Thursday, February 11, 2016

አባ ማቴዎስ ጉዴን ያወጣብኛል በሚል ሥጋት ለእምነት የለሹ ዘሪሁን ሙላቱ ወደ ሥራው እንዲመለስ ደብዳቤ ጻፉለት - ደብዳቤውን ኮሌጁ አልተቀበለውም

Read in PDF

በስነ ምግባር ጉድለት ከቅድስት ስላሴ ኮሌጅ የተባረረውን እምነት የለሹን ዘሪሁን ሙላቱን ወደ ስራው እንዲመልሰው ሲሉ ለቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በቁጥር 1691/6090/2008 በቀን 18/5/2008 ዓ.ም የጻፉት ደብዳቤ በኮሌጁ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸው ማቅ ተሐድሶ ነው ብሎ የከሰሰውን ሁሉ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ከሥራና ከደመወዝ በማገድ ብዙዎችን ለረሃብና ለችግር በመዳረግ አቻ ያልተገኘላቸው አባ ማቴዎስ፣ ይልቁንም ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤ ትይቶና ያለ ጥፋታቸው ይቀርታ እንዲጠይቁ ተደርጎ በይቅርታ እንዲመለሱ የተጻፈላቸውን ሰዎች ጭምር በምህረት የለሽና ጨካኝ ልባቸው ውሳኔ ሲያባርሩ የቆዩት አባ ማቴዎስ  ለእምነት የለሹ ዘሪሁን የይመለስ ደብዳቤ በአስቸኳይ መጻፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ግን ዘሪሁን ቶሎ እንዲጽፉለት ያደረገው የአባ ማቴዎስን ገበና አወጣለሁ በማለቱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
አባ ማቴዎስ በምንኩስና የቂርቆስ አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዜ እዚያው አካባቢ የታወቀች ሴት ሚስት እንደነበራቸውና ይህ ቤተክርስቲያኑ አካባቢ በሁሉም አገልጋዮች ዘንድ የሚታወቅ መሆኑን በአሁኑ ወቅትም ስድስት ኪሎ አካባቢ አንዲት ሴት በማስቀመጣቸው ቅዳሜና እሑድን እዚያ እንደሚያሳልፉ ዘሪሁን ስለሚያውቅ በአባ ሳሙኤል ላይ የጳጳሱ ቅሌት ብሎ እንደጻፈ አሁንም በአባ ማቴዎስ ላይ እጽፍና አወጣለሁ ብሎ በማስፈራራቱ ደብዳቤው እንደተጻፈለት ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአባ ማቴዎስ ማንነትና ሕይወታቸው ምን እንደሚመስል ይህንና ያልተነገሩና ሌሎች መረጃዎችን ወደፊት በአስፈላጊው ጊዜ እናቀርባለን፡፡ ይህን የምናደርገው የሰውን ገበና በማውጣት የምናገኘው ጥቅም ኖሮ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ እያካሄዱና ለዚያ ሽፋን እየሰጡ ያሉ አንዳንድ ጳጳሳትና የቤተክህነት ባለስልጣናት እንዲያ የሚያደርጉት ገበናቸው እንደዘሪሁን ባሉ ገበናን ገላልጠው መጽሐፍ በሚጽፉ ግለሰቦች እና እንደማኅበረ ቅዱሳን ባሉ ቡድኖች “ምስጢርዎን እንጠብቃለን ያ የሚሆነው ግን እኛን ደግፈው ሲቆሙና የምንሻውን ሲፈጽሙልን ነው” ስለሚባሉ ምናልባት ተሸማቀው ከሚኖሩ ነጻ እንዲወጡ በማሰብና የሚያካሂዱትን ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ ትተው ንስሀ እንዲገቡና ለቤተክርስቲያን መለወጥና መሻሻል እንዲሰሩ ለማገዝ ነው፡፡    

