Friday, February 5, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ብዙዎቹን ጥፋቶቹን በተዘዋዋሪ በማመን ጥቂት ነጥቦች ላይ ብቻ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ “የእውነት ጠብታ የሌለበት ምላሽ” ሰጠማኅበረ ቅዱሳን በጅምላ ስማቸውን ማጥፋቱን ተከትሎ መንፈሳዊ ኮሌጆች ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ላቀረቡት አቤቱታ፣ ፓትርያርኩ ለመንፈሳዊ ኮሌጆች በሰጡት ምላሽ ክፉኛ ማዘኑን ገልጾ ምላሽ መጻፉን ሰንደቅ ጋዜጣ የጥር 25 ዕትም ዘግቧል፡፡ ማኅበሩ በፓትርያርኩ ከተገለጹት 12 ጥፋቶቹ መካከል ለመከላከል የሞከረው በጣም ጥቂቶቹን ሲሆን እነርሱንም ቢሆን በደፈናው ንጹሕ ነኝ በሚል መንፈስ እንጂ በማስረጃ በማስደግፍ ለመከላከል አልሞከረም፡፡ በቅዱስነታቸው የተነሡትን አንኳርና አሳማኝ ነጥቦች ሁሉ ዘሎ የኦዲት ሪፖርቱን፣ የጅምላ ክህነቱን፣ ታሪክ አበላሸህ መባሉን የፅጌ ጾምን በተመለከቱ ነጥቦች ላይ ብቻ ነው የተውተፈተፈ ምላሽ ለመስጠት የሞከረው፡፡ ሌሎቹን ጉዳዮች ግን “ሥራዬ ነው” የማለት ያህል ምንም አስተያየት ሳይሰጥባቸው በዝምታ አልፎአቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ግን በፓትርያርኩ ደብዳቤ መናደዱንና ማዘኑን አልደበቀም፡፡
እንዲያውም ፍትሕ ተዛብቶብኛል የሚል ዓይነት ቅሬታ አሰምቷል፡፡ እንዲህ ሲል “ክስ የቀረበበትን አካል አቅርበው ሳይጠይቁ ከርሱም ሳይሰሙ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመስርቶ ፍርድ መስጠት በማንኛውም አካል ዘንድ በተለይም እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ የሆነ ሥርዓት ነው፡፡” በማለት ፍትሕ ተነፍጎኛል ያለው ማቅ፣ እንዲህ ያለውን ድርጊት እርሱ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ትክክል የነበረውንና ብዙዎች ቀርበው ሳይጠየቁና ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ ሳይሰጡ በእርሱ በማቅ ውንጀላ ብቻ ተፈርዶባቸውና “ተሐድሶ” ተብለው ከቤተ ክርስቲያን እንዲሰደዱ እንዳላደረገ ሁሉ፣ የዘራው እርሱ ላይ ሲደርስ ግን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት ነው አለ፡፡ ምናልባት ይህ አጋጣሚ ማቅ የሚማር ልብ ካለው “ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።” (ሉቃ. 6፥31) ከሚለው ቃለ ወንጌል ትምህርት የሚወስድበት ዕድል ሊሆን ይችላል፡፡

