Friday, February 12, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ እንዲጠይቅ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ ወሰነ


ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ቆሜያለሁ እያለ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳውያን ተቋማትን በጅምላ የዘለፈውን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ የካቲት 3/2008 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ማኅበሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ ካልሆነም በሕግ እንዲጠየቅ ወሰነ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎችና ምክትል መምሪያ ኃላፊዎች ይህን የወሰኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ በጠሩት ስብሰባ ላይ ማኅበሩ እየፈጠረ ባለው ወቅታዊ ችግር ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በጋራ በወሰኑት ውሳኔ ነው፡፡
በዚህ አቋም በተወሰደበት ወሳኝ ስብሰባ ላይ ብዙዎቹ የመምሪያ ኃላፊዎች ባልተጠበቀ መልኩ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ይህም የማኅበሩ ጥፋት የት ላይ እንደደረሰ ትልቅ ማሳያ ሆኗል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ አዕላፍ ያዝአለም ገሠሠ በታላቅ ቁጭት “ላለፉት 2ዐ ዓመታት ይህ ማህበር ቤተ ክርስቲያንን እያስጨነቃትና እያሸማቀቃት ነው፡፡ እንዴት መፍትሔ የሚሰጥ ጠፋ? ይህች ቤተ ክርስቲያን ደርግን የሚያህል አምባገንን መንግሥት ተጽዕኖ ተቋቁማ ነው እዚህ የደረሠችው፡፡ አሁን ይህ ማህበር እየሠራበት ያለው ግፍ ከደርግ በላይ ነው” ብለዋል፡፡ “ሃይማኖት የለሾችን የተጋፈጠች ቤተ ክርስቲያን አሁን በእነሱ ተቸግራለች” ሲሉ ማቅ እየፈጠረ ባለው ችግር ቤተክርስቲያን መታወኳን አብራርተዋል፡፡

