Tuesday, March 22, 2016

በኦሮሚያ በብዙ ሥፍራ ተከስቶ የነበረው ግጭት ዓላማው ምን ነበር? ምንስ አስተዋልንበት? (የጃዋር መሐመድ ኦሮሞ - እስላማዊ ፍሬዎች)


Read in PDF
ከዲያቆን ሞቲ
  እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሲፈጥረው ከነሙሉ መብቱ ነው፡፡ አምላካችን እሱን እንከተል ዘንድ እንኳ ማንኛችንንም አያስገድደንም፡፡ ማመን ወይም አለማመን ሙሉ በሙሉ ለኛ የተተወ ነገር ነው፡፡ በነጻነት እንኖር ዘንድ ነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነጻ ያወጣን፡፡ የሰው ልጅ ነጻ መብቱን ተጠቅሞ ሌላውን እስካልጎደሰበት ድረስ እምነቱን እና አስተሳሰቡን ባልተገደቡ መልኩ ተግባራዊ የማድረግ መብት አለው፡፡ ከዚህ የማይገደብ መብት በመነሳትም ሰሞኑን በአሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ ለመምርምር እንሞክራለን፡፡
በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ ዝም ብሎ የልጆች ጨዋታ አድርጎ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ የተነሳው ተቃውሞ መሰረት ያለውና በአስተዳደርና በሌሎች ጉዳዩች የሚደርስበትን በደል በአዲስ አበባ የማስፋፊያ ፕላን ጋር አያይዞ የተቃወመበት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ህዝብ ተበደልኩ ሲል አልተበደልክም ማለት አይቻልም፡፡ በደሉን መስማትና ትክክለኛ የመፍትሔ እንቅስቃሴ ማድረግ በመንግስት በኩል የሚጠበቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የመብት ጥያቄውን በመቃወም የወሰደው የሀይል እርምጃ በምንም መልኩ ተቃባይነት የሌለውና የሚያሳዝን ነው፡፡ በተነሳው ተቃውሞ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡ በጣም በጣም ያሳዝናል፡፡ ሰዎች ከመኖሪያ ቀዬያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ሰዎች ሀብትና ንብረት ተቃጥሎዋል፡፡ ይህም ያሳዝናል፡፡


ችግሩ በረድ ቢልም ጠፍቷል ግን ማለት አይቻልም፡፡ የሚቀለው ተዳፍኗል ቢባል ነው፡፡ መንግስት አሁንም ነገሩን ቸላ ሳይል ለኦሮሚያ ህዝብ የፍትህ የመልካም አስተዳደርና የመብት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡
በርግጥ የነገሮች አካሄድ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው ማለት አይቻልም፡፡ በመንግስት በኩል የተወሰደው እርምጃ አሁንም ከተለመደው ስህተቱ ምንም ያለመማሩን የሚያሳይ ነው፡፡ በህዝቡም በኩል ለምሳሌ በኡመያ አካባቢ የተደረገው የሌላ ብሔር ሰዎችን የማባረር እንቅስቃሴ ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ የአበባ እርሻን እና የችግሩ አካል ያልሆኑትን የትራንስፖርት መኪኖችን ማቃጠልም ተገቢ አይደለም፡፡ ህዝብ በጅምላ ሲወጣ ከሚጫሩ ስሜታዊነቶች በመነሳት ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ መደረጉ የሚጠበቅ ነው፡፡ እንኳን በኢትዮጵያ ሥር የሰደደ የዲሞክራሲ ባህል አላቸው በሚባሉት በነ አሜሪካ እንኳን ህዝብ ለተቃውሞ ሲወጣ ከስሜታዊነቶች ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ስህተቶች አይጠፉም፡፡
ህዝቡ አሁንም ጥያቄ አለው መልስም ይፈልጋል፡፡ መንግስትም በተለይም ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ በመላው ሀገሪቱ እየተነሳበትን ያለውን ተቃውሞ ከግምት በማስገባት በአስቸኳይ የማስተካከል እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ የኦሮሞ ህዝብም ጥያቆዎቹ ተመልሰውለት ኢትዮጵያዊነቱን አምኖበትና እንዲኖር አስፈላጊው ሁሉ ሊደረግለት ይገባል፡

