Wednesday, March 30, 2016

“ሊቃናተ ኢታመጕጽ ተአዘዝ ከመ ዘለአቡከ” “ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት . . . ለምነው።” (፩ጢሞ. ፭፥፩-፪)ከዘሩባቤል
ምሁራንንና አባቶችን የመስደብ አባዜ የተጠናወተው ዳንኤል ክብረት እጅግ ግብዝ እና በትዕቢት የተሞላ መሆኑን ሰሞኑን በፓትርያርኩ፣ በቅዱስ ሲኖዶስና በቤተ ክህነቱ በአጠቃላይም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በጻፈው ድፍረትና ጽርፈት የተሞላው ጽሑፉ ግልጽ አድርጓል፡፡ እርሱና አድናቂዎቹ ስድቡን ሕጋዊና የተፈቀደ ለማድረግ ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ግን እንዲህ ያለው ስሕተት እንዳይፈጸም “ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት . . . ለምነው።” ይላል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን" ፍሬ የሆነው ይህ ሰው ግን ይህን ቃል ተላልፎ በዚህ ርካሽና ቃለ ጽርፈትን በተመላ ጽሑፉ እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያኒቱ ርእስ አድርጎ ያስቀመጣቸውን ፓትርያርኩን ተሳድቧል፡፡ ፓትርያርኩን ብቻም አይደለም፤ እርሳቸው ርእስ ሆነው የሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑትን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጭምር ነው፤ ሊቃነ ጳጳሳቱን ብቻም አይደለም፤ እነርሱ በሲኖዶስ የሚመሯትን ቤተ ክርስቲያን በአጠቃላይ ነው የተሳደበው፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገው ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየነገደ ለማኅበሩ ሲል ነው፡፡  

ምናልባት የእኛ ስም በቀጥታ አልተነሣም ወይም እርሳቸውን እንጂ እኛን አልተሳደበም የሚል ጳጳስ ቢኖር ስሕተት ይፈጽማል፡፡ ቀድሞ እጅግ ይከበሩና እንደ ብርቅ ይታዩ የነበሩ ብፁዓን አበው ማኅበረ ቅዱሳን ከተነሣ ወዲህ በየጊዜው ሲሰደቡና ሲዋረዱ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያት ለማኅበሩ አጎብዳጅና ተገዢ የሆኑትን አንዳንድ ጳጳሳት “ብፁዕ ቅዱስ” እያለ ለእርሱ እኩይ ተግባር ተባባሪ ያልሆኑትን ደግሞ ማዋረዱን በከፍተኛ ሁኔታ ተያይዞታል፡፡ ይኸውና በግልጹም ሆነ በስውሩ አመራር ዘንድ የማይወደደውና በማኅበሩ አባላት ዘንድ ባለው ተሰሚነት ግን እንደ ዋና ሰው የሚታየው ዳንኤል ቅዱስ ፓትርያርኩን አንድ ተራ ሰው እንኳ ሊናገራቸው በማይደፍራቸው ተራ ቃላተ ጽርፈት በመሳደቡ ትልቅ ድፍረትና ቃለ ውግዘት እንዲተላለፍበት የሚያደርግ ጥፋት ነው የፈጸመው፡፡ የእርሱ ጥፋት ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹ ተከታዮቹ ጭምር ይህን አሳፋሪ ድርጊቱን ከማውገዝ ይልቅ በማድነቅ “ጀግናችን በርታ” እያሉ አስተያየት መስጠታቸው ማኅበረ ቅዱሳን ያፈራው ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጠንቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ዳንኤል ከአሁኑም ሆነ ቀደም ካለው የማኅበሩ ግልጽ አመራር ጋር እንደማይዋደድና ጠበኛ እንደ ሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ አሁን ያለው አመራር እርሱን እንደ ትልቅ ሥጋት ያየዋል፡፡ ከስውር አመራሩ ጋርማ ጠብ ውስጥ ከገባ ቆየ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ራሱን በልዩ ልዩ መንገድ በማስተዋወቅ ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ዳንኤል ክብረት እስኪመስል ድረስ ማኅበሩን ሸፍኗል የሚል ነው፡፡ ከማኅበሩ ሰዎች ገንኖ የወጣው እርሱ ስለሆነም ነው፡፡ እርሱም አመራሩን ባይወድም ለማኅበሩ ያለውን ፍቅር ግን እንዲህ ባለው ክፉ ቀን በተቆርቋሪነት መንፈስ መግለጹ አልቀረም፡፡ ማኅበሩን በተሳሳተ አቋሙና አካሄዱ ሲተች ይቆይና ማኅበሩ ላይ ክፉ ቀን ሲመጣ ግን ማኅበሩን የመከላከል ሥራ ይሠራል፡፡ ይህም በአንድ ወገን ለእርሱ ሳያውቅ አዋቂ ያሰኘውና ዝናን ያተረፈለት በማኅበሩ ውስጥ ጎልቶ መውጣቱ ስለሆነ ድንገት ማኅበሩ አንድ ነገር ቢሆን የእርሱም ዝና አብሮ ሊከስም እንደሚችል ስለሚያስብ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ እርሱ ለጻፈው ግብዝነትንና ቃላተ ጽርፈትን ለተመላው፣ በሐሰት መረጃ ላይ ለተመሠረተው ጽሑፉ ምላሽ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡ ለዛሬው ለጽሑፉ ከሰጠው ርእስ እጀምራለሁ፡፡

