Friday, March 18, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን ዳጎስ ያለ ገቢ ለማሰባሰብ አቅዶ ያዘጋጀው አውደ ርእይ እና አንድምታውከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ እየተንቀሳቀሰና የቤተክርስቲያንን መዋቅራዊ አሠራር እየተፈታተነ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ለቤተክርስቲያን ህልውና አስጊ በሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴው መገለጫ ከሆኑት የማኅበሩ ተግባራት መካከል አንዱ የቤተክርስቲያንን ሀብቶችና እሴቶች በመጠቀምና እነርሱን ወደቢዝነስ በመለወጥ ያለ ቤተክርስቲያን ፈቃድ በቤተክርስቲያን ስም የተለያዩ ገቢዎችን መሰብሰቡና ለራሱ ድብቅ ዓላማ ማዋሉ የሚጠቀስ ነው፡፡ ከመጋቢት 15-21/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማእከል ለማዘጋጀት ያሰበው አውደ ርእይ የዚህ ሕገወጥ ድርጊት አንዱ ማሳያ ነው፡፡
ማኅበሩ በዚህ ወቅት ይህን አውደ ርእይ ለምን አዘጋጀ? ለሚለው አሁን ካለበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ከታየ ሁለት ትርፎችን አስቦ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ጠቀም ያለ ገንዘብ መሰብሰብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአውደ ርእዩ ሰበብነት ሰዎችን በቤተክህነቱ ይልቁንም በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ ማነሳሳት ነው፡፡ 