እስክንድር ገ/ክርስቶስ ደግሞ “ከአንጾኪያ፣ ከእስከንድርያ ት/ቤቶች መናፍቃን ወጥተዋል፡፡ በየትኛውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግለሰቡ እንጂ ሁለቱ ት/ቤቶች አልተሰደቡም፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን የውንብድና ተግባር ነው በት/ቤቶቹ ላይ የፈፀመው” በማለት ማቅ ከመስመር የወጣበትን ስሕተት መሰረታዊ ችግር ተናግሯል፡
ሌላው የመምሪያ ኃላፊ ደግሞ “ከዚህ በፊት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በተደረገው ውይይት ወደ ህግ ግባ ብለው ወስነውበት እሱም ተለማምጦ፣ መሬት ልሶ አፈር ልሶ አሁን እንደ እባብ ማንሠራራቱን” በመግለጽ የማኅበሩን እባብነት አስረድተዋል፡፡
ሌላው የመምሪያ ሃላፊም “የአሁኑ የማቅ አካሄድ ከእስከ ዛሬው ለየት የሚያደርገው፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችን ካህናት ማሠልጠኛዎቹን ገዳማትን፣ የአብነት ት/ቤቶችን ሁሉንም መናፍቅ ማለቱ ነው፡፡ በዚህም ሃይማኖት ያለው እኔ ህንጻ ላይ ብቻ ነው እያለን ነው” ሲሉ የማቅን ትዕቢትና ትምክሕት ገልጸዋል፡፡
ሌላው የመምሪያ ኃላፊ “እኔ በዚህ ት/ቤት 20 ሺሕ ብር ከፍዬ ነው ማስተርስን የተማርኩት፡፡ የመመረቂያ ጽሑፌንም የሠራሁት በስጋወደሙ ላይ ነው፡፡ ባለቤቴ ታዲያ በስምዐ ጽድቅ ላይ የወጣውን ዘገባ አይታ እንዴ መናፍቅ ት/ቤት ነው እንዴ የተማርከው? አለችኝ” ሲሉ ፓትርያርኩ በእጅጉ ሰቀዋል፡፡ ሌላው የመምሪያ ኃላፊ ደግሞ “መናፍቃንን መከላከል አልቻልንም፤ ለምን ቢባል ሁሉም መናፍቅ ተብለዋልና” ብለው ተናግረዋል፡፡
አስተዳደር ጉባኤው ከሲኖዶስ ቀጥሎ የቤተ ክህነቱ ወሳኝ አካል መሆኑ ሲታወቅ ጉዳዩን የመመልከትና የመወሰን ሥልጣን አለው፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ በዚህ ጉባኤ ላይ ጉዳይ መታየቱ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ያልተናገሩ የመምሪያ ኃላፊዎች ሲኖሩ በተለይ ፋንታሁን ሙጨ ይጠቀሳል፡፡
ሌላው የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ኃላፊው ፋንታሁን ሙጨ በዝምታ ከማቅ ጎን መቆሙን አሳይቷል፡፡ እርሱ መስጊድ የሌለው ሙስሊም እንደሆነ ሁሉም የተገነዘበበት ጉባኤ ነበር፡፡ ከሀገረ ስብከት ጀምሮ የሠራተኛን አበል በመብላት የሚታወቀው ፋንታሁን በዚህ ሣምንት ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ የመምሪያ ሥራ አስኪያጆች የሕዝብ ቆጠራን በተመለከተ በተሰጠው ሥልጠና ላይ 3ቱንም አሠልጣኞች የመለመለው ከማቅ ሰዎች ነው፡፡ ይህን ያደረገው ፋንታሁን በማቅ ላይ ሁሉም የታዘበውን ሲገልጽ እርሱ ግን ዝምታን በመምረጥ ወግኖ ታይቶአል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ በስብሰባው ላይ እንደተናገሩት ሥራ አስኪያጁ የሦስት አመት ጊዜ ነው ያላቸው፡፡ እኔ ግን የጊዜ ገደብ የለብኝ፡፡ ስለዚህ የተበላሸ ነገር ሳይ ጣልቃ የመግባትና የማስተካከል መብት አለኝ በማለት የአስተዳደር ጉባኤውን ሥልጣንና የስብሰባውን ሕጋዊነት ግጸዋል፡፡
ሌላው ቅዱስነታቸው የተናገሩት ማህበሩ ከቀኖና ውጪ ቦሌ ላይና ሐረር መስመር መልካ ጀብዱ ላይ በአቡነ ጎርጎርዮስ ስም የመሠረተው ቤ/ክ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም መልካ ጀብዱ ላይ ቤተክርስቲያን ተሰርቷልና መርቅ ሲሉኝ፣ “እንዴት አቡነ ጎርጎርዮስን በተመለከተ በሲኖዶስ ያልወሰነውን?” ስላቸው መልሰው በካህናተ ሰማይ ስም ሰይመውታል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሁሉንም የንግድ እንቅስቃሴያቸውን ከአቡነ ጎርጎርዮስ ስም ጋር አያይዘውታል፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስ ለእኛ ወንድማችን ናቸው፤ ማኅበሩ ግን ለእኩይ አለማው ፎቶአቸውን ጭምር ይጠቀምበታል” በማለት የማኅበሩን እኩይ ሥራ ገልጠዋል፡፡ እንደተባለውም በአቡነ ጎርጎርዮስ ስም ቤተክርስቲያን መሰየምና ጽላት መቅረጽ በሲኖዶስ ሊወሰን የሚገባው ጉዳይ ነበር፡፡ ማቅ ግን በማን አለብኝነት ለአባ ጎርጎርዮስ በራሱ ውሳኔ የቅድስና ማእረግ በመስጠት ቦሌ ላይ ቤተክርስቲያን ለመሰየም ብሎ ሲነቃበት ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብጽ ነው በማለት አደናግሯል፡፡ መልካ ጀብዱ ላይም ተመሳሳይ ማደናገሪያ ነው ያቀረበው፡፡
የአስተዳደር ጉባኤው በውይይቱ መጨረሻ ውሣኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን
     1.     ስለፈጸመው ጥፋት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ እንቢ ካለ ግን መጽሔቱና ጋዜጣው እንዲታገድ፣
     2.    በይቅርታ ከተመለሰ ጽሑፎቹ ከመውጣታቸው በፊት በሊቃውንት ጉባኤ እንዲታዩ
     3.    ማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያን አቅም በላይ እየሄደ ስለሆነ ሦስተኛ ወገን መንግሥት ተገኝቶ ውይይት እንዲካሄድ
     4.    አዘጋጁ በህግ እንዲጠየቅ የሚሉ ጉዳዮች በአስተዳደር ጉባኤ ተወስነዋል፡፡
ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ በማቅ ላይ ሁሉም መምሪያ ኃላፊዎች አቋም የያዙበትና ማቅን በጥፋቱ የኮነኑበት ጉባኤ ሆኖ ተጠናቋል፡፡ እንዲህ ያለ ዕድል መፍጠር ስላልተቻለና ሰብስቦ የሚያናግራቸው አጥተው እንጂ ሁሉም በዚህ ማህበር ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እየተቸገረች እንደሆነ ነው ያሰመሩበት፡፡

32 comments:

