Tuesday, February 16, 2016

ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አንዳንዶቹ እንደ ገና ሊጤኑ ይገባልከዘሩባቤል
ክፍል ሁለት
ባለፈው ጽሑፌ የጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ በማጠቃለያው ካወጣቸው የአቋም መግለጫዎች መካከል በ7ኛ ተራ ቁጥር ላይ የሰፈረውን ነጥብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሊያጤነው እንደሚገባ መጠቆሜ ይታወሳል፡፡ ለዛሬው ደግሞ በተራ ቁጥር 8 ላይ የሰፈረውን ነጥብ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ በቅድሚያ ግን ነጥቡን ለማብራራት መንደርደሪያ የሚሆነኝን አንድ መወድስ ላቅርብ፡፡
መወድስ
የዋሀ እስራኤል ሮብዓም ኀሣሤ ልቡና
እምክረ ሊቃውንት ዐባይ ምክረ ሕፃናት ንስቲተ
አሜሃ ኢረብኀ ወኢተበቍዐ ጽሚተ
አማሰነ አላ ነገደ ዐሠርተ
ሕዝበ እስራኤል እስከ አፍቀሩ
እም አምልኮ አምላክ ልዑል ጣኦታተ ንኡሳተ
ሲኖዶስሂ ፍንወ ጽድቅ ዘኢየአምር ጽድቃተ
እም አፍቅሮ ወርቅ ምክረ ዐመፃ ኀበ ኀበ ይፈርህ ማኅበራተ
ቤተ ክርስቲያን ቤቶሙ ዘደመ ኢየሱስ ጽሪተ
አውፅአ ወሰደደ ብዙኀ ሊቃውንተ
ቅኔው ከሰሎሞን በኋላ የነገሠው ርብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ሰምቶ የሕዝበ እስራኤልን ቀንበር ማቅለል ሲገባውና እስራኤልን አንድ አድርጎ ማስተዳደር ሲችል በባልንጀሮቹ ወጣቶች ምክር ተነድቶ ምንም እንዳልተጠቀመና ዐሥሩን ነገደ እስራኤል እንዳጣ ሁሉ (1ነገሥት 12፥1-24) በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ሥር የወደቀውና በእነርሱ ሳንባ እየተነፈሰ ያለው ሲኖዶስም በሊቃውንት ምክር መሄዱን ትቶ በአንዳንድ ውሳኔዎቹ በማቅ ምክር በመነዳት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ከቤተ ክርስቲያናቸው እያወጣ በማሳደድ ላይ መሆኑንና ሌሎችንም የሚጎዱና ሲኖዶስን ትዝብት ላይ የሚጥሉና ተግባራዊነታቸው የሚያጠራጥር ውሳኔዎችን እንዲወስን እየተደረገ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ 

