Sunday, March 6, 2016

ማኅበረ ቅዱሳን በእጅ አዙር ያስጠራውና “ድንገተኛ” ተብሎ የተገለጸው የሲኖዶስ ስብሰባ የማቅን አጀንዳ ሳያስተናግድ ተበተነ፡፡

Read in PDF


ራሱ በጫረው እሳት ችግር ውስጥ የገባውና ከግንቦት ሲኖዶስ በፊት ሊወሰድበት የሚችል እርምጃን በመፍራት ደጋፊና የጥቅም ተጋሪዎቹን ጳጳሳት ይዞ ባልተለመደ ሁኔታ “ድንገተኛ” የተባለ ስብሰባ እንዲጠራለት ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን ያሰበው ሳይሳካ ድንገተኛ የተባለው ስብሰባ ተበትኗል፡፡ በማቅ መንደር የስብሰባው ሴራ ተጎንጉኖና ተሸርቦ የማቅ ደጋፊ በሆኑና፣ በጥቅምና ባለባቸው የሕይወት ድካም በተያዙ ጳጳሳት በኩል ተጠናክሮ በድንገት ለፓትርያርኩ የቀረበው የእንነጋገር ጉዳይ ድንገቴ ከመሆኑ የተነሣ ቅዱስ ፓትርያርኩ የዐቢይ ጾም መግቢያን አስመልከተው የተለመደውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ተገኝተው ሳለ ከመግለጫው ፍጻሜ በኋላ በአባ ማቴዎስ በኩል የቀረበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ማቅ ይህን ጊዜ ለስብሰባ የመረጠው የብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዜና እረፍትን አስመልክቶ ጳጳሳት ለቀብራቸው ስለተሰበሰቡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ጳጳሳቱ ወደየሀገረ ስብከታቸው ከመበተናቸውና ፓትርያርኩ ቀጣይ እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ፓትርያርኩ ላይ አንዳች ጫና በማሳደር ማኅበረ ቅዱሳንን መሥመር ለማስያዝ የጀመሩትን ሕጋዊ ጉዞ ለማደናቀፍና ክፍፍል ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡ የማኅበሩ ልሳን የሆነው ሐራ ከዚህ ቀደም እንደዘገበው ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በያዙት አቋም የተነሣ ፓትርያርኩን እስከ ግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ ከሥልጣን እስከ ማውረድ የደረሰ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ፍንጭ ሰጥታለች፡፡ የአሁኑ በምስጢር ተይዞ በድንገት እንዲጠራ የተደረገው ስብሰባ የዚህ ሴራ አካል እንደ ሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመግለጫው ላይ ከዚህ ቀደም አስከ 8 ያህል ጳጳሳት የሚገኙ ሲሆን በዚህ መግለጫ ላይ በርከት ያሉ ጳጳሳት ተገኝተዋል፡፡ በበዓለ ሲመቱ ላይ ያልነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ሁሉ በሴራው ውስጥ በንቃት ተሳታፊ መሆናቸውን በሚያሳብቅ መልኩ ለማቅ ሲባል በተጠራው ድንገተኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ቀኖና ቤተክርስቲያን እንደሚያዘው በዓለ ሲመት የፓትርያርኩ በዓለ ሲመት ይባል እንጂ የቤተክርስቲያን በዓል በመሆኑ ሁሉም ጳጳሳት የመገኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ በዘንድሮው በዓለ ሲመት ላይ ግን የአቡነ ናትናኤልን ዜና ዕረፍት ምክንያት በማድረግ አንዳንዶቹ ጳጳሳት አልተገኙም፡፡ ቅዱስነታቸውም በአቡነ ናትናኤል ሽኝት ላይ ለመገኘት ወደ አሰላ ደርሰው ለበዓለ ሲመቱ የተመለሱ መሆኑ ታውቋል፡፡
ጋዜጣዊ መግለጫው ከተሰጠ በኋላ አባ ሉቃስ ሌላ ጉዳይ አለን ብለው ፓትርያርኩን የጠየቁ ሲሆን በመቀጠል ዘረኛው አባ ማቴዎስ ድንገተኛ ስብሰባ እንዲጠራ ያደረጉትን አጀንዳዎች ስልታዊ በሆነ መንገድ አቅርበዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ስለሰላምና ስለተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፣ ስለድርቁ በመጀመሪያ ያቀረቡ ሲሆን እነዚህ ለሽፋን የቀረቡ አጀንዳዎች ነበሩ በመጨረሻ ላይ ግን ዋናውና ድንገተኛ ስብሰባ እንዲጠራ ምክንያት የሆነው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የተያያዘው አጀንዳ ሊነሳ ችሏል፡፡ እነዚህ ጳጳሳት እነዚህ ጉዳዮች ያሳሰቧቸው ቢሆን ኖሮ ቀደም ብለው ስብሰባ እንዲጠራ ማድረግ ይገባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እስካሁን ዝም ብለው ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን ለፈጸመው ጥፋት ይቀርታ እንዲጠይቅ መመሪያ መጻፋቸውን ተከትሎ ይህን የሰነበተና በሃይማኖቶች ጉባኤ ላይ ቀርቦ አቋም የተወሰደበትን አጀንዳ እንደ አዲስ ማቅረባቸው ለቤተክርስቲያንና ለሕዝቡ አስበው ሳይሆን ለሽፋንነት ያቀረቡት መሆኑን አሳብቆባቸዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በሁለቱ አጀንዳዎች ዙሪያ መነጋገር የሚቻል መሆኑን ገልጸው ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን፣ ከልዩ ጽ/ቤት እየወጡ ስላሉ ደብዳቤዎች በሚል መልኩ በቀረበውና በውስጡ ለማቅ የተላለፈውን መመሪያ ለመቃወም የተያዘውን አጀንዳ ግን “እርሱን ለእኔ ተዉት” በማለት ድንገተኛው ስብሰባ የተጠራበት ዋናው አጀንዳ ለውይይት ሳይቀርብ ስብሰባው ተዘግቷል፡፡
