Thursday, February 25, 2016

በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥር የሚገኙ ሠራተኞች የማቅን እኩይ ተግባር አወገዙ“ሰይጣንን በጸሎት እናርቀዋለን ማቅን በምን እናርቀዋለን?” ከተሰብሳቢዎች አንዱ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት አለቆች ጸሐፊዎች ሂሳብ ሹሞች ቁጥጥሮችና ሰባክያነ ወንጌል በትናትናው ዕለት ባደረጉት ስብሰባ የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር አወገዙ፡፡ ይህ የሆነው ቤተክርስቲያን ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ለመወያየትና ውሳኔ ለማሳለፍ በተጠራው ስብሰባ ላይ ሲሆን የስብሰባውን ዓላማ ያብራሩት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ስለሀገርና ስለሰላም አጥብቃ የምትጸልይው ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በገዛ አማኞቿ ሰላሟ ድፍርሶባት ትገኛለች፡፡ ችግሩን ከሌላው ጊዜ ይልቅ የተወሳሰበ ያደረገው ድርጅታዊና ዘመናዊ ቅርጽን የያዘ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ቅዱስ ፓትርያርኩንም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚገዳደሩ አካላት ስለተፈጠሩ ይህን በጽኑ መቃወም ይገባናል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ሰለባ ያደረጉት ደግሞ እናንተን ነው፡፡
ሥራ አስኪያጁ አክለው እንደ ተናገሩት እነዚሁ አካላት ቅዱስ ፓትርያርኩንና ቅዱስ ሲኖዶስን የመለያይ ጽሑፍ በተከታታይ አውጥተዋል፡፡ ቤተክርስቲያን ሳታውቀው የራሳቸውን ሥርዓተ ትምህርት የቀረጹ ናቸው ካሉ በኋላ አንድ ምእመን ከፓትርያርኩ ትይዩ በዓለማዊ ጋዜጣ መልስ ሲሰጥ ትክክል ነው ትላላችሁ? ሲሉ ጉባኤውን የጠየቁ ሲሆን ምእመን ብለው የጠቀሱት በጅምላ ክህነት የክብር ቅስና ካላቸው የማቅ ሰዎች አንዱ የሆነውና የወቅቱ የማቅ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሙ ምትኩን መሆኑ በተሰብሳቢዎቹ ዘንድ ግንዛቤ ተይዟል፡፡

