Tuesday, February 9, 2016

ድብቅ ተልእኮ ያላቸው ፀረ ወንጌል ቡድኖች እውነተኛ አገልጋዮችን እያሳደዱ ነው


Read in PDF

ወንጌልን የማመንና የመስበክ አንዱ ውጤት ከዓለም ተቃውሞንና ስደትን ማስተናገድ ነው፡፡ የወንጌልን ቃል የተረዱ፣ ያመኑና የሚሰብኩ አገልጋዮች ይህ የማይቀር ዕጣ ፈንታቸው እንደ ሆነ ያውቁታል፡፡ በወንጌል ያላመኑና ለወንጌል ሳይሆን ለሃይማኖታቸው የቆሙና ለእግዚአብሔር ያለ ዕውቀት የቀኑ የሚመስላቸው ሰዎች ደግሞ እውነተኛ አገልጋዮችን ሌላ ስም ሰጥተው ማሳደዳቸውና በዚህም እግዚአብሔርን እንዳገለገሉ የሚቆጥሩበት ሁኔታ መኖሩ ሁሌም ያለ ክሥተት ነው፡፡ በዚህ ምድር ይህ ሁኔታ መቀጠሉ የማይቀር ቢሆንም ጌታችን በክብር ሲገለጥ ግን እንዲህ በሚያደርጉት ላይ በፍርድ እንደሚገለጥና ስለስሙ መከራ የተቀበሉትን ደግሞ እንደሚያከብር እውነተኛ ነገር ነው፡፡  “ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን። ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው። ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።” (2ተሰ. 1፥3-7)፡፡
ይህን እውነት ባለማስተዋል በእውነተኛ አገልጋዮች ላይ ስደት እያስነሱ ካሉት መካከል የዲሲው / ነጋና መሰሎቻቸው ይገኛሉ፡፡ የዲሲው ደ/ር ነጋ ዓለማየሁ በዚህ ግብር ጸንቶ ለአምስተኛ ጊዜ የቤተክርስቲያን አገልጋይን አባርሯል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ በዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ችግሮችን ሲፈጥር የነበረውና ስውር ተልእኮ ይዞ ወደ ዲሲ ቅዱስ ገብርኤል የገባው ዶ/ር ነጋ አለማየሁ አሁንም ከጥፋቱ ሊመለስ አልቻለም። እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የተፈጠረውን ግርግር በመጠቀም ስልጣን የያዘው / ነጋ እና ተባባሪዎቹ ዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ከስደተኛው ሲኖዶስ ለመለየት የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለዋል። የሲኖዲሱ አባልና ደጋፊ የነበሩትን ካህናት እያባረረ ድብቅ ተልእኮ ያላቸውን እና ክህነት የሌላቸውን ካድሬዎችና የማህበረ ቅዱሳን አባላት እንዲሁም የሐሰት ሰባክያንን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ መቅጠሩን ቀጥሏል። 

በመጀመሪያ ቀሲስ እንዳልካቸውን ክህነት እንዳይሰጠው በማስከልከል ሲያባርረው ቀጥሎም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከመሰረቱት እና ብዙ ከለፉበት ቤተ ክርስቲያን ጥቂት ግለሰቦችን በማሳደም ያለርህራሄ ውጪ አውጥተው ጥለዋቸዋል፣ በቦታውም እነርሱው አዛዥ ናዛዥ ሆነውበታል፡፡ ከዚያም አባ ወልደ ትንሳኤን በሐሰት ውንጀላ አሳስሮአቸው የነበረ መሆኑ ሲታወስ ለዚያም አለ የተባለው ማስረጃ የቪዲዮ ምስል ውሸት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በቅርቡም ከጀርመን ያስመጡዋቸውን አባ ብርሃኑ የተባሉ አባት በህዝብ ፊት የተቀጠሩ መሆናቸውን እና ቤተክርስቲያኑም ዕለት ዕለት ክፍት እንደሚሆን ካሳወቁ በኋላ የኛን ሃሳብ የማያራምዱ ከሆነና ከሲኖዶሱ ደጋፊ ካህናት ጋር ያለዎትን ግንኙነት ካላቆሙ አብረን ልንሰራ አንችልም” በማለት የሁለት ቀን የጊዜ ገደብ በመስጠት እርሳቸውንም አባረዋቸዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ወራት ከደቡብ ኣፍሪካ ወደ አሜሪካ በመግባት በዲሲ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያገለግል የነበረው መምህር በኃይሉ፣ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ እና እየተዘዋወረ በሚያገለግልባቸው በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከአባቶች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው ቢሆንም / ነጋ የሚመራው ቦርድ እና መምህር ፍሬስብሐት ሲቃወሙት ቆይተው፣ ከሎሳንጀለስ የጥምቀት ጉባኤ መልስ ጉባኤውን ከሚሳተፉ ካህናት ጋር ህብረት እንደሌላቸው እና እንደሚቃወሙ በማሳወቅና በድጋሚ የቀናት የጊዜ ገደብ በመስጠት እርሱንም አባረውታል።
በተለይም / ነጋ እና ተባባሪዎቹ ለያዙት አላማ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉት በሥነምግባር ችግር ውስጥ የሚገኙና የቤተክርስቲያንንም ቀኖና ጥሰው የሚገኙት ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል  ጸረ ወንጌል ዓላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለው መምህር ፍሬስብሐት ገድሉ ሲሆን፣ ሚስቱን ፈትቶና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ መቅደስ በመግባት እያገለገለ ሲሆን፣ ሚስቱን ሲፈታም / ነጋ እና ተባባሪዎቹ እንደረዱትና በዶ/ ነጋ የቤት አድራሻ ተጠቅሞ የፍቺ ሂደቱን የጨረሰና የፍቺ /የዲቮርስ/ ወረቀቱን መጨረሱን የደረሰን የዲቮርስ ሰርቲፊኬት ያመለክታል።
 
