Monday, March 7, 2016

የማቅ የመልስ ደብዳቤ ፓትርያርኩን ሽቅብ የሚመለከት ወይስ ቍልቍል?          ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት! ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ሾሟል (ኤፌ.4፥11) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ከእግዚአብሔር በተሾሙ አባቶችና መሪዎች ትወከላለች፡፡ በተለይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን የመወከል ሥልጣን ከእግዚአብሔርም ከሕገ ቤተ ክርስቲያንም እንዳላቸው ግልጽ ነው፡፡

          በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፓትርያርኩ የቋሚውም ሆነ የምልዐተ ጉባኤው ሲኖዶስ ሰብሳቢና መሪ በመሆናቸው ትልቁ ሥልጣንና ሚና ያለው በፓትርያርኩ እጅ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፓትርያርኩ ውጪ በሌላ መሪ የሚመራና የሚሰበሰብ ቢሆን የፓትርያርኩ ሥልጣን ውሱን ይሆን ነበር፡፡

በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ማኅበር በአደረጃጀት፣ በአሠራርና በአካሄዱ ላይ ባለበት ብልሽት ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ሥር ባሉ ሌሎች ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ ይህንንም እያጠናከረው በመሄዱ በማኅበሩ ጥቃት ከተከፈተባቸው መካከል አንዳንዶቹ ቅሬታቸውን ለቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ የበላይ አካል ለሆኑት ለቅዱስ ሲኖዶስና ለቤተ ክርስቲያን መሪና ሰብሳቢ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ማቅረባቸውን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኒቱ በፓትርያርኩ ፊርማ የተበደሉ የትምህርት ተቋማት ላቀረቡት አቤቱታ ምላሽ መሰጠታቸው ይታወሳል፡፡


          ይህንንም ተከትሎ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር እንደ አንድ ድጋፍ ሰጪ አካል እንዲሠራ ፓትርያርኩ በሚመሩት ሲኖዶስ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እንደሆነ በምናውቀው ማኅበር የፓትርያርኩን፣ የሲኖዶሱንና በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ልዕልና የሚያዋርድ የተቃውሞ ደብዳቤ በእኛ እይታ ሽቅብ ለፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፉና ይህንንም ለዓለም ሁሉ ማሰራጨቱን አይተናል፡፡

          በዚህም ምክንያት ማኅበሩ ከፊት ይልቅ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያዋርድ ደብዳቤ በመጻፉና በሌሎቹም ወቅታዊ እየፈጠራቸው ባሉት ችግሮች በአምስት፣ ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅና ይህንንም ይቅርታውን በማሰራጫ አውታሮቹ ሁሉ እንዲገልጽ መመሪያ ለመስጠት በስሙ ለተጻፈለት ደብዳቤ የሰጠውን ምላሽ ስንመለከት ማኅበሩ ፓትርያርኩን የሚመለከተው ቍልቍል እንጂ ሽቅብ እንዳልሆነ ከጻፋቸው ደብዳቤዎች በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡

          ፓትርያርኩን ቍልቍል ያያል ማለት ደግሞ በፓትርያርኩ የሚመራውን ላእላይ የቤተ ክርስቲያን አመራርና ውሳኔ ሰጪ የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስን ጨምሮ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን ቍልቍል እንደሚመለከት አመልካች ነው፡፡

          የሲኖዶስን የስብሰባ አጀንዳና የውሳኔ አቅጣጫ ወደሚፈልገው ለመምራት ከማኅበሩ ጋር ልዩ ግንኙነት ባላቸው ሊቃነ ጳጳሳት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉና ብዙ የሲኖዶስ አጀንዳዎችና ውሳኔዎች የማኅበሩን ፍላጎት የተከተሉ መሆናቸው ሌላው መሠረታዊ ማሳያ ነው፡፡

          ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በፊት ማቅ በስውር አመራሩ አማካይነት እንዲያዝለት የሚፈልጋቸውን አጀንዳዎች በመቅረጽና በአጀንዳነት እንዲያዝ የሚያቀርቡና የሚያስፈጽሙ ጳጳሳትን በመመልመል፣ የአጀንዳውን አስፈላጊነት እንዲያምኑበትና እንዲያቀርቡት በስውር በመሥራት ውሳኔውም ማቅ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንዲያመራ በማድረግ ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለማኅበሩ አገልጋይ በሆኑ ጳጳሳት እየተጠቀመ ብዙ ጉዳዮች እርሱ እንደሚፈልገው እንዲወሰኑና እንዲሄዱ እየሠራ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የሚወቀስበት የመተዳደሪያ ደንቡም ችግር በዚሁ መንገድ ተጠቅሞ በሲኖዶሱ ያጸደቀው በመሆኑ ነው፡፡  

          የማኅበሩ ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት አጀንዳውን ማስያዝ ብቻ ሳይሆን ውሳኔው ምን መሆን እንዳለበት ከማኅበሩ መመሪያ ተቀብለው ስለሚገቡ ያንን ለማስፈጸም ሲታገሉና ሲውተረተሩ ሲረዳዱ ይታያል፡፡ አንዳንዴም እንደሚፈልጉት ማስወሰን ሳይችሉ ሲቀሩ ተጨማሪ ውይይትና ማብራሪያ ለማድረግ አጀንዳው ተንጠልጥሎ እንዲቆይ በማድረግ ወጥተው ከማኅበሩ ጋር ይመክራሉ፡፡ በይደር የተያዙት አጀንዳዎች የማያስኬዳቸው ከሆነ ቢያንስ ማኅበሩን በማይጎዳ መንገድ እንዲወሰን ይጥራሉ፡፡ የሲኖዶሱን ስብሰባ አጠቃላይ ውይይት በዘመናዊ መቅረፀ ድምጽ እየቀረፁ ለማኅበሩ በየእለቱ የሚያቀርቡ አባቶችም አሉ፡፡

          ማኅበሩ በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ ቅዱስ ሲኖዶስን በዚህ መልክ በስውር የመምራትና የሚፈልገውን ለማስወሰን እድል ስላገኘ፣ ሲኖዶሱን ምንም እንኳ መጠቀሚያው አድርጎ የሚቆጥር ቢሆንም “በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የቤተ ክርስቲያን የመጨረሻ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው፣ እርሱ ከፓትርያርኩ ሥልጣን በላይ ባለሥልጣን ነው የሲኖዶስ ውሳኔ ይከበር” እያለ በመጮኽ ላይ ነው፡፡

          የማኅበሩ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑ ጳጳሳት፣ ከማኅበሩ ጋር ያላቸው ግንኙነት የአንዳንዶቹ ፖለቲካዊ የሌሎቹ ኢኮኖሚያዊ ነው፡፡ የጥቂቶቹ ደግሞ በልዩ ልዩ በተገለጡ ድካሞቻቸው ማኅበሩ መረጃ ስለያዘባቸው ያዋርደናል ብለው ከማሰባቸውና ከመፍራታቸው የተነሣ የማኅበሩ ተላላኪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በቅንነት ማኅበሩን ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማል ብለው የሚያስቡ ደጋፊዎቹ ግን ቆም ብለው ካስተዋሉ ማኅበሩ የተሰወረ ማንነቱና ዓላማው እየተገለጠ ስለመጣ ነጻ ለመውጣት ገና አልመሸባቸውም፡፡ ደግሞም ደጋፊዎቹ ከነበሩ አባቶች አንዳንዶች አሁን ማኅበሩ ሥርዐት እንዲይዝ እየተጋደሉ እንደሚገኙ ግልጽ ነው፡፡
          ይህ ጽሑፍ ለማኅበሩና ጉዳይ አስፈጻሚዎቹ ለሆኑ ጳጳሳት በግልጽ የሚረዱት መልእክት ነው፡፡ ለአንዳንዶች ተራ ትችት ሊመስል ይችላል ግን ሁሉም በአደባባይና በብርሃን የሚታይበት ጊዜ ሩቅ ስላልሆነ በትኩረት ተከታተሉ እውነታውን ትረዱታላችሁ! በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያና ተጨባጭ መረጃዎች ስላሉን በሌላ ጊዜ እናቀርባለን፡፡
ማኅበሩ  ከቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ውጪ የገነባው ቢሮው ከመንበረ ፓትርያርኩና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከሚደረግበት ሕንጻ ከፍ አድርጎ መገንባቱ ይህንን “የበላይነቱን” በቋሚ ምሳሌ ለማስረዳት ይሆንን?
          ወደተነሣንበት ጉዳይ ተመልሰን ማኅበሩ የጻፋቸው መቃወሚያ ደብዳቤዎች በወፍ በረር ስንቃኛቸው በተለይ በመጀመሪያ ለፓትርያርኩ የጻፈው ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያን የምህረት ቤት ስለሆነች አንድ ይቅርታ የሚጠይቁበት እድል እንዲሰጣቸው አደረገች እንጂ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የማኅበሩ ጽ/ቤት ተዘግቶ ንብረቱ እንዲወረስና አባላቱም በሰበካ ጉባኤና በሰንበት ት/ቤቶች ተመዝግበው እንዲቀጥሉ ርምጃ የሚያስወስድ ነበር፡፡

