Monday, February 29, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተላለፈለትን ትእዛዝ ወደ ድርድር ቀየረውለቤተ ክርስቲያን ከእኔ በላይ የለም በሚል ትዕቢት ተወጥሮ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ጊዜ በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች ቤተክርስቲያንን ሲያውክና ሲበጠብጥ የኖረው፣ ለብዙ ምእመናን ፍልሰት ዋና ምክንያት የሆነው፣ በርካታ የቤተ ክርስቲያን መምህራንንና አገልጋዮችን ሲያሳድድና ሲያፈናቅል የኖረው ይህም አልበቃ ብሎት የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት የተሐድሶ መፈልፈያዎች ናቸው ብሎ በጅምላ በመፈረጅ ከኮሌጆቹ በቀረበበት ተቃውሞ አጣብቂኝ ውስጥ የገባውና ስለጥፋቱ በ5 ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በቁጥር 248/382/2008 በቀን 16/06/2008 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የ5 ቀናት ቀነ ገደብ የተሰጠው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ይቅርታ መጠየቅ ከብዶት ሲታሽ ከሰነበተ በኋላ ቀነ ገደቡ በሚያበቃበት ዕለት በቀን 21/06/2008 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ይቅርታ ሊጠይቅ የሚችለው ከድርድር በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ ከተሰማው መሆኑን ገለጸ፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ማንነትና ባሕርይ አንጻር እንዲህ እንደሚያደርግና ይቅርታ እንደማይጠይቅ የብዙዎች እምነት ነበር፡፡ ምክንያቱም ማኅበሩ ስለራሱ ያለው ግምት በደብዳቤው ለይምሰል የዘበዘበው “ላጠፋ እችላለሁ” የሚል ትሑት ማንነት ሳይሆን ፍጹም ነኝ አልሳሳትም የሚል ትዕቢተኛ መንፈስ ነው፡፡ በጋዜጣው ላይ መንፈሳዊ ኮሌጆቹን የመናፍቃን መፈልፈያዎች ሆነዋል ማለቱ በግልጽ እየተነበበ እያለ እርሱ ግን በደብዳቤው ላይ ጋዜጦቹ “አይሉም” ሲል ሸምጥጧል፡፡ በዚህም ራሱን ትክክለኛ በጅምላ የተዘለፉትንና ተሰድበናል ያሉትን እንዲሁም በደብዳቤ ጭምር የማስተካከያ ጽሑፍ እንዲያወጣ የጠየቁትን ኮሌጆች (ለምሳሌ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅን) ተሳስተዋል እያለ ነው፡፡ ይህም የትዕቢቱ ልክ የት እንደ ደረሰና እስካሁን የጥፋተኝነት ስሜት እንደማይሰማው  የሚያሳይ ነው፡፡ 

ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ተሐድሶ የሚያጣራ ኮሚቴ ሰይሞ በኮሚቴው የተሐድሶን ሁኔታ እንደሚያስጠና በተናገረበት ሁኔታ ማኅበሩ ግን ኮሚቴውን ለማሳሳት ወይም ደግሞ ማኅበሩ ቀድሞ ካወጣው ያልተጣራ ዘገባ በተቃራኒ ሌላ ድምዳሜ ላይ ቢደርስ ኮሚቴውን ተሐድሶ ነው ለማለት በሚመስል መልኩ ያወጣው ዘገባ ከማጣራት ሂደቱ በፊት የወጣ ዘገባ በመሆኑ ዘገባውም ሆነ የወጣበት ጊዜ የተሳሳተ ነው ለማለት እንኳን ያልደፈረው ማኅበረ ቅዱሳን “ቤተ ክርስቲያን ወደፊት በምትወስደው እርምጃ የሚጣራና የሚታወቅ ጉዳይ እንደሆነ ግልጽ ነው” በማለት እኔ ያቀረብኩት ምክረ ሐሳብ መጽደቁ አይቀርም በሚል መንፈስ ስሕተቱን ለማመን ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሌላው ቢቀር እንኳን ከሕጋዊ አሰራር አንጻር ተጠርጣሪን ጥፋተኛ ማድረግ ለማኅበረ ቅዱሳን ስሕተት ሳይሆን ትክክለኛ አካሄድ መሆኑን አረጋግጧል፡፡  
ከዚህ ቀደም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ በትዕቢትና በማንአለብኝነት ስሜት ምላሽ በመስጠት ከጥፋት ወደ ጥፋት የገሰገሰው ማኅበረ ቅዱሳን ያ ስሜቱ አሁንም እንዳልበረደ በጻፈው ደብዳቤ አስመስክሯል፡፡ ለፓትርያርኩ በድፍረት ስለመጻፉ ምንም የገባው ቅሬታ እንደሌለ ካለማሳየቱም በላይ “ደብዳቤውን እንድንጽፍ ያስገደደን ቅዱስነትዎ እንደ ቤተክርስቲያን አባትነትዎ በአካል ጠርተው ሊያነጋግሩን ሐሳባችንንም ሊያደምጡን ሲገባ፣ ይህ ዕድል ሳይሰጠን፣ በአንጻሩ ስለ ማኅበሩ ለሌሎች አካላት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሚሰጥ ደብዳቤ በቅዱስነትዎ ፊርማ በመሠራጨቱ ነው፡፡” የሚልና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማሠራጨት ረገድ ጥፋቱን የፈጸሙት እርስዎ እንጂ እኛ አይደለንም የሚል መልእክት ያዘለ ደብዳቤ ነው የጻፈው፡፡ ይህን ሲያጠናክርም ማኅበሩ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ ምላሽ የሰጠበት አኳኋን “ሥነ ምግባር አልባ” መሆኑን በደብዳቤያቸው ለገለጹት ቅዱስ ፓትርያርክ “ሥነ ምግባር አልባ” ሆኖ አልታየንም ሲል፣ እኔ ምንም ጥፋት አልፈጸምኩም በማለት አስተባብሏል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በፓትርያርኩ ደብዳቤ የታዘዘው ስለፈጸመው ጥፋት ይቅርታ እንዲጠይቅ ቢሆንም ብልጣብልጡ ማቅ ግን  “… በተጠቀሰው የቅዱስነትዎ ደብዳቤ በአምስት ቀናት ውስጥ መልስ እንድንሰጥ ባዘዙን መሠረት ከጽሑፍ ውጪ ሌላ አማራጭ ስለሌለን ምላሻችንን በታላቅ አክብሮትና ትሕትና ለመግለጽ እንወዳለን” በማለት ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ምላሽ መስጠት ነው የመረጠው፡፡ ይህም ይቅርታ መጠየቅ ለእርሱ ሞት ስለሆነ ይቅርታ መጠየቁን እንዳልወደደው ያመለክታል፡፡ ዝም ማለትም ጥፋተኛ እንደሚያደርገው ስለተገነዘበ በፓትርያርኩ ትእዛዛዊ ደብዳቤ መሠረት ይቅርታ መጠየቅ ሳይሆን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ይህም ማቅ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ አለመሆኑንና እንደ እኩያ አካል መደራደር ነው ያለብን፣ ከዚያ ጥፋቴ ተነግሮኝና ጥፋት መሆኑን ሳምንበት ነው ይቅርታ የምጠይቀው ሲል ለይቅርታ ቅድመ ሁኔታን አስቀምጧል፡፡
መቼም ለይቅርታ ቅድመ ሁኔታን ማስቀመጥ ከመንፈሳዊነት የሚመነጭ ሳይሆን ከሌላ ማንነትና አቋም የሚነሣ ነው፡፡ መንፈሳውያን ኮሌጆች በድለኸናል እያሉት ቤተክርስቲያንም አጥፍተሃልና ይቅርታ መጠየቅ አለብህ እያለችው፣ እርሱ ግን በመጀመሪያ እንደራደርና ጥፋት የተባለው ነገር ተነግሮኝ ምላሽ ከሰጠሁኝ በኋላ ጥፋት ሆኖ ከተገኘ ይቅርታ እጠይቃለሁ ያለው ማቅ ከዚህ ውጪ ይቅርታ የምጠይቅበት ሁኔታ የለም ባይ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር እንኳን በዚህም ደብዳቤ ላይ “አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት” እንጂ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ አለመሆኑን አሳይቷል፡፡ መቼም ጋዜጣውን ያነበበ ሁሉ እንደሚገነዘበው መንፈሳዊ ኮሌጆቹ ቅር የሚያሰኛቸው ነገር ባይጻፍ በባዶ ሜዳ ቅሬታ አይፈጠርባቸውም ነበር፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም ደብዳቤ አይጽፉም ነበር፡፡ ይህ ብቻ እንኳን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ስሕተት ነበር፡፡ ማንአለብኝ ባዩ ማቅ ግን እንደ ጥፋት አልቆጠረውም፡፡ ስለዚህ ድርድርን እንጂ ይቅርታ መጠየቅን አልመረጠም፡፡ ይቅርታ መጠየቅ የትልቅነት መገለጫ እንጂ የሽንፈት ምልክት አይደለም፡፡ ለማቅ ግን ሽንፈት በመሆኑ አላደርገውም ብሏል፡፡
ማቅ ለፓትርያርኩ ትእዛዛዊ ደብዳቤ ይቅርታ በመጠየቅ ፈንታ ምላሽ በመስጠቱ ያዋረደው ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ፓትርያርኩን ብቻም ሳይሆን ሌሎቹንም ጳጳሳት እንዳዋረደ መታወቅ አለበት፡፡ ምናልባት ዛሬ አባቶችን ከፋፍሎ ከጎኑ ለማሰለፍ ቢሞክርና ያዋረደው ፓትርያርኩን ብቻ እንደሆነ ተደርጎ እንዲቆጠርለት ቢጥር ውርደቱ የሁሉም ጳጳሳት ነው፡፡ ማቅ ዛሬ በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ ይህን ንቀት ማሳየቱ ለቀሩትም አባቶች ተመሳሳይ አቋም እንደሚይዝ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ ስለዚህ አባቶች ስለ ቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርስ የሚችል አደጋን ዛሬ ከመከልከል አንጻር የማቅን ድርጊት ሊያወግዙና በአንድ ልብ ሆነው ተገቢውን እርምጃ ሊወስዱ ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ነገ ውጤቱ በእነርሱም ላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

32 comments:

