Friday, February 26, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል በማኅበረ ቅዱሳን ኢመዋቅራዊ አደረጃጀትና ሥራ ግድፈቶች ላይ ባለ19 ነጥብ መግለጫ አወጣ፡፡ምንጭ፡- www.addisababa.eotc.org.et
የአቋም መግለጫው ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ስም እየፈጸመ ያለውን የመዋቅር ጥሰትና ሕገወጥ ድርጊቶችን ሁሉ ያጋለጠ ሲሆን በተለይም በቅርቡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ኮሌጆች ስማችን ጠፍቷል በሚል ላቀረቡት አቤቱታ የሰጡትን አባታዊ መመሪያ በመቃወም ደብዳቤ የጻፈውን ማህበረ ቅዱሳንን በጽኑ የሚያወግዝ መግለጫ ነው፡፡ በሀገረ ስብከቱ ድረገጽ ላይ የወጣው የስብሰባው ቃለ ጉባኤና መግለጫ ሙሉ ቃል እነሆ

ብዛቱ እስከ 2000 የሚገመተው ይህ ጉባኤ የካቲት 17 ቀን 2008 . በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በመገኘት ማህበረ ቅዱሳን በመዋቅር የለሽ አሠራሩ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ  በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ መሆኑን በማስመልከት አስፈላጊው ርምጃ ይደረግበት ዘንድ ጉባኤው በስፋት ከተወያየ በኋላ ባለ 19 ነጥብ  የአቋም  መግለጫ አውጥቷል፡፡

 
የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ እና አቋም መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

በጉባዔው መጀመሪያ የጉባዔው ሰብሳቢ እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚታዩ ሁኔታዎችን በማስመልከት የመግቢያ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ላይ ቤተክርስቲያን የሰላም ቤት መሆኗን፣ ሰላምን ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሀገር እና ለመላው ዓለም የምትለምን እና የምትማልድ መሆኗን፣ ሰላም በሌለበት ዓለም ዋና አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሰላም መሆኑን እንደምታስተምር፣ ነገር ግን አሁን በራሷ ሰላም ያጣችበት ሁኔታ መፈጠሩን ለጉባዔው አብራርተዋል፡፡ 

በመቀጠልም በተለይም የቤተክርስቲያንን ሉአላዊነት የሚጻረሩ ሲኖዶሳዊት ፓትርያርካዊት መሆኗን የሚፈታተኑ የፖሊቲካ ባሕርይ ያላቸው ንቅናቄዎች እንደሚስተዋሉ በዚህም ምክንያት ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ሕዝብን በማነሳሳት መዋቅር የለሽ አደረጃጀት ለመፍጠር የሚሞክሩ የተለያዩ ሙከራዎች እንዳሉ፣ በዚህም የተነሳ ቤተክርስቲያን የሾመቻቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ወኪሎች በአመጽ እና በሁከት ለማስወገድ የሚደረጉ ጥረቶች ለቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ችግሮች እየሆኑ እንደመጡ ገልጸዋል፡፡
የቤተክርስቲያንን ሥርዓት በመከተል ሰማያዊ ዋጋ ይገኛል ብላ የምታስተምረውን ቤተክርስቲያንን በመጋፋት፣ ቤተክርስቲያን የምታንቀሳቀሰው ገንዘብ ምዕመናን የሚሰጡት ምጽዋት ስለሆነ ገንዘቡን የሚያወጣው ምዕመናን ፍላጎት ትመራ፣ የሚል የመንፈስ ቅዱስ እንደራሴ የሆነውን የቅዱስ ሲኖዶስን ስልጣን የሚቀናቀን ግልጽ ያልወጣ የኑፋቄ ትምህርት የሚያስፋፋ እና በዚህም ምክንያት ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር እስከ መገዳደር የደረሱ አደረጃጀቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያፈጠጡ መጥተዋል፡፡
እንዲሁም በሀገረ አቀፍ ደረጃ የሚታዩ የፖለቲካ  ትኩሳቶችን እየተከተሉ የሀገር ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ መሆኑን በመጠቀም የራሳቸውም ዓለማ በቤተክርስቲያን ላይ ለመጫን የሚሯሯጡ እየበዙ እንደመጡም ይስታወላል፡፡

