Friday, March 25, 2016

ቀሲስ የ“ክብረት ልጅ”፥ ምነው በስድብ ቃል በጣም ጮኸ?!ምንጭ፦ የአቤኔዘር ተክሉ ገጽ http://abenezerteklu.blogspot.com/
የክብረት ልጅ እይታዎቹን በሚያቀርብበት ብሎጉ፥ “ፓትርያርኩ፦ ለኢትዮጲያ የደኅንነት ፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል አንድ ጽሁፍ፥ ዛሬ አስነብቦ ድንገት ያየ ሰው ጠቆመኝና ወደጡመራው መድረኩ ገብቼ አነበብኩት፡፡ ዳንኤል በዚህ ጽሁፉ “100% ማኅበረ ቅዱሳን ሊያዘጋጀው ከጫፍ የደረሰውን ዐውደ ርእይ የከለከሉት ፤ ያስከለከሉት ፓትርያርኩ ናቸው”፥ ብሎ ደምድሞ አስቀምጦታል፡፡ የዐውደ ርእዩ ባለቤት ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ፥ በዋናው ጸሐፊው አቶ ተስፋዬ ቢኾነኝ በኩል ትላንት ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ “መግለጫ”፥ “ለመታገዱ ፓትርያርኩ እንደሌሉበትና በመንግሥት አካላት መመሪያ መታገዱን”ይፋዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ 

ዳንኤል ፓትርያርኩን ከሰይጣን እኩል ነበር የሳላቸው ፤ “... ፓትርያርክ ማለት በግሪክ “ታላቅ አባት” ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም ፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፤ ...” በማለት፡፡ እንደከዚህ ቀደም ልማዱ ዳንኤል ሌሎች ማስጮኺያዎችንም በዚህ ጽሁፍ ለማካተት ጥሯል፡፡ አዳዲስ ስድቦችንም ለፓትርያርኩ እንደእጅ መንሻ አቅርቦላቸዋል፡፡

ቅዱስ ቃሉ ግን እንዲህ ይላል፥ “ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብህንም አለቃ አትርገመው።” (ዘጸ.22፥28) የሕዝብ አለቃ ወይም መሪ የሆነ ገዥ በምድር ላይ የእግዚአብሔር ተወካይ ፤ እንደራሴም ነው፡፡ ስለዚህ ልናከብረው ፤ በመውደድም ከሁሉ በፊት ልንጸልይለት ይገባል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሳያስበው ይህን ቃል በመተላለፉ ምክንያት ወዲያው ተጸጽቶ ተመለሰ ፤ አለማስተዋሉንም ተናገረ፡፡ (ሐዋ.23፥4-5) ፍትሐ ነገሥቱም “በእነርሱ ላይ የተሾመውን ጳጳስ ... እንደትልቅ ወንድም ያክብሩት መሪና አስተዳዳሪ እንደመሆኑ መጠን ሊታዘዙለት ይገባል” ይላል፡፡ (አን.4 ቁ.53) ዳኒ! ይህ የሕግ ቃል አንተን አይመለከትም ይሆን?!

የቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥት በአንቀጽ.6 ስለቀሳውስት ድርሻ ባሰፈረበትና ቀሳውስት ከማዕረገ ክህነታቸው ስለሚሻሩበት ሁኔታ ሲዘረዝር “... ሕግን አውቆ የማይሠራባት ... ቄስ ይሻር፡፡” በማለት በግልጥ ያስቀምጣል፡፡ ዳኒ! እንኳን መንፈሳዊውን ሥጋዊውን የዚህን አለም ምድራዊ ሕግ መጣስህን አውቀኸዋል? ማኅበሩ ፓትርያርኩ አልከለከሉኝም እያለ፥ አንተ ግን ለፓትርያርኩ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተሃል፡፡ እንደቤተ ክርስቲያን ቀኖና ከቅስናህ ትሻር ይሆን? እውነታው ግን አይመስልም፡፡

ፓትርያርኩ ቢያጠፉ እንኳ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ምን ነበር የሚለው? ጅል ፣ ሰይጣን ፣ የክፋት አነሳሽ ... እያሉ በአደባባይ ፓትርያርክን መዘርጠጥ አለበት የሚል “ቀኖና” አለን?! ለመሆኑ ስድብ ከማን ነው? የሕዝብን አለቃ አለማክበርስ? ያንን ሁሉ መጽሐፍ የጻፈው “ደራሲና ተመራማሪ” ምነው ምራቅ እንዳልዋጠ “ፍንዳታ”(የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ቃል ናት) ደርሶ ቱግ አለ?! እንዴ ይህ ነበር እንዴ በውስጡ የነበረው?!

ውድ ወንድሜ ቀሲስ ዳንኤል፦ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና አላት ፤ በየትኛውም የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ሽቅብ ፓትርያርክን እንዲህ መዘርጠጥ አይደለም ምእመንን መናገር አጸያፊ ነው፡፡ ተግሳጽ ነው ብትለኝ፥ ለመሆኑ ተግሳጽ መቼ ነው የሚመጣው? ደርሰህ ከመገሰጽህ በፊት ስንቴ ይሆን የመከርካቸው? ስንቴ ይሆን የወቀስካቸው? ስንቴ ይሆን ካሉበት ነቀፌታ እንዲርቁ በሚራራ ልብ አዝነህላቸው እንደእግዚአብሔር ቃል በጸሎት ቃል ወደጌታ የማለድክላቸው? ... ደጋፊ ስላገኙ ብቻ ብዙ ማለት፥ ከማያዳላ ኅሊና ጋር ያፋጥጣል፡፡ ወንድምን ሰባት ጊዜ ሰባ ይቅር ማለትና መቀበል እኮ ከአባት ባሻገር ወንድም ለሚሆነን ፓትርያርክንም ያካትታል ፤ ለመሆኑ ይህን ታውቀዋለህን?!