 1. እርር ድብንንንንንንንንንንንንንንንንንን

  ReplyDelete
 2. Endet tebilo Mahbere Kidusan yisasatal?
  Mewaqirawi ez senselet mastebeq kezih behuwal yemichal yimeslachihuwal?
  Senbet timihrt bet le atbiya betekerstiyan sebeka gubae almetazez keyet yeteqeda new?
  Lela yesefer edir zare le atbiya betekirstiyan astedader algezam bayinet keyet yemeneche new?
  Kiburan liqane papasat nege enaten yemayangawatit tiwuld lalemefeteru min wastina alachihu?
  Tilant ye atibiya kahin sineqef zim maletachin zare patriyark yisasatun yabijum betekerstiyan Bitsue We Kidus bila yeshomechiwun mawared chafu yet new?
  weyis ene kemotku serdo... endetebalew eyehone yalew
  Mahbere Kidusan atefa alatefa aydelem mewaqrun mastebeq weyim masdefer new
  Ere abatoch kechalachihu astarqu kalhone gin neg be ene newuna lijuchun hay beluwachew sedbew betekirstiyanin ayasedibu
  endegna betekirstiyan kahin kibr yatabet yetim yelem
  Egziabher yebetekirstiyanin Tinsae yasayen

  ReplyDelete
 3. አይ እናንተ ማፈሪያዎች!
  ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣችሁት ጽሑፍ ጌታቸው ዶኒ ስለ ሰይጣን እና ማቅ ቀልድ አቅርቦ ከማቅ ሰይጣን ይሻላል ብሎ ተሰብሳቢዎችን በጣም አሳቃቸው አላችሁን። አንድ እውነት ስትጽፉ ለመጀመሪያ ጊዜ አጋጠመኝ። ለጌታቸው ዶኒ ከማቅ ሰይጣን መቶ በመቶ እንደሚሻል የተረጋገጠ እውነት ነው። ምክንያቱም የለየለት መተተኛና ጠንቋይ ስለሆነ። አይ ቤተ ክርስቲያን! ስንቱ ጉድ ነው የተሰገሰገብሽ? እንደ ንቡረ እ ኤልያስና የማነ ዓይነቱ ፖለቲከኛ፣ እንደ አባ ሰረቀ ዓይነቱ መናፍቅ፣ እንደ ጌታቸው ዶኒ ዓነቱ ሃይማኖት የሌለው መተተኛ፣ እንደ ዘካርያስ ሀዲስ፣ ሀይሌ አብርሃና በርካታ እነሱን የሚመስሉ ሙሰኛና ለሆዳቸው ብቻ የሚጨነቁ ኧረ ስነቱ! መቸ ይሆን ከዚህ ሁሉ ነፃ የምትወጭው?

  ReplyDelete
 4. ወይ አባ ሰላማ!
  ንግግራችሁና ተግባራችሁ የማይስማማው ለምን ይሆን?
  እስኪ የብሎጋችሁን መመሪያ ዞር ብላችሁ ተመልከቱት።

  "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ፤ ከሳቴ ብርሃን እየተባሉ የሚጠሩት አባት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ ዕድገት ያደረሱ ባለውለታ አባታችን ናቸው። ይህች ብሎግ የእርሳቸው መታሰቢያ ትሁንልን።
  ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እየተባባሱ የመጡ አመጻዎችን፣ ክህደቶችና የስሕተት ትምህርቶችን፣ በማጋለጥ ማስጠንቀቂያዎችንና ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጀች ናት።
  እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
  ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
  ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁሉንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ራሱንም ከወንበዴዎች እንዲጠብቅ ለመርዳት ነው። እውነተኛ ላልሆኑ መረጃዎች አባ ሰላማ ኃላፊነት አትወስድም። እግዚአብሔር አይለየን!
  አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ፤ ከሳቴ ብርሃን እየተባሉ የሚጠሩት አባት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ ዕድገት ያደረሱ ባለውለታ አባታችን ናቸው። ይህች ብሎግ የእርሳቸው መታሰቢያ ትሁንልን።
  ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እየተባባሱ የመጡ አመጻዎችን፣ ክህደቶችና የስሕተት ትምህርቶችን፣ በማጋለጥ ማስጠንቀቂያዎችንና ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጀች ናት።
  እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
  ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
  ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁሉንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ራሱንም ከወንበዴዎች እንዲጠብቅ ለመርዳት ነው። እውነተኛ ላልሆኑ መረጃዎች አባ ሰላማ ኃላፊነት አትወስድም። እግዚአብሔር አይለየን!"

  ReplyDelete
  Replies
  1. ብዙ ጊዜ እንደታዘብኩት የማቅ ደጋፊዎች ወይም የማቅ አባላት አባ ሰላማ የሚያወጣቸው ሚዛናዊ መረጃዎች ትልቅ ራስ ምታት ስለሚሆንባችሁ የወጣውን ዘገባ በመተቸት ፋንታ ወደ ስድብና ወደባዶ ዘለፋ ትገባላችሁ፡፡ ይህን ርካሽ ተግባር እንደ ስልት መያዛችሁ አሳፋሪ ነው፡፡ እንዲህ ስላደረጋችሁ እውነትን ማዛባት የሚቻላችሁ አይምሰላችሁ፡፡ ለምሳሌ ይህ ዘገባ በማስረጃ ላይ የተደገፈና የማቅን ትክክለኛ ማንነት የገለጸ ነው፡፡ ከማቅ ደብዳቤ እንደምንረዳው ማቅ ወደ ድርድር እንግባ ነው ያለው፡፡ ሌላውም ከደብዳቤው እየተጠቀሰ የማቅን እኩይ አካሄድ ያጋለጠ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሀሰብ መስጠት ሲያቅት ወደ ስድብ መዞር ቅዳሴ ሲያልቅበት ቀረርቶ ሞላበት እንደሚለው ተረት ከመሆን ያለፈ አይሆንም፡፡ ስለዚህ እባካችሁ አስተያየት ስትሰጡ ተራ ስድብና ጭፍን ጥላቻ ላይ የተመሠረተ አይሁን የቀረበውን ሐሳብ በተሻለ ሐሳብ የሚያፈርስ ቢሆን ሁላችንም እንማርበታለን፡፡ ካልሆነ ግን እኔ የምረዳው አባ ሰላማ ያወጣው ዘገባ በማቅ ሰፈር ውስጥ ንዴትና ብስጭት መፈጠሩን ነው፡፡ ስድብና ዘለፋውም የዚያ ውጤት እንጂ ሌላ አይሆንም፡፡ ይህ ስልታችሁ ተነቅቶበታልና ማቆች ስልት ለውጡ፡፡ የእናንተ መንጫጫት መናደዳችሁን ይገልጻል እንጂ ከዚህ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህ እውነትን በስድብ በዘለፋ ጋጋታ የምትቀብሩ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሀል፡፡ ልቦና ይስጣችሁ፡፡