ለዚህ አንዱ ማሳያ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በ8ኛው ተራ ቁጥር ላይ ያሰፈረው የአቋም መግለጫ ነው፡፡ የአቋም መግለጫው ነጥብ እንዲህ የሚል ነው፡- “አንዳንድ የእምነት ተቋማት ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገልገያ የሆኑትን ንዋየ ቅድሳት፣ አልባሳት፣ መስቀሎች፣ መቋሚያ፣ ከበሮ፣ ፀናጽልና የመሳሰሉትን ሁሉ የራሳቸው ያልሆነውን የራሳቸው በማስመሰል እየተጠቀሙ መሆኑን ጉባኤው ተገንዝቦ በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ ለማድረግ ለጥናቱ ብፁዓን አባቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡”
 ይህን የሲኖዶሱን የአቋም መግለጫ ሳነብ ከዓመታት በፊት አንድ ወዳጄ ያወጋኝን ገጠመኝ አስታወሰኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፣ በዘመን መለወጫ በዓል ላይ ነጭ በነጭ ለብሶ የነበረና ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ አባል የሆነ ሰው በዚያው ከተማ የሚኖር የሚተዋወቀውን አንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በመንገድ ላይ ያገኘውና “እንኳን አደረሰህ” ይለዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳኑ ሰው ግን “እንኳን አብሮ አደረሰን” በማለት ተገቢውን ምላሽ መስጠት ሲገባው እርሱ ግን “በማን ካሌንደር?” ሲል መለሰለት፡፡ ይህ እጅግ የሚያሳፍር ምላሽ ነበር፡፡ ይህ የዘመን አቆጣጠር እኛ የፈጠርነው ሳይሆን ከሌሎች ወስደን የእኛ ያደረግነው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ይህን አቆይታ ለኢትዮጵያውን መጠቀሚያ በማድረጓ ባለውለታ ስትሆን ልትመሰገንም የሚገባት መሆኑ በያጠያይቅም የዘመን አቆጣጠሩ ግን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ እንደዜጋ የሚጠቀሙበት ነው እንጂ የአንድ የእምነት ተቋም መገልገያ መሣሪያ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ጤናማነት የጎደለው አስተሳሰብ ነው፡፡
ይህ የማቅ አባል ያሰበው ማኅበሩ እንደሚያስበው ነው፡፡ ማኅበሩ አክራሪና ጽንፈኛ አመለካከት የተጠናወተው ስለሆነ የሚያስበው እንዲህ በጠባቡ ነው፡፡ ይህን አስተሳሰቡን በተጽዕኖው ሥር እንዲውሉ ባደረጋቸው አንዳንድ ጳጳሳት ላይ በማጋባትም ብዙ ጊዜ እታገልለታለሁ የሚለውንና አንዳንድ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በእኛ አልባሳት መስቀል ከበሮና ጸናጽል ወዘተ እንዳይጠቀሙ ማድረግ አለብን የሚለውን አቋሙን ነው በጥቅምቱ የሲኖዶስ ስብሰባ መግለጫ ውስጥ ያነበብነው፡፡ “ከለማበት የተጋባባት” አሉ አበው፡፡
ይህ ነጥብ ሲነሳ ብዙ ነገሮች ይታወሳሉ በቅድሚያ ግን፣ “መኑ የሐትተከ ወምንተ ኮንከ ዘትዜኀር ወትትዔበይ ብከኑ ዘኢነሣእከ እም ካልእከ፡፡ ወእመ ዘብከ ነሣእከ እም ካልእከ ለምንትኑ ትዜኃር ወትትዔበይ ከመ ዘኢነሥአ፡፡” ትርጉም፡- “አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?” (1ቆሮ. 4፥7) ተብሎ የተጻፈው ሐዋርያዊ ቃል ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷ ያዳበረቻቸው ነገሮች የመኖራቸውን ያህል ከሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት የወሰደችው ነገርም አለ፡፡ ለምሳሌ ከላይ በተጠቀሰው ገጠመኝ ውስጥ “በማን ካሌንደር?” ያለው የማቅ አባል የተመካበት የዘመን አቆጣጠሩ አገር በቀል ግኝት ሳይሆን ከግብጻዊው ድሜጥሮስ የተገኘና አባቶቻችን ያዳበሩትና የተራቀቁበት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ቤተ ክርስቲያኗ ከሌላ ያልተቀበለችው ስለሌለ እንዳልተቀበለች ሆና መመጻደቅ የለባትም፡፡
የጥቅምቱ ሲኖዶስ በመግለጫው የቤተ ክርስቲያኒቱ “መገልገያ የሆኑትን ንዋየ ቅድሳት፣ አልባሳት፣ መስቀሎች፣ መቋሚያ፣ ከበሮ፣ ፀናጽልና የመሳሰሉትን ሁሉ የራሳቸው ያልሆነውን የራሳቸው በማስመሰል እየተጠቀሙ መሆኑን ጉባኤው ተገንዝቦ በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ ለማድረግ ለጥናቱ ብፁዓን አባቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡” ብሏል፡፡ የእርሷ መገልገያዎች የተባሉትን ከየት አመጣቻቸው? ምንጫቸው በዋናነት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም እናቷ ከነበረችው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ለምሳሌ ሌሎቹ የሚጠቀሙባቸው አልባሳት የትኞቹ ናቸው? በአብዛኛው የአገር ባህል ልብሶች ናቸው፡፡ እንዲሁም የኮሌጅ ደቀ መዛሙርትና ሰባክያን የሚለብሷቸው ቀሚሶችን ሊሆን ይችላል፡፡ በቅድሚያ የሀገር ባህል ልብሶች የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀብት ናቸው እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ የተለዩ ሀብቶች አይደሉም፡፡ ቢሆኑስ ደግሞ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን መጠቀማቸው ምን ጉዳት አለው? መብታቸውስ አይደለም ወይ? እንዲያውም አልባሳቱ ተጽዕኖ መፍጠር በመቻላቸው ሌሎችም ስለ ለበሱትና ኢትዮጵያዊው አለባበስ በመለመዱ ደስተኛ መሆን እንጂ መከፋት የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን እነርሱ ይህን በመልበሳቸው ከምዕራባዊው ባህል ወደ ኢትዮጵያዊው ባህል መመለሳቸውን በማሰብ ከመደሰት ይልቅ “ልዩነት እንጂ መመሳሰል መታየት የለበትም” በሚል ነገሩን በግራ በኩል ነው የሚያየው፡፡