የዶ/ር ነጋ ቡድን በተደጋጋሚ ጊዜ ከሲኖዶሱ ውጪ የሆኑ ካህናቶችን በማስመጣት ለመቅጠር የሞከረ ሲሆን ከምዕመናኑ በደረሰ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊመለሱ ችለዋል። እንዲህ አይነቱ  ድብቅ አላማ በቶሮንቶ ቅድስት ማርያም  ላይ ያነጣጠረ መሆኑን እየተመለከትን ነው፡፡ በቶሮንቶ ቅድስት ማርያም  ሊቀ ካህናት ምሳሌን እና ዶ/ር ቀሲስ መብራቱን ለማባረር ከፍተኛ እንቅስቃሴና የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተቱት ፍሬስብሐት፣ መርጌታ ተስፋ እና ቀሲስ አንዱ ዓለም ናቸው፡፡ ቀሲስ አንዱ ዓለም  ለህዳር ጽዮን ቶሮንቶ መጥቶ “ተሐድሶ እዚህም ገብቷል” እያለ ቅስቀሳ በማካሄድ እራሱ ባዘጋጀው የሀሰት  ደብዳቤ ሕዝቡን ግራ አጋብቷል፡፡ በተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ላቀዱት ፀረ ወንጌል የጥፋት ተልእኮ ተባባሪ የሆኑት ከላይ የተጠቀሰው የዲሲው ፍሬስብሐትና የቶሮንቶው መርጌታ ተስፋ ናቸው፡፡ እነዚህም ሰዎች በተመሳሳይ የሥነ ምግባር ችግር ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ገበናቸውን የደበቁ መስሏቸው በማቅ ሥር ሆነው ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ በማድረግ ለሃይማኖታቸው ቀናኢ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፡፡ ማቅም ቢሆን እስካሁን እንደታየው ለእርሱ ዓላማ መፈጸም እስከጠቀሙት ድረስ በየትኛውም የትምህርተ ሃይማኖትም ሆነ የስነምግባር ችግር ውስጥ ቢገኙ  እርሱ ግድ የለውም፡፡ እንዲያውም ያንን የሚመርጠው እንደሆነ አያጠራጥርም ምክንያቱም ማስፈራራያ አድርጎ እንደልቡ ይጠቀምባቸዋልና፡፡ እየሆነ ያለውም ይህ ነው፡፡ እነዚህ ሕገወጦች በእውነት ለመሄድ በሚጥሩ እውነተኛ አገልጋዮች ላይ የከፈቱት ፀረ ወንጌል እንቅስቃሴ መቆም አለበት፡፡ ምእመናንም ይህን አውቀው ከምንም በላይ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሚጠቅማቸውን መለየትና በምድራዊ አጀንዳ ላይ ለኣላማቸው መሳካት የሚሯሯጡትን ማስቆም አለባቸው፡፡  ስደተኛው ሲኖዶስ ህጋዊ ነኝ ካለ እነዚህን ህገወጥ የሆኑ ሰዎች በቶሎ ሊያርም ይገባል። እነዚህ ሰዎች በቶሎ ካልታረሙ እና ንስሐ ካልገቡ አባ ሰላማ በእጁ ያሉትን መረጃዎች ለማውጣትና ምእመናን ከሐሰተኞች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ከማስገንዘብ ወደኋላ አይልም፤ ምክንያቱም አባ ሰላማ የቆመው ለእውነት ነውና።


41 comments:

 1. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk................. Degemo beyet metachu.....

  ReplyDelete
 2. "ምክንያቱም አባ ሰላማ የቆመው ለእውነት ነውና።"
  ሃሃሃሃ ውሸታምነታችሁን ሁሉ ሰው ስለሚያውቀው ውሸታም አለመሆናችሁን ለማስረዳት ነው ይሄ ሁሉ መፍጨርጨር? የሃሰት የገዢዎች።

  ReplyDelete
 3. አባ ሰላማ "የዉጩን ሲኖዶስ" ይቀበላል??? የኢትዮጵያዉንስ???

  ReplyDelete
 4. ከመቼ ወዲህ ነው ደሞ ለቀኖና ተቆርቁዋሪ የሆናችሁት፡ አይ እናንተ ተኩላዎች ማ/ቅዱሳን የሥነምግባር ችግርን ሲያጋልጥ ሠምቼ አላውቅም እንደናንተ አይነቶችን ተኩላዎች ግን ሲያጋልጥ ነበር ወደፊትም ይቀጥላል ብዬ አምናለሁ

