Monday, March 28, 2016

ዘማሪ እንግዳ ወርቅ በቀለ ታቦት ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተያዘከመጀመሪያዎቹ የባህታዊ ገብረ መስቀል ተከታዮች አንዱ የነበረውና በኋላ ላይ ስለማርያም ዘማሪ ሆኖ የተገለጠው እንግዳ ወርቅ በቀለ ሰሞኑን ታቦት ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዞ መታሰሩ ተሰማ፡፡ እንግዳ ወርቅ ፀረ ወንጌል አቋም ያለው በመሆኑ በሚያወጣቸው የመዝሙር ካሴቶች 8 የማርያም 2 የክርስቶስን ብቻ በመዘመር ይታወቃል፡፡ ከዚህ የተነሣ “ኦንሊ ማርያም” እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ በቀጥታ ለእግዚአብሔር የተነገረውን በድፍረት ለድንግል ማርያም ሰጥቶ በመዘመሩ ነው ይህ ስም የተሰጠው፡፡ 

በተለይ “ቆይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት” የሚለውን የመዝሙረ ዳዊት ክፍል “ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን” ብሎ መዘመሩ ብዙ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን አሳዝኗል፡፡ በተጨማሪም “በእስራቴ አላፍርም እኔ የማርያም ነኝ ሮማዊ አይደለሁ ፍጹም ክርስቲያን ነኝ” በማለት የክርስትና መሠረት የሆነውን የክርስቶስን ስፍራ በማርያም ተክቶ ዘመሯል፡፡ ሰው ክርስቲያን የሚሆነውና ክርስቲያን ተብሎ የሚጠራው በክርስቶስ እንጂ በማርያም አይደለም፡፡ “በወልድ ውሉድ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን” መሰኘታችን የታወቀ የተረዳ የክርስትና ትምህርት ነው፡፡ እንግዳ ወርቅ ግን እውነትን እስከዚህ ድረስ እየለወጠ ሲዘምርና ክሕደትና ኑፋቄን ሲያቀነቅን ቤተክርስቲያን ድምጿ አለመሰማቱ ምን እየሠራች ነው አሰኝቷል፡፡ ለኑፋቄና ለክሕደት ትምህርት በሯ ምን ያህል ክፍት እንደሆነም የሚያሳይ ነው፡፡ 

ማኅበረ ቅዱሳን የዚህን ሰው መዝሙር አዘውትሮ በመክፈትና በመሸጥ ይታወቃል፡፡ ማኅበሩ የህልውናው መሰረት ባደረገው ስለ ተሃድሶ ግንዛቤ የማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ ሁሉ እንግዳወርቅ እየተገኘ የጉባኤው አድማቂ በመሆን መዝሙሮቹን በማቅረብ ይታወቃል፡፡ አብሮም ያወግዛል፡፡
ለመኖር ሲል የእግዚአብሔርን ስም ፍቆ በኪዳነ ምህረት በመተካት፣ የክርስትና መሠረት ክርስቶስ ሳይሆን ማርያም ናት እያለ በመዘመር ሕዝቡን ከእውነት መንገድ ሲያስወጣ የኖረው እንግዳ ወርቅ ከሰሞኑ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ መታወቂያ የሆነውን ታቦት በ“ብላክ ማርኬት” እንደሚመነዘር ዶላር በድብቅ ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ራስ ደስታ አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስሯል፡፡
ከኢየሩሳሌም የመጡና አባ ገብረወልድ የተባሉ መነኩሴ አሜሪካ ቤተ ክርሰቲያን ለማቋቋም ፈልገው ለዚህም ፅላት እፈልጋለሁ በማለታቸው ዘማሪ እንግዳ ወርቅ ባለፈው ቅዳሜ ከሠዓት በኋላ በቪትስ መኪናው ከሱቁ ማለትም ከጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተከራይቶት ንዋያተ ቅድሳት ማካፋፈያ አድርጐ ከከፈተው ሱቁ ጽላቱን በሱቲ ጨርቅ ጠቅልሎ ለተባሉት መነኩሴ ሲያስረክብና ዋጋውን 90 ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ሊያዝ ሲያዝ ለጊዜው ማንነቱ ያልታወቀ አንድ ባልደረባው (ምናልባትም ፅላት ቀራጭ ሊሆን ይችላል) ሊሠወር ችሎአል፡፡
ቤተክርስቲያን አሉኝ ከምትላቸው ንዋያተ ቅድሳት አንዱ የሆነውና ለሕዝቡ ብሉይ ኪዳን እየተጠቀሰለት እንዲያመልከው የሚደረገው ታቦት እንዲህ እንደ ሸቀጥ በሕገወጥ መንገድ የሚሸጥና የሚለወጥ መሆኑና ከዚያ በኋላ ደግሞ ታቦት ተብሎ የሚሰገድለት መሆኑ ትልቅ ጥያቄ የሚፈጥር ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን ተሐድሶ እንዳይሆንና ይህን ከመሰሉ የስሕተት አሠራሮች ነጻ እንዳትወጣ የእግዚአብሔር የንስሐ ጥሪ ለሆነው ተሐድሶ ሌላ ስምና መልክ  በመስጠትና በማውገዝ ታቦትን በመሸጥና በመለወጥ ጭምር የራሳቸውን ትርፍ ለማግኘት እንዲሁም በማቅ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚደክሙ ዘማሪያን እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ነገር ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡፡
ዘማሪ እንግዳወርቅ በዚህ አጋጣሚ እንደዚህ ተጋለጠ እንጂ ከዚህ በፊት ምን ያህል ታቦት ሸጦ ይሆን? የሚለው ግልሰቡ አሁን ካለበት የመኪና ንግድ ቢዝነስ አንጻር መታየት አለበት፡፡ መቼም ካሴት ሸጦ ብቻ የመኪና ንግድ እንዳልጀመረ የሚታወቅ ነው፡፡ አብያተ ክርስቲያናት የሚያከራዩአቸው ሱቆች ውስጥ ያሉ የንዋየ ቅድሳት ማከፋፈያዎች በተለይም ራጉኤል አካባቢ ያሉት በዚህ በድብቅ የታቦት ንግድ በሰፊው ይታማሉ፡፡ እንግዳወርቅ የቤተ ክርስቲያን ሱቅ የተከራየው ለሽፋን እንደሆነና ታቦትን እንደሚነግድብት በተጋለጠው የታቦት ሽያጭ ድርጊቱ መረዳት ይቻላል፡፡
እንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ የበለጠ አንገት የሚያስደፋ ታሪክ በአባሉና በተቆርቋሪው አልገጠመውም፡፡ማቅም በንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቆቹ ታቦት እያስቀረፀ በተለይ ለውጪ አባላቱ እንደሚልክ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ ደጀኔ ሽፈራው፣ ፍቅረ ኢየሱስ ጋረደው፣ ያሬድ ገ/መድህን በሳምሶናይት ይዘውት በወጡት ታቦት አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን አቋቁመውበታል፡፡ ያውም ያለ ሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ፡፡ እንግዳ ወርቅና መሰሎቹ ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ እንደዳይሆን ተግተው የሚሰሩት ሃይማኖት ኖሯቸው ሳይሆን እንዲህ ያለው የንግድ ትርፋቸው እንዳይቀር ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን በዚህ መንገድ እየተሸጠ እየተለወጠ ላለውና የብሉይ ኪዳን ጥቅስ በተሳሳተ መንገድ እየተጠቀሰለት ሕጋዊ መስሎ ለቀረበው ታቦት የሚሰግደው ሕዝብ ነው፡፡