 1. ለነገሩ ማንም አይሰማችሁም ምክንያቱም እናንተ የአባ ሰረቀና ንቡረ ዕድ አፍ ፓትረያሪኩ የነሱ ተመሪ እና ብዙዎቹ ድግሞ ህሊናቸው ሳይሆን ሆዳቸው የሚነዳቸው ጋሪዎች አሉ ደግሞ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለህሊናቸው ያደሩ ለእውነት የቆሙ እናንተ በመጥፎ የምትገልጹአቸው የእውነት ሰዎች የሚገርመኝ ሳታውቁት ስለነሱ የምትመሰክሩላቸው ስለነሱ እንድናውቅ ስላደረጋችሁን ስናመሰግን ከዚህ መጥፎ እና አስነዎሪ የበሬወለደ ወሬኣችሁ በሽታ ይፈታችሁ ብሎጉ የአባ ሰረቀና ንቡረ እድ ኤልያስ እንደሆነ ታውቋል ለገንዘብ ብላችሁ የምታደረጉትን ድካማችሁ ፍሬ የሌለበት ገለባ ያድርግላችሁ ፡፡
  ማንም ስለማይሰማችሁ ከንቱ ደካም አትድከሙ
  ስለወንጌል እንጂ ወንጀል ስለምትሰሩት አትንገሩን
  ዘላአለም በወሬ እና ሃሜት ግዜአችሁን አታጥፉ
  ለህይወት እነጂ ለሞት አትሩጡ

  ReplyDelete
 2. በዚሁ ከቀጠሉ ጥሩ ነው። የማቅ ማስፈራሪያ አስደንግጦዋቸው ወደ ኋላ እንዳይሉ እንጂ

  ReplyDelete
 3. ለምን ይዋሻል በየትኛው ጉባኤ ነው እንዲህ የተወሰነው እናንተ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ቤ/ያንን ለማፍረስ እየተጋችሁ ብትሆኑም መሠረታ ክርስቴስ ነውና አትፈርስም

  ReplyDelete
 4. Mahibere kidusuan is violating the church's rule by disobeying the patriarch's instruction.So, the license which was given to to this group must be canceled as soon as possible to keep the unity of the church.

  ReplyDelete
 5. Mk is terror organization. This mafiya demolished credibility of the highest rank level of our church college. It is not enough giving for giviness by excuse to say sorry. Otherwise simply playing dirt game.

  ReplyDelete
 6. መናፍቅ ያልሆነው ሰለመናፍቅ ቢጻፍ ምን አስጨነቀው?

  ReplyDelete
 7. Enter your comment... Abet wushet! Abet wushet! Aba selabiwoch enedihu yesedeb ena yehaset afe yesetachehu selabiwu diabilos yaselefelefachehual enje hasabschehu ke megnot ayalefem! masetewalun yadelachu!

  ReplyDelete
 8. በሀገር ቤቱ ካለው ስኖዶስ ጥቅት ሊቃነ ጳጳሳት በማቅ ነዋይ አደበታቸው ተይዞ እዉነትንና ለእዚአብሔር ክብር ከመቆም ለማቅ ክበር እራሳቸው በሰጡበት ሰዓት ላይ እንገኛለን። እግዚአብሔር ምን ያህል ደግ አባት እና የእዉነት ጌታ ስለሆነ ህዝቦቹን ለክፉ ደሰልፎ አይሰጥም። በመሆኑም እነሆ የቁርጥ ቀን ልጆቹን ከስደተኛው ስኖዶስ በማነሳሳት ህዝበ ክርስትያኑ እውነቱን እድያውቁ እጅግ ደስ በሚል ሁኔታ ማቅ የሚጋለጥበት የዉውይት መድረክ ባለፈው ሐሙስ ተከፍቶ አገልግሎት በስልክ ኮንፈረስ ተጅምሮዋል።ስለ አርጋኖ ወንም ኦርጋን ታርካዊ አመጣጥ ከጥንተ ጀምሮና ኦርቶዶክስና ካቶልክ ሳይከፋፈሉ በአርጋኖ ወይንም በኦርጋን መልካም ዝማረን ለእግዚአብሔር ስያቀርቡበት እንደነበረ በተጨባጭ ማስረጃ ቀርቦ ነበር። እነ ቅዱስ ያሬድና አባ ጊርጊስ ሁሉ የዘመሩበትና የጻፉት መጽሐፍት ለማስጃነት ቀርቦ ነበር።እግዚአብሔር ለመምህሩ ቃለ ህይወት ያሰማልን። ስለ እዉተኛው የእግዚአብሔር ቃል ስይጣመም ህዝቡ ማወቅ እንዳለበት መንገዱ ተጀምሮዋል። ማቅ የያዘው የሀሰት ትምህርት በግድ መቆም አለበት፡፤ ለምሳል እመቤታች ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል ናት የምል የተሳሳተ ትምህርትና እንድሁም በመስቀል ላይ የዋለዉ ሥጋ የቅድስት ማርያም ስለሆነ አዳኛችን እርሷ ነት እያሉ እያስተመሩ ስለሆነ ይህ ሁሉ አውነተኛውን ወንጌልና የቀዱሙት አባቶቻችን ያላስተማሩትን ትምህርት መቆም አለበት እንላለን። ይህን መርሀ ግብር እንደግፉ እንተባበራቸው። በረቱ በርቱ እንላለን። ሁላችንም ለሀይማኖታችን እንቁም።