  ReplyDelete
 5. ደስ ሲል እናንተ ይህን ካላችሁ መናፍቃን በትክክል ከሁለት ቤ/ክርስቲያን ተባረዋል ማለት ነው።

  ReplyDelete
 6. መርጌታ ተስፋ እንዲ ነበር ያደረገው ውንፒግ ካናዳ አባ ፍቅረሥላሴን ለማስባረር ፈልጒ በእርሳቸው ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አድርጓ አልተሳካለትም ምዕመናኑም ይህን ሲያውቅ እንዳናይህ አለው አሁንም ቶሮንቶ ሄዶ ውንፒግ ያደረገውን እያደረገ ይገኛል አሁንም የቶሮንቶ ህዝብ እኛ እንዳደረግነው ቦሌ መዳኅኒዓለም ቢደውል የሱን የተስፋን ጉድ ማወቅ ይችላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሄሄ የአብዬን ወደ እምዬ አሉ። ምነው መሪጌታ ተስፋ ተመልሶ በመጣልን። ሴቶች በእልልታ ወንዶች በጭብጨባ እንቀበለው ነበር። የሚገርመው ግን አሁንም እንደቀናችሁበት ናችሁ?ይገርማል!! ለነገሩ መሪጌታ ተስፋ ጠላት የሆነበት እውቀቱ,ድምፁ,ትህትናው ነው። ከዚህ በላይ ያለውን አስተያየት የፃፍከው(ሽው) ሰው ግን፡ መሪጌታ ተስፋ እዚህ ዊኒፔግ በነበረበት ጊዜ ያለህ አይመስለኝም። ብትኖር ኖሮ አባ ፍቅረሥላሴ አውደምሕረቱ ላይ ቆመው ''መሪጌታ እስከ ዛሬ ድረስ ሲያገለግለን ኖሮል አሁን ግን በእድገት ወደ ቶሮንቶ ሄዶአል። ሊቀካህናት ምሳሌ፡ በስልክም በደብዳቤም ጠይቀውኝ ፈቅጄ ልኬዋለሁ።''ያሉትን ትሰማ(ሚ) ነበር። ሕዝቡማ በየቤቱ ምነው መሪጌታ ተስፋ በመጣልን ድምፁ ናፈቀን እያለ ነው። በእርግጥም እውነት ነው። እስቲ ቤተክርስቲያናችን አሁን ያለችበትንና መሪጌታ ተስፋ በነበረበት ጊዜ የነበረውን ድምቀት ሕዝብ ይመስክር። ስለዚህ ወንድሜ(እህቴ) ኢሄንን በቅናት መንፈስ የገባባችሁን ሰይጣን እግዚአብሔር እንዲያሶግድላችሁ በፆም በፀሎት ትጉ።

   Delete
 7. አይ እናንተ የናት ጡት ነካሾች አሁን እኛ ክርስቲያኖች ነን ብላችሁ ነው ዎዬ ቃሉን ብታውቁት ኖሮ ለእውነት ትመሰክሩ ነበር።ነገሩ አታውቁትም ምን እንደሆነ አላማችሁ አይታዎቅም አይሲስ ፊት ለፊት የስውን ህይዎት ይገድላል እናንተ ደግሞ በስውር መሳሪያ የገንዛ ወገኖቻችሁን ታሳድዳላችሁ።እግዞያብሄር ይቅር ይበላችሁ ይህ በእውነት ይሁዳዊነት ነው እባካችሁ ቁሙና አስቡ ስለፍቅር ስለአንድነት።ይህች ናት ሃይማኖት ማለት ሰውን አለማሰናክል።እናንተ ጸረ ሃይማኖት ናችሁ ስድብ አቁሙ ማንም ሰው የግል ሃጢያት ሊሰራ ይችላል ይህን ፍርድ የሜሰጥ አንድ አምላክ ብቻ ነው።እናንተ እንደፈሪሳውያን እያደርጋችሁ ነው።እረ ለመሆኑ ወንጌል የምትሉት የናንተ የጵሮቴስታንት ወንጌል ለቀቅ አድርጉን እኛ ስንዱ የሆነች ስር አት ያላት እንከን የሌለባት ሃይማኖት አለችን።የምታደርጉት አላም ስለታወቀባችሁ አሃ እግዚያብሄር እነዚህን እውነትኛ መስካር አባቶች ስለስጠን እናመስግነዋለን እንቁዬ የቤተክርስቲያን ልጆች ቀሲስ አንዷለምን ቀሲስ ፍሬ ስብሃትን ለቀቅ አድርጐቸው እግዚያብሄር ልብ ይስጣችሁ። ሰላም ሁኑ ስላም ፍቅር ተስፍ ከሁሉም የምበልጠው ፍቅር ነውና እርስ በእርሳችሁ በፍቅር ተመካከሩ በወንድሞች መሃል ጸብን አትዝሩ የዚህ አባ ሰላማ ሰዎች የሁናችሁ ሃይማኖታዊያን ናችሁ ወይስ? ከሞላ ጎደል ከናንተ አጻጻፍ የማዬው ነገር እናንተ የውጭው ሲኖዶስ ተከታዬች ትመስሉኛላችሁ።በጣም ያሳዝናል እኔም የውጭው ሲኖዶስ ስር ያለሁ ምእመን ነኝ ምንም ጥሩ ምሳሌዎች የምትሆኑ ክርስቲያኖች አይደላችሁም።ይልቁንም መንገድ እያጣመማችሁ ሰውንም ሃሳቡን እያስቀየሳችሁት ነው።እኔም የውጪው ሲኖዶስ ባሁኑ ሰአት ከጥቂት አባቶች በስተቀር ሃይማኖታችን ለማቆሽሽ ታጥቀው የተነሱ ጥርቅም ማለት ነው ብዬ ደምድሜአለሁ።ያሳዝናል

  ReplyDelete
 8. ኧረ አታስቁኝ የረባ መረጃ እንዳለው ሠው ደግሞ ለማስፈራራትም ትሞክራላችሁ ያለ ቤታችሁ ገብታችሁ አትፈትፍቱ ሃራጥቃዎች ገና ትጠረጋላችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሄሄ እናንተ ብሎ የቤተክርስቲያን ተቆርቆሪ ውሸታሞች