የዳንኤል ክብረት የጽሑፍ ርእስ ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” የሚል ነው፡፡ ይህ ርእስ ፓትርያርኩ ባለባቸው ኀላፊነትና አደራ ማኅበረ ቅዱሳንን አደብ ለማስገዛትና መሥመር ለማስያዝ፣ ቤተ ክርስቲያንንም ከእርሱ ቅኝ ግዛትና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (በልዩ ልዩ መንገድ ባስገበራቸው አንዳንድ ጳጳሳትና የቤተ ክህነት ሰዎች በኩል) ነጻ ለማውጣት የጀመሩትን ትክክለኛና ተገቢ እርምጃ ሌላ መልክ ለመስጠት የሚሞክር ነው፡፡ በሌላ በኩል በእርሱና በአመራሩ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት በውስጣዊ ሽኩቻ ለሚታመሰው ማኅበረ ቅዱሳን የሌለውን ማንነት ለማላበስ አስቦ የሰጠው ነው፡፡ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን በመንካታቸው ለኢትዮጵያ ደኅንነት ስጋት ሆነዋል ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ሐሳብ ተገልብጦ ሲታይ ማኅበረ ቅዱሳንን መንካት ለኢትዮጵያ ደኅንነት ያሰጋል የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው፡፡
በእኔ እምነት ማኅበሩ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ማንነት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ስሙ አለቅጥ የገነነ፣ ነገር ግን ውስጣዊ ክፍፍል ያለበት፣ እርሱና አመራሩ እንኳን ዐይንና ናጫ የሆኑበት፣ እንደሚወራለት ያልሆነ፣ ይልቁንም ተሐድሶ ተሐድሶ ከማለቱ የተነሣ በተደጋጋሚ ስለእርሱ ስለተወራ የሌለውን ማንነት የተላበሰ የማፍያ ቡድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስጋት ቢሆን ዐውደ ርእዩ ሲታገድ ስጋትነቱን ባሳየ ነበር፡፡ አባላቱና ጀሌዎቹ የፌስቡክ አንበሶች ከመሆን ያለፈ ያወሩትንና የሚያስወሩትን አላደረጉትም፤ ሊያደርጉትም አይችሉም፡፡ ወይም ደግሞ ከስውሩ አመራር መመሪያ እስኪተላለፍለት እየተጠበቀ ነው እንዳይባል ከላይ እንደጠቀስሁት በየፌስቡኩ የነበረው ቅስቀሳ፣ ጫጫታና ሁካታ የዳንኤልም  የ “አትነሣም ወይ!” ነጋሪት ጉሰማ ቀላል አልነበረም፡፡ ያ ሁሉ ግን በአየር ላይ በተገነባ የሌለ ሰብእና ከማስፈራራት ያለፈና ለአገር ደኅንነት ሥጋት የሚሆን ነገር መፍጠር የሚችል አቅም የሌለው ስብስብ እንደሆነ ያሳያል፡፡
ሁሉን ዐውቃለሁ ባዩ ዳንኤል ያልተገነዘበው አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ነው በዱሮ በሬ ለማረስ የሚሞክረው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገሪቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር የምትችል ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ማንም አይክድም፡፡ ሆኖም እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን መንግሥት እስከ መገልበጥ የሚሄድ ነባራዊ ሁኔታ ግን የለም፡፡ ስለዚህ መንግሥትን ቤተ ክህነቱ በሚያመጣው ዳፋ መከራ ለመቀበልስ ዝግጁ ነው? ይህ አካሄድስ ለሀገሪቱ ደኅንነት የሚበጅ ነው? . . . ከቤተ መቅደስ የተነሣ ችግር መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው አይታወቅምና፡፡ በማለት ለማስፈራራት መሞከሩ አስገራሚ ነው፡፡
ለመሆኑ እርሱ “ቤተ ክህነት” እያለ የሚጠራው ቤተ ክህነቱን ነው? ወይስ ከዚህ ቀደም ‘ሌላው ቤተ ክህነት ሆኗል’ ሲል የተቸውን ማኅበሩን ነው? አሁን የሚታየው እውነታ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ሌላ፣ ቤተ ክህነቱ ሌላ መሆናቸውን ነው የሚያሳየው፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጽሑፍህ ላይ “የኑፋቄ ማኅደር” ስትል የጠቀስኸው ቤተ ክህነት በአንተ አነጋገር በኑፋቄ ትምህርት የተሞላ ሆኖ፣ ከእኔ በላይ ኦርቶዶክስ ላሳር ከሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አንተም ራስህ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ የማኅበረ ቅዱሳንን ጦስ የቤተ ክህነቱ አድርገህ ማቅረብህ ትልቅ መሠረታዊ ስሕተትና በአንበሳው ለማስፈራራት እንደመሞከር ነው የሚቆጠረው፡፡ በስውር የጀመራችሁትን የመንግሥት ኩዴታ ብትፈልጉ በግልጽ ባትፈልጉ ደግሞ በወደዳችሁት መንገድ መቀጠል ትችላላችሁ፡፡ ይህን ጉዳያችሁን ከመንግሥት ጋር መጨረስ ትችላላችሁ፡፡ ቤተ ክህነቱ ግን የራሱ ብዙ ሥራ አለበት፡፡    
እዚህ ላይ መጠየቅ የምፈልገው አንድ ጥያቄ ግን አለ፣ ማኅበረ ቅዱሳን እስከ ዛሬ ያፈራው አባልና ጀሌ ሃይማኖተኛ ነው ወይስ ፖለቲከኛ? ወይስ ሁለቱን እያጣቀሰ የሚጓዝ? እነዳንኤል ለማስፈራራት ከሚሞክሩበት ሁኔታ አንጻር ካየነው ፖለቲከኛ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደ ታደሰ ወርቁ ያሉት ሃይማኖትንና ፖለቲካን በጣምራ የሚያራምዱ የማኅበሩ “ፖቲከኛ ሃይማኖተኞች” እንደገለጡት ማኅበሩ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው ቅምጥ ኀይል መኖሩን የጥምቀት ተመላሾችን በስም በመጥቀስ ግልጽ አድርጓል፡፡ መቼም እንዲህ የሚያደርግ ፖለቲከኛ ወይም ሌላ ዐላማ ያለው እንጂ ሃይማኖተኛ ይልቁንም በክርስትና ስም የሚጠራ ሃይማኖተኛ ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ የክርስትና ትምህርት ክርስቲያን በስደትና በመከራ ውስጥ የሚያልፉበት መንገድ ቢሆንም ያንን ሁኔታ በኃይልና በዐመፅ መቀልበስን የሚያስተምር ሳይሆን በመሸነፍ ማሸነፍን ነው የሚያስተምረው፡፡        
ለምእመናን የድኅነት ሥጋት የሆነው ማነው? ዳንኤል በጽሑፉ ርእስ አሁንም ተጠያቂ የሚያደርገው ፓትርያርኩን ነው፡፡ ድኅነት የሚገኘው በወንጌል በተገለጠው እውነት መሠረት በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የአድኅኖት ሥራ በማመን ነው፡፡ በዚያ ላይ ተመሥርቶ በሕያው እምነት ያገኙትን መዳን በበጎ ሥራ እየገለጡና እግዚአብሔርን እየመሰሉ በመኖር ድኅነትን መፈጸም ይገባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምእመናንን ወደዚህ የወንጌል እውነት ለማድረስ እየተጋ ያለው ታዲያ ማነው? በየተገኙበት መድረክ ሁሉ ቤተክርስቲያን ላይ የተጋረጠውን የምእመናን ፍልሰት ለማቆም ወንጌል መሰበክ አለበት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መጠናከር አለበት በማለት የምእመናንን ድኅነት ለማረጋገጥ በቃልም በተግባርም እየተጉ ያሉት ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ማኅበሩ ግን ከዚህ በተቃራኒ እየተንቀሳቀሰ ለምእመናን የድኅነት ስጋት ነው የሆነው፡፡ ከወንጌል ይልቅ ተረትን፣ ከወንጌል ይልቅ ገድልን፣ ምእመናን ለብፁዓን አባቶች ከመታዘዝ ይልቅ ለማኅበረ ቅዱሳን ሐሳብ በማይገዙ ጳጳሳት ላይ እንዲያምፁ የሚያደርግ፣ ከሚያንጽ ይልቅ የሚያፈርስ ነገር በመናገር የተካነውና ምእመናንን ከድኅነት መንገድ ያወጣው ማነው? ቢባል እርሱና ማኅበሩ እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
ዳንኤል እንኳን በዚህ ጽሑፉ ቅዱስነታቸውን አለስማቸውና አለግብራቸው ለምእመናንን ከድኅነት መንገድ የሚያወጡ ብሎ ሲዘልፋቸው እርሱ ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሽሮ አሁንም ከተረት እንደልወጣ በራሱ መስክሯል፡፡ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡ ሲል በልቡ የሞላውንና ከወንጌል ቃል ጋር የሚስማማውን ሳይሆን የሚጣላውን የገድል ክፍል ነው የጠቀሰው፡፡ እውን እንዲህ ይሆናል? ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማነጋገርም ሆነ ማስታረቅ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ተግባር ነውን? ይህ በፍጹም የሚታሰብም ሆነ የሚቻል አይደለም፡፡ በወንጌል የታዘዝነው ዲያብሎስን እንድንቃወመውና ከእኛ እንድናርቀው ነው እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንድናስታርቀው ወይም ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው ከእግዚአብሔር ቃል፣ ፈቃድና ሐሳብ ውጪ ነው፡፡ ስለሆነም እንዲህ አድርጋለች የተባለችው ክርስቶስ ሠምራ ወይም በስሟ ይህን የደረሰው ደብተራ ተሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብም ርቀዋል፡፡ እንደ ግብር አባታችሁ በተረታተረት ጠፍንጋችሁ አስራችሁ ውሳጣዊ ዐይኑ እንዳይበራ ያደረጋችሁት የዋህ ተከታያችሁ ይህን እንደ ትልቅ መገለጥ ወይም እንደ ትልቅ ሐሳብ ቢያየውም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ግን የሚቃረን ትምህርት በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አትቀበለውም፡፡
እስኪ ከቅዱሳን ነቢያትም ሆነ ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ይህን የሞከረ ማነው? እንዲህ እንዲሆንስ ያስተማረ ማነው? ሁሉም በአንድ አፍ ለዲያብሎስ እድል እንዳንሰጠው፣ ዲያብሎስን እንድንቃወመው በቃል አስተማሩን (ኤፌ. 4፥27፤ ያዕ. 4፥7)፣ በተግባርም ገሥጸው እንድናባርረው አሳዩን (የሐዋ. 16፥18)፡፡ እርሱ ከቶም ስለማይታረቅና እርሱን የማስታረቅ ሐሳብም ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ከእግዚአብሔር ጋር እናስታርቅ የሚል ሐሳብ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እነርሱም እንዲህ ከቶም አላሰቡም፤ እንዲህም አይታሰብም፡፡ ታዲያ ሊሆን ቀርቶ የማይታሰበውን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ የሚለው ሐሳብ ተረት እንጂ ወንጌል ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ እንዲህ ባለው የአሮጊቶች ተረት የተሞላው የማኅበረ ቅዱሳን መድረክ ሰውን ከክርስቶስ የማዳን መንገድ የሚያወጣ በመሆኑ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት ነው፡፡
ዳንኤል ግን ክርስቶስ ሠምራ ወይም በስሟ ሰይጣንን ስለማስታረቅ የጻፈው ደብተራ በዚህ ረገድ አብነት ስለሆነው ከዚህ ቀደም ብዙ ተቃውሞ የገጠመውና “ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ” በሚል በተከታታይ ሐመር መጽሔት ላይ ያወጣቸው የነበሩና በኋላም በመጽሐፍ መልክ ያሳተማቸው መጣጥፎቹ እርሱ በምናቡ ሰይጣንን በማነጋገር ሥራ ተጠምዶ እንደ ነበር የሚያስታውስ ነው፡፡ ሰይጣንን ለማናገር የክርስቶስ ሠምራ ገድል ተጽዕኖ ሳያደርግበት አይቀርም፡፡ በዚህ ምናባዊ ሥራው ላይ ዋናው ተቃውሞ ሰው እንዴት ከሰይጣን ጋር ቃለ ምልልስ ያደርጋል? የሚል ነበር፡፡ እንዲህ ያለ ዝንባሌ ያለው እርሱ የተቀደሰውን የፓትርያርኩን ሥራ ከሰይጣን ሥራ ጋር ቢያነጻጽር “እመት ስመኝ ለማያወቅሽ ታጠኝ” ብለናል፡፡  
ዳንኤል ቅዱስ ፓትርያርኩን የዘለፈበት አንዱ ነጥብ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ከማቅ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የጀመሩትን ሥርዐት የማስያዝ ሥራ ከሰይጣን ሥራ ጋር በማነጻጸር ማቅረቡ ነው፡፡ እጅግ ያሳዝናል፤ እጅግም ያሳፍራል፡፡ ፓትርያርክ “ታላቅ አባት” ማለት ነው ብሎ ትርጉሙን የተናገረው እርሱ ታላቁን የአባት ማክበር ተስኖትና ትልቅነታቸውን ከተሰጣቸው ማዕረግና ካላቸው ሥልጣን አኳያ ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም ካለማስከበራቸው አንጻር ነው ያቀረበው፡፡ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ይጎዳል ያሉትን የማኅበሩን አደገኛ አካሄድ መሥመር ለማስያዝ መንቀሳቀሳቸው በእርሱ አስተሳሰብ የሰይጣን ሥራ ተደርጎ ተቆጠረ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ መሆን እንዳልነበረበት ራሱ ከዚህ ቀደም በማኅበሩ ላይ በጻፈው ትችት ገልጾ ነበር፡፡ እንዲያውም “ሌላው ቤተ ክህነት” ወደመሆን መሸጋገሩ ትክክለኛ አለመሆኑንም አስረድቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመሸበት አዳሪው ዳንኤል አሁን ላይ ያን የቀድሞውን ሐሳቡን ገልብጦና የሰይጣን ያለውን ሥራ የመልአክ በማድረግ ፓትርያርኩን አራት ቦታ ላይ ከሰይጣን ጋር ለማነጻጸር ዐይኑን በጨው ታጥቦ ቀረበ፡፡ እርሳቸው ማኅበረ ቅዱሳንን መሥመር ለማስያዝ የሠሩትን ሁሉ የሰይጣን ሥራ አድርጎ ማቅረብ እጅግ አሳፋሪና የእርሱን ባዶነት የሚያሳይ ተግባር ነው፡፡