ከግዜ ወደ ግዜ በተለያዩ አካላት የሚፈጸሙ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ያልጠበቁ ክንውኖች፣ በቅንነት የተፈጸሙ ተራ ስህተቶች ተደርገው እየተወሰዱ ባለመታረማቸው፣ ይህንኑ በመጠቀም የቅድስት ቤተክርስቲያንን ቀኖናዊ አሠራር እና መዋቅራዊ ሉአላዊነትን የሚፈታተኑ ሁኔታዎች እየበዙ እና እየተለመዱ መምጣታቸውን በመግለጽ እነዚህ ሁኔታዎች ጎልምሰው ቅዱስ ፓተርያርኩ ለሚሰጡት መመሪያ የተቃውሞና የድፍረት የጽሑፍም ምላሽ እስከ መስጠት መደረሱን በማብራራት በቀጣይ ይህን መሰል ድርጊቶች ካልታረሙ፣ ለቤተክርስቲያን የሰላም ጠንቆች እንደሚሆኑ በማብራራት ጉባዔው በዚህ አቢይ አጀንዳ ላይ ውይይት በማድረግ ለቤተክርስቲያን አንድነት እና ሰላም፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሉአላዊነት ለመዋቅር መጠበቅ፣ ለምዕመናን ሕብረት እና ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት የሚበጅ፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን የጠበቀ የጋራ ውሳኔ ማሳለፍ  እንደሚገባ በማብራራት ውይይቱን ለጉባዔው ክፍት አድርገዋል፡፡

ጉባዔው በቀረበው አጀንዳ ላይ የግማሽ ቀን ውይይት ያደረገ ሲሆን በርካታ ችግሮች እና ማሳያዎች እየተነሱ ሐሳቦች ተሰጥተዋል፡፡ በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስን ሉአላዊነት የሚዳፈሩ የሃይማኖት ነክ ውሳኔዎች በቤተክርስቲያን አቋም ያልተወሰደባቸው ያልተረጋገጡ እና ሕዘበ ክርስቲያኑን ወደፍርሀት የሚከቱ ትምህርቶች መስፋፋት በቤተክርስቲያን ስም ከሕዝበ ክርስቲያኑ ገንዘብ የሚያሰባስቡ ማህበራት እና ግለሰቦች መብዛት፣ በጉባዔ ሊቃውንት ያልተረጋገጡ እና በቅዱስ ሲኖዶስ ያልተወሰኑ የውግዘት ውሳኔዎች መስፋፋት በዝምታ በመታለፉ ሊቃውንትን ለቤተክርስቲያን በማፍራት ወሳኝ ሚና ያላቸውን የትምህርት ተቋማት ጭምር በደፈናው ስም እስከ ማጥፋት መደረሱ በሰፊው ተነስቷል፡፡

በተለይም የሃይማኖት ችግር ያለበት ሰው ቢገኝ እንኳን በሊቃውንት ጉባዔ ተመርምሮ እና ተረጋግጦ ለንስሐና ለቀኖና የሚሆን ዕድል ተሰጥቶት አልመለስ ያለውን መናፍቅ መሆኑን የሚወስነው እና በውግዘት የሚለየው ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ እራሳቸውን የቤተክርስቲያኒቱ ብቸኛ ጠበቃ አድርገው የሚቆጥሩ አካላት ይህንን የቅዱስ ሲኖዶስ ስልጣን ለራሳቸው በመውሰድ የፈለጉትን ሲያጸድቁ ያልፈለጉትን ደግሞ በራሳቸው መገናኛ ዘዴ ጭምር እንዲሁም የቤተክርስቲያንን አውደ ምህረት በመጠቀም የሚያሰራጩት ትምህርት እና ያለስልጣናቸው የሚያስተላለፉት ውሳኔ ሊወገዝ የሚገባው በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ላይ ያነጣጠረ መሆኑ በጉባዔው ላይ ተወስቶአል፡፡

