Friday, March 11, 2016

“ቤተ ክርሰቲያናችን በቅኝ ግዛት ... በቅኝ ገዢዎች ተይዛለች፡፡” (ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አባ ማትያስ)

Read in PDF

ክፍል 2
የአለማዊ መሪዎችና የፖለቲካ ጉርብትና ጉዞ ቅን መንገድ ይመስላል እንጂ ለቤተ ክርስቲያን የሞት መንገድ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ሕብረቷ ሙሽሪት እንድትሆን ለሙሽራው ኢየሱስ ካጫትና እንድትሆንለትም ዘወትር ከሚያጠራት ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ብቻ ነው፡፡  በዚህ እውነት የሚስማማ ወገን፣ ሕዝብ፣ ነገድ ፣ ብሄር ሁሉ አካሏ ነው ፤ ይህን እውነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚንድና የማይቀበል ግን በማናቸውም አይነት መልኩ ሊዛመዳት ሊቀራረባት ፈጽሞ አይችልም፡፡ 
    ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ማኅበር ቤተ ክርስቲያንን ለዳግመኛ ባርነት ከሚያጭበት መንገድ አንዱ  እንግዲህ ይህ ነው፡፡ ለዚህ ሃሳብ ማስገበርያነት የወንጌል ልብ የሌላቸውን ፤ ዓለማዊ ዕውቀትና ዝና ያላቸውን ጋዜጠኞች ፣ መሪዎች ፣ ነጋዴዎች ፣ የቤት እመቤቶች ፣ አርቲስቶች ፣ ዘፋኞች ፣ ደራሲዎች ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችንና መምህራንን ፣ ለሕዝብና ለእውነት ያላደሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንና ሌሎችንም ይጠቀማሉ፡፡