ቀደም ብሎ ሰባኪዎች የነበሩ ባሕታውያን ይለብሱ የነበረው ልብስ ደበሎ፣ ወይባ ሌሎቹ ደግሞ ነጠላ ወይም ኩታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የሰባኪዎች ቀሚስን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከጥቂት አሠርት ዓመታት ወዲህ ከሌሎች የወሰደችው እንጂ የእርሷ ግኝት አይደለም፡፡ ስለዚህ “መኑ የሐትተከ ወምንተ ኮንከ ዘትዜኀር ወትትዔበይ ብከኑ ዘኢነሣእከ እም ካልእከ፡፡ ወእመ ዘብከ ነሣእከ እም ካልእከ ለምንትኑ ትዜኃር ወትትዔበይ ከመ ዘኢነሥአ፡፡” ትርጉም፡- “አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?” (1ቆሮ. 4፥7)፡፡
ማቅና እርሱ ያሳሳተው ሲኖዶስ ሌሎች በአልባሳቶቻችን መጠቀማቸውን የጠሉበት ምክንያት ምን ይሆን? እኔ እንደሚመስለኝ በአልባሳቶቻችን በመመሳሰል ምእመናኖቻችንን ለመወሰድ ነው የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ምእመናን በዚህ የሚወሰዱበት ምክንያት ብዙም አይደለም፡፡ ምእመናን በዋናነት ወደሌሎቹ የሚሄዱት ግን ነፍስን ሊያሳርፍ የሚችል ትምህርተ ወንጌል ባለማግኘታቸው ነው፡፡ በዚያ ፈንታ ዘወትር ሌሎችን መንቀፍና ተሐድሶ ጉድ ሊያፈላብን ነው፣ መናፍቃን አስቸገሩን በሚሉ አሰልቺ ትምህርቶች መድረኩን ከመሙላት ልብን የሚያሳርፍ ወንጌል ቢሰበክ እንኳን ያለው ሊሄድ የወጣውም ሊመለስ ይችላል፡፡ ስለዚህ መፍትሔው ልዩነትን ማራገብንና ሁሌ ነቀፌታና ትችትን መናገር ብቻ ትቶ ወንጌልን መስበክ ነው፡፡ ምንም ይሁን ምን አብዛኛው ሰው ወደ ሌሎች የፈለሰው የወንጌልን እውነት ፈልጎ ተረት ተረት ሰልችቶ ነው፡፡ የሚፈልገውን ወንጌል ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሰበከች ወደየትም አይሄድም፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የልጅ ምክር ከሚመሩትና ነገሩ ካልገባቸው አንዳንድ አባቶች በቀር ቤተክርስቲያኒቱ ይህን የተገነዘበች ይመስላል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዘንድሮው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ጥቅምት 8/2008 .ም ባስተላለፉት መልእክት ላይ “ቤተ ክርስቲያናችንን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስናነጻጽር በቊጥር እጅግ የላቀ የውሉደ ክህነት ብዝኀነት ያላት ስትሆንታላቁን የቅዱስ ወንጌል ተልእኮንለውሉደ ሰብእ በማዳረስ ረገድ ያለን ውጤት ግን አናሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ባህርን አቋርጦ፣ ድንበርን ተሻግሮ፣ እስከ ጽንፈ ምድር ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በሀገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምእመናንን ማብዛት ብዙ ያልተሄደበት እንደሆነ ማወቅ አለብን ፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያስቆጨው ደግሞ ትናንት ቤተ ክርስቲያንሀብተ ወልድና ስመ ክርስትናሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆችዋ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደሌላው ጎራ የመቀላቀሉ ጉዳይ እጅግ በጣም እየናረ መምጣቱን ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ቅዱስነታቸው እንደጠቆሙት ላጋጠመው ለዚህ ትልቅ ችግርና አደጋ አንዱ ጉድለት “ታላቁን የቅዱስ ወንጌል ተልእኮን” በሚገባ አለመፈጸም ነው፡፡
ዛሬ በልጅ ምክሩ ሲኖዶስን እያሳተ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ሲሰራ የኖረው ምንድነው? በአብዛኛው ወንጌል እንዳይሰበክና በምትኩ ወግና ልማድ እንዲጠረቅ የሚያደርግ ድርጊት ሲፈጽም ነው የኖረው፡፡ ይህን በተለይ በዪኒቨርስቲዎችና በኮሌጆች አካባቢ የግቢ ጉባኤ አባላት በሆኑ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ለእነርሱ የሚያስተምረው ወግና ልማድ ነው እንጂ ወንጌልን አይደለም፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙዎቹ ወንጌልን ወደሚያስተምሩ ወንጌላውያን ይሳባሉ፡፡ ከወንጌል ትምህርት ጋር የማይቃረነው ወግና ሥርዓት ተጠብቆ መቆየቱ ተገቢ ቢሆንም ከወንጌል በላይ ወይም ወንጌልን ተክቶ የሚሰበክ ከሆነ ግን በተለይ በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ነው የሚሆነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሠረት ወንጌል እንጂ ወግና ልማድ አይደለምና፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ወንጌል በሚሰብኩ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ የተመሠረተ ዝማሬ እየዘመሩ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ተሐድሶ መናፍቅ የሚል ታፔላ በመለጠፍ እርሱ ባቀነባበረው ክስ ራሱ ከሳሽ ራሱ ዳኛ ሆኖ ብዙዎችን ለስደትና ለፍልሰት ደርጓል፡፡  