ፓትርያርኩ እያፈረሱ ያሉት የማቅን እኩይ ሥራ ነው፡፡ “የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” ተብሎ ተጽፏል (1ዮሐ. 3፥9)፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እያደረገ ያለውንና ለቤተ ክርስቲያን የማይበጀውን ክፉ ሥራውን ቢያፈርሱ ምስጋና እንጂ ዘለፋ ሊሰነዘርባቸው አይገባም ነበር፡፡ ማኅበሩን ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ለማኅበሩ መጠቀሚያ የሚያደርግ አካሄድ ይብቃ! ሁሉም ነገር እዚህ ላይ መቆም አለበት ባሉ፣ አእምሮ የጎደለው ይህ ሰው ግን በድፍረት ፓትርያርኩንና የተቀደሰ ሥራቸውን ከግብር አባቱ ከዲያብሎስና ከክፉ ሥራው ጋር ለማመሳሰል ሞከረ፡፡ ዛሬ ረስቶት እንደሁ እንጂ በተለይ የማኅበሩ አመራር እርሱን ክፉኛ አስቆጥቶት በነበረ ጊዜ የሐራ አባት “ደጀ ሰላም” ብሎግ ላይ ሰቅሎ በሰዓታት ውስጥ እንዲወርድ በተደረገው ጽሑፉ ውስጥ አመራሩ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን የተመሠረተ መሆኑን ዘንግቶታል፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያን ለማኅበሩ ወደሚል አመለካከትም ዞሯል፡፡ ይህ ፍርሃት ማኅበሩ የሚጠበቅበትን ከመሥራት ይልቅ ራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ወጭ እንዲያወጣ አድርጎታል ብሎ ነበር፡፡ በተለይ “ቤተ ክርስቲያን ለማኅበሩ” የሚለው አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ወደዚህ ትልቅ ኃላፊነት ሲመጡ የዚህን ማኅበር አካሄድ አደገኛነት ተረድተው ለማስተካከል ሲነሡ፣ እርሱ የእኔን አቋም ደግፈውልኛል ብሎ ለእውነት በመቆም ፈንታ ምነው የሰይጣን ሥራ አለው? ታዲያ ይህ አስመሳይነትና እውነትን የመሸጥ አካሄድ እርሱን “ወልደ አቡሃ ለሐሰት” አያሰኘውም ትላላችሁ?
ዳንኤል ፓትርያርኩን እንደ አባት የማኅበሩን አባላት እንደ ልጆች አቅርቧል፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩ የአባትነት ሚናቸውን እንዳልተወጡ ብቻ አድርጎ ነው የጻፈው፡፡ ጉዳዩን እርሱ በጻፈው መንገድ እንኳን ብናየው አባት ለልጆቹ የሚያደርገው ብቻ ሳይሆን ልጆች ለአባታቸው ማድረግ የሚገባቸውን ተወጥተዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ የሚነሳበትን ሐሣብ ነው ያቀረበው፡፡ ሩቅ ሳንሄድ ፓትርያርኩ ማኅበሩ ስሕተት መፈጸሙን ማስረጃ ጠቅሰው ለስሕተቱ ይቅርታ ይጠይቅ ብለው ለጻፉት ደብዳቤ፣ አላጠፋሁም ብሎ ከሚከራከር ይልቅ ይቅርታ ቢጠይቅ ምን ይሆን ነበር? ልጅ ከሆነ አባቱን ይቅርታ ለመጠየቅ አይቸገርም ነበር፡፡ ነገሩ እንዲያ ስላልሆነ ግን ይቅርታ የሚጠይቅ ልብ አልነበረውም፡፡ ይህ ለፓትርያርኩ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ልጅ የራስን ኀላፊነት ሳይወጡ አባትን መውቀስ ሚዛናዊ አይደለም፡፡ እስካሁን እንደታየው ማኅበረ ቅዱሳን ተመክሮ ተዘክሮ ሊመለስ የማይችልና በጀመረው የጥፋት መንገድ ወደፊት ከመቀጠል በቀር የሚስተካከል ማንነት የለውም፡፡ ዳንኤል እንኳ በዚሁ ጽሑፉ ውስጥ አመራሩ እርሱ የነገረውን የማይሰማና ከመለወጥ ይልቅ አንድ ቦታ ላይ “የተቸከለ” መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ ራሱን ፍጹማዊ አድርጎ ለሚቆጥር ማኅበር በር መክፈት በጥፋቱ እንዲበረታ ከማድረግ ያለፈ አንዳች ፋይዳ ስለሌለው ፓትርያርኩ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በር ተከፍቶ የመንግሥት ተወካዮች ባሉበት በተደረገው ውይይት መቼ ለውጥ መጣ? አሁንም በዚህ መንገድ የሚለወጥ ነገር ስለሌለ ለማኅበረ ቅዱሳን የሚከፈት በር አዋጪ አይደለም፡፡
ይቀጥላል