ማህበር ቅዱሳን 5ተኛ ዙር ሲል ያዘጋጀው ይህ አውደ ርእይ እንደከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የሚያጋብስበት ዝግጅት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ይህን ዓይነት ነገር ለማዘጋጀት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያን ፈቃድ ይጠይቅ ተብሎ ተወስኖ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት በሚሊኒየሙ መርሐ ግብር ላይ ከጥንታዊ ገዳማትና አድባራት አውደ ርእይ ላይ ለማሳየት ንዋያተ ቅድሳትን ጠይቆ የታገዱበት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ የአብነት መምህራንን ጠርቶ በግዮን ሆቴል ሊሰበስብ ሲል በቅዱስነታቸው ታግዶ እዚያው ሕንፃው ላይ ስብሰባውን ለማከናወን ተገዶ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ እነዚያ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሌላ አካል ጥሪ ያለ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈቃድ አዲስ አበባ እንዳይመጡ መመሪያ የተላለፈበት ሁኔታ ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ አጋጣሚ በኋላ ይልቁንም አሁን ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ባለበት ሁኔታ ይህን አውደ ርእይ አዘጋጀ፡፡ አሁን ደብዳቤ ያጻፈው በማህበሩ ቀንደኛ ደጋፊ በሆኑት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በአባ ማቴዎስ አማካይነት ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ራሱ እንደ ገለፀው አውደ ርእዩን ከ100 ሺህ ሰው በላይ ይጎበኛዋል ብሎ ገምቷል፡፡ ከወዲሁ የቲኬት ሽያጩንም በየንግድ ተቋሞቹ ውስጥና ከቤተክህነት እየጎረሱ ወደማኅበሩ በሚወጡ እንደ ሰአሊተ ምሕረቱ አለቃ ያሉ አንዳንድ ጥቅመኛ የደብር አለቆች አማካይነት አጧጡፎታል፡፡ አውደ ርእዩ ተካሄደም ታገደም ቀደም ብሎ ከወዲሁ መሸጥ ከጀመረው ቲኬት ዳጎስ ያለ ገቢ መሰብሰቡ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ በገቢው በኩል ማኅበሩ ብዙም ሥጋት የለበትም፡፡ ቢያንስ እንደ ነጋዴ የሚያወጣውን ወጪ መሸፈኑ አይቀርም፡፡  
አሁን ባለው ተጨባጭ የቤተክርስቲያን ሁኔታ ይህን ማዘጋጀት ለምን ፈለገ? የሚለው  ግን አንድምታው ሌላ ነው፡፡ የአውደ ርእዩ መሪ ቃል እንደሚጠቁመው በእርሱ ስብከት የሚደለሉትን የዋሃን ምእመናንን ከጀርባው ለማሰለፍ አቅዶ እንደተዘጋጀበት ያሳያል፡፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ ድርሻችንንም እንወቅ” የሚለው የአውደ ርእዩ መሪ ቃል ማቅ በሌለው ውክልናና ብቃት ስለቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በአውቃለሁ ባይነቱ የራሱን ተረታ ተረት ሊነዛ እንዳሰበና የዋሃንንም የቤተክርስቲያኒቱ ባልሆነና ማኅበሩ አስርጎ ሊያስገባ በሚፈልገውና ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱ ወደፊት መራመዷን ትታ የኋሊት እንድትጓዝ ያደረገበትን የስህተት ትምህርቶቹን እንደ ትክክለኛ ትምህርት አድርጎ በማቅረብ በተሳሳተ መንገድ ጀሌዎችን ለማፍራት አልሞ ያዘጋጀው ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን በዚህ ሰበብ አሁን ከቤተክርስቲያን ጋር ከገባበት አጣብቂኝ ሊወጣ የሚችልበትን መንገድ በመፈለግና አንዳንዶችን ለአመጽ ጭምር ለማነሳሳት ሊጠቀምበት እንደሚችል ሰፊ ግምት አለ፡፡ ከዚህ አንጻር በቤተ ክህነቱ የሥራ ድርሻ ጣልቃ በመግባት በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ መፈትፈቱን እንዲያቆም የሚመለከተው አካል መመሪያ ሊያስተላልፍለት ይገባል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ መጨረሻ ላይ ያወጣው የአቋም መግለጫ ማኅበረ ቅዱሳን ሊያዘጋጅ ያቀደው አውደ ርእይ እንዲሰረዝ የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህም በአውደ ርእዩ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መኖሩን ያሳያል፡፡   
