Monday, February 29, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተላለፈለትን ትእዛዝ ወደ ድርድር ቀየረውለቤተ ክርስቲያን ከእኔ በላይ የለም በሚል ትዕቢት ተወጥሮ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ጊዜ በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች ቤተክርስቲያንን ሲያውክና ሲበጠብጥ የኖረው፣ ለብዙ ምእመናን ፍልሰት ዋና ምክንያት የሆነው፣ በርካታ የቤተ ክርስቲያን መምህራንንና አገልጋዮችን ሲያሳድድና ሲያፈናቅል የኖረው ይህም አልበቃ ብሎት የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት የተሐድሶ መፈልፈያዎች ናቸው ብሎ በጅምላ በመፈረጅ ከኮሌጆቹ በቀረበበት ተቃውሞ አጣብቂኝ ውስጥ የገባውና ስለጥፋቱ በ5 ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በቁጥር 248/382/2008 በቀን 16/06/2008 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የ5 ቀናት ቀነ ገደብ የተሰጠው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ይቅርታ መጠየቅ ከብዶት ሲታሽ ከሰነበተ በኋላ ቀነ ገደቡ በሚያበቃበት ዕለት በቀን 21/06/2008 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ይቅርታ ሊጠይቅ የሚችለው ከድርድር በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ ከተሰማው መሆኑን ገለጸ፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ማንነትና ባሕርይ አንጻር እንዲህ እንደሚያደርግና ይቅርታ እንደማይጠይቅ የብዙዎች እምነት ነበር፡፡ ምክንያቱም ማኅበሩ ስለራሱ ያለው ግምት በደብዳቤው ለይምሰል የዘበዘበው “ላጠፋ እችላለሁ” የሚል ትሑት ማንነት ሳይሆን ፍጹም ነኝ አልሳሳትም የሚል ትዕቢተኛ መንፈስ ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ መንፈሳዊ ኮሌጆቹን የመናፍቃን መፈልፈያዎች ሆነዋል ማለቱ በግልጽ እየተነበበ እያለ እርሱ ግን በደብዳቤው ላይ ጋዜጦቹ “አይሉም” ሲል ሸምጥጧል፡፡ በዚህም ራሱን ትክክለኛ በጅምላ የተዘለፉትንና ተሰድበናል ያሉትን እንዲሁም በደብዳቤ ጭምር የማስተካከያ ጽሑፍ እንዲያወጣ የጠየቁትን ኮሌጆች (ለምሳሌ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅን) ተሳስተዋል እያለ ነው፡፡ ይህም የትዕቢቱ ልክ የት እንደ ደረሰና እስካሁን የጥፋተኝነት ስሜት እንደማይሰማው  የሚያሳይ ነው፡፡ 

Friday, February 26, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል በማኅበረ ቅዱሳን ኢመዋቅራዊ አደረጃጀትና ሥራ ግድፈቶች ላይ ባለ19 ነጥብ መግለጫ አወጣ፡፡ምንጭ፡- www.addisababa.eotc.org.et
የአቋም መግለጫው ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ስም እየፈጸመ ያለውን የመዋቅር ጥሰትና ሕገወጥ ድርጊቶችን ሁሉ ያጋለጠ ሲሆን በተለይም በቅርቡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ኮሌጆች ስማችን ጠፍቷል በሚል ላቀረቡት አቤቱታ የሰጡትን አባታዊ መመሪያ በመቃወም ደብዳቤ የጻፈውን ማህበረ ቅዱሳንን በጽኑ የሚያወግዝ መግለጫ ነው፡፡ በሀገረ ስብከቱ ድረገጽ ላይ የወጣው የስብሰባው ቃለ ጉባኤና መግለጫ ሙሉ ቃል እነሆ

ብዛቱ እስከ 2000 የሚገመተው ይህ ጉባኤ የካቲት 17 ቀን 2008 . በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በመገኘት ማህበረ ቅዱሳን በመዋቅር የለሽ አሠራሩ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ  በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑን በማስመልከት አስፈላጊው ርምጃ ይደረግበት ዘንድ ጉባኤው በስፋት ከተወያየ በኋላ ባለ 19 ነጥብ  የአቋም  መግለጫ አውጥቷል፡፡

 
የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ እና አቋም መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

በጉባዔው መጀመሪያ የጉባዔው ሰብሳቢ እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚታዩ ሁኔታዎችን በማስመልከት የመግቢያ ንግግር አድርገዋል፡፡