34 comments:

 1. Jelewochu enkuan yanten tsihuf likebelu, Geta beakal bimeta ayikebelutem.

  ReplyDelete
 2. መልካም ምላስ ቁጣን ታበርዳለች የዳንኤል ጩኸት ግን ማስተዋልና መታዘዝ ታፈርሳለች᎓᎓ ዳንኤል ሆይ! የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚመረጥ እናምናለን᎓᎓ ሲኖዶስም ዲድስቅልያም ይናገራሉ᎓᎓ ለምንድነው ፓትርያርኩ የምትዝልፍ? ስለማይከሱህ? ስለማያስፈራሩ? የጸሎት አባት ስለሆኑ? በቤተክርስቲያን ተጠግተው የሚዘርፉትን አገልጋዮችም ማህበራትም በግልፅ በመግለጫ ስለተቃወሙ? ዳንኤል ስለምን ትዘልፋቸዋለህ? ለእድሜህ ለመሰረትከው ቤተሰብ ጥሩ ይሆናል? ደግሞስ እንዲህ ያለ አባባል የፖለቲከኞች እንጂ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሃይማኖት ሰው ነኝ የሚል ቋንቋ ነው? ዳንኤል የኢትዮጵያ መንግስት እንዳንተ ባሉ ባለ አስር ምላስ ብእር ይደናገራል ወይም ይደነግጣል ብለህ የምታስብ ከሆነ የዚህ መንግስት መሰረት ለማወቅ ብትሞክር ይሻልሃል᎓᎓ እንደ ኦርቶዶክሳዊ ወግና ስርአት ሃሳብህ ብትገልፅ መልካም ነበር ነገር ግን ፓትርያርክን ያክል አንተ እያልክ ስድ የሆኑ ቃላት እየተጠቀምክ ለማስፈራራትና ለማሳመፅ ያደረግከው ሙከራ መልካም አልመሰለኝም᎓᎓ የመናፍቅነት መጀመሪያ ቀኖናን መጣስ መጀመር ወይም እንዲጣስ በፅሁፍም በቃልም መስበክ ነው᎓᎓ ዳንኤል ፓትርያርክ መዝለፍ ለፓትርያርክ አለመታዘዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ስርአት አይደለም᎓᎓ እስከማውቀው ያስወግዛል በምድራዊ ስርአትም ያስጠይቃል᎓᎓