ሌላው ማኅበረ ቅዱሳን ያነሳው ነጥብ አባቶችን የሚታዘዝበትን ምክንያት ገሃድ ያወጣ ነው፡፡ ማቅ እንደ ማኅበር አባቶችን የሚያከብር መስሎ የሚታየው ከጥቅሙ አንጻር ነው እንጂ መታዘዝን መርሑ ስላደረገ አይደለም፡፡ ማንኛውንም ነገር የሚያደርገው በነጻ አይደለም እያንዳንዱን ጉዳይ ከጥቅሙ ጋር በማስተሳሰር ነው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ጳጳሳትን ከጀርባው ለማሰለፍ የሆነ ነገር ያደርግላቸውና ወይም የያዘባቸውን ነውር እየጠቀሰ ያስፈራራና በሚግባቡበት መንገድ ጥቅሜን አስከብሩልኝ ይላል፡፡ በዚህ ደብዳቤው ላይ እንደጠቀሰውም በቅርቡ ቅዱስ ፓትርያርኩን በአሜሪካ ደማቅ አቀባበል በማድረግ “ያስከበራቸው” እርሱ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ጠቅሶ ፓትርያርኩ ያን ውለታ ገደል ጨምረው ይህን የመሰለ “የሰውን ስሜት በሚያስቆጡ ቃል የሚሸነቁጥ” ደብዳቤ መጻፋቸው በእጅጉ እንዳሳዘነው እንዲህ ሲል ጽፏል፡፡ “አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቡናዎ ያውቀዋል፡፡ ከዚህም በላይ በሀገር ውስጥ ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን በሚዘዋወሩበት ጊዜ በየቦታው በደመቁ ሰልፎች  ተሰልፈው እየዘመሩ በማጀብ የሚቀበሉዎ ማኅበረ ቅዱሳን” ያስተማራቸው አባላቱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡  ከዚህም መረዳት የሚቻለው ፓትርያርኩ ማቅ እርሳቸውን “በማስከበር” ለዋለላቸው ውለታ ብድራት እንዲሆን እርሱ በማይመለከተውና በሌለው ሥልጣን ገብቶ በኮሌጆቹ ላይ ለጻፈው ዘለፋ የፓትርያርኩ ምላሽ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ መጻፍ ሳይሆን ዝምታ መሆን ነበረበት፡፡ ለዚያ ነው ማቅ እንዴት ውለታዬ ገደል ይጨመራል በሚል ድምፀት አካኪ ዘራፍ ያለው፡፡ እውን ያስከበርኩዎ እኔ ነኝ ይባላል? ማቅ እንዲህ የሚያስቡ ያልበሰሉ ሰዎች ጥርቅም መሆኑን በዚህ አነጋገሩ ታውቋል፡፡      
ማኅበረ ቅዱሳን በፓትርያርኩ መመሪያ ክፉኛ መበሳጨቱን ያሳየበት ሌላው ነጥብ እንዲህ ይላል፡፡ “በአጠቃላይ ካሁን ቀደም በተለያዩ የተሐድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጁአቸውና በሚመሯቸው ድረ ገጾችና ብሎጎች ላይ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ሲያወጡአቸው የነበሩትና አንድም የእውነት ጠብታ እንኳ የሌላቸውን ሐሳቦች በርስዎ ደብዳቤ በአጭር በአጭሩ ተጠቅሰው ማየታችን እጅግ አሳዝኖናል፤ አስገርሞናል፡፡” በማለት ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማሸማቀቅ በሚመስል መልኩ እርሳቸው የጻፉት ደብዳቤ “አንድም የእውነት ጠብታ” እንደሌለው አድርጎ ጽፏል፡፡ የማቅ አፍ ሆኖ በነጻ ሚዲያ ስም በመንቀሳቀስ ላይ ያለው ሰንደቅ ጋዜጣም ዘገባውን የሠራው “የፓትርያርኩ መመሪያ የእውነት ጠብታ የሌለበት እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ገለጸ” በማለት በበላበት ጮኾ ነው፡፡ እዚህ ላይ አባ ሰላማን ጨምሮ ሌሎቹም ብሎጎች በማቅም ሆነ በቤተክርስቲያን ዙሪያ የሚያወጧቸው ዘገባዎች በእውነት ላይ የተመሰረቱ እንጂ ሐሰተኛ እንዳይደሉ ማንም ሊክድ አይችልም፡፡ መረጃዎቹ የተገኙትም ከቤተ ክህነቱ ወይም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ነው እንጂ እኛ የፈበረክነው አይደለም፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩን መረጃውን ከእኛና እኛን ከመሰሉ ብሎጎች ወሰዱ ማለት ውሃ የሚቋጥርና እርሳቸውንም ቤተክርስቲያኒቱንም ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በመረጃ ላይ ተመሥርቶ ማቅን መስመር ለማስያዝ በተንቀሳቀሰ ጊዜ ማቅ አባ ሠረቀን የከሰሰው መረጃዎችን ለተሐድሶዎች እየሰጡ አሰደቡን በሚል ነበር፡፡ አሁን ግን እንዲህ ማለቱን ረስቶና ያን ገልብጦ ፓትርያርኩ ደብዳቤውን የጻፉት ከተሐድሶ ብሎጎች ወስደው ነውና መመሪያቸው አንድም የእውነት ጠብታ የለውም አለ፡፡ ይህ ስለማቅ ከማንም በላይ የተሟላ መረጃ ያላቸውን ቅዱስ ፓትርያርኩንና ቤተክህነቱን እንደ እኛ ካሉና በሚያገኙት መረጃ ላይ ተመሥርተው እውነትን ከሚዘግቡት ብሎጎች ወስደው ደብዳቤ ጻፉ ማለት እርስ በእርሱ የተምታታ ነገር ከመሆኑም በላይ ለፓትርያርኩ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ደግሞስ መረጃው ሐቀኛ ይሁን እንጂ ማንስ ቢዘግበው እውነት ሐሰት ይሆናል ወይ?    
ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው ማቅ ለኮሌጆቹ በተጻፈው ደብዳቤ ተበሳጭቶ በሰጠው ምላሽ ብዙዎቹን ጥፋቶቹን በተመለከተ በዝምታ ማለፉ ጥፋቶቹን መፈጸሙን እንዳመነ በግልጽ ያሳያል፡፡ አላምን ብሎ የተከራከረባቸው ነጥቦችም ቢሆኑ በክሕደትና በቀጥፈት የተሞሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው ነጥብ ላይ ፓትርያርኩ “በሌለው ሥልጣን የጾም ዐዋጅን እስከ ማወጅ መድረሱን” ገልጸው ነበር፡፡ ለዚህ ክስ ማኅበሩ በደብዳቤው መጀመሪያ ላይ ሳይሆን በስተ መጨረሻ አካባቢ “ዋና ወንጀል” ብሎ በመጥቀስ የሰጠው ምላሽ “በዐጭር ቋንቋ ማኅበረ ቅዱሳን ያወጀው ጾም የለም” በማለት ሲሆን ከዚህ ቀደም ሐመር መጽሔት 1987 ዓ.ም ነሐሴ ላይ የ1988 ዓ.ም አጽዋማትን ይዞ በወጣው ፖስት ካርድ በ8ኛ ደረጃ ያስቀመጠው የፅጌ ጾም መስከረም 26 ይጀመራል ብሎ በመጥቀሱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በቁጥር 6738/8513/87 በቀን 2/13/87 ደብዳቤ ጽፎ ማኅበረ ቅዱሳን የጽጌን ጾም 8ኛ ጾም አድርጎ በመቁጠሩ ተሳስቷልና አስቸኳይ ማስተካከያ ይስጥ ብሎ ነበር፡፡ ማኅበሩም የተባለውን ስሕተት እንደሚያስተካከል በቀን 3/1/88 ዓ.ም. በቍጥር 002/ማቅ/038 ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ የገለጸ ቢሆንም በተግባር ግን ስሕተቱን እስካሁን ድረስ በጽሑፍ አለማረሙንና አሁንም አልተሳሳትኩም በሚል መንፈስ እየተከራከረበት መሆኑን ከዚህ ደብዳቤ መንፈስ መታዘብ ይቻላል፡፡ የማኅበሩ ተከታዮችም የፅጌ ጾም እያሉ በወርኃ ጽጌ መጾም መቀጠላቸውን ይታወቃል፡፡ የፅጌን ጾምነት የማያውቁ ብዙዎችም የምን ጾም? እያሉ በፅጌ ጾም ዙሪያ መደነጋገር ውስጥ እንደገቡ ከየመስሪያ ቤቱና ከተለያዩ አካባቢዎች የሚሰሙት ወሬዎች ይጠቁማሉ፡፡  
የፅጌ ጾም በልማድ ጾም የሚባል እንጂ በአጽዋማት ቁጥር ውስጥ ገብቶ እንደማይቆጠር ይታወቃል፡፡ በወርኃ ጽጌም በበዓለ ኃምሳ ካልሆነ በቀር ከዓመት እስከ ዓመት ከሰዓት ቅዳሴ ከሚቀደስባቸው አንዳንድ ገዳማት  በስተቀር ቅዳሴው በጠዋት የሚቀደስ መሆኑና በዚህ ወቅት ጥሉላት ምግብ የሚበላ መሆኑ የጽጌ ጾም የሚባለው ለስሙ ወይም በልማድ እንጂ የታወጀ ጾም ላለመሆኑ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ማቅ 8 አጽዋማት አሉ ብሎ በጽሑፍ የፈጸመውን ስሕተት በጽሑፍ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሽምጥጥ አድርጎ መካድና ነገሩን ጾም ይቀነስ የሚሉ ወገኖች ክስ አስመስሎ ማቅረብን ነው የመረጠው፡፡ እንዲያውም “ለጾም አድሉ ብላ በምታስተምር ቤተክርስቲያን ተጨማሪ ጾም ታውጃላችሁ ተብሎ የቀረበብን ክስ በቤተ ክርስቲያን ጾም በዝቷልና ካልተቀነሰ እያሉ በከንቱ የሚደክሙትን ተሐድሶዎች ሐሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ያስመስለዋል” በማለት ፓትርያርኩን ይወነጅላል፡፡ ጾም በዝቷል ይቀነስ የሚለው ሐሣብ የቀረበው በ2ኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን እንደሆነ ለእስራ ምእት በወጣውና ማቅ በተለይም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል እንዳይሠራጭ ሲያከላክለው የነበረውንና በሱቆቹም ውስጥ የማይሸጠውን “የኢኦተቤ ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ እስራ ምእት” የተባለው መጽሐፍ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ማቅ ግን ይህን ከቤተክርስቲያኒቱ የተነሣውን ማሻሻያ እንደኑፋቄ በመቁጠርና “አድለዉ ለጾም”ን ተከልሎ ጾም ማወጁን ያመነ ሲሆን፣ ከፍ ብሎ ግን “ጾም በቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚታወጅም ጠንቅቆ ያውቃል፤ ያስተምራልም” በማለት የማይታዘዘውን ቀኖና ጠቅሷል፡፡ በአንድ በኩል ለቤተክህነቱ መመሪያና ደንብ እንደሚገዛና እንደማይጥስ ቢናገርም በዚህ ነጥብ ላይ ቤተክህነቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያው የጻፉለትን ማስተባበያ ስጥ ለሚለው ትእዛዝ ተገዢ መሆን አልቻለም፡፡ አሁንም 8 አጽዋማት አሉን ያለበትን ምክንያት በሚገባ ማብራራት ሲገባው ያወጅኩት ጾም የለም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል፡፡ ብሂሉስ “… ከካዱ አይቀር ሽምጥጥ” አይደል የሚለው፡፡ ማቅ በዚህ ጉዳይ ላይ እውነተኛ መሆን ካለበት 8ኛ ጾም ያልኩት በስሕተት ነው ብሎ ማስተባበያ መስጠት እንጂ ያወጅኩት ጾም የለም ብሎ ማወናበድ ተገቢው አልነበረም፡፡   
የሚሰበስበውን ገንዘብ በሚመለከት ጥቂቶችን አነሳ እንጂ ያልተነሱ በርካታ የገቢ ምንጮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ተሐድሶን ለመዋጋት እያለ በየጊዜው በግንዛቤ ማስጨበጥ ስም በየሆቴሉና በየአዳራሹ ከባለሀብቶች ስለሚሰበስበው ገንዘብና ገንዘቡ ስለሚውልበት ቦታ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን የአብነት ት/ቤቶች ስም ስለሚሰበስበው መጠነ ሰፊ ገንዘብም ሆነ ሌሎች የቀረቡበትን ጥፋቶች በተመለከተ በተገቢው መንገድ ማስተባበል ተስኖት ደብዳቤውን የጀመረውና የጨረሰው በሚያስቅም በሚያሳቅቅም ሁኔታ ነው፡፡
በደብዳቤው መጀመሪያ ላይ አንዱ ያቀረበው ብሶት ለሦስቱም ኮሌጆችና ለሌሎችም አካላት ግልባጭ ሲያደርጉ ለእኔ አላደረጉልኝም የሚል ነው፡፡ የተማረ ስብስብ ነኝ የሚለው ማቅ ይህ እንዴት ሳይገባው ቀረ? ቅዱስነታቸው እንዳሉት ማኅበሩ በተግባር እየተመራ ያለው ያለ ህገ ደንብ ነው፣ መተዳደሪያ ደንቡም ቢሆን ራሱ እንዳመነው በአየር ላይ ነው ያለው፡፡ አካል ለሌለውና በቤተ ክርስቲያኒቱ አእምሮ ለተበተነ ማህበር ምን ብለው ግልባጭ ያድርጉ? ለመሆኑ እርሱስ ማን ስለሆነ ነው ግልባጭ የሚደረግለት? በቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ ይቅር የማይባል ሥራ እየሠራ ያለ አካል ሆኖ ሳለ ግልባጭ ስላልተደረገልኝ አዝኛለሁ እንዴት ይላል? ይህ ማቅ የሌለውንና ለራሱ ግን የሚሰጠውን ትልቅ ቦታ ነው የሚያሳየው፡፡
ሌላው የሚገርመው ጉዳይ የማቅ ደብዳቤ “የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ እንኳን ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲህ ዓይነት ብያኔ በእርስዎም በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ በከፍተኛ ሁኔታ አሳዝኖናል” ማለቱ ነው፡፡ ይህ ሐሣብ በአንድ በኩል ማቅ ራሱን አለቅጥ ቆልሎ ያስቀመጠበትን ቦታ ሲያሳይ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለእርሱ እንዲደረግለት የሚፈልገውን እርሱ ለሌላው ሳያደርግ የቀረ መሆኑን ለአፍታም እንኳን ማሰብ እንዳልፈለገ ነው፡፡ ማቅ በተከታታይ የጥፋት ጣቱን በሦስቱም ኮሌጆች ላይ ሲቀስር አስቀድሞ የትኛውን የኮሌጅ አካል ጠርቶ ወይም ሄዶ እንዲህ ላደርግ ነውና ምን ይመስላችኋል? ሲል መቼ አወያየ? ደግሞስ በጋዜጣው ኮሌጆቹን ከተሳደበ በኋላ ማስተባበያ ስጥ ተብሎ በተለይ ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ የተጻፈለትን ደብዳቤ ውጦ ዝም አለ እንጂ መቼ ማስተባበያ ሰጠ? ይህ ሁሉ ማቅ እየሄደ ያለው በትዕቢትና በአልታዘዝ ባይነት እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩ “ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም፤ አባቶችን ይዳፈራል” ብለው መጻፋቸው አንድም ስሕተት የሌለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡   
ማቅ በደብዳቤው ላይ እንደገለጸው በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ኮሌጆችን የሚያጠና ኮሚቴ መቋቋሙንና በማስረጃ የተደገፈ ጥናት አጥንቶ እንዲያቀርብ መታዘዙን ተከትሎ ይህን ዘገባ እንዳወጣ ገልጾአል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማቅ ምን አግብቶት ነው የኮሚቴውን ሥራ ነጥቆ ኮሚቴው በራሱ መንገድ እንዳያጠና በጥናቱ ላይ ጥላ የሚያጠላ ሦስቱም ኮሌጆች የመናፍቃን መፈልፈያዎች ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰው? ይህ እንግዲህ ለምሳሌ አንድን የተጠረጠረን ሰው ተጠርጣሪ ከማለት ይልቅ ወንጀለኛ ነው ብሎ ከመዘገብ ያልተለየ በፍርዱ ላይም ጫና ለማሳደር የሚቀርብ ዘገባ ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ምናልባትም የተቋቋመው ኮሚቴ የሚያደርገው ጥናትና የሚያቀርበው ድምዳሜ ማቅ ከሚለው የተለየ ሆኖ ቢገኝ እንኳን እኔ ያልኩት ካልሆነ ጥናቱ የተሳሳተ ነው ለማለት ነው አስቀድሞ በኮሌጆቹ ላይ እንዲህ የጻፈው፡፡ ታዲያ “የ… ጭንቅላት እስኪበስል ማገዶ ይፈጃል” የሚለው ተረት ለማቅ አይስማማውምን?