   Delete
 9. ይገርማል ከመቼ ጀምሮ ነው እናንተ ሰላማዎች የውጭውን ሲኖዶስ መንቀፍ የጀመራችሁት አለቃ አያሌው መቼ ተለመደና ከተኩላ ዝምድና በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ (የጎሮ ቤት ሌባ ቢያዩኝ እስቃለሁ ባያዩኝ እሰርቃለሁ) ስለዚህ ሳትሰርቁን ነቃንባችሁ እኛ ሲኖዶሱ ምን ዓይነት ችግር እንዳለበት ብዙ ጊዜ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል በዚያን ዘመን እናንተ እኛን እንደ ጠላት ትመለከቱን ነበር አሁንም የውጭ ሲኖዶስ ከዘረኝነት እና ከምንፍቅና ካልፀዳ ገና ጉድ ይወጣል ።መኑ ከማከ ነኝ ።

  ReplyDelete
 10. ለመሆኑ በሃይሉ ማነው ክህነት አለው? እውን ለቀኖና ከተቆረቆራቹህ አንተ ይህን የጻፍከው ሁለተኛ ሚስትህን በቅርብ ስታገባ የቀደመችውን ስትተዋት ቀኖና ተከብሮ ነው አንተ ካህንና መምህር ትባላለህ ?ሚስት መፍታት የትኛውን ቀኖና ነው የሚጥሰው ለመሆኑ በቀኖና ታምናለህ ? ለጊዜው ኢየሱስ ብቻ አይበቃህም ቀኖና ምንድን ነው? በተሃድሶ መንደር ክህነት ያስፈልጋል ? አሁን ስለ አንተና ስለ መሰሎችህ ብዙ ብል ምን ይጠቅማል ክፉን በክፉ አትቃዎሙ ይል የለ አንተም ሆነ ተባባሪዎችህ ልቦና ይስጣቹህ ስም ማጥፋት ወንጀል ነው የሐሰት ሰነድም ያስከስሳል መጠንቀቁ አይከፋም ወዳጄ ከንግዲህ ዲሲ ገብርኤል ምኞት ነው መናፍቃን እንዳይደርሱ በሳት ታጥሯል ቶሮቶም ተጀምሯል ካሊፎርንያም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወሰድ ነው የት ትገቡ ?

  ReplyDelete
 11. Ohhh how cute, the hostage takers of DC Saint Gabriel Church who call themselves "board" and spend 24/7 scheming about anything but God's work and reading blogs have the first few comments. I know, truth hurts! How about we learn from John the Baptist's message and fill our very deep chasms, level our mountain of pride and hate, straighten our diabolic ways so that we may see the salvation of God. Too much wrong is being done, too the point one questions whether they are going to church or a political institution, in which hate and revenge are the very Constitution.

  ReplyDelete
 12. የማህበረ ቅዱሳንና የአባላቱ ችግር አንዱና ትልቁ ጥፋትን አለማመን ምንም ይባል ምንም ነገሩን ሳያገናዝቡ ለስድብ መሮጥና ሁሉንም ተሃድሶ ጴንጤ ምናምን እያሉ መሳደብ ነዉ
  እስኪ አንድ ጊዜ እንካን ጥፍት ሊሆን ይችላል ብላችሁ እመኑ .እኔ የምፈራዉ ወደፊት የሚነሳዉ ትዉልድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይልቅ የማህበሩን ቃል እዉነት ነዉ ብሎ የሚያምን እንዳይሆን ነዉ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Seif lay mekomachun binegerachu alesema silalachu seif libelachu new!!

   Delete
  2. አንተ ደግሞ የመቸው ጅል ነህ ወይም አንተው ራሱ የነሱ ተባባሪ ነህ!!!

   Delete
 13. የማህበረ ቅዱሳን ስም ሲጠራ እንደጠመቁት ጋኔል ያንቀጠቅጣችዃል ሃሃሃሃ ደስ ሲል

  ReplyDelete
 14. ይገርማል ሚስቱን የፈታ ያውም በቦርዱ ሊቀመንበር አድራሻ ፍቺውን የፈፀመ ካህን ያገለግላል ነው የምትሉኝ? እዚህ ተደርሱአል እጅግ ያሳዝነል

  ReplyDelete
 15. ምን አለ ስህተታችሁን ብታምኑና ንስሀ ብትገቡ። እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ድረስ ተቀምጠን ስለናተ የማጭበርበር ስራ ነው የምንሰማው። ደሞ ስደት ላይ ተቀምጣቹ ሰው ታሰድዳላቹ። እዚህ 4ኪሎ ተቀምጦ ወያኔ ዲሲ ላይ ያተረማምሳችዋል። እረ ንቁ ዲያስፓራዎች።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የስው ገመና አታዉጡ ፤ ለእግዚአብሔር ተዉት፤ ምናምን እያሉ እድሜ ለዚህ ክፉ ማህበር ማህበረ ቅዱሳን የተከበረዉ ሕዝባችን ሐጢአትን እንዲልለማመድ እያደረጉት ነዉ.ይህ ማህበር ገና ቤተ ክርስቲያናን ጉድጋድ ዉጥ ሳይጥላት አይቀርም።

   Delete
 16. Ayy kirstena Tarik yefred memir Fere sew Bole michael yeseraw gud neew negade leba Gena Bizu gud alle (Gondrew Elias Sweden

