Monday, March 21, 2016

የአፋን አሮሞ የቅዳሴ መጽሐፍ መመረቅ የቤተክርስቲያን ተሀድሶ አንዱ መገለጫ ነው።ግእዝን የአምልኮዋ ቋንቋ አድርጋ ለብዙ ምእት ዓመታት ስትጠቀምበት የኖረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአንዳንዶች ኋላ ቀር አስተሳሰብና ከዘመኑ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር መራመድን በመፍራት ወይም ሃይማኖት የመቀየር ያህል በመቁጠር ከግእዝ ውጪ ሌላውን ቋንቋ ለአምልኮ መፈጸሚያነት መጠቀም የማይቻልባቸው በርካታ ምእት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ግእዝን ቸል እያሉ አማርኛን ያበረታቱ የነበረ ቢሆንም ቤተክህነቱ ግን በሥርአተ አምልኮት ላይ አማርኛን መጠቀም የጀመረው በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እርሳቸውና በዘመናቸው የነበሩት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶች የዘመኑን ተጨባጭ ሁኔታ በማየት የግእዝ መጻሕፍት ወደ አማርኛ እንዲመለሱ በማድረግ ስርአተ አምልኮት ሕዝቡ በሚሰማው ቋንቋም እንዲፈጸም በማድረጉ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ይታወቃል፡፡ እነሆ አሁን ደግሞ መጽሐፈ ቅዳሴ ወደ ኦሮምኛ ተተርጉሞ መቅረቡ በጣም የዘገየ ቢሆንም እንኳን እጅግ አስደሳች ዜና ነው፡፡ 

ከሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች በርካታ የህዝብ ቁጥር ያለው የኦሮሞ ህዝብ የቅዳሴ መጽሐፍን ለመጀመሪያ ጊዜ በቋንቋ ሊጠቀምበት መሆኑ በእርግጥም አስደሳች ዜና ነው። ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋው የወንጌልን እውነት እንዲረዳና አምላኩን እንዲያመልክ መርዳት አንዱና ወሳኙ የወንጌል ተልዕኮን መፈጸሚያ መንገድ መሆኑ ግልጽ ነው።


ቤተክርስቲያኒቱ ላለፉት 10 ዓመታት ስታዘገጀው የነበረው የቅዳሴ መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በኢሌሌ ሆቴል ተመርቋል። የቅዳሴው መጽሐፍ በግዕዝና በኦሮምኛ የተዘጋጀ ሲሆን ኦሮምኛው ቁቤንና የሳባን ፊደል ያካተተ ነው። መጽሐፉ ባለ 516 ገጽ ሲሆን በምረቃው ዕለት የነበሩና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለተለያየ መንፈሳዊ ትምህርት ሲሄዱ በአማርኛ በትግርኛ ቋንቋ ሲቀደስ መንፈሳዊ ቅናትና ቁጭት ይሰማቸው የነበሩ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጅ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች የቅዳሴው መጽሐፍ የኦሮምኛ ትርጉምን በማየታቸው ደስታቸውን በታላቅ ስሜት ሲገልጹ ነበር።

በዚህ የምረቃ በአል ላይ የተገኙት የቀድሞው የኢ... ፕሬዚዳንት ግርማ /ጊዮርጊስ ከመጽሐፉ ዝግጅትና ምረቃ ጋር አያይዘው በተናገሩት ቃል ቤተክርስቲያኗ ከግዕዝና ከአማርኛ ወደ አፋን ኦሮሞ የተተረጎመው መጽሐፈ ቅዳሴ የደስታ ትንሳኤዋ ነው ካሉ በኋላ በትርጉሙ ሥራ ላይ በተለይም ወደ ላቲን ቋንቋ የተተረጎመው በሳባ እና በግዕዝ ቋንቋ ሊተረጎም የሚገባ መሆኑን በመግለጽ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለወደፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ልታስብበት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


