Monday, February 1, 2016

የዘንድሮ ጥምቀት ክስተቶች በሎሳንጀለስ!

Read in PDF

 ዓመታዊው የጥምቀት በአል በቅድስት ማርያም አዘጋጅነት በድምቀትና በሰላም የተፈጸመ ሲሆን አስገራሚ ርምጃዎችን አሳይቶ አልፏል። ከወትሮው በተለየ እጅግ ብዙ ሕዝብና በርካታ ወጣቶች ተሳትፈዋል። በተንኮለኛ ሰዎች ምክንያት በካህናት መካከል ተፈጥሮ የነበረው ልዩነት በዕርቅ ከተደመደመ በኋላ የተደረገ ጉባኤ ነበር። ብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጨምሮ ከስድስት የማያንሱ ጳጳሳት ቆሞሳት፣ ካህናት ዲያቆናትም ተገኝተዋል። በተሃድሶነት ተወንጀለው ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቅ/ማርያም እንዳይመጡ ተደርገው የነበሩት ዋና ዋና ሰባኪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ በጉባኤው ተጋብዘው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በወንጌል ስብከት ከተሳተፉት መምህራን መካከል ቄስ መላኩ ባወቀ፣ ቄስ ልዑለ ቃል፣ ቄስ ደረጀ፣ ቄስ ትዝታው፣ ቄስ በኃይሉና መ/ተከስተ ሲሆኑ ቄስ ትዝታውና ዘማሪት ዘርፌ በዝማሪያቸው ለጉባኤው ውበት ሰጥተውታል። በዚህ ጉባኤ ቄስ አንዱአለም አልተገኘም ለጉባኤው ሰላምና መግባባት የእርሱ አለመገኘት አስተዋጽዖ አለው ተብሏል።
ከወንጌል መልእክቶች ውስጥ ቄስ መላኩ፣ ቄስ ልዑለ ቃል፣ ቄስ ደረጀና መ/ ተከስተ ያስተላለፏቸው መልእክቶች ተያያዥነት ያላቸው ስለነበሩ ትኩረት ተደርጎባቸዋል። 

ቄስ ደረጀ፦ ዓይናችን ሲበራ የእግዚአብሔር የመጥራቱን ተስፋ እናያለን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በኢትዮጵያ ክፍ ሊል ይገባል፣ ያለ መግባባታችን ዋና ምክንያት ለእግዚአብሔር ልጅ አለመታዘዛችን በመሆኑ ንስሐ ልንገባ ይገባል፣ ኢየሱስ ክርስቶስን መሸፈን የለብንም፣ እውነቱ መገለጥ አለበት፣ በማለት መልእክቱን አስተላልፏል።
ቄስ መላኩ፦ የክርስቶስ የደሙ ዋጋ በሚል ርእስ የደሙን አዳኝነት ክፍ አድርጎ በምንም የማይለካ መሆኑን አስምሮ ተናግሯል። ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው የሚለውን ከማቴዎስ 26፥26 የጠቀሰው ቄስ መላኩ በደሙ ከኃጢአታችን ሁሉ እንደምንነጻ ዛሬም ደሙ ጠበቃችን መሆኑን፣ ያለ ደም፤ ሥርየት እንደሌለ፣ ይህን ደም ያቃለለና የናቀ ክፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቀው ጠበቅ አድርጎ ከተናገረ በኋላ በምድር ላይ ከፍተኛ መከራ እና ሥቃይ ተቀብሎ ያዳነን ጌታ በወረፋ የምንዘምርለት አይደለም ሲል መልእክቱን አስተላልፏል። ከዚህ ጋር አያይዞም "በዘለዓለም ኪዳን በደም ሰንሰለት የያዝከን‚ የሚለውን የምርትነሽ መዝሙር ሲዘምር ወደ ሰማይ ወስዶን ነበር።