ፓትርያርኩ ቢያጠፉ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና አላት፡፡ “...የአገሩ ሁሉ ኤጲስ ቆጶሳት ስለእርሱ የሚገባውን ይመረምሩ ዘንድ እርሱንም ለማየት በየዓመቱ ሁለት ጊዜ ከጳጳሳቸው (ፓትርያርካቸው) ዘንድ ይሰብሰቡ፡፡ ስለተሰጣቸው ሥልጣን በምታስፈራዪቱ ቀን መልሳቸው የጸናች ትሆን ዘንድ፡፡” (አን.4 ቁ.55) የሚል፡፡ የሚያዩት ፊቱን ብቻ አይደለም ፤ ሥራውን በማየት ያመሰግኑታል ፤ ነቀፌታም ካለ ይነቅፉታል፡፡ ዳኒ! ይህችን አላነበብካት ይሆን?! ፓትርያርኩን መውቀስና መምከር ፤ መገሰጽም ካለብህ መንገዱን አልሳትከው ይሆን? ይህን ያህል ግን ለምን ይሆን የጠላሃቸው? ዳኒ! ወንድምን ስለመጥላት ቃሉ በትክክል ይወቅስሃል፡፡

በእርግጥ ዳንኤልና ማኅበሩ መንገድ ሲተላለፉ ይህ የመጀመርያው አይደለም፡፡  ግን እውነት ለመናገር ባልተጣራ ወሬ ፤ በተራ አሉባልታ ያውም ስንት ሽልማት ያግበሰበሰው ሰው ይቺን ትንሿን ነገር ከማጣራት ቸኩሎ “በሚቆረቆርላት” ቤተ ክርስቲያን መሪ ላይ የስድብ ናዳ ያወርዳል ብሎ ማን ይጠብቃል?!  ከዚህ ስህተቱ ይማር ይሆን ዳንኤል? ወይስ ወደፊትም ሌላ የስድብና የመዘርጠጥ ጽሁፍ ያስነብበን ይሆን? ወይስ እንደጳውሎስ በግልጥ የይቅርታ ልብ ይዞ “የሕዝብን አለቃ” ስለተሳደበበት ስድቡ ንስሐ ይገባ ይሆን? የምናየው ይሆናል፡፡ ፈጥነህ ንስሐ ብትገባ ግን ማሰናከያን ታስወግዳለህና እስኪ ቀድመህ ወደራስህ እይ!!!

ጌታ ማስተዋሉን ያብዛልን፡፡ አሜን፡፡

30 comments:

 1. አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ከመኾኑ አንጻር ሰሞኑን ከነበረው ውዝግብ ጋር ተያይዞ ፓትርያርኩ በእገዳው ይኖሩበት እንደኾን አቶ ተስፋዬ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ “ከቅዱስ አባታችን ጋር በተያያዘ እስከ አኹን ባለን መረጃ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፤” ሲሉ የተደረሰበት ይፋዊ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

  “ለመታገዱ ፓትርያርኩ እንደሌሉበት" ማለትና "ከቅዱስ አባታችን ጋር በተያያዘ እስከ አኹን ባለን መረጃ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፤” በሚለው አገላለፅ መካከል እጅግ በጣም ሰፊ ልዩነት አለ።

  ስድቡ ምኑ ላይ ነው? እውነት ሲነገር ያማል አይደል?

  ፓትርያርክ ማለት በግሪክ ‹ታላቅ አባት› ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን መክሰስ አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን እንጂ አባት አያስፈልግም፡፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ጠርቶ መውቀስ እንጂ በር መዝጋት አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፡፡ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ማቀፍ እንጂ ማባረር አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን አለ፡፡

  ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች በጎጆ ቤት ዋጋ በሙስና ለዐሠርት ዓመታት ሲከራዩ ተኝተዋል፤ ከመንበረ ፕትርክናቸው ሥር ባለች አጥቢያ የቤተ ክርስቲንን ገንዘብ አናስበላም ያሉ ካህናትና ምእመናን ሲባረሩ ተኝተዋል፡፡ በሕዝብ ጥያቄ ሽፋን ጽንፈኛ አቋምን በሚያራምዱ ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ይተኛሉ፤ የስልጤ ዞን ምእመናን በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ እየተቀበልን ነው ሲሉ ይተኛሉ፤ ቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ሲሆን ይተኛሉ፤ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሲዘጉ፣ ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲበተኑ ይተኛሉ፤ በመሥዋዕትነት የተመሠረቱት የደቡብ አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት በሙሰኛ አመራሮች አደጋ ላይ ሲወድቁ ይተኛሉ፣ ይሄ ሁሉ ዘለፋና ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲዘንብ ይተኛሉ፡፡