  ReplyDelete
 17. ፍሬ ስብሐት መምህር ነው እንዴ የት ያገኘው መምህርነት ነው

  ሚስቱን የፈታዉም በራሱ የጤና ችግር ምክንያት ነው እነ ዶር ነጋም ይህን ምስጢር ስለሚያዉቁበት ነው የነሱ መሳሪያ የሆነው

  ReplyDelete
 18. አይ ዶ/ር ነጋ! ብለህ በለህ ሚስቱን በአሜሪካ ፍርድ ቤት በአደባባይ የፈታ ካህን ተብዬ ያፈረሰ ካህን በተቀደሰው ቤተ መቅደስ ውስጥ አስገባህ። የሚገርም በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የአትላንታው ተኩላ መነኩሴ እና የዚህ ካህን ነኝ ተብዬው ይገርመኝ ነበር። ሁለቱም የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው ሁለቱም የማህበረ ቅዱሳን አባላት። የውጭው ሲኖዶስ እንዲህ ዓይነት መረጃ ካገኘ አስተዳደራዊ ርምጃ መውሰድ አለበት። ለመሆኑ የዲሲ ገብርኤል ምእመናን ዶ/ር ነጋን እንደ ጋሪ ፈረስ ነው እንዴ የሚነዳቸው። ከዚህ በላይ ምን ያርግ? ክህነት የሌለው ልጆቻቸውን ሲያቆርብ ዝም ይላሉ? አባ ሰላማዎች ተባረኩ! እንዲህ ነው ለእምነት መቆርቀር!

  ReplyDelete
 19. ትገርማላችሁ። መቼም ስሙ ሁለት ፊደል ስለሆነ ነው መሰል ስሙን መጥራት ያስደስታችኋል። ኧረ ለመሆኑ የዶ/ር ነጋ አድራሻ ለፍቺ የሚፈለገው ለምንድን ነው። መምህሩ የራሳቸው አድራሻ አላቸው። በየትኛው የሕግ አካሄድ ነው የሌላ ሰው አድራሻ የሚፈለገው?
  ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ መምህሩ ሚስቱን ይፍታ አይፍታ ገና የተረጋገጠ ነገር የለም። ክህነቱን አፈረሰ የሚባለው ግን ሚስቱን ስለፈታ ነው እንዴ? ከሚስታቸው ጋር ተለያይተው ወይም ሚስታቸውን ፈትተው በክህነታቸው የሚያገለግሉ ካህናት የሉም እንዴ? ስማቸውን በጽሑፉ የጠቀሳችኋቸው አባ ብርሃኑ መነኩሴ ሲሆኑ ቀደም ሲል የወለዷቸው ልጆች አሏቸው። ምንኩስናቸው ደግሞ ሚስታቸውን ፈትተው ነው። ሌሎችም መነኮሳት ከሚስታቸው ጋር ተፋትተው የመነኮሱና በክህነታቸው የሚያገለግሉ አሉ። ካስፈለገ ስማቸውን መጥቀስ ይቻላል። መምህሩ አፈረሱ የሚባሉት ሚስታቸውን ፈትተው ከሌላ ሴት ከተያዙ ወይም ሌላ ትዳር ከመሠረቱ ነው። በጥላቻ ምክንያት የምናደርገው ነገር ውሃ አይቋጥርም። የምትሉት ፍቺ እውነት ሆኖ ቢገኝም ክህነቱን የሚያፈርስበት ምንም ምክንያት የለውም።
  ስለወንጌል እያወራችሁ ወንጀል መሥራት ጢሩ አይደለም። እግዚአብሔር መልካሙን ያስመልክታችሁ፣ ልቦና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 20. ኢሄን አስተያየት ለመስጠት የተገደድኩት በጣም ስለገረመኝ ነው። በእውነት በጣም ይገርማል።
  በቀድሞ ዘመን እነ ዮዲት ጉዲት፣ እነግራኝ መሐመድ...ሌሎችም ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ተነስተው ነበር። በእርግጥም ብዙ ጉዳት አድርሰውባታል። ነገር ግን የሲኦል ደጆች ሊያነዋውጡአት አይችሉም ባለው አምላካዊ ቃል መሰረት እነሱ ጠፉ እንጂ ቤተክርስቲያናችን በእግዚአብሔር ሐይልና በቀድሞ አባቶቻችን ቆራጥ የሐይማኖት አርበኝነት ፅኑ አመራር ምክንያት ቤተክርስቲያናችን ታፍራና ተከብራ እዚህ ደርሳለች። እስከ ዓለም ፍፃሜም ትኖራለች።
  የአሁኑ ግን ለየት የሚያደርገው ከውስጧ የተወለዱ የእናት ጡት ነካሾች እራሳችሁን የደበቃችሁ የወያኔ ተላላኪዎች(አባ ሰላማዎች) የዘመናችን ዬዲትጉዲት እና ግራኝመሐመድ በመሆን ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በሰለጠነ መንገድ ተነስታችኋል።
  ይሄውም--አሉ የተባሉ ቤተክርስቲያኒቱ የምትጠይቀውን Criteria ጠንቅቀው የሚያሟሉ በሊቅነታቸው ተመስክሮላቸው የሚያገለግሉትን ሊቃውንቶች ስም ለማጥፋት ከቤተክርስትያኒቱ መድረክ ለማውረድ እንዲሁም ሕዝቡን በዘር በጎሳ ለመከፋፈል ንፁህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችንን ለመበረዝና ቤተክርስቲያኒቱን እንደ ፕሮቴስታንቶች አዳራሽ በኦርጋን መጨፈሪያ ለማድረግ መነሳታችሁ ነው።
  ለምሳሌ፦አሁን ስማቸውን ለማጥፋት የተሞከረባቸውን መምህራን ስንመለከት የእናንተን Ideology ስላልተቀበሉና ድብቅ አላማችሁን ስለሚያጋልጡ የበቀል ዱላችሁን ለማሳረፍ ሞክራችኋል። ከንቱ ድካም ነው።
  እነዚህ መምህራን ከጳጳስ እስከ ምዕመን ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ የቁርጥ ልጆች እና አንጋፋ ሊቃውንት መሆናቸዉ የተመሰከረላቸው ናቸው። ስለዚህ ከምን አንፃር ስማቸውን እንደምታጠፉ ይገባናል።

  አትድከሙ!!!!