ፓትርያርኩ ከያዙት የጸና አቋም ለማናወጥ ሴራውን ሲሸርቡ ከነበሩት መካከል አባ ቄርሎስ፣ አባ ቀውስ ጦስ የተለመደውን ቤተክርስቲያን ያለ ማቅ ዋጋ የላትም የሚለውን ዲስኩር አሰምተዋል፡፡ እንዲህ ለማለት ሞራሉን ከየት አመጡት የሚለው ቢያነጋግርም እነዚህ አባቶች በቅዱስነታቸው በአለ ሲመት ላይ አልተገኙም፡፡ በአሉ የቤተ ክርስቲያን ጭምር ነበር፣ በዚህ በዓል ላይ ሳይገኙ ማቅ ይበልጥብናል በሚል በማቅ የአድማ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማህበረ ቅዱሳን እንደቆሙ የሚያሳይ ነው፡፡
አባ ቀውስ ጦስን ዘረኛነትና አድሎኣዊነት የሚትባቸው በመሆኑ አባት ብሎ ለመቀበል በጣም ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም ተሯሩጠው አሜሪካ ለምነው የአቡነ ጴጥሮስን ቤተክርስቲያን ያሠሩ ሲሆን፣ የወንዛቸው ልጅ ባለመሆናቸው ብቻ በተመሳሳይ መንገድ በፋሺስት ኢጣሊያ የተገደሉትን  የጐሬውን የአቡነ ሚካኤልን ስም እንኳን ማንሳት አይፈልጉም፡፡ በቅርቡ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወደቦታው ተመልሶ እንዲቆም በተደረገበት ሥነሥርዓት ላይ ቅዱስነታቸው አቡነ ሚካኤልም መታወስ ያለባቸው መሆኑን አንስተው ተናግረዋል፡፡ አባ ቀውስ ጦስ ታዲያ በምን ሞራል ፓትርያርኩን ይናገራሉ? ፓትርያርኩ የሁሉ አባት ሲሆኑ አባ ቀውስጦስ ግን የአንድ ወንዝ ልጆች አባት ብቻ መሆናቸውን ነው እያሳዩ ያሉት፡፡ ከኢትዮጵያ በላይ ሸዋን፣ ከኦርቶዶክስ በላይ ማቅን ሃይማኖትና ሃገር አድርገው የኖሩ ስለሆኑ ከእርሳቸው ከዚህ የተሻለ ምንም አይጠበቅም፡፡
ቅዱስነታቸው በመቀጠል አጀንዳ አቅራቢ የነበሩትን አባ ማቴዎስን በእጅጉ የገሰጹ ሲሆን “ተከባብረን እንስራ፣ በማለቂያው ሰዓት አንጣላ ሊያሳስበን የሚገባው የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው” ሲሉ ማቅን ደግፈው የነበሩ ጳጳሳት ሁሉ ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚባለው እኛ የማኅበረ ቅዱሳን አባል አይደለንም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በእነ አባ ማቴዎስ አጀንዳ አቅራቢነት የተጀመረው ድንገተኛ ስብሰባ በዚሁ መንገድ ግቡን ሳይመታ ተቋጭቶአል፡፡ ጉዳዩን የማቅ ብሎግ ሐራም የአቡነ ናትናኤልን ግብአተ መሬታቸውን በተመለከተ እንዴት እንደሆነ ምንም ሳትዘግብ በቀጥታ ይህን ሰበር ዜና ብላ ፅፋ የነበረ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ምንም ማለት ሳትችል ቀርታለች፡፡ ይህም የሚያሳየው ማኅበረ ቅዱሳን በእጅ አዙር ያስጠራው ድንገተኛ ስብሰባ የተጠበቀው ውጤት ሳይገኝበት ለሽፋንነት በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ብቻ ተወይቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጽኑ አቋም መበተኑ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት የያዙትን አቋም የያዘውን ቃለ ጉባኤ ከእነ አቋም መግለጫው ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጀምሮ ለ 9ኙ ርዕሳነ መስተዳደር ግልባጭ ያደረጉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በደስታ ተቀብለውታል፡፡ ይህ የቤተክርስቲያን ህልውና ጉዳይ ስለሆነ ወደ ኋላ አልልም እገፋበታለሁ በማለት የተናገሩ ሲሆን በበዓለ ሲመቱ ላይ ታመናል ብለው ያልተገኙ ጳጳሳት እንኳን ለአድማ ተሽሎአቸው መጥተው የነበረ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ አይመለከታችሁም በማለት ስብሰባውን መበተናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከአገረ ስብከት የአቋም መግለጫውን ለማቅረብ ለመጡ ተወካዮችም እናንተም በርቱ እኔም የቤተክርስቲያንን ህልውና ለማስጠበቅ ስል ወደፊት እንጂ ወደኋላ አልልም ብለዋል፡፡