  መናፍቃንን የሚተች ጽሑፍ በኦርቶዶሳውያን ተጻፈ ሲሏቸው፤ ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ ሕዝቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ ነው ሲሏቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው ሲሏቸው፤ ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ ሲሏቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሊቀርብ ነው ሲሏቸው ያን ጊዜ ብዕራቸውን ይዘው ለማገድና ለመክሰስ ይነቃሉ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ‹ድንግል ሆይ የአንቺን ምስጋና ለመጻፍ ምንጊዜም ብእሬ ቀለም እንደያዘ ነው› ነበር ያለው፡፡ የፓትርያርኩ ብእር ግን ምእመናንን የሚያጽናና ጦማር ለመጻፍ ወይም ድንግልን የሚያመሰግን ድርሳን ለመድረስ የሚጨበጥ አይደለም፡፡ እንደ ጠንቋይ ብዕር ለማፍዘዝና ለማደንገዝ እንጂ፡፡

  የፓትርያርክ ዋናው ሥራው የሀገር ደኅንነት እንዲጠበቅ ‹ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ› እያለ መጸለይ፤ የምእመናን ድኅነት እንዲረጋገጥም ሃይማኖት ማስተማር፣ በጎችን መሠማራትና ቀኖናን መጠበቅ ነበረ፡፡ ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹በጎቼን ጠብቅ፣ አሠማራ› ነበር የተባለው፡፡ መጠበቅ- ከክህደት፣ ከኑፋቄ፣ ከኃጢአት ከበደል፤ ማሠማራት - በትምህርት፣ በምግባር፣ በትሩፋት፣ በአገልግሎት፣ በጽድቅ መስክ ላይ፡፡

  ‹ባለሞያ ሴት የሠፋችውን ወራንታ፣ ጅል ትተረትረዋለች› እንደተባለው በደኅና ጊዜ ትጉኃን አበው የሰበሰቧቸውን ወጣቶች ካልበተንኩ ብሎ እንዴት አንድ ፓትርያርክ ይነሣል፡፡ ወጣቶቹ ሊሳሳቱ፣ ሊያጠፉም ይችላሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ለዚህም መንገድ ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሳይቀሩ የገዛ ልጆችዎን ያወያዩ ሲሏቸው በራቸውን ጠርቅመው የሚዘጉ ፓትርያርክ በታሪክ የሚጀመሪያው መሆን አለባቸው፡፡ በሱራፊ ነበልባል የተዘጋች ገነት ስትከፈት በፓትርያርክ የተዘጋች የቤተ ክህነት በር ልትከፈት አልቻለችም፡፡ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡ ኢየሱሳውያንን በዐደባባይ ሳናነጋግራቸው መሄድ የለባቸውም ብለው የተሟገቱ እነ እጨጌ በትረ ጊዮርጊስ በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን ለማነጋገር በር የሚዘጋ እጨጌ ተፈጠረ፡፡ የመካ ቁራይሾችን አሳልፈን ለጠላቶቻቸው አንሰጥም የሚሉ አበው በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን አሳልፎ የሚሰጥ አባት መጣ፡፡

  ReplyDelete
 2. Leboch yetehadso telalikiwoch selmatawkut mawerat tewedalachu

  ReplyDelete
 3. Your always working against our church but now you Sims like supporter of our father kkkkkkk

  ReplyDelete
 4. ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ እሉ።አይ አንተ ከሀዲው፣ አንተ እንኳን እመ ብርሀንን እና ቅዱሳንን ተሳድበህ አደል እንዴ ተወግዘህ የተለየህ ::እኛ ኦርቶዶክሳዉያን የቤተክርስቲያንን ታርክ ስለምናውቅ፣እነ እትናቴወስ በነበሩበት አርዮስ እንደነበረ ሁሉ::እነ እቡነ ተክለ ሀይማኖት በነበሩበትም ካድሬ መቀመጡንም ጠንቅቀን እናውቃለን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ ያልሆነ ሁሉ ለእናንተ ተወግዞ የተለየ ነው አይደል? ማፈሪያ

   Delete
  2. ጅሉ እኔም አባል አደለሁም፣ግን አልተውገዝኩም ምክኒቱም ከሀዲ ሆዳም አደለሁም፤የማቅ ምዕመናን። አላማም ምዕመናንን ማፅናት እንደሆነ በደንብ ታውቃለህ ማፅናት። አሁን መድረሻ አጣችሁ፣ይች እድሜ ልካችሁን ውሸት የምትለቁባት ገፅ ነች የቀረች

   Delete
 5. ልክ ብለሃል

  ReplyDelete
 6. Meche new degmo kes yehonew??kehnet mekeljja hone ezih betecrstiyan wost.

