያሳተው ያለው? ይህ ስውር አመራር ይሆን የማህበሩ ሥልጣን በቅዱስ ሲኖዶስ ከተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ እየወጣ በማይመለከተው እየገባ እንደዛባር እያደረገ ያለው?” ሲል መግለጫው ይጠይቃል፡፡
እንደተባለውም ማኅበሩ ከተቋቋመለት ዐላማ ውጪ በተደጋጋሚ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ይህን የሚዘውሩና አመራር የሚሰጡ ስውር አመራሮች በውጭ መኖራቸውም አንድና ሁለት የለውም፡፡ እዚህ ያሉት ግልጽ አመራሮች ውሳኔ የሚያሳልፉት ከውጭ በስልክ ወይም በሌላ የመገናኛ ዘዴ የሚተላለፍላቸውን መመሪያ በመቀበል መሆኑን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ያ ባይሆን ማኅበሩ እዚህ ደረጃ ላይ ባልደረሰ የቤተክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማትም ለመስደብ ባልቻለም ነበር፡፡ ምንም ሽፋኑ ሃይማኖታዊ ቢሆንም ዋና አጀንዳው ቤተክርስቲያኗን ተቆጣጥሮ በኢኮኖሚም ደርጅቶና ተጠናክሮ በሂደት ፖለቲካዊ ሥልጣኑን ለመጨበጥ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ትግል ለዚህ ካልሆነ እዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ባልተገባ ነበር፡፡
“ማህበሩ በሚጽፈው ጽሑፍ ለምሳሌ ቀጥታ በማህበሩ ስም ባልሆኑት ነገር ግን የማህበሩ አቋም በሚፀባረቅባቸው ዌብሳይቶቹ ቀደም ብሎ በደጀ ሰላም አሁን ደግሞ በሐራ ዘተዋሕዶ ብዙ ጊዜ የማህበሩ አቋም ይንፀባረቃል፡፡ በእነዚህም ሆነ በሚታወቁት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና ሐመር መጽሔት በቅዱስ ፓትርያርኩ እምነት የለውም፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እምነት የለውም፡፡ አሁን ደግሞ በጋዜጣው በግልጽ እንደተቀመጠው በቤተክህነት መሥሪያ ቤቶች በደብር አስተዳዳሪዎች በአብነት ትምህርት ቤቶች በካህናት ማሠልጠኛ ስፍራዎች በገዳማት ማን ቀረ በሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ማህበሩ እምነት የለውም፡፡ ታዲያ በማን ነው የሚተማመነው? የማህበሩ አባላት ብቻ በሆኑ በተለያየ ቦታ ባሉ ሠራተኞችና ደቀመዛሙርቱ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡”
በአንድ በኩል ማኅበሩ አሁን ከሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ ይልቅ ስሙ ገዝፎ ስለወጣ ብዙ ደጋፊ ያለው ይምሰል እንጂ እንደስሙ እንዳልሆነና ብዙ ጠላቶችን እንዳፈራ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ አንዳንዶች የሚፈሩት ስሙን ሌሎችም የሚያስፈራሩት በስሙ ነው እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሚወራው ያን ያህል አስፈሪ እንዳልሆነና ውስጡ እየላላ መምጣቱን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ የተለመዱ ፕሮግራሞችን ስለሚያካሂድና የዚያኑ ያህል ሁከትና ዐመፅ ስለሚቀሰቅስ ግን እርሱን እንደ ሕጋዊ አካል መቁጠር ተገቢ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሁሉም መብቱን ሊያስከብር፣ ቤተ ክህነቱም ከማኅበሩ የማስፈራራት ተጽዕኖ ነጻ ወጥቶ ትክክለኛውን ፍትሕ መስጠትና ማኅበሩ ለሚከሳቸው አገልጋዮች ጥበቃ ማድረግ ችግር ካለም በተገቢው መንገድ ፍትሕ መስጠት አለበት፡፡     
“አሁን ማህበሩ እየሠራው ያለው ሥራ ፍፁም ከተሰጠው የሥራ ዓላማ ውጪ ነው፡፡” የሚለው መግለጫው የሚከተሉትን ማሳያዎች አቅርቧል፡፡
1.     የሕትመት ጽሑፎቹ በቤተክህነት ሊቃውንትና በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ ማምሪያ ማለፍ ሲገባቸው አሁን ከዚህ ውጪ በሆነ መንገድ የተሰጠውን መተዳደሪያ ደንብ እየጣሰ ነው፡፡
2.    በሌለው ሥልጣንና በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ ቤተክርስቲያንን እየከፈለ የሚገኝ መሆኑ፡፡ ለምሳሌ፡- እገሌ መናፍቅ ነው መረጃ አቀርቤያለው ሊወገዙ ይገባል ዓይነት ጥያቄዎች በተለይ ደግሞ አሁን የጻፈው መንፈሳዊ ኮሌጆች የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው የሚለው ተጠቃሽ ነው፡፡ ለመሆኑ ስለኑፋቄ መኖር አለመኖር የሚያጣራ፣ አንድ ትምህርት ኑፋቄ መሆን አለመሆኑን የሚለይ ማነው? ሥልጣኑስ የማን ነው? ሂደቱስ እንዴት ነው መሆን የነበረበት? በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩ ኮሌጆችን ማህበረ ቅዱሳን ሳይነጋገር እንዴት በድፍረት በውንጀላ እንዲህ ሊል ይችላል?
3.    በተለያዩ አህጉረ ስብከት እየዞረ ቅስቀሳ እያደረገ ነው፡፡ ቤተክርቲያን በዚህ መልኩ የምትቀጥል ከሆነ አደጋ ይደርስባታል፡፡ ማህበሩ በተቀመጠለት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሊገዛ ወይም እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እንላለን፡፡
4.    አሁን በተጨባጭ ሁኔታ የማህበሩ አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ መናፍቅ ወይም ተሐድሶ ይባላል፡፡ የማህበሩ ደጋፊ አባል ሆኖ የፈለገውን ነገረ ቢሠራ ደግሞ ንጹሕ ኦርቶዶክሳዊ ይሉታል፡፡ በማህበሩ ካልተረጋገጠ በስተቀር ኦርቶዶክሳዊ የለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የማህበሩ ሥልጣን የእምነት ብቃት ማረጋገጫ ሰጪ ተቋም ሆኖአል ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ መልኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሰፊ ልዩነት እየተፈጠረ ነው ያለው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ እና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ለቤተክርስቲያን አነድነትና ትውልዱን ለመታደግ ሲባል ሕጋዊ እርምጃ እንደወስዱ እንጠይቃለን።” ይላል መግለጫው፡፡
