Friday, February 5, 2016

ለባለቤት አልባው ደብር ለደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውሳኔ ተሰጠ


  Read in PDF
ከይነጋል በጊዜው
ለበርካታ ወራት በአመጸኞች የተነሳ ያለ አለቃ ሲጓዝና በዓላትን ሲያከብር የነበረው ባለቤት አልባው ደብር በአ.አ. ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ አገኘ፡፡
በከሳሽም በተከሳሽም ወገን ለሀገረ ስብከቱ በቀረበለት ሰነድ መሰረት የደብሩ አለቃ አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል ጥፋተኛ የሚያደርጋቸው ነጥብ እንዳልተገኘ ጉባኤው ወስኗል፡፡ በውሳኔውም መሰረት አለቃው ስራቸውን በደብሩ ተገኝተው እንዲቀጥሉ መመሪያ ተላልፏል፡፡
በውሳኔው መሰረት ያለጨረታ በህገ ወጥ መንገድ በውርስ የተገኘውን ባለ ሁለት ፎቅ ቤት እራሳቸው ሻጭ እራሳቸው ገዢ እራሳቸው ውል ተዋዋይ ሆነው ለሀገረ ስብከቱም ሆነ ለደብሩ ምዕመናንና ካህናት ሳያሳውቁ  በሚያሳዝን ሆኔታ የፈጸሙት ሽያጭ ህገ ወጥ መሆኑ ተሰምሮበት ሽያጩን ያገደ ውሳኔ ተወስኗል፡፡ ይህን ያደረጉ ሰዎች ከኛ በላይ ለደብሩ ለአሳር የሚሉ መሆናቸው ለምናውቅ ወገኖች ደግሞ የፈጸሙት ግፍ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ በመሆኑም የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ ሥራ ም/ሰብሳቢ እስጢፋኖስ በህግ እንዲጠየቅ ሀገረ ስብከቱ ወስኗል፡፡
ይህ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ዋና አቀነባባሪው ደግሞ  ከግሮሰሪ ተጠርቶ የሰበካ ጉባኤ አባል ሳይሆን የሰበካ ጉባኤ ሊቀመንበር የነበረው ዮናስ ሽፈራው (በቅጽል ሽሙ ጃምቦ) ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ምክትል የሰበካጉባኤ ሊቀመንበር የሆነበት ሰበካ ጉባኤ ሃላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣ አዲስ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ አቶ ዮናስ ልብ ቢኖረው ኖሮ የቤተክርስቲያኒቱን መብት አስጠብቆ የካህናትን ህይወት ማሻሻል ይገባው ነበር፡፡ እሱ ያገኘውን እድል ቤተክርቲያንን ለማጥፋትና ራሱን ለመጥቀም ተጠቅሞበታል፡፡ በድርጊቱ ተጠያቂነት እንዳይደርስበት ደግሞ ለወንጀለኞች ጠበቃ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ሥር ተከልሎ ሲያደዘድዝ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ 