14 comments:

 1. እባክህ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር ስጥ፡፡ ዓላማህንም አስተካክል፡፡ አዛኝ ቅቤ አንጓች አትሁን፡፡ በተለይ በከፋሺት ኢጣሊያ ጋር በተገናኘ ያነሳኸው በእጅጉ ትዝብት ውስጥ የሚከትህ ነው፣ የአባቶቻችን ገዳይ የሆነቸውን የቫቲካንን መንበር ሄደው ዱሮ ወዳጅ ነበርን ያሉት ቅዱስነታቸውን ዛሬ በሥራዎ በእነ አቡነ ሚካኤል ሰማዕትነት ላይ ጥቁር ቀለም የቀቡ መሆኑን እንዲረዱ ምከራቸው፡፡ ወንጌሉ እኮ ዛሬ የክርቶስን አምላክነት ባለመቀበል ሐሰተኛ ወሬ የሚነዙትን "… በሥራችሁ ክርቶስን ዳግም ሰቀላችሁት ነው…" ነው የሚለው፣ ቫቲካን በኢትዮጵያ ላይ የሠራችውን ሥራ እንደሌለ መመስከር ማለት ከ16 መቶ ክፍል ዘመን እስከ 20ኛው መቶ ክፍል ዘመን የነበረውን የአባቶችን የተጋድሎ ዘመን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በመካድ የእነርሱን ሰማዕትነት የሚያሳንስ ሥራ ከመሥራት የበለጠ ኢትዮጵያዊያን የዋረደ ሥራ የሠራ አባት በኢትዮጵያ ታሪክ ያለ አይመስለኝም፡፡ መሄዳቸው ካል ቀረ የሠሩትን ግፎች አስተውሶ ዛሬ ለዚያ ንስሐ ገብተው የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን የሚክሱበትን ሁኔታ ተወያይተው ቢመለሱ ኖሮ ቤተክርስቲያንን ባኮሯት ነበር፡፡ እርሳቸው ተነጋርው የኢትዮጵያ ብርድ ካስት ኮርፖሬሽን ይህንን ሳይነገረን የቀረ ከሆነ እርሻቸውን ከሕዝብ ጋር የቃቃረው እርሱ በመሆኑ ይቅርታ ሊጠይቃቸው ይገባል፡፡ ለማስተካከያም ያደረጉትን ውይይት በሌላ ፕሮግራም ሊነግረን ይገባል የምል እምነት አለኝ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በጽሑፉ የቀረበው ከሰማዕቱ አቡነ ሚካኤል ጋር በተያያዘ ተሐፊው ያነሳው ትዝብት ውስጥ የሚከት ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. ማቅ የቅዱስነታቸዉን ስም በሰፊዉ እያጠፋ ነዉ።
  ቅዱስ አባታችን ይበርቱልን ቤተ ክርስቲያንን ታደጝት
  በተረፈ የማቅ የግፍ ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ያለ ጉዳይ ነዉ
  ይልቁንስ ማቅ ክርስትና ካለዉ ይቅርታ ጠይቆ በንስሓ ቢመለስ መልካም ነዉ።
  ግን ማቅ ንስሓ ይገባል ወደልቡ ተመልሶ ይቅርታ ይጠይቃል ብላችሁ ታምናላችሁ???
  አይመስለኝም ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. kemin yitadegwat ketehadiso, ke endate yalu zerafiwoch woyis...