ይህ የኮሌጆቹ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማኅበር ሕጋውያኑንና በጀት መድባ የተማረ የሠው ኀይል የምታፈራባቸውን ኮሌጆች በሌለው ሥልጣን ሲዘልፍና ስም ሲያጠፋ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢነት የለውም፡፡ ማኅበሩ ኮሌጆቹ ላይ በዋናነት ያነጣጠረው አስመርቆ የሚያሰማራቸው ደቀመዛሙርት የተሻለ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ስለሚሰጡና የማኅበሩ አባላት ዘመኑን የዋጀና ከተረት የወጣ ነገር ማቅረብ ስላልቻሉ በምቀኝነት ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሱቅ ውስጥ የሚሸጠውና “460 ቀናት በመንበረ ፓትርያርክ” የተሰኘው መጽሐፍ በገጽ 139-140 እንዳሰፈረው እንዲህ ዓይነቱ ተቃውሞ ቀድሞ በባህላዊ መንገድ በሚያስተምሩና በኮሌጅ ምሩቃን መካከል ነበረ፡፡ “ቀድሞ ቀሳውስቱ ስብከታቸው እና አልፎ አልፎ አንዳንዶቹ የሚያሰሙት ቁጣ እና ማስፈራራት ወጣቱን ትውልድ ከቤተክርስቲያኑ እያራቀው መሄዱ የአደባባይ ምስጢር ነበር፡፡ ይህንንና ሌሎች መሰል ችግሮችን በመፍታት በስብከተ ወንጌል ጎዳና የተሻለ አቅጣጫ ለመያዝ ያቀደው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር የቴዎሎጂ ምሩቃንን ከዘመናዊ የስብከት ዘዴና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር በበቂ ሁኔታ ሥልጠና በመስጠት በየዐውደ ምሕረቱ ላይ  የስብከቱን ሥራ እንዲያከናውኑ በማድረጉ ፍልሰቱን በመጠኑም ቢሆን የገታው ይመስላል፡፡ ይህ ሁኔታ ታዲያ ነባሮቹ በስፍራው ለዘመናት ይዘውት የነበረውን የበላይነት ቀስ በቀስ እየሸረሸረው በመሄዱ የተነሳ አዲሶቹን ሰባኪዎች ከፕሮቴስታንቶች የአሰባበክ ስልት አንጻር በመመልከት የጴንጤ ሰባኪዎች እያሉ ማጥላላታቸው አልቀረም፡፡ ይህ ጥላቻቸው ታዲያ በህብረተሰቡም ሆነ በከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ  አለቆች ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ  በወጣቶቹ ሰባክያን ላይ ከቃላት ያለፈ ጉዳት ማምጣት አልቻለም፡፡”
ይህን የቀድሞ ቀሳውስትና ባህታውያንን መንገድ የወረሰውና በዚያ መንገድ ተከታዮችን ለማፍራት እየታተረ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ዛሬ ማህበሩ የተጠመደበት አገልግሎት ትክክለኛውን ወንጌል መስበክ ሳይሆን የተሸቃቀቀጠ ወንጌል መስበክ በየመድረኩ ተሐድሶ መናፍቃን ሊወርሱን ነው የሚል ማስፈራሪያ ማሰማት ነው፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጆቹ ጋር ቅራኔ ውስጥ የከተተው አንዱ ምክንያትም ይኸው ችግር እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
5.   ማህበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ መሆኑ፣
ማህበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ 43 አንቀጽ የያዘ ባለ 36 ገጽ ላይ
1.     ማህበሩ መተዳደሪ ደንቡን ተለልፎ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው
2.    በ1994 ዓ.ም. ተሻሽሎ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ክፍተት አለበት፡፡
1.    ማህበሩ መተዳዳሪያ ደንቡን በመተላለፍ በራሱ አካሄድ ብቻ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው አንቀጽ አራት ተራ ቁጥር 6 ላይ በመመሪያው በኩል በሰንበት ት/ቤቶች ማዳራጃ መመሪያ ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ አካላት ጋር በመነጋገርና በማስፈቀጽ ትምህርተ ወንጌል በተለያዩ ዘዴዎች በመጽሔቶች በጋዜጦች በበራሪ ጽሑፎች በካሴቶች በኢንተርኔት በኤሌክትሮኒክስ መገናኛና በመሳሰሉት እንዲስፋፋ ማድረግ፣ ወጣት ሰባክያንንም ማበረታታት ይላል፡፡ ነገር ግን ማህበሩ በራሱ አካሄድ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን መተዳደሪያ ደንብ በመጣስ ቤተክርስቲያንና ሀገረ የሚያለያይ ጽሑፍ በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣው እና በዌብሳይቱ በማሠራጨት በሀገር ደረጃ ሁከት እንዲፈጠረ እያነሳሳ ይገኛል፡፡
2.   ማህበሩ በ1994 ዓ.ም. ተሻሽሎ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ክፍተት ስላለው በአዲስ መልኩ የማህበረን የሥራ ድርሻ ሥልጣንና ተግባርን የሚገልጽ ከቤተክርቲያኒቱ አሠራርና ጥቅም አንፃር ሊሄድ በሚችል መልኩ ተስተካክሎና ታርሞ ቢሻሻል እንዲሁም ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ያለውን የመዋቅር አሠራር ጠብቆና አክብሮ ሊሄድ በሚችልበት አሠራር ካልተስተካከለ ለቤተክርስቲያኒቱ ህልውናም ሆነ አሠራር ከፍተኛ እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡
“ሌላው ማህበሩ ህልውናም ሆነ አሠራር ከፍተኛ እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው ማህበሩ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንደ ሆነ መተዳደሪያ ደንቡ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ማህበሩ በተዘዋዋሪ መልኩ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ ከቤተክርስቲያኒቱ ዓላማና አቋም ፍፁም የራቀ ድርጊት ነው፡፡ ለምሳሌ በቋሚነት የማህበሩ እንቅስቃሴ፣ ዓላማና አገልግሎት የሚዘገብባቸው የግል ጋዜጦች አሉ፡፡ ስለዚህ ማህበሩ በተዘዋዋሪ መልኩ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሌላ የተደበቀ አላማውን እያራመደ ስለሆነ ይህ ድርጊት የቤተክርስቲያኒቱን ዓላማ ፍፁም ስለሚቃረንና ለቤተክርቲያኒቱ እንደ አጠቃላይ ስሟን የሚያጠፋ ድርጊት ስለሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለበተክርስቲያኒቱ ጥቅም ሲባል እርምጃ እንደወስዱ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