ማንኛውም ክርስቲያናዊ ማህበር ወይም ግለሰብ በምክረ ካህን በቤተክርስቲያን መዋቅር ታቅፎ መኖር ግዴታው ቢሆንም፣ በሰበካ ጉባዔ አባልነት ሳይታቀፉ የማሕበራት አባላት በመሆን  በክርስትና ስም ተሸፍነው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ ቤተክርስቲያን ላይ ሁከት በመፍጠር ሕዝበ  ክርስቲያኑን በቡድን በመክፈል ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ እና የሰላም ጠንቅ እየሆኑ ስለሆነ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከነዚህ ቀሳጢዎች ለመጠበቅ ሰፊ ትምህርት ቢሰጥ እና ስብከተ ወንጌል መጠናከር እንዳለበት፣ በተለይም በቤተክርስቲያን ሥርዓት ማን ምን እንደሚሰራ እንዲያውቅና ለአጽራራ ቤተክርስቲያን ከለላ የሚሆን ነገር እንዳይፈጠር የማሳወቅ ሥራ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ በተለይም በተለያየ ስም በቡድን የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ኔትወርክ በመፍጠር በቤተክርስቲያናችን የአስተዳደር ወማቅር ላይ ጥቃት በማድረስ አንድነቷን ለማናጋት ዝግጅት ያላቸው እና አጥቢያ  ቤተክርስቲያንን በመገንጠል በቦርድ ለመምራት የሚደረጉ ሙከራዎች በሃይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ የአጽራራ ቤተክርስቲያን ተግባራት እና የግል ጥቅመኞች እኩይ ሥራዎች ስለሆኑ በንቃት በመከታተል የቤተክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ በጉባዔው ላይ በአጽንኦት ተገልጾአል፡፡
የስህተቶች መደጋገም ስህተቶችን ልምድ፣ ልምዶችን ደግሞ ሥርዓት፣ ስለሚያስመስል በስህተቶች ድግግሞሽ በመቀጠል፣ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ሳይቀር እስከ መገዳደር ድረስ የቅዱስ ሲኖዶን አንድነት ለመለያየት የሚሄዱበት አግባብ ጸረ ቤተክርስቲያን በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው የሚሉ በርካታ ሀሳቦች ቀርበው በሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የጉባዔው ተሳታፊዎች  የሚከተለውን ነጥቦች የያዘ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