ሌሎቹ ይጠቀሙበታል የተባለው ሌላው ነገር መስቀል ነው፡፡ መስቀል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ሳይሆን የክርስትና ምልክት ነው፡፡ የትኛውም በተለይም በሥላሴ የሚያምን ቤተ ክርስቲያን አርማው ውስጥ መስቀል አለ፡፡ መስቀል ላይ በተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ ድኅነት የተፈጸመ በመሆኑ መስቀል የክርስትና ምልክት ወይም አርማ ሆኗል፡፡ ምናልባት ጌጠኛ ተደርጎ የተሠራው መስቀል የእኔ ነው የምትል ከሆነ ልክ ነው፣ ክርስቶስ ግን በተመሳቀለ ዕንጨት ላይ እንጂ በጌጠኛ መስቀል ላይ አልተሰቀለምና እርሷም ሳትጠይቃቸው ሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ለጌጥ የተሠራውንና ክርስቶስን ሳይሆን ራሱን የሚያሳየውን “ጌጠኛውን መስቀል” ትተዉላት የክርስቶስን ሕማም የሚያስታውሰውን መስቀል መጠቀም ይችላሉ ባይ ነኝ፡፡
ከመስቀል በተጨማሪ ከዜማ ዕቃዎች መካከል “መቋሚያ፣ ከበሮ፣ ፀናጽል” የተባሉ የዜማ ዕቃዎችንም እንዳይጠቀሙ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እንዲደረግ ነው የጥቅምቱ ሲኖዶስ መግለጫ ያስገነዘበው፡፡ በቅድሚያ የእግዚአብሔር ቃል መቋሚያን ባይጠቅስም በከበሮና በጸናጽል እግዚአብሔርን አመስግኑት ይላል (መዝ. 150፥4-5)፡፡ ባህላዊ የዜማ ዕቃዎችን ቤተ ክርስቲያኒቱ በማቆየቷ የሚያስመሰግናት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ለቤተ ክርስቲያኗ ዕውቅና መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት በእነዚህ የዜማ ዕቃዎች ሲገለገሉ ያየ ማንም ሰው የሚያስታውሰው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ነው፤ ይህም ለቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ ክብርን የሚያሰጣት ሁኔታ እንደ ሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ ይህን መልካም እሴት መመልከት አለመቻልና በሌላ መንገድ መረዳት ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ ከበሮና ጸናጽሉ የእኔ ብቻ ንብረት ነውና በከበሮና በጸናጽል መዘመር አትችሉም ብላ ለመከልከል ማሰብ እንኳን ከቤተ ክርስቲያኗ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ልከልክል ብትልም አያስኬዳትም፡፡ መብቱን መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጥ በመሆኑ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ወደዚህ መመለሳቸውም መልካም እንጂ የሚያስነቅፍ አይደለም፡፡ ሲኖዶሱን እዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ የከተተው የማኅበረ ቅዱሳን የልጅ ምክር ነው፡፡ ስለዚህ ከሮብአም ስሕተት መማር አለበት፡፡
በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ቅዱስ ሲኖዶስ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ እየተወያየና እየወሰነ ያለው ውሳኔና እያወጣ ያለው የአቋም መግለጫ በሲኖዶሱ ላይ ጥያቄን የሚያስነሣ እየሆነ ነው፡፡ ሲኖዶሱ እየተመራ ያለው በማን ምክር ነው? በሊቃውንቱ ምክር ወይስ በልጆች ምክር? መቼም በልጆች ምክር የተመራ እስካልሆነ ድረስ “አንዳንድ የእምነት ተቋማት ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገልገያ የሆኑትን ንዋየ ቅድሳት፣ አልባሳት፣ መስቀሎች፣ መቋሚያ፣ ከበሮ፣ ፀናጽልና የመሳሰሉትን ሁሉ የራሳቸው ያልሆነውን የራሳቸው በማስመሰል እየተጠቀሙ መሆኑን ጉባኤው ተገንዝቦ በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ቀርቦ ውሳኔ እንዲያገኝ ለማድረግ ለጥናቱ ብፁዓን አባቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡”  የተባለው የአቋም መግለጫ ሆኖ ባልወጣም ነበር፡፡ ይህ ምክር የልጅ ምክር እንጂ የሽማግሌ ምክር አይደለም፡፡ ስለዚህ ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለውም፡፡ ትዝብት ላይ የሚጥል እንጂ የሚያስከብር አይደለም፡፡ ስለዚህ ሲኖዶስ መካሪውን በጊዜ ቢለውጥ አይሻልም ትላላችሁ? አሊያ እንደ ሮብዓም ለቤተክርስቲያን መከፈል ምክንያት እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ለሁሉም መልእክቴን በመወድሱ ልደምድም
የዋሀ እስራኤል ሮብዓም ኀሣሤ ልቡና
እምክረ ሊቃውንት ዐባይ ምክረ ሕፃናት ንስቲተ
አሜሃ ኢረብኀ ወኢተበቍዐ ጽሚተ
አማሰነ አላ ነገደ ዐሠርተ
ሕዝበ እስራኤል እስከ አፍቀሩ
እም አምልኮ አምላክ ልዑል ጣኦታተ ንኡሳተ
ሲኖዶስሂ ፍንወ ጽድቅ ዘኢየአምር ጽድቃተ
እም አፍቅሮ ወርቅ ምክረ ዐመፃ ኀበ ኀበ ይፈርህ ማኅበራተ
ቤተ ክርስቲያን ቤቶሙ ዘደመ ኢየሱስ ጽሪተ
አውፅአ ወሰደደ ብዙኀ ሊቃውንተ   