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከተሾሙ ከሦስት ዓመታት በላይ ሆናቸው፡፡ ከማፍረስና ከማገድ በቀር ይህን ሠርተዋል ብለህ ቆጥረህ ንገነኝ፤ ከዚያ በኋላ ስለሳቸው አባትነትና ክብር ብናወራ አይሻልም ... ወሬ ከመደርደር!

   Delete
 3. በአብነት እና በመንፈሳዊ ኮሌጅ ባታልፍም ከረጅም ዓመት ንባብ እና ከእድሜ የተማርክ ትመስለኝ ነበር፡፡ለካ በጭብጨባና በደጋፊ ብዛት ታውረህ በዚሁ መስመር ቁልቁል የምትራመድ ሰው ነህ፡፡ምን ከምን ተነጻጽሮ እንደሚጣፍ እንኳ ሳታውቅ ስሜታዊነትን እንደቀናኢነት ቆጥረው በስሜጥ ሽምጥ የሚጋልቡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን ጭብጨባ ለማግኘትና ለመጽሐፍህ ገበያ አብዛኛው ተደራሲ የሚገኝበትን ስሌት በመስራት የጻፍከው ነውረኛ መጣጥፍ ለራስህ አለማሳፈሩ ያስገርማል፡፡ ቅሬታን ለማቅረብ ስንት የለዘበ መንግድ እያለ እንዲህ አይነት ልቅ ርእስ በአንዲት የቤተክርስቲያን ርእሰ መንበር ላይ መጠቀም እድሜና ንባብ ያልለወጠህና በጭብጨባ ያበድክ ተራ አማተር መሆንህን ከማስመከስከር ውጭ ጠቀሜታ የለውም፡፡ የማዝነው አንተን እንደአርአያ ተከትለው በየፌስቡኩ፣ብሎጉ እና የግል ጋዜጣው አባትን ማራከስ እንደትልቅ ሞያ ለተያያዙት ውሪዎች ነው፡፡እናንተማ አንድ ጊዜ ተጣማችሁ ነውራችሁን የአባቶች ድክመትና የቤተክህነት መዝረክረክ የሚደብቅላችሁ መስሎአችሁ ጎዳናውን ተያይዛችሁ ወደ እርግና ተጠግታችኋል፡፡
  በእርግጠኝነት የምነግርህ ማንኛውም በአባቶች እግር ስር ያደገ ደቀመዝሙር ይህን መደዴ ጽሑፍህን አያደንቅልህም፡፡እንኳንስ ከታች ወደላይ ከላይ ወደታች እንኳ አባቶች ልጆቻቸውን ሲገስጹ ወግ አለው፡፡እንዲህ አይነት ገና ከርእሱ ጀምሮ በስድብና በማንጓጠጥ የተሞላ ጽሑፍ ከትበህ የተሳዳቢዎች ቁንጮ ለመሰኘትና በወቅታዊ አለመግባባት ስሜታዊነት ውስጥ የገባውን የማኅበር አባል ትኩረት ለመሳብ ያደረከው ርካሽ ጽሑፍ ርካሽ ተወዳጅነት ለማግኘት ከማሰብ የመነጨ ነው ከማለት ውጭ ሌላ ትረጉም የለውም፡፡ራስህን ለጭብጨባ አስገዝተህ ለቤተክርስቲያን የነቀፋ አብነት ከመሆን በጊዜ ጥሩ የግል ጋዜጣ ወይም መጽሔት አቋቁመህ ሚናህን ለይ፡፡በዚህ መጣጥፍ መጥላት ብቻ ሳይሆን ንቄሀለሁ፡፡ሁለተኛ ወደብሎግህ አልመጣም፤ላይህም አልፈልግም፡፡እስካሁን አንተን እንደጥሩ መምህር መከተሌም ይቆጨኛል፡፡ራሱን ለርካሽ ጭብጨባና ዝና ሚያስገዛ ሰው ስለማልወድ አንተ ላይ ልደብቀው የማልችል ጥላቻ አድሮብኛል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ራስክን እና እርሱ የፃፈውን መጽሐፍ አንብብ፡፡ አርሱ ከገለጸው መካከል እውነት ያልሆነ ካለ ተቸው፣ በቅዱሳን አማላጅነት የምታምን ቤተክርስቲንን የሚመሩ አባት አላናግርም ብቻ ሳይሆን ምልጃም አልሰማም ነው ያሉት፡፡ ኦርቶዶክስ ከሆንክ ይህንን ተች፣ አለበለዚያ ምን እደሆነክ በራስህ ላይ ትመሰክራለህ አንጂ እውነት ላይ ለመረማመድ አትሞክር፡፡

   Delete
  2. ዳንኤል ክስረትን አሁን ካወቀውም ጥሩ ነው። ለዘመናትና አሁንም ህዝቡንና ካህናቱን ፣ ካህናቱን ከካህናቱ የሚያጋጭ ለሰይጣን ማህበሩ አገልጋይ ነው እኮ። ላንተ እንደገባህ ሌሎችም ቢገባቸው ጥሩ ነው። ተባረክ ።

   Delete
 4. ደደብ። አንብበህ እንኳን የማትረዳ የጴንጤ ተላላኪ።

  ReplyDelete
 5. ቆይ ሰውዬው ኦርቶዶክስ መስለውኝ እንዴት በእናንተ የደገፉ? ለማንኛውም አቅማችሁን እወቁ ራሳችሁን በማታለል ጌዜአችሁን አታባክኑ ቢቻላችሁ ፁሙ ፀልዩ ንስሐ ግቡ ባይቻላችሁ መሰናክል አትሁኑ ፍርድ አለ በሰማይ የሐሰት አነደበቶች ነገ ይታሰራሉ።