“ማህበረ ቅዱሳን የሚለው ስያሜ በራሱ አጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱን የሚወክል ስያሜ እንጂ አንድ የተደራጀ ኃይል ወይም ውስን ድርጅት የሚያመለክት ስለሆነ ከስያሜው ጀምሮ ማስተካከያ እንዲደረግ እናሳስባለን፡፡” ይላል መግለጫው፡፡
ስያሜውን በሚመለከት ማኅበረ ቅዱሳንና እርሱ ለራሱ የሚወስዳቸው ስያሜዎች ፈጽሞ ዐብረው የማይሄዱ ናቸው፡፡ እንደተባለው ማኅበረ ቅዱሳን በክርስቶስ ያመኑና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው የልጅነትን ማኅተም የተቀበሉ ሁሉ ናቸው፡፡ እርሱ ግን ያለፉትን ቅዱሳን ለመዘከር በሚል ነው ስሙን እየተጠቀመበት ያለው፡፡ እንዲህ ሲያደርግም ክርስቶስን ሸፍኖታል፡፡ ግብሩም ከታየ የማኅበረ ቅዱሳን ሳይሆን ተቃራኒውን ነው፡፡ ስምዐ ጽድቅ የተባለው የጋዜጣው ስምም እንደስሙ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በአብዛኛው ሐሰትና ሽብር የሚነዛበት ጋዜጣ ነውና፡፡
ይህ የኮሌጁ መግለጫ የማኅበረ ቅዱሳንን ትክክለኛ ማንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን፣ የእርሱ ደጋፊዎች ሌሎች ስሙን ለማጥፋት የሚያስወሩት ወሬ ነው የሚሉትን የሁልጊዜ ማስተባበያቸውን ሐሰት ያደረገ መግለጫ ነው፡፡ ማኅበሩ አሁን ባለበት ደረጃ የሚሰራው ሥራ ሁሉ የተገለጸ በመሆኑ ትክክለኛ ማንነቱን ለማወቅ ብዙ ጥናትና ምርምር እንደማያስፈልግ የታወቀ ነው፡፡ ማኅበሩ በሕገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ቢታወቅም አንዳንድ ጳጳሳትን፣ የቤተክህነት ሠራተኞችን፣ የደብር አስተዳዳሪዎችንና የመሳሰሉትን አካላት ለሃይማኖት የቀና በመመስል፣ በጥቅማ ጥቅምና በነውር ሥራቸው ተገዢ በማድረግ ያሻውን እያደረገ ይገኛል፡፡ እንደተባለው በመንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ ማኅበሩ ልቡ ክፉኛ ማበጡንና በማንአለብኝነት አባዜ መያዙን ያሳያል፡፡
በኮሌጆቹ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በከፈተበት ጋዜጣ ላይ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ስም ለደቀመዛሙርትና ለመምህራን ነጻ የትምህርት ዕድል መስጠቱን ያወጀ መሆኑና በተመሳሳይም ኮሌጆቹ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው ማለቱ ኮሌጆቹን አሳጥቶ እኔ አሁን ያዘጋጀሁላችሁ ነጻ የትምህርት ዕድል ይሻላችኋል ለማለት ነው የሚሉ ወገኖች፣ ይህን የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተበት ወቅት ደግሞ በኦሮሚያና በጎንደር አካባቢ ተከሥተው የነበሩ ግጭቶችን ጠብቆ መሆኑ ድብቅ ዓላማውን የሚያሳካበት ጊዜ የደረሰ ስለመሰለውና ተመሳሳይ ሁከት ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ተፈጥሮ ሥልጣኑን እርሱ ለመቆጣጠር በማቀድ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ይህም ማኅበሩ በሂደት የቤተክርስቲያኒቱን የሥልጣን መዋቅር ለመቆጣጠርና በእጁ ለማስገባት እየተንቀሳቀሰ ያለ ማኅበር መሆኑን ያሳያል፡፡ አሊያ ብዙ ችግር ውስጥ ገብቶና ከብዙዎች ተጋጭቶ የሚገኘው ማቅ በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ድፍረት ከየትም አያመጣውም ይላሉ፡፡
ስለዚህ ለሆዳቸው ያደሩትንና በጥቅማ ጥቅም የተገዙትን እንዲሁም ነውራቸውን ይዞ ተገዢው ያደረጋቸውን አንዳንድ ጳጳሳትና በየመዋቅሩ ውስጥ የሚገኙትን አይዞህ ባዮቹን ነጻ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማኅበር በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የራሱን አጀንዳ ጭኖ ቤተክርስቲያኒቱን እያስጨነቀና ብዙ ጥፋት እያደረሰ ነው፡፡ አቡነ ጳውሎስ ማኅበሩ ካደረሰው ጥፋትና ከሚንቀሳቀስበት ሕገ ወጥ መንገድ የተነሣ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ሲችሉ እሹሩሩ ብለው እዚህ አድርሰውታል፡፡ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተደግፎ የቀረበውንና ማኅበሩን ክፉኛ የናጠውን የአባ ሠረቀን ሐቀኛ ትግል የሚደግፉ የሲኖዶስ አባላት ቢኖሩ ኖሮ ነገሩን ባጭሩ መቅጨት በተቻለ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን አልረፈደም፡፡ ማኅበሩ እኩይ ዓላማውን ትቶ ይለወጣል ማለት ግን ዘበት ነው፡፡ በተደጋጋሚ ለቤተክርስቲያን ውሳኔ አልገዛም በማለት እስካሁን እንደ ቀጠለ ሁሉ አሁንም በዚያው መንገድ ነው የሚጓዘው፡፡ ስለዚህ በማኅበሩ ላይ ተገቢውን እምርጃ በመውሰድ ታሪክ መሥራትና ቤተክርስቲያኒቱን ከማኅበሩ ተጽዕኖ ማላቀቅ ከቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ከሲኖዶስ አባል የሚጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ ዛሬ ይህ ካልሆነ ግን ነገ ቤተክርስቲያኗ መከፋፈሏ አይቀሬ ነው፡፡  