   Delete
 3. ማቆች ክርስትና እልህ እንዳልሆነ ተረድታችሁ እባካችሁ
  እስካሁን የበደላችሄትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ጠይቁ።

  ReplyDelete
 4. ልብ ይስጣችሁ ነው እንጂ ምን ይባላል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመበረዝ ሌት ተቀን ትኳትናላችሁ፥ ምድረ ተሓድሶ መናፍቃን …. ቤተ ክርስቲያን የገሐነም ደጆች አይችሏትም እንደተባለው እናንተ ስለቀባጠራችሁ ምንም አታመጡም።

  ReplyDelete
 5. ሰበር ዜና – መፍቀሬ ኢትዮጵያ ወገባሬ ሠናይ: የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ aba selamaweche enanete sele abatochachen yemenagere ahkemome deferetom yelachewem ye enanete ahlama abatochen ke ahbatoche magachete be zere mekefafele ye Abatachon ye Dabilosen sera masefafate new ....le meweno lemin yewen sele abatachen zena erfete yalenegerachewen ???? ewenetegna ye beate kiresetan lijoche selalewenacho eko new

  ReplyDelete
 6. ግን እኮ እውነት! ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከሀገራቸው፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣ ከወንድሞቻቸው ሊቃነ ጳጳሳት ተለያይተው መቅረታቸው ነው ማለት ነው? እባካችሁ አንዱን የሲኖዶስ ጉባኤ አሜሪካን አድርጉላቸው። መቼም ኢትዮጵያ እንደናፈቃቸው ነው የሚሞቱት!

  ReplyDelete
 7. እንዴት ሰው በቁሙ ይቀደዳል? ምናለ አንድ እውነት ብትናገሩ?
  ነገሩ ከግብር አባታችሁ የተማራችሁትም አይደል (አቡሀ ለሀሰት) ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 8. በመንበሯ የተቀመጠውን ፓትርያርክ መዝለፍ ቤተ ክርስቲያኗን ማዋረድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲህ ዓይነት ጋጠ ወጥ ባሕል የላቸውም፡፡ ስለዚህ ብትታረሙ ይሻላችኋል፡፡

  ReplyDelete
 9. ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጀምሮ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን /ሮምና ቫቲካን/ ያልጐበኘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የለም፡፡ ስለዚህ ምኑ ነው ብርቁ ድንቁ፣ አዲስ ነገር?

  ReplyDelete
 10. የውሽት ሪከርድ ሰብራችኋል የዲያብሎስ ባሪያዎች(ገብረ ሳጥናኤል)

  ReplyDelete
 11. aye harateka hula, tekatelachehu aydel? hiduna ye kidus sinodosen wusane hedachehu eyuna ahun letefu.

  ReplyDelete
 12. << የሲኖዶስ ስብሰባ የማቅን አጀንዳ ሳያስተናግድ ተበተነ፡፡ >> MK do not have special agenda than the agenda addressed by the holy synod. The holy synod has undertake an urgent meeting not because of MK but because of the country and the church cases. One of the church case is illegal journey of the Patriarch. Therefore, MK is pleased by the firm stand of our fathers in the holy synod. TEHADESO will fail down!!!!
  Tasfa ze-tewahedo

  ReplyDelete