  እንዳለመታደል በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ ምክንያታቸውና ውጤታቸው በውል የማይታወቁ ከግጭቶች እስከጦርነት የሚደርሱ አያሌ ክስተቶች አሉ፡፡ የቅርብ ዘመን ታሪክ ብናነሳ በኢትዮ ኤርትራ መካከል የተደረገውን ጦርነት ብናስተውል በመቶ ሺህዎች የሚገመት ቁጥር ዜጋ ቢረግፍም እንደአንድ መንፈሳዊ ሰው ይቅርና እንደአንድ ነጻ ሰው ሆነን ከተሰጠው የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጋር ብናመዛዝነው፥ “ታዲያ ያ ሁሉ እልቂትና ፍጅት ለምን?” የሚያስብል ከፍ ያለ የቁጭት ጥያቄ ያስነሣል፡፡ እንደመንፈሳዊ ሰው ደግሞ ስናስበው ያለንበትን እጅግ ዝቅተኛ ወይም የሞተ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ መሆናችንን ቃሉ በግልጥ ይነግረናል፡፡
      ወደግል ነገር ማተኮር ስንጀምር በትውልድ ፊት አጸያፊ የነውር ታሪክ እናስቀምጣለን፡፡ የኮሚኒስት መንግሥት ደርግ ለአብያተ ክርስቲያናት የጋራ ጠላት ስለነበር አብያተ ክርስቲያናት ጠንካራ ሕብረት ነበራቸው፡፡ ነገር ግን “የነጻነቱ ዘመን” ሲመጣ የሃይማኖት ተቋማት እርስ በእርስ መነካከስ ፣ አንዱ ብሔር በሌላው ላይ “ልንገስ” የሚል ፈሊጥ ይዞ መጣ፡፡ [1] የጋራ ጠላት የሌላት አገር የጋራ ነገሯ ጠላት ሲሆንባት በኢትዮጲያና በቤተ ክርስቲያን በትዝብት እናያለን፡፡
በዚህ ርዕስ ላይ ለመጻፍ ስነሳ አንባቢ ከሁሉም በፊት እንዲያተኩርልኝ የምፈልገው በምንም መልኩ የኦሮሞ ሕዝብ ፍትሐዊ ጥያቄ እንዲዳፈንና ምላሽ ሳያገኝ እንዲቀር የማልፈልግ መሆኔን ነው። የኦሮሞ ህዝብን ተገቢ ጥያቄ አፍኖ ለራሱ እኩይ አላማ ሊያውል የሚፈልግን ሰው እና ቡድንን ግን የማገለጥ ግዴታ እንዳለብኝ አምናለሁ። ምስኪኑ የኦሮሞ ህዝብ መቸም ቢሆን አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል የመብት ጥያቄዬ አካል ነው ብሎ አያምንም። በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሳቸውን እስላማዊ አጀንዳ ወሽቀው የሚቀሳቀሱ ሰዎችንም በዝምታ ማለፍ አግባብነት የለውም።
ስለጃዋራዊ እንቅስቃሴ ጥቂት ዳራ
    ኢትዮጲያችን ከዘርፈ ብዙ ችግሯ ለመውጣት “በጥቂቱ” የምትታትረውን ያህል ፤ ካለችበት ችግሯና የሰቆቃ አዘቅቷ እንዳትወጣና በመማቀቅ እንድትኖር ተግተው የሚሠሩ እንዳሉ ካስተዋልንበት ክስተት አንዱ ተከስቶ የነበረው ግጭት ትልቅ አንዱ ነው፡፡ [2] እርግጥ ነው በአገራችን ኢትዮጲያ ቅያሜና ቁጣ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉ ሥር የሰደዱ ችግሮች አሉ፡፡ ዘረኝነት ፣ ጉበኝነት ፣ ፍትሕ ማጣት ፣ ማኅበረሰባዊ የወደቀ ሥነ ምግባር ... ብዙ ችግሮች አሉብን፡፡ ከችግራችን ለማገገም ግን ከእውነተኛ ሕብረት “ፈጣሪዎች” ጋር ስምምነት ሲኖረን ብቻ ነው፡፡
     ይህን የአገሪቱን ጠቅላላ ችግር በአግባቡ ማንሳትና መሟገት ፤ መከራከርና መቃወም ትክክልና ሊሆን የሚገባው ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ለግል ፍጆታ ማዋልና የራስን እኩይ ዓላማ ለማስፈጸም የድኈችንና የንጹሐንን ደምና እምነት መጠቀም ኢ ሥነ ምግባራዊና እጅግ አስነዋሪ ድርጊት ነው፡፡ በተለይም በዚህ ድርጊት ዋና ተዋናይና በኦሮሚያ በየቦታው የነበረውን ግጭትና ሁከት OMN[3] በሚባለው በግል ሚዲያው ግጭት ቀስቃሽና አነሳሽ ንግግሮችን ሲያደርግ የነበረው የሚድያው [ባለቤት]እንደሆነ የሚነገርለት ጃዋር መሐመድ የሚባለው ሰው ግንባር ቀደሙን ሥፍራ ይይዛል፡፡
      የሰውየውን መሠርይና እኩይ ጠባዩን ፤ አፍቃሬ እስላማዊና ጸረ ክርስቲያን መሆኑን ለመረዳት የኦሮሞ ሙስሊም ማኅበረሰብ ስብሰባ ላይ የኢትዮጲያ ሙስሊሞች በኢትዮጲያ ምድር የፖለቲካ የበላይነትን መያዝ እንዳለባቸው በአሜሪካ ሚኒሶታ ለተሰበሰቡት ለኦሮሞ እስላማዊ መሪዎች እንዲህ በማለት የተናገረውን ንግግር ማጤን በቂ ነው፦