  ReplyDelete
 21. አቶ ፍሬሰውን ከቦሌ ጀምሬ አውቀዋለው። አንድ አስተማሪ የሆነች ሴት አግብቶ ነበር። ከዚያም አሜሪካን ለመምጣት ሌላ ሴት አገባ። ያረጋል የሚባል የወያኔ ተቀጣሪ ዘመድ አለው ዲሲ ገብርኤል ውስጥ አብረው ነው የሚያተራምሱት። በተለይ ያረጋል የዲሲ ህዝብ ያወቀው የመንግስት ተቀጣሪ ነው። አባ ሳሙኤልን ያባረሩት ይህን ጉድ እንዳያወጡባቸው ነው።

  ReplyDelete

 22. እባካችሁ አንብቡት አባሰ (አባ ሠላማ ዎች)
  ይገርማል ለመሆኑ "አባሰ" ዎች ተግሳፅን የምትሰሙበት፣የምትመከሩበት፣የምትመለሱበት እንደዉ በአጠቃላይ ክፋታችሁን እለት ተእለት ከማባስ (ከመጨመር) የምትድኑበት ጥቂት ልቦና ከአዉሬዉ ቅኝ ግዛት ተርፎላችሁ ይሆን ??? የሚከተለዉ ድክመታችሁን ለመግለፅ የሞከርኩበት ነዉና ብትመለሱ እኔም የናንተን አፀያፊ ሐጢያት ከመግለፅ ብድን መልካም ነዉ እላለሁ፡፡
  • የሰዉን የግል ሃጢያት እና ድካም መግለጥ በምንም ምክንያት ቢሆን በተለይም በሐዲስ ኪዳን ሃጢያት ነዉ፡፡ማወቅ ያለባችሁ እንዲህ የምትፅፉ እስቲ ዞር ብላችሁ ያለፋችሁት ህይወት ተመልከቱ?ሃጢያታችሁ በጌታ አልተከደነምን? ደግሞስ ወንጌልን በሚመቻችሁ መንገድ ማሻሻልም ጀምራችኋል ???
  • እዉነት የሆነ ጌታ ድንቅ መካር ሃያል አምላክ አዳኝ የሆነ የዘላለም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ስትሰብክ እና ስትመሰክር ለዘመናት የኖረችዉን ቤተክርስቲያን ከናንተ ጎን ሆኖ ያልሰደበ ፣ያላሳደደ ፣ያልካደ፣ እና ያላስካደ ለዚህም የማይሰራ ከሆነ ወይ ዘማዊ ነዉ ወይ ማህበረቅዱሳን ነዉ እናንተጋ ይህም በጌታ ዘንድ ዋጋ ያስከፍላችኋል እና ተመለሱ

  ReplyDelete
 23. what really make me feel sad was that the church members who bought and pay off the church were driven out with the deacons and priests who were there since the onset of its foundation. when that happened, we told them that the move was reckless and dangerous; most of the supporters of the then "motto" of the group was "he got to go", when asked who is the one who has to go? there answer was the Bishop- Abune Samuel, a man of prayer and innocent father, and this brought the rest of the people together so that they could evade his removal, but the thing was that supporters of the bishop were not organized and know each other better; due to this fact, they continued to remove the then deacons, our beloved ones who are indeed love, with succulent liturgical voices and humble approach to every one, very hard working in every part of their church services.It was never stopped there, in fact, the primary action was mounted on Kesis Enidalkachew, who for sure is the follower of the teachings of yohannes wenelawi-focused on the Trinity, the scarifies of Jesus, and also who is often times keen to say that salivation was attained through the death of Christ but that salivation was and is the power of the trinity, the trinity is part of it, while Christ in person died on the cross.
  Endalkachew is an evangelist who is centered on the divine unity and he loves to say that GOD is always with us if our hearts are open for the holly spirit, he is not there to make the people happy devoid of addressing the nitty-gritty, I am happy for we have him.
  Now, the people at Saint Gebriel Church are again for the second time on a topsy-turvy, who probably thought things would go the way they thought, but that was not the point, the wave and tide is to drive them out unless they stick with the status quo, goodness gracious,it did not even take five years when the accusers are accusing, you know, what goes around comes around.
  In life people really need to be wise, in fact it might not occur to every one but the more you give chance to talk with your opponent and continue that way, one day you would come to the point of identifying the truth. regarding Saint Gebreil church in particular and the churches in North America what is going on is nothing different, the problem is people are not aware of the gospel and need still live with what is the thought of the crowd, unless you stay away from a crowd, there still is a problem, and the other thing is that always quite a few strongly organized forces in any situation whether political or otherwise are influential, you can not beat them, but to the degree you stay with the truth, truth will prevail, and that is what makes people hopeful, and "Jesus is the truth, the way and the life", so in Christ, it is a real matter that we in our times see the holly spirit take the hearts and minds of the people and every language will say nothing except" ADONAY, ELSHADAY, YAHWE, JESUS CHRIST, HOLLY SPIRIT", with the name of the deity, the incarnate logos, oh my GOD, we see a practical change of hearts and minds, when we look from the heavenly down to the earthly, the devil will never colonize that nation.
  so in general, what is now circulating about DC gebriel will probably change if for sure the members come jointly hand to hand with the former founders who are now in a different church. it won't take long to see things change now a days.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Find Woyane’s 52, page manual on how to dismantle diaspora churches and organizations. Woyane allocated $90,000,000 to get the job done. What you have in St. Gabriel literally every diaspora congregation that is under the legal synod has them. They have been organized and are working together by misleading the clergy at large. The name of the game is “GREEN BUCKS” you play it you are in you don’t you are out. Can you name one church in any state that is peacefully worshiping God. I can’t because They have infiltrated every congregation if not for loot to create havoc. You can smell the Negas’, the Solomons’, the Amabachews’ from a mile away. I am sure you know what I am alluding to, if you don’t thank God for the internet.
   Rightful establishers of churches get together throw out the rascals and take back your churches. Get Bible teachers listen and learn what God is saying to you. Whether you like it or not there will be a day of reckoning when each of us would stand in front God to answer for how we lived our lives. You have to be ready with an answer that will satisfy God. We came with nothing we go back with nothing. Most of all pray for the Rascals for God to show them the way!!