69 comments:

 1. ይህን አደገኛ ውንብድና የተፈጸመው የማህበረ ቅዱሳኑ እንግዳወርቅ መሆኑ የማህበሩን ቁልቁለት አመላካች ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቤት አቤት ፍርሃትና መደናበር! ቀንና ሌሊት የሚያስበረግጋችሁና እንቅልፍ የሚነሳችሁ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ራሳችሁ በነገር ውስጥ ሁሉ እሱን በማስገባታችሁ ተገለጠባችሁ እኮ! ዲ/ን እንግዳ ወርቅ ወንጀል ፈጽሞ እንኳን ቢሆን/ያወጣችሁት ማስረጃ የለውምና/ ለምን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ታጣብቁታላችሁ፤ ነገራችሁ ሁሉ እሱን ከመስደብና ከማሰደብ አላልፍ ያለው ለምንድን ነው፤ በጾመ ሁዳዴ አንድም ትምህርት የላችሁም እንዴ ደግሞ የማታምኑበት ታቦት ቢሰረቅ ባይሰረቅ ምን አገባችሁ፡፡
   የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ እኮ ስለነፍስና ስለጾም ግንኙነት እያስተማረ ይጽፋል፡፡ እናንተ ግን….. ማንነታችሁን ሥራችሁ ገልጦላችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
   አቤት አቤት ፍርሃትና መደናበር! ቀንና ሌሊት የሚያስበረግጋችሁና እንቅልፍ የሚነሳችሁ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ራሳችሁ በነገር ውስጥ ሁሉ እሱን በማስገባታችሁ ተገለጠባችሁ እኮ! ዲ/ን እንግዳ ወርቅ ወንጀል ፈጽሞ እንኳን ቢሆን/ያወጣችሁት ማስረጃ የለውምና/ ለምን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ታጣብቁታላችሁ፤ ነገራችሁ ሁሉ እሱን ከመስደብና ከማሰደብ አላልፍ ያለው ለምንድን ነው፤ በጾመ ሁዳዴ አንድም ትምህርት የላችሁም እንዴ ደግሞ የማታምኑበት ታቦት ቢሰረቅ ባይሰረቅ ምን አገባችሁ፡፡
   የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ እኮ ስለነፍስና ስለጾም ግንኙነት እያስተማረ ይጽፋል፡፡ እናንተ ግን….. ማንነታችሁን ሥራችሁ ገልጦላችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

   Delete
 2. ይሄ የሰይጣን ፈረስ

  ReplyDelete
 3. ይህን ብሎግ የከፈተዉ የማነ ዘመንፈስቅዱስ ነዉ እንዴ? ስለዚህ ሌባ ሰዉዬ ዝም አላቸሁ?እዉነተኛ ተቆርቋሪ ሳትሆኑ እንደ ኳስ ጫወታ ያዋጣኛል አያዋጣኝም ስሌት ዉስጥ ገብታችሁ የምትፅፉ የቤ/ክ ነቀዞች ናችሁ