     “መስማትን ጆሮ ያለው ይስማ” የሚለውን የማያስተውልና ለወንጌል እውነት የማይገዙ ፤ የንስሐ ልብ የሌላቸው የትኞቹም አካላት (አለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ካባ የደረቡ ቢሆኑ) የመስቀሉ ሥራ እንቅፋት ናቸውና ጠላት ከሚለው የዘለለ ስም የላቸውም፡፡ (ፊልጵ. 3፥18) የመጀመርያይቱ ቤተ ክርስቲያን አባላት እንዴት “ነጻነት እንኳ ያልነበራቸው ሰዎች” እንደነበሩ ስናስተውልና ጌታ ግን ሮማንና የአለምን ዳርቻ በወንጌል እሳት ለማቀጣጠል እሳት የለኮሰው ከታች መሆኑን ስናስተውል ይህ አደራጃጀት የምን እንደሆነ ማስተዋል መንፈስ ቅዱሳዊ ልብ እንጂ ሌላ ያስውላል ብሎ መጠበቅ የዋኅነት ነው፡፡
    ማኅበረ ቅዱሳን ይህ መንገድ ስላልጣመው ወይም ብርና ወርቅ ስለማያመጣለት ደመወዝና የንግድ ወረት ያላቸውን እግር በ’ግር እየተከተለ ያጠምዳል፡፡ እንዳለመታደል የሰው አገር መሪ ጣዖት ሆኖብን እስከማፍቀር ስንደርስ ፤ የአገራችንን መሪ ግን በቅጡ “በሙያ ቋንቋ” ከመውቀስና ከመገሰጽ ይልቅ መሳደብ ፣ ማንጓጠጥ ፣ ማንቋሸሽ ፣ መጥላት ይቀናናል እንጂ የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር (ብዙ ድካምና ነቀፌታ ቢኖርባቸውም) “ሰለፊያ የማኅበረ ቅዱሳን ግልባጭ ነው” ብለውም ነበር፡፡
    የፖለቲካው መሪ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሃይማኖት ካባ ለብሶ የፖለቲካ ኅብረት” የፈጠረውን ማኅበር በልኩ ገልጠውታል ማለት ይቻላል፡፡ በእርግጥም የማኅበሩን ረዣዥምና ስውር የሌሊት ስብሰባዎቹን በማስተዋል የተከታተለ ይህን እውነት ለመረዳት እማኝ አያስፈልገውም፡፡ ከዚህ ባሻገር ከዋና ማዕከል እስከንዑስ ጣቢያ [i] በፖለቲካዊ ዕዝ አደረጃጀት መልክ እስከ ወረዳ መውረዱን ላየው እንዲህ ያለውን ትምህርት ከማን ተማረው ብሎ መጠየቁ እባባዊ ብልኅነት እንጂ “ርግባዊ የዋኅነትን” አይጠይቅም፡፡
    የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከቫቲካን ዋና ማዕከሏ በጽኑ ሠንሠለታዊ ዕዝ “በአንድ መንፈስ” ትመራለች፡፡ ነገር ግን እንደምናየው ፖለቲካዊ እንጂ መንፈሳዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር “አልታደለችም”፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አካሄድ ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አካሄድ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለመቆጣጠርና ቅኝ ገዥ አድርጎ ለመምራት የሚጥረው በመንፈሳዊ ሕይወት ልኬትና ቅድስና ሕይወት በበዛበት በወንጌል ልብ ሳይሆን አስተዳደራዊ መዋቅሩን በመቆጣጠር የመሪነት ሥልጣኑን ለመቆናጠጥ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽፋን ተጠቅሞ “በለብ ለብ” ሥልጠና “ግራ ቀኛቸውን” እንኳ በደንብ የማያስተውሉ ደጋፊዎችን የሚያከማቸው፡፡
     እኒህ ደጋፊዎቹም በየድኅረ ገጾች ስድብ ፣ ጥላቻ ፣ ስም ማጥፋት ፣ አሽሙር ፣ ክስ ፣ ባዶ ጩኸት ፣ ዛቻ ፣ አድማ ፣ ሐሰተኝነት ... ዋና መገለጫቸው ነው፡፡ ደስ የሚለው ስለማያውቋቸው ወገኖች ጥሩ የማስታወቂያ ሠራተኞች መሆናቸው ነው፡፡
ስለቤተ ክርስቲያን ግን ይህ ያስጨንቀኛል!
    ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አደረጃጀቱ ቤተ ክርስቲያንን ላይጠቅማት እንደሚችል ለመናገር ነቢይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ምናልባትም በዚህ ሥራው የሰምርኔስንና የፊልድልፍያን ቤተ ክርስቲያን ያውኩ እንደነበሩት አይሁድ ከተሰጠው ስያሜ አያመልጥም፡፡ ትልቁ መሻታችን ግን ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ እጅግ ከሚነቀፍበትና ካባ ለብሶ ስውር ደባውን ከሚያራምድበት ተግባሩ ልቡን ወደወንጌል አድልቶ  ንስሐ ገብቶ ቢመለስና ለቤተ ክርስቲን ራስ “ለክርስቶስ ኢየሱስ” ቢገለጥ የተሻለና መልካም ነው፡፡
    ከዚሁ ጋር ትይዩ ማኅበረ ቅዱሳንን በመጻረር የቆሙ አካላትም ለቤተ ክርስቲያን ምን ያህል የሚበጁና የሚጠቅሙ ናቸው የሚለውንም ማናሳቱ ግድ ይመስላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በማጮኺያው “ተሃድሶ” የሚላቸው ወገኖች ጨፍኖ እንጂ አጥርቶ አይመስልም፡፡ ነገሩን የእብድ የእብድን የመረረ ጥላቻ የሚያስመስልበት ግብረ ሰዶማውያንን ጭምር አካቶ ማጠልሸቱ መዝለፉ ነው፡፡ ለእኔ ማኅበረ ቅዱሳን ተሃድሶ የሚላቸው አካላት ሁለት ፍጹም ተቃራኒ መልክ አላቸው፡፡
      የመጀመርያዎቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደፍጹም ፕሮቴስታንታዊነት ለመለወጥ የሚሠሩ ፤ በጀት ተበጅቶላቸው የሚንቀሳቀሱ ፤ የለየለት ጥላቻ በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው ሲሆኑ፥ ሁለተኛዎቹ ግን ለእውነተኛቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ማደግና መለምለም ፤ በሁለ ነገሯ መዋብና ለሙሽራው የተገባች ሆና እንድትገኝ ሳይታክቱ የሚሠሩላት ናቸው፡፡ እኒህ ወገኖች ከግብረ ሰዶማውያን “ተሃድሷውያን” ፤ ከማኅበረ ቅዱሳን በፍጹም ተቃራኒ መንገድ ላይ የቆሙ ለወንጌሉ እውነት ብቻ የቆሙ ናቸው፡፡ ማቅ እኒህን ለእውነት ያደሉ ወንጌላውያን ወንድሞችን ተሃድሶ በሚለው ማስጮኺያው ከግብረ ሰዶማውያንና ከሌሎች ጋር ቀይጦ የሚጠራው ራሱን ቅዱስና ንጹሕ አድርጎ ላመቅረብ ነው፡፡ የወንጌል እውነት ግን ሕያውና የዘላለም እውነት ነው፡፡  
      ትልቁ እውነት ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አካሄዱ ቤተ ክርስቲያን እንዳልጠቀማት ሁሉ ለአገርም የማይጠቅም መሆኑ “የተነቃበትን” ያህል ወደእርምጃ የገባ ዕለት መልክ መቀየሩና ተመሳስሎ እንዳለ መኖሩ እንዳለ ሆኖ ምናልባት ግን “ጭሬ ላበላሸው” ወደሚል ወደባሰ ከንቱ ሃሳብ ቢሄድ “የራሱን አባላት በመያዝ የመከፋፈል ሂደት ውስጥ እንዳይገባ” ትውልድን መታደግ የሚችል በመንፈሳዊ ብቃቱ የጎለመሰ አቅም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለን? የሚል አንገብጋቢ ጥያቄ በውስጤ ይላወሳል፡፡ እውነት ግን ለእግዚአብሔር ብቻ ያደላና ቤተ ክርስቲያንን አሁን ካለችበት መንፈሳዊም ሆነ አስተዳደራዊ ችግሯ ነጻ ማውጣት የሚቻለው እውነተኛ አካል አለን? ካለስ እንዲህ ላለው ታላቅ መንፈሳዊ ሸክም ራሱን ያዘጋጀ ነውን?
      እንግዲህ “ስም ተልቆ ሥራ እንዳያንስብን” ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ሚዛንነት በሕይወትም  በቃልም የበረታን ሆነን ልንገኝ ይገባናል፡፡ ከተያዘችበት አለማዊ ባርነትና ፖለቲካዊ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ቤተ ክርስቲያንም  ቤተ ክርስቲያን ተብላ እንድትጠራ ለማኅበር ህልውና ሳይሆን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ልንሠራ ይገባናል፡፡