  ReplyDelete
 9. ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር
  እግዚአብሔር ስራዉን የሚሰራበት ጊዜ አለ ክብር ለስሙ ይሁን
  ማቅ እዉን ክርስቲያን ከሆነ አሁኑኑ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ።
  ግን ያረገዉም። ምክንያቱም ማቅ በትቢት የተወጠረ ይቅርታን የማያዉቅ የክፉዎች ስብስብ ነዉና
  ስንት ጊዜ ስህተቱን እንዲያርም እየተነገረዉ እያድበሰበሰና የሱን ችግር ማስረሻ ሌላ ችግር እየፈጠረና አቅጣጫ እያሳተ የኖረ የክፉዎች ስብስብ መሆኑ አገር ያወቀዉ ጸሃይ የሞቀዉ ሞለጭላጫ ይቅርታን የማያዉቅ ነዉና ።

  ReplyDelete
 10. 1)ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ ይላል ቃሉ!!!
  2)ትእቢት ውድቀትን ትቀድማለች ይላል መጽሐፉ !!!
  3)ሳውል ሳውል ስለ ምን ታሳድደኛለህ??? አለ ጌታ!!!
  4)ስንት የቤተ ክርስቲያኒቷ ዓይናማ ሊቃውንት ተወግረው ተሰደዱ???
  5)አቤቱ ጌታ ሆይ እስከ መቼ ድረስ እውነትን ግፈኞች ይናጠቋታል???
  6)የዚች ቤተ ክርስቲያንስ እጣ ፋንታ ምን ይሁን???
  7)ወደ ቀደመው የወንጌል ጅማሬዋ ተመልሳ የደም ዋጋ ከከፈለላት ሙሽራዋ ጋር መታረቁ አይሻላትምን??? እስከ መቼስ ድረስ የመጣ ጉልበተኛ ሁሉ ይወሽማታል??? ታማኝ ልጆቿስ በአሉባልታ ወሬ እየተሰደዱ የሌላውን ቤት በማሞቅ ያሳደገች እናታችን ለምን የወላድ መካን ትሁን??? ኧረ አገር/ሕዝብ ይስማውና ማን ምን እንደሆነ ይታወቅ???

  አገራችንን አምላካችን እግዚአብሔር ይጠብቅ!!! አሜን።

  በማቅ
  ከእናቱ ቤት ከተባረሩት አንዱ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቱልቱላ መናፍቅ ፣መናፍቅ ሆነህ አዳራሽ እንጂ ቤተክርስትያን ውስጥ መዝለል አይፈቀድም፣ካልተመለስክ ለምን እመቀእመቃት አትገባም እንኳን መባረር? አሁን ያለኸው ድሮም የነበርከው መናፍቃን ጋር ነበርክ።

   Delete
 11. ሲጀመር፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ ያውቃል እንዴ? እነርሱ እኮ ከክርስትና ከወጡ ዘመን አልፎታል!!!

  ReplyDelete
 12. ስንት ዓመት ሙሉ እንታገሰዋለን? ማኅበሩ ከእጅ ከወጣ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ሲጠባ ያደገ ጥጃ ሲይዙት ይጓጉራል አይደል የሚሉት አበው?

  ReplyDelete
 13. እርር ድብን ትላላችሁ እንጅ ማህበሩ ምንም አይሆንም ምክንያቱም እውነትን ስለያዘ። ለፍርፋሪ እና ለሰልባጅ ብላችሁ ህሊናችሁን አትሽጡ ሃራጥቃዎች።

  ReplyDelete
 14. ቤተ ክህነቱም ሆነ ማኅበሩ አንድ ሆነው የፈጣሪን ቤ/ክርስቲያን ማገልገል ሲገባቸው
  የሚወዛገቡ ከሆነ ለሚያምንም ለማያምንም መሰናክል ሆነዋልና ልባቸውን በፈጣሪ ቃል መወልወልና ማደስ ይገባ ነበር። ዳሩ ግን በሁሉም ጓዳ ዝገት በመኖሩ ባለመታደሱ
  ለክፋ ውዝግብና ክርክር ተዳርገዋል።በመሆኑም ቃሉ ተጥሷል ፪ ጢሞ ፪.፳፪---፳፯
  ተመልሰው መለያየትን አስወግደው በንስሓ ካልታደሱ በስተቀር በሌሎች ላይ ጣትን መቀሠር የሠማርያው ንጉሥ ኢዮርብአን መምሰል ሳይሆን መሆን ይመጣል።

  ReplyDelete
 15. አኔ አምለዉ ማህበሩና የማህበሩ ኣባላት ይቅርታን ያዉቃሉ ወይ?
  አንካን ይቅርታን ኃጢኣትንም ለይቶ የሚያዉቅ ኣይመስለኝም
  ምክንያቱም የማህበሩ ኣባል ከሆነ ኣታመንዝር የሚለዉ የአግዚኣብሔር ቃል በነሱ ላይ ኣይሰራ
  "" "" ኣትግደል "" ""
  "" "" ኣትስረቅ የሚለዉ ቃል ኣይሰራ ባጠቃላይ ወንጀል ለነሱ ወንጌል ነዉ የሚመስላቸዉ
  ለዚህ ነዉ ሁልጊዜ አየገደሉ አያሳደዱ አየተሳደቡ የሚኖሩት