          ማኅበሩ ግን በስውር በሚመራው ሲኖዶስ ተጠቅሞ ፓትርያርኩን ከሥልጣን ሊያነሣቸው እንደሚችል እንኳ ተስፋ እንዳለው በዜና ማሰራጫዎቹ እስከ መዘገብ ደፈረ እንጂ የይቅርታውን እድል አልተጠቀመበትም፡፡ በመሆኑም በስሙ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለጻፉለትና ይቅርታ ጠይቅ ለሚለው መመሪያ የሰጠው ምላሽ የተሞላውን ትዕቢት የገለጸበት መሆኑን ለማሳየት የሚከተሉትን ነጥቦች እናንሳ፡፡ ለማኅበሩ የተሰጠው መመሪያ ይቅርታ ጠይቅ እንጂ መልስ ስጥ የሚል አልነበረም ግን ተወያይተን አሳምኑኝ የሚል የአቻነቱን መግለጫ ነው የሰጠው፡፡
በሃገራችን የተከሰቱትን ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት ሁሉም አካል በየዘርፉ በሚረባረቡበት በዚህ ትልቅ ኃላፊነት ያለባት የቅ/ቤተ ክርስቲያን አባትና ልጆች እንዲህ ዐይነት ደብዳቤዎችን በመጻጻፍ መጠመዳችን ግን እጅግ ያሳዘነን መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ሳንገልጽ አናልፍም፡-
ፓትርያርኩ ለማኅበሩ የጻፉት ደብዳቤ የግል ማስታወሻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ወክለው በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ናት ለማኅበሩ ደብዳቤ የጻፈችው ማኅበሩ ፓትርያርኩን ከሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ለመለየት እየሠራ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም የግል ደብዳቤያቸው አድርጎ ለማቅረብ መሞከሩ የሚያመለክተው አጠቃላይ ምልከታው ሸውራራ መሆኑን ነው፡፡

ሌላው ቤተ ክርስቲያን ለመንፈሳዊ የትምህርት ተቋማቶቿም ሆነ ለማኅበሩ በስሙ ለመጻፍ የተነሣችው ማኅበሩ ወቅቱን ተጠቅሞ የመንግሥት ትኩረት ወደ ሌሎች በሃገሪቱ ወደ ተከሰቱ ማኅበራዊ ቀውሶች ስለሆነ ለእኛ ይህን ጊዜ መጠቀም አመቺ ነው ብሎ በማሰብ 1ኛ በስውር አመራሩ በወሰነው መሠረት የተሐድሶ ጉዳይ የጥቅምቱ 2008 ዓ/ም የሲኖዶስ አጀንዳ እንዲሆንና ውሳኔውም በቤተ ክርስቲያንና በተቋሞቿ ውስጥ ትርምስ የሚፈጥር እንዲሆን በማሰብ በሚፈልገው መንገድ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረግ ለዚህም ድጋፍ እንዲሆን ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተጠና መንገድ የሲኖዶሱን ውሳኔ ለማዛባትና ወደሚፈልገው አቅጣጫ ለመዘወር በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣው ስለ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ መድረስ ተከታታይ ጽሑፍ መዘገብ ጀመረ፡፡ በተሐድሶ ጉዳይ የጻፈውን ጽሑፍ ሲኖዶሱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ለጳጳሳቱ ሁሉ በማሰራጨትና በማንበብ ግንዛቤያቸውን ወደ ማኅበሩ ፍላጎት በማሸፈት የዝግጅት ሥራ ሠርቷል፡፡

በዚህም መሠረት ሲኖዶሱ ማኅበሩ በጋዜጣው ስለ ተሐድሶ እንደገለጠውና አስጊ እንዳለው እንዲሁ በማለት በኮሌጆቹና በደቀ መዛሙርቱ ላይ ከኮሌጆቹም በተመረቁት አገልጋዮች ላይ በጀት ተመድቦለት የሚያጠና ኮሚቴ ሰየመ፡፡

          ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የሚያደርገውን ትግል እንቅፋት ይሆኑብኛል ብሎ የሚያስባቸውን የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማቱንና ከተቋማቱ ተምረው የወጡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን የሚቆረቆሩ ቀሳውስትንና አለቆችን ስለሆነ በመደለያው ሊያጠምዳቸውም ስላልቻለ ተሐድሶ የተባለውን ታርጋ በመለጠፍ አገልጋዮችን ከቤተ ክርስቲያንና ከሕዝብ ለመለየት ቆርጦ እየሠራ ይገኛል፡፡

          ሲኖዶሱ የማቅን አጀንዳ በሚፈልገው መንገድ ተወያይቶ እንደወሰነለት ሲረዳ የተሰየመውን አጥኚ ኮሚቴ የጥናት ሥራና የሚገኘውን ውጤት ለማዛባትና ወደሚፈልገው አቅጣጫ ለመውሰድ በስውር ለኮሚቴው ማኅበሩ አጠናሁት የሚለውን ሲኖዶሱን ያሳሳተ መረጃ በመስጠት ከዚህም በተጨማሪ በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና የተሐድሶ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ያለውን ጉባኤ በየአጥቢያውና በሁሉም አህጉረ ስብከቶች በማድረግ ፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ በሚል ሽፋን ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሁሉ በተሐድሶነት ለመፈረጅ ዘመቻውን በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ አጠናክሮ ቀጠለ፡፡

ብዙ ሽብር ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደገባች በማስመሰል ምእመናንን አወከ፣ ጉባኤ እየሠራ ሕዝብን በወሬ እንዲፈታና በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና መሪዎች አመኔታ እንዲያጣ መጠነ ሰጪ የስም ማጥፋት ዘመቻ አቀጣጠለ በብዙ ዐውደ ምህረቶች ላይ ሰባክያነ ወንጌልንና መሪዎች አወገዘ አጣጣለ፡፡

          በማኅበሩ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የመንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት አቤቱታቸውን ለቤተ ክርስቲያን በማቅረባቸው ቤተ ክርስቲያን ሓላፊነቷ ስለሆነ ለተቋማቱ ምላሽ ሰጠች፡፡

          ማኅበሩን ያሳዘነው ቤተ ክርስቲያን የሰጠችው ምላሽ አግባብ ስላልሆነ ሳይሆን ጉዳዩ ማኅበሩ እየሠራ ያለውን ድብቅ ሥራ የሚያደናቅፍ በመሆኑ ነው፡፡ እንደ እርሱ ፍላጎት ቤተ ክርስቲያን ከተቋማቶቿ ለቀረበው አቤቱታ ወቅቱ ሀገሪቱ በብዙ የማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ ስለሆነች ተዉ የፈለጉትን ይበሉ እናንተ ዝም በሉ ታገሱ እንድትል የፈለገ ይመስላል፡፡

ማዘን ካለበት ሀገር ችግር ላይ ስትሆን ወቅት እየጠበቀ በቤተ ክርስቲያን ሁከት የሚፈጥር ሥራ ቤተ ክርስቲያንን የማተራመስ ሥራ እንዲሠራ የሚያነሣሣውንና የሚያስገድደውን ሥውር ዓላማ በመያዙ ነው፡፡

          ማዘን ካለበት የሚፈጽመው ክፉ ሥራ ተቃውሞ ሲገጥመውና አስተካክል ሲባል ከመመለስ ይልቅ በዓለም አደባባይ በሚሰማ ደረጃ የሲኖዶስና የቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑትን ፓትርያርክ ውሸታም ብሎ በመሳደቡና ቤተ ክርስቲያንን በማዋረዱ ልዕልናዋንም በመድፈሩ ነው
ማዘን ካለበት በሀገሪቱ ችግር ላይ ብዙ የመፍትሔ ሥራ መሥራት የምትችለውን ቤት ክርስቲያን በውስጧ እሳት አቀጣጥሎ ከሓላፊነቷ እንድትጎድልና በውስጥ ጉዳይ እንድትያዝ በተጠናና የወቅቱን አመቺነት ከለላ አድርጎ በመንቀሳቀሱ ነው፡፡
          ማዘን ካለበት ከዚህ ቀደም የማንንም ስም ከማጥፋት እንዲቆጠብ የተሰጠውን መመሪያ ጥሶ እንደ እብድ ውሻ ይቃወሙኛል የሚላቸውን ሁሉ መናከሱን መተው ባለመቻሉ ነው፡፡

‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እንዲከበሩና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም አካላት ሕግን አክብረው በአገልግሎቷ እንዲሳተፉ ለማበረታታትና ኣርኣያ የሚሆኑ ተግባራትን ከማከናወን ጋር የሚቻለውን ሁሉ በመፈጸም ላይ ይገኛል››
          ማኅበሩ በዚህ ክፍል ደግሞ የፓትርያርኩን ሥልጣን ለማሳነስ ጥረት ያደርጋል፡፡ በግድም ቢሆን መቀበል የሚገባው የሲኖዶሱ ሰብሳቢና መሪ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱም መሪና በሁሉም ሥፍራ ቤተ ክርስቲያኒቱን መወከል መቻላቸውን ነው፡፡
          ፓትርያርኩን፣ የተሰጣቸውን ሓላፊነትና ሥልጣን አለመቀበል ሲኖዶስንና ቤተ ክርስቲያንን አለመቀበል ነው፡፡
          ከዚህ በተጨማሪ የማኅበሩ አደረጃጀትና አወቃቀር በሒደት ቤተ ክርስቲያኒቱን በመቆጣጠር በእጁ በማስገባት በራሱ ለመተካት የተዘጋጀ መዋቅር ነው፡፡
          የማኅበሩን አቋምና አካሄዱን የተገነዘቡ አንዳንድ አባቶች የማኅበሩ መዋቅር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር አቻ የሚያደርገው እንጂ በሥሯ ሆኖ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችለው አይደለም የሚሉትን እውነት ማኅበሩም አልካደም፡፡ ስውርም ቢሆን የራሱ ሲኖዶስን የሚያህል ወሳኔ ሰጪ አካል አለው፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያ ክፍሎች ሁሉም በማኅበሩም ውስጥ ተከፍተዋል፤ እንደ አህጉረ ስብከቶች ንዑሳን ጽ/ቤቶች እስከ አጥቢያ ድረስ ዘርግቷል፡፡ አባላት አለው፣ አስራትና መባ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ከአባላቱ ያለከልካይና ያለ ተቆጣጣሪ ይሰበስባል፡፡ ተጠሪ ነኝ ለሚልለት አካል ሪፖርት አያቀርብም ኦዲት አይደረግም፡፡ ራሱን ችሎ ከቤተ ክርስቲያኗ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ዋና ጽ/ቤትና በክልሎችም ንዑሳን ጽ/ቤቶች አሉት፣ ብዙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ብቻ የሆኑ ሥራዎችን ቀምቶ ይሠራል፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ጉዳይ ያለ ገደብ ጣልቃ ይገባል፡፡ አባቶችን ለቤተ ክርስቲያንና ለክርስቶስ በአንድ ልብ እንዳይቆሙ በፖለቲካ፣ በዘር፣ በጥቅም፣ በደካማ ጎናቸው በመግባት አቧድኖ ያታግላል፡፡ ከሀገር ውጪ የራሱን አብያተ ክርስቲያናት እያቋቋመና እየመራ ሲሆን አባላቱ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለማቅ ቅድሚያ ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ ማኅበሩ በአውሮፓና በአሜሪካ ባደረገው ቴሌ ኮንፍረንስ ከ1000 በላይ የሆኑት አባላቱ ያነሡት አሳብ ማሳያ ነው የኮንፍረንሱን ዝርዝር በሌላ ጽሑፍ እንመለስበታለን፡፡ 
          ማኅበሩ አደረጃጀቱ  ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያደክምና በቁጥጥሩ ሥር እንደትወድቅ የሚያደርጋት መሆኑን ተከትሎ ተቃውሞ ሲነሣበት አንድም ቀን የሚነሳው ታቃውሞ ልክ አይደለም ብሎ አላስተባበለም፡፡

          ማኅበሩ የሚያነሣው ማስተባበያ የምትሉት ልክ ነው፣ ግን ይህን ሥልጣን የሰጠኝ ሲኖዶስ ነው፣ በመመሪያዬ መሠረት የምሄድባት ጉዞ ልክ ነው እያለ ነው ይህ ማለት ዋና ችግሩ ያለው ሲኖዶስ ጋ እንጂ ማኅበሩ ጋ አይደለም፡፡ ማኅበሩ ሙሉ ለሙሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታ ተክቶ እንዲሠራ የሚያደርገውን ደንብ ሲኖዶሱ ያጸደቀለት ነው፡፡ ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባው መጠየቅ ያለበት ሲኖዶሱ ነው፡፡ ይህ ማለት የቤተ ክርስቲያን የቤት ሥራ ነው፤ መዋቅሩ ሲስተካከል የማኅበሩን የሥራ ድርሻ ፣ የሥልጣን ገደብ ተጠያቂነት በሚገባ የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ አንድ ማኅበር ቤተ ክርስቲያን የምትሠራውንና መሥራት የሚገባትን ሁሉ መሥራት የሚችል ሆኖ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ መመሪያ ሊጸድቅለት አይገባም፡፡

          ይህ ካልታረመ አሁን ፓትርያርኩን የሚሞግተው፣ በሚመሩት ሲኖዶስ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥልበታል፡፡ መፍትሔም የለም፡፡

          ማኅበሩ በጋዜጣና በደብዳቤ ለጻፋቸው የቤተ ክርስቲያን ክብር የሚነካና ሕዝብን ከቤተ ክርስቲያን የሚያርቅ ድርጊቱ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የድርጅቶችና የተቋማት መሪዎች ጉባኤ ሠርተው ሲያወግዙና የአቋም መግለጫ ሲያወጡ የአዲስ አበባ  ሀገረ ስብከት አለቆችና ሰባክያን አጠቃላይ ስብሰባ አድርገው ማኅበሩ በአስቸኳይ የእርማት ርምጃ እንዲወሰድበት ሲጠይቁ በዋናነት የተዋረደውና የተደፈረው ቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አሁን አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ የማኅበሩን ሕገ ወጥና መረን የሆነ አካሄድ በማያዳግም ሁኔታ መፍትሔ መስጠት ሲገባው ቋሚ ሲኖዶስ እንኳ በጉዳዩ ላይ የወሰደው ርምጃ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

          እንደውም የሲኖዶስ አባላት ከሆኑት መካከል ማኅበሩ ይቅርታ እንዳይጠይቅ ምላሽና ተቃውሞውን በደብዳቤ እንዲጽፍ እያማከሩና እያበረታቱት መሆኑ እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡
ፓትርያርኩ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማኅበሩን ሥርዐት እንዲይዝ አቋም ስለያዙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ ተጠሪ መሆናቸውን መቀበል የፈለገ አልመሰለንም ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ለማቅ ደብዳቤ ስትጽፍለት ማቅ ለቤተ ክርስቲያን (ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት) ቢጽፍ ይሻል ነበር ጉዳዩን የግል ጥላቻ ለማስመሰል ሞክሯል ባይሳካም፡፡ ፓትርያርኩን የቅዱስ ሲኖዶስ ሰብሳቢና መሪ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱም መሪ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንደሆኑ ሊቀበል ይገባል ወይስ በልቡ ሌላ ያስቀመጠው ስውር ፓትርያርክ ይኖር ይሆን?

ማኅበሩ ‹‹የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎች እንዲከበሩና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም አካላት ሕግን አክብረው በአገልግሎቷ እንዲሳተፉ በማበረታታትና አርኣያ የሚሆኑ ተግባራትን ከማከናወን ጋር የሚቻለው ሁሉ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ ብሎ ስለ ራሱ ያስቀመጠውን ቅጥፈት እንኳን ፓትርያርኩና ማንም ከቤተ ክርስቲያን ርቆ ያለ ቢመለከተው ሐቅ ነው ብሎ አይቀበለውም፡፡ ስንት ጊዜ ሕገ ወጥ በመሆኑ ተከሰሰ? ስንት ጊዜ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈበት? ስንት ጊዜ በሲኖዶስ ሥርዐት እንዲይዝ በሕግ እንዲመራ ተወሰነበት? ስንት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ተባለ? ስንት ጊዜ የአገልጋዮችን ስም በጋዜጣና በመጽሔት በሕገ ወጥ መንገድ መስደቡን እንዲያቆም ደብዳቤ ተጻፈበት? ስንት ጊዜ የማይፈልጋቸውን አገልጋዮች በኃይል አስደበደበ? ስንት ጊዜ አባቶችን በጽሑፍ ሰደበ? ስንት ጊዜ ወጣቶችን ለአመጽ አነሣሣ . . .  ሕገ ወጥነቱ የባሕርይው ስለሆነ ተዘርዝሮ ስለማያልቅ እዚህ ላይ እናቁመውና መልሱንም ለማኅበሩ እንተውለት፣ ምክንያቱም ትልልቅ መጻሕፍት ያጻፈ ሕገ ወጥነት በማኅበሩ ተፈጽሟል፡፡

          በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከመስከረም 15/2008 ጀምሮ በተከታታይ ማኅበሩ ያወጣቸውን ጽሑፎች  ሲያስተባብል የሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ሓላፊነቴን ለመወጣት ነው ብሏል፡፡ ግን  ሲኖዶስ በተወያየበትና በወሰነበት አጀንዳ ኮሚቴ ተሰይሞ ይጣራ አለ እንጂ ውሳኔያችንን ሁሉም አካል በሚገባ እንዲያውቁት ይደረግ አላለም፡፡ ሁልጊዜ በሲኖዶስ ለሕዝብ እንዲገለጡና ይፋ እንዲሆኑ የተወሰኑ አጀንዳዎች ሲኖሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳናት ይወጣሉ፡፡ ማቅ ስለ ተሐድሶ ቀድሞ በጋዜጣው ያወጣው ሆን ብሎ ነው፡፡ አጀንዳውን በተላላኪዎቹ ያቀረበው ማኅበሩ፣ ውሳኔውን ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንዲያመራ ያደረገ እርሱ፣ አባቶችን ለማሳሳት ከሲኖዶስ ስብሰባ ቀድሞ በጋዜጣው ስም ማጥፋት የጀመረው እርሱ፣ የተሰየመው ኮሚቴ የማቅን ጥናት እንዲያጸድቁለት የተሯሯጠው እርሱ፣ ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ ሥርዐት እንዲይዝ መመሪያ ሲሰጠው የሌባ ዐይነ ደረቅ ይህን ሁሉ ስህተት ፈጽሞና አባቶችን አሳስቶ ሲያበቃ የተሰጠውን የይቅርታ እድል መጠቀም ስለማይሆንለት ያለ አግባብ የፈጸመውን ድርጊቱን በጋዜጣ እንዲወጣ ማድረጉን የአገልግሎት ግዴታዬ ነው ብሎ ምላሽ መስጠቱ ማኅበሩ ወዴት እየተጓዘ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡
          ሌላው በማኅበሩ ደብዳቤ ውስጥ በተደጋጋሚ ራሱን የቤተ ክርስቲያን አካል እንደሆነ ለመግለጽ ሞክሯል? በማኅበሩ አባል የሆኑ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት እንዳሉ የታመነ ነው፡፡ እንደ ማኅበር ሲታይ ግን የቤተ ክርስቲያን አካል ነው ለማለት የሚያስደፍር አንድም ነገር የለውም፡፡ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን በማኅበሩ ላይ እየወሰደች ያለው ርምጃም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካል እንዲሆን ለማድረግ ይመስለናል፡፡ ይህ ሰፊ ነገር የሚያጽፍ ቢሆንም አካል እንዳልሆነ ለብዙዎች አሁን ግልጽ ስለሆነ እንለፈው፡፡
          ማኅበሩ ራሱን የቤተ ክርስቲያን አካል ነኝ እያለ! መንፈሳዊ ኮሌጆቹን ግን “ሌሎች አካላት” ይላቸዋል፡፡ ኮሌጆቹን የቤተ ክርስቲያኒቱ አድርጎ ስለማይቀበልና ሊያፈርሳቸው ታጥቆ ስለተነሣ ይህም የራሱን ት/ቤት ስለከፈተ ኮሌጆቹ እንዳይቀናቀኑት የከፈተው ዘመቻ ይመስላል፡፡ ፓትርያርኩ ለኮሌጆቹ የጻፉትን ደብዳቤ ለሌሎች አካላት በእርስዎ ፊርማ ደብዳቤ ስለጻፉብን እኛም እርስዎን ሰድበን ለሰዳቢ ለማድረስ በመላው ዓለም ለቀቅነው በሚመስል አገላለጽ ጽፈው ስላሰራጩብን ጽፈን አሰራጨን ብሏል፡፡
ፓትርያርኩን የሰደበበትን ደብዳቤ አሳባችንን ለማስረዳት ብቸኛ መንገድ እርስዎን መሳደብ ነው የሚል አንድምታ ያለው ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ማኅበሩ የጻፈው ደብዳቤ ‹‹ሥነ ምግባር አልባ›› መሆኑን መረዳት ያልቻለው ማኅበሩ ካለበት ሥር የሰደደ ብልሹነት አንጻር የተጻፈው ደብዳቤ በእርሱ እይታ የተሻለ ይዘት ስላለው ነው፡፡
          ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ተቃውመውኛል ያላቸውን ሰዎች በመግደል፣ በመደብደብ፣ በማሳደድ፣ ስም በማጥፋት ብቻ ሳይሆን ሕይወትን ሁሉ በማበላሸት ስለሆነ የተካነው ለፓትርያርኩ የጻፈው በማኅበሩ እይታ በጣም ጥሩ በሥነ ምግባር የተሞላ ጽሑፍ መስሎ ነው የሚታየው፡፡ በጣም እንደታገሳቸው ነው በጣም በትህትና አሳቡን እንደገለጠ ነው የሚሰማው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የራቀው ማኅበር ይህን ቤተ ክርስቲያንንና አባቶችን የሚያዋርደውን ደብዳቤ በጣም በትህትና መንፈስ ሆኜ የጻፍኩት ነው ቢል አያስገርምም፡፡
          ‹‹ደብዳቤ ለእርስዎ ቅር አሰኝቶዎ ከሆነ ከፊትዎ ቀርበን ልናስረዳና ጥፋት ሆኖ ከተገኘም ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁዎች ነን፡፡›› በሚለው አሳብ ማኅበሩ እንዴት የጠለቀ መንፈሳዊ ችግር ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ለሆኑትን ሁሉ አንገት ያስደፋ፣ ያሳፈረ፣ ለሰዳቢ አባቶችን አሳልፎ የሰጠ፣ ብዙዎቻችንን ያስለቀሰ ደብዳቤ ነው፡፡
          ይህን ያፈጠጠ ፓትርያርኩን ብቻ ሳይሆን ጳጳሳቱን፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮች ሁሉ ያቃለለ የስድብ ደብዳቤ በትህትና እንደጻፈው ከመሰለው እንዴት ነው ማኅበሩን ማሳመን የሚቻለው እንደተሳሳተ ፈጽሞ ሊያምን አይችልም፡፡ እንደውም ፓትርያርኩን ይቅርታ እንዲጠይቁት ሳይፈልግ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም በሰጠው መልስ ላይ እርሳቸው የጻፉትን ደብዳቤ ‹‹ ትክክል ያልሆነ መረጃ የሚሰጥ›› በማለት ነው የገለጸው የእርሱን ስድብ ‹‹በትሕትና እውነታን ለመግለጽ የሞከረ እንጂ ምግባር አልባ ሆኖ አልታየንም›› ነው ያለው ታዲያ ማኅበሩ ነው ይቅርታ የሚጠይቀው ምንም ተጨማሪ ውይይት ሳያስፈልግ በደብዳቤው በሰጠው ምላሽ ፓትርያርኩ ይቅርታ እንዲጠይቁት ነው የሚፈልገው፡፡
          ሌላው መንፈሳዊ ኮሌጆቹ ሁሉ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው ብሎ ከጻፈ በኋላ ይቅርታ ላለመጠይቅ አላልኩም ሲል ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል፡፡ ለነገሩ ከላይ እንደገለጽነው ኮሌጆቹን የቤተ ክርስቲያን አካል እንዳልሆኑ ሌሎች አካላት እንደሆኑ አድርጎ ስላያቸው አላልኩምም ቢልም ልዩነት የለውም፡፡
ሌላው ማኅበሩ ለተጻፈበት ደብዳቤ ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አለመጻፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለፓትርያርኩ ምላሽ ከሆነ የሚሰጠው ግልባጭ ላደረጉበት ሁሉ እርሱም ግልባጭ ማድረጉ ምን ይባላል ማኅበሩ ልቡ ምን ያህል እንዳበጠ የሚያሳይ ለራሱ የሰጠው ግምት ከፓትርያርኩ በላይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ በላይ እንደሆነ አድርጎ ስለሆነ ነው፡፡ ግልጹን እንነጋገር ከተባለ ይህንን ደብዳቤ በዚህ መልክ ግልባጭ አድርጎ መልስ መስጠት ፈጽሞ የማይመጥነው ቢሆንም ማኅበሩ ግን ቀይ መብራት ጥሶ አደገኛ መስመር ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ ነው፡፡
          አጠቃላይ የጻፉቸውን ደብዳቤዎች ስንመለከት ማኅበሩ ፓትርያርኩንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ቁልቁል ከሥሩ እንደሆኑ እንጂ ለበላይ አካል የጻፈው እንዳልሆነ ለማኅበሩም ሆነ በትኩረት ለሚያነበውም ግልጽ ነው፡፡
          ማኅበሩ ይቅርታ እንዲጠይቅና ይቅርታውንም በሚዲያዎቹ እንዲያሰራጭ የተሰጠውን መመሪያ በ5ኛ ቀን በመጨረሻዋ ሰዓት በጻፈው ደብዳቤ ሕገ ወጥነቱን አሳይቷል፡፡
          ይቅርታ ከጠየቀና ይቅርታ መጠየቁን በሚዲያው ከገለጸ በኋላ ነበር ቅሬታ ካለውም ይግባኝ ማለት የነበረበት ግን ይቅርታ አልጠይቅም ከፈለጉ እንነጋገር እንወያይ በማለት አቻ እንደሆነ አድርጎ ራሱን አቅርቧል፡፡

መቼም ከማኅበሩ ጋር ያለ ደረጃዋ ወርዳ ቤተ ክርስቲያን ትደራደራለች ብለን አናምንም፡፡ ይህንን የይቅርታ እድል ሳይጠቀም እንደውም ፓትርያርኩ ስለ ማኅበሩ ትክክል ያልሆነ መረጃ ለሌሎች አካላት ሰጥተዋል ብሎ ይቅርታ እንዲጠይቁት ባሳሰበበት ደብዳቤ እንነጋገር ለመወያየት ዝግጁዎች ነን፣ የውይይት መድረክ ይዘጋጅልን እናስረዳ በማለት. . . ያቀረበው ሌላው የትዕቢቱ መጠን ማስተዋሉን እንደወሰደበት አመላካች ነው፡፡
          ማኅበሩ በደብዳቤው መጨረሻ ሲኖዶሱ በማኅበሩ መንገድ ላይ የተፈጠሩትን ‹‹እንቅፋቶች›› እንዲያስወግድለት ጠይቋል፡፡
          ማኅበሩ እንደፈለገ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያተራምስና ሕልውናዋን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሥነ ምግባር የጎደለውን ሕገ ወጥ ጉዞ፣ እንዲያስተካክል የጠየቁትን እርሱ እንቅፋት ሆነውብኛል ያለው እነማንን ይሆን?
          ኮሌጆቹን ይሆን? ወይስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎችን? ወይስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትንና በሥሩ ያሉ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን? ወይስ ፓትርያርኩን? ብቻ ሁሉንም ሊሆን ይችላል ብለን እናስባለን እንቅፋት ስለሆኑበት ሲኖዶሱ እንቅፋቶቹን አይቶ እንዲያርምለት ፍላጎቱን ገልጿል፡፡

ለቤተ ክርስቲያንና ለክርስቶስ ወንጌል ተቃዋሚ ሆኖ ከተነሣባት ከዚህ አጋንንታዊ ማኅበር እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ያድን!