ማቅ በኮሌጆቹ ላይ ለጻፈው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከመጸጸት ይልቅ ትክክል እንደሆነና የከሰሱት ኮሌጆቹ ሆነው ሳለ አሁንም ግን ጥቂት የተሐድሶ አራማጆች እያለ እንደሚጠራቸውና ፓትርያርኩም እነርሱን “በርቱ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት” ያሉ በማሰመሰል በደብዳቤው ግልጽ አድርጓል፡፡ የቀረበው ክስ ማቅ እንዳለው ሳይሆን የኮሌጆቹ ነው፡፡ ታዲያ ምነው የከሰሱት ኮሌጆቹ መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ እርሱ ግን “የተሐድሶ እምነት አራማጆች” ሲል በሐሳቡ የፈጠራቸውና በጉዳዩ ውስጥ የሌሉ አካላት እንደከሰሱት አስመስሎ ለምን ጻፈ? እዚህ ሁሉ ውዝግብ ውስጥ ከሚገባ ኮሌጆቹን አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ ቢል የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ እዚህ ደረጃ ላይም አይደረስም ነበር፡፡
ሌላው ማቅ ለማሳመን አይሉት ለመከላከል ወይም መልስ ለመስጠት ግራ የገባው ጽሑፋዊ ምላሹ ስለ ማህበራት ያቀረበውና ማቅ “ከራሱ ውጪ ለየትኛውም ማህበር መቋቋም ኃላፊነት የለበትም” ማለቱ ነው፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ “ለእነዚህ ማህበራት መቋቋም በጐ አመለካከት ቢኖረንም” ይላል፡፡ እንደ ገና መልሶ “ቤተክርስቲያን የማታውቀውና በቤተክርስቲያንም ሥርዓት የማይመራ ማኅበር ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው” ብሏል፡፡ ታዲያ የቱን እንመን? ማቅስ የቆመው የቱ ጋ ነው? ፓትርያርኩ ግን በመረጃ ላይ ተመሥርተው ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ ለሚሄዱ የመንደር ማህበራት መቋቋም ተጠያቂው ማቅ ነው ብለዋል፡፡ እውነት ነው፡፡ የጥምቀት ተመላሾችን ያደራጀ ማን ነው? የቅርቡን “ፍኖት ዘተዋሕዶ”ን ለማቋቋም መንገድ ጠርጐ የነበረው ማን ነው? በዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማህበረ ፅዮን ተብለው በጠበል ቤት ውስጥ የሚማሩት በእነማን ቡራኬ ነው የጀመሩት? የማቅ አባላት ተገኝተው የማያስተምሩበትና መመሪያ የማይሰጡበት፣ ድንጋይ ወርውሩ የማይሉበት የመንደር ማህበር ከቶ የትኛው ነው? ቤተክርስቲያኒቱ አባት የላትምና እንደግብጾች አባት ሰጣት ብለው ያላስተማሩበት የመንደር ማህበር ይገኛል ወይ? ዋልድባ ተደፈረ፣ የዝቋላ ገዳም ተቃጠለ ብለው ወጣቱን ለአመፃ ያላነሳሱበት ማህበር አለ ወይ? የአባይነህ ካሴ፣ የያረጋል አበጋዝ፣ የብርሃኑ አድማስ፣ የታደሰ ወርቁ ውሎ የት ነው? ማህበሩ የወለዳቸው የመንደር ማህበራት ውስጥ አይደለምን? እነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያን የማታውቃቸውና በቤተክርስቲያንም ሥርዓት የማይመሩ ማኅበራት ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም እያለ በተግባር ግን ከጀርባ ሆኖ ማደራጀቱና ድጋፍ መስጠቱ ራሱ በደብዳቤው እንደገለጸው ቤተክርስቲያንን ለመጉዳትና የእርሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ካልሆነ ሌላ ምን ትርፍ አለው?
ማቅ በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ “ለአባላቱ በጅምላ ክህነት እያሰጠ ብለው መግለጽዎ በምን ምክንያት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡” ማለቱ የሚጠቀስ ሌላው ነጥብ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ምን አጠፉ? ይህ እኮ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው፡፡ ለዚያውም በአየር ላይ በሚደረግ ቡራኬ የጅምላ ክህነት የሚሰጠው ለማቅ አባል አይደለም እንዴ! እንደ አባ ኤልያስ አይነቶቹ በማቅ ነውራቸው ለጊዜው “የተሸፈነላቸው” ጳጳሳት ዘወትር የሚያደርጉት እኮ ነው፡፡  አምና አርባ ምንጭ ላይ የተመረቁ ከ280 በላይ የሚሆኑ የማቅ አባላት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጅምላ ክህነት ከአባ ኤልያስ መቀበላቸው የአደባባይ ምስጢር ነው እኮ፡፡ እርግጥ ማቅ የጅምላ ክህነት ለአባላቱ ማሰጠቱን አላስተባበለም፡፡ ነገር ግን የማቅ “ቀሳውስት” አሐዱ አብ ብለው የማይቀድሱ ዲያቆናቶቻቸውም “ተንስኡ ለፀሎት” የማይሉ መሆናቸውንና በግብጻውያን ዘመን እንደነበረው ዛሬም የጳጳስ ዕጥረት ያለ ይመስል ላያገለግሉበት ለአባላቱ ክህነትን በጅምላ ማሰጠቱ ከቶ ለምን እንደሆነ መመለስ አልቻለም፡፡ እንዲህ እያደረገ ያለው ያው ቅዱስነታቸው እንዳሉት “ለድብቅ ዓላማው መስፈጸሚያ” ነው፡፡
የሚገርመው ግን በጅምላ ክህነቱ ዙሪያ ማቅ ተጠያቂ ለማድረግ የሞከረው ራሱን ወይም የጅምላ ክህነት ተቀባይ አባላቱን ሳይሆን ክህነት ሰጪዎቹን ጳጳሳት ነው፡፡ እንዲህ በማለት “መቼም ክህነት የሚሰጠው በእናንተ በብፁዓን አባቶች እንጂ በሌላ አካል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ታዲያ በዚህ ጉዳይ ቀኖና የጣሰው ማነው ለማለት ነው?” ሲል ተጠያቂዎቹ ራሳቸው ጳጳሳቱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ይህ በአንድ በኩል እውነት ነው፡፡ ላይቀድሱበት ወይም ተገቢውን አገልግሎት ላይፈጽሙት በጥቅም ተጠልፈው ለእነርሱ የጅምላ ክህነት የሚሰጡ ጳጳሳት ተጠያቂዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡
ቀጥሎም “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈፀመ ይገኛል ያሉን በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ ተሰጥምቶናል” ብሏል፡፡ በብዙ አቅጣጫ ሲፈተሽ ማቅ ብዙ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እያደረሰ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ማቅ ከተመሰረተ ወዲህ የታየው ነገር ሁሉ ቤተክርስቲያኗ በዘመኗ አይታ የማታውቀው ጥፋት ነው፡፡ ከፍ ብለን ካነሳነው የጅምላ ክህነት ጋር በተያያዘ እንኳን እንናገር ብንል ከወለዱ በኋላ ክህነት የተቀበሉ የማቅ አባላት በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም አሉ እኮ! ይህን ታሪክ ይቅር ይለዋል? እነ በላቸው በሁለት ሚስት ክህነት ተቀብለዋል፡፡ እሸቱ ወንድም አገኘሁ ከ10 በላይ ሴቶችን ደፍሮ (ጉዳዩ በፖሊስ ፕሮግራም መተላለፉ ይታወሳል) አሁን ግን ቀኖና ቤተክርስቲያንን በጣሰ መንገድ ቅስና ተቀብሎአል፡፡ እነ ሰሙ ምትኩ፣ እነ ሙሉጌታ ከጋብቻ በፊት ክህነት እንደ ተቀበሉ/እንደ ቀሰሱ ይነገራል፡፡ አባይነህ ካሴ ከሠራተኛው ጋር ሲማግጥ ተደርሶበት በዚህም ምክንያት ከሚስቱ ጋር ተለያይተው የወለዷቸውን ልጆች ተከፋፍለው ባሉበት ሁኔታ “በክህነቱ” እየተጠራበት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ማኅበሩ ሲነሳ ታሪክ ይቅር የማይላቸው የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና የጣሱ ተግባሮች አይደሉም ወይ? ማህበሩ የራሱን ፓትርያርክ በህሊናው እንዳስቀመጠስ በዜና ቤተ ክርስቲያን ተዘግቦ የለም ወይ?
ማቅ ለሃይማኖቴ ዘብ ቆሜያለሁ እያለ በሚለፍፍበት ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የምእመናን ፍልሰት በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በዋናነት ማቅ የሚሠራው የማሳደድ ሥራና የሚሰብከው ተረታተረት ብሎም ዘወትር ተሐድሶ መናፍቃን የሚለው የጥላቻ ትምህርቱ ነው፡፡ የሕዝቡን ፍልሰት ለመግታት መፍትሔው ስብከተ ወንጌልን ማጠናከር ቢሆንም ማቅ ግን በርካታ ሊቃውንትንና ወንጌል ሰባኪዎችን ተሐድሶ መናፍቅ እያለ በመክሰስ እንዲባረሩ ማስደረጉና በምትኩ ወንጌል ሳይሆን ተረታተረቶችና እንዲሁም ተሐድሶ መናፍቃን እንዲህ ናቸው፣ እንዲህ አደረጉ … የሚለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ብዙዎች ቃሉን የተጠሙና ተረትና በጥላቻ የተሞላ ትምህርት መስማት የሰለቻቸው ምእመናን ቤተክርስቲያኑቱን ትተው ወደሌሎች እንዲሄዱ ያደረገ ምክንያት ነው፡፡ ማቅ ተሐድሶ መናፍቃን ካላለ ህልውና ያለው እስከማይመስል ድረስ እንዲህ ማለቱን የዘወትር ወንጌሉ አደርጎ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ በሰጠው ምላሽ እንኳ ፓትርያርኩ በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመሥርተው ላቀረቡት ትክክለኛ ማንነቱ ተገቢውን ማስተባበያ ወይም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ተሐድሶ መናፍቃን እያለ በየቦታው የተለያየ ነገር አንስቷል፡፡ አንድ ማኅበር ዘወትር ከሳሽ ብቻ ሆኖ እንዴት ሊቀጥል ይችላል? ዘወትር ተሐድሶ መናፍቃን ማለትን ለህልውናው መሠረት አድርጎ እንዴት ይኖራል? በዚህ አንጻር ቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንትና ምእመናን አልባ እያደረጋት በመሆኑ ታሪክ ይቅር የማይለው ድርጊት ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው፡፡
ለመንፈሳዊነት ነው የተቋቋምኩት ብሎ ፖለቲካ የሚያካሂድ ማህበር ከእሱ ውጪ ማን አለ? ጳጳሳቱን እርስ በርስ የሚያጋጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን አህሎ በእስዋ ቁመና መዋቅር የዘረጋን ማህበር ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? በጣሊያን ወረራ ጊዜ እኩል የተገደሉና ስለ አገራቸውና ስለ ሃይማኖታቸው ሰማዕትነትን የተቀበሉት አቡነ ሚካኤል እና አቡነ ጴጥሮስ ቢሆኑም፣ የሸዋ ተወላጅ ስለሆኑ ብቻ ለአቡነ ጴጥሮስ ጽላት ሲቀረጽ ቤተ ክርስቲያን ሲታነፅ ተግቶ የረዳ ገንዘብ ያሰባሰበ ዘረኛ ማኅበርን ታሪክ እንዴት ይቀር ይለዋል?
አቡነ ቴዎፍሎስን አስይዘው፣ አሳስረው፣ አስገድለው፣ በተሰወረ ቦታ እንዲቀበሩ ያደረጉ ሰዎች የወለዱትንና ያንኑ ሊቃውንትን የማሳደድና የማንገላታት ግብሩን የገፋበትን ማህበረ ቅዱሳንን ታሪክ እንዴት ይቅር ይላቸዋል? የክርስቶስ ንፅህና ከድንግል ማርያም የተነሣ የተገኘ ነው ብሎ የጻፈ አባል ያለበትንና ኑፋቄው በጽሑፍ እንዳይታረም እስካሁን ድረስ በአባ ማቴዎስ በኩል አዳፍኖ ያለውን፣ የቤተክርስቲያንን ሃይማኖት በተረታተረት በመተካት ወደር ያልተገኘለትን ማህበር ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? የመንግስት ሥልጣን ከአንኮበር፣ ፓትርያርክ ከደብረ ሊባኖስ ብቻ መውጣት አለበት ብሎ የሚያምንን ዘረኛ ማህበር ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? ኮሌጆቹ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው እኔ ያቋቋምኩት ውስጥ ብቻ ነው እውነተኛ ትምህርት ያለው ብሎ ራሱን የገለጠውን ተመጻዳቂና ጽንፈኛ ማህበርን ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? አገለግላለሁ ብሎ በቅንነት የገባውን ማህበርተኛውን የሚሰልልና በስለላ የቆመውን ማህበር ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? ለቤተ ክህነት መመሪያና ደንብ አልታዘዝ በማለት ለብዙዎች መጥፎ አርአያ የሆነውን ማህበር ታሪክ እንዴት ይቅር ይለዋል? ብቻ ስንቱ ተዘርዝሮ ያበቃል? ማቅ ምን ያልፈፀመው የታሪክ ጥሰት አለ?
በጣም አስቂኝ ነገር በደብዳቤው መጨረሻ የሰፈረው ተማፅኖ ነው፡፡ “አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን እንድታደርጉልን ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን በፍፁም ትህትና እንጠይቃችኋለን” ይላል፡፡ በቅድሚያ እንዲህ ይባላል ወይ? ምናልባት እንዲህ ያለው ጳጳሳቱን በውዳሴ ከንቱ ለመጥለፍ አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ያነበቡ ሰዎች ጳጳሳት ተሰቅለው ነበር ወይ ብለው ሊጠይቁ እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ ማቅ ወትሮም ቢሆን ነገረ መስቀሉ በልቡ ውስጥ የለም እንጂ ቢኖር ኖሮ ከእግረ መስቀሉ ሥር መቆም የሚለው ሲታሰብ በመስቀሉ ስር ቆመው የነበሩትን ዮሐንስንና ማርያምን የሚያስታውስ አነጋገር ነው፡፡ እንዲህ ብሎ ለጳጳሳት መናገር ምንም መሠረት የሌለው አነጋገር ነው፡፡ ይህን አነጋገር ለደብዳቤ መዝጊያ ማድረግም መቀበልም ስሕተት ነው፡፡ ያው እንግዲህ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ጳጳሳትን ሰቅሎ አረፈው፣ ከእግረ መሰቀላችሁ ሥር ወድቄአለሁ ብሎአልና፡፡ ለዚህ ነው በብዙ ሕጸጽ የተሞላህ ነህና ታረም፣ ተስተካከል የሚባለው ስለዚህ ነው፡፡ በአጠቃላይ ማቅ ራሱን ካላስተካከለና ወደትክክለኛው መስመር ካልገባ ቀጣዩ እርምጃ የከፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