  ReplyDelete
 6. "በጋሻውን ማሀበረ ምናነምንቴዎች ተሀድሶ ነው ብለው ያሉት ተሀድሶ ሆኖ ሳይሆን ማህበረ ----- ስለነካ ነው "ብሎ ዳንኤል ፅርፈት የፃፈውን ፅሁፍ አንብቤአለሁ።ዳኒ ግን የአንተን ጉድ እግዚአብሄር ቢገልፀው ማንም ፊትህ አይቆምም።ደብረ በጥብጥ እኮ ነህ።በሄድክበት ሁሉ ሁከትና ሽብር አረ በኪዳነ ምህረት ይበቃህ የበታተንከውን ምእመን አንድ ለማድረግ ልቦናህን እግዚአብሄር ይለውጥልህ ትውልዱን በሙሉ እኮ ተሳዳቢ አደረግከው አባቶቹን ቀና ብለው እንዲሳደቡ አደረግህ።ባንተ ዘመን እንደሆነው ቤተ ክርስቲያን ተከፋፍላ ተሸብራ አታውቅም።የክርስቶስም ስም ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ እንደዚህ ተንቆ ተየጠላው በአንተ ዘመን ነው።እግዚአብሄር እምሮህን ይፈውስልህ።ልብህን ይፈውስልህ ከትእቢትህ ያስታግስህ ።ይህ የተበለሻሸ ትውልድ እግዚአብሄር ይድረስለት።

  ReplyDelete
 7. ግሩም ትንታኔ ነው፡፡ ለገድል ወንጌሉ ዳንኤል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚገባው አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም ዳንኤል ቅዱስ ቃሉ “ሊቃናተ ኢታመጕጽ ተአዘዝ ከመ ዘለአቡከ” “ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት . . . ለምነው።” (፩ጢሞ. ፭፥፩-፪ ይልሃልና በፓትርያርኩ ላይ ስለተናገርከው ክፉ ቃል ሁሉ ንስሐ ግባ ይቅርታም ጠይቅ፡፡

  ReplyDelete
 8. ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማነጋገርም ሆነ ማስታረቅ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ተግባር ነውን? ይህ በፍጹም የሚታሰብም ሆነ የሚቻል አይደለም፡፡ በወንጌል የታዘዝነው ዲያብሎስን እንድንቃወመውና ከእኛ እንድናርቀው ነው እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንድናስታርቀው ወይም ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው ከእግዚአብሔር ቃል፣ ፈቃድና ሐሳብ ውጪ ነው፡፡ ስለሆነም እንዲህ አድርጋለች የተባለችው ክርስቶስ ሠምራ ወይም በስሟ ይህን የደረሰው ደብተራ ተሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብም ርቀዋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ant danielen tasdibowal eyalik. andaned agodaje papas(በልዩ ልዩ ምክንያት ለማኅበሩ አጎብዳጅና ተገዢ የሆኑትን አንዳንድ ጳጳሳት “ብፁዕ ቅዱስ”) maletun min ametaw. miriqat meseleh(). esun kemetechetih besfit erasihin atira.

   Delete
 9. ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር አምላክ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ፡፡ አንተ ተረፈ አርዮስ እና ሉተር ምንም አላችሁ ምን እግዚአብሔር ይመስገን ነቅተናል፡፡ ቅጥፈታችሁን ይዛችሁ ባዶ አዳራሻችሁ፡፡

  ReplyDelete
 10. ANTE AHUN ANAWKIHEM HIWETIH MINDINEW TEW ENDENANTE TESADABI MEHON KASFELEGE MEREJA YALEW MAKREB YICHALAL GIN ENTEWEW EWNETEGN KIRISTYAN KEHONK BEGILU LEMIN ATMEKIREWM WEYM YEBETEKIRISTYAN SHIMAGLEWOCH YIZEH LEMIN ADEBABAY AWETAHEW WEYS ESU ADEBABAY AWTOTAL ENEM MAWTAT ALEBIGN NEW WEYS ANTE DEGIMO LEYU BALEADERA LEMEHON NEW? DANIEL YEHAYMANOT CHIGIR YELEBETIM ZARE YETECHEGERNEW YEORTHODOXIN GUDAYE LEORTHODOXOCH METEW YALCHALU YANTENA YEMESELOCHIH GUDAY NEW GIEZ SILETEKESK YEGNANETIH MASREJA AYHONIM BEAKAL ENDAGEGNEH ESHALEHU YEMITAZEWTIRIBAT BET GIN ATIMECHEGNIM ENE EDWILELHALEHU

  ReplyDelete
 11. GUDAM LEMIN YETSAFIKUTIN ATAWETAWIM BEAKAL ENGENAGN EN ENAWIRA

  ReplyDelete
 12. ayiehew kbie tebash yiluhal endant yalewun new diakon danielen yawaredih mesiloh kidusan papasatin endih bileh sedebihachew በልዩ ልዩ ምክንያት ለማኅበሩ አጎብዳጅና ተገዢ የሆኑትን አንዳንድ ጳጳሳት “ብፁዕ ቅዱስ”

  ReplyDelete
 13. Criticizing without Justification and evidences do not have meaning.
  Deacon Daniel pointed out that the malpractice of the persons who lead the Church. If you justify the points he raised with evidences you are welcome unless shouting simply doesn't bring anything. As a son of GOD, Do you really believe that the church leaders free from politics? Does GOD permit the church leaders should be from one ethnic Group( Tigray) only.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear bro at March 31, 2016 at 5:49 AM. do not waste your valuable time giving response to these idiots. They are working for Satanic kingdom. Just keep your great works. all in 'aba selama' blog are donkeys. do not forget that for this idiot work that they are getting wadge from their employers

   Delete
 14. እጅግ ያሳዝናል፣ ልብም ይካል፡፡ ሁሉም የስድብ ምላሱ የረዘመ፣ አዋቂ ነኝ ባይ፣ እዉተነኛ ነኝ ባይ፣ ለሌላዉን ማብጠለጠል፣ ሌላዉ ተሳስቷል ማለት፣...የራስን ድብቅ ዓላማ ለማስፈጸም መሯሯጥ እንጂ ...ከስሀተት የሚያርም የጽድቅ መንግድና ስራ አይሰለኝም፡፡ በወንጌል እንተጻፈ በጎችን ለሚያስተዉ ወዮለት!

  ReplyDelete
 15. Yemigrem Newoeko bemechersha betkrestiyan endehe aynet yesedeb afe yetsetewo sewo aferach malet newo erebakachehu egezio enebele Iselam meteto angete esekemikoret newo woye yemetetebekut
  Nicodimos

  ReplyDelete
 16. Daniel did not insult our patriach, but he insulted to all the orthodox followers, so the church should excommunicate him.