Thursday, February 25, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥር የሚገኙ ሠራተኞች የማቅን እኩይ ተግባር አወገዙ“ሰይጣንን በጸሎት እናርቀዋለን ማቅን በምን እናርቀዋለን?” ከተሰብሳቢዎች አንዱ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት አለቆች ጸሐፊዎች ሂሳብ ሹሞች ቁጥጥሮችና ሰባክያነ ወንጌል በትናትናው ዕለት ባደረጉት ስብሰባ የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር አወገዙ፡፡ ይህ የሆነው ቤተክርስቲያን ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ለመወያየትና ውሳኔ ለማሳለፍ በተጠራው ስብሰባ ላይ ሲሆን የስብሰባውን ዓላማ ያብራሩት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ስለሀገርና ስለሰላም አጥብቃ የምትጸልይው ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በገዛ አማኞቿ ሰላሟ ድፍርሶባት ትገኛለች፡፡ ችግሩን ከሌላው ጊዜ ይልቅ የተወሳሰበ ያደረገው ድርጅታዊና ዘመናዊ ቅርጽን የያዘ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ቅዱስ ፓትርያርኩንም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚገዳደሩ አካላት ስለተፈጠሩ ይህን በጽኑ መቃወም ይገባናል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ሰለባ ያደረጉት ደግሞ እናንተን ነው፡፡
ሥራ አስኪያጁ አክለው እንደ ተናገሩት እነዚሁ አካላት ቅዱስ ፓትርያርኩንና ቅዱስ ሲኖዶስን የመለያይ ጽሑፍ በተከታታይ አውጥተዋል፡፡ ቤተክርስቲያን ሳታውቀው የራሳቸውን ሥርዓተ ትምህርት የቀረጹ ናቸው ካሉ በኋላ አንድ ምእመን ከፓትርያርኩ ትይዩ በዓለማዊ ጋዜጣ መልስ ሲሰጥ ትክክል ነው ትላላችሁ? ሲሉ ጉባኤውን የጠየቁ ሲሆን ምእመን ብለው የጠቀሱት በጅምላ ክህነት የክብር ቅስና ካላቸው የማቅ ሰዎች አንዱ የሆነውና የወቅቱ የማቅ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሙ ምትኩን መሆኑ በተሰብሳቢዎቹ ዘንድ ግንዛቤ ተይዟል፡፡

Wednesday, February 24, 2016

“ቤተ ክርሰቲያናችን በቅኝ ግዛት ... በቅኝ ገዢዎች ተይዛለች፡፡” (ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ)
ከዲያቆን ኢሩባኖን ዘኢየሱስ
    ክፍል 1
 ቤተ ክርስቲያን በነጻነት ዘመን ከምትፈተንባቸው ዋና ነገሮች አንዱ አለማዊነት ነው፡፡ በመከራ ዘመን የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ትልቁንና ዘላለማዊውን ተልዕኮዋን መቼም ሳትዘነጋ በጽናት የእውነትንና የመዳንን ወንጌል ሰብካለች፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ወንጌልን መስበኳ ብቻ ሳይሆን በሰማዕትነት ዘመኗ በጭካኔያቸውና በፍጹም አሳዳጅነታቸው የታወቁ መሪዎችንና ወታደሮችን ጭምር ፊታቸውን ወደክርስቶስ ዘወር እንዲያደርጉ በተጋድሎ አሳይታለች፡፡
    ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን “ነጻነትን” ሲሰጥ ቤተ ክርስቲያንን “ብቻዋን” ሊተዋት የወደደ አይመስልም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት እኩል ሊሰማ እንዲችል መንገድን ለራሱ አበጀ፡፡ [i] ስለዚህም የጳጳሳት ጉባኤ በሚደረግበት “በማናቸውም ጊዜ” በሰብሳቢነት ወይም እንደ“የበላይ ጠባቂነት” መገኘትን “አዘወተረ”፡፡ ከፍ ሲልም ውግዘት እንዲሻር እስከማዘዝ ደረሰ፡፡ [ii] ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ኬልቄዶናውያን “ጳጳሳት” በኋላ ዘመን “መለካውያን” [iii] ለመሆን ያበቃቸው ጅማሬው በታላቁ ቆስጠንጢኖስ ያቆጠቆጠው የቤተ ክርስቲያን ንጉሣዊ ጣልቃ ገብነት ሥር ሰዶ ፍሬ በማፍራቱ ምክንያት ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡

Sunday, February 21, 2016

በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሁከት ፈጣሪዎች የማቅ ተላላኪዎች ታሠሩ ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃልከፍተኛ ሙስናና ልዩ ልዩ የማጭበርበር ወንጀሎች ሲፈጸሙበት በቆየው የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማሳኞቹና ሙስናቸውንና ልዩ ልዩ ወንጀሎቻቸውን ለመሸፈን በሚል ሁከት የፈጠሩትን የማኅበረ ቅዱሳን ጀሌዎች ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ ከዚህ ቀደም እየተፈጸመ የነበረውን ሙስናና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ስናጋልጥ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ሐራ ዝምታን መርጣ መቆየቷና የማቅ ጥቅም በተነካ ጊዜ ግን በተቃራኒው ስትጽፍ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን አሁንም በሁከት ፈጣሪዎቹ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የማቅ ጀሌዎች ለምን ተነኩ በሚል የፈጸሙትን ወንጀልና ሕገ ወጥ ድርጊት በመደገፍ አሰፋሪ ዘገባ አውጥታለች፡፡ የሁከት ፈጣሪዎቹን ጥፋትም እንደ ጽድቅ ሥራ በመቁጠር አበጃችሁ ከማለትም ወደኋላ አልተመለሰችም፡፡
እነዚህ ከማቅ አይዟችሁ የሚባሉት ሁከት ፈጣሪዎች በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱስ ፓትርያርኩንም ሆነ ሀገረ ስብከቱን አናውቅም ብለው እስከ መናገር የደረሱ ሲሆን፣ በተለይም ወረቀት በመበተን ጭምር ደብሩ ውስጥ ሁከት ለመፍጠርና በዚህም የፈጸሙትን የሙስና ወንጀል ለመሸፈን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራ ለማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ለቤተክርስቲያን የቆመች ባለመሆኑ ሁከት ፈጣሪዎቹ የፈጸሙትንና በማስረጃ የተረጋገጠውን ወንጀላቸውን በመሸፈን ወይም እንደ ጽድቅ በመቁጠር ይህን ወንጀል ለማጋለጥ የሠሩትንና ነገሩን ወደብርሃን ያወጡትን በመኮነን ጽፋለች፡፡ በዚህም የሐራ ውሸት ቆሞ በእግሩ መሄድ መጀመሩን መመልከት ተችሏል፡፡ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማቅ መቆሟንም በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ላይ ሙስና እየተፈጸመ፣ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ሲፈጸሙም እንደ ጽድቅ በመቁጠር በርቱ ግፉ ማለቷ ፀረ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን በተግባር አስመስክራለች፡፡ 

Tuesday, February 16, 2016

ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ እንደ ገና ሊጤኑ ይገባልከዘሩባቤል
ክፍል ሁለት
ባለፈው ጽሑፌ የጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ በማጠቃለያው ካወጣቸው የአቋም መግለጫዎች መካከል በ7ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሰፈረውን ነጥብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሊያጤነው እንደሚገባ መጠቆሜ ይታወሳል፡፡ ለዛሬው ደግሞ በተራ ቁጥር 8 ላይ የሰፈረውን ነጥብ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ በቅድሚያ ግን ነጥቡን ለማብራራት መንደርደሪያ የሚሆነኝን አንድ መወድስ ላቅርብ፡፡
መወድስ
የዋሀ እስራኤል ሮብዓም ኀሣሤ ልቡና
እምክረ ሊቃውንት ዐባይ ምክረ ሕፃናት ንስቲተ
አሜሃ ኢረብኀ ወኢተበቍዐ ጽሚተ
አማሰነ አላ ነገደ ዐሠርተ
ሕዝበ እስራኤል እስከ አፍቀሩ
እም አምልኮ አምላክ ልዑል ጣኦታተ ንኡሳተ
ሲኖዶስሂ ፍንወ ጽድቅ ዘኢየአምር ጽድቃተ
እም አፍቅሮ ወርቅ ምክረ ዐመፃ ኀበ ኀበ ይፈርህ ማኅበራተ
ቤተ ክርስቲያን ቤቶሙ ዘደመ ኢየሱስ ጽሪተ
አውፅአ ወሰደደ ብዙኀ ሊቃውንተ
ቅኔው ከሰሎሞን በኋላ የነገሠው ርብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ሰምቶ የሕዝበ እስራኤልን ቀንበር ማቅለል ሲገባውና እስራኤልን አንድ አድርጎ ማስተዳደር ሲችል በባልንጀሮቹ ወጣቶች ምክር ተነድቶ ምንም እንዳልተጠቀመና ዐሥሩን ነገደ እስራኤል እንዳጣ ሁሉ (1ነገሥት 12፥1-24) በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ሥር የወደቀውና በእነርሱ ሳንባ እየተነፈሰ ያለው ሲኖዶስም በሊቃውንት ምክር መሄዱን ትቶ በአንዳንድ ውሳኔዎቹ በማቅ ምክር በመነዳት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ከቤተ ክርስቲያናቸው እያወጣ በማሳደድ ላይ መሆኑንና ሌሎችንም የሚጎዱና ሲኖዶስን ትዝብት ላይ የሚጥሉና ተግባራዊነታቸው የሚያጠራጥር ውሳኔዎችን እንዲወስን እየተደረገ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ 