[i]  ማኅበሩ ይህችን በየወረዳና አጥቢያ ያላውን ጽ/ቤት ለፓትርያርኩ በጻፋት ደብዳቤ ላይ በአጥቢያና በደብር ላይ ምንም አባልና ጽ/ቤት የለኝም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል፡፡

14 comments:

 1. የማህበረ ቅዱሳን አካሄድ በዚች ቤተ ክርስቲያን ስም ሆነ እንጂ(ከእውነተኛ ባሏ ተፋታ ባለ ብዙ ውሽማ የሆነች)ለእኔም የኢሕአፓን ሽታን ነው የሚሸተኝ፤
  ለጸሐፊው ግን ጥያቄ አለኝ??????
  1)በእውነት በጀት ተመድቦለት ኦርቶዶስን ፕሮቴስታንት ለማድረግ የሚሠራ ተሐድሶ አለ? ስማቸውን ቢጠቁሙኝ ተከታትየ በማረጋገጥ እንድሞግታቸው!
  2)ያገራችን ፕሮቴስታንቶችስ የሚሠሩት ሰው በክርስቶስ እንዲድን ነው ወይስ ኦርቶዶክስን ፕሮቴስታንት ለማድረግ? አዎ ከሆነ መልስዎ ለምን እረ አሁንም ለምን???
  እባክዎት እነዚህን ጥያቄዎች በ eunethiwot@gmail.com በአስቸኳይ ቢልኩልኝ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል።

  ለሁላችንም የሰማይ ማስተዋል ይብዛልን!

  በማይለውጥ በእግ/ር ፍቅር

  የቀደመውን ፍቅርሽን ትተሻል ልጅ
  ከመቀሌ ከተማ

  ReplyDelete
 2. ወረኞች ናችሁ። ይህን ትርኪምርኪ የምትጽፉበትን ጊዜ ለቁም ነገር ብታውሉት ይበጃችሁ ነበር። ያልታደላችሁ

  ReplyDelete
 3. ለሀራጥቃ ቦታ የለንም፡፡ አትታክቱ ሁላችንም ለቤተክርስቲያናችን ማኀበረ ቅዱሳን ነን፡፡ አምላከ ቅዱሳን አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፡፡

  ReplyDelete
 4. 99.9% of your issue is all about MK. please leave MK alone,they have a lot of responsibility from God. go away and do your Protestantism missionary out of the Church. no body hears your barking.

  ReplyDelete
 5. Mk abaltum mahberum 666 kemahber lay aynachun ansuna aynachun yemotelachu geta lay adregu.hezbu kerstosn endaywed endayaye mehal lay yetedeneqre mahber.yebetcrstiyan kefafay atfi mahber.ye elsabel lejjoch mahber.

  ReplyDelete
 6. That is absolutely correct.They make really no point,just barking Mk...kkkk...

  ReplyDelete
 7. አዬ ጉድ ከራሱ ጋር የተጣላ ትውልድ እንዴትኮ ለትክክለኛ አቅጣጫ ይቆማል?
  ስንኳንስ አይኑን ያልገለጠ ሦስትኛው ዐለም፤ ዐይን ገልጠናል የሚለው ዐለም ግራ ተጋብቶ የሚይይዘውን የሚጨጠውን በማጣት የባቢሎን(ሰናዎር)ግንብ ገንቢዎችን መስሎ አርፎታል።ይሁንጂ ሕልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር ነውና ከሆነ ስድብ ሳይሆን ደርዝ ያለው ክርክር ያስፈልጋል።መሥመሩን እንዳይስት ግን አጥብቆ ይጠነቀቋል።ይትወላወል ሰብእ እምጊዜ ልደቱ እስከ ዕለተሞቱ(ሰው ተወልዶ እስኪያረጅ ተሹሞ እስኪሻር ተኝቶ አያድር ሁልጊዜ በሥጋትና በጥርጥር ስለሚኖር ማነኛውም የሰው ፍጡር የቅጽል ስሙን ማንበብና መመርመር ይገበዋል።ቅጽሎችም
  "ወላዋይና መናፍቅ"ናቸው።እነዚህንን እና የመሳሰሉትን የቅጽል ቃላት በየመድረኩ የሚጠቀሙ ሰባክያን የባሰባቸው መናፍቃን ናቸውና መጥኖውን ይስጣቸው ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ የሚለውን የሽማግሎችን አባባልንም ቢያስታውሱ መልካም ነው።