መ/ተከስተ ጫኔ፦ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ በሚል ርእስ ወንጌል ያለምንም ድንበርና ገደብ መሰበክ አለበት፣ ቤተ ክርስቲያን በምድር የተቀመጠችው ጌታ የጀመረውን ይህን መለኮታዊ ተልእኮ ለመፈጸም መሆኑን፤ እግዚአብሔር አላማው ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እንጂ ሌላ ጉዳይ የለውም ብሏል። ወንጌል አስቀድሞ የተሰበከው ለአብርሃም ሲሆን የሰበከውም እግዚአብሔር መሆኑን "አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ እግዚአብሔር ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ከሚለው ከገላትያ 3፥8 ላይ ጠቅሶ ተናግሯል። ወንጌል ሲባልም የሰዎች ታሪክና የባልቴቶች ተረት ሳይሆን በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደው እንደቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን ስለተነሳውና በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለተገለጠው ስለ ልጁ የምንናገረው ነው ሲል ከሮሜ 1፥3 ጠቅሷል። ወንጌል የታዋቂ ሰባኪዎች ስብከት ሳይሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠው ብቸኛ የኃጢአተኞች ተስፋ የምስራች ነውና የገሌ ስብከት የንቶኔ ስብከት እያላችሁ ሰው መከተላችሁን አቁሙ ወንጌል የእግዚአብሔር ነው፤ ብሏል። ወንጌል ሁለንታዊ በረከት እና መፍትሔ ስላለው የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፈታው በወንጌል ነውና እርሱን እንስበከው ብሏል። የክርስቶስን ወንጌል የሚያጣምሙና ልዩ ትምህርት የሚሰብኩ ሁሉ የተረገሙ መሆናቸውን አስምሮበታል።
ቄስ ልዑለ ቃል፦ ወቅታዊና አነጋጋሪ የሆነውን የተሐድሶ ጉዳይ አንስቶ አስተምሯል። ተሐድሶ በየቀኑ ልናደርገው የሚገባ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ መሆኑን አጠንክሮ ተናግሯል ይህም ንስሐ መግባት ማለት እንጂ ሌላ ሃይማኖት ማምጣት አይደለም ብሏል። ተሐድሶ አላዋቂ ሰዎች ስለሚያራግቡት በክፉ መታየት እንደሌለበት በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ሐሳብ መሆኑን፣ ተሐድሶ የማያደርግ ፍጥረት እንደሌለ፣ የማይታደስ ቤት ሊፈርስ እንደሚችል የማይታደስ ዕቃ እንደማይጠቅም፣ ብረት እንኳ ሲዝግ ተሐድሶ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም በየቀኑ መታደስ አለባት ብሏል። ምንም ስሕተት የለብንም የሚለው አባባል ከንቱ መሆኑንና በጣም ብዙ ስሐተት እንዳለብን ተረድተን እራሳችንን ማደስ አለብን፣ የማንታደስ ከሆነ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመጣባት የትውልዱ ፈተና ማዳን አንችልም፤ ለሚመጣው ትውልድ ጥያቄውን መልሰንለት ንጽሕት ቤተ ክርስቲያንን ነው ማውረስ ያለብን ብሏል። መምህር ልዑለ ቃል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትግል እያካሐዱ ያሉትን ሰዎች በሦስት ክፍሏቸዋል።
1ኛ ተሐድሶ አያስፈልገንም የሚሉ፤ ሁለተኛ ተሐድሶ ያስፈልገናል የሚሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ 3ኛ በተሐድሶ ስም ለፕርቴስታንት የሚሰሩ ቅጥረኞች ናቸው ብሏል። ተሐድሶ አያስፈልገንም የሚሉት አላዋቂዎች መሆናቸውን የግንዛቤ እጥረት ያለባቸው ናቸው በማለት ለቤተ ክርስቲያን የሚያስቡ ከሆኑ ራሳቸውን ፈትሸው አቋማቸውን ማስተካከል አለባቸው ብሏል። ለፕሮቴስታንት የሚሰሩ ሕዝብን ከቤተ ክርስቲያን እያደናበሩ የሚያስወጡትን ሰዎችን አጥብቀን መቃወምና ተንኮላቸውን ካላቆሙ አውግዘን