25 comments:

 1. እኔ የሚገርመኝ በማያገባችሁ ገብታችሁ መዘባረቃችሁ ብቻ አይደለም መንነታችሁም ለራሳችሁ የጠፋችሁ ይመስላል እናም እራሳችሁን ፈልጉ እራሳችሁንም ሁኑ ለነገሩ ከጸሁፋችሁ እነደምረዳው እራሳችሁን በቤተክህነት ውስጥ የደበቃችሁ ባንዳዎች ናችሁ ኢትዮጵያዊ መልክ ግን ሥራችሁ ኢትዮጵያዊነት የሌለው የፕሮቴስታንት መልክተኞች ተልኳችሁ የሰይጣን ግብራችሁ የሰይጣን ብንሰማችሁ በተበጣበጥን ነበር ግን አልተሳካላችሁም ለምን ?? የቆምነው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተማርነው ትምህርት ስለሆነ ብዙ አትልፉ ጠባቂያችን አያንቀላፋም ባይሆን ወደልቦናችሁ ተመለሱ ክረስቶስንም በሰላሳ ብር የሸጠው ይሁዳ በተከፈለው ብር አላተረፈም ታንቆ ነው የሞተው እናንተ ግን የሚከፈላችሁ የተላላኪነት ክፍያ ህይወት አይሆናችሁምና በምድር ላይ ከምታገኙት ገንዘብ ህይወት ይሻላልና በምህረት ዘመን ምህረት ብትጠይቁ የተሸለነው የምህረት ባለቤት ሰላማዊ ንጉስ ኢያሱስ ክርስቶስ ለሀገራችን ሰላምን ለናንተም ልቦናን ይስጣችሁ ከሰይጣን መልክተኛነት ንሰሀ ገብታችሁ ሕግዚአብሔርን ለመገዛት ያብቃችሁ፡፡

  የቅዱሳን ተራዳይነት የድንግል ማርያም ምልጃ
  የሕግዚአብሔር ምህረት አይለየን
  አጽራረ ኦርቶዶከስን ልቦና ይስጥልን

  ReplyDelete
 2. ይደልዎ ይደልዎ ይደልዎ

  ReplyDelete
 3. ለምን??? ምስጢራችሁ ስለወጣ ነው??? ስራችሁን ነው እኮ ያወጡት??? እኔ በሙሉ አንብቤዋለሁኝ፣ ትክክለኛ መረጃ እንደናንተ ስድብና ነቀፋ የሌለበት ያለውንና የሚታየውን መጥፎ ምግባራችሁን ነው ያሳዩት፤ እግዚአብሔር ይመስገን እነዚህን ለቤተክርስቲያን ቀናኢ ልጆችን ማህበረ ቅዱሳንን ያስነሳ የቤተክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ይባረክና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁንና፡፡ መጀመሪያ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ፡፡ መጀመሪያ ቤተክርስቲያናችሁን ለመሸጥ ከመስማማት ትምህርታችሁን ተምራችሁ በተሰማራችሁበት አገልግሎት አትሰማሩም ነበር??? ከይሁዳነት ባህሪያችሁ ተመልሳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሀ ለብሳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 4. Oh...the protestants are barking. Don't be fooled. Mahibere Kidusan is not about a single association. It's about the faith we all have. As much as you try to defame Mahibere Kidusan, I started to like them more and more. We know what this blog stands for.