  ReplyDelete
 7. ወይ ጉድ !
  የማይገለጥ የተሠወረ የለም ይገርማል!
  ዳንኤል ስትባል መንፈሳዊ ሰው መስሎኝ ነበር
  ለካስ የበግ ለምድ ለብሰህ ምዕመናንን ወደ ሲኦል የምትመራ ሰይጣነ ጸሪፍ ያደረብህ ቍንጽል(ቀበሮ) ነህ
  የጦር መሳሪያ ይዘው እንዲነሱ ተቀሰቅሳለህ ስንኳን ያንተ ቅስቀሳ (የጃዋር መሐመድ ኦሮሞ - እስላማዊ ቅስቀሳ)እንኳ አልሰራም።
  መንፈሳዊ አልመሆንህን የጻፍከው ብዕር ምስክር ነው።
  በመሰረቱ ዲያቆን አይደለህም በምን ዕውቀተህ?
  ዲቁናው ከማን ተቀበልከው? ምናልባት (ከጃዋር መሐመድ ኦሮሞ ተቅብለኸው ከሆነ ልክ ነው ይመስላል።
  የክርስቲያን ሃይማኖት በሃይማኖታችሁ ሙቱበት እንጂ ግደሉበት አይልም ፣ ትህትና እንጂ ትእቢት አያስተምርም
  (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 12)
  ----------
  16፤ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።

  17፤ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።

  18፤ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።

  19፤ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።"
  (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 13)
  ----------
  1፤ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

  2፤ ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።

  3፤ ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤

  " ግበ ከረየ ወደሀየ።
  ወይወድቅ ውስተ ግብ ዘገብረ።"
  ወይገብእ ፃማሁ ዲበ ርእሱ " የተባለውን አስብ።
  በቆፈርከው ጕድጓድ እንደ ሃማ ሳትገባ አትቀርም እየተጠናህ ነህ።
  ይበቃል ልብ ይስጥህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Alemawek hatyat aydelem mejemrya tarekehen ewek

   Delete
 8. ፓትርያርኩ አለማስቆማቸው አንተ እረግጠኛ ነህ? ማህበሩ "በኦፊሴል የምናውቀው ነገር የለም”
  አለ እንጅ የሉበትም አለ?

  ReplyDelete
 9. Daniel is the pseudo priest, and has no moral to insult our patriarch, first he is not legal priest. This man consider himself as church scholar,but he is illiterate man and brought up in the illegal association MK. This is the result of MK for the church.Now it is the right time to revoke MK's license to keep the its unity and respect her authority.

  ReplyDelete
 10. Ahun bante bet neger serah malet new melikt yemhedibetin bet yemyankuakawen dej yawkal sehtet yalebetin sew mestawet akiribo erasun endeyayibet madireg hatiat aydelem esti endedaniel astemiren ahunem lematalat sew ayasfeligim seytan beki new enanten yizo mech hail aterew?

  ReplyDelete
 11. ‘’...ሕግን አውቆ የማይሠራባት ... ቄስ ይሻር’’
  ይህ በትክክል የሚገባው ለአባ ማትያስ ነው፡፡
  እስኪ ዳንኤል ከዘረዘራቸው ጥቂት ስራዎቻቸው ሀሰት የሆነው የቱ ነው??

  ‘’ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች በጎጆ ቤት ዋጋ በሙስና ለዐሠርት ዓመታት ሲከራዩ ተኝተዋል፤ ከመንበረ ፕትርክናቸው ሥር ባለች አጥቢያ የቤተ ክርስቲንን ገንዘብ አናስበላም ያሉ ካህናትና ምእመናን ሲባረሩ ተኝተዋል፡፡ በሕዝብ ጥያቄ ሽፋን ጽንፈኛ አቋምን በሚያራምዱ ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ይተኛሉ፤ የስልጤ ዞን ምእመናን በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ እየተቀበልን ነው ሲሉ ይተኛሉ፤ ቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ሲሆን ይተኛሉ፤ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሲዘጉ፣ ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲበተኑ ይተኛሉ፤ በመሥዋዕትነት የተመሠረቱት የደቡብ አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት በሙሰኛ አመራሮች አደጋ ላይ ሲወድቁ ይተኛሉ፣ ይሄ ሁሉ ዘለፋና ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲዘንብ ይተኛሉ፡፡

  መናፍቃንን የሚተች ጽሑፍ በኦርቶዶሳውያን ተጻፈ ሲሏቸው፤ ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ ሕዝቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ ነው ሲሏቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው ሲሏቸው፤ ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ ሲሏቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሊቀርብ ነው ሲሏቸው ያን ጊዜ ብዕራቸውን ይዘው ለማገድና ለመክሰስ ይነቃሉ፡፡ ‘’
  ‘’ማኅበሩም ኦፊሲያል በሆነ መልኩ ያወቅነው ነገር የለም’’ እንጂ እጃቸው የለበትም አለበትምም አላለም፡፡
  እስኪ መናፍቅ ተነካ…ብሎ መጮህ ምን ይሉታል? ከማን ወገን ቆመው ይሆን ካከበረቻቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን ወይስ ከመናፍቅ አማሳኞች? እናንተ ሳትሆኑ ቀን ይመልሰዋል፡፡

  ReplyDelete
 12. ማቅ ምቅቅቅ ያለ ማሕበር ነው

  ReplyDelete
 13. ይገርምሃል ዲያቆን ዳኒ መቼም ይሁን መቼ ተጨባጭ ነገር ሳይዝ አይጽፍም አይናገርምም። ከላይ አንድ Anonymous እንደለው "በኦፊሴል የምናውቀው ነገር የለም”
  አሉ እንጂ የሉበትም በሎ አልተናገሩም ባይናገሩም የተዋቀ ነው። እናንተ ሁሉም ነገር የሚገባችሁ እንደ አህያዋ ስለሆነ ባለማመዛዘናችሁ አይፈረድባችሁም።