ትልቁ ጥያቄ ማቅ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ ሰዎች እንዲጠነቅቁ ለማድረግ ምን ብቃት አለው? የሚለው ነው፡፡ ማኅበሩ ከሚከሰስባቸው ነጥቦች አንዱ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርትና ሥርዓት በማዛባቱ ነው፡፡ ታዲያ እንዴት አድርገው ነው ሰዎች በማኅበረ ቅዱሳን በኩል የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ መጠንቀቅ የሚችሉት? ይህ በእውነቱ ቀልድ ነው፡፡ “ድርሻችንን እንወቅ” የሚለውስ እንዴት ይታያል? ማቅ ደርሻውን አውቆ እየተንቀሳቀሰ ያለ ማኅበር ነው? ብዙ ጊዜ የቤተክርስቲያንን መመሪያ አልቀበል እያለ ሲያውክ የኖረው ድርሻውን ካለማወቅ በመነጨ ስሜት አይደለምን? በተለያዩ ጊዜያት ለተላለፉለት መመሪያዎችና ትእዛዞች እንቢ ብሎ በየደረጃው ላሉ የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎችና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለሆኑት ፓትርያርክ ቃል እንኳን አልታዘዝ ያለው ድርሻውን ስለማያውቅ አይደለም እንዴ? ታዲያ እርሱ ድርሻን ስለማወቅ ለማስተማር ምን ሞራል፣ ምን ብቃትስ ይኖረዋል? ባይሆን ይህ አውደ ርእይ ለፓትርያርኩ መመሪያ ያሳየውን አልታዘዝ ባይነትና የእርሱን መጥፎ ምሳሌነት ለሌሎችም ትክክል አስመስሎ የሚያስተምርበት አጋጣሚ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡
ይህች ቤተክርስቲያን አሁን የምትፈልገው ማኅበረ ቅዱሳን ያባባሰውን የሕዝቡን ፍልሰት የሚገታ፣ ምእመኑ ሕይወት በሆነው በወንጌል ትምህርት እንዲያርፍ፣ ሁከት ብጥብጥ የሚታይበት አውደ ምህረት ችግሩ እንዴት እንደሚፈታ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያመጣ እንጂ በሚፈጠረው ግጭት ለማትረፍ “ጦር አውርድ” የሚል፣ በተገቢው ስራ ላይ ላይውል ገንዘብ ይሰብሰብ የሚል አይደለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን መቼም ይህን አያስብም፡፡ አለማሰቡም እድለ ቢስ ስለሆነ ነው፡፡ ውድቀቱን እያፋጠነ ያለውም ለዚህ ነው፡፡ እድለ ቢስ በጀርባው ቢወድቅ የሚሠበረው አፍንጫው ነው ይባላል፡፡
ማቅ በዚህ ወቅት ይህን ያሰበው በተለይ በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አውደ ምህረት እየተነፈገው ስለመጣ ያጣውን አውደ ምህረት በአግዚቢሽን ማእከል ለማካካስ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱ አሁን በእነ ያረጋል አበጋዝ፣ በእነ ታደሰ ወርቁ፣ በእነ አባይነህ ካሴ ላፕቶፕና ፕሮጀክተር ሊሞሉ የነበሩና ያበጡ አውደ ምህረቶችን አስተንፍሶአል፡፡ ከዚህ የተነሳ ማቅ ወደ አንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጉያ ውስጥ እቅዱን ከቶአል፡፡ ስለዚህ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የማቅ መደበቂያና የትምህርት ጉድፉ ማራገፊያ እንዳይሆኑ እነርሱን ማን ያስተምራቸው የሚለው ሥርዓት ሊበጅለት የሚገባ ቀጣይና ትልቅ ሥራ መሆን አለበት፡፡ እንደ አውደ ምሕረቱ ሁሉ ሰንበት ት/ቤቶችን ህጋዊ ሰውነት ያለው እንጂ ማንኛውም ሰው እንዳያስተምር ቢደረግ የበለጠ ሰላም ይሆናል፡፡
በመጨረሻም አውደ ርእዩ የፖለቲካና የግጭት መድረክ እንዳይሆን፣ በጓዳ በፓትርያርኩ ላይ እየተጎነጎነ ያለው አድማ ወደ አደባባይ የሚወጣበት አጋጣሚ እንዳይፈጠርም ከወዲሁ አስፈላጊው የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ ማኅበሩ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ጥብቅ መመሪያ አልታዘዝ ባለበት ሁኔታ፣  የጠቅላይ ቤተክህነቱ አስተዳደር ጉባኤም ማህበሩን እያሳሰበና እያስጠነቀቀና እስካሁን እየሠራ ያለው ያለ ሕግ ነው እያለ ባለበት ወቅት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ኃላፊዎች አውደ ርእዩ መታገድ አለበት እያሉ ባለበት ሁኔታ ነውና አውደ ርእይ ለማቅረብ ያቀደው ከወዲሁ ማስቆም ይገባል፡፡ እየተሸጠ ያለውን የቲኬት ገንዘብም ኦዲት ሊያደርገው ይገባል፡፡