  ReplyDelete
 5. ማቅ ማለት በሰዉር አመራር የሚመራ ድብቅ አጀንዳ ያለዉ ነዉ
  መረጃ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

  ReplyDelete
  Replies
  1. Awo Endalkew yihun ena woyanem yidemesesal agerim hager tihonalech tehadisom dirshu yitefal betecrstianim titsenalech,polletical issue binorewus,woyane ye ethiopian hizib alasimererewum litil bileh new???

   Delete
 6. great continue working on it

  ReplyDelete
 7. እናንተስ ለኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃችሁ ይሆን? ወይስ ታሀድሶ ለምን ተነካብን፤ ማኅበሩስ እንዴት ዕቅዳችንን አወቀብን ብላችሁ? የምትጽፉትን እኮ ስናነበው ነው የኖርነው፤ ሁላችንም እንደ ከዚህ በፊቱ ስንወናበድላችሁ የምንኖር አይምሰላችሁ፡፡ አሁን ማን እንደሆን ለቤተ ክርስቲያኗ በትክክል የሚቆረቆረው በደንብ ተረድተነዋል፡፡ ማኅበሩን ሁሉም ጠልቶታል ከማለታችሁ በፊት እናንተን ምን ያህል እየተጠላችሁ እንደሆነ ከሚጻፉላችሁ አስተያየቶች ተረድታችሁ ራሳችሁን ለመፈተሸ ሞክሩ፡፡ አያ ጅቦ ሳታማሀኝ ብላኝ አለች -------

  ReplyDelete
 8. ማህበረ ቅዱሳንን ከቤተክርስቲያን ላይ ያንሳልን!!!!!

  ReplyDelete
 9. Merdokyos vs Hama? Metshafe Aster; nitseha bitigebu yishalal!!

  ReplyDelete
 10. ለምን አያገባቸውም? አንንተም ያገባኛል ብለህ ዘባርቀቀሃል! ማንነትህስ ማን አወቀው?