የሥራ አስኪያጁን የመግቢያ ንግግር ተከትሎ መድረኩ ለወይይት የተከፈተ ሲሆን የተለያዩ ሃላፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ ከተናገሩት መካከል የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ አፈወርቅ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሶስቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች ላስተላለፉት መመሪያ ቀና ብሎ መልስ መስጠት ድፍረት ነው በማለት የተናገሩ ሲሆን ተሰባሳቢውን ነጻ ሁኑ እስከ መቼ በዚህ ማኅበር ትሸማቀቃላችሁ? አንገታችን ላይ እንደ ሰንሰለት ታስረው ከብደውናል ስለዚህ ራሳችንን ነጻ ማውጣት አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መላከ ገነት አባ ተስፋ የተባሉ አለቃ ደግሞ የታክሲ ረዳቶችን በመጥቀስ ተለቅ ያለ ሰው ተሳፍሮ መልስ ሲጠይቃቸው “ለአባቶች መልስ የለም” በማለት ኅብርነት ያለው ምላሽ በቀልድ መልክ ይሰጣሉ፡፡ ማቅ ግን በድፍረት የተሞላና ለራሱ ያለው ግምት መንፈሳዊነት የጎደለው በመሆኑ ቀና ብሎ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ መልስ መስጠቱ በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አሳፋሪ ድርጊት ነው ብለዋል፡፡ በመቀጠል አንዳንድ አለቆች በደብራቸው አውደ ምሕረት ላይ ስድ አድርገው የለቀቋቸው አሉ በማለት አንዳንድ ደብሮችን በስም ሳይጠሩ በደናፈው ተናግረዋል፡፡ (በዚህ ረገድ ማቅ የሚፋንንባቸው እንደ ጎፋ ገብርኤል አዲሱ ሚካኤልና ጎላ ሚካኤል ያሉት ደብሮች ተጠቃሽ እንደሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል)፡፡ እኚህ አባት አክለው ማቅ በፈጸመው ድፍረት አሁን ቦንብ ማፈንዳት ብቻ እንደ ቀረው አረጋግጧል ብለዋል፡፡
የመካኒሳ አቦ አስተዳዳሪ መላከ ብርሃን አባ ሄኖክ በበኩላቸው ይህ ማኅበር ሳይመቹት ሲቀሩ ነፍሰ ገዳይ ዘማዊ ሌባ ብሎ የሰደበውን ጳጳስ አሁን የልማት አርበኛ ብሎ ይጠራል፡፡ በዘር በሰፈር በመንደርተኝነት ያለውን አስተሳሰብ ትተን ለፓትርያርኩ ዓላማ ድጋፍ መስጠት አለብን ብለዋል፡፡ ተሐድሶን በሚመለከት ከሳሹ፣ መስካሪው አጣሪው አውጋዡ ያው ማቅ የሆነበት አሰራር ነውና ያለው ልናስብብት ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
መምህር ሠናይ የተባሉ አለቃ ደግሞ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ማኅበራት አሉ፡፡ የእነዚህ ሁሉ ማኅበራት ዋናው አጫዋች ማቅ ነው፡፡ ስለዚህ አጫዋቹንም ተጫዋቹንም መስመር ማስያዝ አለብን፡፡ ከነካካችሁት እናድማው ከመሰብሰብ ባለፈ ፋይዳ ይኑረን ሲሉ አሁን ተቸግረው ያሉት አስቀድሞ ፊት የሠጡት አካላት ናቸው፡፡ በእርግጥ አሉ እኚህ አባት ማቅ እንደ እባብ ጭንቅላቱ መመታት ያለበት መሆኑን ጠቁመው ብልጦች እባብን መርዙን አውጥተው ይጫወቱበታል፡፡ የእኔ ሐሣብ ይመታ የሚል ሳይሆን መርዙን አውጥተን ብንጫወትበት ደስ ይለኛል ብለዋል፡፡ መልእክታቸው ማቅ ሰው ይሁን እባብነቱን ይተው የሚል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ደግሞ ይህ ማኅበር በደርግ ጊዜ ኢሰፓና ወታደር የነበረ ሲሆን ይህን ይዞ ቤተክርስቲያንን ሊቆጣጠር ነበር ነገር ግን ይህ አልሆነም፡፡ በቅርቡ የለውጥ መዋቅር ብሎ ካህናትን አስወጥቶ እሱ ሊገባ ነበር፡፡ ይህም አልሆነም፡፡ አሁን ደግሞ በኮሌጆች ላይ ዘመተ፡፡ በኮሌጆች ተሐድሶ ካለ የሚያጣራ ኮሚቴ ተሰይሞ እያለ አስቀድመው እነሱ የተሐድሶ መፈልፈያ ናቸው ብሎ መጻፉ፣ የተቋቋመው ኮሚቴ ችግር የለም እንኳን ቢል ኮሚቴውን ተሐድሶ ነው ሊል ነው፡፡ እኚህ አለቃ አክለውም ለዚህ እኩይ ማኅበር ሱቅ የምታከራዩ አለቆች አላችሁ፡፡ በገንዘብ እያበለጸጋችኋቸው ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ከእናንተ ጋር ተማምነን ልንኖር እንችላለን? (ይህም እንደ ሰአሊተ ምሕረት ያሉ ደብሮችን የሚመለከት ሲሆን ለማቅ እስከ 2 ያህል ሱቅ በማከራየት የማቅን የገንዘብ አቅም በማፈርጠሙ ሂደት ተባባሪ መሆናቸውን እንዲጠቁም በተሰብሳቢዎቹ በኩል ግንዛቤ ተወስዷል)፡፡        
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ያነሱት ማቅ በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ማቅ ለማዘጋጀትና ከፍተኛ ገቢ አጋብስበታለሁ ብሎ ያሰበውን ኤግዚቢሽን ሲሆን ማቅ ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማሰደብና አሁን የተሳሰተበትን መንገድ የበለጠ ሁከት የሚያነሳሳበትን ቦታ እያመቻቸ ስለሆነ የመግቢያው ትኬት ደግሞ በአንዳንድ አድባራት እየተሸጠ መሆኑን እየሰማን ነውና ይህ እንዲቆም እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
አንድ አባት ደግሞ የማኅበሩን ትክክለኛ ማንነት ሲገልጹ አባቶችን የከፋፈለ ዘረኝነትን በቤተክርስቲያን የጀመረ በገንዘብ ደልቦ የፖለቲካውን ሥልጣን ለመያዝ እየጣረ ያለ ማኅበር ከእሱ ሌላ ማን አለ? ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ኮሚኒስቶች ነበሩ፡፡ ከብላቴ መልስ ጥቂቶች ወደ ዝዋይ ሲመጡ አቡነ ጎርጎርዮስን አስተምሩን ብለው ገቡ፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስ በቅንነት የተማሩ ሰዎችን መንፈሳዊ ነገር ብናስተምራቸው ይጠቅሙናል ብለው ተቀበሏቸው እንጂ እንደ ዛሬው በሽታ ይሆናሉ ብለው መች አሰቡ? ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ተሰብሳቢውን ያሳቀ አንድ ቁምነገር በቀልድ መልክ አቅርበዋል፡፡ ወደአንድ ሙስሊም ቤት ማቅና ሰይጣን ሄዱ፡፡ ሙስሊሙም በሩን ከፍቶ ሰይጣንን ግባ አለው ማቅን ግን ከለከለው፡፡ ማቅ እንዴ እርሱ እኮ ሰይጣን ሲል ሙስሊሙም እርሱ በጸሎት ይወጣል አንተ ግን በምን ትወጣለህ? አለው፡፡ በመቀጠልም ሙስሊሙ እንኳን እኔ ቤት እዚያው አንተ ቤት ችግር እየፈጠርክ አይደለም እንዴ አለው ብለው ተሰብሳቢውን በከፍተኛ ሁኔታ አሳቁት፡፡
እነዚህና ሌሎችም አስተያየቶች ከተሰጡ በኋላ ሁሉም በአንድ ድምፅ ማቅ መስመር እንዲይዝ እንዲደረግ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ “ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጡ የጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር መምሪያ ኃላፊዎች ማኅበረ ቅዱሳን በሕግ እንዲመራ ጠየቁ” በሚል ርእስ ዜና አውጥቷል፡፡ 