  ReplyDelete
 14. እግዚኦ ያንተ ያለህ ባሁኑ ጊዜ ለራብተኛው ሕዝብ ምህላ መያዝ ጸሎት መጸለይ ሲገባ
  የጥቅምና የስልጣን ሽኩቻ የሚገባበት ጊዜ ነው? አየጉድ ምናለ ካልቻሉበት ቢተውት
  እልክ መጋባት ጥፋትና ውድመት የሚያመጣ መሆኑን ግራም ቀኙም ያውቁታል።
  ዳሩ ግን አንተ ወጣዖታቲክ ኅቡረ ትወርዱ ውስተ ገሀነም እንደተባለው ሁሉም ለጥፋት ተዘጋጅቷል እናም በጊዜው ጊዜ ወደ ሸለቆ ይወርዳል።ፈራጁም ቀይ ብዕር ጨብጧል ፌርማውን ለማስቀመጥ ተዘጋጅቷል በምን አውቀህ ትሉኝ እንደሆነ መልሱ
  እንደናንተ ነዋ!

  ReplyDelete
 15. የዳንኤል የትእቢት ጽሁፍ የተሻለ መልስ ያስፈልገዋል። አባ ሰላማዎች እስኪ እዚጽ ላይ ስሩባት። ጽሑፉን በጽሞና ላነበበው ምን ያህል ግብዝነት የተሞላበት እንደሆነ ማንም ያስተውላል። I am not sure if Daniel understands how hypocrite he is. ምነው ራሱና የራሱ ማህበር ላይ ሲመጣ ነው በር ስለመዘጋት ከዚያም አልፎ የክርስቶስ ሰምራን ገድል ጠቅሶ ሰይጣንን እንኳ ማናገር እንዳለብን እስከመናገር የደረሰው። ስንቶቹ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን በግፍ እና በሃሰት በሱና በሰይሳኑ ማህበር ከሳሽነትና ፈራጅነት ብቻ በሌሉበት ተፈርዶባቸው ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል? የነሱ እንዴት አልቆረቆረውም? ለነገሩ የዳንኤልም የማቅም አሰራር ግብዝነት (hypocrisy) የሞላበት እንደሆነ ስለማውቅ አልገረመኝም ግን ትንሽ አንጀት ይመልጣል።

  ReplyDelete
 16. የማይገሠፅ ፓትርያርክ የለንም !
  (ርዕሱን የተጠቀምኩት ፥ በፌስቡክ ከአንድ የሌላ ሰው ጽሑፍ ሥር ከተሰጠ አስተያየት ቀጥታ በመውሰድ የራሴን ሐሳብ ለማብራራት ተመራጭ ሆኖ ስላገኘሁት ነው)
  ፓትርያርኩ ሮምን ጎብኝተው በተመለሡ ማግሥት ጀሌዎቻቸው ተሰበሰቡና " ማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርኩን ይቅርታ ይጠይቅ " አሉ ። ቀደም ብለው እኝህ ሰው አባ ማትያድ " ከካቶሊክ ጋር የሰፋ ልዩነት የለንም ፤ ልዩነታችን ጠባብ ነው " ማለታቸውን ልብ ላለ ሰው እና የጀሌዎቻቸው "ይቅርታ ይጠየቁ " ምክር የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን ።
  ሲጀመር እኛን ኦርቶዶክሳውያንና እነዛን ካቶሊካውያን አንድ የሚያደርገን የሃይማኖት ትምህርት የቱ ነውና ነው " ከካቶሊክ ጋር የሰፋ ልዩነት የለንም ፤ ልዩነታችን ጠባብ ነው " የምንባለው ?!
  ባይሆን ፦ ሆዳቸው እንደ ባሕር የሰፋ ፣ አዕምሮአቸው እንደ መርፌ ቀዳዳ የጠበበ የፓትርያርኩ ጀሌዎች " ለፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፍና ሽቅብ እሳቸውን መናገር ስህተት ነው " አሉና " ማኅበረ ቅዱሳን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል " በማለት ስፋትና ጥበት የሌለበትን የራሳቸውን ካቶሊካዊ አስተምህሮና እምነት ፥ ቀድሞ ፓትርያርኩ " ልዩነት የለንም " ሲሉ ፤ አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ " እሳቸውን ማን ተናግሮ ?! " አሉና " ይቅርታ ይጠየቁ " በማለት የእምነት ጠርዛቸውን "ፓትርያርኩ የክርስቶስ እንደራሴ ነው ፤ የፓትርያርኩ ሁሉ ነገር ትክክል ነው " በሚለው የካቶሊክ ፈሊጥ ለክስ ተነሡ ።
  አሁን ለእኔ ትርጉም የሰጠኝና ሰውም እንዲያስተውለው የወደድኩት የአባ ማትያድንም ሆነ የግብረ አበሮቻቸውን " ካቶሊክ ፣ ካቶሊክ " የሚሸት ተግባር ነው ። ለዚህም ነው የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን ያልኩት። እንጂ " መሰደብ አለባቸው (ምናልባት ተሰድበው ከሆነ ፥ ማኅበረ ቅዱሳን አልተሳደበም እንጂ) ፣ ይቅርታ መጠየቅ አያስፈልግም ... " ዓይነት ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ ለመግባት አይደለም ።
  ሆኖም ግን የአባ ማትያድን " ከካቶሊክ ጋር ልዩነት የለንም " እና የጀሌዎቻቸውን " ይቅርታ ይጠየቁ " የሚለውን ምክንያተ ነገር በዚህ ጽሑፍ ልለፈውና " ፓትርያርክን ሽቅብ መናገር አይገባም ፤ ፓትርያርኩ የተናገረውና የሚያደርገው ሁሉ ትክክል ነው ፤ እሱ የክርስቶስ እንደራሴ ነው ፤ እርሱን መናገር ድፍረትና ስህተት ነው " የሚሉ ጨዋታዎች ላይ ጥቂት ነገርን ለማስገንዘብ ወድጃለሁ ።
  ይኼም አስተሳሰብ በአንዳንድ የዋሃን ምዕመናን ዘንድም ሲነገር ስለምሰማ ነው ፦
  - እሳቸው አባት ናቸው መታዘዝ አለባችሁ
  - ያሏችሁን እሺ ብላችሁ ብቻ ተቀበሉ
  - ፓትርያርኩን መናገር የለባችሁም
  - እግዚአብሔር ነው የሾማቸው ( ቀልድ ¡ ... አላየንም አልሰማንም አሉ ሲሾሙ ¡ .... አስቀድሞ ሳጥናኤልን የሾመው ማን ነበር? ግብሩ ሌላ ሆነ እንጂ! ... ሳኦልን ንጉሠ እሥራኤል አድርጎ የሾመው ማነው? ... ውጤቱን አይተነዋል እንጂ! ... ይሁዳን ሐዋርያ ያደረገና እንዲያውም የማኅበረ ሐዋርያት ዐቃቤ ንዋይ /ገንዘብ ተቀባይና ሰብሳቢ/ አድርጎ የሾመው ማን ነበር? ... ሣንቲም ይሰርቅ ነበር እንጂ! ..... መሾሙንማ እግዚአብሔር ሾሟቸው ነበር ፤ ግን ተገስፀዋል ፤ ሽቅብም ተመክረዋል ። አልሰሙምና ተጥለዋል እንጂ )