የጋራ የአቋም መግለጫ
1. ሐዋርያዊት እና ሲኖዶሳዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከቅዱስ ፓትርያርክ  ውጪ በምድር ላይ ሌላ መሪ ስለሌላት ፓትርያርካዊትና ሲኖዶሳዊት እንዳትሆን የሚደረገውን ማንኛውንም ጥረት እንቃወማለን፡፡
2.ቤተክርስቲያናችን በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ብቻ የምትኖር  መሆኗን ለካህናት ለምዕመናን እንዲሁም ለሰንበት /ቤት ወጣቶች እናስተምራለን፡፡
3.በቤተክርስቲያን ዕድሳት፣ በአብነት ትምህርት ቤቶች እና በገዳማት ስም፣ ገንዘብ እየሰበሰቡ ኦዲት የማይደረጉ ማሕበራት የሚሰበስቡት ገንዘብ በጠቅላይ ቤተ ክሕነት በየዓመቱ ኦዲት እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡ በተለይም ማህበረ ቅዱሳን ከአባላት የሚሰበስበው መዋጮ በአብነት መምህራንና ትምህርት ቤቶች፣ በገዳማት ልማት በስብከተ ወንጌል ማስፋፋፊያ፣ በፕሮጀክትና በመሳሰሉት ስም ከምዕመናን የሚቀበለውን ማንኛውንም ገንዘብ እና የዓይነት ስጦታ በቤተክርስቲያኒቱ ሞዴል ሞዴሎች እንዲቀበል እና በቤተክርስቲያናችን የሒሳብ አጣሪዎች በየዓመቱ እንዲመረመር እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡
4.ማህበረ ቅዱሳን በስሩ ያሉትን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እና ሕንጻዎች ወደ ግል አክሲዮን እየቀየረ በማሸሽ ላይ በመሆኑ ከላይ የተጠቀሱትን ሐብትና ንብረቶች ክትትል ተደርጎ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሐብት መዝገብ  እንዲያስመዘግብ አብክረን እንጠይቃለን፡፡
5.ማህበሩ የቅዱስ ሲኖዶስን ስልጣን በመጋፋት በሌለው ስልጣን ግለሰቦችን በማውገዝ የሚፈጸመው ተግባር ባለመታረሙ የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማትን በጅምላ ወደ ማውገዝ ተሸጋግሯል፡፡ ይህ አይነቱ ድርጊት ከሥርዓተ ቤክርስቲያን ውጪ በመሆኑ ከስህተቱ እንዲታረም ጥሪ እናቀርባለን፡፡
6.ማህበረ ቅዱሳን በሠራው ስህተት ወደፊት እንዳይቀጥል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ  ዘመንበረ /ሃይማኖት የወሰዱትን አቋም እንደግፋለን፡፡ ለተግባራዊነቱም በቅዱስነታቸው አባታዊ አመራር ሥር የሚጠበቅብንን እንወጣለን፡፡
7.ማህበሩ እንደ አበው ሥርዓት የቅዱስ ሲኖዶስ ርዕሰ መንበር የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ ፓተርያርክ የሰጡትን ምክር እና ተግሳጽ መቀበል እና መጸጸት ሲገባው ለቅዱስ ፓተርያርኩ የከሰሳና ወቀሳ መልስ በጽሑፍ መስጠቱ ፍፁም የተሳሳተ እና ከመስመር የወጣ በመሆኑ የማህበሩ መሪዎች ለፈጸሙት የሕገ ቤተክርስቲያን ጥሰት ይቅርታ እንዲጠይቁ እንጠይቃለን፡፡
8.ማህበረ ቅዱሳን ከመጋቢት 15 እስከ 21 2008 በተከታታይ 7 ቀናት በአዲስ አበባ እግዚብሽን ማዕከል ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ፓትርያርኩ ሳያውቁት በቤተክርስቲያን ስም ያዘጋጀው አውደ ርዕይ  እንዲታገድ ስንል እንጠይቃለን፡፡
9.ማህበረ ቅዱሳን በርካታ በጎ ምግባር ያላቸው እራሳቸውን ለምክረ ካህን ለፈቃደ ቤተክርስቲያን ያሰገዙ አባላት ያሉት በመሆኑ ጥቂት አባላት በሚፈጽሙት ተግባር መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዳይደናቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና የቤተክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት የአበውን ተግሳጽና መመሪያ እንዲከተሉ ለማሕበረ ቅዱሳን አባላት ጥሪ እናቀርባለን፡፡
10.በቀላል ቋንቋ የሚገለጹ፣ ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነት የሚፈታተኑ፣ መግለጫዎችን አስተያየቶችን እና ትምህርቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን፡፡ 
11.ቤተክርስቲያን ልትፈረስ አደጋ ላይ እንዳለች በማስመሰል ለሕዝበ ክርስቲያን በተለይም ለወጣቶች በተለያዩ ሆቴሎች እና አዳራሾች የሚሰጡ ትምህርቶች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በክርስቶስ ደም የተመሰረተች የማትፈርስ የማትሸነፍ የቃል ኪዳን  ቤተክርስቲያን መሆኗን  የሚያቃልል የኑፋቄ  ትምህርት በመሆኑ እናወግዘዋለን፡፡
12.ወጣቶች ቤተክርስቲያናቸውን በደማቸው እንዲጠብቁ፣ ማህበራትን በሕይወታቸው እንዲታደጉ፣ በመቅስቀስ እና በማነሳሳት የሌለ እና ሊሆን የማይችል አስጨናቂ ሁኔታ በመፍጠር ግጭት ለመቀስቀስ የሚጥሩ አካላት እና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ወጣቶችም የሚደርሳቸው መልዕክት እና የሚማሩት ትምህርት በቤተክርስቲያን የታመነበት በሊቃውንት ጉባዔ የተመረመረ እና ቤተክርስቲያን ያጸደቀችው መሆኑን ለማረጋገጥ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 
13.የመንግሥት አካላት ከቤተክርስቲያናችን ጋር በሰላም እና በልማት መስኮች አብረው የሚያደርጉት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተክርስቲያንን ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት አስፈላጊ የሆነውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ 
14.በወጣቶቻችን ያለውን ዕምቅ አቅም ለቤተክርስቲያናችን ጥቅም ለማዋል ሰንበት /ቤቶችን ለማጠናከር እና ወጣቶችን የሚያሳትፉ ተግባራትን በስፋት ለማከናወን ጥረት እናደርጋለን፡፡ 
15.ሀገረ ስብከታችን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት በመሆኑ በቅዱስነታቸው እና በክቡር ዋና ሥራ አስኪያጃችን በሀገረ ስብከታችን የተጀመረውን የመልካም አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት ሙስናን ለማስወገድ የተጀመሩ ሥራዎችን እንደግፋለን ተጠናክረው እንዲቀጥሉም እንጠይቃለን፡፡
16.በቤተክርስቲያናችን መዋቅር ተሰግስገው የቤተክርስቲያን ላልሆነ የግል ጥቅም እና ቡድናዊ ፍላጎትን ለማሳካት በተለያዩ ዕለታዊ ችግሮች ተከልለው ለመኖር የሚጥሩ አካላትን አንድነታችንን አጠናክረን እናጋልጣቸዋለን ድርጊታቸውንም እናወግዘዋለን፡፡ 
17.በቤተክርስቲያን ሥር ተደራጅተው ነገር ግን የአባሎቻቸው ማንነት የማይታወቁ ማህበራት የአባሎቻቸውን ማንነት የመኖሪያ አካባቢ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ለየሚኖሩበት ሀገረ ስብከት እና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲያሳውቁ አስገዳጅ ሕግ እንዲወጣ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችንንና ቅዱስ ሲኖዶስን እንጠይቃለን፡፡
18.ዘመን የወለዳቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የቤተክርስቲያናችንን ስም እና ቋንቋ፣ የቤተክርስቲያንን አንድነት የሚሸረሽሩ፣ የብፁዐን አበውን ክብር የሚነኩ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በሕዝበ ክርስቲያኑ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ሀሰተኛ ትምህርት የሚያስፋፉ፣ አጽራረ ቤተክርስቲያን መነሳታቸውን ከሚያሰራጩት መረጃ እና ከድርጊታቸው ማወቅ ይቻላል ስለሆነም ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ከነዚህ የአጽራረ  ቤተክርስቲያን ተልእኮ ፈጻሚ ብሎጎች የስህተት መረጃ እንዲጠበቅ እና የእናት ቤተክርስቲያንን ድምጽ የካህናትን ምክር ብቻ እንዲሰማ እናሳስባለን፡፡
19.በቅዱስ ሲኖዶስ ያልተፈቀደላቸው ሰባክያንን እና ራሳቸውን መምህር ያደረጉ ሐሰተኛ መምህራንን ለመከላከል ያወጣቸው ተደጋጋሚ ውሳኔዎች እና መመሪያዎች በመላው ኢትዮጵያ እንዲተገበሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በያለንበት ሁሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተፈጻሚነት ተግተን የምንሠራ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