“... ኦሮሞና ኦሮሞ በተነካ ቁጥር እስልምና ይነካል ፤ እስልምና በተነካ ቁጥር ኦሮሞም ይነካል የሚል ያነሳሁት አለ ፤ የኦሮሞ ድሎች ደግሞ የሙስሊሞች ድል ናቸው ብያለሁ ፤ እንደኦሮሞ ሕዝብ ትግል የእስልምና መጠናከር ወሳኝ መሆኑን በተለይ ሌሎች መገንዘብ አለባችሁ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ … የኦሮሞ ሕዝብ እዚያ አከባቢ እስካልተጠናከረ ድረስ ብዙም መሄድ አይቻልም፡፡ ጎንደር ውስጥ ተከብራችሁ ጎንደር ውስጥ ፣ አክሱም ውስጥ mosques(መስጊድ) መሥራት የምትችሉት የኦሮሞ ሕዝብ የአከባቢ ፖለቲካ ላይ “influence” መጫወት ሲችል ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው የእናንተ ወንድሞች  የሃይማኖት ወንድሞች ይህ ማኅበረሰብ ስለሆነ ነው፡፡ ይህን መገንዘብ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ እኔ ባለሁበት ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ሙስሊም ነው[4] ፤ ማንም ሰው ደፍሮ አንገቱን ቀና አያደርግም ፤ በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው፡፡ …” [5]

      ሰውየው የሚድያ ድጋፍ እንዲያገኝ ከአልጀዚራ የዜና ምንጭ ጋዜጠኞች በተለይም ከጋዜጠኛ መሐመድ አደም ትልቅ እገዛ በማድረግ ተጫውተውለታል ፤ የቪኦኤዎቹ የአማርኛ ፕሮግራም አዘጋጆችም “ያለአቅሙ የፖለቲካ ተንታኝነትን ሹመውት” እርሱን በተደጋጋሚ በማቅረብ ለመታወቁና ለ“ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ” ያላሰለሰ ጥረት አድርገውለታል፡፡

ጃዋርና ባልደረቦቹ የሚመሩት የኦሮሞ እስላማዊ ማኅበር [6]
      የዲያስፖራው ዓለም የሚናጥበት ሁለት ጥግ ጭፍን ፖለቲካና አክራሪ ሃይማኖተኝነት ነው፡፡ አገር ቤት ሳሉ ስለፖለቲካ ስሜት የማይሰጣቸው ሰዎች ድንገት ደርሰው ዲያስፖራነት የቀናቸው ዕለት የፖለቲካ ተንታኝነት ይቃጣቸዋል ፤ ከፍ ሲል ያለንባትን እየኖንባት ያለንባትን አገር ከገሃነም ጥቂት ብቻ ከፍ ያደርጓታል፡፡ ለእነርሱ ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የቱም ነገር እውነት ሳይሆን ፍጹም ሐሰትና ያልተደረገም ነው፡፡ ይህንን በደንብ ለማስጮኽ ደግሞ ከመቶና ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት የተፈጸሙትን ነውርና ርኩሰት ልክ አሁን እንደተፈጸሙ አድርገው ያቀርቡልናል፡፡
      በዚህ ጉዳይ እንደ ጃዋርና ፤ እንደመሠረተው ኦሮሞ እስላማዊ ማኅበርና ተከታዮቹ የተዋጣለት ደግሞ የለም፡፡ የሰውየው ማስጮኺያ “ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ ሕዝብ ተበድሏል” የሚለው ንግግሩ ትልቁ ሽፋኑ ነው፡፡ ይህ ብሔር ላይ የሚያጠነጥን የዘረኝነት አባዜ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ፖለቲከኛ መሪዎች የረከሱበት ክፉ ጋኔን ነው፡፡
     እውነት ለመናገር ሰውየውም ሆነ ማኅበሩ የነጻነት ታጋይ ቢሆኑ በኢትዮጲያ ምድር የተበደለው ፣ ፍትሕ ያጣው ፣ ጉበኝነት ያጎበጠው ፣ መልካም አስተዳደር የተነፈገው ፣ በዘረኝነት የታመሰው ፣ ሃሳቡን በግልጥ የመግለጥ መብቱን የተነፈገው … ኦሮሞ ብቻ ተነጥሎ አይደለም፡፡ እንደነጻነት ታጋይ እንኳ ብናስብ ወንድማማችነት ከሚያሰፍን ከአንድነት መንፈስ እንጂ ከመለያየትና የራሴ የሚሉትን ብሔርና ነገድ ቆርሶ ከመነሣት አልነበረም፡፡  ጃዋራዊነትና እስላማዊው የኦሮሞ ማኅበር መቁረስ ፣ መከፋፈል ፣ መለያየት … ከሚጠላው መንግሥት የተዋረሰውና የተዋሰበው ክፉ ኃጢአቱ ነው፡፡
ጃዋር የኦሮሞ ህዝብ የመብት ረገጣ ያሳሰበው የሚያሳስበውም ሰው አይደለም። የጁሀር ትልቁ አላማ በመብት ረገጣ ስም የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ካስገነጠለ በኃላ እስላማዊ የኦሮሞ መንግስት ማቋቋም ነው።