  ReplyDelete
 17. Yihe mahi.. Kidusan yemibal betbach group iskemeche naw zim yeminilew?

  ReplyDelete
 18. የቀሲስ ዳንኤል ክብረትን ጽሁፍ አንብቤአለሁ አልታነጽኩበትም እንጂ።
  ክርስቲያኖች በመከራቸው ጊዜ ሲጨነቁ (ሲጨመቁ) የሚወጣቸው ምን እንደሚሆን ጌታችን ሲያስተምረን “የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የሚል ቃል በመስቀል ስብከቱ ተናግሮአል። ዛሬም ይህ የጌታችን ጸሎት ይሰራል እስከ አለም ፍጻሜም ሲሰራ ይኖራል። ከጌታችን የተማሩ እውነተኞቹ ክርስቲያኖች እንደነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ያሉ ቅዱሳን ሰማዕታት ይህን የከበረ ቃል ደግመው ተናግረዋል። አብዛኞቹ ቅዱሳን በመከራ ሲያልፉ ከድግስ ቤት ጠግቦ እንደሚወጣ እድምተኛ ደስ እያላቸው በጌታቸው ሐሴትን እያደረጉ በስድብ በግርፋት በንቀትና በውርደታቸው ስለስሙም በመገፋታቸው ከአምላካቸው የክብር አክሊል እየተቀዳጁ በፀጋ ላይ ፀጋ ሲጨመርላቸው አይተናል ሰምተናል አንብበናል። ታዲያ የቅዱሳን ልጆች ነን ብለው ከቅዱሳን በረከትን ለማግኘት ማህበራቸውን “ማህበረ ቅዱሳን” ብለው ሰይመው የቅዱሳን ልጆች ተብለው እራሳቸውን ጠርተው እንዴት በቅዱሳን ግብር መገለጥ አቃታቸው። የዝግጅቱ አለመቅረብ ለማህበሩ አባላት ከባድ ፈተና ሆኖ ሊሆን ይችል ይሆናል። ይሁንና ሁሉንም ለበጎ ነው ብሎ ለመቀበል መቸገር አልነበራቸውም። ከመስዋዕት መታዘዝ ይበልጣልና በእሽታ ቢያልፉት ታላቅነታቸው ይገለጥ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉን ለበጎ ያደርጋልና ማንነታቸው እንዲገለጥ ይህን ፈተና አመጣ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ሆነ። የሚሰዱባችሁን መርቁ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመተላለፍ በቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ስልጣን ላይ የስድብ ናዳ አወረዳችሁ። የተሰደቡት እሳቸው ሳይሆኑ በብዙ ሚሊዮን የምንቆጠረው የቤተክርስቲያኗ ልጆች ነን። እግዚአብሔር በቤቱ የሾመውን በጊዜው ለማንሳት ብቃት እንዳለው እናምናለን። ይሁንና እኛን ባልተመቸን ቁጥር ግን እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጃችንን ለማንሳት አፋችንን ለማላቀቅ ብዕራችንን ለመሳል ድፍረት የለንም (ካመናችሁ ያለእግዚአብሔር ፈቃድ ምንም እንደማይሆን)። በእርግጥም የከለከሉት እሳቸው ቢሆኑስ በልጅነት መንፈስ መጀመሪያ በመጸለይ ተግሣጽም ቢኖር በአግባቡ ማድረግ ሲገባ እንዲህ ያለ አሳዛኝ ጽሁም በአለም መበተን እጅግ ያሳዝናል። መቼም ቀሲስ ዳንኤልና ማህበረ ቅዱሳን ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደሆኑ ይታወቃል። የማህበሩም አቋም ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ እጅግ ያሳዝናል እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግስት ቤትም ቢሆን አይጸናም ብሎናልና ጌታችን። ስለዚህ ቤተክርስትያን እጅግ ልታስብበት ይገባል። ቢያንስ በአለም የስራ ስፍራችን ያሉትን አለቆች የምናከብረውን ያህል ክብርና መታዘዘ እንኳን ለቤተክርስቲያን አባቶች ልናሳይ ይገባል። ዛፍ በፍሬዋ ትታወቃለችና ቀሲስ ዳንኤል ያሳዩት ፍሬ መራርና መርዝ የሞላበት ነውና ብዙዎች በልተው እንዳይታመሙ ቀሲስም ለመረገም እንዳይቀርቡ ከወዲሁ ለይቅርታ ብዕራቸውን አንስተው የበደሏትን የሰደቡአትን ቤተክርስቲያን (ማህበረ ምዕመናንን) ይቅርታ እንዲጠይቁ በትህትና እንጠይቃለን። ከማህበረ ምዕመናን ለመለየት ዳር ዳር እያለ ያለውን ማህበራቸውን ወደ ማህበረ ምዕመናን እንዲያስገቡ (ከታሪክ ተወቃሽነት) እንዲተርፉ እናሳስባለን። የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ልብና ልቡናን እንዲሰጥዎትም እንጸልያለን።

