Sunday, February 21, 2016

በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሁከት ፈጣሪዎች የማቅ ተላላኪዎች ታሠሩ ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃልከፍተኛ ሙስናና ልዩ ልዩ የማጭበርበር ወንጀሎች ሲፈጸሙበት በቆየው የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማሳኞቹና ሙስናቸውንና ልዩ ልዩ ወንጀሎቻቸውን ለመሸፈን በሚል ሁከት የፈጠሩትን የማኅበረ ቅዱሳን ጀሌዎች ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ ከዚህ ቀደም እየተፈጸመ የነበረውን ሙስናና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ስናጋልጥ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ሐራ ዝምታን መርጣ መቆየቷና የማቅ ጥቅም በተነካ ጊዜ ግን በተቃራኒው ስትጽፍ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን አሁንም በሁከት ፈጣሪዎቹ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የማቅ ጀሌዎች ለምን ተነኩ በሚል የፈጸሙትን ወንጀልና ሕገ ወጥ ድርጊት በመደገፍ አሰፋሪ ዘገባ አውጥታለች፡፡ የሁከት ፈጣሪዎቹን ጥፋትም እንደ ጽድቅ ሥራ በመቁጠር አበጃችሁ ከማለትም ወደኋላ አልተመለሰችም፡፡
እነዚህ ከማቅ አይዟችሁ የሚባሉት ሁከት ፈጣሪዎች በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱስ ፓትርያርኩንም ሆነ ሀገረ ስብከቱን አናውቅም ብለው እስከ መናገር የደረሱ ሲሆን፣ በተለይም ወረቀት በመበተን ጭምር ደብሩ ውስጥ ሁከት ለመፍጠርና በዚህም የፈጸሙትን የሙስና ወንጀል ለመሸፈን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ የማቅ ብሎግ ሐራ ለማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ለቤተክርስቲያን የቆመች ባለመሆኑ ሁከት ፈጣሪዎቹ የፈጸሙትንና በማስረጃ የተረጋገጠውን ወንጀላቸውን በመሸፈን ወይም እንደ ጽድቅ በመቁጠር ይህን ወንጀል ለማጋለጥ የሠሩትንና ነገሩን ወደብርሃን ያወጡትን በመኮነን ጽፋለች፡፡ በዚህም የሐራ ውሸት ቆሞ በእግሩ መሄድ መጀመሩን መመልከት ተችሏል፡፡ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማቅ መቆሟንም በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ላይ ሙስና እየተፈጸመ፣ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ሲፈጸሙም እንደ ጽድቅ በመቁጠር በርቱ ግፉ ማለቷ ፀረ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን በተግባር አስመስክራለች፡፡ 