   Delete
 24. አይ ዲሲዎች ሁሉን አባራችሁ ከማን ጋር ልትኖሩ ነዉ?
  እኔስ ፈራሁ ምን ቀረ ምእመናኑን አባረራችሁ፤ ከፓትርያርክ እስከ ጳጳስ ፤ ከመነኩሴ እስከዲያቆን አባረራችሁ ምን ቀረ ? ገብርኤል ና ስላሴ ታቦታቱ ብቻ ! ከነሱም አንዳቸዉን ከግቢ እንዳታባርሩ እሺ!!!ልብ ይስጣችሁ
  ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
  Replies

  1. When I think about the DC saint Gebriel church congregants, what it reminds me about is:" the naive bull which was never though of the cliff, but devour the grass that brought about its demise." they were told by many of the wise, religious and smart people that something illusive or a kind of monster should have been behind all of that so as to brutally demonize, harass, inflict pain to the children, women and innocent members of the church; after all of that, especially defeaming and blackmailing Abaweldetnsae, abune Samuel,Abune Yakob, Abune Yosef, Aba gebreslassie and the others, now it is in the hands of different people. If there is at least one person among these people who wanted to recollect the serious events that took place, remorse will never replace the damage which had been inflicted up on the entire children of GOD.

   Delete
 25. Gena Gud yesmale kehager__ ??+ M/r Free Sew Ante ena M/r Sahile Mariam Afeworq from Uk achberbaree Lebwoch anten Belo memhir kakakaka+kkkkkkkk

  ReplyDelete
 26. አስተያየት ሰጩ አልሰማህም!!!
  ዲሲዎች እነ እገሌ እገ. እገ ሥላሴን ካበሩ ቆዩኮ አንተ ስላልሰማህ ነዉ እንጅ!
  እ!አዎ
  ያነተ ያለህ
  እረ እዲያዉም ገብርኤልንም ፈርተዉት ነዉ እንጅ እስካሁን አያቆኡትም ነበር
  እና ጉልበት ያለዉ ነዉ የሚኖር እያልከኝ ነዉ ?
  አዎ ፬ ነጥብ።

  ReplyDelete
 27. እንደ አባ ሰላማ ያለ አንድ አምስት ወብሳይት ቢኖር ኑሮ ስድብን ለአለም ማስተዋወቅ ይቻል ነበር ግን አንድ ብቻ በመሆኑ ቢዝነሱ አዋጭ የሆነ አይመስለኝም አሁን በአባ ሰላማ የሚሰደቡ እንደክብርና ኩራት እየተሰማቸው ነው ታቦት አያስፈልግም የሚል ቅዱሳን አያማልዱ የሚል ክርስቶስ አማላጅ ነው በሚል ድረ ገጽ መሰደብ በረከት ነው የሚሉ እየበረከቱ መጥተዋል ሰላማዎች አቅጣጫ ቀይሩ እናተ ይምታዋርዷቸውን ህዝቡ እያከበራቸው ነው ይህ ደግሞ ከተቋቋማቹሁበት አቋም ጋር ይጻረራል ይህ ጥቆማ የሚጠቅም ከሆነ ገምግሙት

  ReplyDelete
 28. ግን? ግን? ይች የዲቦርስ ወረቀት ፎርጅ ብትሆንስ? ሰዎቹ አሁንም አብረው ነው የሚኖረ የሚል ወሬ አለ እውነት ቢሆንስ?ፍቹ እውነት ቢሆንስ 15 ትዳር ፍቶ የኖረው የዛሬ አመት የመነኮሰው። አባ ብርሃኑ ይህን ያህል አመት ሲኖር ክህነቱ ያልፈረሰው የአባ ሰላማ ደጋፊ ስለሆነ ነው? ወይስ ዲሲ ገብርኤል ቢሆን ኑሬ ከሚስቱ ሲጣላ ገና ይፈርስ ነበር ለማንኛውም ደሲ ገብርኤል መኖር ወንጀል ከመሆኑ በፊት ይህ መምህር ቢለቅ ጥሩ ነው?ይመከር። ካልሆነ ደግሞ በስቸኳይ ሌላም ጽሁፍ ይውጣበት ።ለስም ማጥፋት ጽሁፍ እኔም እተባበርአለሁ እሱ ለቆ እነ አባ ወልደ ትንሳኤ እስካልተመለሱ ድረስ አንለቀውም አሁን ጊዜው ነው