19 comments:

 1. እርግጥ ነው አውደ ርእዩ መታገድ አለበት!!!! እየተሸጠ ያለውን የቲኬት ገንዘብም አዲሰ አበባ ሀገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ኦዲት ሊያደርገው ይገባል፡፡ ምእመኑን የሚመራው ቅ/ሲኖዶስ እንጂ ማ/ቅ ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ አብይ ጾም ወቅት አውዳ ርእይ አስታኮ ለማነሳሳት የታቀደ ቢጥብጥ ተቀባይነት የለውም

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውሾች ሆይ ላንቃችሁ እስኪሰነጠቅ ደጋግማቹህ ጩኹ፤ ግመሎች ሆይ እናንተም ዝም ብላችሁ ጉዟችሁን ቀጥሉ!

   Delete
 2. አባ ሠላማዎች ሐሰት መናገር በሐሰት ወንድምን መወንጀል ሐጢያት ነዉ፡፡በእርግጥ እናዉቀዋለን ፅድቁ ይቅርብን ማህበሩን ከመንግስትም ከፓትርያርኩም ቢሆን አጋጭተን ይፍረስ እንጂ ያላችሁ ልቦናችሁ የደነደነ የክፉ ትንቢት መፈፀሚያዎች የዲያቢሎስ አገልጋዬች ናችሁ፡፡ በቃኝ "አዉቆ ያንቀላፋን ቢቀሰቅሱት አይሰማም"

  ReplyDelete
 3. Doro bitalim tirewan yibalal yemyasgomjachihu zarem yemitdekimut legenzeb enji haimanot silmaytayachehu mintadergu Haimanot andken segebachihu tenberkikachihu yikirta titeykachewalachihu. En emlew mahibere kidusan baynor bezih blogachihu min takerbuneber daru blogum ayinor yetekuakamew lesidib silehone.Atwetutim engin siletenagerku wotolignal

  ReplyDelete
 4. hahahahahahaha.... besak motin eko!

  ReplyDelete
 5. eshe Yegna baladerawoch,tekorkuariwoch...Yebetekrstian chigrua angebegbachihu medaw teyazebachihu mechem aylekeklachihum mahiberum Egziabhern agazhe bemadreg eskemechereshaw yketilal!!!! kesdib lela afachihu silemaygeba enante yedabilos sira asfetsami nachihu .

  ReplyDelete
 6. Ay Aba selama tesfa yelachihum endiaw zim bilachihu new yemtdekmut!!! lemehonu ye enante alama mindn new? Betekrstianin lemafres? Mk min yiseral?
  Be ewnet atlfu Mk yifersal bilachihu kehone bekentu dikam new!!! Be Egziabher feqad yetemesereten mahiber .....????

  ReplyDelete
 7. Abba Selamawoch bemakkenawen laay yallach'hut tersun yagettete yesim matfat zemecha bizegeyyem beEgziabher enna besaow fit endemmiyasteyyeqach'hu atteterateru!
  Kristiyanawi alama binorach'hu noro, ewnetegna chegger aggatteme kalach'hu guddayun bemasrejja betedegefe abetuta leQdus Sinodosu taqerbu nebber. Bemadreg laay yallach'hut gin Seytanawi tegbar mehonu tawqobbach'huwal!!!

  ReplyDelete
 8. የትም አይደርስ -ዘመኑ አክትሞአል

  ReplyDelete
 9. አይ ሀራጥቃ እንኳን በእግዚአብሔር ፈቃድ ለበጎ አላማ የተቋቋመ ማኀበር እናንተም ለክፉና ለበላችሁበት ትጮሃላችሁ፡፡ ማኀበሩን የነኩት አይደለም የተናገሩት ምን እንደሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ተዋሕዶ እናንተ እንደሚመስላችሁ በቀልድ እዚህ የደረሰች አይደለችም፡፡ በየዘመኑ ዘመኑ እንደሚጠይቀው ፈጣሪ ጠባቂ ያስነሳል፡፡ ማኀበረ ቅዱሳንም አይናችሁ እያየ በዓለም የተንሰራፋው እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ራሱን ያለ ምስክር ስለማይተው ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም ልፉ ማኀበሩም ይጎለብታል፡፡ ገና ምን አይታችሁ.... የመናፍቃን ተላላኪ እንዲያው በናችሁ ትቀራላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 10. መስሎሻል አለች መሰሉ.... ማን እንዳቆመው አታውቁማ ሀራጥቃ ተሐድሶ

  ReplyDelete
 11. Aba selamawoch ebakachihu timihirt kalachihu astemirun. minew bilogun eko yesidib aderegachihu.yemahiberun sira legziabiher titachihu sila menfesawiwu asibut.