  ReplyDelete
 11. በእዉነት እኔ ከሁለታችሁም ወገን አይደለሁም ነገርግነ
  የቤተክርስቲያኒቱ ኮሌጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቁ
  የሚለዉ ጽሁፍ በስድብ የተሞላ ለምሰሌ ማቅ፤ ስምአ ሀሰት ሌሎችም የማልጠቀሳቸዉ ስድቦች
  ለምን እንደዘሂህ ከሚሆን ማህበረ ቅዱሳንን ይህንን ዉንጀላ ያቀረብከዉ ከምን ተነስተህ ነዉ የጽሁፍ ፤ የቪዲኦ፤ የፎቶግራፍ መረጃ አቅርብና ቤተክርስቲያንን በቢመራዉ አካል በቅዱስ ሲኖዶስ የሶስቱም መንፈሳዊ ኮሎጆች ተወካዮች የማህበረቅዱሳን ተወካዮች ተገኙና ማህበሩም መረጃዉን ያቅርብና ተነጋገሩበት እነማን ከነዚህ ከ 3 ኮሌጆች መናፍቅ ሆኖ እንደተመረቀ ያሳይ በተጨማሪም ከነዚህ ኮሌጆች የወጡ በአገልግሎት በዉችም በአገርዉስጥም የምንፍቅና ትምህርት የሚያስተምሩትን ወደሌላ በረት የተቀላቀሉትን ማህበሩ ያሳይ በነገራችን ላይ በህዝቡ ዘንድ በአማንያኑ ሶስቱም ኮሌጆች በተለያየ ግዜ መናፈቅ የሆኑ ተማሪዎች ተመርቀዉ ወጥተዋል ይሄ ማንም የማይክደዉ እዉነት ነዉ ፡፡ ቢሆንምቅሉ የኮሌጆቹ ዲኖች አስተዳደሮች ሳያቁ እንደሚሆን እገምታለሁ ፡ 100 የዲግሪ የስነመለኮት ተማሪዎች ከ 3ቱም ኮሌጆች ቢመረቁ በርግጠኝነት 20 ያዉ መናፈቅ ሆነዉ ይወጣሉ
  የተቀሩት ደግሞ የተዋህዶ አንበሶች በቅዱስ ቄርሎስ ፤በአትናቲዎስ ፡በተፈጻሜተ ሰመእት በቅዱስ ጴጥሮስ በሃዎርያትና በነቢያት መሰረትላይ ታንተጸዉ ይመረቃሉ ይህንንም ላደረጉ መንፈሳዊ ጥበብን ለተሞሉ ለኮሌጁ ዲንና አስተዳደር እንዱሁም ለሚመለከታቸዉ አካላት ከፈጣሪ ምስጋና ይድረሳቸዉ ፡፡ በሚቀጥሉት የምራቃ ፕሮግራም ደግሞ 20 ዎቹ መናፍቃን ሳይሆኑ የተዋህዶ አንበሶች ሆነዉ ይጨርሳሉ የሚል ተስፋ አለኝ ፡ አባታችን አቡነጴጥሮስ በራሱ ሀገርና ም ድር በ አ.አ ከተማ ከአዉሮፓ በመጡ በመናፍቃን ሃይማኖትህን ቀይር ተከታዮችህም ተዋህዶ የሚለዉን ይተዉና እኛን ይምሰሉ ሲሉት ብዙዎች ለሆዳቸዉ አድረዉ መናፈፍቅ በሆኑበት እምቢ ብሎ በመጽናቱ በስምንት ጥይት ተደብድቦ ሰማእትነትን ተቀበለ የወንጌል እንቅስቃሴ ችቦን ለተዉልድ ካቀበሉ ዋነኛ ጀግኖች አንዱ ለ ወንጌል በህይወትም በሞትም የመሰከረ ፡፡ የተቀሩት ተመራቂዎች በአባታችን በአቡነጴጥሮስ ፈለግ ሆነዉ እንደሚመረቁ ተስፋአለኝ ደግሞ ኮሌጆቹ ተቀናጅተዉ እነዚህን ከየት እንደሚላኩ ማንእንደሚልካቸዉ በጥበብ ማጥናት ከማህበረ ቅዱሳን ጋራ አብሮ በጋራ መስራት ቤተክርስቲያንን ማሳደግ
  ሁላችሁም ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከሆነ የቆማችሁት የአባቶቻችሁን የቀድሞዉን የድንበር ምልክት ሳታፈርሱ ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጥቅም በጋራ መስራት ይጠበቅባችሁአል፡፡ ሶስቱም ኮሌጆች አንቱ የተባሉ መምህራንን እንዳስመረቁ በምግባራቸዉና በአስተምህሩአቸዉ ፍጽም ሃዋርያትን የመሰሉ የቤተክርስያን የቁርጥ ቀን ልጆች እንዳፈሩ አሌየማይባል እዉነትነዉ፡ እንደሂዚሁ ሁሉ ሶስቱም ኮሌጆች አንቱ የተባሉ መናፍቃንን አጽራረ ቤተክርስቲያንን አፍርተዋል፡፡ ማህበረቅዱሳን ደግሞ ለቤተክርስቲያን ዘብ በመቆም እንዚህን 20 መናፍቅ ሆነዉ የሚመረቁትን የተሰማሩበትንና የሚያስተምሩትን ትምህርተ ያዉቃል ካባቶች ትምህርት ያፈነገጠ የእዉነተኛዉ የወንጌል ትምህርት ያልሆነ የቤከተክርስቲያን እራስ ከሆነዉ ከጌታ ያልመነጨ እነዚህን እንጂ 80 ዎቹ ምሩቃንን አይከታተላቸዉም ለምን የተዋህዶ አንበሶች በቅዱስ ቄርሎስ ፤በአትናቲዎስ ፡በተፈጻሜ ሰመእት በቅዱስ ጴጥሮስ በሃዎርያትና በነቢያት መሰረትላይ ታንተጸዉ የተመረቁናቸዉና በአገልግሎትም የመስሉታልና፡፡
  ማህበሩ ጥሉ ከ 20ዎቹ መናፍቀን ጋርና እነሱን በስዉር አሰልጥነዉ ካወጡት መምህራን ጋር ነዉ፡ በእዉነት ለመመስከር መህበሩ መህበረ ቅዱሳን ለክርስቶስ ቤ/ክ መጠበቅ ሲለፋና ሲደክም አዉቀዋለሁ 600,000 የከፍተኛ ተቋም ተማሪ አባላት እንዳሉት ይታወቃል መልካሙን ሃይማኖታዉ ገድል እየተጋደለ ነዉ ፡፡
  3ተም መንፈሳዉ ኮሌጆች ከማህበረ ቅዱሳን ጋር እጅና ጉአነት ሆናችሁ ብተሰሩ አንተ ትብስ እኔ እያላችሁ ሆደሰፊ ሆናችሁ ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ማበብ ብትደክሙ እናንተን ተስፋየምናደርግ በጎች ጎጋዉ ምእምኖች እጅግ እጅግ ደስይለናል የናንተ መስማማት አብሮ መስራት እኛን ምእምናን ዉስጣችንን በሀሴት ይሞላል ስትጣሉ ስትነቋቆሩ ግን ይከፋናል መሄጃዉ ይጠፋናል ተስፋ ያደረግናችሁ እናንተ ስትበጣበጡ ተስፋ እናመነታለን ተስፋእንቆርጣለን ፡፡‹‹ ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል›› ።ምሳ 1፡5 እንዳለ መጻሃፍ አስተዋይሁኑ ለእኛ ምንም ለማናዉቀዉ ምእምናን ናን የጌታችን የክርስቶስ ቤ/ክ እንዳትናጋ መሰረቷን እንዳትለቅ ስትሉ፡፡ ‹‹እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤›› 1ጢሞ 1፡19 እባካችሁ ምእምናን እንዳንጠፋ በጎህሊና ይኑራችሁ፡፡ ክብርና ምስጋና ይችን የክርስቶስን ቤ/ክ በታላቅ ተጋድሎ እዚህ ላደረሱት አሁንም ፈለጋቸዉን ለተከተሉት ፡፡