መለየት ይኖርብናል ብሏል። ነገር ግን ቤተ ክርስርስቲያን ዶግማዋንና ቀኖናዋን ጠብቃ መታረም ያለባቸውን እንድታርም መጠበቅ ያለባቸውን እንድትጠብቅ ሌት ከቀን የሚተጉትን እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያንን ካሳዳጆች መጠበቅና ከጠላት መከላከል ከጎናቸው መቆም አለብን ብሏል። ቄስ ልዑለ ቃል ማንም በድፍረት ሊናገረው የማይችለውን ሐሳብ በሕዝብ ፊት በመናገሩ ከፍተኛ አዳናቆትና አክብሮት ተችሮታል። ወደ ፊትም ግልጽ ውይይት ተደርጎበት የትውልዱ ጥያቄ ባግባቡ መመለስ አለበት እንጂ በዚህ መልኩ ሕዝባችንን ለተለያዩ መናፍቃን እየገበርን የምንሄደው ጉዞ አደገኛ ነው ብሏል። ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያንን ከማነኛውም እድፍ የመጠበቅ የማንጻት ሥራ እንጂ የማፍረስና ሌላ የመሥራት ሥራ አይደለም በማለት መልእክቱን በማስተላለፉ ያለምንም ተቃዋሚ ብጭብጨባ ተደግፏል።
 አርብ ማታ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ብቻ ነበር የሕዝቡን ዋና ዋና ጥያቄዎች ጠቅለል አድርጎ ያቀረበው መ/ተከስተ አድማሱ ሲሆን መልሱን የሰጡትም ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ነበሩ። የመጀመሪያው ጥያቄ አሁንም በተሐድሶ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነበር። ስለ ኦርጋን፣ ስለ ሴት ዘማሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት ስለሚካሄዱ ከወንጌል የወጡ ሰባኪዎች ማዕከላዊነት ስለሌው ትምህርት ነበር።
 አቡነ መልከ ጼዴቅ ሲመልሱ፦ ማዕከላዊ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የመጣ ስሕተት ነው በሚለው አስምረውበታል። ሁሉ በግሉና በየአካባቢው የተማረ ነው፤ የኔታ እገሌ እንዲህ ይሉታል፣ የየኔታ እገሌ ደግሞ እንዲህ ነው እያለ በማዕከላዊ ትምህርት ያልፈተሸ አስተማሪ ስለሚበዛ ልዩነቱ ብዙ ነው ብለዋል። ስለዚህ አንዱ ከሌላው እየተገነጠለ ቤተ ክርስቲያን እየገዛ ዕዳ ሲከፍል ከሚኖር ትምህርት ቤት ቢከፍትና ካህናቱ ቢሰለጥኑ መፍትሔ ይመጣል ሲሉ ጠቁመዋል። ስለ ስሕተት ትምህርቶችም ምሳሌ ጠቅሰው ውሸት በመምህራኑ ዘንድ መኖሩን አስረድተዋል። ለምሳሌ ታምረ ማርያም ሰምቶ የሄደ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል የሚለው ትምህርት ሐሰት መሆኑን አስረድተዋል፤ ሥጋውና ደሙን ለመቀበል የሚያግዳችሁ ምኑ ነው? ሲሉ የጠየቁት ብፁዕነታቸው ሥጋውና ደሙ ከኃጢአት የሚያነጻ እንጂ ኃጢአተኛ የሚያደርግ አይደለም፣ በሄትኛውም ዕድሜ ላይ ያለው ክርስቲያን ሥጋውና ደሙን መቀበል ማቆም የለበትም ብለዋል። ሌላ የስሕተት ትምሕርት ምሳሌ ሲጠቅሱም፤ ንጉሥ እስክንድር ከገነት ስለአመጣው እና በሰሎሞን ቤት በር ላይ ተጋድሞ ይኖር ስለነበረው ግንድ ነው። ይህ ግንድ ንግሥተ ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄድች ጊዜ እንደ አህያ ጀላፋ የሚመስል ጥፍር እግሯ ላይ እንደነበራትና ይህ ግንድ ሲያደናቅፋት እንደወለቀላት የሚተርከውን አንድምታ ወንጌል ከውነት የራቀ ነው ብለውታል። ምክንያቱን ሲያስረዱ ደግሞ እስክንድር እና ንጉሥ ሰሎሞን በ600 ዓመት የሚራራቁ መሆናቸው ነው ። እስክንድር ከሰሎሞን በኋላ ዘግይቶ የመጣ ግሪካዊ ንጉስ ስለሆነ በሰሎሞን ጊዜ ወይም ከርሱ በፊት አልነበረም ስለዚህ በግምት የሚነገሩ ተረቶች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለሞሉ በትምህርት ነው የሚወገዱት ብለዋል።