  ReplyDelete
 4. ሰው ከአጋንንት እጅ ካልወጣ በስጋ ስለ ሆነ ከዚ የከፋም ሥራ ይከተለዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ መደሕኒቱ ክርስቶስ ኢየሱስ ቢቻ ነዉ፡፡ አገራችን በከፋ ሞራላዊ ውድቀት ውስጥ ገብታለች፡፡ መፍትሔው እዉነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ ይዘምር ነበረ ግን እዉነት አልነበረም፤ለተገለጠ አጢኀት ተገልቷል፡፡ ታዲያ እዉነትን አውቆ ቢሆን እዉነት አርነት ታወጧዉ ነበር፤ቢያምንበትና ታቦት ተብየው ልክ ቢሆን ይሁሉ ባል ሆነ፤በመዝሙሮቸሀ በጣም እናዝን ነበር በዚህ መንገድ መዋረዱን ባንፈልግም……..ግን ሆነ ለህይወቱ ጌታ የድረስለት ከዚ የከፋ ሲኦል አለና፤

  ReplyDelete
 5. berewelede zena manbiluachihu!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. you protestants you really fictitous

  ReplyDelete
 7. ብሉይ ኪዳን እየተጠቀሰለት እንዲያመልከው የሚደረገው ታቦት: የብሉይ ኪዳን ጥቅስ በተሳሳተ መንገድ እየተጠቀሰለት ሕጋዊ መስሎ ለቀረበው ታቦት የሚሰግደው ሕዝብ ነው::

  በአዲስ ኪዳንስ?
  1.ወደ ዕብራውያን 9፥4 በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥
  2.የዮሐንስ ራእይ 11፥19 በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።

  ReplyDelete
 8. ወይ ጊዶ ወይ ጊዶ ወይ ጊዶ

  ReplyDelete
 9. ሁሉንም ነገር ከማህብረ ቅዱሳን ጋር ማያያዝ ትወዳላችሁ፥ አረ ትንሽ አምላክን ፍሩ፥ ዉሽት ምሆኑ ብዚህ ያስታውቃል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሁሉንም ነገር ከማህብረ ቅዱሳን ጋር ማያያዝ ትወዳላችሁ፥ አረ ትንሽ አምላክን ፍሩ፥ ዉሽት ምሆኑ ብዚህ ያስታውቃል

   Delete
  2. ምነው ቀንደኛ አደል እንዴ ስያተፋ ልክዱት ነው ኪኪኪኪኪ

   Delete
 10. mindegna leba zembele tabote ahysasefelegachewem bile atasetemerem zora temitem kemitezore ..... min ahle endabatacho asetene bicha eyaweracho ezebine kemitasaseto Nisa gebitacho Kiresetane biteweno
  keza lenesemacho enchelalen .... keze weche gin yetelate Dabelousen Were Anesemam bekeneto atedekemo ...

  ReplyDelete
 11. Minewe Ye Kenedegnawen Leba yenanetewe Abat Yewenote yemesekerotete Ye Yemane Birhane Lebinete debekachewete .... endenanete Leba selewen new beadebabaye ... erso Kenedegna Leba new mebalon yemiteshefenote

  ReplyDelete
 12. ጉድ በል ያገሬ ሰው!ለነገሩ ችግር የለውም ማህበረ ቅዱሳነ የሰፈቱልናለ።አይዞህ በርታ ወንድማችን ታቦት መሸጥ በአንተ አልተጀመረ ።

  ReplyDelete
 13. ውሸታሞች። ከስም ማጥፋት ውጪ ምን ታውቃላችሁ። ያላችሁት ሁሉ አንድ ቀን እውነት ሳይሆን እየተመለከታችሁ ደጋግማችሁ መዋሸታችሁ ያው የዲያብሎስ ልጅ ዲያብሎስ ሥለሆናችሁ ነው። ክፉዎች።

  ReplyDelete
 14. ዘማሪ እንግዳወርቅ በዚህ አጋጣሚ እንደዚህ ተጋለጠ እንጂ ከዚህ በፊት ምን ያህል ታቦት ሸጦ ይሆን?

  ReplyDelete
 15. እግዚያብሄር እንዲህ ሰውን እንደምታሳድዱ እርሱ ያሳዳችሁ እናተ ስራ አጦች ስራ ቢሶች ሰውን እየተሳደቡ መኖርን ጽድቅ አድርጋችሁታል እግዚያብሄር ይገስጻችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሳዳጅ ማን ሆኖ ነው? ሌላው ሰው አደለም እንዴ ሲያሳድ የቆየው ጌታ ፈራጅ ነው ይልቁንስ ይሄ ምንም አደለም ከዘላለም ፍርድ እራሱን ቢያስመልት