የተነሣው ግጭት ምን መልክ ነበረው?
     ግጭቱ በምስራቅ ሐረርጌ ፣ በምዕራብ ሸዋ ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋና በምዕራብ አርሲ ዞኖች ጠንከር ያለ ሽፋን ሲኖረው በድርጊቱ “ክርስቲያኖችም” ተሳትፈውበታል፡፡ ሽፋኑን ላየውና አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ በብዙ ቁጣ የሚያስነሣና “ነጻነት ነጻነት ቢያሸተትም”፥ ዲያስፖራውያኑን ጃዋርንና ሌሎችን ተከትለን ፤ መልካም እሴቶቻችንን ሙሉ ለሙሉ ደምስሰን መነሣታችን ፤ ከማን ጋር ምን ልሠራ ነው ይህን የማደርገው? አለማለታችን በታሪክ ፊት የሚያስወቅስ ጥፋት እንጂ ምንም እንዳልሠራን አሳብቆብናል፡፡
     ሲጀመር የግጭት ቀጠና ኦሮሚያ እንድትሆን መደረጉ ምንን ነበር የሚያሣየው? የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በዚህ ላይ የሠራው ሥራ ቀላል የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በዚያ የቲቪ ፕሮግራም የሚተላለፈውን ሰዎች “እንደኢየሱስ ቃል” ትክክል ብለው መውሰዳቸው ከሁሉ ይልቅ ልብ ይሰብራል፡፡ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችና ሰባክያን በዓመጹና በነፍስ ግድያው ፤ በንብረት ማውደሙ አብረው መሳተፋቸው በእርግጥ ይሰብኩት የነበረውን ወንጌል “ጂሃዳዊ” ማድረጋቸው በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ መዘበታቸው ወዲያው ነበር የተከሰተልኝ፡፡
    ወንጌላውያንና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ይህን ያህል የዘመኑን መልክ የማያስተውሉ ስለምን ሆኑ? ጌታችን ፈሪሳውያንን በአንድ ወቅት የወቀሰው በዚህ ጉዳይ ነበር፡፡
“ … በመሸ ጊዜ፦ ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ ፤  ማለዳም፦ ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?  ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ።(ማቴ.16፥2-4)