ስለሴቶች ዘማሪዎች ሲናገሩ እነርሱ እግዚአብሔርን እንዳያመልኩ የሚከለክል ሕግ የለም። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ እያለሁ ሴቶች የቅዳሴ ተሰጥዖ እንዲቀበሉ፤ መዝሙር እንዲዘምሩ አስለጥን ነበር። በዚህ ምክንያት ተከስሼ ንጉሱ ላይ ቀረብኩ፤ ንጉሡም ጠርተው ሥራ መሥራት ጀምረሃል መሰለኝ ከሳሽህ በዝቷል አሉኝ፤ ምንድን ነው ጥፋቴ ብዬ ስጠይቃቸው ሴቶችን ለማስቀደስ እያሰለጠንክ ነው ተብለሃል አሉኝ፤ እኔም ተሰጥዖ እንዲቀበሉ መዝሙር እንዲዘምሩ እያስተማርኋቸው ነው እንጂ ገብተው እንዲቀድሱ አይደለም፤ ነገር ግን "ሴቶችን ሊያስቀድስ እንጂ ሊያስረክስ” ባለማለታቸው ተመስገን ነው ስላቸው ስቀው በደስታ የዝማሬ ዕቃ ኦርጋን ሰጡኝ ሥራየንም ደግፈው ስለአበረታቱኝ ከመቶ በላይ ዘማሪዎች አስልጠኜ ነበር። በኦርጋን መዘመር ነውር የለውም። ወጣቱም ሆነ ካህናቱ ኦርጋን ተምረው መዘመር አለባቸው ብለዋል። ኦርጋንን የሚቃወሙትን ተነክረው ያልራሱ ተጋግረው ያልበሰሉ ናቸው በማለት ገልጠዋቸዋል።
  በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል እርቁ መቼ ይፈጸማል ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ይህ ነው የምለው ቀን የለም እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው በኛ በኩል ግን ስለ እርቅ አናስብም ሕዝቡ ነጻ ስለሚወጣበት ማሰብ አለብን የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። በመጨራሻም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ትጉ እርስ በርስ በዘር መከፋፈል ያጠፋችኋል ተጠንቀቁ በማለት የመጨረሻ መልእክት አስተላልፈዋል።
 ስለጉባኤው የታዘብነውን ጠቅለል አርገን ለመግለጥ ወንጌል በድፍረት የተሰበከበት፤ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ለውይይት የቀረቡበት በመሆናቸው አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ተችሏል ያስብላል። አቡነ መልከ ጼዴቅ የማይረሱ ወሳኝ ወሳኝ መልእክቶችን ያስጨበጡበት፤ ሕዝቡና ካህናቱ የተናበቡትና ወደ አንድ ሐሳብ የመጡበት ሁኔታን የፈጠረ ነበር ማለት ይቻላል። ነገር ግን ውስጥ ለውስጥ ማቆጥቆጥ የሚፈልጉ የማህበረ ቅዱሳን መናፍስት መኖራቸውን ሳንጠቁም አናልፍም። ማስረጃችንም ኦርጋን ሲመታ እየወጡ የሚሄዱ ከላስቤጋስ እና ከዚያው ከቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ ዘማሪዎች ነበሩ። የቅድስት ማርያም ዘማሪዎችና የኦክላንድ መድኃኔ ዓለም ዘማሪዎች በተረት ላይ የተመሠረተ የማርያም መዝሙር ሲዘምሩ ብዙ ሰው አፍሮባቸዋል። ለምሳሌ ቅድስት ሃና እመ ሳሙኤል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ቆይቼ ደጅ ጸናሁት እግዚአብሔርን የሚለውን የጌታ ያምልኮ መዝሙር ቆይቼ ደጅ ጸናኋት ኪዳነ ምሕረትን ብለው ገልብጠው ዘምረዋል። ይህ ከንቱ ነገር ወደፊት መታረም አለበት ቄስ መብራቱ በአንድነት ጉባኤው ላይ ይህ ስሕተት መሆኑን በማስተማሩ ዛሬ በካናዳ በስደት ላይ እንደሚገኝ ይወራል። በዚህ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ላይ ስለሚካሄደው አድማ ቅዱስ ሲኖዶስ ምን እርምጃ ሊወስድ አስቧል? ያልተማሩ ሰዎች በሚፈጽሙት ስሕተት ቤተ ክርስቲያን በቲኦሎጂ እስከ ዶክትሬት ያስተማረችውን ሰው ማጣት አለባት? ዕድሜ ልኩን የተማረው ታዲያ ካልተማሩት ተሽሎ እንዲገኝ አይደለምን? በእንደነዚህ ዓይነት ዓይነ ሥውር ከሳሾችና ያልታረመ መዝሙር በሚዘምሩ ዘማሪዎች ላይ አስቀድሞ እርምት ካልተወሰደ የቤተ ክርስቲያንን ጉዙ ያደናቅፋል የሚለውን ለማሳሰብ እንወዳለን።
በመጨረሻም አባ ጽጌና መ/ተከስተ እንዲሁም የሎስ አንጀለስ ምእመናን እግዚአብሔር ይባርካችሁ ለኢትዮጵያም የለውጥ ምክንያት እንድትሆኑ አምላካችን ጸጋውን ያብዛላችሁ እንላለን።       