  ReplyDelete
 8. ደስ ሲል! ዛሬ ሐራ ጥቃዎች/ተሐድሶ/ ለሁለት ተከፈሉ፡፡ ከላይ በቀረበው ጽሑፍ እንደተገለጸው “የመጀመርያዎቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደፍጹም ፕሮቴስታንታዊነት ለመለወጥ የሚሠሩ ፤ በጀት ተበጅቶላቸው የሚንቀሳቀሱ ፤ የለየለት ጥላቻ በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው ሲሆኑ፥ ሁለተኛዎቹ ግን ለእውነተኛቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ማደግና መለምለም ፤ በሁለ ነገሯ መዋብና ለሙሽራው የተገባች ሆና እንድትገኝ ሳይታክቱ የሚሠሩላት ናቸው፡፡” ሲሉ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡ ነቄው ማኅበረ ቅዱሳን ሁል ጊዜ ምንድ ነው የሚለው፡፡ እኔ ከማውቀው እንኳን ብናገር ሐራ ጥቃዎች/ተሐድሶ/ እራሳቸውን እንደአሜባ ሴል በየጊዜው እራሳቸውን እንደሚከፍሉ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ከ3ሺ በላይ እርስ በርስ የማይግባቡ የሚመስሉ ግን ለአባታቸው ማርቲን ሉተር የሚሰሩ የፕሮቴስታን ሴሌች አሉ፡፡ ጥረታቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ፕሮቴስታንት ማድረግና ከውጪ የሚመጣውን ፈንድ መቀራመት ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ ደግሞ በጀት የሚመደብላቸው እንደሆኑ ከላይ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ የተቀመጠውና በዚሁ “አባ ሰላማ” ድረ ገጽ ላይ የወጣውን ጽሑፍ መመልከት ብቻ በቂ ያደርገዋል፡፡
  “አባ ሰላማ”ዎች እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ይህንን ድረ ገጽ ለምታንቀሳቅሱት አካላትና በድረ ገጹ ላይ ጽሑፍ ለሚጽፉ አካላት በጀቱን የሚመድብላችሁ ማን ነው? ከልብ ይቺን ጥያቄ እንድትመልሱልኝ እፈልጋለሁ! ከዚያም አብረን እንቀጥላለን፡፡ ምርጫ ልስጣችሁ መሰለኝ!
  ሀ/በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ እራሳቸውን ፕሮቴስታንት ነን ብለው ካወጁ አካላት፡፡
  ለ/በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ሙዳይ ገልባጮችና እንዳይነቃባቸው ከሚፈልጉ አካላት፡፡
  ሐ/በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ላይ ሆነው ቤተክርስቲያኒቷን ፕሮቴስታን ለማድረግ ጥረት ከሚያደርጉና የውጪ ድጋፍ ካላቸው፡፡
  መ/ መንግሥት መዋቅር ላይ ካሉና የቤተክርስቲያኒቷን ውድቀት ከሚሹ አካላት፡፡
  ሠ/ሁሉም