      ፈሪሳውያን ምልክት እንዲያሣያቸው ጥያቄውን የጠየቁት ለመፈተን እንጂ የእርሱን መሢህነት በማወቅ ለማመንና እርሱን ለመከተል አልነበረም፡፡ ምልክቱን የፈለጉት ለፈተና ብቻ ነው ፤ ምክንያቱም ከዚያ በፊት ብዙ ተአምራትን ቢያደርግም ከማመን ይልቅ በአጋንንት አለቃ ኃይል ያደርጋል ሲሉ ነበርና፡፡ (ማር.3፥22) ስለዚህም ጌታ ሰማዩን ብቻ በማየት ሊዘንብና ብራ ሊሆን እንደሚችል ካመናችሁና መርምራችሁም ከተቀበላችሁ የእግዚአብሔር መንግሥት መምጣትዋንና ለሰው ሁሉ ልትሰጥ መሆንዋን የሚያሳዩ ምልክቶችነ የማይመረምሩ ለምንድር ነው? (ሉቃ.12፥54) ልክ እንዲሁ የእኛ ዘመን በዓመጽ ፣ በነፍስ መግደልና በሰው አካል መጉደል ላይ የተሰማሩ አገልጋዮች የተባሉቱ ምነው ይህ ነገር ከሰይጣን መሆኑ መመርመርና ማወቅ ተሳናቸው?
      መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የጦርነትና የግጭት ሁሉ መንስኤ የሕዝቦች አለመስማማት መከሰት መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ የዚህም ዋና ምንጩ ከሰው ኃጢአት የተነሣ ወደ ዓለም የገባ መሆኑን ይነግረናል፡፡ በጦርነትም ሆነ በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ልንክደው የማንችለው እውነት ቁጣ ፣ ንዴት ፣ መራርነት ፣ ጩኸት ፣ ስድብ ፣ በክፉ መቅናት ፣ ደም ማፍሰስ ፣ አካል ማጉደል ፣ መግደል አለ ፤ ይህ ደግሞ “በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ (ማቴ.5፥22) ፤ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤ (ሮሜ.3፥14) ፤ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። (ኤፌ.4፥31)  አትግደል (ዘጸ.20፥13 ፤ ማቴ.5፥21)” የሚለው የቅዱስ ቃሉ ተግሳጽ ይወድቅብናል፡፡
     በተለይም የመስቀሉ ማኅበረሰብ ሌሎችን እንዲቸነክር አልተባለለትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ለማስፋፋት የክርስቶስና የመንፈስ ቅዱስን ሃሳብ ለመፈጸም ብናስብ እንኳ በመንፈሳዊ ኃይል መሆኑን ቅዱስ ቃሉ “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው። የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥” (2ቆሮ.10፥3-5) በማለት በግልጥ አስቀምጦታል፡፡ (ማቴ.26፥52 ፤ ኤፌ.6፥12) በተለይም እውነተኛ ክርስቲያን በጦርነትም ሆነ በማናቸውም መንገድ ሰው ላይና ንብረቱ ላይ ጥቃት በማድረሱ እጅግ አሳዝኝ ተግባር እንደሚፈጽም እጅግ ማስተዋል ሲገባው ለክርስቶስ ወንጌል ጠላቶች ከሆኑ ጋር በመስማማት “የገዛ ወገኑን” ማጥቃቱና መበደሉ እጅግ አስነዋሪነታችንን ያጎላዋል፡፡
     ምዕራብ አርሲ ላይ ያየነው እውነት ይኸንን በደንብ ያጎላዋል ፤ የአብያተ ክርስቲያትን ማምለኪያ ቅጥር ማፍረስ እውነት የነጻነት ሰዎች ተግባር ነውን? ትላንት የጅማና የኢሉባቡር እልቂት ምን መልክ እንደነበረው የሚዘነጋ ነውን? እንግዲህ ቀርቦ እስከ ደጅ ሲመጣ እንዲህ ነው? ጃዋርና ወዳጆቹ ቶሎ እዚህ ደረጃ መምጣት አልፈለጉም እንጂ የመጨረሻ የስብከታቸውና የቆሙለት ትልቁ ዓላማና ግባቸው ይኸው ነበር፡፡ የመስቀሉ ማኅበረሰብ ይህን ያህል ግን ምን አጃጃለው? እንዴት መናፍስትን መመርመር ይሳነዋል? እንዴት ከመግደልና ከማጥፋት ጋር ፤ ከቁጣና ከንዴት ጋር ፣ ከዓመጽና ከምሬት ጋር ከስሜታዊነት ጋር ፍጹም ይወዳጃል? በእውነት እግዚአብሔር እንዴት አዝኖብን ይሆን? በእውኑ የዘር ሃረግ ማለፍ ያልቻልን እኛ ነን እንደቅዱሳን ሐዋርያት እስከአለሙ ዳርቻ ሁሉ ወንጌል እንድሰብክ የምንላከው? አጠገባችንን ያለውን ወገን ድንበር ሰርተን እያሳደድን ፤ ንብረቱን እያወደምን በሩቅ ላለው ለማን ነው የምንላከው?
ይህ ለምን ሆነብን?