  ReplyDelete
 16. በማቅ ከናቱ ቤት ከተባረሩት አንዱ ላልከው
  ማህበረ ቅዱሳን ያባረረው ክርስቲያን የለም መናፍቃንን እንጅ ስትቀላውጥ ከተገኘህ ግን በማስረጃ አስደግፎ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያበርሃል። እውነተኛ ከሆንክ በዚህ በዚህ ብለህ በማስረጃ መውቀስ ነው የሚገባህ ወንድሜ። ከህሊና ወቀሳ ነፃ ሁን።

  ReplyDelete
 17. ውሳኔው ጥሩ ነው ግን ማኅበሩ ይቅርታ የሚጠይቅበት የጊዜ ገደብ መቀመጥ አለበት።

  ReplyDelete
 18. mewaqrun eyaferesut yalut mahibere kidusan bicha aydelum betam bemiyasazin huneta andand liqane papasatm yihen eyetegeberu new
  Be America yemigegnut Abune Fanuel yemidenequbet neger binorim ke Kidus patriarik Abune Matias betetsararinet lemegedadr kemishut Denver Medhanealem agelgayoch gar mehon hunetawoch sayteru metebaber riese menberun meqawem new
  Betekirstiyan yihen sirat alqoyechilinim tilant ende alemawi mengist menebere siltan lemegelbet siyaser behulam yebetekirstiayan amlak yakeshefewun ye Abune Samuel sera hulachinim yeminiresaw aydelem
  Ebakachihu abtoch siltanu ye egziabher silehone ebakachihu chama batilekaku yetarik teweqash endathonu kesimet betseda saygebachihu bemenberu yeshomachihun geta batasazinu melkam new
  Ers be erswa yematismama mengist titefalech endetebalew lemengawu asibu
  Yihichin Tintawitna hawariyawit betekirstiyan bitichilu kenekibruwa enditqoy bitiseru melkam new
  Balen godahu bila aynet akahed lebetekirstian aybejim
  Esti patririkun agzowachew chigir kalem beguwada fitut betenatil andu be andu lay termamdo erasin masayet yiqir
  yebetekirstiyan amlak mengawun kemebeten yitebiqilin

  ReplyDelete
 19. በዉስጤ ያስቸገረኝና አንዳንድ ሰዎችንም ጠይቄ መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ

  የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ለምንድን ይቅርታን የሚፈሩት ? ኣናጠፋም ለማለት ነዉ ወይስ ሌላ?
  ብዙ ጊዜ በብፁአ አቡነ ጳዉሎስም ሆነ, በብፁአ ኣቡነ ማትያስ በማህበሩ ሰዎች የሚታየዉ ያዉ አንቢተኝነት ነዉ ለምን?
  አምታዉቁ ሰዎች አባካችሁ ስለ አግዜአብሔር መልሱልኝ፡
  በቅንነት ጥያቄየን ለሚመልስልኝ ከወዲሁ አመሰግናለሁ።
  አግዜብሔር ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 20. ይቅርታን ለመጠየቅ አስቀድሞ ቅርታን የሰጠንን የሰላም አባት ኢየሱስ ከርስቶስ ብቻ እንደሆነ ማመንን ይጠይቃል። በጣም የምገርመው ነገር በኦርቶዶሰክ ቤተ ከርስትያናችን ያለት ችግር መፍተህ ልያገኝ የሚችለው በመጀመርያ ደረጃ የማቅ አባለት በማህርና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ጠንቅቀው ልያውቅ ይገባቸዋል። ምክንያቱ የማህበሩ አባለት ከኦርቶዶክስ ስርዓት ይልቅ የማህበሩን በማስቀደም ይፈጽሙታል። የጌታችን የኢየሱስ ከርስቶስ ሞትንና የእመቤታችን ሞት ለይተው ልረዱት ያስፈልጋቸዋል።በመስቀል ላይ የፈሰሰውን የኢየሱስ ደምና በመስቀል ላይ ያለፈሰሰውን የመእመቤታችንን ደም ለይተው በየትኛው እንደዳን ማወቅ በግድ ያስፈልጋቻዋል።ማቅ ይቅርታን ለመጠቅ መቅድምያ አዳኛችን ጌታችን ኢያሱስ ከርስቶስ ነው ወይንስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ? ይህን በትክክል ጠንቅቀው መልስ እስካልሰጡበት ድረስ የቅርታ የመጠየቅ ልብ ፈጽሞ የላቸው።ለማቅ አባላት ትልቅ የመዳን ጥሪ እውነተኛው የተዋህዶ ልጆች እያቀረቡ ናቸው። ሕዝባችንን ወጣቱ በአሁኑ ሰዓት ወንጌልንና ተረታተረቱ ጠንቅቆ የተረዳበት ዘመን ስለሆን ማደናገሩንና ማጭበርበሩን ትታችሁ ወደ ነፍሳችሁ አዳኝ ተመለሁ። ማርም ስበዛ ይመራሉ ብለው አበው እንደ ተናገሩት እናነተም ማቆች ይበቃችዋል። ብረሌ ከነቃ አይሆነም እቃ ተበሎዋልና። ተዋህዶ ልዶች አዳኛችን በመስቀል ላይ ነፍሱን ስለ ብዞዎቹ የከፈለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ አውቀዋል። በቅድስት ማርያም ስምና በቅዱሳኑ ስም የበላችሁን ገንዘብንና ያገኛችሁ የዉሸት ክህነት ይዛችሁ አረፍ በሉ።ከእንግድህ ማንም አያዳምጣችሁም። ይልቁንስ በየቤተ ከርስትያናችሁ ሥርዓተ ቤተ ከርሰቲያን ለመፈጸም ልባችሁን ሰብራችሁ ተመሉስ እንላለን።