አማሳኞቹ ከዚህ ቀደም ከአካባቢው ፖሊስ ኃላፊዎች ጋር እየተሞዳሞዱ ወንጀሉን ለመሸፋፈን ሙከራ ማድረጋቸው በህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲገፉበት በማድረጉ በዚሁ በኩል ፍትሕ እንደማይገኝ የተገነዘበው የደብሩ አስተዳደር ለበላይ አካል አቤት በማለቱ ሁከት ፈጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን ለፍርድ እንደሚቀርቡም ይጠበቃል፡፡ እንዲህ በመሆኑም ሁከት ፈጣሪዎቹ ፖሊስም ፌዴራል ፖሊስም በድሎናል በማለት እስከ መናገር ደርሰዋል፡፡ ሐራ ግን በዚህ አጋጣሚ ለማቅ የጎን ውጋት ሆኖ የቆየውን የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ ማብጠልጠልን ነው የመረጠችው፡፡ ይህም ያረጋገጠው ችግሩ ያለው ታሳሪዎቹ ላይ መሆኑን ነው፡፡
አሁን ቀንደኞቹ በሕግ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን የፈጸሙትን ወንጀል አለማመናቸውና በደል ደረሰብን ማለታቸው “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የሚለውን ብሂለ አበው አስታውሷል፡፡ ከዚህ ቀደም በማስረጃ አስደግፈን ያቀረብናቸውና ውሳኔ ያገኙት ጉዳዮች ምን ሊሆኑ ነው?
1ኛ. በየሰንበቴው ውስጥ በፉካ መቃብር ንግድ የሚተዳደሩት ነጋዴዎች ለደብሩ ፐርሰንት ሳያስገቡ የመቃብር ፉካ የሚሸጡት መቃብር የቤተክርስቲያን ንበረት አይደለም ወይ? ወይ በመንግሥት በኩል ግብር አይከፍሉ? እንዲህ ማድረግ ሙስና አይደለም ወይ?
2ኛ. “ሰንበት ትምህርት ቤቱን ሊያፈርሱ ነው” የተባለውስ ከምን በመነሣት ነው? የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በባዶ ሜዳ ነወይ? ከሕዝብ የተሰበሰበ 75 ሺህ ብር ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሳይሰጥ ሰጥተናል ብለው፣ ሆስፒታሉ ሲጠየቅ አልደረሰኝም ካለ በኋላ የት አደራሳችሁት ሲባሉ ወጣት መንክር ግርማ ለአከባቢው ጉዳይ ሰጥተናል ብሎ በደብዳቤ አቅርቦ የለም ወይ? ይህ ለምን በአቤቱታቸው ውስጥ ተዘነጋ? የት እንደደረሰ ያልታወቀው የሰንበት ት/ቤቱ ቴፕና ቴሌቪዥን ጉዳይስ እነዚህን ሁከት ፈጣሪዎች በወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቃቸው አይደለምን?
3ኛ. ለመንግሥት ባቀረቡት አቤቱታ ሀገረ ስብከቱ ለቤተ ክርስቲያኑ የተሰጠውን ቤት በህገ ወጥ መንገድ መሸጣቸውን በማስረጃ ነው ያረጋገጠው፡፡ ቤቱን የሸጠው ግለሰብ እስጢፋኖስ ሀይሉ ሌላው ሁሉ ይቅር ያለጨረታ መሸጡ ወንጀል አይደለም ወይ? እርሱና ግብር አበሮቹ ምን ያህል እንደሸጡት እንኳ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን መናገር አልፈለጉም፡፡ ይህን ገሃድ የወጣ እውነት ለምን ዘለሉት?
4ኛ. በጣም የሚገርመው ከቤቱ ሽያጭ ላይ ለአለቃው 680 ሺ ብር ሰጥቻለሁ ማለታቸው ነው፡፡ ለምን ይህን ያህል ገንዘብ ሰጡ? እንዴት ሰጡ? በምን ሰነድ ሰጡ? ለደብሩ ነው ወይስ ሻይ እንዲጠጡበት ነው የሰጧቸው? ይህ ራሱ እስከ ዛሬው ያልወጣ ሌላው ምስጢር ሆኖአል፡፡ ሲሰጡስ በደረሰኝ ነበር? ይህን ምስጢር እስከ ዛሬ ደብቀው አሁን ሲጣሉ ለምን አወጡት? ይህን ያህል ገንዘብ ሰጥተናል ማለታቸው በራሱ ወንጀለኛ መሆናቸውን የሚያመለክት አይደለምን? እንዲህ ዓይነት ሙስና ፈጽመው አሁንም ለቤተ ክርስቲያኑ አሳቢ ነን ሲሉ ትንሽ እንኳ አለማፈራቸው ያስገርማል፡፡