32 comments:

 1. Yihenen yenanten teret ena yemender wore kemititsifu Lemin medlote tsidk lay mels atsetum .ye kelebat lijoch

  ReplyDelete
 2. Enkirdad tizeralachu!!?

  ReplyDelete
 3. Church Fathers taught us, every thing should be practiced in the context of the Holy church.
  From where you learn't such violations of the Holy church Fathers order.) You peoples, in any way, you are heretical for what you are doing now. If you were real children of the Holy church, you would first bring such cases to the Holy church ( Holy Synod). Church Fathers did not taught us to take an action, in the way that you are doing now.

  ReplyDelete
 4. Please use the word pastor instead of 'kes'.because all of them that you mentioned are pastors and laymen not 'kes' we know them very well.

  ReplyDelete
  Replies
  1. What is the difference between kes and pastor ?

   Delete
 5. Why you are say nothing about thousands of youth who have wear t-shirts which says 'our church did not be reformed' in the Ethiopian epiphany at Jalmeda?

  ReplyDelete
 6. Replies
  1. Seitan ke 7000 Amet belay experience sinorew Enantena ye betekihinetu werobeloch belatachhut!!!?

   Delete
 7. ስለ ሎስ አንጀለስ የጥምቀት በዓል ያቀረባችሁትን አስተያየት አንብቤዋለሁ በእያንዳዱ አረፍተ ነገር ላይ የምለው ቢኖረኝም ሳልተች ላልፈው የማልፈልገው ዋና ነግር ለበዓሉ መሳካት አስተዋጽዎ ያደረጉት በሙሉ ካህናት መሆናቸው እየታወቀ ሁሉቱን ብቻ ስም ጠቅሳችሁ ማመስገናችሁ ተገቢ አይደለም እንዲህ አይነት አስተያየት ካህናትን የሚከፋፍል ነው፡ በሎስ አንጀለስ የሚገኙት ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማህበረ ቅዱሳንን ስውር አላማ ጠንቅቀው ያውቃሉ ማህበረ እርኩሳን በዚህ በኩል ሾልኮ ለመግባት በር እያዘጋጃችሁ ከሆነ ተሳስታችኃል ካህናቱን በመከፋፈል የተጓዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይብቃችሁ ቤተ ክርስቲያንናችን ከመቼው ጊዜ በላይ በዚህ ክፉ እና እኩይ አላማ ባለው ጸረ ተዋሕዶ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ በሚገኝው ማህበረ እርኩሳን ላይ የማያዳግም እርምጃ ትወስዳለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን

  ReplyDelete
 8. Webgel enji mefeker ayadenm ye ethiopia timket wengel alba new ye America yibeltal wengel selehone alamawo.

  ReplyDelete
 9. በጣም ጥሩ ዘገባ ነዉ፡፡ ሰዉ ሁሉ ወደ ልቡ ቢመለስና ፡ ልቡን አኛን የክብር ልብስ ያብሰን ዘንድ ራቁቱን በተሰቀለዉ ጌታ ላይ ቢያኖር መልካም ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 10. በጣም ጥሩ ዘገባ ነዉ፡፡ ሰዉ ሁሉ ወደ ልቡ ቢመለስና ፡ ልቡን አኛን ከበደላችን ያድነን ዘንድ ራቁቱን በተሰቀለዉ ጌታ ላይ ቢያኖር መልካም ነዉ፡፡መነቃቀፉና መሰዳደቡ አኛንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችን አይጠቅምም። ይልቁንስ አዉነተኞች አባቶቻችን አንጠይቅ አነሱን አንከተል ። ዛሬ ተከተሉኝ የሚለን ሰዉ በዝታል ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡በአዉነት (ዘመኑን ዋጁት) ተብለናልና ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብና አመለካከት ቢኖረን ለኛም ለቤተክርስቲያናችንም መልካም ነዉ።አግዜብሔር አስተዋይ ልቦና ይስጠን።

  ReplyDelete
 11. ተሃድሶ ግዴታ መምጣት አለበት።በዚህ እንቅስቃሴ የምትደክሙ ሁሉ ታሪክ አይረሳችሁም። በርቱ ምእመኑ ውስጥ ለውስጥ ይደግፋችኋል በቁርጠኝነት የሚመራውንና አላማችሁን በግልጽ የሚያስረዳው ሰው የፈልጋል በስውር የሄዳችሁት መንገድ እስካሁን ጥሩ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ግን በግልጥ አስረዱ

  ReplyDelete
 12. ቀሲስ መልአኩ ባወቀ ጌታን እንደሚያገለግል ሁሉ ወንድሙም ቀሲስ ንጉሴ ባወቀ በወንጌል ጌታን እየገለጠው ነው

  ReplyDelete
 13. በእዉነት ደስ ይላል ዘገባው። እዉነት ሁለ ግዜም እዉነት ነው። ከመቼ ጀምሮ ነው በኦርጋን መዘመር ሀጢአት የሆነው? የግብጽ ኦርቶዶክስ የግርክ ኦቶዶክስ የአርመን ኦቶዶክሳዊያን በኦርጋነ ነው እግዚአብሔርን የምያመሰግኑት። ይልቁን ስርዓትን እያደሱ ያሉት ማህበረ ቅዱሳን አባላት ና ቸው። የቅዳሴውን ሥርዓት ሽረው የፓትራርኩ እና የሊቀ ጳጳስምን ስም በቅዳሴ ግዜ አይጠሩም እራሳቸውን ገለልተኛ አማኞች አድረገዋል። የነ ቀሲስ ደጀን ቤተ ክርስትያን በደንቨር የሚገኘው እነድሁም ሥርዓተ ቤተ ክርስትያንን አስተምራለሁ እያለ በየፈስ ቡክ ግራ የሚያጋበው ቀሲስ ዘበነ ለማ የእርሱ ቤተ ከርስትያን ገለልተኛ ነው። የትኛውን የቤተ ክርስትያናችን ስርዓት ነው የምያስተምረው? ዛሬ እኮ በማቅና በወዳጆቹ ዘንድ ቅዳሴ ስርዓቱ ተሽሮዋል። በኦርጋን መዘመር ሐጢኤት አይደለም። እውነት ለተዋህዶ እምነት ስርዓት ከሆነ ለምን በገለልተኛ ቤተ ከርስትያን የሚካሄደውን የስራት አጥፍተው ያሉትን አይቃወሙም? ዉሸታሞች ሁላ>>>>>>>>>>>>>>

  ReplyDelete
 14. Enter your comment...