  ReplyDelete
 21. ሰበር ዜና ላልሰማና ላላዬ!
  ማህበረቅዱሳን የመናፍቃን ማህበር መሆኑ ተረጋገጠ ::::
  ምንፍቅና ማለት በቤተክርስቲያኒቱ ትውፊት : ዶግማና ቀኖና የማያምንና የማይመራ የሚጠራጠር ማለት ሲሆን ማህበረ ቅዱሳን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ይንን ተግባር እያከናወነ ይገኛል፡፡
  ለምን ቢባል እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና እምነት አንድ ካህን ዲቁናም ሆነ ቅስና የሚቀበለው የቤተክርስቲያኗን መሠረታዊ ትምህርት ተምሮ ሲሆን ማህበረ ቅዱሳን ግን በዝሙት ጊዜያቸውን የጨረሱ አባላቶችን በ40 እና በ60 ዓመታቸው በተክሊል እያጋባ በአንድ ቀን ማለትም በሰርጋቸው ማግስት ዲቁናና ቅስና በነውረኛ ጳጳሳት እያሰጠ ቄስና ዲያቆን እያሰኘ በመንፈስቅዱስ እና በመንፈሳዊ ዕውቀት የሚገኘውን የቤተክርስቲያን ስልጣነ ክህነት እያራከሰው ይገኛል ፡፡ ይሔም ማለት የለየለት መናፍቅነት ነው፡፡
  ምሳሌ፡- ከብዙ በጥቂቱ የቤተክርስቲያኗን ትምህርት ሀ ሳይሉ ቄስና ዲያቆን የተባሉ
  1.ደረጀ ዘወይን( የክብር ዲያቆን)
  2. ዳንኤል ክብረት( የክብር ዲቁና)
  3. የማህበሩ መሥራች ብርሀኑ ጎበና/የክብር ዲቁናና ቅስና
  4. የዕውነት ዶክተር ሰሙ የማህበረቅዱሳን ሰብሳቢ /የክብር ዲቁናና ቅስና /
  ባጠቃላይ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ከሴቶች በቀር ሁሉም ከ40-70 ዓመት ድረስ ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ውጭ የክብር ዲቁና እና ቅስና ወደፊት ደግሞ የክብር ጵጵስናም እንይዛለን ብሎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዚሁ አያይዞም ቤተክርስቲያንን ተገን በማድረግ ዘውዳዊ መንግስት ለመመሥረት እየተዘጋጀ መሆኑን ከውስጥ አዋቂ ምንጭ ለመረዳ ተችሏል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወሽካቶች እናንተ ተሀድሶውያን በቤተ ክርስቲያን ጎን ላይ እንደተባይ የተለጠፋችሁ ደም መጣጮች ለመሆኑ እነዚህን የዘረዘራችሁቸውን ሰዎች ብታንቋሽሿቸው ዱጭ የሚልብን ይመስላችኋል፡፡ እናንተ እኮ ከእነሱ በአላማም፣በእምነትም፣ በጽናትም፣ በተቆረቋሪነትም …. አረ በስንቱ ምናቸውም ጋ የማትደርሱ የአትዮጵያን አንድነትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን ለመፍታት የተላካችሁ ቅጥረኞች ናችሁ፡ ስለዚህ ከእናንተ እኮ ምንም አንጠብቅም፤ ብሎጋችሁንም የምንከፍተው እኮ አንድም ዛሬ ምን ወሸከቱ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በቀጣይ ምን ልትወሸክቱ እንደምትችሉ አስቀድሞ በማወቅ ጽናታችንን ለማጠናከር አንድም ለመዝናናት እንከፍታል፡፡ እራሳችሁ በሬ ወለደ ትጽፋላችሁ እራሳችሁ በሬ ወለደ ውሽከታችሁን ደግፋችሁ እንደ አስተያየት ሰጪ ዳግም ትወሸከወታላችሁ፡