Friday, February 12, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ እንዲጠይቅ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ወሰነ


ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ቆሜያለሁ እያለ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳውያን ተቋማትን በጅምላ የዘለፈውን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ የካቲት 3/2008 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ማኅበሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ ካልሆነም በሕግ እንዲጠየቅ ወሰነ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና ምክትል መምሪያ ኃላፊዎች ይህን የወሰኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ በጠሩት ስብሰባ ላይ ማኅበሩ እየፈጠረ ባለው ወቅታዊ ችግር ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በጋራ በወሰኑት ውሳኔ ነው፡፡
በዚህ አቋም በተወሰደበት ወሳኝ ስብሰባ ላይ ብዙዎቹ የመምሪያ ኃላፊዎች ባልተጠበቀ መልኩ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ይህም የማኅበሩ ጥፋት የት ላይ እንደደረሰ ትልቅ ማሳያ ሆኗል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ አዕላፍ ያዝአለም ገሠሠ በታላቅ ቁጭት “ላለፉት 2ዐ ዓመታት ይህ ማህበር ቤተ ክርስቲያንን እያስጨነቃትና እያሸማቀቃት ነው፡፡ እንዴት መፍትሔ የሚሰጥ ጠፋ? ይህች ቤተ ክርስቲያን ደርግን የሚያህል አምባገንን መንግሥት ተጽዕኖ ተቋቁማ ነው እዚህ የደረሠችው፡፡ አሁን ይህ ማህበር እየሠራበት ያለው ግፍ ከደርግ በላይ ነው” ብለዋል፡፡ “ሃይማኖት የለሾችን የተጋፈጠች ቤተ ክርስቲያን አሁን በእነሱ ተቸግራለች” ሲሉ ማቅ እየፈጠረ ባለው ችግር ቤተክርስቲያን መታወኳን አብራርተዋል፡፡

Thursday, February 11, 2016

አባ ማቴዎስ ጉዴን ያወጣብኛል በሚል ሥጋት ለእምነት የለሹ ዘሪሁን ሙላቱ ወደ ሥራው እንዲመለስ ደብዳቤ ጻፉለት - ደብዳቤውን ኮሌጁ አልተቀበለውም