  ReplyDelete
 29. ዛሬ ፍሬሰው እዛ የተቀደሰ መድረክ ላይ ቆሞ ለ 30 ደቂቃ ሲሳደብ ነው የዋለው። ይህ የሚያሳየው የሰው ልጅ አወዳደቁን ሲያበላሽ ነው። በእግዚአብሔር መድረክ ላይ ቆመክ ወንጌል እና ይቅርታን እንደመስበክ እኔ ቅድስ ነኝ አዋቂ ነኝ ዝም ስል ፈርቼ አይደለም ስትል ዋልክ። በእርግጥ ያንተን ቅድስና የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው። ወደ ቅድስና እንዲያመጣህ ጸሎቴ ነው። ነገር ግን ይህን ሁሉ ሰው ቢመሰክርልህ ይሻልህ ነበር። እውቀትህንም እንዲሁ። ለዛ ሁላ ሰአት አፍህን ስትከፍት የታየው ባዶ የሆነው አስተሳሰብህ ነው። አንድ ነገር ልምከርህ ወዳጄ ለሚያልፈው ነገር ሁሉ ብለህ አምላክህን አታሳዝነው። ክፋትን ሁሉ አውጥተህ ከእስጥህ ጣል። አውቃለው ስላልክ ታውቃለህ ማለት አይደለም። በዘመናችን ብዙ ቅድሳን እና አዋቂዎችን አይተናል ግን ሰው ነው እንጂ የመሰከረላቸው ስለራሳቸው አላወሩም። አትታበይ!! ዛሬ በል በል የሚልክ ነገ አውጥቶ ይጥለሀል። ከአንተ በፊት የነበሩትንም እንዲሁ ነበር ያደረጉት። አንተ ተሀድሶ የምትላቸው ሰዎች ምን አይነት በክርስቲያኖች እንደሆኑ ብታውቅ ጥሩ ነበር። የዛሬው ትምህርት መልሰህ ብትሰማው በጣም ነው የምታዝነው። አንድ አዋቂ ነኝ ከሚል ቀፎ ራስ አይጠበቅም። ነጋ፣ ያረጋል የዚህ ህዝብ ላብ እና ደም ይፉረዳችሀል እና እናንተ ጥቂት የነሱ ጋሪዎች ስለ እውነት ኑሩ እባካችሁ።

  ReplyDelete
 30. ለ30 ደቂቃ ሲሳደብ ነው የቆየው ---ለዚያሁላ ሰአት አፍህን ሰትከፍት ነው የዋልከው 30 ደቂቃ እና አፍህን ስትከፍት ምን አኛኘው? ስድብ ውሸትና እውነት ለይተሽ ለመናገር 80 መሙላት አለብሽ በሰባው አልተሳካም ወ/ሮ አፕሬቲፍ እየመረቅሽ ነው? ምነው ስጋ ውና ደሙን ብትቀበይ መምህሩ እኮ ያለው በሥራዓት ኑሩ ቤተክርስቲያን ማስመሰያና ጊዜ ማሰለፊያ አይደለችም ነው ያለው ካልገባሽ ኢድ ሙባረክ ካልሆነ በቀይ ኮከብ ዘመቻ እናስገድደው አለን ባል ከማስገደድ አይበልጥም የተሃድሶ አቀንቃኝ መሆን መብት ቢሆንም ደሲ ገብርኤል በቃቃቃቃቃ ቂቂቂ

  ReplyDelete

 31. When we were together during the good old days at saint gebriel church, what was at least one good thing which one can really learn was that gospel preaching was an important element, although the weak part was clearly observed from the men side with partial negligence, in fact which would not allegedly imply all. If one has to do survey how much they really were impressed with the teachings of Abba Weldetnsae is just almost okay, but he preached so as to equip the congregants with the word of GOD, so that members of the church would develop their understanding of the parable to the extent of knowing it fully; whereas many in other US churches really turned themselves in to a disciple. In this regard I can not mention one in the DC area, why? the hearts were never open for the gospel could somehow answer the question, that is why they were standing against their fathers, like the organization doing this sort of business, who knows, they probably might have been mislead by those people who are marked by doing business of this kind mischievously for a decade; obviously the actors are the very same people we know, and now when they come to realize that they were abandoned by these impudent rascals, what they really need to do, is allying themselves with the very founders of the church and refrain from accepting new members and creating a way that would pull in gospel preachers of the old days, creating a committee that would initiate the ground work for the commencement of a conciliatory course between the members who left the church. Besides, it is also vital to identify the church members who are thought to be allying themselves with dangerous elements.
  I am sure these people would never give another chance to be fooled and dress embarrassment; it is not fun watching a church bought by congregants taken away by a strong group which did not spend a single penny.
  in history that I have known by confiscating a house was the DERG regime, and this time now, an organization so adamant is doing the same business of confiscating churches of congregants,and by this I still say to myself if DERG elusively is active and harassing Ethiopians world wide?

  ReplyDelete
 32. አባ ሰላማዎች በጌታ በኢየሱስ አምነን ዳግም ተወልደናል የምትሉ ከሆነ ገብርኤል ሚካኤል "ቤተክርስቲያን" ውስጥ ምን ትሠራላችሁ?
  ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
  15 ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? (2 ቆሮ 6:14-15)

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless you my brother

   Delete