ቅዱስ ፓትርያርካችንንም በምሕረቱ ይጠብቅ ለብፁዐን አበው ማስተዋልን ይስጥልን!

ለቤተ ክርስቲያን ከሚቆረቆሩ

23 comments:

 1. ብዙዎቻችንን ያስለቀሰ ደብዳቤ ነው.... You are so funny menafik leba man lay new ye mitalagitew...እንቅፋት

  ReplyDelete
 2. ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ ያለ ተረካቢ ትውልድ ማፍራቷ እጅግ ያሳዝናል "የማታድግ ጥጃ ሽቅብ... ቆዳዋም ተመልጦ እርስዋም ትሞታለች" እንደተባለው ተረት ነው። ለሁለት ሺ ዘመናት ቤተ ክርስቲያን የቆየችው ከክርስቶስ የተማሩ ትሁታን ልጆችን ስላፈራች ነበር። በቋንቋ በዘር የማይመስሏትን ጳጳሳት በሃይማኖት አባቴ ብላ ተቀብላ የሾመላትን አምላክ አመስግና እግራቸውን አጥባ በረከታቸውን ተቀብላ ኖራለች። እነዚያ ትሁት ልጆቿ ነበሩ በረከትን ከአምላካቸው በረከት እያሰጡአት እዚህ ያደረሱዋት። መቼም የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ አባቱን የሚሰድብ ትውልድ እንደ ኖህ ልጅ ለመረገም የተዘጋጀ ትውልድ ተፈጠረ። ማህበረ ቅዱሳን ከቅዱሳን አባቶች ሊማር በተገባው ነበር። ቅዱሳን አባቶች ለዋኖቻቸው ይገዙ ነበርና። የቤተ ክርስቲያንን የቅዱስ ጴጥሮስ ስልጣን መጋፋት መናቅ ከጀመራችሁ እንዴት ነው ቤተ ክርስቲያን የምትከበረው። ይልቁንም መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣልና የቤተክርስቲያንን ክብርና ልጆቿን እንዲሁም ሃብቷን መልሱላት። በስሟ ከመነገድ አቁሙ። ልብ ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 3. እናንተ መናፍቃን ማቅ አላማችሁን ስለሚያውቅ እና እግር በእግር እየተከታተለ ስለሚያከሽፍባችሁ ከውሸት አባታችሁ አጋንት የወረሳችችሁትን ግብር ማቅ ላይ ትተገብራላችሁ ፡፡ ይልቁኑምለሆዳችሁ ማደር አቁማችሁ በጊዜ በንስሃ ብትመለሱ ጥሩ ነው ማቅ በእግዚአብሄር ፍቃድ የተመሰረተ ማህበር ነው ስለዚህ እናንተ የቱንም ያህል ብትጠሉት እግዚአብሄር ይጠብቀዋል፡፡

  ReplyDelete
 4. አጥርተን እንድናይ፣ ቤተክርስቲያናችንን በይበልጥ እንድንረዳ፣ የጠላትን ስውር እና ግልጽ እንቅስቃሴ በይበልጥ በትኩረት እንድንከታተል ስላደረገን ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠብቅልን፡፡ እናንተም እነ ሆድ አምላኩ በርቱልን በሚገባ እንድናውቃችሁ ስለረዳችሁን፡፡ መቼም ቢሆን ግን እንደማይሳካላችሁ ተገንዘቡ፡፡ ሁላችንም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለቤተክርስቲያናችን ነፍሳችንን እንኳን ለመስተጠት አናመነታም፡፡ አምላከ ቅድሳን ሀራጥቃን ያስታግስልን፡፡

  ReplyDelete
 5. ማኅበራችንን ጠብቅልን፡፡ የዲያቢሎስን ሰራዊት አስታግስልን፡፡በከንቱ አትድከሙ በአባቶቻችን ፈንታ ልጆች ተወልደዋልና፡፡
  ቁር………………………………………………………..

  ReplyDelete
 6. አጅግ በጣም ተቆርቆራችኋል፡፡
  ከተቆረቆራችሁ ለቤተ ክርስቲያን ሥሩ፡፡ በረከታቸው ይድረሰን እና አንድ ወቅት ላይ ለአቡነ ጳውሎስ ሐመር መጽሔት፣ ስምዓ-ጽድቅ ጋዜጣ እና መለከት መጽሔት ብዙ አንባቢ ስለአላት ሰዎች ሌሎች እንዳይነበቡ አድርገዋል የሚል ስሞታ ቀርቦላቸው እናንተም እንደ እነርሱ ፃፉ አሉ ይባላል፡፡
  ስለዚህ የሚያዋጣው ወሬ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን መሥራት ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. Tehadiso let me tell you the fact, it is impossible to eliminate the church.Errrrr.... dibinnnnn.....belu

  ReplyDelete
 8. ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር እንደ አንድ ድጋፍ ሰጪ አካል እንዲሠራ ፓትርያርኩ በሚመሩት ሲኖዶስ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እንደሆነ በምናውቀው ማኅበር.....ቂቂቂቂቂ..... ማን ነገራችሁ??

  ReplyDelete
 9. እርግጥ ፓትሪያርኩ ሚዛናዊ አባታዊ አቋም ባለማያዛቸው እየተጎዱ ያሉት እሳቸው ናቸው እንጂ ቤተ ክርስቲያን አይደለችም። አንድ ፓትርያርክ ምክር መጠየቅ ከአባቶች እንጂ ከወንጀሎች መሆን የለበትም። አንድም በጸሎት አንድም ረጋ ብሎ ሁኔታዎችን መመልከት ሲቻል እንደ ሕጻን ልጅ የሰሙትን ማስተጋባት ስለሆነ ችግሩ ከማንም የበለጠ በራሳቸው ላይ የሚብስ ነው የሚሆነው። አሁን ያስነበባችሁት ጽሑፍ ደግማችሁ ብታነቡት እርስ በርሱ የሚቃረን ነው። አንድ አባት ለአንድ ማኅበር ሲጽፍ ለመላው ዓለም መርጨት አለበት እንዴ? ይህ ራሱ ከመስመር የለቀቀ ነው። በሳቸው በኩል መስተካከል ያለበት ስለአለ ወደ ልባቸው እንዲመለሱ አባቶችም ሆን ምእመናን በጸሎት ልንራዳቸው ይገባል። በማኅበሩ በኩል የተያዘው አቋም ምንም ስህተት የለውም። ስህተቱ ከሳቸው ጋ ስለሆነ በሰከነ መንፈስ ከአባቶች እየተመካክሩ ቢወስኑ ለራሳቸው ነው ጥቅሙ አለበለዚያ ግን ይጎዱበታል። እግዚአብሔር አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ይስታግስልን።

  ReplyDelete
 10. ማህበሩ እኮ መስመር ከሳተ ቆየ
  አንድ ክርስቲያን ነኝ የሚል አካል «አጥፍተሃል ይቅርታ ጠይቅ» ሲባል እንዴት አሻፈረኝ ይላል ።
  ፩ "ትክክል የሚሰጥ"
  ፪ "ከአንድ የሃይማኖት አባት ቀርቶ ከአንድ ምእመን እንካን የማይጠበቅ"እያለ የቅዱስ ፓትርያርኩን ደብዳቤ እየተቸ እንዴት አልተሳሳተም ይባላል
  አረ እባካችሁ ጎበዝ እናስተዉል
  መደገፍ መብት ቢሆንም ህሊናን መሸጥ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ያስፈርዳል።
  ጽሑፉ በእዉነት አቅጣጫን የሚያመለክት ጽሑፍ ነዉ ።
  እግዚአብሔር ለማቅ አስተዋይ ልቡና ይስጠዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. zim bilesh achebichibi anchi....

   Delete
 11. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

  ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  ኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ፤

  (የአገርን ሰላም እሹ ፈልጉ የአገራችኹ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)

  የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

  የሀገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ፥ ሰላም ከእግዚአብሔር መኾኑን ያውቃል፤ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡

  ኢትዮጵያ ሀገራችን የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ተቻችለውና ተረዳድተው የሚኖሩባት የዓለም ምሳሌ ናት፡፡ ይህን ዓለምን የሚያስደንቅ ገጽታችንን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲከተለው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

  የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት፤

  ኢትዮጵያ አህጉረ ሰላም(የሰላም አገሮች) ከሚባሉት ከዓለም አገሮች አንዷ ስትኾን በአኹኑ ጊዜ በአንዳንድ ክልሎችና ከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ኹሉንም የሚያሳሳብ ኾኖ አግኝተነዋል፡፡