   Delete
 22. እኔ እንደ ተራ የቤተክርስቲያኒቷ ተከታይኔ የሚስጨንቀኝ ለአባ ማቲያስ ማኅበሩ መልስ ስለመስጠቱ አይደለም፡፡ ነገር ግን አባ ማቲያስ የተሰጠውን ምላሽ እንዴት ተረዱት የሚለው ነው፡፡
  አነሳሳቸው ለቤተክረስቲያን ከመቆርቆር ከሆነ ለቤተ ክርስቲያን በመቆርቆር ነው እየሠራሁ ያለሁት በሚል ማኅበሩ የገለፀውን ከእርሳቸውን ሥጋት ጋር በማመዛዘን፣ ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዲሁም እርሳቸው ወደ መንበሩ ሲመጡ ይዘው የመጡትን ሐሳብ ማስታረቅ መቻሉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆን አለበት፡፡
  እንደ እኔ እርሳቸው መንበር ላይ ከወጡ ጀምሮ ያቀዱት፣ ያወሩት፣ በኮሚቴ እንዲጠና ያደረጉት ነገር በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያን ያሰቡት መልከም ነገር ሁሉ ምንም አልተሳካለቸውም፡፡ በመጀመሪያ ሊያስጨንቃቸው የሚገባው ይህ ነው፡፡ ይልቅኑ ብለው ብለው ሲያንፀባርቁ ለነበሩት መልካም ነገር እና ተስፋ አድርገን ስንጠብቀው ለነበረው ነገር ሁሉ እራሳቸው ተቃራኒ ሆነው ቆሙ፡፡ ለግንዛቤ ያህል፣
  • የዘረኝነት መንፈስን ከቤተክርስቲያኒቷ አስወግዳሉ አሉ እርሳቸው ቀንደኛ የዘርኝነት ከዚያም አልፎ የጎጠኝነት ተወና ዋይ ሆኑ፣
  • መልካም አስተዳደርን አሰፍናለሁ አሉ የመልካም አስተዳደር ጠንቅ ሆኑ፣
  • ሰንበት ተማሪዎችን ለሐሳቤ ከጎኔ ሁኑ አሉ ጥሪውን ተቀብለው ከጎናቸው የቆሙትን ወጣቶች ለእስራት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኑ፣
  • የቤተክርስቲያኒቷ ዶግማና ቀኖና እንዲከበር እሠራሉ አሉ ለዶግማና ቀኖና መጠበቅ ጠንከሮ እየሠራ ያለውን ማኅበር እጅ እግሩን አስረዋለሁ አሉ፣
  • በተሀድሶ እንቅስቃሴ ላይ የሚሠራ በሊቀ-ጳጳስ ደረጃ የሚሠራ ኮሚቴ ሰየሙ ተመልሰው የተሀድሶ ደጋፊ ሆኑ፣
  • ምንዕመን ስለ ቀነሰ ድንበር የለሽ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አስፋፋለሁ አሉ በሐሳብ ደረጃ ቀድሞ በመጀመር በተለያዩ ሐገረ-ስብከቶ ከሚገኙ ብፁአን አባቶች እና የቤተከርስቲያኒቷ አገልጋዮች ጎን በመቆምና ድጋፍ በማድረግ አባቶች ሐዋሪያዊ አገልግሎታቸውን እንዲወጡ የሚያግዘውን እና ድንበር የለሽ የቤተክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳን አፍርሰዋለሁ አሉ፡፡
  • ይህን ያህል ምዕመን የሥላሴን ልጅነት አገኘ ብሎ የሚያበስራቸውን ማኅበር ሽባ አደርገዋለሁ ሲሉ የተቀበሉትን አደራ እንዲወጡ እያገዛቸው ያለውን አገልግሎት ለመገደብ ተነሱ፣
  • የ24 ሰዓት የቴሌቪሽን አገልግሎት አስጀምራለሁ አሉ የተጀመረውን ከማበረታታት ይልቅ አንድ አለን የምንለውን አዘግተው አረፉ፣
  • ውጪ አገር በሄዱ ጊዜ በሚሰጠው ድንበር የለሽ አገልግሎት መደሰት ሲገባቸው አገር ቤት መጥተው እንዲያውም እንደ ክስ አቀረቡት፣
  • አባቶች ተጨንቀው የዘረጉት የቤተክረስቲያን አስተዳደረዊ መዋቅር እና የአሠራር ሂደት ባለ ማክበር እንዲያው ምን ሲኖዶስ አለና ሲሉ ተሰሙ፣
  • የአገልግሎት ጊዜን የሚያረዝመው እና የሚገድበው ቅዱስነታቸውን በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው እግዚአብሔር መሆኑን ዘንግተው በቅዱስ ሲኖዶስ የተመረጡትን የጠቅላይ ቤተከህነት ሥራ አስኪያጅ ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ መሰናክል እንደሚሆኑ ተሰማ፣ ለመሆኑ ከአሁን በኋላ ሦስት ዓመት የማገልግል ዕድሜን የሚሰጠው ማነው? አግዚአብሔር አይደለንም? ከዚያ በኋላስ ተጨማሪ ዓመት እንዲያገለግሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ አድሮ የሚመርጠው አግዚአብሔር አይደለንም? ይህን በማለትዎ ቅዱስ ሲኖዶስን በመንፈስ ቅዱስ የማይመራ የግለሰቦች ሐሳብ አራማጅ ተደርጎ እንዲታሰብ አደረጉ፣
  • የአገርን፣ የዜጎችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ታሪክን፣ ቅርስን….. ወዘተ ከእግዚአብሔር በታች ከበላይ በኃላፊነት እንዲጠብቅ ሕዝብ ይሁንታ የሰጠውን መንግሥት እንደ የግላቸው ሐሳብ አራማጅ በመውሰድ ከመንግሥት ጋር በመሆን ለቤተክርሰቲያን አገልግሎት የሚሠሩትን አጠፋለሁ አሉ፡፡ ባለፈው ዓመት ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ውይይት መንግሥት የአሸባሪነት ትርጉም ካልገባችሁ ጠይቁ እንደ ተባለ ከተለያዩ ማህበራዊ ገጾች አንብቤአለሁ፣ እኔ በግሌ መንግሥት ዞሮ የሚያይበት አንገት አለው ብዬ አምናለሁ፡፡
  • ……… አረ ስንቱን ይጠቀሳል፡፡ ደከመኝ፡፡
  ነገር ግን በቅዳሴ ጊዜ ስለ እርሳቸው የሚፀለየው ፀሎት፣ እኔም በአቅሜ ውዳሴ ማሪያም ፀሎት ሳደርግ ፀሎታ ለማሪያም ወስህለታ ለርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳቲነ ይቀባ …. እያልኩ የምፀልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ተቀብሎ ለእርሱ ብቻ እንዲሠሩ ያደርጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  እግዚአብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅል፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቅዱስነታቸውን እግዚአብሔር ይፈውሳቸው፡፡