አባ ማቴዎስ ለቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ በጻፉት ደብዳቤ ኮሌጁ ዘሪሁንን ከሥራ ሲያባርር የተለያዩ የህግ አንቀጾችን እንደ ሻረና መብቱን እንደገፈፈ አስመስለው ያሳጡት ቢሆንም ኮሌጁ ግን ግለሰቡ በፈጸመው ጥፋት የተነሣ ማባረሩን ለግለሰቡ የጻፈለትን የስንብት ደብዳቤ መሠረት በማድረግ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይሁንና የሦስቱም ኮሌጆች የበላይ ኃላፊ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንጂ ሥራ አስኪያጁ አባ ማቴዎስ ባለመሆናቸው በሦስቱም ኮሌጆች ላይ ሥልጣን ስለሌላቸው የጻፉት ደብዳቤ በኮሌጁ በኩል ተቀባይነት አላገኘም፡፡ አባ ማቴዎስ ኮሌጆችን የማስተዳድረው እኔ ነኝ ካሉ ማኅበረ ቅዱሳን እርሳቸው በሚያስተዳድሯቸው ኮሌጆቹ ላይ በተለይም እሳቸውም ጭምር በተማሩበት መንፈሳዊ ት/ቤት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲከፍት አንድም ትንፍሽ ሳይሉና ድምፃቸውን እንኳን ሳያሰሙ ለአንድ ተራና እምነት የለሽና በጥፋቱ ምክንያት ለተባረረ ግለሰብ አስቸኳይ ደብዳቤ መጻፋቸው ከቤተ ክርስቲያን አንፃር ሳይሆን ከራሳቸው ችግር አንፃር ደብዳቤውን የጻፉ ስለሆነ ራሳቸውን ትልቅ ትዝብት ላይ ጥለዋል፡፡
አባ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት የማቅን ጥቅም ከማስጠበቅ ውጪ ምንም እየሠሩ እንዳይደለና በበጀት ዕጥረትና በቁሳቁስ አለመሟላት የጠቅላይ ቤተክህነቱ መምሪያዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከሙ እንደሚገኙ ለምሳሌ የስብከተ ወንጌልና የካህናት አስተዳደር መምሪያዎች በማማረር ላይ ይገኛሉ፡፡ ማቅን በሚመለከት ግን ከፍተኛ የገጽታ ግንባታ ሥራ ሲሰሩ እንደነበር “ዐዋጅ ነጋሪ” በተሰኘውና በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በጥቅምት 2008 ዓ.ም ባሳተመው መጽሔት ስለማቅ የቀረበውን ሰፊና ጥልቅ ዘገባና ስለመምሪያዎች የቀረበውን ቁንጽል ዘገባ በማነጻጸር ብቻ እንኳን አባ ማቴዎስ ለማን እየሠሩ እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ መናፍቁ ሃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ 2007 ላይ የጻፈውን ኑፋቄ በተመለከተ እንኳን በሊቃውንት ጉባኤ ሪፖርት ውስጥ የቀረበው ዘገባ እጅግ የተለሳለሰና በወንዝ ልጅነት ላይ የተመሠረተ የማኅበረ ቅዱሳንን ስሕተት ለመሸፈንም ያለመ ሆኖ ይገኛል፡፡ ሪፖርቱ “በ2007 ዓ.ም በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ “በእርሱ አምሳል እንወለድ ዘንድ” በሚል ርእስ በታተመው መጽሔት ላይ “እመኵሉ ሕዝብ ድንግል ማርያም” በሚል ንኡስ ርእስ በቀረበው ጽሑፍ ውስጥ ከምሥጢረ ሥጋዌ አስተምህሮ ውጪ የሆነ ትምህርት ስላለበት የጽሑፍ አቅራቢ ግለሰብና የጽሑፉን ኮሚቴውን በማቅረብ ጉባኤው ከጠየቀ በኋላ እንዲስተካከል አድርጓል” ነው የሚለው (ዐዋጅ ነጋሪ ገጽ 74)፡፡ ነገሩ ተድበስብሶ ቀረ እንጂ በተግባር እስካሁን ምንም የተደረገ ነገር እንደሌለ ይታወቃል፡፡ አንደኛ በጽሑፍ የተበተነው ኑፋቄ ለስሙ “እንዲስተካከል አድርጓል” ተባለ እንጂ በምን መንገድ እንደተስተካከለ የተባለ ነገር የለም፡፡ ከአሠራር አንጻር እንደሚጠበቀው ግን ተመጣጣኝ የሆነ የጽሑፍ ምላሽ በቤተክህነቱ ጋዜጣ ወይም መጽሔቶች ምላሹ እንዲሰጥ አልተደረገም፡፡ ግለሰቡም በይቅርታ ተመልሶም ከሆነ ስለተሰጠው ቀኖና የተባለ ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ሃይለ ጊዮርጊስ የአባ ማቴዎስ የወንዝ ልጅ ነዋ፣ ወዲህም የማቅ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡ ሁለተኛ የተጻፈው ኑፋቄ መሆኑ እየታወቀ በስሙ ኑፋቄ ብሎ ከመጥራት ይልቅ “ከምሥጢረ ሥጋዌ አስተምህሮ ውጪ የሆነ ትምህርት” ተብሎ ጉዳዩ በአዎንታዊ መንገድ ነው የቀረበው፡፡ የሌሎችን ትክክለኛ ትምህርት ኑፋቄ ለማለት ማንም የማይቀድማቸው አባ ማቴዎስ ትክክለኛውን ኑፋቄ አድብስብሰው ማለፋቸው ለማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ለቤተ ክርስቲያን እንዳልቆሙ ማስረጃ ነው፡፡ ይህን ጊዜ ሌሎች እውነትን ተናግረው በማቅ ተከሰው ቢሆን ኖሮ ይቅርታ ቢጠይቁም እንኳን ከማባረር ውጪ ምንም አይታያቸውም ነበር፡፡
በሥልጣን ዘመናቸው ለማኅበረ ቅዱሳን ሲሰሩ የቆዩት አባ ማቴዎስ በቢሮአቸው ዘርፈ ብዙ አስቸኳይ ምላሽ የሚሹ የአቤቱታ ዶሴዎች ተከምረው እያለ እያለ በጥፋቱ ለተባረረው ለዘሪሁን አስቸኳይ ብለው ወደቦታው ይመስል ሲሉ መጻፋቸው ጉዴን ያወጣብኛል ከሚል ፍርሃት እንደሆነ ሁሉም ተረድቶታል፡፡ “ባልበላውም ጭሬ አፈሰዋለሁ አለች ዶሮ” እንደተባለው አባ ማቴዎስ አሁን እየሄዱበት ያለው መንገድ ግንቦት ሳይመጣ አበላሽቼው ልውረድ ነው የሚመስለው፡፡