Read in PDF

በስነ ምግባር ጉድለት ከቅድስት ስላሴ ኮሌጅ የተባረረውን እምነት የለሹን ዘሪሁን ሙላቱን ወደ ስራው እንዲመልሰው ሲሉ ለቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በቁጥር 1691/6090/2008 በቀን 18/5/2008 ዓ.ም የጻፉት ደብዳቤ በኮሌጁ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸው ማቅ ተሐድሶ ነው ብሎ የከሰሰውን ሁሉ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ከሥራና ከደመወዝ በማገድ ብዙዎችን ለረሃብና ለችግር በመዳረግ አቻ ያልተገኘላቸው አባ ማቴዎስ፣ ይልቁንም ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤ ትይቶና ያለ ጥፋታቸው ይቀርታ እንዲጠይቁ ተደርጎ በይቅርታ እንዲመለሱ የተጻፈላቸውን ሰዎች ጭምር በምህረት የለሽና ጨካኝ ልባቸው ውሳኔ ሲያባርሩ የቆዩት አባ ማቴዎስ  ለእምነት የለሹ ዘሪሁን የይመለስ ደብዳቤ በአስቸኳይ መጻፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ግን ዘሪሁን ቶሎ እንዲጽፉለት ያደረገው የአባ ማቴዎስን ገበና አወጣለሁ በማለቱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
አባ ማቴዎስ በምንኩስና የቂርቆስ አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዜ እዚያው አካባቢ የታወቀች ሴት ሚስት እንደነበራቸውና ይህ ቤተክርስቲያኑ አካባቢ በሁሉም አገልጋዮች ዘንድ የሚታወቅ መሆኑን በአሁኑ ወቅትም ስድስት ኪሎ አካባቢ አንዲት ሴት በማስቀመጣቸው ቅዳሜና እሑድን እዚያ እንደሚያሳልፉ ዘሪሁን ስለሚያውቅ በአባ ሳሙኤል ላይ የጳጳሱ ቅሌት ብሎ እንደጻፈ አሁንም በአባ ማቴዎስ ላይ እጽፍና አወጣለሁ ብሎ በማስፈራራቱ ደብዳቤው እንደተጻፈለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአባ ማቴዎስ ማንነትና ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ይህንና ያልተነገሩና ሌሎች መረጃዎችን ወደፊት በአስፈላጊው ጊዜ እናቀርባለን፡፡ ይህን የምናደርገው የሰውን ገበና በማውጣት የምናገኘው ጥቅም ኖሮ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ እያካሄዱና ለዚያ ሽፋን እየሰጡ ያሉ አንዳንድ ጳጳሳትና የቤተክህነት ባለስልጣናት እንዲያ የሚያደርጉት ገበናቸው እንደዘሪሁን ባሉ ገበናን ገላልጠው መጽሐፍ በሚጽፉ ግለሰቦች እና እንደማኅበረ ቅዱሳን ባሉ ቡድኖች “ምስጢርዎን እንጠብቃለን ያ የሚሆነው ግን እኛን ደግፈው ሲቆሙና የምንሻውን ሲፈጽሙልን ነው” ስለሚባሉ ምናልባት ተሸማቀው ከሚኖሩ ነጻ እንዲወጡ በማሰብና የሚያካሂዱትን ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ ትተው ንስሀ እንዲገቡና ለቤተክርስቲያን መለወጥና መሻሻል እንዲሰሩ ለማገዝ ነው፡፡    

Tuesday, February 9, 2016

ድብቅ ተልእኮ ያላቸው ፀረ ወንጌል ቡድኖች እውነተኛ አገልጋዮችን እያሳደዱ ነው


Read in PDF

ወንጌልን የማመንና የመስበክ አንዱ ውጤት ከዓለም ተቃውሞንና ስደትን ማስተናገድ ነው፡፡ የወንጌልን ቃል የተረዱ፣ ያመኑና የሚሰብኩ አገልጋዮች ይህ የማይቀር ዕጣ ፈንታቸው እንደ ሆነ ያውቁታል፡፡ በወንጌል ያላመኑና ለወንጌል ሳይሆን ለሃይማኖታቸው የቆሙና ለእግዚአብሔር ያለ ዕውቀት የቀኑ የሚመስላቸው ሰዎች ደግሞ እውነተኛ አገልጋዮችን ሌላ ስም ሰጥተው ማሳደዳቸውና በዚህም እግዚአብሔርን እንዳገለገሉ የሚቆጥሩበት ሁኔታ መኖሩ ሁሌም ያለ ክሥተት ነው፡፡ በዚህ ምድር ይህ ሁኔታ መቀጠሉ የማይቀር ቢሆንም ጌታችን በክብር ሲገለጥ ግን እንዲህ በሚያደርጉት ላይ በፍርድ እንደሚገለጥና ስለስሙ መከራ የተቀበሉትን ደግሞ እንደሚያከብር እውነተኛ ነገር ነው፡፡  “ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን። ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው። ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።” (2ተሰ. 1፥3-7)፡፡
ይህን እውነት ባለማስተዋል በእውነተኛ አገልጋዮች ላይ ስደት እያስነሱ ካሉት መካከል የዲሲው / ነጋና መሰሎቻቸው ይገኛሉ፡፡ የዲሲው ደ/ር ነጋ ዓለማየሁ በዚህ ግብር ጸንቶ ለአምስተኛ ጊዜ የቤተክርስቲያን አገልጋይን አባርሯል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ በዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ችግሮችን ሲፈጥር የነበረውና ስውር ተልእኮ ይዞ ወደ ዲሲ ቅዱስ ገብርኤል የገባው ዶ/ር ነጋ አለማየሁ አሁንም ከጥፋቱ ሊመለስ አልቻለም። እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የተፈጠረውን ግርግር በመጠቀም ስልጣን የያዘው / ነጋ እና ተባባሪዎቹ ዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ከስደተኛው ሲኖዶስ ለመለየት የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለዋል። የሲኖዲሱ አባልና ደጋፊ የነበሩትን ካህናት እያባረረ ድብቅ ተልእኮ ያላቸውን እና ክህነት የሌላቸውን ካድሬዎችና የማህበረ ቅዱሳን አባላት እንዲሁም የሐሰት ሰባክያንን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ መቅጠሩን ቀጥሏል። 