በተጨማሪም ይህ የአቋም መግለጫችን ለብፁዕወቅዱስ ፓትርያርክ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት፣ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እና ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ሁሉ እንዲደርስ በመወሰን ስብሰባችንን በጸሎት ፈጽመናል፡፡

የካቲት 17 ቀን 2008 .

አዲስ አበባ

24 comments:

 1. 18.ዘመን የወለዳቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የቤተክርስቲያናችንን ስም እና ቋንቋ፣ የቤተክርስቲያንን አንድነት የሚሸረሽሩ፣ የብፁዐን አበውን ክብር የሚነኩ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በሕዝበ ክርስቲያኑ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ሀሰተኛ ትምህርት የሚያስፋፉ፣ አጽራረ ቤተክርስቲያን መነሳታቸውን ከሚያሰራጩት መረጃ እና ከድርጊታቸው ማወቅ ይቻላል ስለሆነም ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ከነዚህ የአጽራረ ቤተክርስቲያን ተልእኮ ፈጻሚ ብሎጎች የስህተት መረጃ እንዲጠበቅ እና የእናት ቤተክርስቲያንን ድምጽ የካህናትን ምክር ብቻ እንዲሰማ እናሳስባለን፡፡
  That is for Abaselama and other tehadiso blogs but...END DAYS

  ReplyDelete
  Replies
  1. መግለጫው ስብሰባው ከተካሄደብት ዓላማ አንጻር በጣም ጥሩ መግለጫ ነው፡፡ በተራ ቁጥር 18 የቀረበው ግን በጣም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ለመሆኑ አባ ሰላማ ላይ ተጥዶ የሚውለውና የሚያመሸው ማነው? በዚያ ስብሰባ ላይ የተገኘው ሁላ አይደለም ወይ? ታዲያ በአባ ሰላማ መረጃዎችን እያገኘና እየተጠቀመ አባ ሰላማንና እርሱን የመሰሉትን ብሎጎች አታንበቡ ማለት ተገቢ አልነበረም፡፡ ለነገሩ አታንቡ ማለት አንብቡ ማለት መሆኑን ባለመገንዘብ ነው መግለጫው የወጣው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ማቅን ለማስደሰትና ሚዛናዊ ለመምሰል ሲባል ነው በመግለጫው ውስጥ ይህን ነጥብ ያካተቱት፡፡ ይህ መግለጫ ግን የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ የሆነው ሐራ ዘተዋህዶንም ማካተት አለበት፡፡ ለምን ከተባለ በመረጃ ላይ ተመሥርቶ ባይሆንም የጠላውንና ለማህበረ ቅዱሳን አስጊ የሆኑትን አባቶች ስም በክፉ ያነሳልና፡፡ ሰሞኑን እንኳን ቅዱስ ፓትርያርኩን እየዘለፈ ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ጳጳሳትን ስም በክፉ መንገድ ጽፏል፡፡ ስለዚህ የተሐድሶ ብሎግን ብቻ የሚመለከት ነው መባል የለበትም፡፡