   Delete
  2. Asasach aquamachihu ayitaweqm. Yemeweyaya saihon yenufaqie merze mastelalefiya blog mehonun hulum teredtotal.Atachiberberu!

   Delete
 5. ሀሰትን የሚናገሩ አንደበቶች በእውነት ዲዳ ይሁኑ።

  ReplyDelete
 6. ሺዎች እንደተከተልነው ምነው ባወቃችሁ፡፡ እውነት እግዚአብሔር በዘመናት ራሱን ያለምስክር እንዳልተወ ቤተክርስቲያንንም ለጨለምተኞች አሳልፎ እንዳልሰጠ ማኀበረ ቅዱሳን ምስክራችን ነው፡፡ እንደው ዝናራችሁን ትጨርሱአታላችሁ፡፡ በማኀበሩ ላይ የተነሱ ቀንደኞች የደረሰባቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ረሳችሁት እንዴ የቅዱሳን ጸሎት እሳት ሆኖ ያጠፋችኋል፡፡ ከንቱ ሠራተኞች፡፡

  ReplyDelete
 7. ወይ ጥጋብ ወይ ትዕቢት ማቅ እውነትም ማቅ ነው

  ReplyDelete
 8. "መቼም ጋዜጣውን ያነበበ ሁሉ እንደሚገነዘበው መንፈሳዊ ኮሌጆቹ ቅር የሚያሰኛቸው ነገር ባይጻፍ በባዶ ሜዳ ቅሬታ አይፈጠርባቸውም ነበር፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም ደብዳቤ አይጽፉም ነበር፡፡"
  ቅዱስነታቸው ከእስራኤል ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ጋዜጣ፣ መጽሔት እና መጽሐፍ አንብቤ አላውቅም ብለዋል ይባላል፡፡ ስለዚህ ይህንንም ጋዜጣ አላነበቡም ማለት ነው፡፡ ካላነበቡ ደግሞ ጋዜጣው ምን እንዳለ አያውቁም፡፡ ማኅበሩ ስለጋዜጣው ይዘት ላስረዳዎት፣ መነሻውም እርሶ በተገኙበት የተወሰነ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ነው ማለቱ ትክክል ነው፡፡ ይቅርታ ለመጠየቅ ጥፋቱ በሚገባ ሊታወቅ ይገባል፣ ጥፋቱ የት ላይ እንደሆነ ሳይረጋገጥ በሜዳ ላይ ይቅርታ ጠይቅ ማለት በራሱ ኢ-ፍትሐዊ አካሄድ ነው፡፡
  ቅዱስነታቸው ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ከሆነ ሁሉንም አድምጠው ይሄ ትክክል ነው፣ ይሄ ስህተት ነው ማለት ሲገባቸው በስማ በለው ለዚያውም ማኅበሩ ለቤተክርስቲያን በምሰጠው እና ልሰጥ በምችለው አገልግሎት ከዚያም ከፍ ብሎ ለቤተክርስቲያኒቷ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ላይ ሥጋት እየሆኑ ነው ብሎ የሚወቅሳቸውን አካላት ብቻ ሰምተው መፍረድ አልነበረባቸውም፡፡ ሌላ ተልዕኮ የሌላቸው ከሆነ ከሳሹንም ተከሳሹንም አድምጠው ለዚህ ነገርህ ምን መረጃ አለህ ብለው ከመዛዘኑ በኋላ ለቤተክርስቲያኒቷ አገልግሎት በሚበጀው ላይ ሊመክሩ ይገባ ነበር፡፡
  አግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኒቷ ሰለም ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 9. Bereto Aba Selamaweche eyen Leba Mahber Atefolen

  ReplyDelete
  Replies
  1. Atefiwe Enedaytfa ken gebraberochu Anetna meslochehe ? Lebe YAlew Lebyeble Ahun bziheche shate mekeneyate anetna mslochehe Menendemtenagruna enedmetseru lmawkena lmrdate YEGZIABHERE ken kerbe new.