  ከዚኽም ጋር ባለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተው ያልተጠበቀ ችግር፡-

  በአንዳንድ አካባቢ የሰው ሕይወት ሲጠፋ፤ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ፤ የንግድ ተቋማት፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት ሲወድም፤ የሕዝባችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ሲናጋ ኹሉም ኅብረተሰብ የችግሩ ተጠቂ ኾኗል፤ የዚኽ ዓይነቱ ድርጊት በዚኽ ኹኔታ ከቀጠለ የሕዝባችን ህልውናና የትውልዱም የወደፊት ዕድል አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል፡፡
  ባሳለፍናቸው ሳምንታት በተከሠተውኹኔታ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመሪር ሐዘንና በጸሎት እናስባቸዋለን፡፡ ስለዚኽ ኹላችሁም ልጆቻቸን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ፣ ሴት፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ችግራችኹን ሰላማዊ በኾነ መንገድ ለሚመለከተው እንድታቀርቡ፣ መንግሥትም የሕዝቡን ችግርና ሰላማዊ ጥያቄ በመገንዘብ መፍትሔ በመስጠትና ሰላም ለማምጣት እያደረገ ያለውን የዕለት ከዕለት ጥረት እንዲቀጥልበት በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን፡፡
  ሕዝባችንና ሀገራችን በርኀብ፣ በድኅነትና በበሽታ ቸነፈር በተቸገረበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መሠረታዊ ወደኾነው የልማት የሰላምና የድርቅ ጉዳይ በማተኮር መልስ ሰጭ መኾን ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡
  ወገኖቻችን ሆይ፣ በአኹኑ ጊዜ የወቅቱ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ(ብሎገሮችና የፌስቡክ) ተጠቃሚዎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ከሞያችኹ ከዕውቀታችኹ ተጠቃሚዎች የመኾን ምኞታቸው የላቀ ነው፡፡ ኾኖም መልካሙንና ለዕድገት የሚያግዛቸውን ዕውቀት እንጂ ኅብረተሰቡን የሚለያይና የሚያራርቅ መረጃ(ኢንፎርሜሽን) ዕለት ዕለት ብታስነብቡት ትርፉ መራራቅን እንጂ መቀራረብን፤ መለያየትን እንጂ መግባባትን አያመጣም፤ ከዚኽ አንጻር የእናንተም ጥረትና ድካም ከንቱ ኾኖ ይቀራል፡፡ በመኾኑም የተከበረ ዕውቀታችኹን፣ ሞያችኹን፤ ለሕዝባችን ፍቅርና አንድነት፤ ለሀገራችን ሰላምና ዕድገት እንድታውሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትጠይቃለች፡፡
  የተወደዳችኹ ኢትዮጵያውያን፤

  ተቻችሎና ተረዳድቶ የመኖር የተቀደሰ ነባር ባህላችንን የሚያጎድፍ ማናቸውንም አስተሳሰብና እንቅስቃሴ በአንድነት መቋቋም እንደሚገባ አበክረን እየገለጽን፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን በሙሉ፣ በተለይም አገር ተረካቢ ትውልድ የኾናችኹ ወጣቶች፣ ሁከትና ብጥብጥብን ከሚያስከትሉ መጥፎ ድርጊቶች እንድትቆጠቡ፤ ለአገር ሰላምና ልማት ጠንክራችኹ እንድትቆሙ በልዑል እግዚአብሔር ስም አጥብቀን እያሳሰብን በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የሀብትና የንብረት ውድመት፣ በተለይም የሕዝብ መገልገያ የኾኑ የእምነት ተቋማት መቃጠል የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፡፡

  ይልቁንም ከኹሉም በላይ ኹሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔር አምላካችን፤ ለኢትዮጵያ ለሀገራችን ሕዝቦች ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ይስጥልን ዘንድ፤ ድርቁን ረኀቡን አስታግሦ መጪው ጊዜ ዝናመ በረከቱን ይሰጠን ዘንድ በያዝነው በዐቢይ ጾም ሱባኤ ጸሎተ ምሕላ በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

  እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ::

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

  የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.
  meche new wed Egizahber endete mekerebe endaleben yemitenegeron ....Beate Kiresetanachen Tsome ena Tseloten ahwejaleche entsome enetseley Fikerene ena anedeneten Egizaheber endadelen ..... lenegero enanete ke Abatacho ke Dabelose selewenacho ...meleyayeten ..zeregneneten ... minefekenane ..enije wed Egizhber mekerebawen minegede ahtawekotem

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማዎች የጻፋችሁት ጽሁፍ ተስፋ የቆረጣችሁ አስመሰላችሁ ምነው አናታችሁን በዱላ የተመታችሁ አስኪመስል ተስፋ ቆረጣችሁሣ;; ስም እንጂ ክረስትናው እንደሌላችሁ ያስተውቃል ለምን እግዚአብሔር ይሰራል ከሆነ ቀድሞም ለሰይጣን ነበር የምትሰሩት አሁን ህዘብ በደንብ አወቃችሁ ደግሞስ ከእግዚአብሔር ተዋገቶ ማን ያሸንፋል ???? ማንም!!! ስለዚህ ምንጀመራችሁ የርሱ የሆኑትን መሳደብ እና መቃወም ግን አይሆንም ከንቱ ድካም ከንቱ ሩጫ ልብ ይስጣችሁ፡፡
  ስለእውነት የቆማችሁ አባቶቼ በእድሜና በጤና ይጠብቅልን በረከታችሁ አይለየን ከእናንተ ስለ እውነት መኖር እና እውነት መናገርን አስተማራችሁን ያከበራችሁ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ለዘለአለሙ አሜን

  ReplyDelete
 13. ብጹእ ወቅዱስ አባታችንን በዙሪያ ከበው እያሳሳቱ ያሉት አማሰኞች እነ ንቡረ ዕድ ኤልያስ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት ተሃድሶ እና አማሳኝነት ህገወጥ የጥቅም ጋብቻ ፈጽመዋል፡፡ ስለዚህ ስለተሃድሶ ሲጻፍ ሙሰኛው ይነሳል ፣ ሙሰኛው ሲነካ ተሃድሶው ያለቅሳል፡፡ አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል የተባለው ነገር አሁን ገብቶናል፡፡ አማሳኞቹ ሆዳቸው እስካልጎደለ እና የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት መዝረፍ እስከቻሉ ድረስ ነገረ ተሃድሶ ለእነሱ ምናቸውም አይደል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ዝም ቢላቸው ኖሮ ስሙንም አይጠሩት…ይህንን ደግሞ አሳምራችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ማኅበሩ ተሃድሶዎች በርቱ ኮሌጆቻችንን እንደፈለጋችሁ ፈንጩባቸው እንዲላችሁ ትፈልጋላችሁ? ማኅበሩ ከፓትርያርኩ ጋር ልነጋገር እፈልጋለሁ ያለው እኮ ፓትርያርኩን በዙሪያ ሆነው እያሳሳቱ ያሉ ግለሰቦችን ስለሚያውቅ እኮ ነው፡፡ ፓትርያርኩ ይህንን እውነታ ቢረዱ ምን አልባትም ማኅበሩ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ነገር እየሰራ መሆኑን አውቀው በዙሪያቸው ያሉ አማሳኞችን ሊያጸዱ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ግን ማኅበሩ ወደ እርሳቸው እንዳይቀርብ እና የአማሰኞቹን ጉድ እንዳያወጣ ተደረገ፡፡ እውነት ትዘገይ ይሆናል እንጂ መገለጧ አይቀርም፡፡ እግዚአብሔር ሃይማኖታችንን ከአማሳኞች እና ከሃራጥቃ ጠብቅልን፡፡ ተመየጢ ተመየጢ ተሃድሶ ቀሳጢ፡፡

  ReplyDelete
 14. እናንተ ለቤተ ክርስቲያን የምትቆረቁሩ!

  ReplyDelete
 15. Benante bet neger sertachihu motachihu Yet yihon yeseyetenachihut mak mak eyalachihu leman yihon yemitinegrut kefireachew yemetaweku silehone lekebariw aredut Endayihon seytan rasu yiferachew yihonal enji ayamachewim.

  ReplyDelete
 16. EWNETEM AGANENTAWI MAHEBER. YE KIRSTOS TEKAWAMI MAHEBER. AND MENGED KIRSTOS BECHA. LELA YELEM. YEHEN NAW MENAFEK YEMTELUT. BE KIRSTOS MAMEN????? ENQUAN MENAFEK HONEN BEKIRSTOS SELAMENEN. YEMANEN WENGEL NAW YEMTSEBKUT YE KIRSTOSEN WOIS YELELAWEN GEDEL??? WENGEL ALGEBACHEHUM. BESEDEM YETEMOLACHEHU. WENGEL KIRSTOS NAW LELA ADELEM. WENGEL KIRSTOS NAW!!!!! KIDUSAN, MELAEKT, SEWOCH ADELUM WENGEL. JESUS IS THE ONLY WENGEL.