56 comments:

 1. ይገርማል እንዲህ አይነት ባዶ ሀሳብ ይዞ ወደ ህዝብ መቅረብ….. ማኅበረ ቅዱሳንን የምናውቀው በወሬ ሳይሆን በተግባር ነው…….

  ReplyDelete
 2. እናንተ የአሪዎስ ቅሪቶች ምንም ብታወሩ ማኅበረ ቅዱን የቤተክርስቲያን ቅን አገልጋይ ወንድሞች እና እህቶች ስብስብ መሆናቸውን በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያን ላለን ምእመን ቀላል ነው…. ደስ የሚለው ማኅበረ ቅዱሳንን በደንብ እንድናውቀው፣ እንድንደግፈው፣ ጠላቶቹ የነማን ወገን መሆናቸውን እንድንለይ ለምትሠሩት ሥራ ሳለመሰግን አላልፍም

  ReplyDelete
 3. ከማን ለማን እንደተጻፈ እንኳን የማይገልፅ ጭፍንና ለቤተክርስቲያን ያላችሁን ጥላቻ ከሚገልጥ ውጪ ተራ የቃላት ድርድር ነው፡፡
  እንደናንተ ሆድ ዓምላኩ ለሆኑ ሳይሆን የጽጌ ፆምን በፈቃድ ለሚፆሙ ቀኑን መንገር ሕገ-ቤተክርስቲያንን መጣስ ዓይደለም ፡፡
  ባንድ በኩል ህልውና የላችሁም ትላላችሁ በሌላ በኩል ህልውናቸውን አምናችሁ ተራ የማብጠልጠል ወሬያችሁን ትነዛላችሁ፡፡
  ይልቅ የሳታችሁ ሰይጣን እንዳይታዘባችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የናንተ የተሃድሶዎች አላማ ብትችሉ ሙሉ በሙሉ መረከብ ያለዛም እንደ ህንድ ቤ/ክርስቲያን ለ2 በመክፈል ለፕሮቴስታንት ከዛም እንደ አዉሮፓና አሜሪካ ለሳይጣን አምላኪዎች አሳልፎ መስጠት ነዉ ግን ምን ዋጋ አለዉ
   እነዛ የቁርጥ ቀን ልጆች ማህበረ ቅዱሳኖች ነቁባችሁ ስራችሁ ሁሉ በመድሎተ ጽድቅ ዝርዝር ብሎ አይተነዋል::ብቻ ያን መጻፍከምታነቡ መሬት ተከፍታ ብትዉጣችሁ ይሻላል::

   Delete
 4. በጣም ጥሩ ትንታኔ ነው የሰጣችሁት፡፡ የማቅን ባዶ ደብዳቤ ይበልጥ ባዶ ነው ያስቀራችሁት፡፡ መቼም የማቅ ደጋፊዎች የሥድብ ናዳ እንደሚያወርዱባችሁ ጠብቁ፡፡ ይህ የሚያሳየው ጽሁፉ በቂ ምላሽ መስጠቱን ነው፡፡ በርቱ ይበል ብለናል