   Delete
 16. እውነትነቱ የፈለጋችሁት ዘማሪውን ማጥላላት ሳይሆን የሃሰት ትምህርታችሁን ለማስተላለፍ የተጠቀማችሁበት መንገድ ነው በመጀመሪያ እግዚአብሄር በሰማይ ያከበረውን እናንተ ማናችሁና ነው የምንሰማችሁ ሁለተኛው ደግሞ በራሳችሁ ያለውን ጉድፍ ሣታወጡ በውንድማችሁ ላይ ያለውን የምትመለከቱ እናንተ የእፍኝት ልጆች አስተውሉ ለነገሩ ጌታ በቃሉ ታያላችሁ ግን አትመለከቱም ታደምጣላችሁ ግን አታስተውሉም ያለው እንደናንተ ላለው ነው ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 17. በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ተዋህዶን የሲኦል ደጆች አይችሉአትም! እናንተ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ሆይ ተመለሱ እግዚአብሔር መሀሪ ነውና

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአብርሀም ዘር ሚባል የለም አንተ ፈሪሳዊ አጉል አትመፃደቅ

   Delete
 18. የማህበረ ቅዱሳንን ዶክትሪን ያጠኑ ሰዎች ዘማሪ እንግዳ የሥነ ምግባር እንጂ የሃይማኖት ችግር የለበትም ብለው እንደሚከራከሩለት እጠብቃለሁ

  ReplyDelete
 19. Seyetane baitune Seretobathuhale yeker yebelathu yetewahedone telate yatefalen

  ReplyDelete
 20. tiliku dabo lithone geta yidreslet

  ReplyDelete
 21. ጉድ ነው<! ሚገር መገለት ሌባ ክብሩን ያታው የሰረቀ ለት ነው ! እኔ በበኩሌ አሁን ከማቅ ምጠብቀው ሰርቀሀል ሳይሆን ላተፋው ማስተባበያ ነው ምክንያቱም እሱ ማለት ማቅ ስለሆነ ኪኪኪኪኪኪኪ

  ReplyDelete
 22. ኪኪኪ በናታችሁ የት ታሰረ እንጠይቀው ንገሩን ውሉደ ዲያብሎሶች

  ReplyDelete
 23. በእውነት አድርጎት ከሆነ ፈጣሪ የጁን ይስጠው፡፡ ነገር ግን በ ማሂበረ - ቅዱሳን ማሳበብ ጥላቻችሁን እንጂ እውነትን አላስተማራችሁንም ሊበሏት ያሰቧትን ጂግራ ደሮ ናት ይሏታል ሆነባችሁ ጥላቻችሁን መምክንያት አትርጩ፡፡ ሌባ የትም ቦታ ይኖራል ድርጊቱም አስከፊ ነው፣ አሁን እስኪ ከናንተ ውስጥ የቤተ ክርስቲያናችንን ቅርስ ታሪክ ንብረት ያወደመ የለም? ሙላውን መኮነን ግን በራሱ ሃጥያት ነው፡፡

  ReplyDelete
 24. Almachihu Tabot yitfa new minim yehaimanotu ewket yelachihum beaby tsom yebeg kiltim eyebelachihu piasa makiato eyecheletachihu yehaymanotu sew mesilachihu tikomalachihu lemehonu engdawerk yemahibere kidusan abal yehonew meche new? negerochin lemayayaz timokiralachihu metsehaf yenegeren yeamilikot melk alachew hailun gin kidewal bilo new enante degmo yeamilikotim melk yelachihu hailunim kidachihual wituna ezaw zanigaba betachihu gibu

  ReplyDelete
 25. Bezih blog yesew widket des yemiasegn yemihonibet lemin yihon yawm chaf yizachihu yesew widket des yemiasegnew degimo seytan new esti meles bilachihu temelketu benante blog haimanot temirenibet anawkim sidib enji mak mak kemalet yemakin rub bitizu melkam nebere gin minalbatim yadegachihubet akababi yimesilegnal tabot aytekimim eyalachihu yetewahido tekorkuari memsel yetabotu aserakiwoch enantew satihonu alkerachihum gena hig enkuan yalferedebetin enante yehaimanot sewoch leba alachihu yesewochin hatyatachewn yikir bitilu yenante hatyat yikirta yagegn neber.Atbizut ajirewin eko beletachihut

  ReplyDelete
 26. ዘላችሁ ማህበረ ቅዱሳን ላይ ፊጥ ማለት ትወዳላችሁ የቅድስት ድንግል ማርያምን ስም በክፋት ሳታነሱ አታልፉም ይባስ ብላችሁ ደግሞ ስለቅድስት ድንግል ማርያም በመዘመሩ ታወግዙታላችሁ፥፥ ለመሆኑ ከዕናንተ መካከል ሃጢያት ያልስራ ይህቺን ሴት ወግሮ ይግደላት የሚለውንስ የእየሱስ ክርስቶስን ቃል ዐላነባባችኹም ወይ 2ኛ ማንም ስው ተጠርጥሮ ይያዛል ያ ሰው ወንጀለኛ የሚባለው በማስረጃ ተደግፎ ፍርድን ሲያገኝ ብቻ ነው በተረፈ ወሬ ከማነፍነፍ አና አሉባልታ ከመንዛት ትንሽ ቆም ብላችሁ ብታስቡ ጥሩ ነው

  ReplyDelete
 27. Egziabher libuna yistachihu!!! enante menafqan!!!