ከዚህ በተጨማሪም ቅዱስ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን የመንፈሳዊ ኮሌጆቹን ስም በማጥፋት እንዲሁም ለቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ የቤተክርስቲያንን ህልውና የሚዳፈር ደብዳቤ በመጻፉ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መምሪያ በወሰነው መሠረት ለፈጸማቸው ተደጋጋሚ ጥፋቶች በ5 ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ ካልሆነ ግን በቀኖና ቤተክርስቲያን መሠረት የማስተካከያ ሥራ እንደሚሠራ በጥብቅ የሚያስታውቅ ደብዳቤ መጻፋቸውን የማኅበሩ ልሳን የሆነችው ሐራ ዘተዋሕዶ ብሎግ ደብዳቤውን በራሷ መንገድ አዛብታና ገልብጣ የዘገበች ሲሆን ፓትርያርኩ “ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መጣሳቸው፤ በተሾሙበት ቀን የፈጸሙትን ቃል አለመጠበቃቸው፤ በአጠቃላይ ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር መፈጸማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ በተጨባጭ ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ሊወሰንም ይችላል፡፡” ስትልም በማኅበረ ቅዱሳን መንደር የተመከረውን እንደዘበት ጽፋለች፡፡
 ደብዳቤው እነሆ

15 comments:

 1. His holiness Abune Mathias the patriarch of Ethiopian Orthodox Tewahido Church is doing a great job by keeping the unity of the church.Mehibere Kidusan is illegal and has hidden agenda and did not hearing the voice of the church.So, the church must cancel the licence which was given to this group.

  ReplyDelete
 2. ማህበረ ቅዱሳን ማንነቱን የገለጸበት ወቅት ቢኖር አሁን ነዉ
  እንዴት ይቅርታ ለመጠየቅ እሻፈርኝይላል እምነቱ የት ላይ ነዉ
  እንካን አገር ያወቀዉ ጸሐይ የሞቀዉ ጥፋት እያለ ባያጠፋስ አባቶች ይቅርታ ያልጠየቀ ማንን ሊጠይቅ ነዉ ይህማ ዓይን ያወጣ ድፍረት ነዉ።
  ለነገሩ ማቅ አባቶችን ከናቀ ቆይⶆል
  እግዚአብሔር ልብና ይስጠዉ።

  ReplyDelete
 3. ይቅርታ የሚያስጠይቅ ስራ አልሰራም ቢጠይቅ ነበር እንጅ የማዝነው አለመጠየቁ ትክክል ነው ።ሌቦችና መናፍቃን ቢጫጩ። ለጥቅማቸው ነው። የሌባ ምስክር መናፍቅ ነው እነዚህ ሳይጠፉ ማህበረ ቅዱሳን አይጠፋም