የቅዳሴው መጽሐፍ የኦሮምኛ ትርጉም ይቃመሙ የነበሩ አንዳንድ አክራሪ ግለሰቦች እንደነበሩ ሲታወቅ ይህ ግን የወንጌልን አላማ እና ግብ ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ነው። እንደ እኛ እምነት ቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናንዋን በቋንቋው ማገልገል መጀመርዋ ለተሃድሶዋ አንዱ አስፈላጊ ነገር ነውና ይበል የሚያሰኝ ነው።
ሰው እውነቱንም ስህተቱንም ሰምቶ ነው እና የሚመዝነው መዝኖም ነው እና የሚለወጠው በኦሮምኛ በተተረጎመው የቅዳሴ መጽሐፈት ላይ ያለውን የክርስትና እውነት በማጉላት ሰው ሁሉ ክርስቶስን ወደ ማወቅ የሚያደርገውን ጉዞ ያግዛል ብለን እናምናለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወሬዎችን በሰበር ለማውራት ማንም የማይቀድማት፣ ማኅበረ ቅዱሳን የልቡን የሚተነፍስባት ሐራ የተባለችው የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ይህን ታላቅና በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ክስተት ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር በዝምታ ያለፈችው መሆኑ በብዙ አነጋግሯል፡፡ ይህ የሆነበትን ምክንያት ለማኅበረ ቅዱሳን ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደሚናገሩት ማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፈ ቅዳሴው  ወደ ኦሮምኛ በመተርጎሙ ደስተኛ ስላልሆነ ነው ይላሉ፡፡ የዚህ መጽሐፈ ቅዳሴ ወደ ኦሮሚፋ መተርጎም ማኅበሩ በሃይማኖት ካባ ተሸፍኖ ከሚያራምደው ፖለቲካ ጋር አብሮ የማይሄድ ስለሆነ ነው ሲሉም ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ማኅበሩ ፖለቲካውን ላለማበላሸት ይህን ጉዳይ በእነ “ስምአ ጽድቅ” ሊዘግብ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ 

12 comments:

 1. waw waw waw i like it so much.

  ReplyDelete
 2. ayenate Zeregnoche Mahber Kidousane enko ahgerachen be Semaye new bilo yemeamine Kirestetane yalebete new eskey eweneto enenegager ketetebale eye Meteafe ke metatemo befeet eko new be Oromogna Kaneka Online TV yejemerewe .... Meche new Eweneten Mawerate yemitechelote ..... enate Abatacho Dabilose Selewen wulegize ke ahyemiracho Endeabatacho Asetene Ahfelekacho Tenageralacho ... Enanete ye Asete Leijoche Nacho Sele Mahbere Kidousan minem bitelo mesemagno yelem ... egna Kiresetanoche Yeteleyaye Minegesete SEmayate yelenem ... Zeregnoche Zore belolene lemeleyayete le meleyaete ema ahlamachewe segaweyaene yeweno sewche yebekonale .... Egna Kirestenache Wulachen be Kiresetose ande nehen .. Zeregnoche nacho be tame A.S Tebiyeweche

  ReplyDelete
  Replies
  1. ere wedaje teregaga krstyan negn tlaleh wedih demo tsadebaleh ayyyyyy

   Delete
 3. MK is the first to publish Orthodoxy books into Affan Oromo. They translated several books including Amde Haymanot and Wudassie Maryam while you were talking. They trained thousands of students in Affan Oromo. Guys can you tell us what you did as Tehadiso?

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳን ለዘላለም ይኑር፡፡

  ReplyDelete
 5. ሃሃሃ ንዴት ላይ ናችሁ። ማህበሩማ ስንት ነገር በኦሮምኛ ሲያዘጋጅ ነበር እኮ። እናንተ ታራላችሁ፣ ትቀናላችሁ እንጂ ስራ ይሰራል። አይ የጴንጤዎች ተላላኪ።

  ReplyDelete
 6. Your mission is to inherit th Kingdom of God but. If that is so you should not have alwas lied to accuse Mahibre Kidusan. Where will you end?

  ReplyDelete
 7. Mahber mahber.....atebelu yefersal.betecrstiyan lezelalem tenoralech.

  ReplyDelete
 8. የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን ከምን ልትመድቡት ነው

  ReplyDelete
 9. leba siyabarirut batagagna kadada lamagibat yifaligal,inanite dagmo bazi lamaxaqam timkiralachu,zimare ba oromgna,sibkatu ba oromgna nabara,iska zare lamin ye tahadiso maglacha naw satilu? leboch tanaqabachu

  ReplyDelete
  Replies
  1. eree sawachii ortdoxii tangitalech hikoo makana yisusii b45 qonqa matsifi qidusin taqayirolii

   Delete