  ReplyDelete
 28. Wegen Yezih tsihuf Alama/menfesu bitawek melkam yeslegnal

  ReplyDelete
 29. አሁን የተወራው ሌላ አንተ መታወራው ሌላ! አራምና እና ቆቦ እኮ ነው፡፡ የማነን ሌባ ያላችሁት እናንተ! ለመሆኑ ስንት ሌባ ነው ማኅበረ ቅዱሳን ጉያ ውስጥ ተከልሎ ያለው? የቤተ-ክርስቲያን አምላክ ያውቃል፤እሱም ይፈርዳል፤ ማህበሩን ያተቃወመ ሁሉ ሥም ማጥፋት እስከመቼ ነው የሚቻለው? እውን መንፈሳዊነትስ እንዲህ ነው?

  ReplyDelete
 30. እስከ ዛሬ ድረስ አባ ሰላማ የተሀድሶ ብሎግ ነው ሲባል አላምንም ነበር አሁን ግን አረጋገጣችሁልኝ ሲጀመር እንግዳወርቅ ይህንን ተግባር አይፈፅምም ሲቀጥል ደግሞ እናንተ ቤተክርስትያንን ማህበረቅዱሳን አላስደፍር ስላላችሁ ስማቸውን ማጠልሸት የምትፈልጉዋቸውን ሰዎች በሙሉ ከማህበረቅዱሳን ጋር ታያይዛላችሁ

  ReplyDelete
 31. ዘማሪ እንግዳወርቅ በዚህ አጋጣሚ እንደዚህ ተጋለጠ እንጂ ከዚህ በፊት ምን ያህል ታቦት ሸጦ ይሆን?

  ReplyDelete
 32. Enante yediabilos telalakiwoch yemisemachu yelem

  ReplyDelete
 33. Sew amlakun yiserkal sisegdina siyasegid noro

  ReplyDelete
 34. እንኳን ሰረቀ በሱ አልተጀመረ ።ዘማሪያችንን ለቀቅ አድረጉ።አባ ሳሙኤል ምድርን ከፍ አድርገው ተሸክመው አስባረኩ ብሎ የዘመረልን ያለ ዘማሪ እንግዳ ወርቅ ማን አለ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. በለው ከሰው ፍርድ የእግዛብሄርን መቆቆም ይችላል ብለህ ነው ጎሽ ምትለው ሌባ የሚያበረታታው ሌባ መሆን አለብክ

   Delete
 35. እንኳን ሰረቀ በሱ አልተጀመረ ።ዘማሪያችንን ለቀቅ አድረጉ።አባ ሳሙኤል ምድርን ከፍ አድርገው ተሸክመው አስባረኩ ብሎ የዘመረልን ያለ ዘማሪ እንግዳ ወርቅ ማን አለ?

  ReplyDelete
 36. በእንግዳወርቅ ታቦት መሸጥ በሃይማኖት ስም የሚነግደዉ ነጋዴዉ ዘመድኩን ምን አለ? መቸም የእርሱም እጅ ሳይኖርበት አይቀርም ዘመድኩን ገንዘብ ካየ ቤተ ክርስቲያን ከመሸጥ ወደ አይልም ተሾመ ነኝ ከአራዳ ጊዮርጊስ

  ReplyDelete
 37. ወሬ አያስፈልግም ክርስቲያን ከሆን። መጸለይ ነው ሰዎች ናቸው ተሳሳቱ በስህተታቸው ከኛ ውስጥ ኃጢያት የሌለበት ክርስቶስ እንዳለው በድንጋይ ይውገራቸው ካልሆነ ግን ዝም እንበል

  ReplyDelete
 38. አባ ገ/ወልድን ለቀቅ አድርጉት እሱ ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን ለመግዛት ሄደ እንጂ የተሰረቀ ይሁን አሊያም ሌላ ነገር እሱ እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነው። እንግዳወርቅም ቢሆን የቤተክርስቲያናችን እውነተኛ አገልጋይዋ ነው የስንቶቻችን ልቡና ያውቀዋል ያላየነውን ቅዱሳን ቦታ በነሱ አሰባሳቢነት ረግጠናል መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሰው ችግር ሲገጥመው በዛው በችግሩ ላይ ማባባስ ይወዳል እንጂ እንግዳወርቅ የቤተክርስቲያናችን ባለውለታ ነው ለማንኛውም መካሰሱ አይጠቅመንም እውነተኛ ክርስቲያኖች ከሆንን አንዱ የአንዱን በደል መተው አለበት ለእናንተ አልነግራችሁም ሁሉንም ታውቁታላችሁ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፍቅር ይስጠን።

  ReplyDelete
 39. የጽሑፋ አቅራቢ የሆንከው ራስህ የታቦት መሸጥ የሚያንገበግብህ ከሆነ አንተ ዳግም አልተወለድክም ማለት ነው
  በርሱ የሚያምን የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና(ዮሐ 3:16)
  ኢየሱስም መልሶ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። (ዮሐ 3:3)  ReplyDelete
 40. አቤት ይሄ ብሎግ የሚያስቅ ትውልድ የሚታይበት ነው፣ ኧረ አሁን ይሄንን የጸፍከው ሰው እኮ ማንነትህ ቢጣራ ስንት ታቦት በድብቅ ሸጠሀል፣ ስንት እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ነገር ሰርተሀል??? አንተ ግብዝ የራስህን ጉድፍ ስትመለከት የወንድምህን የአይን ገለባ ለማውጣት ትሄዳለህ፣ አንተ ግን የሰውን ጉድፍ ብቻ አውርተህልና የራስህን ጉድፍ ለማወቅ ምንም ድካም አይፈልግም፣ ማስተዋሉን ይስጥህ፣