  ReplyDelete
 15. ጌታ ይባረክ! ጌታ ሲሰራ የሚከለክለዉ የለም! አሜን አሜን!

  ReplyDelete
 16. I am recently become protestant Christian. I grew up at EOTC, who leaded me to protestant Church? The holy spirit period. Let me give you a little worning for those who oppessing the true gospel preacher like Memeher Tikest and others, millions will leave Orthodox Church very soon to protestant Church. May the Almighty of God open your heart to his kingdom!

  ReplyDelete
 17. ወይ ሃራጥቃዎች
  ሰው ባይዋጋችሁ እውነት ይዋጋቸኋል፡፡ እግርን እግረ ነህ ካላሉት ቆይቶ እጅ ነኝ ይላል አሉ፡፡
  ምንም ብታሽሞነሙኑት ፀረ ቤተክርስቲያንነታችሁ ሊደበቅ በማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡
  ልብ ይስጣችሁ
  ወይ ሃራጥቃዎች
  ሰው ባይዋጋችሁ እውነት ይዋጋቸኋል፡፡ እግርን እግረ ነህ ካላሉት ቆይቶ እጅ ነኝ ይላል አሉ፡፡
  ምንም ብታሽሞነሙኑት ፀረ ቤተክርስቲያንነታችሁ ሊደበቅ በማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡
  ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 18. Praise God for His mercy upon us!

  Dear brothers and Sisters, It is a sign for our beloved historical Church to see herself in the mirror of God's Word. You, heros of our mother church, I would like to encourage you to go forward in doing for the Truth so that we can see the resurrection of our mother Church. Please let you know that I was forced by the wicked people to leave out my main church and becoming member of one protestant church. But now I am glad to join Tehadiso Orthodox so that I can contribute something in this huge task to bring back our church to its original beauty based only on the Gospel of Jesus Christ!!!! Please don't give up! This is the only way and means to safe our beloved Country from any form of trouble.

  Dekike Estifanos

  ReplyDelete
 19. https://www.youtube.com/watch?v=f1BAKA68uRA

  ReplyDelete
 20. https://www.youtube.com/watch?v=4ttQyv12x4s

  ReplyDelete
  Replies
  1. Devil have >7000 years experience but hama & tehadso more than him!!!

   Delete
 21. Kes hahahaha defar neh bakih? Ayehew newrihin yetekesikachew hulu hodam yeluter lijoch ekek sebakiwoch nachew

  ReplyDelete
 22. Wengel wengel ......ወንጀል ይቁም እዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ።

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር ይርዳን መጣላት ሲገድል እንጂ ሲያፀድቅ አላየንም ህዝቡ ማንን እንደሚያምን ግራ ገብቶታል እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን እርሱንም እንሰማለን። ለንስሓ ያብቃን አሜን

  ReplyDelete
 24. ኤም ኬ በህዝበ ክርስቲያኑ ውስጥ ያስገባው የስድብ መንፈስ በ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይፍረስ።የተሻላችሁ ፀልዪ ።መፅሀፍ ስድብ ሀጢያት ነው ብሏል ሰው እግዚአብሄርን ከመስማት ይልቐ ዳንኤል ክብረትን ነው የሚሰማው እሱ ተው ቢላቸው ይተዋሉ መሪያቸው ቅዱስ መፀሀፍ ሳይሆነ ማቅ ነው።ይህነ ህዝብ አምላክ ይፍታው በስድብ ተተብትቧል።