  ReplyDelete
 5. አሳማዎች ሆይ የምትጮሁት አጣችሁ ካልሆነ እኛ የቤተክርስቲያንን ድምጽ እናውቃለን

  ReplyDelete
 6. የሀሰት አባት የሆነው የሳጥናኤል ቅሪቶች ከዚህ የተሻለ ጉዳይ መናገር የሚችል አቅም አይኖራችሁም ምክንያቱም ከጹህፋችሁ እንደምንረዳው እናንተ የያዛችሁት ክህነት ከመሠረቱም የውሸት ነበር ማለት ነው ( የዚህ ብሎግ ቋሚ ጸሓፊዎች የምናውቃችሁ ቤተክርስቲያን ጉያ ውስጥ ያሉት ተሐድሶዎች እና ሙሰኞች) ካልሆነ ይህን ማሰብ ባልቻላችሁ ነበር፡፡ እኔ እስከ ዛሬ በጥቅም የተቀየራችሁ ነበር የሚመስለኝ ከመጀመሪያው ነው አስባችሁ የገባችሁበት ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. እኔ የሚገርመኝ አንዴ ፆም አያስፈልግም አሁን ደግሞ ለምን ተጨመረ ትላላችሁ፡ አንዴ አቅሙን አያውቅም ሌላ ጊዜ ቤ/ያንን አክሎ ትላላችሁ ለፍርፋሪ ብላችሁ አትዋረዱ። የማህበሩ አባላት ግን ታድላችሁ ለቤ/ያን ጠበቃ በመሆናችሁ

  ReplyDelete
 8. የቤተክርስቲያኗ ካህናቶች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ካላገለገሉ በስተቀር በቅርብ ግዜ ኦተቤክ ባዶዎን ትቀራለች። ለማስረጃ ያህል የነብይ በላይ ሽፈራው፥ ሱራፊል ደምሴ፥ ታምራት YouTube ተመልከቱ። ሰው ሁሉ ቤክ እየለቀቀ ነው እውነትንና ፈውስን ፍለጋ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም በናይጄርያ አንደ የወገኖችህ የፕሮቴስታንት ቸርች ውስጥ ነብይ ልክ እንደ ነብዩ በላይ ሽፈራው እና ሱራፈኤል ታምር ብሎ ሳር ያስበላቸውን እና አስር ቤት የገባውን ነብይ ታሪክ በዩትዩብ እንድት መለከተው ስጋብዝህ የተለየ ሀሳብ በውስጤ ሳይኖር ላንተ ለወንድሜ የቆምክበት አሸዋ መሆኑን እንድትገነዘብና እንድታይ መሆኑን ለማስረዳት ሲሆን እግዚአብሔር ታይና ትገነዘብ ዘንድ ይርዳህ ፡፡

   እውነትም ህይወትም ክርስቶስ ኢየሱስ ነው እንጂ ማንም ቸርቻሪ ፓስተር አይደለም አንተ መናፍቅ

   Delete
 9. ይበል አንጀት አርስ ጽሑፍ ነው። በርቱ ቃለ ህይወት ያሰማልን እድሜ ይስጥልን።

  ReplyDelete
 10. ለመሆኑ የማቅ አባለት ማን ሆነው ነው ለፓትራርኩ መልስ የምሰጡት? ኤረ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች ይህ አስመሳይ እና በቅዱሳን ስም እየነገደ ያለው መናፍቅ የሆነ ድርጅት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መነቀል አለበት። የማቅ ተከታዮች እራሳቸው መናፍቃ ናቸው። የአንድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባት ከፍ ዝቅ እያደረጉ ማዋረድ መስደብ ማናፍቅነት ነው። ሥርዓት አልባነት ነው። በእውነት እንነጋገር ማቅ ይህን ያህል ገንዘብ ለኦርቶዶክስ ቤተ ከርስትያናችን ሰጠ እየተባለ በእነርሱ ወብ ሳይቶች ስጻፉ እያየን ነው። ማን ሆነ ነው ይህ ማህበር ገንዘብ የምረዳው? ማቅ መጽሐፍ ቅዱስን አሳትሞ አወጣ ተብሎ ስነገር በጣም የምያሳዝን ዜና ነው። ቅዱስ ስኖዶስ በሀገርቱ ላይ የለም ማለት ነው? ወይንስ ምንድነው ነገሩ? የቤተ ከርስትያናችን ሥርዓት እያፈለሰና እያፈረሰ ያለው ማቅ ነው። የእን ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው በደንቬር ኮሎራዶ ያለው ቤተ ክርስትያን ገሌልተኛ ነው። ይህ ሥርዓተ ቤተ ከርስትያንን ማደስ ማፍረስ አይደለምን? ሥርዓተ ቅዳሴን ሽረው ወይንም አሻሽለውት የፓትራርክና የሊቀ ጳጳሱም ስም አይጠራም። በላስ ቬጋስ የሚገኘው የእነ አባ ገ/ኪዳን ቤተ ከርስቲንም በማመጽ በቅደሴ ግዜ የፓትርያርኩ ስም አይጠራም።ይህ ስርአተ ቅዳሴን ማደስ አይደለምን? ለምን ስለ ኦርጋን እንጨነቃለን። ዋናው የቅዳሴ ሥርዓቱ በማቅ ተሽሮ የለምን? ምነው ዝም አላችሁ? ወዬ ጉድ ጉድ የማቅ ጥፋት እጅግ ብዙ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያው ቅዱስ ስኖዶስ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ አለቤት። ቢሮው በአስቸኳይ መዘጋት አለበት። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አንድት ናት። የውጪውም ስኖዶስ በአንድነት የማቅ ክፉ ስራ በማጋለጥ ህዝበ ክርስቲያኑን ማስተማር አለባቸው። የማቅ አባለት ምን ሥርዓተ ቤተ ከርስትያን ነው የምያስተምሩን ? መልስ ከሁላችሁም እፈልጋለሁኝ። ሥርዐተ ቅዳሴ መሻር ወይንስ በኦርጋን መዘመር የበለጠ ሥርዓትን ያፈረሰው ?

  ReplyDelete
 11. ተሀድሶዎች ሆዳቸው አምላካቸው

  ReplyDelete
 12. ተመቶ የማያዉቅ ጥጃ ሲይዙት ያጋጉራል አንደሚባለዉ ማህበረ ቅዱሳን ለረጅም ጊዜ ሀይ ሳይባል ስለቆየ
  ኣሁን ሀይ ሲባል መንፈራገጥ ጀመረ
  ማህበረ ቅዱሳን በአዉነት በአዉነት የክፉወችና የከሳሾች ሰብስብ ነዉ ።

  ReplyDelete
 13. The flame of the torch of 'TEHADISO' is way far away to be extinguished. I think what is better for MK is to get out of the way!

  To Aba Selama people, I want to say the following:
  Many people (those who don't shout empty words) are now seeing the real truth; many people, sick of MK, are now finding consolation in Aba Selama Blog. So,don't ever be discouraged by people crying "tehadiso menafikan" regardless of their number. Because, they don't matter much. They never have. God bless you!

  ReplyDelete
 14. የምትገርሙ ርጉም ፍጥረቶች ናችሁ። ምንም ይሁን ምን ቤተ ክርስቲያንን ለፕሮቴስታንት አሳልፋችሁ ለመስጠት የምታደርጉት ጥረት እያማራችሁ ይቀራል እንጂ አታገኛትም። የማያንቀላፋ አምላክ ስለሚጠብቃት። ማኅበረ ቅዱሳንን ሁሉም ስለሚያውቀው በከንቱ አትልፉ ። እነርሱ ዝም የአባታቸውን የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን ቃል ጠብቀው እየሰሩ ነው ያሉት። እንዲህ ብለው የተናገሩትን ቃል አክብረው። "  ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ፦ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን:: ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ ይጨቃጨቅ፡ተወው ፡አንበሳው ሲያገሳ ፍንክች አትበል የሰይጣንን ውሻዎችን ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎችን በማባረርም ጊዜህን አታጥፋ።ሥራህን ሥራ፦ ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፤ ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ። አንተ ግን እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈፀም ምንም ነገር እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።"

  ReplyDelete
  Replies
  1. የማህበረ ቅዱሳን አባል ነህ ወይንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶሰክ አባል ነህ/ነሽ ?

   Delete
  2. Ye "aba" serekena ye hama zeroch bitasibubet ?? Seif lay komachhol!!?

   Delete
  3. ዝም ብለው ይሰራሉ የምትለው ከእወነት የራቀ ነው። በስማ ጽድቅ ጋዜጣቸው ስም ያጠፉት እነርሱ አይደሉም? ነገር ቆስቋሹ እነርሱ ሆነው እያለ ዝምተኞች ናቸው ትላለህ? ዝምታ ምንድን ነው?

   Delete
 15. As a orthodox tewhado church followers we all know about your wrong missions to destroy our church real teaching so that doesn't be mindles....hope MK will continue his hard work better than before

  ReplyDelete
  Replies
  1. Brother, first you have to understand between Mk and Orthodox tewahedo church difference. Instead of believe in God you worshiping Mk. All MK members are allergic to holy bible and name of Jesus Chris. Our Othodox church members never trust Mk. pls do not waste your time with MK. Our orthodox Tewahedo church members understood about Mk never believe in Holy God.

   Delete
 16. Amlake Esrael, Enatachen kedist dengel maryam, kidusan melaket BETKRSTIYANACHNEN ena MAHIBER KIDUSANEN yetebekelen enanten mastewal yestelen

  ReplyDelete
 17. ማቅ ምን ያህል በትዕብትና ትምክት ያለ ቅዱስ ስኖዶስ ፈቃድ የሚሰራቸው ሥራዎች። ይህ ሁሉ በንግድ የሰበሰበውን ገንዘብ እንደ አንድ የእምነት ተቋም ለቤተ ክርስትያናችን እርዳታ የሚወጠው። በማቅ ድህረ ገጽ ላይ ከወጣ የተወሰደ ነው (ሐራ ተዋህዶ)
  ማኅበረ ቅዱሳን: የኦርቶዶክሳዊነትን ዓለም አቀፋዊነትና በቤተ ክርስቲያን የምእመናንን ድርሻ የሚያስገነዝብ ዐውደ ርእይ ያዘጋጃል

  February 6, 2016 Comments: 7
  ከመቶ ሺሕ በላይ ተመልካቾች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል
  ኦርቶዶክሳዊ ክውን ጥበባት ልዩ ገጽታዎቹ ይኾናሉ ተብሏል
  ለአጠቃላይ ዝግጅቱ ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል
  የዐውደ ርእዩ መሪ ቃልና መለዮ ዛሬ በማዕከሉ ጽ/ቤት ይፋ ይኾናል

  ReplyDelete
 18. International Journal of Workplace Health Management

  ReplyDelete
 19. LONG LIVE MK!!!!!