9 comments:

 1. የስንት ሊቃዉንት ፋይል መልስ አጥቶ ጥረጴዛቸዉንና መሳቢያቸዉን አጨናንቆት
  ለዚህ አጭበርባሪ እምነተቢስ ዘሪሁን በአስቸካይ መጻፋቸዉ ሌላ ምን ይባላል ስማቸዉን እንዳያጠፋ ዉለታ ለማስቆጠር ነዉ እንጅ
  ዘሪሁን እንደዉ ምንም ቢያደርጉለት ፩ ቀን ማዉጣቱ አይቀር እድሜ ይስጠን እንጅ በቅርቡ እናያለን
  የሊቃዉንቱና የንጹሃን አባቶች ፋይልማ በየ ቢሮዉ ወድቆ የሚመለከተዉ ጠፍቶ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

  ገንዘብና የስድብ አፍ ባይኖራቸዉም ለእያንዳንዱ እንደስራዉ ዋጋዉን የሚከፍለዉን ጌታ ፈርታችሁ ሊቃዉንቱንም አስባቸዉ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ

  ReplyDelete
 2. elelllllllllllllllllllelleleleleleleleelelelelel temesgen wed sera temeles! netsu sew!

  ReplyDelete
 3. What is the overall idea of the script? title different, content different. I guessed the writer is SATAN itself cos spiritual writers know the concept of KEBATE ABESA.
  !!!!!!!!DO NOT WRITE SINCE ONLY YOU ARE SPONSORED BY LUTHERIANS......

  ReplyDelete
 4. ትክክለኛ የአሪዎስ ቅሬቶች ናችሁ….. ክፉ የሚያወራ የክፉ ሰይጣን አሳማዎች ናችሁ

  ReplyDelete
 5. ነዉር የሌለበት በኮንፊደንስ የተጣለበትን ኃላፊነት የሚጣ አባት እግዚአብሔር ለቢርተክርስቲያናችን ይስጥልን

  ReplyDelete
 6. Enantem ye papasu lijoch nachu ende?

  ReplyDelete
 7. What nensas and stuped ideas do you raise
  Menafikan Tawkobachuhal
  We will be more strong to fight you.
  Nari

  ReplyDelete
 8. ይህ ሁሉ ጥላቻ ከምን የመጣ ነው? እባካችሁ ለቤተክርስቲያን እናስብ። ሰው እንዲጠፋ ሳይሆን እንዲመለስ እናድርግ። ይህ ሁሉ መዘብዘብ ምን ያደርጋል?

  ReplyDelete