14 comments:

 1. አባ ሰላማዎች ወይም ተሐድሶዎች የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መሆናችሁ ቅኔያችሁ ምስክር ነው። ስለዚህ ተሃድሶዎች እንኳንስ ከሁለት ወር ኮርስ ተማሪው ከማህበረ ቅዱሳን ከቤተ ክህነት አቅም በላይ መሆናችሁን ተገንዝቤያለሁ። ኦርቶዶክስ አሁን ወገቧን ተይዛለች ማምለጫ የላትም ራሷን ማየት የሚቀላት ይመስለኛል።ሊቃውንቷ ተሃድሶ ከሆኑ ታዲያ ማን ሊያመልጥ ይችላል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. we know also you are thadso so your witness is for only thadso.

   Delete
  2. ልክ ነህ ወንድሜ
   ሊቃዉንቱ ተሀድሶን ይፈልጋሉ ።
   ነገር ግን ተሃድሶ የሚለዉ ስም ለመናፍቃን የሚሰጥ ስም አይደለም
   ምክንያቱም ከሐይማኖት/ከእምነት / በስተቀር ሁሉም ነገር ተሀድሶ ያስፈልገዋልና
   አሁንም ቤተ ክርስቲያና ብዙ ነገሮችን ማረምና ማደስ ካልቻለች በስድብና ሰዉን በአመለካከት ልዩነቱ በመጥላትና በማባረር መፍትሄ የማታመጣ መሆኑን በሚገባ ማረጋገጥ ይኖርባታል።

   Delete
 2. የሞኝ ወሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ!!!