  ReplyDelete
 20. we have mind. we can judge everything. so don't tell what we already have read. we can distinguish truth. you guys are doing your father's work. HE is the father of lie. You're saying the Ethiopian orthodox tewahido church is wrong and you now say we are the members of Ethiopian orthodox tewahido church. this is self contradictory. please repent and be on the right way

  ReplyDelete
 21. ፍርዱን ለዘላለም አምላክ ለእግዚአብሔር እና ለታሪክ ልተወዉ
  አባ ሠላማ ብሎ ሥድብ፣ ጥላቻን ፣ነቀፋን ፣መከፋፈልን ፣የሰዉን ገመና መግለጥ (ሊያዉም እዉነት ከናንተ ባይገኝም እንኳ ልብ አድርጉ እግዚአብሔር ነዉራችንን ሸፍኖ ለንስሃ እድሜ የሚሰጠንን ግለሰብ ማለቴ ነዉ) ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት (የቱንም ያህል ቢሄድ ከቶዉንም አይቻለዉም እንጂ) ቆርቶ ከተነሳ የመጨረሻዉ ዘመን የአዉሬዉ መንፈስ አራማጆች ጋር ምን እዉነት አለ?እስቲ ልጠይቃችሁ ማስተዋል ካላችሁ
  1. አሁን እናንተ ተሀድሶ የሚለዉን የጥፋት አላማችሁን እና መጠሪያችሁን ይፋ ከማድረጋችሁ ቀደም ብሎ ማህበረ ቅዱሳን ቀድሞ አላወጣዉምን?
  2. ተሃድሶ የሚባሉትስ ግለሰቦች ይህ የጥፋት አላማችሁ አራማጆች አይደሉምን? ያልሆኑ አሉ?
  3. የብዙ አባቶችን ገመና በተደጋጋሚ ይህን ሰሩ እያላችሁ ለንባብ አላቀረባችሁምን?የእናንተን አላማ የሚሳካ እስከመሰላችሁ ድረስ የማትሄዱት ርቀት የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ያኔ የምን ወንጌል ምድራዊ (ሠይጣናዊ ጀብደኝነት ነዉ አንግባችሁ ያላችሁት)
  ልብ ይስጣችሁ ሌላ ምን እላለሁ፡፡

  ከቶ ከናንተ ምን እዉነት አለ???

  ReplyDelete
 22. ይገርማል ዝም ብሎ መጽለይ ይሻላል አሁን እናንተ በእውነት ሃይማኖት ያለው ሰው ምግባር አላችሁ ለመሁኑ።እኛ ማእመናን ልቅም አድርገን አውቀናችኋል እራሳችሁን ደብቃችሁ የተሃድሶ ድርጂት ስራ አስፈጻሚዎች ሃይማኖታችሁን በገንዘብ የሸጣችሁ።እንደው በጥቅሉ ያው እነ ፓስተር ጋር አዳራሻችሁ ለምን አትዘሉም።እናንት ይህን ያህል የይሁዳ ታባባሪዎች ሁናችሁ ሰው ስታሳድዱ ሰው ስትሳደቡ።ስራ አጦች ነገር አቀባባዮች ቅጥረኞች ለስው መሰናክል እየሁናችሁ ነው ተመለሱና በንስሃ እራስችሁን በቤቱ አኑሩ እግዚያብሄር ሃያል ነው ለንስሃ ጊዜ ዛሬን ሰጥቷችኋል።ተጠቀሙበት ምንም እያተረፋችሁ አይደለም።እንደው በከንቱ በስድብ ወንድሞቻችሁን እያሳደዳችሁ እስከመቼ።ከአባቶች ክብር የእግዚያብሄር ክብር ይበልጣል የሜገርመው ለቅዱሳን ክብር የማትሰጡ ስወን ለሚያሰናክሉ አባት አባቶችን ትላላችሁ።አዎ እንደክርስቲያን በታላቅነታቸው ሊከበሩ ይገባል እንደስራቸው ግን እግዚያብሄር ይፍረድ።እርሱ በቃሉ ተናግሮታልና አንድም ሰው መሰናክል ሊሆን እንደማይገባው።አትሞኙ እኛ ናናያችሁ የግብዞችን ስራ እየሰራችሁ እንደሆን አምላክ ያያችኋል።ስራ ስሩ ስራ ስሩ እነዚህ እንዲህ የምተስድቧቸው ማህበረቅዱሳን ስራ እየሰሩ ነው የግድ ነው ስራ ሳይሰሩ እንደው አካኪ ዘራፍ አይሰራም በሃይማኖት ድርድር የለም እስከዚህ ድረስ ነው።አዎ የስልጣን ችግር አለባችሁ የፓለቲከኝነት ችግር የገንዘብ ወዳድነት አብሶ አብሶ አብሶ ዘረኝነት። እነዚህ ችግሮች አሉባችሁ።ከሱ ሁሉውጡ ለነፍሳችሁ ጸለዬ ልንገራችሁ መልካም እረኝ ቢኖረን ማ እርስ በርሳችን እንዲህ ባልተሰዳደብን ነበር እነሱ ለራሳቸው ስልጣን እኛ የዲያብሎስን ስራ ያሰሩናል ወንድሞቼ እህቶቼ ጊዜ መሽቷል ለራሳችሁ ትጉና ጸልዪ ሌላውን ለእግዚያብሄር እናድርግ እግዚያብሄር አምላካችን ሰላማችን ይስጠን አንድ ያድርገን ሃይማኖት አንዲት ናትና ሰላም ሁኑልኝ

  ReplyDelete
 23. Waw what an article

  ReplyDelete
 24. አንተ ሌባ አረሆ ሲጀመር የማህበሩ ዲቃላ ስለሆናችሁ እንጂ ዉነቱ የት እንዳለ ጠፍቶዋቸው አአይደለም። ማቅ
  እኮ አላማው ሌላ ነው። አባ ሠላሞች አአይዣችሁ በርቱ
  የማቅን አፍና ስድብ ፈርቶ እንጂ ፻ በ ፻ ህዝቡ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር ነው There Is time for everything

  ReplyDelete
 25. በጣም አስቂኝ ነገር በደብዳቤው መጨረሻ የሰፈረው ተማፅኖ ነው፡፡ “አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን እንድታደርጉልን ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን በፍፁም ትህትና እንጠይቃችኋለን” ይላል፡፡ በቅድሚያ እንዲህ ይባላል ወይ? ምናልባት እንዲህ ያለው ጳጳሳቱን በውዳሴ ከንቱ ለመጥለፍ አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ያነበቡ ሰዎች ጳጳሳት ተሰቅለው ነበር ወይ ብለው ሊጠይቁ እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡
  hahahahahahahahahhahahahhahahahaahahhahahahhahaa----------------------------------------------------------------

  ReplyDelete
 26. hoy hoy endih new engi mesaf. yibel belenal gobez.bertulen

  ReplyDelete
 27. እኔ በጣም የምትገርሙኝ ለምንድን ነው የምናውቀውን እውነት ውሸት እንደሆነ ለማሳመን የምትሰሩት?????????? እኔ የምናውቀውን እውነት ውሸት ነው ካላችሁን ስለማናውቀው ነገር ስትነግሩን እንዴት እንመን????????????? በስህተት እኮ ስለማህበሩ አንድም እውነት እኮ አላወራችሁም??? በእርግጥ ከየት የተማራችሁትን እውነት ትነግሩናላችሁ??????????? ቢሆንም ቢያንስ ተኩላውን ምሰሉ ለምን አውሬውን ትመስላላችሁ???? እናንተ ገና እራሳችሁን ሳትገልጹ አውሬ ከሆናችሁ እራሳችሁን ስትገልጹ ምን ልትሆኑ ነው???? በተቻላችሁ አቅም ከአውሬነት ቀዝቀዝ ብላችሁ ተኩላውን ምሰሉ፡፡ ደረጃው ጠብቁ፡፡ሁሉ ነገር በሂደት ነው የሚያምረው፡፡ ለነገሩ ምናባቱ ከጠፋን አይቀር ማንነታችንን ገልጸን እንጥፋ ከሆነ ደግሞ ጥሩ አይደለም፡፡ ቢያንስ የሚከተላችሁ ህዝብ አያሳዝናችሁም፡፡ አታሳፍሯቸው እንጂ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ሙሉጌታ በስድብ ጋጋታ እውነት ወደ ሐሰትነት ልትለወጥ አትችልም አራት አምስት ቦታ ስድብ ብቻ ከምትለቀልቅ ምናለ ዝም ብትል፡፡ እንዲህ ማድረግ ወይም በተደጋጋሚ መሳደብ ያንተ እስትራቴጂ መሆኑ ነው፡፡ አትታለል ስድቦችህ አንድ ላይ ቢከማቹ አንድም የእውነት ጠብታ የላቸውም፡፡ የምናውቀው እውነት ያልከው የቱ ነው? ለምን አትጠቅሰውም ተራ የስድብ ቃላትን በማንጋጋት ለማደናገር አትሞክር፡፡ እስትራቴጂህ ታውቋል፡፡ በብዙ የጥያቄ ምልክት ብታስጌጠው ጽሑፍህ ተራ ስድብ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ለነገሩ ከማቅ ምን ይጠበቃል ...