  ReplyDelete
 17. እኔ የሚገርመኝ ማንነታችሁን ባደባባይ መግለጻችሁና አለማፈራችሁ ነው። በአባቶች ፈንታ የተወለዳችሁ እናንተ እንግዲህ አባት አያስፈልግም ማለታችሁ ነዋ። ለዚህም ነው ለካ ከፓትርያርኩ ጋር እኩል የምትነጋገሩት። እኩል ካደረጋችዃቸውን ጥሩ ነው። ለእናንተ እሳቸው ተስተካከሉ ስለሚሏችሁ በተሃድሶ ተጽዕኖ የሚንቀሳቀሱ አድርጋችሁ ነው የሚታዩአቸው። እናንተ የቅዱሳንን ስም የያዛችሁ እርኩሳን የእሳት ልጅ አመድ። ነፈሰ ገዳዮች (ሰውን ያለስሙ ስም ሰጥታችሁ እራሳችሁ ከሳችሁ እራሳችሁ ፈርዳችሁ እራሳችሁ የምትደበድቡ የምትገድሉ። ሰውን ልጅነት ካገኘበት ቤ/ክ እየለያችሁ የመናፍቃን ሲሳይና የፓስተሮቻቸው ደሞዝ ከፋይ እንዲሁም የአዳራሾሻቸው መሙያ ያደረጋችሁ። እውነትም ልጆች ተወለዳችሁ። ቤተ ክርስቲያን በልጆች ሳይሆን በእግዚአብሔር ልጆች እንድትመራ ፍቀዱ። ሰውን በመናፍቃን ስለምታዩ በክርስቶስ ሰውን ማየት ስለማትችሉ ስትሰበሰቡ የምታወሩት ስለመናፍቃን፡ ወንጌላችሁ የጥላቻ ወንጌል፡ግደለው ስቀለው አባረው አሳደው የሚል ነው። ይህን የሚያደርጉ የማን ልጆች እንደሆኑ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስምሮናል። የባዘነውን ፈልጉ አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፡ለደካሞች ትጉላቸው፡ጠላቶቻቻችሁን ውደዱ የሚለው ዘላለማዊ ትዕዛዝ በእናንተ ዘንድ አይሰራ ቅዱስ ቃል ስለማታነቡ። አሁን የቀራችሁ ፓትርያርኩም መናፍቅ ስለሆኑ የራሳችንን ልዩ ቤተ ክርስቲያን እንክፈት ማለት ነው። እግዚአብሔር ግን እንዲህ ግራ የምታጋቡትን የሞተለትን ህዝብ ቸል አይልም በጊዜው መልስ ይሰጣል። ልጆች እባካችሁ በመንፈስ እደጉ

  ReplyDelete
 18. "በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።" የማቴዎስ ወንጌል 18:6
  ይድረስ ለ"አቡነሰላማ" ጸሀፊያን
  ወንድሞቼ:-
  ቤተክርስቲያንን በደሙ የመሰረታት እሱ ራሱ ራሷ የሆነ ጌታ መድኃኒአለም እየሱስ ለቅጽበት እንኳን አይተዋትም። እንደበደላችንም ሳይሆን እንደቸርነቱ ማደሪያው የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያንያችንንም እንደሚጠብቃት አምናለሁ። እኛም የቅዱስ መንፈሱ ማደሪያ እንድንሆን የተቀደሰ ፈቃዱ ይሁንልን።
  ለመሆኑ ህሊና ላለው ሰው እንደምን የእውነተኛው ቅዱስ እግዚአብሔር ወንጌል በአሉባልታ፣ በስም ማጥፋት እና በውሸት ይሰበካል? ውሸታምስ እንዴት የቅዱሱን እግዚአብሔር ቃል ሊሰብክ ይነሳል? አገልግሎት እየሰጠ ነው ከተባለስ አገልጋይነቱስ ለማነው? የምትሟገቱለትን ሀሳብ እንዴት በሀሰትና በቀጣፊነት ለፍጻሜ ቢደርስ እንኳን የመንፈስ ቅዱስን ስራ በምን መመዘኛ ገላጭ ይሆናል። የሚዋሽ ሁሉ ለራሱ ሲል ያድረገው እንጂ ለአምላከ ቅዱሳን እየሰራሁ ነው ብሎ ራሱን በፍጹም አያታልል።
  እናም ነፍሳቸውን ለዲያብሎስ ከሸጡት ጋር ወግናችሁ እኔን መሳይ ታናናሾችን፣ በዓለም ውጣውረድ ባዝነን ያልጸናነውን የሚያሰናክል ሀሰተኛ ወንጌል ሰባኪ ከሆናችሁ፣ ያልተባለውን ተባለ ያልተደረገውን ተደረገ ብላችሁ ከቀባጠራችሁ፣ የፍርድ ባለቤት እሱ በመጨረሻው ቀን የእግዚአብሔርን ስም በክፉ ስላስነሳችሁ እሱ ፍርዱ የማይጓደለው አምላከ ቅዱሳን በቸርነቱ ያስባችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው። ፍርዱማ የሱ የራሱ ብቻ ነው።
  የሀሰት አንደበታችሁን ማህበረ ቅዱሳንን ለማዳከምና ከመልካም ስራው ተስተጓጉሎ በአሉባልታና እንካሰላንቲያ እንዲጠመድ የማድረግ ጉዳይ ብቻ አድርጋችሁ አታስቡት። በህያው እግዚአብሔር ቃል የተመሰረተችውን አንዲት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንንም አስተምህሮ በመሳደብም እንጂ። ስብከታችሁ የራሳችሁን ኃጢአት መልሶ ያመለከት ለመመለስም የበቃ ልቦና ይሰጣችሁ ዘንድ ጌታ ፈቃዱ ይሁን። ከኃጢአት ግብር መመለስ ነው ዋናው ቁምነገር እስትንፋሱ ላለ እንደኔና እንደናንተ ተስፋ መንግስተ ሰማያት በደጁ የሆነ የሰው ልጅ።
  ለእኔ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ካልሆነ በስተቀር እራሳችሁን እስኪ ጠይቁ: ጌታን መቃወም (በሀሰት ክስ) ማንን ለማሸነፍ? መቼም በሀሰት ክስና አሉባልታ የክርስቶስን መንግስት እየገነባን ነው ብላችሁ እንደማታምኑ እንደማትሞኙ እገምታለሁ።
  ማህበሩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ተግባር ፈጽሟል ብላችሁ የምትዘግቡት ነገር ስድብና አሉባልታ ብቻ ነው። ለምሳሌ በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እንዲህ እንዲህ አለ ከምትሉን ለምን ሙሉውን ጽሁፍ (ሌላ የማያንጸውንና የማይጠቅመውን አባራችሁ እንደምትለጥፋት) አትለጥፋትምና አናነበውም። ያን ብታደርጉ የሚያሳጣችሁ ዋጋ ስላለ ግን ለማድረግ አመነታችሁ። አስኪ አድርጉት!? ማኅበሩ የስህተት አስተምሮትን አይቀበልም የአዳሽ ነን ባዮቹም (ያላወቁ አሳዋቂዎቹ) አስተካካይ መዶሻ መሆኑን በተግባር አሳይቶኛል።
  የእናንተን በዚሁ ጦማር ላይ የተለጠፉ ጽሑፎችን መለስ ብላችሁ ብታነቡኮ የእውነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነትንና አስተምህሮት ተቃዋሚ መሆናችሁ ግልጽ ነው። ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያንን 'ቤተክርስቲያናችን' ብሎ ለመጥራት እንዴት ይቻላችኋል? የበግ ለምድ የለበሰሰ ተኩላነት ከዚህ በላይ ምን አለ? በውሸት ማገልገል ያሸልም ካልሆነ በስተቀር እንግዲህ... ከነ የሀሰት አባት መሪዎች ዘንድ! መውጊያውን መቃወም የሚብሰው ለማን ይሆን?
  አንድ እውነት ግን ይገባኛል። ይኸውም የምታገለግሉት እምነት እንዴት የዘቀጠ እንደሆነ ነው! የምትታገሉለት የሀሰት አባት በመስቀሉ የተሸነፈ በአምላካችን ፊት አቅም የሌለው የተዋረደ ነው። በፍጹም የሰራዊት አምላከ የሀሰተኛ ሰባኪያን ወይም ቀጣፊ ወንጌላውያን እገዛና አገልግሎት አያስፈልገውም። አንዴ በደሙ እውነትን ለአለሙ የሰበከ ጌታ በሀሰት ሊገለገል አይችልም እናም ሀሰተኞች ሆይ ስብከታችሁ ለማን ነው?
  አዲስ ነኝ።

  ReplyDelete
 19. Egziabher baleh lay yichemirlih saynore altenagerkimina saynorachew yeminageru weyim endinorachew yemaytselyu mehon yemechereshaw dereja yeminfikina megelecha new aysemum gin yinegerachewal yewinet amlak winetun yigletlachew. En simon meserri erefu

  ReplyDelete
 20. GIZEWE YE NEGER AHYEDELEM YE TSOME YE TSELOTE YE SEBEKETE GIZE NEW ESKY TEMARO KEMASETEMARACHO BEFEET TADISO MENAFEKANEዘወረደ


  የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ዘወረደ
  ማለት፣ ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም
  የአምላካችን ሰው መሆን ያመለክታል፡፡ ከሰማይ ከወረደው
  በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን
  ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሳት ሊቁ
  ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ “ዘወረደ እምላዕሉ
  አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ
  በቃሉ” በማለት በጾመ ድጓው መጀመሪያ ላይ ገልጾት
  ይገኛል፡፡
  አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፣
  የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም
  አላወቁም ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ
  ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት
  ዋዜማ፣ መግቢያ፣ /መሐትው/ ሆኖ ከዋዜማ በፊት
  ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፡፡ ይዘመራል፡፡ ይመሰገናል
  ማለት ነው፡፡
  ስለዚህ የሳምንቱ ስያሜ ከዚህ የተወሰደ ነው፡፡ እንዲሁም
  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን
  የጀመረው፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሰው በመሆን ፣
  በዮርዳኖስ ተጠምቆ በማስተማር እንደሆነ ሁሉ
  የመጀሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡
  በዚህ ሳምንት በተለይም እሑድና ሰኞ የሚነገሩት
  ውዳሴያት ከመጻሕፍተ ኦሪትና ነቢያት የተወሰዱ ናቸው፡፡
  ሁለተኛም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር
  አምላክ አዳምን ለማዳን ከሰማይ መውረዱንና በመስቀል
  መሰቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡
  በተጨማሪም ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ጾመ ሕርቃል
  ይባላል፡፡ በ714 ዓ.ም.ሕርቃል /ኤራቅሊየስ/ የቤዛንታይን
  ንጉሥ ነበረ፡፡ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበት ምክንያት
  በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወርረው የጌታችን መስቀል
  ማርከው ወስደው ነበር፡፡ እርሱ ወደፋርስ ዘመቶ መስቀሉን
  ከእነርሱ ነጥቆ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሷል፡፡
  ሕርቃል ከፋርሶች ጋር ከመዋጋቱ በፊት ሐዋርያት
  በሲኖዶሳቸው ነፍስ የገደለ ሰው እስከ እድሜ ልኩ ይጹም
  ብለው ሥርዓት ሠርተዋልና ጾሙን ፈርቶ ስለነበር
  በኢየሩሳሌም የነበሩ ምእመናን አሳቡን ደግፈው “አንተ
  ጠላታችንን አጥፋልን ፣መስቀሉን አስመልስልን እንጂ
  የአንድ ሰው እድሜ ቢበዛ ሰባ ሰማንያ ነው ፡፡
  ጾሙንአምስት አምስት ቀን ተከፋፍለን እኛ ተከፋፍለን
  እንጾምልሃለን፡፡”ብለው ጾመውለታል፡፡
  ይህንን መሠረት በማድረግ ያላወቁት አንድ ጊዜ ጾመው
  ትተውታል፡፡ ያወቁት ግን ቀድሞም ሐዋርያት ጾመውታል
  ብለው ሥርዓት አድርገው በዓመት በዐቢይ ጾም መጀመሪያ
  ላይ ጾመ ሕርቃል እያሉ የሚጾሙት ሆነዋል፡፡ስለዚህ
  ቤተክርስቲያናችን ይህንን መሠረት በማድረግ በጌታችን
  ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የመጀመሪያውን
  ሳምንት ጾመ ሕርቃል በሚል ስያሜ ሰማይ እንዲጾም
  አድርጋለች፡፡ /መጋቢት 10 ስንክሳር ይመልከቱ፡፡/
  የቤተ ክርስቲያናችን ታሉቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ፣ በዘወረደ
  ጾመ ድጓው ሰንበት ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን፣ ሕይወት
  ላለው ነገር ሁሉ ጸጥታና ሰላም የሰፈነባት የዕረፍት ቀን
  ስለመሆኗ “አዘዞ እግዚአብሔር ለሙሴ ወይቤሎ ሰብዕከ
  ወላህምከ ወኲሉ ቤትከ ያዕርፍ በሰንበት”
  ዘፀ.20፥10፣23፣12፣ ጾመ ድጓ፣ እግዚአብሔር ሙሴን
  ሕዝብህ የከብትህ መንጋህ ቤተሰብህ ሀሉ በሰንበት ቀን
  ከድካማቸው ይረፉ በማለት አዘዘው ይላል፡፡ በዚህም
  ዘመነ ጾም፣ ወይም ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡
  በጾመ ድጓው ዘወረደ እየተባለ የሚታወቀው፣ በጾመ
  አርባው ወቅት በተለይም በመጀመሪያው ሳምንት
  የሚገኘው ያሬዳዊ ድርሰት በነግህ በሠለስት፣ በቀትርና
  በሠርክ እንዲሁም ቅዳሜና እዡድ በሌሊት የሚዘመር
  ነው፡፡ በውስጡም የያዘው ፍሬ አሳብ፣ የጾምን፣ የጸሎትን፣
  የምጽዋትንና የፍቅርን ጠቃሚነት አጉልቶ የሚያስተምር
  ነው፡፡
  በዚህ በጾም ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት
  በአብዛኛው ከቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ውስጥ የሚዘመረው
  ምዕራፍ የተባለው ነው፡፡ ምዕራፍ የተባለበት ምክንያትም
  በየመዝሙራቱ መሀል ሃሌታና ድጓ እያስገባ ለመዝሙሩ
  ማረፊያ ስላበጀለት በዚህ ምክንያት ምዕራፍ የሚል ስያሜ
  ሊያገኝ ችሏል፡፡ ይህ የዜማ መጽሐፍ በሁለት ታላላቅ
  ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ይኸውም የዘወትር ምዕራፍና የጾም
  ምዕራፍ በመባል ይታወቃል፡፡የዘውትር ምዕራፍ የሚባለው
  በዓመቱ ውስጥ ባሉት ቀናት ውስጥ ሳምንታትና በዓላት
  ሁልጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን፣ የጾም
  ምዕራፍ የሚባለው ደግሞ በጾመ አርባ ብቻ ለአገልግሎት
  የሚውል ነው፡፡
  ከዚህም በተጨማሪ በዐሥሩ ምህላት አርዕስተ ምህላ
  በዚሁ ክፍል ይካተታል፡፡ የምዕራፍ ቅንብር ከመዝሙረ
  ዳዊት፣ ከድጓና ከጾመ ድጓ ጋር የተቀናጀ ነው፡፡
  የትምህርት አሰጣጡም እንደ ድጓው ወይም እንደ ዝማሬ
  መዋሥዕቱ መጽሐፍ ተዘርግቶ ሳይሆን በቃል የሚጠናና
  የሚወሰን ነው፡፡ ስለሆነም ምዕራፍን ለመማር 150
  መዝሙረ ዳዊትን፣ ከነቢያት 15 ምዕራፎችንና 5
  መኃልያተ ሰሎሞንን በቃል ሸምድዶ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  ወይም ግድ ነው፡፡
  ጾምን መጾም የፈቃድ ብቻ ሳይሆን የትእዛዝም ነው፡፡
  በዘመነ ብሉይ ነቢዩ ኢዩኤል “ቀድሱ ጾመ ወስብኩ
  ምህላ” ጾምን ያዙ አጽኑ ምሕላንም ዐውጁ ሸማግሌዎቹን
  ከፈጣሪያችን ቤት ሰብስባችሁ በአንድነት ሁናችሁ ወደ
  እግዚአብሔር ጩሁ /ለምኑ/ ብሏል፡፡ ኢዮ.ምዕ.1፥11፣
  2፣12፣15-16 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ወኲኑ
  ላዕካነ፣ ለእግዚአብሔር በጾም ወበንጽሕ፡፡ በጾም፣
  በንጽሐና ተወስናችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ ብሏል
  2ቆሮ.6፥4-6፡፡
  ጾም ከሌለ ወይም ተገቢ ካልሆነ ጌታችን በምትጾሙበት
  ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ ስለ ጽድቅ የሚራቡ የሚጠሙ
  ንዑዳን ክብራን ናቸው ለምን አለ? ማቴ.5፥፣6፣16፡፡ ነቢዩ
  ዳዊትም ሰውነቴን በጾም አሳመምኳት በቀጠና፣ በሰልት
  አደከምኳት ለምን አለ መዝ.34፥68፣ ት.ዳን. 9፥3-4፣
  14፥5
  ነብዩ ሚኪያስ ሐዋርያት ሙሸራውን ከነሱ ለይተው
  የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ ያለውን
  የጌታን ቃል መሠረት በማድረግ ክርስቶስ በሞት
  ከተለያቸው በኋላ ጾመዋል፡፡ ጾምንም ሠርተዋል
  የሐዋ.ሥራ 13፥3፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ሐዋርያት
  የጾሙትንና እንዲጾም የወሰኑትን መጾም ይገባል ብለው
  ቤተ ክርስቲያን የተቀበለቻቸውን አጽዋማት እንዲጾሙ
  መወሰናቸው ይህን የጌታ ቃል መሠረት በማድረግ ስለሆነ፣
  የትእዛዝ መሆኑን ተገንዝበን መጾም አለብን፡፡ ጌታችን
  መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠራዔ ሕግ እንደመሆኑ
  አርባ ቀን አርቦ ሌሊት ጾመ እንጂ እርሱ ሳይጾም ጾሙ
  አላለንም ማቴ.4፥2፡፡

  ReplyDelete
 21. የቤ/ክያን የመጨረሻው ስልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ እንጂ የፓትርያርኩ እንዳልሆነ ጠፍቷችሁ አይመስለኝም ። "ፓትርያርኩን የቅዱስ ሲኖዶስ ሰብሳቢና" "መሪ" አላችሁ በእርግጥም ሰብሳቢ ናቸው፥ የቅዱስ ሲኖዶሱ መሪ ግን መንፈስ ቅዱስ ነው ። ለኑፋቂያችሁና ለዝርፌያችሁ እንዲመቻችሁ እንደ ካቶሊኮቹ ፓፕ አይነት ስልጣን ለመስጠት ያላችሁን ምኞት ያሳብቅባችኋል። እንደ ፓትርያርክነታቸው ተገቢውን ክብር መስጠት ተገቢ ነው፣ ከዚህ ውጪ ግን ቤ/ክያን በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪነት በቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ጠባቂነት እዚህ እንደደረሰች ወደፊትም ትቀጥላለች። ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮችን ታስገኛለች እንጂ ፓትርያርኮች ቤተ ክርስቲያንን አያስገኙም።

  ReplyDelete