  ReplyDelete
 17. እኔ የሚገመኝ ቅዱሳንን የሚሳደበው "አባ ሰላማ" ብሎግ ቅዱስ ፓትርያርኩ ተሰደቡ ማለቱ ነው። ሁሌ ሀሰት ብቻ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች ሲጣፍ ተሻምቶ ያነበበ እና ያስነበበ ሁላ፤ የሃዉልቱ ስር ቁማርተኞችንም ያናበበ፣. እንዲሁም የስድብ አፍን ያስቸበቸበ… ሁላ ዛሬ ምን ነክቶት ነው…. ‹‹እንዲህ … እንዲያ › › ሚለው?
   ዳንዔል እይታውን አኑሯል… እኛም … መተቸት ካለብን ሃሳቡን እንጂ… ሰውየው ምን አጠፋ?
   ደግሞስ ‹አትስደብን› እየሰበኩ መሳደብስ ምን ይሉታል?
   ለሁሉም ግን ዕይታው ከሞላ ገደል መልካም ነው፡፡ ‹አዳልቷል… ለማኅበሩ ሳይድ ይዟል › ለምትሉ… ፅሁፉን ተንደገና አንብቡት፤፤፤፤፤፤፤፤፤
   ከዚህ ይልቅ ‹ለምን እንዲህ ሊል ቻለ?› ብሎ ማሰብና ለማሰላሰል መሞከሩ መልካም ይመስለኛል…..

   Delete
 18. Tarik yfaredewal. Egziabherm, ye eju ayassataw. Yhin yemesele defarna aryos, be betekrstyanchin taytom tesemtom ayawkim. Mengiste hone, betekrstyanitu behalafinet meteyek alebachew. Kesu yebase, Zeregnana tesadabi betekrstyanachin aytam semtam atawkim. Mewegezna, be hig meteyek alebet.

  ReplyDelete
 19. ከዚህ የጡመራ ገጽ ባጠቃላይና ከዚህ ጽሑፍ በተለይ ግርም ከሚሉኝ አንዱን ብቻ ላንሳ። ይኸውም የአማርኛ ቋንቋ የሰዋስው አጠቃቀም ችግር ነው። ይህም የሚያሳየው ሁሉንም የሚጽፈው አንድ ሰው (እሱም የሚያቀርብበትን ቋንቋ [አማርኛ] እንኳ አጣርቶ የማያውቅ) ሲሆን ለማሳሳት የተለያየ ስሞችን እንደሚጠቀም ነው። ለዚህ ማሳያ ከላይ ከቀረበው ጽሑፍ ውስጥ ".......በስሟ ይህን የደረሰው ደብተራ ተሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብም ርቀዋል፡፡..." የሚለውን ብቻ ማየት በቂ ነው። ስለዚህ ጽሑፋችሁ ቢያንስ ስለ ቋንቋው እንኳን ተነባቢ እንዲሆን "በአማርኛ" ብትጽፉ መልካም ነው እላለሁ።

  ReplyDelete
 20. ቆይ ሰውዬው ኦርቶዶክስ መስለውኝ እንዴት በእናንተ የደገፉ? ለማንኛውም አቅማችሁን እወቁ ራሳችሁን በማታለል ጌዜአችሁን አታባክኑ ቢቻላችሁ ፁሙ ፀልዩ ንስሐ ግቡ ባይቻላችሁ መሰናክል አትሁኑ ፍርድ አለ በሰማይ የሐሰት አነደበቶች ነገ ይታሰራሉ።

  ReplyDelete
 21. በተቻለ መጠን "አንተ" እና "እሱ" እያላችሁ ከምትጽፉ፣ የምትጽፉበትን ቋንቋ የሰዋስው ሕግ መጠንቀቅ እንኳን ባትችሉ ለንባብ የማይሻክር ጽሑፍ ብታቀርቡ ምናለበት? ጽሑፋችሁ የ"አማርኛ" አማርኛ ሳይሆን የ"..." አማርኛ ነው የሚመስለው።