   Delete
 2. አዲስ አባባ ሀገረ ስብከት በሙሉ እና የቤተክህነቱ በከፊል ተሐድሶ መሆናችሁን እና የጋራ ሥራችሁን ነው እያሳያችሁን ያላችሁት በርቱ………

  ReplyDelete
 3. እውነት እንዲህ የጠፋችበት ዘመን ምነው አባቶቻችን እንዲህ ወረዳችሁ እውነትን ካዳችሁ……. እዩት ከሃዲዎች ተሳለቁባችሁ ልጆቻችሁን የምትከሱ አባቶች ሆናችሁ…… ይብላኝ ለእናንተ እኛስ ቸሩ አምላክ ይመስገን እውነተኞቹ ቸባቶቻችን ከማኅበረ ቅዱሳ ጋር በሠሩት ሥራ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ድምጽ፣ትምህርት፣ አካሄደ አውቀናል፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

  ReplyDelete
 4. ይህ የአቋም መግለጫ ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች እንጂ ውስጧ ሆነው ጡቷን ከሚጠቡ አካላት የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ ዳሩ ይሁዳም ስርቆቱ አልበቃ ብሎት ጌታውን ስለሸጠ ፍቅረ ንዋይ ልቡናውን የዘጋው ሰው መጨረሻው ቤተ ክርስቲያንን መሸጥ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. አስተያየት ስንሰጥ በእዉነት አድላዊነት ባናደርግ መልካም ነዉ።
  ልጆችስ /ማቅ/አባቶቻቸዉን አልከሰሱም ወይ? እርስ በርስ መወነጃጀልን መካሰስን ያስተማረ ማቅ ነዉ።
  ብበድሮ ጊዜማ «አባት አይከሰስ ሰማይ አይታረስ» ይባል ነበር
  ለአባት መልስም እይሰጥም ነበር
  የቤተ ክርስቲያናን አባት ተግሳጽ ወይም ንግግር «የወረደ» «መሰረተቢስ» «እንካን ከአንድ የቤተ ክርስቲያን አባት ከአንድ ምዕመን የማይጠበቅ »እያለ የሚሳደብ ማን ነዉ??
  እባካችሁ በማስተዋል እንሂድ።

  ReplyDelete
 6. History raised the pagan (Dergue) to make revolution over the Feudalist (Haileselassie); TPLF (the university students) over Dergue; the remnant of dergue (MK) over the kolo- temariwotch(Betekhinet); the boarding temariwotch (theology students) over MK.

  CONCLUSION:
  since the span of MK is depreciated, we Addis Ababa diocesans too accepted your (MK)dethronement.
  MK, Does this give sound for you?

  ReplyDelete
 7. በዚህ የአቋም መግለጫ ላይ ደስ ብሏቸው የሚፈርሙ እና ስብሰባው ላይ የተገኙት ማኅበረ ቅዱሳንን ቀደም ሲል በመጥላት አጋጣሚ ይፈልጉ የነበሩ ጥቂቶች ሲሆኑ፣ አብዛኛው ሰው ግን ከሥራ ላለመፈናቀል በዝውውር ሰበብ ከደረጃ እና ከደመወዝ ዝቅ ላለማለት ፈርቶ ብቻ ነው። ምክንያቱም የት አቤት ይባላል፦ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ "ሥራ አስኪያጅ" አቡነ ማቴዎስ ሁሉን እርግፍ አድርገው ትተው የግንቦት ሲኖዶስን እንደ እርጉዝ ሴት ይቆጥራሉ፣ ፓትርያርኩ "በአማሳኙ ንቡረ ዕድ" እና በቀሳጢው "የማነ ዘሙስና" ታፍነው እንኳን የሚሰሩት የሚወዱትን እንቅልፍ እንኳን ሲተኙ የሚያልሙት ህልም ተነግሯቸው ነው። ታዲያ በዚህ ሁሉ ውስጥ የአ/አ ሀገረ ስብከት ካህናት እንኳን በማኅበረ ቅዱሳን በራሳቸውስ ላይ ምንም አንጠቅምም መበተን አለብን ብለው የአቋም መግለጫ ቢያወጡ ምን ይደንቃል! አይ የማነ ጊዜ አልፎ ያገናኘን።