  ReplyDelete
 9. ኤጭ! አሁንስ “አባ ሰላማዎች” አበዛችሁት፡፡ እራሳችሁ እንዴት እንደምንሳደብ አስተምራችሁን ትውልዱ ተሳዳቢ ሆነ ትላላችሁ እንዴ? አይደብርም? ይህን ጽሑፋችሁንንና ከዚህ በፊት በራሳችሁሁ በዚሁ ድረ ገጽ የወጡትን ጽሑፎች ተመልከቷቸው እስቲ! እውነቴን ነው የስድብ አስተማሪ እኮነው የሆናችሁት፡፡ በስድብ ከዚህ ዓለም የሚጠፋ ቢሆን ኖሮኮ ማኅበረ ቅዱሳን ይሄኔ ቤርሙዳ ውስጥ እንኳን ቢፈለግ አይገኝም፡፡ እባካችሁ ስድብ ቀንሱ፡፡ ለራሳችሁ ጥሩ አይደለም፡፡ “ተሳዳቢ ጸሐፊ ተሳዳቢን ትውልድ ያፈራል፡፡” ስድብ ጽፋችሁ ራሳችሁ “ተሳዳቢ አትሁኑ” ትላላችሁ፡፡ ስትገርሙ!
  እባካችሁ ትውልዱን የሚቀርጽ ጽሑፍ አስነብቡን፡፡ እስካሁን ግን እውነቴን ነው የምላችሁ አልተመቻችሁኝም፡፡ እውነተኛ ከሆናችሁ ስድቡን ትታችሁ ማኅበሩ ድክመት ካለበት በጎውን አንስታችሁ ለመምከር ሞክሩ፡፡ ይህን መንገድ ትምህርት ቤት ገብታችሁ አልተማራችሁም?፡፡ በቅርቡ ማኅበሩ ለፓትሪያሪኩ የሰጠውን መልስ አንብቡ፡፡ አውቃለሁ አንብባችሁታል፡፡ ግን ተማሩበት ነው የምለው፡፡ ይህንንም ማኅበሩ የሰጠው መልስ ፓትሪያሪኩን ወደላይ ነው ወደታች ያየ በሚል እኛን ሥነ ምግባር ለማስተማር ጥራችሁ ነበር፡፡ በጸሎት የሚመራ ማኅበር ደብዳቤው እንኳን እንዴት አስተማሪ እንደነበር አያችሁ አይደል፡፡ አቃቂር ለማውጣት ደጋግማችሁ ስታነቡት እንደነበር አውቃለሁ፡፡ እንዲሁ ገመትኩኝ፡፡ ግን አልተሳካላችሁም፡፡ ግን እባካችሁ ሥነ ምግባር የሚባል ነገር ተማሩ!

  ReplyDelete
 10. Tegeremahlacho edemelekachon were bicha endaweracho ye beatekeresetane habetan eyemezeberacho yamenewene kirsetane menafeke eyaderegacho "wedacho amilakacho keberaracho be neweracho Asbacho midderawe " selewenacho enatete ke Zeregnenete ke meleyayet yalefe serane ateserom .... egna ahgerachen be semay new anesemachewem ......

  ReplyDelete
 11. እውነት "ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ፍጹም ኘሮቴስታንታዊነት ለመለወጥ የሚሠሩ፣ በጀት ተበጅቶላቸው የሚንቀሳቀሱ፣ ..." ካሉ አንድ አስተያየት ሰጭ እንዳሉት በግልጥ ብናውቃቸው፡፡ ማቅ ምናምን የሚባለውን ተዉት፣ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች አሳዳጅነቱ ገና ድሮ ታውቋል፡፡ አሁን ደግሞ የዘራውን ሲያጭድ፣ ራሱን በራሱ ጠልፎ እየጣለ ነው፡፡ ጀሌዎቹም ረጅም የስድብ ምላስ እንጂ ሌላ ቁም ነገር የላቸውም፡፡ ስድና ጸያፍ ንግግራቸውን ከመስማት አምላከ ቅዱሳን ጆሮቻችንን ይጠብቅ፣ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 12. And enkua wengel yemaysebekibet blog.U are here to write about mk only?Eski ende mk blog Timehret Tsafuna bewengel mizan enmezinachihu.Alamachihu mesadeb bicha new ende.

  ReplyDelete
 13. Eyen wuolo good yezacho new Tadiso menafekane ena Amasagno Musegnawe Group Mahber Kidousan Lay Tatachewen Yemitekeserote .... lenegero eyen Newrwerachewen eyagaletebacho selewenen new ke memelese ena be Egizahber Kale ke menore yeleke ke atatate lay ateyaten yemitechemirote....

  ReplyDelete
 14. please 'Aba selama'/Tehadiso reply the following questions: 1) Don't you know that Mahibere kidusan is accepted by the Ethiopian orthodox synod but you rejected(during 2004E.c synod assembly)?? 2)Can you Mention at least one wrong preaching of Mahibere kidusan? 3)why you always talk about Mahibere kidusan?Don't you have any other Agenda/preaching rather than Mahibere kidusan? Any way Long Live Mahibere Kidusan!!!!!

  ReplyDelete