Friday, February 5, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ብዙዎቹን ጥፋቶቹን በተዘዋዋሪ በማመን ጥቂት ነጥቦች ላይ ብቻ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ “የእውነት ጠብታ የሌለበት ምላሽ” ሰጠማኅበረ ቅዱሳን በጅምላ ስማቸውን ማጥፋቱን ተከትሎ መንፈሳዊ ኮሌጆች ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ላቀረቡት አቤቱታ፣ ፓትርያርኩ ለመንፈሳዊ ኮሌጆች በሰጡት ምላሽ ክፉኛ ማዘኑን ገልጾ ምላሽ መጻፉን ሰንደቅ ጋዜጣ የጥር 25 ዕትም ዘግቧል፡፡ ማኅበሩ በፓትርያርኩ ከተገለጹት 12 ጥፋቶቹ መካከል ለመከላከል የሞከረው በጣም ጥቂቶቹን ሲሆን እነርሱንም ቢሆን በደፈናው ንጹሕ ነኝ በሚል መንፈስ እንጂ በማስረጃ በማስደግፍ ለመከላከል አልሞከረም፡፡ በቅዱስነታቸው የተነሡትን አንኳርና አሳማኝ ነጥቦች ሁሉ ዘሎ የኦዲት ሪፖርቱን፣ የጅምላ ክህነቱን፣ ታሪክ አበላሸህ መባሉን የፅጌ ጾምን በተመለከቱ ነጥቦች ላይ ብቻ ነው የተውተፈተፈ ምላሽ ለመስጠት የሞከረው፡፡ ሌሎቹን ጉዳዮች ግን “ሥራዬ ነው” የማለት ያህል ምንም አስተያየት ሳይሰጥባቸው በዝምታ አልፎአቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ግን በፓትርያርኩ ደብዳቤ መናደዱንና ማዘኑን አልደበቀም፡፡
እንዲያውም ፍትሕ ተዛብቶብኛል የሚል ዓይነት ቅሬታ አሰምቷል፡፡ እንዲህ ሲል “ክስ የቀረበበትን አካል አቅርበው ሳይጠይቁ ከርሱም ሳይሰሙ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመስርቶ ፍርድ መስጠት በማንኛውም አካል ዘንድ በተለይም እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ የሆነ ሥርዓት ነው፡፡” በማለት ፍትሕ ተነፍጎኛል ያለው ማቅ፣ እንዲህ ያለውን ድርጊት እርሱ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ትክክል የነበረውንና ብዙዎች ቀርበው ሳይጠየቁና ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሳይሰጡ በእርሱ በማቅ ውንጀላ ብቻ ተፈርዶባቸውና “ተሐድሶ” ተብለው ከቤተ ክርስቲያን እንዲሰደዱ እንዳላደረገ ሁሉ፣ የዘራው እርሱ ላይ ሲደርስ ግን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት ነው አለ፡፡ ምናልባት ይህ አጋጣሚ ማቅ የሚማር ልብ ካለው “ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።” (ሉቃ. 6፥31) ከሚለው ቃለ ወንጌል ትምህርት የሚወስድበት ዕድል ሊሆን ይችላል፡፡