   Lebe Yesetehe,Yefweshe

   Delete
 10. enate le memare ahyemirachowen yedefenachew selewene new enij Mahbere Kidousane eko yetsafelacho Debedabe bicha sayewen timiretem chemere neber .............. Aba Selamawewche esk meche genezebe Ahmilake bicha wenacho tekeralacho ....Abone Matias Kiss yetsefalo yalemetadele weno ..bereketachewe yederebene ena Bitso Abatachew Abon Shenoda senete menefesawe hiwoten yemelewete metsafe endetsafo saesebe yegnawe abate tebey yetsafote be seletane zemenachew YEKISE DEBEDABE BICHA NEW SEGEREMO

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላማ፦ የሚገርም እና ትክክለኛ የሆነ ትንታኔ ነው። የማቅን ትህትና የሚመስል ነገር ግን የትዕቢት ደብዳቤ አይቼ አዝኜ ነበር። እዱስነታቸውና የሚመለከተው ሁሉ በቀጥታ ይህንን ማህበር ማፍረስ ይኖርበታል። መጀመሪያውንስ ለምን ማህበር ያስፈልጋር ራሷ ቤተ ክርስቲያን እያለች። ብዙዎች ማህበሩ ቢስተካከል ይላሉ ግን ተሳስተዋል። ማህበሩ ሊስተካከል ከሚችልበት ደረጃ አልፏል። አሁን ያለው ብቸኛ አማራጭ ማህበሩ ፈርሶ፣ ንብረቶቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተዛውረው፤ አባላቶቹ ደግሞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሰው ሲፈልጉ በአጥቢያቸው የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሆነው ማገልገልና መገልገል ይችላሉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እዱስነታቸውና የሚመለከተው ሁሉ በቀጥታ ይህንን ማህበር ማፍረስ ይኖርበታል።
   Lik New idus Sayihonu Edus nachew ende aba selamawech

   Delete
 12. enanite leboch mahibere kidusan bainor Orthodox tefita neber enenite kesoch menekuse debitera merigeta hodamoch bezeke setitalu enji min menifesawinet takalachihu denezoch. menafiku aba selama degimo jib bekedede usha yigebal endilu menafiku ze ale aysakalihem menafik

  ReplyDelete
 13. His holiness, Abune Mathias is doing a great job for the unity of our church, but mahibere kidusan, group of laities want to divide the church. So, every body should be aware and condemn this MK devilish deed.

  ReplyDelete
 14. ABA ASAMAWOCH WERE BECHA MENEM AYFETERM

  ReplyDelete
 15. I don't think no negotiation with Mk. Must accept order of higher authority decision and obey it. Why our Patriarch Abune Matheias negotiate with lower association. Its not appropriates of our church tradition and rule. Mk is likes any kind of lower organization must obey the law of our holy church.Mk not over church rules of laws.

  ReplyDelete
 16. አንድ ማህበር የበላይ አካል ትዕዛዝ መቀበል እጅ እንደ አንድ የበላይ አካል ዉይይት እንጅ ይቅርታ አልጠይቅም በማለት ለፓትርያርኩ ምልስ መጻፍ ምን ያህል ቤተ ከርስትያናችን እንደ ናቅ የምያሳይ ግለጽ ነገር ነው። ለመሆኑ ማህበረ ቅዱስ ለአጠፋው ጥፋት ከስርዓት ቤተ ከርስትያን ውጭ በማን አለብኝነት ትምክት በተሞላ መንገድ የሰራውን ጥፋት አለመቀበልና ውይይት ማደረግ አለብኝ ማለቱ በራሱ አሳፋር ነው።ምን ያህል አማጸኛ ማህበረ እንደሆነ እራሱን በራሱ በለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ህዝብ እያጋለጠ ነው። እራሱን በራሱ አንገቱን ለገመድ እየሰጠ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ስራው ድንቅ ነው። ለሁሉም ነገር ግዜ ሰዓት ወቅት አለው። ተዋግው እግዚአብሔር የእውነት አምላክ እንጅ ገንዘብ አይደለም።ፓትርያርኩም ሆኑ ቅዱስ ስኖዶስ አባለት ከአንድ ማህበር ጋር ድርድር ማድረግ አግባብነት የለውም። መመሪያ ሰጭ አካል ወይንም የአንድ ሀይማኖት ራስ የሆኑት አባቶች የሰምያስተላልፋት ትዕዛዛትና መመሪያዎች ተፈጻም መሆን አለበት። አንድ የመኪና ሾፈር መኪናው እየነዳ ቀይ መብራት ላይ ሳይቆም ብያልፍ ህግን ስለ ተላላፈ ይቀጣል እራሱን ለወደፊቱ አሻሽሎ በስርዓት መኪናው ካልነዳ መንጃ ፈቃዱ ይሰድበታል። ይህ አለማዊ ህግ ተፋጻምነት ካገኘ ታዲያ የቤተ ከርስቲያንቱን ሥርዓት ህግ ላፈረሰው ድርጅት እንዴት ቅጣት አይገባውም?

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጮህ ለውጥ ቢያመጣ ኖሮ ብዙ የሓሰት ጩህቶች እውነት ሆነው ባየናቸው ነበር ነገር ግን እንዳንተ ያለ ለእውነት ሳይሆን ለሓሰት ህሊናውን ለውጭ በገንዘብ የሸጠ ሰው በሚኖርባት አለም እውነት ብትዘገይም አትቀርም እሰከዚያው ግን ሁላችንም በያለንበት ብንቆም የተሸለ ነው መች የያዘ አባዜ አሳርፎ ያስቀምጥሀል ማለፊያህን አተፍጥን ለመኖር መሞት እንጂ ለመሞት መኖር አይጠቅምም አየህ የሚጠቅመው ይህው ነው የሚያስተውል ልቦና ይስጥህ

   Delete
 17. የመሬትና የገቢ ማስገኛ ተቋማት ኪራይ ውሳኔው አልተተገበረም፤ የጥናቱም ሒደት ታጉሏል
  የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የማያስከብሩ ውሎች በወጥነት መስተካከል ነበረባቸው
  በጥናቱ የታዩ ጥፋቶች እንዲቀጥሉና አድባራቱ ተገቢ ጥቅማቸውን እንዲያጡ አድርጓቸዋል
  በፍጻሜው፥ ቤተ ክርስቲያን የመሬትና የሕንፃ ኪራይ ፖሊሲ እንዲኖራት አስተዋፅኦ ነበረው
  * * *

  የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ውሳኔውን ወደ አጥቢያዎቹ ባለማስተላለፉ ለውጤታማነቱ ተግዳሮት ኾኗል፡፡ ይህም ለቀጣዩ ጥናት ዕንቅፋት በመኾኑ ሒደቱ እንዲስተጓጎል አድርጎታል፡፡
  የሕግ አውጭና የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ የኾነውን የበላይ አካል ውሳኔ አለማክበርና አለማስከበር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ያለን ንቀት ከሚያመለክት በቀር ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም፡፡
  ብዙ የተደከመበት እና የውጤት ጭላንጭል የታየበት ጥናት በከንቱ እንዳይቀር፣ የሚመለከተው አካል በትኩረት ሊከታተለው ይገባል፡፡
  ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የመሪነት ሚናውን በማስከበር ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል ብሎ የወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ እንዲኾን ሓላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል፡፡
  /የአጥኚ ኮሚቴው ጸሐፊ ለዜና ቤተ ክርስቲያን ከጻፉት/

  * * *

  Yemane with parish heads

  ዜና ቤተ ክርስቲያን በዚኽ ወር እትሙ በርእሰ አንቀጽ ደረጃ እንደነገረን፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፥ ሙስናን አዳክመናል፤ መልካም አስተዳደርን አስፍነናል በሚል ራስን በራስ ለማስመስገን የሚካሔደው መሸላለም ድራማዊና የሚያስተዛዝብ ነው፡፡ በሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና የምዝበራ ሰንሰለቱ እየተደረሰና እየተዘጋጀ በአማሳኞቹ የሚተወነው ድራማ በዚኹ ሳያበቃ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስም በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ ቀጥሎ ውሏል፡፡

  ቀንደኞቹ አማሳኞች(ሃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ፣ ነአኵቶ ለአብ አያሌው፣ ተስፋ ፍሥሓ)፤ የተሐድሶ ኑፋቄን በኅቡእ ከሚያቀነቅኑ ስመ ሰባክያንና እንደ አፈ ወርቅ ካሉ የክፍለ ከተማ ምግባረ ብልሹ ሓላፊዎች ጋር በመሪነት በተወኑበት ድራማ፥ ነውረኛ ሙስናቸውን ጽድቅ አስመስለው ሲያቀርቡ፤ ለዕቅበተ እምነት፣ ለሙስና መወገድ፣ ለመልካም አስተዳደርና ለፍትሕ መስፈን በየአጥቢያው የሚጋደሉ የምእመናን ማኅበራትን ግን በሁከት ፈጣሪነት፣ በፖሊቲከኛነትና በጥቅመኛነት ሥለዋል፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ተመልሰው ባደሩ ጥያቄዎች ጭምር የተወነጀለ ሲኾን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አጸድቆና ፈቃድ አግኝቶ በቀጣዩ ወር አጋማሽ ላይ ለማሳየት እያዘጋጀው የሚገኘው ዐውደ ርእይም፣ “ቅዱስ ሲኖዶስና ቅዱስ ፓትርያርኩ አያውቁትም” በሚል እንዲታገድ ተጠይቋል፡፡

  ድራማውን በአንክሮ ሲከታተሉ የነበሩ ታዳሚዎች እንደተናገሩት፥ “ሲኖዶሳዊት ፓትርያርካዊት ቤተ ክርስቲያንን መፈታተን”፤ “የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን መቀናቀን”፤ “ከቅዱስ ሲኖዶስና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር መገዳደር”፤ “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ አሠራርና መዋቅራዊ ሉዓላዊነት መፈታተን” የሚሉ ሐረጋተ ተውኔት ከድራማቲስቱ ሥራ አስኪያጅ በተደጋጋሚ መደመጣቸው መድረኩን ይበልጥ አስደናቂ (dramatic irony) አድርጎታል፡፡ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነትም በደብር ዋና ጸሐፊነትም አጃምሎ በያዘው ኢ-ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ሥልጣን፣ የተጠያቂነትን መርሕ በመፃረር ቆዳውን ለማዳንና የበለጠ ለመጠቀም እየሠራ ባለበት ተጨባጭ ኹኔታ፤ ለመዋቅራዊ ሉዓላዊነት ጠበቃ መስሎ ሲኖዶሳዊነትንና ፓትርያርካዊነትን ሲደሰኩር መዋሉ(እያምታታም ቢኾን)፤ ድራማዊውን መድረክ በርግጥም በእጅጉ ምፀታዊ ያደርገዋል፡፡

  በድራማዊ ስብሰባው ማግሥት ለንባብ የበቃው ዜና ቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ እትሙ፣ ይኸው የየማነ ዲስኩር ከንግግር ያለፈ አንዳችም ፋይዳ የሌለው መኾኑን በማሳያ አስነብቦናል፡፡ ጋዜጣው ከርእሰ አንቀጹ ባሻገር፣ “ንገሩን እንንገራችኹ” በተሰኘው ዓምዱ፣ “የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ስለምን ውኃ በላው?” በሚል ርእስ እንዳስነበበን፣ ቤተ ክርስቲያን የራሱዋ የገቢ ማስገኛ ተቋማትና የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ እንዲኖራት ታስቦ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በናሙናነት የቀረበው ጥናት፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አስተዳደር ጉባኤ ተቀባይነት አግኝቶ ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ በሸፈናቸው 48 የሀገረ ስብከቱ አድባራትና ገዳማት እንዲተገበር መመሪያ ከተላለፈ ወራትን ቢያስቆጥርም፣ አፈጻጸሙ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ቢሮ ታፍኗል፤ ጥናቱ፣ ባልሸፈናቸው አጥቢያዎችም እንዲቀጥል በቋሚ ሲኖዶሱ ቢወሰንም ሒደቱ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አልታዘዝ ባይነት ተስተጓጉሏል፡፡

