Wednesday, March 16, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ላይ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማሰጨበጫ እንዳይተላለፍ ታገደበአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሩ እየተዘጋበት ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ዕድሜውን ለማራዘምና ደጋፊዎቹን ለማብዛት እየሰራባት ያለውን ስለተሐድሶ ግንዛቤ አስጨብጣለሁ የሚለውን ስልቱን ወደ ክፍለ ሀገር በማዞር በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ሲታወቅ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰሞኑን በደቡብ ክልል በዲላ ከተማ በገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ከመጋቢት 2-4/2008 ዓ.ም አዘጋጅቶት የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በሰንበት ት/ቤቱ ተጋድሎ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ለግንዛቤ ማስጨበጫው ወደ ዲላ የሄዱት ፖለቲካና ሃይማኖትን እያጣቀሰ የሚንቀሳቀሰው የማቅ አባል ታደሰ ወርቁ እና ዓባይነህ ካሴ ሲሆኑ ኪነጥበብና ወርቅነሽ ተፈራ መዝሙር ለማቅረብ የተገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨባጨውን ያመቻቹት የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ታዬ ሲሆኑ እኚህ አለቃ ከማቅ ጋር የተጠበቀ ግንኙነት ያላቸውና ማቅ በአርአያውና በአምሳሉ የቀረጻቸው ስለሆኑ በልማት ስም እየተንቀሳቀሱ ከሚገኝው ትርፍ በአካፋ ለራሳቸው እየዛቁ ለቤተክርስቲያን ግን በማንኪያ የሚያስገቡ አማሳኝ ናቸው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ዘንድ ማቅን መደገፍ በሙስናም ሆነ በማንኛውም ወንጀል የማያስጠይቅ በጎ ስራ ተደርጎ ስለሚወሰድ አባ ታዬም ማቅን ተጠግተው የቤተክርስቲያንን ገንዘብ የሚበዘብዙ አማሳኝ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም ለማቅ ትልቅ ቦታ በመስጠት ከሰንበት ት/ቤት ጋር የሚጋጩ አለቃ ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያለን ሰንበት ት/ቤት አሳንሶ ማየትና ለማቅ ቦታ መስጠት በጥቅም ግንኙነት የሚመጣ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የአለቃውን አማሳኝነት የተገነዘቡት የደብሩ ሰንበት ተማሪዎችም አለቃው አማሳኝነታቸው ሳያንስ ከማቅ ጋር በመሞዳሞድ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል የተዘጋጀውን መርሐ ግብር በመቃወም መርሀ ግብሩ አይካሄድም በማለት ከአለቃው ጋር ግጭት ውስጥ የገቡ ሲሆን አለቃውም በመጀመሪያው ቀን ሸሽተው ሄደዋል፡፡

ተቃውሞው ቀጥሎ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚቃወሙ ምእመናንና የሰንበት ተማሪዎች መርሐግብሩ መካሄድ የለበትም የሚል አቋም ይዘው የታገሉና ከዚህ ቀደም በክልላችን ሲበጠብጥ የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን ድጋሚ እንዲበጠብጥ ዕድል ሊያገኝ አይገባም በሚል የተቃወሙ ሲሆን ጉዳዩ ከወረዳው ቤተክህነት ወደዞኑ አስተዳደር ደርሶ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የተሞከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ማቅ ከዚህ ቀደም እየፈጠረ ያለው ችግርና የተያዘበት ሪከርድ አደገኛ መሆኑ ስለታመነበትም ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚለውን መርሀ ግብሩን እንዳያካሂድና ሌላውን ትምህርት ግን ኃላፊነት ወስዶ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲያካሂድ ከስምምነት ላይ ተደርሶ በዚያ መልኩ መርሐ ግብሩ ሊካሄድ ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በላፕቶፕና በስክሪን ተደግፈው የሚያቀርቡትን የግንዛቤ ማስጨባጫ ተብዬ ዲስኩራቸውን በቀጥታ ማስተላለፍ ባይችሉም የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ ወንጌልን መስበክ ሳይሆን ተሐድሶ ተሐድሶ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡

ስለጉዳዩ ዘግይተው የሰሙት የክፍሉ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለወረዳው ቤተክህነት ደውለው ስለጉዳዩ በመጠየቅ ጉባኤው እንዲታገድ ያዘዙ ቢሆንም ጉዳዩ ከላይ በተገለጸው መልኩ ተይዞ ከስምምነት ላይ መደረሱ ስለተነገራቸው ሊቀጥል መቻሉን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡     