  ReplyDelete
 19. ከዚህ በላይ የጻፍከው ሰው የገለጽከው መቶ በመቶ ትክክል ነው፡፡ ከሳሽ እነሱ ስም አጥፊ ሰይጣን እነሱ የአውሬውን የስድብ ምላስ ገንዘብ ያደረጉ እነሱ፡፡ ታዲያ "ማኀበረ ቅዱሳን" ወይስ "ማኀበረ ርኩሳን"? ይህ ዳንኤል የምትለውም እርሱ በኑፋቄ የተሞላ ሆኖ እያለ ቤተ ክህነትን የኑፋቄ ማህደር ይላል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ ሰይጣን ከማለት የበለጠ ክህደትና ሰይጣናዊ ትዕቢት የለም፡፡ ምናልባት እንዳልከው ሕሊና ቢኖረውና ልቦና ቢሰጠው በጅምላ የሰደባቸውንና ያዋረዳቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመናን ይቅርታ ቢጠይቅና ለራሱም ንስሐ ቢገባ ይሻለዋል፡፡

  ReplyDelete
 20. ሰቃልያን ዛሬም ለመስቀል አልታከቱም - እኛም ተስፋ አንቆርጥም

  ንጹሕ ደም አሳልፈው በመስጠት የኅሊና እርካታ ያገኙት ተረፈ አይሁድ ዛሬም ቤተክርስቲያንን ዕለት ዕለት ለመስቀል ይሮጣሉ፡፡ ለዚህ ኃይል የተሰጣቸው ናቸውና በእውነት ለማገልገል ከሚወጡ ከሚወርዱት የተሻለ ጊዜ እና ሁኔታ የተመቻቸላቸው ይመስላል፡፡
  እውነተኛ እና ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የተሰማ ዕለት መርዝ እንደጠጣ ያንፈራግጣቸዋል፡፡ ይኽም እውነትን ለመስቀል ነው፡፡ በጉቦ ቅሌት ዓይን ያወጣ ምዝበራቸውን ለማጧጧፍ ብዙ ድንጋይ ይፈነቅላሉ ይሳካላቸዋል፡፡ እምነትን ለመስቀል! በቤተ ክህነቱ መዋቅር ሥልጣን ያመቻቻሉ፣ ይመቻመቻሉ… በመደለል እና በደላላ "ይሾማሉ" ቤተ ክርስቲያንን ለመስቀል! ዛሬም ከሁለት ሺህ ዓመታት ወዲያ ከወትሮው ስቅሎ ስቅሎ "መዝሙራቸው" አልተላቀቁም፡፡
  ግን እኮ ከመስቀል ባሻገር ትንሣኤ አለ፡፡ እነርሱ ይሰቅላሉ ቤተ ክርስቲያን ግን ትነሣለች!