  ReplyDelete
 12. አባ ሠላማዎች ሐሰት መናገር በሐሰት ወንድምን መወንጀል ሐጢያት ነዉ፡፡በእርግጥ እናዉቀዋለን ፅድቁ ይቅርብን ማህበሩን ከመንግስትም ከፓትርያርኩም ቢሆን አጋጭተን ይፍረስ እንጂ ያላችሁ ልቦናችሁ የደነደነ የክፉ ትንቢት መፈፀሚያዎች የዲያቢሎስ አገልጋዬች ናችሁ፡፡ በቃኝ "አዉቆ ያንቀላፋን ቢቀሰቅሱት አይሰማም"

  ReplyDelete
 13. You 'Aba Selama's are always against Mahibere Kidusan b/s you assume that you rejected by the Ethiopian Orthodox Tewahido (During 2004 E.c Synod assembly)due to Mahibere kidusan.so,you are doing a kind of revenge for that matter.But don't you know that your preaching is like protestants!Please first be Orthodox to talk about the Ethiopian orthodox Tewahido church. Any Way God Bless Mahibere kidusan!!!!!

  ReplyDelete
 14. ke 11,000 belay Kiresetane Megabete 11/07/2008 Be Geferesa Debere Genete Kidous Geouregis beatekeresetane Mulo Kenen Kale Egizahberen Semegebe Wahle Tadiso Menafekane Be CD selawetote Ye Minefekena Timerete beke Genezahben Le Ezebe Kiresetano Tesete ....... ........ Egizahbere Yeserale engname Barawecho enseralene .... Tadiso Manafekane "Egizahber Tewage new Semome Egizahber New" .... Aba Selamaweche Mahberkidousan Sera lay new Yasemachewem

  ReplyDelete
 15. ዳይ መኾኑ ታምኖበት፣ ከገዳሙ ገቢ ላይ ብር 500‚000 ወጪ ኾኖ እንዲመደብ ከዚኽ ውስጥ ብር 300‚000 በገዳሙ ስም፤ ብር 200‚000 በገዳሙ ሠራተኞች ስም ተሠይሞ መጠነ ሒሳቡ በገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ አማካይነት ለክቡር ሥራ አስኪያጁ ስም እንዲደርሳቸው” በሚል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

  የገዳሙ ጽ/ቤት፣ ውሳኔ ያሳለፈበትን ቃለ ጉባኤ አባሪ በማድረግ በውሳኔው መሠረት እንዲፈጸምና ሒሳቡ እንዲወራረድ የካቲት 30 ቀን ለሒሳብ ክፍሉ በጻፈው መሸኛ ትእዛዝ ቢሰጥም ሒሳብ ሹሟ ክፍያውን እንደማይፈጽሙ በመግለጽ ውሳኔውን ተቃውመዋል፤ ይህንኑም ተከትሎ አራት ወራት ያስቆጠረው የምደባቸው ጉዳይ በሽፋንነት ተጠቅሶ ባለፈው ሰኞ በዋና አስተዳዳሪው ፊርማ ከጽ/ቤቱ ወጪ በኾነ ደብዳቤ ከሥራ እና ከደመወዝ መታገዳቸው ታውቋል፡፡

  ሒሳብ ሹሟ እገዳውን በመቃወም ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አቤቱታ ማቅረባቸው የተጠቆመ ሲኾን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱም ጉዳዩን በመረጃ ደረጃ እንዲያውቀው መደረጉ ተገልጿል፡፡

  Ye Egizahberen Genezebe mezerefe yelemede eko beze bicha ahyakomeme gena yeketelale ke atatate lay ateayate meserato ..... Egizahber Gin zeme belem yemekedemewe yelem

  ReplyDelete
 16. come on guys...let Mr. Yemane zemenfeskidus write a letter to mahibere kidusan to allocate half of the Exhibition income to his.......

  Wa....if you refuse , you will be kicked off from your job.

  ReplyDelete
 17. ምድረ መናፍቅ አርፍችሁ ተቀመጡ እናንተን ምን አገባችሁ

  ReplyDelete