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሩ የተዘጋበት ማቅ ትኩረቱን ክፍለ ሀገር ላይ በማድረግ ብዙዎችን ወደዓላማው ለመሳብ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ በየቦታው ከሚያደርጋቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቤተ ክህነቱ የሚያወጣው መመሪያ በመላ አገሪቱ ተግባራዊ ካልሆነ ለቤተክርስቲያን እንድነት ትልቅ ችግር የሚፈጥር ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡ በጠንካራ የአንድነት መንፈስ የሚታወቀውና ማንም ሊሸረሽረው የማይችለው የተባለለትን የቤተክርስቲያኒቱን ተቋማዊ መዋቅር ማህበረ ቅዱሳን በመለመላቸው ጀሌዎቹና በተለያየ ምክንያት በሚደግፉት ጳጳሳት አማካይነት በቤተክህነት አስተዳደር ወጥነት እንዳይታይ እያደረገ ነውና እንደአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሁሉ ሌሎቹም አህጉረ ስብከቶች ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የቤተክርስቲያንን ሉዓላዊነት ማስከበር አለባቸው፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን ሳይሆን ለቤተክርስቲያን መሥራትም ይጠበቅባቸዋል፡፡      

     

8 comments:

 1. የመንደር ወሬ..... ክስ አለቀባችሁ?

  ReplyDelete
 2. “አባ ሰላማዎች” እባካችሁ የአንድ ጽሑፍ ርዕስ ዋጋ አለው፡፡ ጽሑፉንም እንዲወክል ተደርጎ ነው ርዕስ የሚሰጠው፡፡ ይህ አልገባችሁም? “ማኅበረ ቅዱሳን ዲላ ላይ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማሰጨበጫ እንዳይተላለፍ ታገደ” ስትሉ ምን ማለት ነው? ለእኔ እንደሚገባኝ ሊደረግ የታሰበው ጉባኤ ተሰረዘ፣ ሳይካሄድ ቀረ ማለት እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ ግን ጽሑፋችሁ ሲነበበ ይህን አይልም፡፡ ሊታገድ የነበረው ጉባኤ በስምምነት እንደቀጠለና መምህራኖቹ ስለተሐድሶ ሲያስተምሩ እንደነበር ነው የሚገልጸው፡፡

  በዚሁ ጽሑፋችሁ ሦስተኛው አንቀጽ መጨረሻ ላይ

  “ይሁን እንጂ በላፕቶፕና በስክሪን ተደግፈው የሚያቀርቡትን የግንዛቤ ማስጨባጫ ተብዬ ዲስኩራቸውን በቀጥታ ማስተላለፍ ባይችሉም የእግዚአብሔርን ቃል በመጥቀስ ወንጌልን መስበክ ሳይሆን ተሐድሶ ተሐድሶ ሲሉ ሰንብተዋል፡፡” ብላችኋል

  ምን ይሻላችኋል? እውነትን በየቀኑ መስቀልና ብሎጉን የሚያነበውን ሰው ለምን በአንድ ብዕር ሁለት ነገር ጽፋችሁ ታሳስቱናላችሁ፡፡ አንድ አንባቢ “ከዝንብ ማር አይጠበቅም” ያለው እንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ አስነብባችሁት በሆን አለበት፡፡

  እናንተ የሰው ጊዜ ማቃጠል ብቻ ሳይሆን እኛ ምዕመናንን ምን እያደረጋችሁን እንደሆነ አሁን ገባኝ... ሰላም!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እናንተ የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ምን ይሻላችሀል፡፡ ብዙ ጊዜ እውነትን የመቃወምና የማስተባበል አቅም ሲያንሳችሁ፡፡ ወደስድብ ትዞራላችሁ፡፡ አሁን ይህ ዜና ርእሱና ውስጥ ያለው ዝርዝር መቼ የተለያየ ሆነ? ለእኔ ግልጽ ነው፡፡ ታገደ የተባለው የግንዛቤ ማስጨበጫው ነው ይህም በስክሪን የሚተላለፍ ነበር፡፡ ያ ቀርቶ ትምህርት እንዲሰጥ ተደረገ ነው የዜናው መልእክት፡፡ ይሁን እንጂ እነ ዓባይነህ ካሴ በስክሪን ቢቀርም በትምህርት ስም በህገወጥ መንገድና የገቡት ቃል አፍርሰው ግንዛቤውን ተዘዋዋሪ ሰጡ ነው፡፡ ሆኖም በሁለቱ መካከል ልዩነት አለ፡፡ የስክሪኑ በተሐድሶ ላይ የቀረበ ዝግጅት ነው፡፡ በትምህርቱ ግን መጽሐፍ ቅዱስን በመታከክ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ ተሐድሶን የማጥላላት ነገር ተንጸባርቋል፡፡ ስለዚህ በሁለቱ መካከል ልዩነት አለና የግንዛቤ ማስጨበጫው ታገደ ቢባል ከቀረበው ዝርዝር ጋር የሚጋጭ አይደለም፡፡ ከሁሉም የገረመኝ ግን አባ ሰላማን በንቃት እየተከታተላችሁ እንደማትከታተሉ ለማሳየት የምትሞክሩበት መንገድ ነው፡፡