  ReplyDelete
 22. ይህች የማወናበጃ ቋንቋህን ለራስህ አድርገው ግእዝ የተጠቀምከው የቤተክርስቲያን ሰው ለመምሰል ነው??? እባክህ ሰይጣን ያደረበት ሰውም እኮ ቅዱስ ጴጥሮስ የመሰከረውን ምስክርነት ሰይጣንም መስክሮለታል ማር 1፣23 የጌታ መልሱ ዝም በል ነው፣ እኔ ዝም በል ይሆናል፣ እናንተ አባቶችን እየመረቃችኋቸው ነው??? እስኪ ገጽህን ተመልከተው???? ኪኪኪኪኪ፣ ፎቶ እየለጠፋችሁ የምትሰድቧቸው አባቶች እኮ የሀይማኖት ስህተት ኖሮባቸው ሳይሆን የስጋ ድካም ስለታየባቸው ነው ይህ ሁሉ በስድብ ድንጋይ የምታወርዱባቸው፣የእኛ ጌታ ግን አይደለም የስጋ ድካም የነበረበትን ቅዱስ ጴጥሮስን ቀርቶ የሀይማኖት ችግር የነበረበትን ይሁዳን እንኳን እያወቀው አልተቃወመውም በራሱ ሰዓት ነው የወደቀው፣ እንደው እናንተ እንደጌታ ሁሉን የማወቅ ስልጣን ቢኖራችሁ እኮ ወደፊት የሚሰራውን ኃጢያት እየኮነናችሁ ባስቸገራችሁን ነበር፣ ጌታ ስሙ ይመስገን ለሰይጣንም ቢሆን ይህንን ጸጋ አልሰጠውም፣ በዚህ ነው ትንሽ ያረፍነው፣ ዳኒ የእናንተን የኑፋቄ ትምህርት ስለሚቃወም እንጂ በእውነት ዳኒ የተናገረው ስህተት ኖሮት አይደለም፣ አሁን እንጊዜ የናንተን አስተምሮ የተቀበለ ቢሆን ኖሮ ውደሳው አያስቀምጠንም ነበር፣ ኪኪኪኪ የተሀድሶ አምልኮተ ጣኦት የሚደግፉትን የሚያወድስ የሚያሳድዱትን የሚያሳድድ፣ ኪኪኪኪ የት ነው የተማራችሁት????? ይህንንማ አህዛብም ያደርጉታል አላማረባችሁም፣ በዚህ ዘመን እንደዚህ አይነት አካሄድ ‘Expire Date’ አልፎበታል፣ በሌላ መንገድ ብትመጡ ይሻላላ፣ ከዳኒ ጋር በምንም እኮ ነው የማትገናኙት፣ በእውቀት ብትሉ፣ ለሚናገረው ኃላፊነት በመውሰድ ብትሉ፣ በምንም አትገናኙም፣ እንደናንተ ተደብቆ ማንነቱን ሰውሮ አይደለም የተናገረው፣ ክርስቲያን ነገር አይፈራም፣ እናንተ እኮ በዶላርና በፓወንድ የለወጣችሁት ቤተክርስቲያን ምንም ቢትሆን ለናንተ ደስታ ነው፣ የፓትራይርኩ የቤተክርስቲያን መፍረስ ዝም ማለት ለናንተ ጥሩ የማፍረሻ መንገድ ስለሆነ እንጂ መቼም ፓትሪያርኩ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ምንም ለቤተክርስቲያን የሚፈይድ ስራ እንዳልሰሩ ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ፣ በበለጠ ለወንጌል መሰናክል ሲሆኑ ነው የተመለከትነው፣ አንድ ቀን በስህተት እንኳን አንድ ጥቅስ ጠቅሰው ሲያስተምሩ እንኳን አልተመለከትንም፣ የተጻፈላቸውን ነው ሲያነቡ የተመለከትነው፣ እስኪ በስህተት ይህንን ሰሩ ብለህ እንኳን መጥቀስ አልቻልክም፣ ይህንን ለምን ገለጠብን ብላችሁ ነው እንደዚህ ለወሬ ተፈታችሁ የምትቀባጥሩት፣ ወንጌላዊ ብትሆኑ ይህንን የጻፋችሁበትን ጉልበት ለጌታ ወንጌል ብታደርጉት ጌታ እንዴት ደስ ባለው???????????? የናንተ ክፉ ወሬ እናንተን እንድንጠላና እንድንጸየፋችሁ ነው እያደረጋችሁ ያላችሁት፣ እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያስተማረችን ወንጌልና እያስመለከችን ያለው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ እንደናንተ አይነቱን አስተምሮና ወሬ አበክሮ የሚጠላውን አምላክ የሁሉንም ስህተት የሚሸከም ሁልጊዜ መልካም ስራችንን በአለት ላይ ኃጢያታችንን በአሸዋ ላይ የሚመዘግብ፣ መንፈሱ የሚያሳድድ ቃል የሚያሸክም ሳይሆን አሳዳጁን መንፈስ አስጥሎ ፍቅርንና የቃሉን ሙላት የሚያሸክም እንደሆ ነው እኛ ቤተክርስቲያናችን ያስተማረችን፣ ስለዚህ የናንተ ትምህርት እናንተን እንድንጠላና እንድንጸየፍ ነው ያደረገን፣ኪኪኪኪ በዚህም በ21ኛው ዘመን እንደዚህ አይነት ሰው መኖሩ ኪኪኪ ያስቃል፣ ጌታ ማስተዋሉን ይስጣችሁ፣

  ReplyDelete
 23. ስታስቁ እናንተ እኮ በጣም ነው የምታስቁት እንኳንም ስማችሁንና ማንነታችሁን ደበቃችሁ ምን ክብር አላችሁና ማንነታችሁን ትገልጻላችሁ??? ትንሽ እንኳን ሰባዊነት አይሰማችሁም??? ከስድስት ወር በፊት ወንድማችን ዳንኤል እያላችሁ እንዳላቆላመጣችሁት፣ ዛሬ ስሙን መግለጥ አቅቷችሁ እንደአውሮፓውያን በአባቱ ስም ትጠሩት ጀመር ኪኪኪ ስሙን ተጸይፋችሁት ነው፣ ለነገሩ እውነታችሁን ነው ስሙ እኮ ዳንኤል ትርጉሙ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነው ማለት አይደል፣ ዳኝነቱ ስለተዛባባችሁ ነው ስሙን መጥራት የተጸየፋችሁት??? ጥሩ ነው ፍርሀተ እግዚአብሔር መኖሩ፣ ያን ጊዜ ማህበሩን የሰደበ ስለመሰላችሁ ነበር ስታከብሩት የነበረው??? ዛሬ ለሀሳባችሁ ማሳኪያ የሆኑትን ፓትሪያርክ ስራቻውን ስለገለጠ እናንተ አባት አክባሪ ሆናችሁ ሞታችሁ ነው ይህንን ሁሉ የጸፈፋችት፣ kakakakakakak እኛ ፓትርያርኩን አናቃቸውም አይደል በናንተ አስተሳሰብ፣ ኧረ ግርም ነው የምትሉኝ ደግሞ እኮ አታናድዱም እኮ፣ ፍርፍር አድርጋችሁ ነው የምታስቁት በእውነት፣ ጌታ ማስተዋሉን ይስጣችሁ፣

  ReplyDelete
 24. አይ ማህበረ ሰይታን በመሳደብ ነው ተቆርቆሪነታችሁን የምታሳዩት:-) አባ ሰላማዎች ጌታ ይርዳቹ ያአባቴ ብሩካን!

  ReplyDelete
 25. ዶፍ ወረደበት! ሲያሳዝን! ግን ምን ያደርጋል ሰውዬው አፍ እንጂ ልብ የለውም።

  ReplyDelete
 26. አባ ሳማዎች ደረጃ የሚባል ነገር አለ፡፡ ደረጃቺሁን አውቃችሁ ዚቄዎች ጋር ተነጋገሩ፡፡ ማለቴ በሃይማኖት እውቀት ገና የሆኑትን መረጣችሁ አጭበርብሩ፡፡ ከዲ/ን ዳኒኤል ምናችሁም አይደርስም፡፡ በእውቀት ፤ በእምነት ፤ በስራ ፤ ……………. ሁላችሁም ዝቄ ናችሁ፡፡አባ ሳማዎች ደረጃ የሚባል ነገር አለ፡፡ ደረጃቺሁን አውቃችሁ ዚቄዎች ጋር ተነጋገሩ፡፡ ማለቴ በሃይማኖት እውቀት ገና የሆኑትን መረጣችሁ አጭበርብሩ፡፡ ከዲ/ን ዳኒኤል ምናችሁም አይደርስም፡፡ በእውቀት ፤ በእምነት ፤ በስራ ፤ ……………. ሁላችሁም ዝቄ ናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 27. አባ ሰላማ እኮ ተሃዲሶ ነው፤ ተሃዲሶ ደግሞ ሰይጣን ተሸካሚ ነው። ሰይጣን ከጥንት ጀምሮ ማሪያምን አይወድም፤ እሳም አትወ፤ አናንተም እሳን መጥላታችሁ ትክክል ናችሁ፥ ምክንያቱም የሱ ናችሁና

  ReplyDelete