  በዚኽም ሳቢያ ሀገረ ስብከቱ፣ የአጥቢያ አማሳኞች ከጥቅመኛ አካላት ጋር ተቆራኝተው የአድባራቱን መብትና ጥቅም በማሳጣት በገቢ ማስገኛ ተቋማቱ ላይ የሚፈጽሟቸው ምዝበራዎች ሳይታረሙ እንዲቀጥሉ ከማድረጉም በላይ በተገቢ የኪራይ ውሎች ቤተ ክርስቲያን ልታገኝ ይገባት የነበረውን ጥቅም እንዳታገኝም አድርጓል፡፡ “የሕግ አውጭና የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ የኾነውን የበላይ አካል ውሳኔ አለማክበርና አለማስከበር ለቤተ ክርስቲያን ያለን ንቀት ከሚያመለክት በቀር ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም፤” ያለው ጽሑፉ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፣ በአልታዘዝ ባይነት የተስተጓጎለውን ውሳኔውን በማስፈጸምና የጥናቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ ችግሩን ከመሠረቱ የሚፈታ ርምጃ እንዲወስድና የመሪነት ሚናውን እንዲያስከብር በአጽንዖት ጠይቋል፡፡

  Haile and Yemaneየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አፈጻጸሙን ያፈነበትና ሒደቱን ያስተጓጎለበት ምክንያቱ ግልጽ ነው፤ በዋና ጸሐፊነት በሚሠራበት ደብር፣ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ልዩነት በታየበት የሕንፃ ዲዛይን ክለሳ ሰበብ ቃለ ዐዋዲውን በመተላለፍ ከፍተኛ ምዝበራ መፈጸሙን ጥናታዊ ሪፖርቱ አረጋግጧል፤ በዚኽ ረገድ የሚጠብቀውን የተጠያቂነት ዳና አጥፍቶ ሕገ ወጥ አካሔዱን ሕጋዊ ለማስመሰል፣ የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑን ተጠቅሞ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ለማጸደቅ ያደረገው ሙከራ ታዲያ ከሽፎበታል፤ መሰል ግንባታዎችንም በቋሚ ሲኖዶሱ ከተላለፈው ውሳኔና በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከተሰጠው መመሪያ ውጭ በደብሩ እያስፈጸመ ይገኛል፡፡

  ReplyDelete
 18. ቀንደኞቹ አማሳኞች(ሃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ፣ ነአኵቶ ለአብ አያሌው፣ ተስፋ ፍሥሓ)፤ የተሐድሶ ኑፋቄን በኅቡእ ከሚያቀነቅኑ ስመ ሰባክያንና እንደ አፈ ወርቅ ካሉ የክፍለ ከተማ ምግባረ ብልሹ ሓላፊዎች ጋር በመሪነት በተወኑበት ድራማ፥ ነውረኛ ሙስናቸውን ጽድቅ አስመስለው ሲያቀርቡ፤ ለዕቅበተ እምነት፣ ለሙስና መወገድ፣ ለመልካም አስተዳደርና ለፍትሕ መስፈን በየአጥቢያው የሚጋደሉ የምእመናን ማኅበራትን ግን በሁከት ፈጣሪነት፣ በፖሊቲከኛነትና በጥቅመኛነት ሥለዋል፤ ማኅበረ ቅዱሳንም ተመልሰው ባደሩ ጥያቄዎች ጭምር የተወነጀለ ሲኾን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አጸድቆና ፈቃድ አግኝቶ በቀጣዩ ወር አጋማሽ ላይ ለማሳየት እያዘጋጀው የሚገኘው ዐውደ ርእይም፣ “ቅዱስ ሲኖዶስና ቅዱስ ፓትርያርኩ አያውቁትም” በሚል እንዲታገድ ተጠይቋል፡፡

  ድራማውን በአንክሮ ሲከታተሉ የነበሩ ታዳሚዎች እንደተናገሩት፥ “ሲኖዶሳዊት ፓትርያርካዊት ቤተ ክርስቲያንን መፈታተን”፤ “የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን መቀናቀን”፤ “ከቅዱስ ሲኖዶስና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር መገዳደር”፤ “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ አሠራርና መዋቅራዊ ሉዓላዊነት መፈታተን” የሚሉ ሐረጋተ ተውኔት ከድራማቲስቱ ሥራ አስኪያጅ በተደጋጋሚ መደመጣቸው መድረኩን ይበልጥ አስደናቂ (dramatic irony) አድርጎታል፡፡ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነትም በደብር ዋና ጸሐፊነትም አጃምሎ በያዘው ኢ-ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ሥልጣን፣ የተጠያቂነትን መርሕ በመፃረር ቆዳውን ለማዳንና የበለጠ ለመጠቀም እየሠራ ባለበት ተጨባጭ ኹኔታ፤ ለመዋቅራዊ ሉዓላዊነት ጠበቃ መስሎ ሲኖዶሳዊነትንና ፓትርያርካዊነትን ሲደሰኩር መዋሉ(እያምታታም ቢኾን)፤ ድራማዊውን መድረክ በርግጥም በእጅጉ ምፀታዊ ያደርገዋል፡፡