  ReplyDelete
 41. ኪኪኪኪኪ አሳቃችሁኝ፣ አሁን እናንተ ወንጌላዊ ሆናችሁ ሞታችሁ ሰው ደግሞ ጸረ ወንጌል ትላላችሁ??? ለመሆኑ ወንጌል ወንድሙን ስደብ፣ ወንድሙን ንቀፍ፣ ወንድሙን አሳድ የወንድምህን ኃጢያት አደባባይ አውጥተህ ተናገር የሚል ትምህርት ታስተምራለችን??? እናንተን የሚያሳድዷችሁን ስደቡ አሳዱ የሚል የተጻፈው ወንጌል ላይ ነው ወይስ ጸረ ወንጌል ላይ??? እራሳችሁ ጸረ ወንጌል ሆናችሁ ሰውን ትከሳላችሁ ሆረር የሆነ ብሎጓችሁን ብትመለከቱን ጸረ ወንጌል እንደሆነ እንኳን አታውቁም፣ እናንተ ወንጌል እያደሳችሁ ወንጌልን ከምታሰድቡ እባካችሁ በወንጌል ታደሱ፣ እናንተ ቁራን ነው እንዴ የምታነቡት????????? አሳዳጁን የሚያሳድድ መጽሐፍ የቁራን መጽሐፍ እንጂ የወንጌል መጽሐፍ አልነበረም፣ ስለዚህ ጸረ ወንጌል ጸረ ክርስቶስ ማለት እናንተ መሆናችሁ ነው ብሎጋችሁ በግልጽ የሚያሳየው፣

  ReplyDelete
 42. አሁን እናንተ የታቦቱ መሸጥ ነው ያንገበገባችሁ??? ኪኪኪኪ ታቦት እኮ መሰረቅ የተጀመረው የናንተ የኑፋቄ ትምህርት በቤተክርስቲያን መዝራት ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ነው፣ ካዲያ የናንተ የትምህርት ውጤት ነው፣ ምን ይገርማል???? በሌላ አነጋገር ደስታችሁን ነው እየገለጻችሁ ያለው??? ምንፍቅና በተግባርና ምንፍቅና በስብከት፣ ምንፍቅና በሀሳብ፣ ምንፍቅና በወሬ ሁሉም አንድ ናቸው፣

  ReplyDelete
 43. ምነው ስለማሪያም ሲነሳ የሚያማቹህ ? የዲያቢሎስ ልጆች

  ReplyDelete
 44. I need to buy tabot. Can you post the tabot dealer sale office Engeda phone number? We have used fake tabot. Mereke

  ReplyDelete
  Replies
  1. bilachihu bilachehu melake selam kesiss dejenen bezih menged aworachihubachew amlak yikir yibelachehu enanten yedem bizatachihun yekesekesew zemariw kidiste kidusan dingil mariamen sile awodese new min yarge, erso eraso <>bilalechina degimo erso lesim ateraro kibire yigibatena besew lije yemedan menged talake dirsha alat kirstosin be man awokachihutina........