  ተስፋ ማስቆረጥ የሚችሉ መስሏቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተስፋ የሚቆርጡ ሀሞታቸው የፈሰሰ ልጆች ኖሯት አያውቅም፡፡ እናም በዚህ ተስፋ አንቆርጥም፡፡ "ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።" የሚለው ቃል የቁርጠኝነታችን ማኅደር ነው፡፡ ዕን ፫፥፲፯-፲፱። እየዘመርነው እንጋደላለን፡፡ እውነት ስትሰቀል አብረን አንሰቅልም፡፡ በዚህ ክፉ ሥራ መቼም አንተባበርም፡፡ ለትንሣኤዋ ግን እንፋጠናለን፡፡ ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም፡፡
  ዕውቅና የምንሰጠው የእነርሱን መለምለም ሳይኾን የእኛን ወገንነት ነው፡፡ እነርሱ ቢበረቱም እውነታችንን ግን ሊቀሙን አይችሉም፡፡ ሐዋርያት "የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም" ያሉት ለዚህ ነው፡፡ "ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።"እንዲል፡፡ ፪ጢሞ ፪፥፱። በለስ ባታፈራም እግዚአብሔር አይካድም፡፡ ለጊዜው ክፉ ሥራ እንደ ከፍ ብሎ ቢታይም ስንመለስ ግን አናገኘውም፡፡
  "የእግዚአብሔር ጠላቶች በከበሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠፋሉ። . . . ኃጥእን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።" እንዲል መዝ ፴፮፥፳። ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም፡፡ እነርሱ ባይጠፉም እኛ ተስፋ አንቆርጥም፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ "ባያድነንም ላንተ ጣኦት አንሰግድም" እንዳሉት እኛም እንከተላቸዋለን፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ስለ እግዚአብሔር ከሃሊነት "አምላካችን ከሚነድደው እቶን ሊያድነን ይችላል" በማለት አሚናቸውን ገልጠዋል፡፡ ነገር ግን ችሎታው እያለውም ቢኾን እኛ ሰማዕትነት እንድንቀበል ፈልጎ ከኾነ ደግሞ ላያድነን ይችላል፡፡ ስለኾነም ላንተ ጣዖት የማንሰግደው ስለሚያድነን ብቻ ሳይኾን ባያድነንም ጭምር ነው ብለው ተናገሩ፡፡ ስለዚህም በሚኾነው እየኾነም ባለው ተስፋ አንቆርጥም፡፡

  ReplyDelete
 21. እናንተ ሰዎች ግን በጣም ነው ምትግርሙ ፥ ልናንተ ሲሆን ነው ቀኖና ሚሰራው

  ReplyDelete
 22. በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ሬድዮ በሚተላለፍ ድራማ ላይ እማማ ትርፌ የሚባሉ ገፀ ባህርይ ነበሩ። የእሳቸው ብሎግ መሆኑ ገባኝ።

  ReplyDelete
 23. አነበጋሻው አዳራሽ ጉባኤ አደረጉ ብላችሁ ስታብዱ አልነበረ? ለ ማቅ ሲሆን መካነ እየሱስ ቸርች እንኴን አውደ ርእይ ቢያዘጋጅ ችግር የለም።ለማንኛውም በጋሻው ዝም ብሎ ይበልጥሀል።ቢያንስ ዲቃላ አልወለደም።

  ReplyDelete
 24. ተሀድሶ ፣ ዝም ብለህ የሚሰጥህን ብር ብላ፡፡ እንደ አንተ አይነቱ ፣ ዳንኤል ክብረትን ሊናገር አይችልም፡፡ የማናቃችሁ መሰላችሁተሀድሶ ፣

  ReplyDelete
 25. ትርጓሜ ዘመናፍቃን፣ ኪኪኪኪ፣ አይገባችሁም እኮ???? እውነትን ለናንተ አላርጅክ ናት፣ እናንተ የምትፈልጉት የውሸት አምልኮታችሁን እየተቀበለ እንደተሳቢ መኪና የሚሳብ እንጂ እውነትን የሚያሳይ ሰው ለናንተ አላርጅክ ነው፣ ለውሸት ተከታይ አይመችም፣ ዳኒ እውነት እግዚአብሔር ይባርከው፣ እንደናንተ እራሱን ደብቆ አይደለም መስቀልን ተሸክሞ ነው እውነቱን ያሳየው፣ የተደረገውን እንጂ ያልተደረገው አልተናገረም፣ ሳጥናኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ነበረ፣ነገር ግን ከክብሩ ሲወርድ አይ አለቃዬ ነው ብሎ አላለፈውም ተዋግቶ ነው ያሸነፈው ራእ 12፣7-8፣ አባት ስለሆኑ ከእነስህተታቸው ተሸከሟቸው አልተባለም፣ የአባትነት ስራቸውን ካጣንባቸው እውነታን ማሳየት ግድ ይላል፣ ጌታም እኮ በወንጌሉ የሚገርም የተግሳጽ ትምህርት ሲያስተምር ሰምተነዋል፣ ከውሾች ተጠበቁ፣ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፣ የመጥምቁ የሐንስ ስብከት እናንተ የእፍኝት ልጆች ፣ሌሎችም እነዚህ ቃላቶች እኮ ካላስተዋልናቸው በሰዋሰወኛው ከባድ ቃል ነው፣ ግን ይህንን ቃል በተረጎምንበት ህሊና ደግሞ የዳኒን እውነታ ብናየው ኖሮ ይህንን የሚያስቅ ከመንፈሳዊ እውቀት ጽድት ያለ ንግግር ባልተናገራችሁ ነበር፣ ለነገሩ በወንጌሉ የለመዳችሁት አእምሮ ስለሆነ የምትተረጉሙት ምንም ብትሉ አይገርምም፣ ዳኒ እግዚአብሔር ይባርከው፣ አሁንም ጤናውን ቤተሰቡን ሁሉ እድሜና ጤና ይስጠው፣ የአገልግሎት ዘመኑን ይባርክለት፣

  ReplyDelete
 26. 'patriarch mal tiliq abat naw'of course sawun tilik yemiyasagnaw sim bicha aydelam tagbarim chimir inji .source pap shinoda

  ReplyDelete