  ReplyDelete
 3. ቤተ ክርስቲያን ማንንም አታሳድድም፣ አላሳደደችም፡፡ ነገር ግን ክፉ ሥራቸው እና ድርጊታቸው በቤተ ክርስቲያኒቷ ሥርዓት መሠረት ስለማያስኬዳቸው ለራሳቸው የመሰደጃ መንገድ ፈጥረው ተሰደዱ፡፡ ለዚህ ተጠያቂዋ ቤተ-ክርስቲያን ሳትሆን ተሰደድን የሚሉት ሰዎች ስለሆኑ ራሳቸውን መፈተሸ አለባቸው፡፡
  ማንም ተሰደድኩ የሚል ህሊናውን እና አግዚአብሔርን መዋሸት አይችል፡፡ ይሁዳም እኮ የሠራውን ሥራ እያወቀ ጌታ ከናንተ መካከል አሳልፎ የሚሰጠኝ አለ ብሎ ሲናገር ራሱን ነፃ ለማድረግ እኔ እሆንን ብሏል፡፡ ዛሬም ተሰደድን የሚሉት በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈጸሙትን ደባ እያወቅ ተሰደድን፣ እገሌ አሰደደን ይላሉ፡፡ እውነተኛ ከሆኑ ለምን ወደ ሚመስላቸው ሄዱ፡፡ አንድ ሰው የበለጠ ሊያስጨንቀው የሚገባው መጠርጠር ሳይሆን የተጠረጠረበትን ነገር ሆኖ መገኘት ነው፡፡
  ብላችሁ ብላችሁ የቤተክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት ከባሕላዊ አልባሳት እና ቁሳቁስ ጋር አንድ አድርጋችሁ መቁጠር ጀመራችሁ፡፡ ይሄ ራሱ ለፍላጎታችሁ ታላቅ ምስከር ነው፡፡
  ልቡና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 4. <” አሁን ማንነታችሁን በደንብ ግልጥ አደረጋችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠላት መናፍቅ መሆናችሁን ስራችሁ በደንብ ይመሰክራል እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነዉ
  ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

  ReplyDelete
 6. «ዘቦ እዝን ሰሚአ ለይስማዕ»
  እንደ እዉነቱ ከሆነ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ማስከበሩ ጥሩ ነዉ።
  ግን ስለከሮና ጸናጽል ስለ ልብስ ሲኖዶሱ መወያየቱ የሲኖዶሱን ማንነት ጥያቄ ይከተዋል።
  ምክንያቱም በዉጭ ብቻ ሳይሆን በዚያዉ በዉስጥ ይእጳጳሳቱ የቀሳዉስቱ፡ የዲያቆናቱ የመነኮሳቱ የመዘምራኑ የአለባበስ ስራቱ ትክክል ነዉ ወይ? ወይስ የዉስጡን ሳያስተካክሉ የዉጩን ለማስተካከል መሞከሩ ሞኝነት አይሆንም ወይ?
  ሲኖዶሱ ከበረታ ሌላ ስንት የሚስተካከል ነገር ነበር ገድላቱ ድርሳናቱ ተአምራቱ ስንት ስንት ይርሚታረምና የሚስተካከል ነገር አለ
  በእዉነቱ ሲኖዶሱ ከበረታ የትዉልዱን ጥያቄ መመለስ ቢችል ቤተ ክርስቲያናን ክችግርና ከሁከት ሊያድናት ይችል ነበር
  እንደኔ እንደኔ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ሁልጊዜ ለሚነሳዉና ምእመነንን ግራ ለሚያጋባዉ ችግር ተጥያቂ ሲኖዶሱ ነዉ።ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ የኔ ነዉ ይህ የኔ ነዉ ጾማችን ይህ ነዉ የጾማችን መጨረሻ ይህ ነዉ ብሎ ሲኖዶሱ ቢወስን ኖሮ ማንም ድንጋይ አይወራወርም እንዱ ሌላዉን መናፍቅ እንተ መናፍቅ እየተባባሉ ወጣቶቹ መእመናኑን ግራ አያጋቡትም ነበር
  ስለዚህ ሲኖዶሱ ልቤተክርስቲያና ካሰበ ማተኮራ ያለበት አቢይ ጉዳይ ይህ ይመስለኛል ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aryosm lik neber yibalal beneber Kere!!? Tenkoluna tirtarew leyechew! Yekomachu meselochual wedkachual. Yebirhan Melak memsel yichalal mehon gin aladelachum!!!??