አክራሪ እስላማዊ ኃይላት በአፍሪካ ቀንድ እንደልባቸው ለመመላለስ ያስቻላቸው አንድ ነገር ቢኖር የኢትዮጲያ በዚህ ዙርያ ላይ ጠንካራ መንግሥታዊ አቋም እንደሆነ በዚህ ዙርያ ያጠኑ ባለሙያዎች ያትታሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ማሳያ እንዲሆን አይ ኤስ አይ ኤስ ክርስቲያን ወገኖቻችንን ክርስቲያን ብቻ ስለሆኑ የወሰዳቸውና እየወሰዳቸው ያለውን አሰቃቂና አስነዋሪ ድርጊቶችን ነው፡፡ [7] ጃዋር ለአንገት ሜንጫ ሸላሚ ነውና የአይ ኤስ አይ ኤስ አንድ ግልባጭ ነው፡፡ ጃዋራውያን በተቻላቸው መጠን ኢትዮጲያን በአክራሪ ሙስሊሞች ማስወረር ፤ በጎንደር በአክሱም መስጊድን የመሥራት እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚጨነቅና የሚያስብ ራዕይ ፈጽሞ እንዳላናገቡ ነገረ ሥራቸው ሁኩ ይመሰክርባቸዋል፡፡
   ”Ethiopian Advocacy Center“ የተባለው አካል “The Rise of Sectarian Islamic Oromo Nationalism” በሚል ርዕስ የሠራው አስደናቂ ዶክመንተሪ ፊልም ይህንን አውነት አበጥሮ በደንብ ያሳየናል፡፡ ጃዋርና ተከታዮቹ አዘውትረው ከሚጠቀመት ባንዲራቸው ጀምሮ ሕልምና ራዕያቸው አክራሪ እስልምናን በኢትዮጲያ ምድር ማስፈን መሆኑን ፊልሙ በሚያስገርም አስተሳሳሪነት ያሳየናል፡፡ እንደሐሰተኛ ነቢያትና መምህራን ጃዋርና ተከታዮቹ ግን ይህን የሚሠሩት ለኦሮሞነት የሚቆረቆር በሚያስመስል ሽፋን ፤ ራሳቸውን ፍጹም በመደበቅና ባለመግለጥ ነው፡፡
እንግዲህ የመስቀሉ ማኅበረሰብ ስለክርስቶስ ከመሞት ይልቅ “ለአገር ነጻነትን” በሚል ክፉ ልክፍትመግደልና ተመሳሳዩን ነገር አብሮ ሊፈጽሞ ከማያምኑ ጋር በአንድነት ወነበደ፡፡ ስለዚህም ይህ የሆነብን ለኃጢአት የወረደ አመለካከታችንን ያሳያል፡፡ የመስቀሉ ማኅበረሰብ “ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።” (ሮሜ.12፥18) የሚለውን ቃል የሚተገብረው ክፉን በክፉ በሚመልሰው  ሰይጣናዊ ንስሐ ምላሽና ድጋፍ በመስጠት አይደለም፡፡ ከሌላው ጋር በሰላም የምንኖረው ጠብ አጫሪ ባለመሆንና የተጫረው ጠብ ውስጥ ባለመሳተፍ ይልቁን በማስተራረቅ ፤ ለሚያሳድድ በሚጸልይ ፣ ለሚረግም በሚመርቅ ፤ ለሚጠላ በሚወድድ ማንነት ውስጥ በመሆን ነው፡፡
ምን እናድርግ?
      እንደሞኝ ሰው እላለሁ፥ “ስለአገራችን ጸልዩ”፡፡ በኢትዮጲያ ብዙ አስከፊና አጸያፊ መንግሥታዊ በደሎች አሉ፡፡ መንግሥት በብዙ የተያዘባቸው አስከፊ ነውሮች አሉ፡፡ ቁሳዊ እድገት እንጂ አዕምሮአዊ እድገት የተዘነጋ ያህል ተጥሏል፡፡ ትውልዱ “ለገንዘብና የተሻለ ነገር ፍለጋ” በስደት ሲሄድ ጆሮ ጭው የሚያደርጉ የባህርና የበረሃ ጉዞ ያደርጋል፡፡  በአገር ቤት ውስጥ ውስጥ ያለው በብዙ ነገር በሚያስከፋ ሱሰኝነትና የቁሳዊነት አምላኪነት ውስጥ ገብቷል ፤ መሪው ስለሚቆጠረው አሃዛዊ የገንዝብ እድገት እንጂ እየወደቀ ስላለው የሥነ ምግባር ብዙም የሚጨነቅ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን መፍትሔው አክራሪ የእስልምና መሪዎችን እንጃዋርንና ማኅበራቸውን መደገፍና አብሮ ማበር አይደለም፡፡
      መፍትሔው ሁሉን በሚችል አምላክ እጅ ብቻ ነው ፤ ጸልዩ ፤ ደግሜ እላለሁ ጸልዩ፡፡ እግዚአብሔር የተሻለ ነገር ለትውልዱ እንዲያመጣ ፤ ለአገራችን ቅንና የትውልዱን በቁመቱ ልክ መውደቅ በቅንዓት እያንገበገበው የሚያነሣ ልዩና አዲስ መሪ እንዲያስነሣ ጸልዩ፡፡ ጸልዩ! የእስልምና አክራሪዎች መንፈስ ከምድሪቱ ላይ እንዲነሣ ጸልዩ፡፡ መፍትሔው ከአማኞች እኛው ለእኛው እንዲመጣ ጸልዩ፡፡ በሰው ምድር ላይ የገዛ ኑሮአቸውን በቅምጥልነት እየኖሩ ፤ ያለንበትን ሁኔታ በትክክል ሳያስተውሉ ፤ ከእናንተ ይልቀ እኛ በደንብ እናውቅላችኋለን እያሉ እንዳንስማማ ከመንግሥት በማይተናነስ መልኩ ከሚያባሉን ግብረ ሰዶማውያንና ጸረ ክርስትናና ፤ አፍቃሬ አክራሪ ሙስሊም ዲያስፖራውያን ዘንድ መፍትሔ አለ ብለን አናምንም፡፡ እባካችሁ ወገኖቼ! ጸልዩ ፤ ለኢትዮጲያችን ፤ ለምድራችንም ጸልዩ!!!