በቅዱስ ፓትርያርኩ ተሾመው የነበሩትን አለቃ በህገ ወጥ መንገድ በማባረር ራሳቸውን የሰንበቴ ማህበራት ህብረት ብለው የሰየሙ የመቃብር ነጋዴዎች አባረናል ብለው መወሰናቸው ለሌላው ደብር በጎ አርአያ ካለመሆኑ የተነሳ ፉካ ነጋዴዎቹ የተለያየ ወንጀሎችን ሰርተው በሰንበቴ ቤት በመደበቃቸው ሀገረ ስብከቱ እነዚህን አካላት በህግ እንዲጠየቁ ወስናል፡፡
በተራዘመ የህንጻ አሰራር ጉዞ በርካታ የኮሚቴው አባላት የበለጸጉበትን ህንጻ ላለፉት 13 ዓመታት ኦዲት ተደርጎ ስለማያውቅ ኦዲት እንዲደረግ ተወስናል፡፡ በውሳኔው መሰረት ኦዲት ከተደረገ የሚወጣው ጉድ አንዳንዶችን ከሀገር ሊያስለቅቃቸው እንደሚችል የታመነ ነው፡፡
በሰንበት ት/ቤቱ የሸመገሉ በሰንበት ት/ቤት ስም ዝርፊያ የሚያከናውኑ ለጥቅር አንበሳ ሆስፒታል እንረዳለን በማለት ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለራሳቸው የበሉ፣ ለዚህም ማረጋገጫነት ሆስፒታሉ ሳንቲም እንዳልደረው የመሰከረባቸው የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ከርስተ ጉልታቸው እንዲነቀሉ ወስኗል፡፡ ሥራ ፈቶቹ አዛውንት የሰንበት ት/ቤት አመራሮች የገንዘብ ጥማታቸውን ለማርካት የሰንበት ት/ቤቱን ቴፕና ቲቪ ጭምር መሸጣቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
 አለቃው በስራቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ማቅ በየጓደው ያደራጃቸውና በሌላቸው ስልጣን አለቃ እስከማባረረር ድረስ የሚደፍሩ ነውረኛ የሰንበቴ ፉካ ነጋዴዎች ተከታታይ አድማ ቤተክርስቲያንን እንደሚጠብቃት ይታመናል፡፡ የእነዚህ ለዲያስፓራ አስከሬን 40ሺ ለሎካል አስከሬን ደግሞ 20ሺብር የፉካ መቃብር ተመን አውጥተው በአስከሬን ላይ አድልዎ እየፈጸሙ እየበዘበዙ ያሉ አድመኞች ሥራቸውን ተከታትሎ ሥርዓት ማስያዝ በቀጣይነትም ከሀገረ ስብከቱ የሚጠበቅ ነገር መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
እነዚህን እበላ ባዮች የቀሰቀሱ ያደራጁና ያሳመጹ ወሮበሎች፣ በነጻ አገልግሎት ላይ ያሉ ሥራ ፈት ዲያቆናትና እነዚህን ሰዎች ደግሞ እያበሉ እያጠጡ የሚልኩት በታቦት ላይ እያሟረቱ የሚጠነቁሉትና የሚያስጠነቁሉት የፒያሳ ነጋዴዎች ጥረት አለመሳካቱ ለቤተክርሰቲያን ትልቅ ድል ነው፡፡ ቤተክርቲያንም በአድመኞች ልትመራ እንደማትችል የሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ያመለክታል፡፡


የውሳኔውን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡7 comments:

 1. Luterawiyan yimeleketachewal ende??!!!?

  ReplyDelete
 2. የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም በመርቆርዮሥ ታቦት ላይ የጥንቆላና የአስማት ሥራ በመሥራት የሚታወቀው እሥጢፋኖስ ኀይሉ በሀገረ ሥብከቱ በህግ እንዲጠየቅ መወሰኑ እጅግ በጣም የሚያስደሥት ነው ምክንያቱም ሀብታም ሆኖ እያለ ለደብሩ በራሱ ገንዘብ መርዳት ሢችል ካርታ ተቀብሎ እራሱ ተዋውሎ እራሡ ሸጦ ገቢውን ለቤተ ክርሥትያን አለማሳወቁ በጣም የሚያሳዝን ነው ስለዚህም በሕግ እንዲጠየቅ መወሰኑ ትክክለኛ ውሳኔ ነው በዚህ አጋጣሚም ምንም ሀብታም ቢሆኑ ከህግ እንደማያመልጡ ሀገረ ሥብከቱ አሳውቋል

  ReplyDelete
 3. ለካ እስከ አሁን የምትፅፉት ሁሉ ውሽት ነበር በስመ አብ አለቃው እውነተኛ ነበሩ ስትሉ ትንሽ አታፍሩም እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አታነብም እንዴ የተጻፈውን?አለቃው እውነተኛ ናቸው አልተባለም። የተባለው በአመጽ መነሳታቸው ስህተት ነው ነው።

   Delete
  2. አታነብም እንዴ የተጻፈውን?አለቃው እውነተኛ ናቸው አልተባለም። የተባለው በአመጽ መነሳታቸው ስህተት ነው ነው።

   Delete
 4. ለምን ታድያ በነካካ እጃችሁ የቁልቢን ዘራፉዎች እና ስለ አለቃው ሚስት ከሜዳ ተነሰታ ገንዘብ ላይ ስለተነከረችው እና ስላሉት የደብሩ የሙዳይ ምጽዋት ገልባጮች ጉድ ዘክዝከካችሁ ቦታው ቢቀደስ? ????

  ReplyDelete
 5. religious writer don't you know lie by hand writing
  is a sin

  ReplyDelete