   Delete
  2. ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ እንደፈለግ መንጫጫት ትችላላችሁ ማህበሩ ግን ከመሰራትና የእናንተ ከይሲ ሀሳብ ለህዝብ አሳውቆ ሕዝቡም የእናንተ ርካሽ ተግባር እንዲረዳ ይሰራል፡፡ ደግሞም ለህዝብ ሰላም ብሎ ነው እንጂ የእናንተ ባዶ ቀፎ የሆነ ወሬ በአንድ ቀን ማጥፈት ይችላል፡፡ ደግሞ እናንተም ታውቁታላችሁ በሰው ኃይል ሳይሆን በእግዚአብሔር ረዳኤት የእናነት አፍራሽ ተግባር ለመመከተ ግልበት እንዳለው፤ ሰስለዚህ በእናንተ ፕሮፓጋንዳ የሚደነግጥ ማንም የለም፡፡ ቅጥል በሉ አሁን ሕዝቡ ነቅቶባችኋል ከሕዝቡም ሂሊና ወጥታችኋል፡፡ ይህም በመሆኑ ነው የሞታ ጣር የምታደርጉት፡፡ እናንተ በአማሪካ ዶላርና በአውሮፓ ዩሮ ተመክታች እንዲህ ልባችሁ ደነደነ እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር እንመካልን እግዚአብሔርም ተስፋ እናደርጋልን በእግዚአብሔር ኃይል ድል እነሳችኋለን፡፡ ኢትዮጵያ አገራችን ሀገረ እግዚአበሄር የተባለችውም በአባቶቻችን እምነት እንጂ በእናንተ ዲቃላና አተላ እምነት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሕዝቡም የእናንተ አተላ እምነት የሚሰማበት ጊዜ አሁን አልፏል ስታታልሉት ኖራችኋል አሁን ይብቃችሁ በሏል፡፡

   Delete
 3. ምን መልዕክት እንዳለው እንኳን ግልጽ አይደለም፡፡ እንደው በደመነፍስ እንደምትንቀሳቀሱ በዚህ ይታወቃል፡፡ ማኀበረ ቅዱሳን፣ ማኀበረ ቅዱሳን እያላችሁ ዘወትር ከምታላዝኑ እስኪ አንድ የሠራችሁትን ቁም ነገር አሳዩን፡፡ ወሬና በጌታ ስም መቀለድ .... ዋጋችሁን አታጡም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ግን የቱንም ያህል ፈተና ብትሆኑ በድል ከነ እንቁዕ ልጆቿ ማንጸባረቋን ትቀጥላለች፡፡ የጭቃ ውስጥ እሾሆች ለንስሀ የሚሆን ጥቂት ልብ ካላችሁ ግን ተመለሱ አልረፈደም፡፡

  ReplyDelete
 4. አይ የጴንጤ ጀሌዎች።

  ReplyDelete
 5. “ሰው ድንጋይም ለማምለክ ነፃነቱ አለው፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ መናፍቃንን ዓላማ ማራመድ አይቻልም፤ እኛም ለሃይማኖታችንና በኖላዊነት ለምንመግባቸው ምእመናን እስከ ደም ጠብታ ድረስ መሥዋዕትነት እንከፍላለን፤” መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ“ሰው ድንጋይም ለማምለክ ነፃነቱ አለው፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ መናፍቃንን ዓላማ ማራመድ አይቻልም፤ እኛም ለሃይማኖታችንና በኖላዊነት ለምንመግባቸው ምእመናን እስከ ደም ጠብታ ድረስ መሥዋዕትነት እንከፍላለን፤” መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ

  ReplyDelete
 6. tahadiso mahonachihun iyasawaqachihun tiganyalachiw guba'e altaquraxam mulu ba mulu batasaka hunata tafasama,ba ayne balay noro amanachiw nabara.ahiya shintuwan lamadraq bila ye hod iqawan asayech alu

  ReplyDelete