[1]የአንድ ብሔር ገዢነት ለኢትዮጲያ የነበረ ያለ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ወደአንድነት የማድላቱ ነገር ይዘወተር እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡
[2]የተከሰተው ግጭት አይደለም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች ቢኖሩም፥ እኔ ከዓላማው አንጻር ከዚያ የዘለለ ፋይዳ ነበረው ብዬ እቸገራለሁ፡፡
[3]ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የሚባለውና ሳተላይት ዲሽ ላይ የሚተላለፈው የኦሮሚኛና የአማርኛ ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ ለኦሮሞ እንደሚቆረቆር ራሱን የሚገልጥ ሚድያ ነው፡፡
[4]እኔ ባለሁበት የሚለው የኢትዮጲያን ምስራቁን ክፍል ነው፡፡ ሜንጫ የሐረርጌውያኑ የእርሻ በተለይም የጫት ማስተካከያ ሲከፋ ደግሞ ለጦር ዕቃቸው የሚጠቀሙበት መሣርያቸው ነውና፡፡ ጃዋር ይህን ክፍል ምዕራቡንና ምሥራቁን የሐረርጌ ክፍል ዘጠና ዘጠኝ ክፍሉ ሙስሊም ነው በማለት አይን ያወጣ ውሸት ይዋሻል፡፡ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን ሳያካትት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻዋን በምሥራቅ ሐረርጌ ሃምሳ ፤ በምዕራብ ሐረርጌ ደግሞ ሰማንያ አራት ከገጠር እስከ ገዳም የበዙ አብያተ ክርስቲያናትን ተክላለች፡፡ የምዕመናንንም ቁጥር ብናነሣ ማዕከላዊ እስታቲክስ ኤጀንሲ በ2007 ዓ.ም(እ.ኤ.አ) ባወጣው መረጃ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች በምሥራቅ 4.51% ፤ በምዕራቡ ደግሞ 11.28% መሆኑን ለአለም ሁሉ ይፋ አድርጓል፡፡ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሲጨመርበት ደግሞ ቁጥሩ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ጃዋር ሌላም ነገር ይክዳል ፤ ተቻችሎና ተጋግዞ በመኖር የሚታወቀውንና በዩኒስኮን የታወቀውን የሐረርና የአከባቢዋን ማኅበራዊ እሴት በመካድ፥ ማንም ሰው ደፍሮ አንገቱን ቀና አያደርግም ፤ በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው፡፡” ይላል፡፡ ጃዋር እርሱ ዛሬ በሥልጣኔ ዘመን ላይ ቆሞ አንገትን በሜንጫ ሊመታ ሲያስብና ሲሰብክ ትክክል ነው ፤ ከዓመታት በፊት የተደረገውንና ትውልድን በይቅርታ ልብ በማጨባበጥ በሠላም ከማኖር ግን በክፋት ልብ እያነሳ ይራገማል፡፡ እነዚያ ቋንጃና አንገት ሲቆርጡ ምክንያታቸውን አልሰማንም ፤ ጃዋር ግን ዛሬ ላይ አንገት ሊቆርጥ ሲነሣ ምክንያቱ ምን ይሆን? ነጻነት? እንዳልሆነ አንገት በመቁረጥ የተካነው የአይ ኤስ አይኤስ የደም ማኅበር ጃዋራዊውን ምክንያት ያለማስመሰል ያብራራል፡፡   
[5] ስለጃዋር እስላማዊ እንቅስቃሴና በእስልምና ነክ ነገሮች ላይ የዚህ ጽሁፍ ጸሐፊ ያዘጋጀውን በሚቀጥለው ጊዜ ለማስነበብ ቃል ይገባል፡፡
[6]ይህን ማኅበር በዋናነት ጀዋር መሐመድ ፣ አብዲ ፊጤ ፣ ሴክ አህመድ አብዱልቃዲር ፣ ሃምዛ አብዱረዛቅ ፣ መሐመድ ሐሰን ፣ መሐመድ አብዶሽ ፣ ራምይ መሀመድ ፣ ሙራድ ደሚና ፣ አብዱሰመድ ኡመር ፣ አህመድ ገልቹ ፣ በድሪ መሐመድ የሚባሉ ማኅበረ ሙስሊማዊ ኦሮሞዎች ይመሩታል፡፡
[7]ሶርያን ብናስተውላት ግልጽ ምሳሌ ትሆነናለች፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የክርስትና እምነት ታሪካዊ አሻራዎችን አይ ኤስ አይ ኤስ የሚያጠፋው ለምንድር ነው? ከተማይቱን ወደመንደርነትና ፤ ወደፍርስራሽነት የቀየራት ስለምንድር ነው?  የሶርያን ክርስቲያኖች እንደዚያ እንዲያ አርዶ ፣ ቀልቶ ፣ ደማቸውን አፍስሶ ፣ በሕጻናቱ ጭምር አስነዋሪ ድርጊት ፈጽሞባቸው ያልረካው ለምን ይመስላችኋል? እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ብዙ ጊዜ ጠበቀን እንጂ በዘረኝነታችን አባዜ ይህ ክፉ አክራሪ እስላማዊ ቡድን ይህችን ቢከሰት ምን የሚሆን ይመስላችኋል? እዚህ ድረስ የመጣሁት ጃዋርና ወገኖቹ ከዚህም ከፍ ብለው መሄዳቸውን እያየሁ ስለሆነ ነው፡፡ 


