Sunday, March 20, 2016

ደስታ ጌታሁን በቀሰጠው የመዝሙር መጽሐፍ ምክንያት ታሰረየሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ያሳተመውን መጽሐፍ ደግሞ በስሙ ማኅበረ ቅዱሳን ያሳተመለት ደስታ ጌታሁን ተከሰሰ፣ በህግ ቁጥጥር ስርም ውሏል፡፡ ከዚህ ቀደም “የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ … በተለያዩ ደራስያን የተደረሱ ዝማሬዎችን በመሰብሰብ የሰንበት ት/ቤቶች እንዲጠቀሙበት በሚል ያሳተመውን መጽሐፍ ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በተባለው ቀሳጤ ድርሰት ስም ማሳተሙ ውዝግብ ማስነሣቱን” ዘግበን ነበር፡፡ ውዝግቡ ቀጥሎ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመዝሙር መጽሐፉን በስሙ ባሳተመው በዲ/ን ደስታ ጌታሁን ላይ ክስ መሥርቶ ደስታ በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋሉን፣ መታሰሩንና ፍርድ ቤት መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደስታ ፍርድ ቤት ቀርቦ የዋስ መብት የጠየቀ ቢሆንም ከእርሱ ጋር ተጨማሪ የሚፈለጉ አካላት በመኖራቸው ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆበት በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደርጎ ጉዳዩ ለመጪው እሮብ ተቀጥሯል፡፡

ደስታ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ወንጀሎችን ፈጽሞ ተከሶ የነበረ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ የመጋቤ ሐዲስ በጋሻውን ስም በማጥፋት ባጻፋትና በስሙ ባሳተማት ትንሽ መጽሐፍ ምክንያት ተከሶ በሁለት ዓመት ገደብ መለቀቁ ይታወሳል፡፡ ቤተክህነት ውስጥ ከተቀጠረ ጀምሮ ደስታ የልደት፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት በመሸጥ፣ ከመዝገብ ቤት ደግሞ ደብዳቤዎችን ቀድሞ ለደጀ ሰላም አሁን ደግሞ ለሀራ ብሎጎች በመስጠት የሚታወቅ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ ሰው እጅ በርካታ ወንጀሎችን የሰራ ሲሆን አንድም ቀን ግን እንዲማርና እንዲሻሻል ያደረገበት ሁኔታ የለም፡፡ ምክንያቱም ከተማረና ከተሻሻለ ነገሮችን በአእምሮ ማከናወን ይጀምራልና ለማቅ ገንዘብ አይሆንም፡፡ ስለዚህ አሁን ደግሞ ማኅበሩ ተባባሪው ሆኖ እርሱ ሰርቆ በስሙ ባሳተመው የመዝሙር መጽሐፍ ምክንያት ለእስር ተዳረገ፡፡

ድርሰቱ የሌሎች መሆኑንና የመሰብሰቡን ስራ ሠርቶ “መዝሙረ ማኅሌት” በሚል ስም በ1993 ዓ.ም ያሳተመው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መሆኑን እያወቀ መጽሐፉ በታተመ በ15 ዓመቱ ራሱ እንደሰበሰበውና ንቡረ እድ ኤልያስ እና መ/ር ዕንቆባሕርይ ተከሥተ ግጥሙንና ዜማውን እንዳስተማሩት በማስመሰል “ዋይ ዜማ” በሚል ስም በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት በ2008 ዓ.ም ያንኑ መዝሙር መልሶ ያሳተመው ደስታ በተለይ የሁለቱን መምህራን ስም የጠቀሰው ማንኛውም ጥያቄ እንዳይነሳበት አስቀድሞ ለመከላከል እንደሆነና ስማቸውን ከጠቀስኩኝ ምንም አልባልም በሚል እምነት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ የመጽሐፉ ባለቤትና አሳታሚ የሆነው የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቷል፡፡

ደስታ መጽሐፉን በስሙ በማውጣቱ ተጠያቂ መሆኑ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ከእርሱ ይልቅ ግን ይህን የተሰረቀ ድርሰት እንደተሰረቀ እያወቀና ኀላፊነት በጎደለው ስሜትና ለጥቅም በማድላት ያሳተመው ማኅበረ ቅዱሳን የበለጠ ተጠያቂ መሆን ያለበት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ማኅበሩና አንዳንድ አባላቱ የሰውን ድርሰት የራሳቸው ድርሰት በማስመሰል ማሳተማቸው የተለመደ ነው፡፡ ስለዚህ ደስታ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ያሳተመውን የመዝሙር መጽሐፍ በስሙ ሲያቀርብለት ተው በማለት ፈንታ ማሳተሙ ማኅበሩ በጥቅም ምን ያህል እንደታወረና በማንአለብኝነት ምን ያህል እንደተሞላ የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ ጥያቄው በስሙ ባሳተመው በደስታ ላይ ብቻ ሳይሆን ይህን ሕገወጥ ድርጊት በመፈጸም ተባባሪ የሆነው አሳታሚው ማኅበረ ቅዱሳንም ተጠያቂ መሆን ስላለበት እርምጃው ከቅርንጫፉ ወደ ግንዱም መሄድ የግድ ይኖርበታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ህሩይ ወንድይፍራው ከ3 ደብዳቤ በላይ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ስም ፊርማውንና ማኅተሙን አስመስለው በመፈረምና በማተም ሰዎችን ቀጥረው በመገኘታቸው ለእስር መዳረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ ህሩይ ለእስር የተዳረጉት በሐሰት ሰነድ የቀጠሯቸው ሰዎች በቀረበባቸው ማስረጃ ምክንያት አባ ህሩይ የቀጠሯቸው መሆናቸውን በመጠቆማቸው ነው፡፡ አባ ህሩይና ዲ/ን ደስታ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅና ጸሀፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡

11 comments:

 1. Kkkkkkk,Enante koy mahibere kidusanin yemaysadeb tsihuf mechie new metawetut.Ye blogachihun sim keyrut,Anti mahibere kidusan belut Aba Selama keserachihu gar fetsimo ayehadim. Menafik hula ende abatachihu seytan mekses enji mesrat yematawku.

  ReplyDelete
 2. ሲያንሰው ነው

  ReplyDelete
 3. Seytan yemimesekiribeten enante eyefeterachihu titsfalachihu mahiberekidusan yalgebabet tsihuf tsihuf aymeslachihu enersu eyeseru enante eywerachihu zemenat tekotere. Semonun tshayu tenker bilual mahiberkidusan ejachew yinoribet yihon?

  ReplyDelete
 4. አይ ደስታ ምን አቅበጠበጠህ

  ReplyDelete
 5. ውሸታም የዲያብሎስ ፈረሶች።

  ReplyDelete
 6. እስክንድር ክፉኛ ተደናግጧል ።እንቆባህርይ ጅግና ነው ። አሉላ የመረጃ ድርቅ ይይዘዋል በደስታ እስር አቡነ ማቴዋስ ማቅን ለማስደሰት ዝም ማለታቸው ያስገርማል ።

  ReplyDelete
 7. ደስታና ሳህሉ እስላም ናቸው

  ReplyDelete