   Delete
 45. የአባ ሰላማ ብሎግ እኮ የፕሮቴስታንት/የከሃድያን ብሎግ ነው፡፡ ነገር ግን መቀመጫውን ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ በስውር ቆብና ካባ ደብቆ ተኩላዎቹን ያሰማራ ነው፡፡ ድምጸ ተዋሕዶ የሌለው፤ ትምህርተ ተዋሕዶ የማገባው፤ ሙሰኞችና መናፍቃን እንዲሁም ዘረኞች የሚስማሙት የተሃድሶ ቡችላ ድምጽ ነው፡፡ እንዴት ስለ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ‹ሌባ› ተብሎ በቅዱስ ፓትርያርኩ መነቀፍን፤ ከሹመቱ መነሳቱን ይጽፋል፤….. ሆዳቸው አምላካቸው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ጠላታቸው፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እሺ ቢሉ ቢመለሱም እናታቸው፣ እምቢ ቢሉ እንደካዱ ቢቀሩ ግን አዋራጃቸው የሆነችባቸው እኩያን ናቸው፡፡
  ብሎጉን አባሰላማ ማለታቸውም ለሽፋን፤ ለቤ/ክ ተቆርቋሪ መምሰላቸውም የአዞ እንባ ነው፡፡ ግን ወዮላቸው ቀን የከዳ ዕለት፤ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ በክብር በተገለጠ ዕለት፤ ወዮላቸው የሰደቧቸው ቅዱሳን በብርሃን ሰዳቢዎቹ ግን በጨለማ ቆመው ሲተያዩ፤ ወዮላቸው ነገ ጓዳቸው ተገልጦ መና ሲቀሩ፤. . . . . . . . . እግዚአብሔር ግን ለእኛም መጽናትን ለእርሱም መመለስን ያድለን፡፡
  የአባ ሰላማ ብሎግ እኮ የፕሮቴስታንት/የከሃድያን ብሎግ ነው፡፡ ነገር ግን መቀመጫውን ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ በስውር ቆብና ካባ ደብቆ ተኩላዎቹን ያሰማራ ነው፡፡ ድምጸ ተዋሕዶ የሌለው፤ ትምህርተ ተዋሕዶ የማገባው፤ ሙሰኞችና መናፍቃን እንዲሁም ዘረኞች የሚስማሙት የተሃድሶ ቡችላ ድምጽ ነው፡፡ እንዴት ስለ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ‹ሌባ› ተብሎ በቅዱስ ፓትርያርኩ መነቀፍን፤ ከሹመቱ መነሳቱን ይጽፋል፤….. ሆዳቸው አምላካቸው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ጠላታቸው፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እሺ ቢሉ ቢመለሱም እናታቸው፣ እምቢ ቢሉ እንደካዱ ቢቀሩ ግን አዋራጃቸው የሆነችባቸው እኩያን ናቸው፡፡
  ብሎጉን አባሰላማ ማለታቸውም ለሽፋን፤ ለቤ/ክ ተቆርቋሪ መምሰላቸውም የአዞ እንባ ነው፡፡ ግን ወዮላቸው ቀን የከዳ ዕለት፤ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ በክብር በተገለጠ ዕለት፤ ወዮላቸው የሰደቧቸው ቅዱሳን በብርሃን ሰዳቢዎቹ ግን በጨለማ ቆመው ሲተያዩ፤ ወዮላቸው ነገ ጓዳቸው ተገልጦ መና ሲቀሩ፤. . . . . . . . . እግዚአብሔር ግን ለእኛም መጽናትን ለእርሱም መመለስን ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 46. አንደ ኤምኬ መነአፍቅ የለም።እረረኩሶች እናንተ ስታደርጉት ሀጢያቱ ፅድቅ ሀሰቱ እውነት ይሆናል። የኛ ፃድቃኖች።በዚህ ዘመን እናንተ ቤተ ክርስቲየሰናችንን እና አባቶችን እንደአስደፈራችሁ እንዳቃለላችሁ የወለዳችሁት ልጆቻችሁ ይስደቧችሁ የ ታቦት ሌቦች ።ይህነዜ በጋሻው ቢሆን የሰረቐው መከራውን ታበዙት ነበር ።ቤተ ክርስቲያንን እራስዋን ቢመቸው ይሸጣል።ይህኔ ስንት ቅርስ ከ ማቅ ጋር ተመሳጥሮ ሽጦአል በደንብ ይመርመር እሱ እና ዘመዴ ቲያንስ ዳኒ ክስረት እንዲሁም ሌሎች ከእንደዚህ አይነቶች በተገዛ ታቦት የሚጠቀሙ ።

  ReplyDelete
 47. አላማችሁ ሁለት መሆኑን አዉቄያለሁ !!!!!!!!!

  ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ማጥላላት
  የሚያጋልጣችሁ ምኅበረ ቅዱሳንን መተቸት
  የሚያጋልጣችሁ ምኅበረ ቅዱሳንን መተቸት

  ReplyDelete
 48. ምን አገባችሁ እናንተ ምቀኞች ቅናት አጥንት ያነቅዛል የቅናተኛው የዲያብሎስ ልጆች ቅናተኛ ጴንጤዎች ቅናተኛ ተሀድሶዎች፡ በቅዳሴ የምትቀኑ በምስጋና የምትቀኑ በዜማ የምትቀኑ ባቋቋም የምትቀኑ በጸሎት የሞትቀኑ በመዝሙር የምትቀኑ በሰዓታት የምትቀኑ በቅዱሳን የምትቀኑ በመላእክት የምትቀኑ በእመብርሀን የምትቀኑ በዉዳሴ ማርያም የምትቀኑ በተዓምረ ማርያም የምትቀኑ በሀይማኖተ አበው የምትቀኑ በገድላት የምትቀኑ በስንክሳር የምትቀኑ በቄስ የምትቀኑ በዲያቆን የምትቀኑ በሰንበት ተማሪ የምትቀኑ በታቦት የምትቀኑ በጾም የምትቀኑ በስግደት የምትቀኑ በመስቀል የምትቀኑ በሰኔ ጎልጎታ የምትቀኑ በፀበል የምትቀኑ በማማተብ የምትቀኑ በአስራት የምትቀኑ በፍትሀት የምትቀኑ በ40 በ80 የምትቀኑ በክርስቶና የምትቀኑ በአንገት ማህተም የምትቀኑ በነጠላ በጋቢ በልብሰ ተክህኖ የምትቀኑ በጥምቀት የምትቀኑ አረ ብዙ ብዙ ምን የማትቀኑበት አለ የምቀኛው የአባታችሁ የዲያብሎስ የመንፈስ ልጆች ምቀኞች... ከምትቀኑ ወደ እውነተኛዪቱ በክርስቶስ ደም ወደተዋጀችው ቅድስቲቱ ንፅህቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተመለሱ ተመለሱ ተመለሱ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንዳንዱ ሰው በቃ ዝም ብሎ ይደነቁራል። ምንድር ነው የምትል? በሼር ነው እንዴ የምትሰሩት ከታቦት ነጋዴው ጋር? ዝም ብለህ ከምትዘባርቅ ቢያንስ የሃይማኖት ጠባቂ ነኝ እያለ የሚያጭበረብረው ወንድምህ ጽላት መሸጡ ስህተት መሆኑን እመን አጻጻፍህ እኮ ስለተጋለጠና ዝርፊያው ስለቆመ ያናደደህ ነው የምትመስለው

   Delete
 49. ሸጦ ከሚበላ እግዛብሔር ይሰውረን እግዚያብሔር ኢትዩጵያን ይባርክ

  ReplyDelete
 50. I need to buy tabot. Can you post the tabot dealer sale office Engeda phone number? We have used fake tabot. Mereke

  ReplyDelete
 51. AYE MECHERESHAW ZEMEN?