  በድራማዊ ስብሰባው ማግሥት ለንባብ የበቃው ዜና ቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ እትሙ፣ ይኸው የየማነ ዲስኩር ከንግግር ያለፈ አንዳችም ፋይዳ የሌለው መኾኑን በማሳያ አስነብቦናል፡፡ ጋዜጣው ከርእሰ አንቀጹ ባሻገር፣ “ንገሩን እንንገራችኹ” በተሰኘው ዓምዱ፣ “የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ስለምን ውኃ በላው?” በሚል ርእስ እንዳስነበበን፣ ቤተ ክርስቲያን የራሱዋ የገቢ ማስገኛ ተቋማትና የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ እንዲኖራት ታስቦ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በናሙናነት የቀረበው ጥናት፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አስተዳደር ጉባኤ ተቀባይነት አግኝቶ ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ በሸፈናቸው 48 የሀገረ ስብከቱ አድባራትና ገዳማት እንዲተገበር መመሪያ ከተላለፈ ወራትን ቢያስቆጥርም፣ አፈጻጸሙ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ቢሮ ታፍኗል፤ ጥናቱ፣ ባልሸፈናቸው አጥቢያዎችም እንዲቀጥል በቋሚ ሲኖዶሱ ቢወሰንም ሒደቱ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አልታዘዝ ባይነት ተስተጓጉሏል፡፡

  በዚኽም ሳቢያ ሀገረ ስብከቱ፣ የአጥቢያ አማሳኞች ከጥቅመኛ አካላት ጋር ተቆራኝተው የአድባራቱን መብትና ጥቅም በማሳጣት በገቢ ማስገኛ ተቋማቱ ላይ የሚፈጽሟቸው ምዝበራዎች ሳይታረሙ እንዲቀጥሉ ከማድረጉም በላይ በተገቢ የኪራይ ውሎች ቤተ ክርስቲያን ልታገኝ ይገባት የነበረውን ጥቅም እንዳታገኝም አድርጓል፡፡ “የሕግ አውጭና የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ የኾነውን የበላይ አካል ውሳኔ አለማክበርና አለማስከበር ለቤተ ክርስቲያን ያለን ንቀት ከሚያመለክት በቀር ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም፤” ያለው ጽሑፉ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፣ በአልታዘዝ ባይነት የተስተጓጎለውን ውሳኔውን በማስፈጸምና የጥናቱን ቀጣይነት በማረጋገጥ ችግሩን ከመሠረቱ የሚፈታ ርምጃ እንዲወስድና የመሪነት ሚናውን እንዲያስከብር በአጽንዖት ጠይቋል፡፡

  ReplyDelete
 19. eyenewola godachewen le Ezebe Kiresetano yemegaletewe Mahber Kidousan selewen endefelegacho lemewen yegede Ende Amilakache Eyesos Kiresetose Mahber Kidousane Mesekele felegacho

  ReplyDelete
 20. Oh mother orthodox tewahdo, now you are completely dominated by the so called MK. I wish I weren't one of the people who attended their first Gubae at bête kihinet adarash. Now they are completely out of control. Their moto is "either with us or against us". I think it is time to return sovereignty to the church. I am looking forward to see a church who is guided only by the holy sprit. One church for all. Our fathers, please take this opportunity to bring respect to mother church back again. MK never existed and it will not exist, but the church. It is time to choose between a bunch of mean, arrogant, unbelievers, disrespectful the so called doctors and engineers. The church was originally built by fisher men, tax collectors uneducated men of God. I know MK will try to destroy the church if anyone try to dismantle it but the church will be fine since its foundation is from heaven. I cannot wait to say MK R.I.P.
  "Long live Tewahdo"

  ReplyDelete
  Replies
  1. we know all Orthodox who you are and for whom stands don't waste your time go hell evil messenger. our fathers will give solution for all.

   Delete
 21. You will be a crease man because you didn't know the gift of God MK is given by God to help followers of this religion. Do you think MK is an obstacle for tewahido please think so many times if you are not biased to the wrong thinker.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you for your best wish. I would like to let you know that I am baptized and got my citizenship when i was 40 days old. I call my heavenly father my dad. He is a loving father and does not want me to go to hell. He died for me to express his love. So i rely on his love and forgiveness even though i am a sinner. Regrading MK, It was established in 1980s and if i am not mistaken the church survived 1000 years plus 980 years. The bible says false prophets will come later, i am afraid MK is making the situation perfect. I didn't expect to bless me as the bible commands true Christians to bless their enemies. Since the tree is known by its fruit, as MK member you have shown that cursing is what you know best. As true orthodox christian, i would like to say to you that i still don't care about MK but the church. God bless you dear MK supporter.

   Delete
  2. you just proved my point
   look at what you wrote
   "you didn't know the gift of God MK is given by God to help followers of this religion" where is the church in this statement. If you think MK is the church well it is up to you. I don't deny that MK is very good in organizing stuff and coordinating ppl. What I am saying let it be as one of the good will organizations like NGOS and stop interfearing in the church theological activity. Even though MK does not recognize our current fathers' theological capability at least MK should know that God appointed them and he can help them do great things.

   Delete
 22. what are going now people to support Aba Matias only going out of Kidous Senodous stop zis one just discs backing

  ReplyDelete