  ReplyDelete
 8. ከማህበር ጋር አታብሩ ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጂ።ምን አይነት ትውልድ ነው?ማቅ ስርአት እያበላሸ ነው እየተባላችሁ እኮ ነው።አሁንም ይህ ግፈኛ ማህበር እግዚአብሄር ያጋልጠዉ ።ስውሩ አመራር የተባሉትን ደግሞ ያጋልጣቸው።ከጀርባ ሁነው በተስኪያኒቱነ የሚያውኩትነ እግዚአብሄር የጋልጣቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ ስርአት እያበላሸ ነው እየተባላችሁ እኮ ነው Who said this my dear? The Holly Synod did not say this. It is the holy synod gave the rule to give service in the church. The holy Synod can make the last decision if MK is doing wrong. But who are you saying ማቅ ስርአት እያበላሸ ነው እየተባላችሁ እኮ ነው?????????? Logically Answer this. The last and the only deciding body in EOTC is the Holly Synod not the Patriarch.

   Delete
 9. Mahbere Kidusan Bemil Sim yetesebasebu Zerafiwoch Betekrstiyanin weklew yesebesebut yemutsiwat Genzeb Aksyon silegezubet Tefamalet Aydelem YIMELESU YIMELES zemanawi Leboch nachew

  ReplyDelete
 10. መግለጫው ለእናንተ በሚመች መልኩ አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመሸጥ የተደራደራችሁበትን ገንዘብ ለመቀበል እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቃሪ ሆናችሁ አይደለም። የቤተ ክርስቲያን አምላክ እርሱ ይፋረዳአችሁ።

  ReplyDelete
 11. ለካስ ሁላችሁም ተሃድሶ ሁናችሁልናል

  ReplyDelete
 12. እስቲ አንድ በሉ! በርካታው የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ለምክረ ካህናት ታዛዥ ለቤተክርስቲያን ቀናኢ እንደሆኑ በዚህ ጽሑፍ ነገራችሁን፡፡ ጥቂት የማኅበሩ አባላት በተለይም በአመራር ላይ የሚገኙ አባላት ደግሞ እንደማይታዘዟችሁ ጠቆማችሁን፡፡ በዚሁ ጽሑፋችሁ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ተቋም እንዳይኖር ተግታችሁ እየሠራችሁ እንደሆነ በግልጽ ነገራችሁን፡፡ እናንተ ከወዴት ናችሁ? ለምንስ ይህን ያህል፤ በዚህ ደረጃ በርካታ ሥራ የሠራና እየሠራ የሚገኝን ማኅበር ለማፍረስ ታተራችሁ? በዚህ ደረጃ እውነትንስ ለመስቀል ለምን ፈለጋችሁ? የስብሰባውንስ ጊዜ ለምን ስለቤተክርስቲያን አንድነት ለመጸለይ አልፈለጋችሁም?
  ስለቤተክርስቲያን አንድነት፣ ስለሰላም፣ በናንተና በመንግሥት ስለሚደርስብን የአስተዳደር በደልና ስለምትቀበሉት እጅ መንሻ ስለምን አትጸልዩም?ተግታችሁስ አትሰሩም? ጊዜ የማያልፍ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋ፡፡ ወንበር እንደሞቀ የሚቀጥል ከመሠላችሁ የቤተክርስቲያኒቷንና የሀገሪቷን ታሪክ አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ ጥቂት ዓመት ስትበሉና ስትጎራረሱ የተቀመጣችሁበት ወንበር የማይወሰድባችሁ ይመስላችኋል?
  ከዚህ በፊት አስተያየቴን ስሰጥ “የማኅበሩ አባል ስለሆንክ ነው” ብሎኛል አንዱ፡፡ ይህንን ለመረዳት የግድ የማኅበሩ አባል መሆን ይጠይቃል? ሙዳዬ ምጽዋት ገልባጭ ሁሉ! ሲያምርህ ይቀራል እንጂ ማኅበሩ በእግዚአብሔር እቅፍ ውስጥ ያለ፣ ከአባላቱ ባሻገር እንደ እኔ ባሉ ምዕመናን ልብ ውስጥ የተጻፈ ማኅበር ነው፡፡
  እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ህሊናችሁን ግን ተሸክማችሁ ነው የምትሄዱት፤ አንድም ጥያቄ አያነሳም? መቼም ይኼ ማኅበር ጉሮሯችንን እየዘጋ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ይታነጹ፤ እራሳቸውንም ይቻሉ ስላለ ነው አይደል፤ እንዲ የምትወርዱበት? ቤተክርስቲያን መታደስ አለባት፤ ቅዳሴዋም ረዝሟል እያላችሁ ለመቆነጻጸል እድል ነፈጋችሁ አይደል? አይማኅበረ ቅዱሳን፤ የእግር እሳት ወነባችሁ እኮ! አንተን የፈጠረ አምላክ ይክበር ይመስገን! ማኅበረ ቅዱሳኖች እባካችሁ በርቱ ጊዜ የለም! ዲያብሎስ ይህን ያህል እየሮጠ ነው፤ እንደምትቀድሙት የቅዱሳን የአባቶቼና እናቶቼ አምላክ እንደሚረዳችሁ፣ የአዛኝቷ እናቱ ምልጃ፣ የመላዕክት ተራዳይነት፣ የቅዱሳኑ ጸሎት ከናንተ ጋር እንደሆነ አልጠራጠርም፡፡ እግዚአብሔርን የያዘ አይሸነፍምና!!!