  ENDIH ENDEKELD BEGNA YEDRES?


  GETA RASU,LE SIM ATERTARU KIBIR YEGBAWUNA,
  YESEW LIJ(KIRETOS)SIMETA 'EMNETIN YAGEGN"YEHON BILO YETENAGERW DERSO .....HAYMANOT ENDASHE FELA ADEL?

  ReplyDelete
 52. አንድ ጥያቄ የፈጠረብኝና ያልገባኝ ነገር አለ:: በድሮ ዘመን ካህኑ ዔሊና ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ባደረሱት በደል ምክንያት (1ሳሙ 3: 27-30) የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤሎች ላይ ነዶ የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጤማዉያን ከተመረከ በኋላ (1ሳሙ 4:10-17) የተማረከው የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጤማዉያን ላይ ታላቅ መቅሰፍትን በማስከተሉ ፍልስጤሞች የእግዚአብሔርን ታቦት ከላያችን መልሱ ባሉ ጊዜ (1ሳሙ 5: 3-11) ንጉሡ ዳዊት ታቦቱን ከአቢዳራ ቤት ሲያስመጣ በሬዎች ሲፈንኑ ዖዛ የሚባል ሰው ታቦቱ እንዳይወድቅ እጁን ሲዘረጋ እንደተቀሰፈ እናያለን:: ይህ የሆነበትም ምክንያት ታቦቱን እንዲነካ ያልተፈቀደለት ሰው ስለሆነ ነበር:: ታዲያ ዛሬ ታቦት: ሥርዓቱና ኃይሉ የሚሠራ ከሆነ ያልተፈቀደለት ሰው ሲነካው እንኳን ይቀጽፍ የነበረው ታቦት እንደማንኛውም እቃ እንዴት ሊሠረቅ ቻለ? ሥርቆት ደግሞ ኃጥያት ነው (ዘፀ 20: 15; ዘደግ 5: 19; ማቴ 19: 18). እንድዚህ ዓይነት ዜና ከዚህ በፊትም ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዉሸታም ማደሪያ የለዉም፡፡ በራሳችሁ ቤት እበዱ እንጂ ጠናማ ሰዉን አታሳብዱ፡ ብላችሁ ብላችሁ፤ ጮሀችሁ ጮሃችሁ፡ አላዋጣችሁ ሲላችሁ በአባ ሰላማ ስም ተቀየራችሁ እንዴ፤ እናንተን ብሎ ታሪክ አዋቂ፤ 100 ጊዜ ብትፈጠርም የዲ.ን ዳንኤል ክብረትን ዕዉቀት አታገኘዉም፡፡ ለሱ የተሰጠዉን 0.00005% ለማግኘት ከፈለክ ዓይንህን አብርህ/ገልጠህ ፀልይ፡፡ እዚያ 24ሠዓት የሚታመነዥገዉ ሆድህ ጎደለህ መሰለ፤ አባ ሠላማ ብለህ ተነሣህሳ፡፡ የበለዓም አህያ በለዓምን በለጠችዉ፡ የእግዚአብሔርን መልአክ ክብር መስክራለች፡፡የቢታኒያ ድንጋዮች ጌታችንን አማላጅ ሳይሉ አምላክ ፈጣሪ ብለዉ አመሰገኑ፡፡ አንተ ግን…………..አንተ ግን……….

   Delete
 53. enanet yenat tut nekashoch maninetachihun silminawik bekentu batidkimu melkam new. mekniyatum tewahidon yesiol dejoch selmayichiloat. MK letifat telekoachihu enkifat silhun kezih belay bitilum ayidenkenim. yilkun maninetachihu/tser betkristiayan mehonachihu yibelti eytawekebachihu new

  ReplyDelete
 54. wwoshetam tehadeso menem behon bete christiyan attadesem protestan hulu atkebatiru

  ReplyDelete
 55. ይህ የጠላት ወሬ ነው እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ ቅድስት የሆነች ድንግል ማርያምን ማመስገኑ ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ድሮስ ጥላቻችሁ ምን ሆነና ነው በተዘዋዋሪ ግን ግብራችሁን እና ማንነታችሁን እያጋለጣችሁ መሆኑን አላወቃችሁትም ለማንኛውም እግዚአብሔር ይቅር ባይ ስለሆነ ብትመለሱ መልካም ነው አለበለዚያ በሐጢያት ላይ ሐጢያት ባትጨምሩ ጥሩ ነው

  ReplyDelete
 56. yehenen yezendo melasachehune koreto bahere mechemer new ..............

  ReplyDelete