ለባለቤት አልባው ደብር ለደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውሳኔ ተሰጠ


  Read in PDF
ከይነጋል በጊዜው
ለበርካታ ወራት በአመጸኞች የተነሳ ያለ አለቃ ሲጓዝና በዓላትን ሲያከብር የነበረው ባለቤት አልባው ደብር በአ.አ. ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ አገኘ፡፡
በከሳሽም በተከሳሽም ወገን ለሀገረ ስብከቱ በቀረበለት ሰነድ መሰረት የደብሩ አለቃ አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል ጥፋተኛ የሚያደርጋቸው ነጥብ እንዳልተገኘ ጉባኤው ወስኗል፡፡ በውሳኔውም መሰረት አለቃው ስራቸውን በደብሩ ተገኝተው እንዲቀጥሉ መመሪያ ተላልፏል፡፡
በውሳኔው መሰረት ያለጨረታ በህገ ወጥ መንገድ በውርስ የተገኘውን ባለ ሁለት ፎቅ ቤት እራሳቸው ሻጭ እራሳቸው ገዢ እራሳቸው ውል ተዋዋይ ሆነው ለሀገረ ስብከቱም ሆነ ለደብሩ ምዕመናንና ካህናት ሳያሳውቁ  በሚያሳዝን ሆኔታ የፈጸሙት ሽያጭ ህገ ወጥ መሆኑ ተሰምሮበት ሽያጩን ያገደ ውሳኔ ተወስኗል፡፡ ይህን ያደረጉ ሰዎች ከኛ በላይ ለደብሩ ለአሳር የሚሉ መሆናቸው ለምናውቅ ወገኖች ደግሞ የፈጸሙት ግፍ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ በመሆኑም የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ሥራ ም/ሰብሳቢ እስጢፋኖስ በህግ እንዲጠየቅ ሀገረ ስብከቱ ወስኗል፡፡
ይህ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ዋና አቀነባባሪው ደግሞ  ከግሮሰሪ ተጠርቶ የሰበካ ጉባኤ አባል ሳይሆን የሰበካ ጉባኤ ሊቀመንበር የነበረው ዮናስ ሽፈራው (በቅጽል ሽሙ ጃምቦ) ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ምክትል የሰበካጉባኤ ሊቀመንበር የሆነበት ሰበካ ጉባኤ ሃላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣ አዲስ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ አቶ ዮናስ ልብ ቢኖረው ኖሮ የቤተክርስቲያኒቱን መብት አስጠብቆ የካህናትን ህይወት ማሻሻል ይገባው ነበር፡፡ እሱ ያገኘውን እድል ቤተክርቲያንን ለማጥፋትና ራሱን ለመጥቀም ተጠቅሞበታል፡፡ በድርጊቱ ተጠያቂነት እንዳይደርስበት ደግሞ ለወንጀለኞች ጠበቃ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ሥር ተከልሎ ሲያደዘድዝ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ 

Monday, February 1, 2016

የዘንድሮ ጥምቀት ክስተቶች በሎሳንጀለስ!

Read in PDF

 ዓመታዊው የጥምቀት በአል በቅድስት ማርያም አዘጋጅነት በድምቀትና በሰላም የተፈጸመ ሲሆን አስገራሚ ርምጃዎችን አሳይቶ አልፏል። ከወትሮው በተለየ እጅግ ብዙ ሕዝብና በርካታ ወጣቶች ተሳትፈዋል። በተንኮለኛ ሰዎች ምክንያት በካህናት መካከል ተፈጥሮ የነበረው ልዩነት በዕርቅ ከተደመደመ በኋላ የተደረገ ጉባኤ ነበር። ብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጨምሮ ከስድስት የማያንሱ ጳጳሳት ቆሞሳት፣ ካህናት ዲያቆናትም ተገኝተዋል። በተሃድሶነት ተወንጀለው ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቅ/ማርያም እንዳይመጡ ተደርገው የነበሩት ዋና ዋና ሰባኪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በጉባኤው ተጋብዘው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በወንጌል ስብከት ከተሳተፉት መምህራን መካከል ቄስ መላኩ ባወቀ፣ ቄስ ልዑለ ቃል፣ ቄስ ደረጀ፣ ቄስ ትዝታው፣ ቄስ በኃይሉና መ/ተከስተ ሲሆኑ ቄስ ትዝታውና ዘማሪት ዘርፌ በዝማሪያቸው ለጉባኤው ውበት ሰጥተውታል። በዚህ ጉባኤ ቄስ አንዱአለም አልተገኘም ለጉባኤው ሰላምና መግባባት የእርሱ አለመገኘት አስተዋጽዖ አለው ተብሏል።
ከወንጌል መልእክቶች ውስጥ ቄስ መላኩ፣ ቄስ ልዑለ ቃል፣ ቄስ ደረጀና መ/ ተከስተ ያስተላለፏቸው መልእክቶች ተያያዥነት ያላቸው ስለነበሩ ትኩረት ተደርጎባቸዋል።