  ReplyDelete
 25. ‹‹ የምትጠፋ ከተማ ነጋሪት ቢመቱላት አትሰማ»
  እንዲህ የሚለዉ የአባቶች አፈ ታሪክ በእኛ ላይ እንዳይፈጸም ያሰጋኛል
  ይህን የምለዉ እንደኦርቶዶስ ተዋሕዶ ልጅነቴ ሰሞኑን በኦርጋን ዙሪያ እየተደረገ ያለዉን ቅጥ ያጣ እሰጥ አገባና ከክርስትና ዉጭ የሆነ ዘለፋ በጣም አሳስቦኝ ነዉ አስታያየቴን ለመስጠት የተነሳሁት።
  እንደ ኦኔ እንደኔ በእዉነት በጣም ያዘንኩበት ወቅት ቢኖር ይህወቅት ነበር ምክንያቱም ስንት የምንነጋገርበትና የምንወያይበት ሐይማኖታዊ ጉዳይ እያለ በዚህ በቁስ አካል [በኦርጋን]ዙሪያ ጊዜያችን ማሳለፉ በጣም ያሳዝናል ። የእግዚአብሔ መንግስት ወንጌል ቢገባን ኖሮ እንዲህ በተራ ነገር በኦርጋን ይህን ያህል አንጨቃጨቅንም ነበር
  ለኔ ኦርጋን ተዘመረበት አልተዘመረበት ምንም ስሜት አይሰጠኝም ያሬዳዊዉን ዜማ ጠብቆ ከሄደ መልካም መልካም ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር ቢዉል በጣም ያስደስተኛል ነገር ግን ሰዉን የሚያሰናክል ከሆነ ቢቀርምስ ምን አለበት።
  እኔን በጣም እያሳሰበኝ ያለ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያናችን አጠቃላይ ሁኔታ ነዉ ምክንያቱም ቤተክርስቲያና ምእመና ተራርቀዋል ሆድና ጀርባ ሆነእዋል ቤተክርስቲያን በዚህ ሰአት ማን እንደሚመራት አይታወቅም ።
  አባቶች ናቸዉ ? ማህበራት ናቸዉ ? ም¦መናን ናቸዉ ? አይታወቅም ወይም ሁሉ መሪ የሆነባት ቤት ሆናለች ማለት ነዉ ይህ ደግሞ እንÎን ለታላØ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀርቶ ለአንድ ሰዉ ቤትም አይሆንም አደጋ ነዉ አያዘልቅምና። ይህን ያልኩበት ምክንያት መደማመጥ፤ መከባበር ጠፍቶ ሁሉም በየፊናዉ እኔ ነኝ ፤እኔ ነኝ ያለâ ስንል መታየታችን በዉጤ ጥያቄ ስለፈጠርብኝ ነዉ።
  በኦጋን እንዲህ የተረበሽን ሌላ ሐይማኖታዊ ጉዳይ ቢነሳ እንዴት ልንሆን ነዉ ?ይልቅስ ይህ የሰሞኑ የኦርጋን ጉዳይ ለአባቶቻችን የማነቃቂያ ደወል ነዉ ብየ አምናለሁ
  አባቶቻችን ተሎ ብለዉ መከፋፈሉን ትተዉ ለሚያልፍ ጊዜ አንዱ ሌላዉን ከመወንጀል ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ከጥፋት ሊታደት ይገባል ከዚህም ጋር የተአምራት የገድላት የድርሳናት ጉዳይ ታስቦበት በየጊዜዉ ችግር ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሚታረሙት ታርመዉ ቢቀመጡ መልካም ነዉ።
  አልያ ነገ ደግሞ ሌላ ነገር መነሳቱ አይቀሬ ነዉ። ሁሉን ነገር በጽሞና ተመልክቶ በሁሉም ነገር ላይ የማያዳግም ዉሳኔ መስጠቱ አስፈላጊ ነዉ ።
  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅልን ።

  ReplyDelete
 26. Betekedesew Sifira Pasteroch tesebisibew sitayu tetenikeku!! Niku!!!

  ReplyDelete
 27. lebnet be ken tejemere

  ReplyDelete