  ReplyDelete
 12. ‹‹ተረት›› የምትለዋን ተደጋጋሚ ቃል ራሳችሁ ናችሁ የጨመራችሁት፤የኮሌጁ ሰዎች እንደሱ አላሉም፡፡በተረፈ ከሞላ ጎደል ደኅና ዘገባ ሰርታችኋል፡፡ማኅበረቅዱሳን ፕሮቴስታንትና ተሐድሶን ለመዋጋት የሚያደርገው ጥረት ከነኅፀፁ ማንም ዐይን ያለው ሰው ሊያደንቀው የሚገባ ነው፡፡በውጊያው ግንባር በየዐውደምሕረቱ የተሰለፉትን የኮሌጁ ፍሬዎች አብሮ አስተባብሮ እንደመሰለፍ ኃላፊነት የጎደለው ቋንቋ እየተጠቀመ ኮሌጆቹን በጅምላ ማነወሩ ግን ገና አለመብሰሉን ነው የሚያሳየው፡፡ማኅበረቅዱሳን ኮሌጆችን እንደ ርኩስ ከማየት በቅዱስ ሲኖዶስ በጀት የሚተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱ አካላትና በተሰሚነትም ቀላል የማይባል ቦታ ያላቸው መሆናቸውን ተገንዝቦ መቀራረቡ ነበር የሚጠቅመው፡፡ኮሌጆቹን እንዲያ አድርጎ ሲፈርጅ በሞኝነት ርስት መልቀቁ አልገባውም፡፡የኮሌጁን ፍሬዎች በኔትወርክ ሲያገልና ከአለባበሳቸው ጀምሮ ሲያነወር በራሱ ላይ ተቃዋሚ መፍጠሩ አልተገለጸለትም፡፡

  እኔን ያላንቆለጳጰሠ ሁሉ ተሐድሶ ነው እያሉ ለተሐድሶዎቹ ብሎጎች ለነሰላማ የወሬ ማማሟቂያ ከመሆን ከኮሌጆቹ አስተዳደር ጋር ተቀራርቦ ቢሰራ ተሐድሶን ከዚህም በላይ መዋጋት ይቻል ነበር፡፡ከዚህም ከዛም፤ካገር ውስጥም ካገር ውጭም መቆራቆሱን እንደ መልካም ሥራ ቆጥረውት ሁሉንም እጎነተሉ ከሰው ሲነጠሉ ‹‹ሁሉም የቤተክህነት እና የኮሌጅ ሰው ተሐድሶ ስለሆነ ነው የሚጠላን›› ማለታቸው አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ያላዋቂ አማተር ንግግር ነው፡፡ውስጣዊ ትዕቢትም አለች፡፡ቤተክርስቲያን በማኅበረቅዱሳን ጥረት ብቻ ያለች ይመስላቸዋል፡፡እንዲያ ሲሉ ከተቀረው ቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ መነጠላቸው አልተገለጸላቸውም፡፡

  በትርፍ ጊዜ በሚያገለግሉ የማኅበር አባላት ብቻ አይደለም ቅድስት ቤተክርስቲያን የቆመችው፡፡በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የሙሉ ሰዓት ካሕናትና ሰባክያን አሏት፡፡ይደከምም ይጠንክርም ከወረዳ እስከ ማዕከላዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የተዘረጋ የራሷ መዋቅር አላት፡፡ይሕን እውነት አድበስብሶ እኔ ብቻ ነኝ ዐይኗ፣እኔ ብቻ ነኝ የጀርባ አጥንቷ፣እኔ ብቻ የስስት ልጇ፣እኔ ብቻ እንደ ዮሐንስ ስትሰቀል ከስር ቆሜ የተገኘሁት ብሎ ከድርሻ በላይ መታበይ የተሳሳተ አካሄድ ነው፡፡በዚህ አካሄዱ ማኅበሩ በላይኛው መዋቅርና በፓትርያርኩ ብቻ ሳይሆን በተራ ካሕናትና በልዩ ልዩ የአገልግሎት መስክ በተሰማሩ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችም ይወቀሳል፡፡የማኅበረቅዱሳን አባላት ይህን አካሄድ አርመው ሁላችንም የቤተክርስቲያን ልጆች ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፕሮቴስታንትንና የእሱ ቅጥረኛ እግረኛ ወታደር የሆነውን ተሐድሶ መክሮ አስተምሮ ለመመለስ፤ያልተመለሰውንም ከውስጣችን በውግዘት ለማጥራት የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን፡፡አሜን፡፡

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሔር ይመስገን እነዚህን ለቤተክርስቲያን ቀናኢ የሆኑ ልጆች ማህበረ ቅዱሳንን ያስነሳ የቤተክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ይባረክና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን:: ዕቀብ ማኀበርነ ማኀበረ ቅዱሳን

  ReplyDelete
 14. wa enant sawech btarfw ysalachal ydengle Maryam yasrat legwech endhwenew enanten man endhnach ywkwchal benant wera ymwenabed yalam har tkawec!! egezabher amlak ymhber kidusan lgachen ytabklem enantanme lnsha ybkach egan abatochachen sedeb alstmarnem ewntwen endglaslacheh enslylachalen nsh geg tmlesew atsfew wganwech amen!!

  ReplyDelete
 15. እናንተ ይሁዳዳዎች እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ እንዲህ የሰይጣን እና የሰራዊቱ መጫወቻ ትሆኑ ለንስሀ ሞት ያብቃችሁ ምድረ መናፍቃን ቅጥረኛ ሁላ ሀራጥቃ አይሆንም ዕቃ።

  ReplyDelete
 16. አባሰላማዎች በእውነት በጣም የሚግረም ነው ይህቺ ቤ/ክርሰቲን ያለሰው ለማሰቀረት ቀን ለሌሊት ሚሰራውን ማቅ ይባስ ብሎ ቤ/ክርስቲያን ከቁጥር የማይጋቡትን መንፍሳዊያ ኮሌጅ ለማዘጋት መሞከር አንድ አይን ያለሁን ሰው ይችኑ ዓይኑን ማጥፋት ማለት ነው ፡፡

  ReplyDelete
 17. ሊበሏት ያሏት ምን ምን ይሏታል እንደሚባለው ገናለገና ማህበሩን የማጥፋት ስራችሁ አልተሳካ እንደሁ በሚል "ይህ ካልሆነ ግን ነገ ቤተክርስቲያኗ መከፋፈሏ አይቀሬ ነወው" ብላችሁ