  ReplyDelete
 4. እኔ የማህበሩ አባል ወይም ተቃዋሚ አይደለሁም ግን በጣም የሚያሳስበኝ ፩ንእገር አለ
  ስለ ይቅርታ ሁልጊዜ የሚጮኽዉ ማህበር እንዴት ይቅርታ አልጠይቅም ይላል
  ይቅርታ እኮ መሽነፍ አይደለም ። ይቅርታ አልጠይቅም ማለት ግን በየትኛዉም መስፈርት ቢሆን የክርስትና ሕይዎት አይደለም ፍጹም ነዉ።
  ስለዚህ ማሕበሩ ቅዱስነታቸዉንና የሚመሩዋትን ቤተ ክርስቲያን በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ።
  እኔ የቅዱስነታቸዉ ስልጣን ቢኖረኝ ቢያንስ ላልተወሰነ ጊዜ እዘጋዉ ነበር ።

  ReplyDelete
 5. What is mk? Is that religion or organaziation?

  ReplyDelete
 6. ይቅርታ የሚያስጠይቅ ስራ አልሰራም ቢጠይቅ ነበር እንጅ የማዝነው አለመጠየቁ ትክክል ነው ።ሌቦችና መናፍቃን ቢጫጩ። ለጥቅማቸው ነው። የሌባ ምስክር መናፍቅ ነው እነዚህ ሳይጠፉ ማህበረ ቅዱሳን አይጠፋም

  ReplyDelete
 7. የሰይጣን ልጅ ይቅርታ አያውቐም።ማቅ የሰይጣን ስራ አስፈፃሚ ማህበር ።

  ReplyDelete
 8. Yepoletica sibsib ekonew meche yebetekrstiyan mahber honena Mahberkidusan Betselotna Besgdet Altemeserete degmo Tole wetaderawi masltegna lay tetemeserete Hageryekedu Feritemariwoch yemeseretut parti Ekonew Eyandanu yemak Halafi keaksyon kemiyagegnew wich Matemiyabet Fabrika yemesaselu habtoch Aluwachew keyet Amtitew new Iss eyeredaw eko new

  ReplyDelete
 9. Setan hul gize lemezgat yimegnal gin ayisakaletim enante le betekristian tekorkuari kehonachihu lemin siletekatelut abiyatekristiyanat tinfish alalachihum hodachihu amlakachihu yehone kehadi hula yenante guday hul gize defender of the true faith yehonew mahibere kidusan new. Yekidusan amlak yigesitsachihu.

  ReplyDelete
 10. ማቅ ይቅርታ አይወድም "ይቅርታ" የሚለውን ድምጽ ሲሰማ ያንገሽግሽዋል እና ማቅ ክርስትና አለው ብላችሁ ታስባላችሁ ??

  ReplyDelete
 11. ማቅ ይቅርታ አይወድም "ይቅርታ" የሚለውን ድምጽ ሲሰማ ያንገሽግሽዋል እና ማቅ ክርስትና አለው ብላችሁ ታስባላችሁ ??

  ReplyDelete
 12. Ahun min yadergal machiberber, Abatochin enkua lemin Yasasitalu? le gil tiqim sibal Mahiber matfat lemin asfelege? Ehunet kirstian kehonachu lmin Y kirstian mahiber/Mahiberekidusan tiwagalachu. Aba Mathiasin enkua hasabachewun endih yemiaskeyir min aynet hail ena siltan, difret binorachu new? Siwur tehadiso asmesay hulu ahunma tenekabachu!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. ማቅ ብሎ ክርስቲያን። ማቅ ማለት ስልጣን የጠማው ሀይማኖት የለሽ ኮሚንስት ነፍሰ ገዳይ። የሰይጣኑ የዘርአ ያቆብ አቀንቃኞ። ለአቡነ ማቲያስ እረጅም እድሜ ይስጥልን። እነኝህን ፀረ ትውልድ ፀረ ሕዝብ ፀረ ቤተክርስቲያን የምን ይቅርታ ጠይቁ ማለት ነው፡ የሕዝብና የቤተክርስቲያን ንብረት አስረክበው ይውጡልን። አባታችን ስለ ህያው ዓምላክ ብለው ይህን የዋህ ሕዝብ ገላግሉት።

  ReplyDelete