   Delete
  2. የማቅን ደብዳቤ ያረቀቀውና የፈረመበት የሚጽፈውን እንኳን የማያውቅ ተራ ሰው መሆኑንና ማኅበሩን ያዋረደ ደብዳቤ መጻፉን ይህ ድንቅ ጽሑፍ አጋልጧል፡፡ ማቅም እርቃኑን ቀርቷል፡፡ በተረፈ ማቆች ሌላ ሞያ ስለሌላችሁ እንዲህ ዓይነት በሎጂክ ላይ የተመሰረተና የማቅን ትክክለኛ ማንነት የገለጸውን ጽሁፍ መተቸት ባይሆንላችሁም መለፍለፋችሁን ቀጥሉ ...

   Delete
 28. ማህበሩን እኮ በደንብ ነው የምናውቀው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ቤቱን ለመጠበቅ ያስቀመጣቸው የቤተክርስቲያን አጥር ናቸው፡፡ ማንስ ቢሆን ማንነቱን የሚገልጥበትን ይወዳል????????????????? እየተከታተሉ ማንነታችሁ አደባባይ ያወጡ ንጹሀን የተዋህዶ ልጆች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አውሬው የፈለገው ቢቀባጥር ቢያቅራራ እነርሱ መቼ ለስማቸው ክብር ይሰራሉ???? እነርሱ ስማቸው የተጻፈው በሰማይ እንደሆነ ስለሚያውቁ ዓለም በፈለገው መንገድ እየቀባጠር ቢጮህ፣ ቢከሳቸው ፣ዲያቢሎስ ሁልጊዜ እያታለለ እያወናበደ መክሰስ እንደሆነ ዋናው ባህሪው ነውና መገለጫው ነው፡፡ ምን ይገርማል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ከአባቶቻቸው የተማሩት እግዚአብሔርንና ቅድስት ቤተክርስቲያን ብቻ ማገልገልና ሳትበረዝ ለትውልድ ማስተለለፉ ነው ፡፡አለቀ አለቀ አለቀ አላማቸው አንድና አንድ ነው እስከሕይወታቸው ፍጻሜ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ሐይማኖት ዶግማና ቀኖና ስርአት ሳትበረዝ ሳትከለስ ከአባቶቹ የተረከበውን ለአለም ከፍ አድርጎ ማሳየትና ለትውልድ ማስረከብ፡፡ ካዲያ ይህንን እውነት ካዲያ በዚህ ክፉ ዘመን ማስቀጠል ከባድ ቢሆንም እግዚአብሔር ከፈቀደ ግን ማን ሊያስቆመው ይችላል?????????????????????? አልጋ በአልጋ ተኩኖ አይደለም ጉዞ፤ ማህበረ ቅዱሳን በትክክለኛ ሰዓት እግዚአብሔር ቤቱንና የቅዱሳንን ጸሎትና ቃል ኪዳን ለማስጠበቅ ያስነሳቸው ስለሆኑ አውሬው በፈለገው መንገድ ማቅ ምናምን እያለ ቢያጓራ፣ ቢጮህ፣ ቢጽፍ፣ ቢያቅራራ የተዋህዶ ቁረጠኛ ልጆች ገና ታሪክ ይሰራሉ፡፡ የተሀድሶን አስተምሮ ከተዋህዶ ቤተመቅደስ ውስጥ መሬት ቀብረው እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምእራፉ የሚለውን መዝሙር ሳይዘምሩማ አይቀሩም፡፡ በቅርብ ቀን ይህን ታሪክ ይሰራሉ፡፡ እድሜና ጤና ይስጠን፤ ሊነጋ ሲል ይጨልማል፡፡ እግዚአብሔር እንደሆነ በተለያየ መንገድ የተሀድሶን ማንነት በራሳቸው አንደበት እያወጡ እየገለጡት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይወደናል፡፡ ይህው በቅርቡ እንኳን ማንም የማይጠብቀውን ማንነታቸውን በራሳቸው አንደበት ገለጹ፡፡ የአቡኑ ደብዳቤን የተመለከተ ሰው እግዚአብሔር እንዴት ነው ይህችን ቤተክርስቲያን የሚወዳት አሁን እኝህን ማን በዚህ መልክ ያስባቸው ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔር ጭንቅላታቸውን አስከፍቶ ማንነታቸውን ነገረን፡፡ ክብር ለመድሀኒያለም ለእግዝአብሔር ይሁን፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ውለታው ምን ይከፈለዋል፡፡ ክብር ለአንተ ይሁን ከማለት ውጪ፡፡ የሚገርመው እግዚአብሔር ሲሰራ ዲያቢሎስ ደግሞ የቀደመ እየመሰለ የኑፋቄውን ወሬ ማቀባጠሩን አያቆምም፡፡ የእኛ ጌታ ግን መሬት ሳይቀብረው አይለቀውም፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ ስለሆነ፡፡ ጌትነቱ በወሬ የሚወራለት ሳይሆን በተግባር ነው ጌትነቱን የሚያሳየው፡፡ ጌትነትና ኃይለኝነት የባህሪው ነው ማን ይችለዋል፡፡ አሁንም ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ስለሆነ ነው ዝም ያለ የመሰለው፡፡ ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ከምድር ገዢዎችና አስመሳይ አገልጋየች ይልቅ ሰማይ ስለምትቀርባቸው የዚህ ተጠራጣሪ፣ ለእፉኝት ልጆች እናቱንና አባቱን ገድሎ እራሱን ብቻ ለሚያኖር ትውልድ እንዴት ሆነው ሊመቹ ይችላሉ???????????????????????????? አይሰማችሁም፡፡ እነርሱ አሁንም ደግሞ ደስ የሚል የተሀድሶ ፊት አውራሪዎች ብለው የጻፉት ጹሁፍ ደግሞ እንዴት ደስ ይላል???????????????? እግዚአብሔር አምላክ እንደዚህ አይነት ማህበርን ያብዛልን፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን ደግሞ እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን የወጣትነት እድሜያቸውን ይባርክልን የመንግስቱ ወራሽ ያድርግልን፡፡ ገና ይህ ማህበር ታሪክ ይሰራሉ እጠብቃለሁ፡፡ማህበረ ቅዱሳን፣ ማህበረ ቅዱሳን፣ ማህበረ ቅዱሳን ስማቸውን በተግባር ያሳዩ፤ አላውያን መንግስታትና መናፍቃን የሚፈሩት ማህበር፤ እውነትም ማህበረ ቅዱሳን፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቤተክርስቲያን በማቅ እንደምትጠበቅ አስበህ የጻፍክ ጊዜ ነው የአንተ ነገር የበቃኝ፡፡ ከቶ አላነበብክም እንዴ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያልቀላፋም እንደተባለ? የቤተክርስቲያንም ጠባቂ አንድ ጋጠወጥ ማኅበር ሳይሆን ራሱ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህ አትሳሳት

   Delete
 29. ደግሞ ጥፋቱን በማመኑ?????????? የትኛውን ጥፋታቸውን ነው አመኑ እያላችሁ የምትዘባርቁት??? የሰጡትን መልስ እኮ ከአንድ ሁለት ጊዜ ነው እኔ በደንብ ያነበብኩት!! በጣም ትህትናን የተሞላበት እንደዚህ ነው ልጅ ከአባቱ የወረሰውን ምግባር ማሳየት፡፡ ልብ ቢኖራችሁ ከእነርሱ ብዙ በተማራችሁ ግን በየትኛው ጸጋችሁ ይህንን ልታደርጉ ትችላላችሁ?????? አምላካችሁ አውሬው መምህራችሁ ሉተር!!! ምሳሌያችሁ ይሁዳ!!! ጥሩውንም እኮ ለመቅሰም ጸጋና መሰጠት ይፈልጋል፡፡ ለነገሩ እንኳን በሰው አእምሮ የተጻፈውን በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈውንም በማጣመምና ያልተነገረውን ተነገረ በማለት የመጀመሪያው መናፍቃን ስለሆናችሁ አይገርምም ማስተዋል ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ እውነት ብለሃል ማቅ ማጥፋት እንጂ ጥፋቱን ማመን አይሆንለትም፡፡ አንድ ነገር ግን ተሳሳትክ ትህትና የሚባለውን ነገር ፈጽሞ የምታውቀው አልመሰለኝም፡፡ ማቅ የቱጋ ነው በትህትና የተናገረው? ሲዝት ሲያስፈራራ ሲታበይ አይደለም እንዴ በደብዳቤው ውስጥ ያነበብነው፡፡ ፓትራርኩን ያስከበርኮት እኔ ነኝ ማለት ነው ትህትና? አንድም ያጠፋሁት ነገር የለም ማለት ነው ትህትና? እኔ ብቻ ነኝ ልክ ማለት ነው ትህትና? አላወቅከውም እንጂ ማቅ ትእቢተኛ ነው፡፡ ብዙ ስህተቶችን ፈጽሞ እያለና በብዙዎች እየተወነዘለ መቼ ነው ተሳስቻለሁ ማለት የሚጀምረው? ታዲያ እኒደህ ያለውን ባለ ድንጋይ ልብ ትሕትና አለው ልትል እንዴት ቻልክ? ምናልባት ከእግረ መስቀልዎ ሥር ወድቀን ቂቂቂቂቂቂቂቂ ያለውን ነው እንደ ትህትና የቆጠርከው? ይህንንማ ጽሑፉ አላዋቂነት መሆኑን አስረዳን፡፡ አይ ማቅ አንተም ደጋፊዎችህም ታሳዝናላችሁ አንድ እንኳን ለእውነት የሚመሰክር ሰው ይጥፋባችሁ? አባ ሰላማዎች ብራቮ በርቱልን