14 comments:

 1. ይህ ጉዳይ ሲርየስ ጉዳይ ነው። በዚህ ደረጃ ያየው እና ያስቀመጠው ሰው ግን የለም። ሞቲ ስለግንዛቤው እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 2. LE AGERE YEMETEKEM ANDENENETEN YEMEATENAKERE ENDEZE AHYENETE NEGERE MAKEREBE SETECHELO WUOLE SELE MELEYAYETE BICHA TAWERALACHO .... JOARE MAHMED YE ETHIOPIAN BEATE KIRESTANE LEMATEFATE KORETO YETENESE SEW NEW LEZEM MASAYAWE BEZE GICHETE WEKETE YASAYEWE BEATE KIRESETANE LAY YADERESEW KATELO NEW

  ReplyDelete
 3. very good analysis

  ReplyDelete
 4. “ማንም ሰው ደፍሮ አንገቱን ቀና አያደርግም ፤ በሜንጫ አንገቱን ነው የምንለው፡፡” አለ ጁሐር ጌታ በመስቀሉ ቀይሮ አንተን ለንሰሐ እኛን ለበረከተት ያደርግዋል አትጠራጠር አለው ነገር ጌታ ታዛጋሽ ነው ጸሐፊው እንዳለው እባካችሁ ወገኖቼ! ጸልዩ ፤ ለኢትዮጲያችን ፤ ለምድራችንም ለህዝቡም ጸልዩ እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!! አሜን

  ReplyDelete
 5. የኦሮሞ ተቃውሞን ከእስልምና አስተሳሰቦች ጋር ለመደባለቅ ማሰብ የህዝቡን ትግልን የሚያቀጭጭና ፋይዳ ቢስ እንዲሆን የሚያደርግ ስለሆነ... የሃይማኖት ዓላማ ይዘት ያለው የፖለቲካ አራማጆቸ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል......
  ኦሮሞነትና እስልምና ፖላር ኦፖዚት ናቸው......... ኦሮሚ ውስጥ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች አሉ ......... አጉል የኦሮሞ የነጻነት ትግልን ከእስልምና ጋር ለመደባለቅ መሞከር ከሸፍጠኝነት ተለይቶ አይታሰብም.... ሃይማኖትን ከብሄርን መለየት ያስፈልጋል.....
  የኦሮሞ ነጻነት የትግሉም ጀማሪዎችም ሆኑ መሪዎች ሙስሊሞች ሳይሆኑ የሸዋ ክርስቲን ኦሮሞ መሆናቸው የታወቀ ነው....
  የአቶ ጃዋር አጉል ብልጣብልጥነት መጤን ይገባዋል

  ReplyDelete
 6. It is real that through out our history the oromo people are suffered a lot by different governments and there was delebrate undermining attitude by orthodox church. BUT Jawar and Jawarian are not the solution for this nation they are parasite who want established Islamic state. The church will pay for this for not doing her home work in advance very well. We lost the influence of the church in this nation....biiiig lose.

  ReplyDelete
 7. በጣም የሚመሰገን ሥራ ነዉ፡፡ ብዙ ሰዉ ተገቢ መረጃ የለዉም በሁሉም መታወቅ አለበት፤ ተከታታይ መረጃዎች ብትሰጡን በጣም ደስ ጡሩ ነው

  ReplyDelete
 8. ኦዴፍኖን ኑፍ ኬኒቴ ባዬ ጋሪ ዋን ተኤፍ ገራ አፋን ኦሮሞቲ ጂጂሩዳን ሁመኒ ኬኛ ከና አዳን ባፈቴ ሚርገሳ አካ ኢን ደበኔ ጎዳሙ ቀባ፡፡ኢላልቺ ኬ ባዬ ነቲቶሌ ጂራ

  ReplyDelete
 9. Egziabher yibarkih etselyalew

  ReplyDelete
 10. This is a very dangerous and very irresponsible, specially when it comes from religious website. The writer should have done a little more to find about Jawar instead of basing his writing from face book. Does the writer know Jawar's background, upbringing, education his many writings and his stand on peaceful protest. Also, if the writer I have a huge respect for him. I do not think it has to do with Jawar it is fear of the Oromo protest and what it will bring. The Oromophobia is playing a huge role.

  ReplyDelete
 11. የፍቀር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጴጥሮስ የአንዱን ወታደር ጆሮ በሰይፍ ሲቆርጠው “ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ” አለው። ሰውን በፍቅር ማሸነፍ ይቻል ይሆናል እንጂ በጉልበት ለጊዜው ድል ቢገኝም አሸናፊው ጉልበቱን አጥቶ ተሸናፊው ሲፈረጥም መልሶ የሰፈሩት የጥላቻና የበደል ብድር ወለዱን ጨምሮ ያስከፍላልና እንደ ባለ አእምሮ ሰው ቆም ብለን እናስብ!!!
  ደግሞም በኦሮሞ ወገኖቻችን መካከል ክርስቲያኖች ስላሉ ለኦሮሞ ሕዝብ ቆሜያለሁ እያልን ክርስስቲያንን ስታገኙ አንገቱን በሰይፍ ቅላው ማለት ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ጭምር ማለት ስለሆነ ጉዳዩ ማስተዋል የጎደለው እብድነት ነው የሚመስለውና ኦሮሞዎች ወገኖቼ በደንብ እንነጋገርበት???

  ReplyDelete
 12. To live in peace religions need to be tolerance each other and help each other from the oppressor. orthodox as the first religion emerge in Ethiopia accommodate and love others religions from the bottom of the heart and others religion also need to respect the existence of the orthodox. Regard Oromo: Oromo have different religions that means christens Muslims they live together before they live together for the future. some people Tplf agent Focusing personal attack the person to divide Oromo plus to isolate the struggle from others Ethiopian people but it doesn't work. What help for all us support each other and fight the oppressor.

  ReplyDelete
 13. I honestely thank the writer

  ReplyDelete