   Delete
 7. Orthodoxoch lebachew yetedefene ferisawyan nachew. ferisawyan getachenen yesekelut lekoye bahelachew, tarikachew, amlakochachew, wegachew belew naw. orthodox must differentiate culture, religion and Christianity. temtatobachew, yemyamnut teret teret metsehafachew bezto endihu beye tabotu yedakeralu. ewnetu tegeltso eyale. meskin hezb. yetetameme wengel eyesebeku hezbachewn yasasetalu.

  ReplyDelete
 8. የዋሀ እስራኤል ሮብዓም ኀሣሤ ልቡና
  እምክረ ሊቃውንት ዐባይ ምክረ ሕፃናት ንስቲተ
  አሜሃ ኢረብኀ ወኢተበቍዐ ጽሚተ
  አማሰነ አላ ነገደ ዐሠርተ
  ሕዝበ እስራኤል እስከ አፍቀሩ
  እም አምልኮ አምላክ ልዑል ጣኦታተ ንኡሳተ
  ሲኖዶስሂ ፍንወ ጽድቅ ዘኢየአምር ጽድቃተ
  እም አፍቅሮ ወርቅ ምክረ ዐመፃ ኀበ ኀበ ይፈርህ ማኅበራተ
  ቤተ ክርስቲያን ቤቶሙ ዘደመ ኢየሱስ ጽሪተ
  አውፅአ ወሰደደ ብዙኀ ሊቃውንተ ሲኖዶስን የማይቀበል ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሚመስል የመናፍቅ ጽሁፍ ትርጉሙን ሳይገባህ ሰምና ወርቁን ሳትለይ ቅኔ አዋቂ ለመምሰል ነው፡፡ ድፍን ቅል መናፍቅ ብሂል ድፍንቅል ሲከፍቱት መራራ

  ReplyDelete
 9. የሚገርመው ነገር (የራሷን አበሳ በሰው አብሳ) እንዲሉ መናፍቃኑ ከሀድያኑ ራሳቸው የሚሉትን ሲሆኑ እያወቁ ሊቃውንቱን መሳደባቸው ነው። ሆድ ሲያውቅ ማታ ዶሮ ነው
  ለነገሩማ የጨለማው ዓለም ኗሪዎች ናቸውና ከጨለማው ዓለም ገዥ እንዲሳደቡ አፍ
  ስለተሰጣቸው ሊቃውንቱ ቢሰደቡም አይገርማቸውም ራሳቸውን ያውቃሉና ሌላው የሚገርም ነገር አንዳንድ የሲኖዶስ አባላት ሁኔታው እየገባቸው እንዳልገባቸው አብረው
  መናጆ መሆናቸው ነው።ይህ አካሄድ በጊዜው ርማት ካልተሰጠው ቤተ ክርስቲያችን ራስ አልባ መሆኗ አይቀሬ ነው።ከራስ ጀምሮ እስከ እግር ያለው አካል ከኔ በስተቀር
  ሌላው ለኀሳር ካለ፤ ታራሚም አራሚም አይኖርምና ውጤቱ የከፋ ይሆናል።(አዋቆች ካልሰጡት ማረሚያና አራሚ ንፍጥ ይለቀልቃል አላዋቂ ሳሚ የዘመኑ ትውልድ ስንኳንስ ምሥጢሩ ንባቡን ስለማይረዳ ስድብ ምስጋና ይመስለዋል በመሆኑም ፀረ ሊቃውንት የሆነውን ትውልድ በረቀቀ መንገድ ማረም የሚችል ፈጣሪ እርማት እንዲሰጠው እንመኛለን። እውነት ተናጋሪዎች ግን ትከውኑ ጽሉዓነ በእንተ ስምየ ተብለዋልና ሥራቸውን በድል አድራጊነት ሊወጡ ይገባል የማታማታ እውነት ይረታ

  ReplyDelete
 10. Ere endet aynet dedeb neh..?! Bileh bileh, Menfes kidus yemimerawin gubaie - chigir alew tilaleh? wey gudd, lenegeru hasabu tiru new gin yemenfes kidus gubaien mesadeb newir new. Le'Afih leket abejilet.

  ReplyDelete
 11. Menew abaselam samint alefat teresach. Eko wer tererebat ende?

  ReplyDelete