   Delete
 30. ለነገሩ እናንተ ይህን የመሰለ ምግባርና ትህትና ስለሌላችሁ በትህትና የአባቶችን ግሳጼ መቀበል ያላጠፉትን ጥፋት የሰው ድካም ነው ብለው በትህትና መልስ መስጠታቸው ድንገት እናንተ ያልጠበቃችሁት ነው፡፡ ምክንያቱም እናንተና አቡኑ የጻፉት አባቶቻቸውን አያከብሩም በማለት ብዙ ትዘባርቁ ስለነበር እናንተ የምትሉትና በተግባር የሚታየው ስለተለያየባችሁ ያላችሁ እድል ይህንን የውሸት ወሬያችሁን ለመሸፈን እንደዚህ አይነት የውሸት ተረት ተረት መጻፍ ግድ ያላችሁ ነቄ ነቄ ነቄ ነቄ ብለናል፡፡ ትህትናቸውን ለእናንተ እንደዚህ ከሆነ የተሰማችሁ ብዙ አላዋቂነት እንዳለባችሁና ምን ያህል ከመንፈሳዊ እውቀት ጸዳ እንዳላችሁ ጹሁፋችሁ ያሳብቃል፡፡

  ReplyDelete
 31. ማኅበረ ቅዱሳን ብዙዎቹን ጥፋቶቹን በተዘዋዋሪ በማመን ጥቂት ነጥቦች ላይ ብቻ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ “የእውነት ጠብታ የሌለበት ምላሽ” ሰጠ፡፡ አላችሁ፣ ስታሳዝኑ ምንድን ነው ጉዱ!!! እስከ መቼ በውሸት እስከመቼ በኃጢያት በማስመስል ሕይወት፡፡ የፓትራያርኩንም ደብዳቤ አንብበናል የማህበረ ቅዱሳንንም መልስ አንብበናል፡፡ የናንተ ጹሁፍ ግን የጻፋችሁት እርእስና ጹሁፋችሁ እንኳን ጭራሽ በሀሳብም ይሁን በምንም አይማሰልም፡፡ አይደለም ስለደብዳቤዎቹ መልስ አሰጣጥ ልትረዱ፡፡ ጭፍን ጥላቻ፤ ምንድን የናንተ አንባቢዎች ማንበብና ማሰብ ማስተዋል የማይችሉ ናቸው እንዴ???????????? ለነገሩ ማስተዋል የቻለ አእምሮ ቢኖራቸው እናንተን ሊከተሉ አይችሉም ነበር፡፡ የሚፈልጉትን ብቻ ከሚያምን አማኝና አስተማሪ ምን ይጠበቃል???? ጠያቂ የለ አስተዋይ የለ በሙሉ በአውሬው መንፈስ የተያዘ፡፡ ከባርነት ሕይወት ያልወጣ ሕይወት አስቸጋሪ ነው፡፡ ዛሬ አህዛብ እንኳን ባላቸው አቅም አስተዋልን በማለት አንዳንድ እውነት የሚመስል ነገር ይታይባቸዋል፡፡ ቢያንስ ርእሱንና ንባቡን እንኳን እንደምንም ብላችሁ ለማገናኘት ብትሞክሩ ተኩላነታችሁን እንቀበል ነበር አውሬውን ግን መቀበል ይከብዳል!!!!!!!!!! አትዘባርቁ፡፡

  ReplyDelete
 32. ምንድነዉ ሶስት አይነት ማልያ እየለበሱ ማደናገር ? ፆም ሲነሳ በመቃወም ለተሃድሶ መጫወት : ቅድሱነታቸዉ ተሃድሶን አጠፋለሁ ሲሉ ለስደታኛዉ ፓትሪያርክ መጫወት : ቅዱስነታቸዉ መሃበረ ቅዱሳንን እጁን አስራለሁ ሲሉ ለቅዱስነታቸዉ መጫወት :: እስቲ በመጀመሪያ የጥሩ ምግባር ባለቤቶች ሁኑ :: አሳፋሪዎች

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስማ ጌታው ማሊያ የሚቀየረው የተቃራኒው ቡድን አለባበስ እየታየ መሰለኝ፡፡ አባ ሰላማዎችን እንደተከታተልኳቸው ለእውነት እንጂ ለተለያየ ክለብ አልተጫወቱም፡፡ በአግባቡ እንጹም እንጂ ጾም አያስፈልግም አላሉም፡፡ የተቃወሙት ጾም የሚያውጅ ሲኖዶስ እንጂ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም በሚል ነው፡፡ ታዲያ ለምን ታደናግራለህ?

   Delete
 33. Orthodox ppl have no time for Jesus. They have over 50 amlaktoch to worship, bow and celebrate as equal as Jesus. Wow!! They are blind, and covered with others. Busy people for nothing. busy people occupied by saints, angels, culture, ficticious stories of people. God's aim is to reveal Jesus, his begotten son for us. The whole bible tells us about Jesus, not about saints and .... kotetoch, Bututo atsebsebu, just worship Jesus, son of God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabher yiqr yibelih. Eyesus Kirstos (Egziabher) yakeberachewn Enatun Dingil Mariam endihum Kidusanum eyetesadebk maregn bleh nisha kalgebah yiqr yemilegn yimeslhal?????? Wedesewnetik Amlak yimelsih. Ahun endesew sayhon ende awrie honehalna!!!!! MAstewalun Yadlih.....

   Delete
 34. ይህን ፁሁፍ አንብቦ ደብዳቤውን የፈረመው ሰሙ ምን ብሎ ይሆን? ራቁቱን አስቀራችሁት እኮ በእውነትና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ፁሁፍ ነው በርቱልን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. lekso tekemtowal hahahhahha

   Delete
  2. እጄን ይስበረው ብሎ ራሱን እየረገመ መሆኑ አያጠራጥርም

   Delete
 35. You are the father,brother, sister and mother of Evil because you didn't know Jesus but i tell you the truth 100 and over trillion times orthodox know the Father, the Son and the Holy Sprite very well and Worship only trinity.
  All Orthodox people Pray for this blindly hate Orthodox guy/lady.

  ReplyDelete
 36. የእናንተ አንድ ደብዳቤ ባገኛችሁ ቁጥር ደብዳቤውን ከተጻፈበት ዐላማ ውጭ ለጥጦ መተርጎም፣የራሳችሁን ስሜት ቀላቅሎና ለውሶ ማቅረብ፣ግራ ቀኝ ሳያጣሩ የተገኘውን ሁሉ ለጥፎ ወሬ ማሟሟቅ አስተዋይ ኅሊና ለሌለው ሰው መስህት ነው፡፡ጥንተ ተፈጥሮአችሁን ለምናውቅ ግን አይገርመንም፡፡የአላማጂቱ ልጅ አእምሮዎን ለብዎውን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 37. ለ፡- Muluget Enawegawወይም ዳሞት
  አንተ ሰውየ በደርግ ጊዜ ተወልደህ ቢሆን ኖሮ አሪፍ መፈክር አሰሚ ይወጣህ ነበር፡፡ ዘወትር መፈክር ለማሰማት አለመታከትህ እና ለስድብ ያለህ ጥማት ይገርማል፡፡እንደዚህ እየጻፍክ ራስህን እንደ ትክክለኛ ኦርቶዶክስ የሚያይ ኅሊና በመያዝህ ልትደሰት ይገባል፡፡ሳያስቡና ያለይሉኝታ አንድ ጊዜ ‹‹ዳሞት›› ሌላ ጊዜ ‹‹ሙሉጌታ›› እያሉ እዚህም እዚያም ስድብ ሲደረድሩ መዋል ታላቅ ስጦታ ነው፡፡ወደፊት የስድብ ጋይድና ዲክሽነሪ እንድታሳትም እመክርሀለሁ፡፡አቡነ ማትያስ ላይ የምትሰነዝረውን ሁሉን አቀፍ ስድብ ጫን ካደረከው ደግሞ ኅትመቱን ማኅበረቅዱሳን ስፖንሰር እንደሚያደርግህ ተስፋ አለኝ፡፡ማኅበረቅዱሳንን መውደድና ማፍቀር ዝም ብሎ በየደረሱበት መቀደድ ማለት አይደለም፡፡አባልነትህን የሚመጥንና ቁጥብነት ያለው በሳል ንግግር ተናገር፡፡በወረደ አስተያየት ሃይማኖቱንም ማኅበሩንም ከሚያስነቅፉት ወገን ነው አሁን ያለው ጭፍን ያለና በስድብ ተጀምሮ በስድብ የሚያልቅ አስተያየትህ

  ReplyDelete
 38. ውሾች ይጮሃሉ ግመሎችም ይሄዳሉ፡፡ከማሕበረ ቅዱሳን ጋር ወደፊት!!!!!!

  ReplyDelete
 39. mselosh new komatit

  ReplyDelete
 40. አዎ ግመሎች የአረብንና የዉሮፓን ሸቀጣሸቀጥ ተሸክመዉ ቤተ ክርስቲያናንና የቤተ ክርስቲያናን ልጆች እየገፈተሩ ይጋዛሉ
  እና ምንም እንካን ባናደርግ አትጩሁ አትናገሩን ነዉ የምትሉት
  አረ አበዛችሁት

  ReplyDelete
 41. ሁሌም የእናንተን ጽሑፍ ባነበብኩ ቁጥር በተቃራኒው እረዳዋለሁ፤ እናንተ አስተሳሰባችሁም ሆነ ዓላማችሁ ግራ ነውና! በተለይ ደግሞ እናንተ የምትንቁት የቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ሁሉ ትክክልነቱ እየገባኝ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በወቀሳችሁት መጠን እየወደድኩት መጣሁ! በርቱ፤ እናንተ ስትንጫጩ ያኔ እኔ ውስጤ ሰላም ይሞላልና!!!

  ReplyDelete