5ኛ. በደብሩ ላይ የተወሰነው ውሣኔ የሥራ አስኪያጅ ውሣኔ ብቻ አይደለም የአስተዳደር ጉባኤ ውሣኔ እንጂ ታዲያ ችግሩን የሥራ አስኪያጅ ለምን ያደርጉታል? የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤም ውሳኔ ያሳለፈው የቀረቡለትን ማስረጃዎች በማጣራት ነው፡፡ ለአለቃው ሰጠን ያሉትን ብር የሰጡበትን ሰነድ ማቅረብ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተክህነት የሾመውን አለቃ አናስገባም ብሎ ማገድና ማባረር ህገ ወጥነት ነው፡፡ አለቃው የፈጸመውን ወንጀል በማስረጃ አስደግፎ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ውሳኔ ማግኘት እንጂ በሌለ ሥልጣን ማገድ ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡ ማቅ ግን እንዲህ ያለውን ሕገወጥነት ይፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም የቤተ ክህነቱን ሥልጣን በሕጋዊ መንገድ ሊያገኝ ስለማይችል እንዲህ ያለውን የሁከት መንገድ በመጠቀም ሥልጣን ለመያዝ ሙከራ እያደረገና ራሱን እየፈተሸ መሆኑን ያሳያልና፡፡  
6ኛ. የህንፃ እቃ ግዢ የሆነው በለጠ ደሳለኝ (ጉዳ) ያለ ጨረታ አይደለም ወይ እቃ ሲገዛ የኖረው? ይህ አማሳኝ ግለሰብ ለብዙ ጊዜ በጅምር የቀረውን ቤቱን የህንፃ እቃ ገዢ ሆኖ ሲመደብ በ5 ወራት ውስጥ አይደለም ወይ ባለ5 ፎቅ ሕንጻውን ሠርቶ በጥድፊያ ያጠናቀቀው? ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦዲት መደረግን ለምን ፈሩ?
7ኛ. የእህቱ ባል አቶ ይድነቃቸው መኮንን ለቤተ ክርስቲያኑ የወለል ንጣፍ የህንፃው ኮሚቴ እሱ ከሚሠራበት ዋንዛ ፈርኒቸር ያለጨረታ ሲገዛ ሀገረ ስብከቱ የምትገበዩትን ደረሰኝ አቅርቡ ነው ያለው፣ ይህን ማቅረብ ግን አልቻሉም፡፡ ይህን ሐቅ ለምን ይሸፍናሉ?
8ኛ. ያለ ጨረታ በሕገ ወጥ መንገድ የተሸጠውን የደብሩን ቤት በተመለከተ ሲጠየቁ የቤቱ ገዢ ጀርመን ነው ያለው በማለት ነው የመለሱት፡፡ ይህም ጊዜ ለመግዛትና ሙስናውን ለማዳፈን ያደረጉት ጥረት አካል በመሆኑ ራሱን የቻለ ሌላ ችግር አይደለም ወይ?
9ኛ. አቤቱታቸውን ሁሉ በማስረጃ አስደግፈው ኃላፊነትን ወስደው በአካል ቀርበው ከማስረዳት ይልቅ ከምዕመናን እና ከምእመናት ተፃፈ ብለው ወረቀት መበተን ውስጥ ለምን ገቡ? ጉዳዩን በሁከት አቅጣጫ ለማስቀየር አይደለምን? እስከ ዛሬ በተገቢው መንገድ በአካል የቀረቡት መቼ ነው?
10ኛ. አሁን ችግር ፈጣሪዎች የራሳቸውን ስህተት ሸፍነው ይባስ ደግሞ ፌዴራል ፖሊስን ተጠያቂ አደረጉ፡፡ በመሠረቱ በአዲሱ ገበያ አካባቢ በሚፈጠሩ ማንኛቸውም ሁከቶች እጁን በተደጋጋሚ የሚያስገባው ሻለቃ ጣሰው፣ ሰንበት ት/ቤት ውስጥ 4 ልጆቻቸውን አስገብተው ሁከት የሚያስነሱት አቶ ሙሉአለም ነገሮችን ሁሉ ወደ ሁከት እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ እንደ እነ አቶ ታሰበወርቅ ለህግ ሊቀርቡ ይገባል፡፡ አሁንም ቢሆን ተራ ወረቀት ከመበተን በማስረጃ አስገደግፎ የደብሩ አስተዳደር እንዳደረገው ለሀገረ ስብከቱ ውሣኔ የሚረዳ አቤቱታቸውን በማስረጃ አስደግፈው መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን ስሕተትን በሁከት ለመሸፈን መሞከር ነውና ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡
አሁን እየታየ ያለው ነገር ከህንፃ አሰሪ ኮሚቴው ለምን ኦዲት እናደርጋለን? ሰንበት ት/ቤቱም እንደ ድሮው ያለተጠያቂነት እንዝረፍ እንጂ ለምን እንወርዳለን የሚል ነው፡፡ በየትኛውም ቦታ ያልታየ 310 ካሬ በስጦታ ተሰጥቶ ራሳቸው ውል ተዋዋይ ሻጭ ገዢ የሆኑበት ጉዳይ ለምን ይፋ ወጣ? መቃብር ነጋዴዎች ፐርሰንት ክፍሉ ልንባል ነው ይህ እንዴት ይሆናል? በሚል ስለሠጉ ነገሮች ሁሉ ተደማምረው ችግሮች ተባብሰዋል፡፡
ሀገረ ስብከቱ በዋናነት በወሰነው ውሣኔ መሠረት የቤቱን ካርታ ተረክቦ ያለ ጨረታ የሸጠውን እስጢፋኖስ ሀይሉን በውሣኔው መሠረት የክስ ቻርጅ ደርሶት ክስ ሲመሠርት ነገሮች ሁሉ ወደ መስመራቸው እንደሚገቡ የሁሉም እምነት ነው፡፡ ረብሻው ሁሉ ይህን ለመሸፈን ነውና የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ችግር የአለቃው ብቻ አለመሆኑንና ነገሮች ሁሉ ከበስተጀርባቸው ሌላ ገር እንዳዘሉ የሚጠቁም ነው፡፡ አሁን ለጊዜው በሁከት ፈጣሪነት ተይዘው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙት ህገወጥ ግለሰቦች፦
·        የሰበካ ጉባኤ አባል ሳይሆን የማቅን አጀንዳ ለማስፈጸም ሊቀመንበር የሆነው ዮናስ ሽፈራው
·         ምንም ስራ የሌለውና ነገሮችን እያወሳሰበና እያጋጨ እሱ ግን እስከ ዛሬ ሳይገኝ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ዮናስ መኮንን፡፡
·        ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ክስ አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አክሊሉ እሸቱ
·        የመቃብር ነጋዴ ሽማግሌዎችን ለአድማ ሆ እንበል የሚለው የመድኃኔ አለሙ ሰንበቴ ሊቀመንበር
·         ሌሎች የሀገረ ስብከቱን ውሣኔ የመቃወሙ የወረቀቶችን የበተኑ የሰንበት ት/ቤት አባላት ይገኙበታል፡፡

4 comments:

 1. Ayi ye_Aba selama tsehafiwoch yewushet korojowoch,bitiwashu,bitiwashu ayalkibachihum? Neger gin yegibir abatachihu diabilos yesetachihun tsega endet titewutalachihu? Yefird qen simeta yane tigelagelutalachihu.

  ReplyDelete
 2. ከታሰሩት መካከል በድብድብ የሚያምነው ወረብ አስጠናለሁ እያለ የብዙ ሴቶችን ሕይወት ያበላሸው አለም ስዩም ይገኝበታል፡፡

  ReplyDelete
 3. blog yemikefetew lemastemar mehonun aminalehu endenante aynet yewered ayche alwkim yewishet fabrikawoch nachihu haymanot bemanignawim mesferet yelachihum benant afincha sew endeyashet tifeligalachihu sewu gin berasu afincha ashitito man yebetekirstyan meaza endalew man yenufake meaza endalew keleye ametat tekoteru amilak lib yistachihu

  ReplyDelete
 4. ለሰሎሞን ሲባል የተፈቱት ይታሰሩ ለአለቃው ሲባል ችግር የሚፈጥሩት ብቻ ይታሰሩ

  ReplyDelete