  መተንበይ ጀመራችሁ አይደል፡፡

  ReplyDelete
 18. እኔ የሚገርመኝ በማያገባችሁ ገብታችሁ መዘባረቃችሁ ብቻ አይደለም መንነታችሁም ለራሳችሁ የጠፋችሁ ይመስላል እናም እራሳችሁን ፈልጉ እራሳችሁንም ሁኑ ለነገሩ ከጸሁፋችሁ እነደምረዳው እራሳችሁን በቤተክህነት ውስጥ የደበቃችሁ ባንዳዎች ናችሁ ኢትዮጵያዊ መልክ ግን ሥራችሁ ኢትዮጵያዊነት የሌለው የፕሮቴስታንት መልክተኞች ተልኳችሁ የሰይጣን ግብራችሁ የሰይጣን ብንሰማችሁ በተበጣበጥን ነበር ግን አልተሳካላችሁም ለምን ?? የቆምነው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተማርነው ትምህርት ስለሆነ ብዙ አትልፉ ጠባቂያችን አያንቀላፋም ባይሆን ወደልቦናችሁ ተመለሱ ክረስቶስንም በሰላሳ ብር የሸጠው ይሁዳ በተከፈለው ብር አላተረፈም ታንቆ ነው የሞተው እናንተ ግን የሚከፈላችሁ የተላላኪነት ክፍያ ህይወት አይሆናችሁምና በምድር ላይ ከምታገኙት ገንዘብ ህይወት ይሻላልና በምህረት ዘመን ምህረት ብትጠይቁ የተሸለነው የምህረት ባለቤት ሰላማዊ ንጉስ ኢያሱስ ክርስቶስ ለሀገራችን ሰላምን ለናንተም ልቦናን ይስጣችሁ ከሰይጣን መልክተኛነት ንሰሀ ገብታችሁ ሕግዚአብሔርን ለመገዛት ያብቃችሁ፡፡

  የቅዱሳን ተራዳይነት የድንግል ማርያም ምልጃ
  የሕግዚአብሔር ምህረት አይለየን
  አጽራረ ኦርቶዶከስን ልቦና ይስጥልን

  ReplyDelete
 19. ለምን??? ምስጢራችሁ ስለወጣ ነው??? ስራችሁን ነው እኮ ያወጡት??? እኔ በሙሉ አንብቤዋለሁኝ፣ ትክክለኛ መረጃ እንደናንተ ስድብና ነቀፋ የሌለበት ያለውንና የሚታየውን መጥፎ ምግባራችሁን ነው ያሳዩት፤ እግዚአብሔር ይመስገን እነዚህን ለቤተክርስቲያን ቀናኢ ልጆችን ማህበረ ቅዱሳንን ያስነሳ የቤተክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ይባረክና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁንና፡፡ መጀመሪያ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ፡፡ መጀመሪያ ቤተክርስቲያናችሁን ለመሸጥ ከመስማማት ትምህርታችሁን ተምራችሁ በተሰማራችሁበት አገልግሎት አትሰማሩም ነበር??? ከይሁዳነት ባህሪያችሁ ተመልሳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሀ ለብሳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. Enter your comment...አይ አባ ሰላማዎች መጨረሻችሁ እንዲህ ሆነ፡፡

  ReplyDelete
 21. ኮሌጆቹ ህግ ተጥሷል ካሉ ወደ ፍ/ቤት መሄድ ነዉ! ደግሞም የጥል ደቦ የለውም!

  ReplyDelete
 22. ''Kefreachew tawkuachulachu'' ale geta....yihew freachu yesidb af endetesetew diablos sidb, yewendmoch kesash endetebalew seytan kis bicha new...ewnetegna yekrstos lijoch bithonus wongeln akntachu besebekachu neber....neger gin zerachu kewendmoch kesash, kehaset abat kediablos endehone freachu geletew.....ahun and neger bewendmawi fikr elachuhalew....''genzebin mewded yekifat hulu sir newna'' yihuda kirstosn endeshete enantem betekirstiyanin shetachu yemitagegnut genzeb yemitbelut aymselachu....''bekentu yakemachalu yemisebesbuletin gin ayawkum'' endetebale...yihudam yan ye'amets genzeb albelam rasun lemot darege enji.....rasachihun lemot atidargu bemedan ken bemihret amet mengedachihun mermiru temelesum..... ''egziabher siran hulu yetesewerewnm neger hulu, melkamim bihon kifum bihon wede fird yametawalna.''

  ReplyDelete
 23. ስለ አባ ሰላማ ብሎግ

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ፤ ከሳቴ ብርሃን እየተባሉ የሚጠሩት አባት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ ዕድገት ያደረሱ ባለውለታ አባታችን ናቸው። ይህች ብሎግ የእርሳቸው መታሰቢያ ትሁንልን።
  ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እየተባባሱ የመጡ አመጻዎችን፣ ክህደቶችና የስሕተት ትምህርቶችን፣ በማጋለጥ ማስጠንቀቂያዎችንና ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጀች ናት።
  እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
  ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
  ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁሉንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ራሱንም ከወንበዴዎች እንዲጠብቅ ለመርዳት ነው። እውነተኛ ላልሆኑ መረጃዎች አባ ሰላማ ኃላፊነት አትወስድም። እግዚአብሔር አይለየን!

  ReplyDelete
 24. SELETAWOKEBACHIW NEW ESHI MECHEM BIHON mabere kidusan yinoral lenanye gin lib yistachiw tuti nekashoch

  ReplyDelete