  ReplyDelete
 13. ewnt tngark enam gadafachaw enat neg bsrachaw bmydergwet ychen orthodox twhedow ement ansbrezem slalew slhon bzew sadkan smetat tbkew yasrkbnn haymanot atbrezwem atlfew ydengl Maryam leg lnant bot ylawen smachuen en lawetalach ? ab sanalmn tawen degwen abat ytlekew legwech byachalh !! nesh gebun tmalesw gzaw sylkebach alblzy mserow mmchaw mleketw eytay naw abatwech enanten tketlew eysatw new sahwne ybkaz nesh gbw gatachen madhanetache yeses chrestas ydengle Mariam leg mhare amlak lew tmalesw ftanew!!fetanew!! egezabher lbna ystach aman!!

  ReplyDelete
 14. ማህበረ ቅዱሳን በሙሉ መልካም ስራ አልሰራም ያለ የለም።
  እየተባለ ያለዉ "ከመስመር እየወጣ ነው" አባቶችን አያከብርም አባቶችን እየከፈለና እርስ በርስ እያባላ በነገር ብቻ ተጠምደው እስለቤተክርስቲያንና ስለ መጣፎቻ እንዳያስቡና እንዳይወያዩ እያደረገ ዙሮ አባቶችን የሚወቅስና የሚያስወቅስ እራሱን ብቻ ለቤተክርስቲያን ቕሚ አድርጎ የሚያይ ማህበር ነው።ስለዚህ መስመር ይያዝ ነው የተባለው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲህ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ሆነህ ማኅበረ ቅዱሳንን የምትከስ ከሆነ እስቲ የአቋም መግለጫ እስኪያወጡ ዝም የተባሉትን ዐራ ጥቃዎች/ተሐድሶ/ እስኪ አንድ በልልን! ሙዳዬ ምጽዋት ገልባጭ ሁሉ!!! ስትወሰልቺ ተገኝተሽ ዞር በይ የተባልሽ ሁሉ በየብሎጉ ትፎክሪያለሽ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  2. tesfu ze-mehal agerMarch 4, 2016 at 5:19 AM

   Can u / any body clearly show what red-line did MK passed???? Take care, that red line must be lined by the Holly Synod, not by any body. Even the Holly Patriarch is under the Holly Synod. He ca only take care of the line made by the Synod. Try, my dear

   Delete
 15. ቤተክርስቲያናችን በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ብቻ የምትኖር መሆኗን ለካህናት ለምዕመናን እንዲሁም ለሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እናስተምራለን፡ This is the critical idea you raised and decided. And Mahibere Kidusan is Critically following. Your and related collections are based on the Patriarch Interest ONLY, not the Kidus Synodos Interest. And You Keep silent on TEHADESO issue, Why Why Why???????

  ReplyDelete
 16. Leba plice seyay yidenegital hatyategna sew tsadik ategeb mekom aychilim midre leba bebetkihnet demoz sayhon betkirstyanin bemeziref yedelebachihu silehone yemyagalit aymechachihum haimanot yelelachihu poletican tegen adirgachihu yemitawenbidu amlak yiferdal bejiraf gerfo yasiwetachihual ende beleam memerek yalebetin sew lemergem yetezegaje gizew dersual wenfitu kerbual ewnet yebetekirstyan shum meslachihu satihonu yalachihu gizew legelet new hatyaten yemtamenechu selamawoch gin selam yelelachihu kenu dersual besigam benefisim titeyekalachihu.

  ReplyDelete
 17. If you are realy belonging to our church why don't you say about Tehadiso? do you oppose the existance of tehadiso?What about robbing in our church? why you always support those who hate Mahibere Kidusan? this seems you are also from.......

  ReplyDelete
  Replies
  1. In black and white, knowingly or unknowingly they are under Tehadeso category, my dear. Let God take of the Church!!!!

   Delete