   Delete
 23. እስኪ እናንተ ስለ ቤተክርስቲያን ለመናገር እናንተ እነማን ናችሁ??
  ለምንፍቅና ስራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መሰናክላችሁ ስለሆነ
  እናንተ የምትፈልጉትን ቅሰጣ ለመፈጸም መጀመሪያ መንገዱን ማጽዳት አስፈለጋችሁ፡፡
  በርቱ በጠላት መኖር ቤተክርስቲያን የበለጠ ትጸናለች፡፡

  ReplyDelete
 24. እስከዛሬ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስምና ስዕል ለተራ ቢራ ማስታወቂያ ሆኖ ሲኖር አንድ ቃል ያልተነፈሳችሁ ዛሬ የቤተክርስቲያንን የልማት ተቋማት ፀረ መናፍቅ በሆኑት በአቡነ ጎርጎርዮስ ስም መሰየሙ ካንገበገባችሁ ለቅዱሳን ክብር በማሰባችሁ ሳይሆን ለከርሳችሁ በማሰብ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በክፉ ደዌ ተይዛችኋል ብትጸበሉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የልማት ተቋም ሌላ ታቦት ሌላ ምኑን ከምን ነው የምታምታታው?

   Delete
 25. ማህበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጫቸው የሆነው ፒኤልሲ እንዳይዘጋባቸው በውስጥም በውጭም ባሉት ሆዳም ቅጥረኞቻቸውና አባላቶቻቸው ተሐድሶ ተሐድሶ የሚለውን ነጠላ ዜማ ያቀነቅናሉ፡፡ አሁን እነ በጋሻው መጀመሪያ መቼ ተማሩና ነው መናፍቅ የሆኑት ማ/ቅ አባላት እውነት ለሓይማኖት ከቆማችሁ እና አነሱ ተሐድሶ ከሆኑ ለምን አስተምራችሁ አልመላሳችኋቸውም፡፡ ሌላው እምነት አዲስ አማንያንን እያስተማረ አባላ ያደርጋል ፡፡ እናንተ ያለውን ስም እያጠፋችሁ ታሳድዳላችሁ ፡፡ በእውነት በእናንተ ላይ እግዚአብሔር ፍርድ ይሰጣል፡፡ በአገር ቤት ግን በአክራሪ ኦሮሞዎች ቤተ ክርስቲያናት እየነደዱ ነው፡፡ ለግል ጥቅማችሁ ብላችሁ ምእመናንን ከምትከፋፍሉ ንስሐ ገብታችሁ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሕልውና በጋራ ሥሩ፡፡ በማህብር ስም ያቆማችሁትንም ፎቅ ለቤተ ክርስቲያን በፍጥነት አስረክቡ፡፡

  ReplyDelete