Wednesday, March 9, 2016

ችግርን በትክክል መረዳት የመፍትሔ ጅማሬ ነው
ከመምህር አዲስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ስትሆን በምድረ ኢትዮጵያ ቀዳሚትና ለአገሪቱ በርካታ ነገሮችን ያበረከተች ታላቅ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች የተመሠረተችበትን ዋናውን የወንጌል ተልእኮ በሚገባና የሚፈለገውን ያህል ስላልተወጣችና አባሎቿን በተገቢው ትምህርተ ወንጌል መያዝ ሳትችል በመቅረቷ ምእመናኖቿ ወደሌሎች እየፈለሱ የእርሷ ምእመናን ቁጥር ደግሞ እየተመናመነ መምጣቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ አባቶች አንደበት ጭምር እየተነገረ ይገኛል፡፡ እስካሁን ሲነገር የቆየው ግን ለምእመናን ፍልሰት ሌሎቹን የእምነት ተቋማት አሊያም ምእመናኑን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ ምክንያት ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ለችግሩ ራስንም ተጠያቂ ማድረግ መጀመሩ ቤተክርስቲያኗ ችግሩን በመግለጥ መፍትሔ ለመፈለግ እየተዘጋጀች መሆኗን የሚያመለክት ፍንጭ እየሰጠ ነውና ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ራስን ንጹሕ አድርጎ ሌሎችን ብቻ ችግር ፈጣሪ አድርጎ መውቀስ ችግሩን ከማባባስ ውጪ መፍትሔ አላመጣም፡፡ ስለዚህ የራስን ጉድለት እንደ አንድ ችግር ማየት መጀመሩ መፍትሔውን ለመፈለግ ወሳኝ መነሻ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦርቶዶክስ አማኞች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱ ያሳሰባቸው የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ችግሩ የወንጌልን ተልእኮ በተገቢው መንገድና ዘመኑን በዋጀ ሁኔታ መፈጸም አለመቻላችን ነው እያሉ ነው፡፡ ስለዚህ አባቶች ቆም ብለን ማሰብ ካልጀመርንና አሠራራችንን ሳናሻሽል በዚሁ ከቀጠልን ባዶአችንን እንዳንቀር ያሰጋል ሲሉ ስጋታቸውን እስከ መግለጽ የደረሱበት ሁኔታ አለ፡፡ ይኸው የምእመናን ፍልሰት ሊቆም የሚችለው የወንጌልን ተልእኮ በተገቢውና ዘመኑን በዋጀ መንገድ መወጣት ሲቻል መሆኑን ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች መናገራቸው ለቤተክርስቲያኒቱ ችግር መፍትሔ ለመፈለግ ጅማሬ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

የካቲት 24/2008 ዓ.ም በተከበረው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፫ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ላይ ንግግር ያደረጉት ቅዱስ ፓትርያርኩ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በንግግራቸው ትኩረት የሰጡት ነጥብ፣ እንዲሁም ለበዓለ ሲመቱ የታተመው ልዩ መጽሔት መልእክት ቤተ ክርስቲያኒቱ በምእመናን ፍልሰት ትልቅ ችግር ላይ መሆኗንና እስካሁን የተጓዝንበት መንገድ የሚያዋጣ መሆኑን ተገንዝበን ለዚህ መፍትሔ የሆነውን የስብከተ ወንጌልን ተልእኮ በተሻለና በተገቢው መንገድ መወጣት መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡

“ከበዓለ ሲመቱ የሚጠበቅ” በሚል ርእስ የተላለፈው የመጽሔቱ መልእክት የሥራ አስኪያጁን ንግግር ጠቅሶ እንዳሰፈረው “የሰው ልጆች ለሰው ልጆች በሰጡት ገደብ የለሽ የሃይማኖት ነጻነት አንዱ ቀልጣፋ የሃይማኖት ተቋም ከሌላው ፈዛዛ የሃይማኖት ተቋም በረት ውስጥ ገብቶ  በጎችን እንዳይቀስጥ የተደነገገው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ድንጋጌ ተጥሶ የዘመናችን ነጣቂ የሃይማኖት ተኩላዎች ከበረታችን ውስጥ ገብተው በጎቻችንን እየቀሰጡብን ነው፡፡ መልካም እረኛ በማጣት በራሳቸው ፈቃድ ከበረታቸው እየወጡ ወደሌሎች በረት የሚገቡ በጎቻችንም እየበረከቱ ሄደዋል፡፡” ይላል፡፡ መጽሔቱ “ቀልጣፋ” ሲል የጠራቸው የሃይማኖት ተቋማት ፈዛዛ ሲል የጠራትን የሃይማኖት ተቋምን ፍዘት በመመልከት ወደበረቷ ገብተው መንጎቿን እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ምእመናንም መልካም እረኛ በማጣት ምክንያት በፈቃዳቸው ወደሌሎች እየፈለሱ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡ ስለዚህ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፍዘቷን ትታ ለወንጌል ተልእኮ መቀላጠፍ አለባት ነው መልእክቱ፡፡ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትም ምእመናንን መያዝ የማያስችልና እረፍተ ነፍስ የማያሰጥ ተራ ዲስኩር ከመሆን ወጥቶ ለሰዎች ሕይወት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ልዕልና የሚሰበከው ሕይወት ስለማይሆንና ሰዉን ይዞ ማቆየት ስለማያስችል በወንጌል ትምህርት መተካት አለበት፡፡ ሌሎችን ያናደድንና ቅዱሳንን አለቅጥ ያከበርን መስሎን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጪ ስለቅዱሳን እየተሰበከ ያለው ሌላ የመዳኛ መንገድ ሕዝቡን ሕዝቡን በወንጌል ከተሰበከው ከእውነተኛው የመዳን መንገድ የሚያወጣ ነውና ስለአዳኙ ኢየሱስ ወንጌል ሊሰበክ ይገባል፡፡

መልእክተ መጽሔቱ አክሎም “ከእንግዲህ ወዲህ በራስ ሩጫ እንጂ እንደ ቀድሞው በመንግሥት ትእዛዝ የሚስፋፋና የሚጠበቅ ሃይማኖት ስለሌለ በትምህርተ ወንጌል እንጂ በዝማሬና በቅዳሴ ብቻም ተከታዮችን ማፍራት” እንደማይቻል ገልጾ “ወደፊት ምእመናን አልባ ቤተክርስቲያን እንዳትሆን ክፍት በሆኑትና ተደርበው በተያዙት አህጉረ ስብከት ወቅቱን ሊዋጁ የሚችሉ  ሁለገብ ዕውቀትን ከቅድስና ጋር አዋሕደው የያዙ ዓለምን የሚገዙት እንጂ ዓለም የማይገዛቸውን ኤጲስ ቆጶሳት መርጦ መሾም ይዋል ይደር የማይባል ዐቢይ ጉዳይ ነው፡፡” በማለት ብቁ የሆኑ ጳጳሳትን መሾም እንደሚገባና ለስብከተ ወንጌል በመፋጠን ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡

እዚህ ላይ መልእክተ መጽሔቱ “ከእንግዲህ ወዲህ በራስ ሩጫ እንጂ እንደ ቀድሞው በመንግሥት ትእዛዝ የሚስፋፋና የሚጠበቅ ሃይማኖት ስለሌለ በትምህርተ ወንጌል እንጂ በዝማሬና በቅዳሴ ብቻም ተከታዮችን ማፍራት” አይቻልም ማለቱ እውነት ነው፡፡ ይህን ለማስተዋል ግን ቤተክርስቲያን በጣም ዘግይታለች፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቀድሞው አሠራሯ ጸንታ የኋሊት እያየች ወደፊት ለመጓዝ ስትሞክር የቆየችውና በቅዳሴና በዝማሬ ብቻ ሕዝቡን አቆየዋለሁ ያለችው ቤተክርስቲያን ብዙ ሕዝብ ማጣት ግዴታዋ ሆኗል፡፡ ወንጌል ይሰበክ ወንጌልን ካልሰበክን የሕዝቡ ፍልሰት አይቆምም ያሉትን ሊቃውንትና መምህራን ወንጌል ሰባኪዎችንና ዘማሪዎችን ማበረታትና የስብከተ ወንጌል ዐውዱን ማስፋት ሲገባት ተሐድሶ መናፍቃን እያለች አሳዳለች፡፡ ዛሬ ግን አባቶች መፍትሄ ያሉት እነዚህ ቀደም ብለው ተሐድሶ እየተባሉ የተባረሩትና በወፈገዝት መንገድ የተወገዙት አባቶችና ወንድሞች ቀደም ብለው መፍትሄ ያሉት ወንጌል ይሰበክ የሚለው መፍትሄ ነው፡፡ ዛሬም በርካቶች በማኅበረ ቅዱሳን ሰላይነት ጠቋሚነት ከሳሽነት ምስክርነትና ፈራጅነት ተሐድሶ የሚል ስም እየወጣላቸው በስደት ውስጥ ያሉ ሊቃውንትና መምህራን ወንድሞችና እህቶች ጥያቄም የሕዝቡን ፍልሰት ማስቆም የሚቻለው ወንጌልን በመስበክ ነውና ወንጌል ይሰበክ የሚል እንጂ ማኅበረ ቅዱሳንና መሰሎቹ እንደሚያወሩት ሌላ አይደለም፡፡   

ወደ ቅዱስነታቸው መልእክት ፍሬ ሐሳብ ስናልፍ “መነ እፌኑ ኀበ ሕዝብየ እስራኤል፤ ወደ ሕዝቤ ወደ እስራኤል ማንን እልካለሁ?” (ኢሳ. 6፡8) በሚል ቃለ እግዚአብሔር መነሻነት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ይህ በነቢዩ የተላለፈው ጥሪ “ዛሬም በዚህ ዘመን ለሚገኝ ትውልድ የሚጣራ የእግዚአብሔር ሕያው ድምፅ ነው፤ ብዙ ክፋት፣ አስመሳይነት፣ አታላይነት፣ የፍትሕ መዛባትና ነውር ኃጢአት ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ያጥለቀለቀው የዘመናችንን ዓለም የሚያስተምር፣ የሚመክርና የሚገሥፅ ጠንካራ የወንጌል ልኡክ ዛሬም እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡” በማለት የተናገሩ ሲሆን፣ “በኢሳይያስ ጊዜ የነበረ የመምህራን እጥረት ዛሬም እንዳለ ነው፤ ልዩነቱ በዚያን ጊዜ ይጣራ የነበረ እግዚአብሔር ብቻ ነበረ፤ ዛሬ ግን እግዚአብሔርም ሕዝቡም በጥምር ሆነው እየተጣሩ ነው፤ አስተምሩን የሚሉ ወገኖች በዓለም ዙሪያ ዛሬም ብዙ ናቸው፤ ሆኖም ለዚህ የሚሆን በቂ መልስ መስጠት አልተቻለም ምክንያቱም በመልእክተ ወንጌል ዙሪያ ብዙ ሊያሠሩ የሚችሉ ተግባራት በሚገባ አለመሠራታቸው ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው እንዳሉት እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም አስተምሩን እያለ በከፍተኛ ሁኔታ ጥያቄ እያቀረበ ይገኛል፡፡ ለሕዝቡ የወንጌል ጥማት እርካታ የሚሰጥና ወንጌልን በግልጥነት የሚሰብክ ሰባኪ ግን አልተገኘም፡፡ ቢኖርም ጥቂት ነው፡፡ ወንጌል እንሰብካለን በሚለው ተግባር የተሰለፉ መስለው ወንጌልን ሳይሆን በወንጌል ስም የተለያዩ ነገሮችን የሚሰብኩ ግን ሞልተዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ንጹሕ ወንጌል እንዳይሰብኩ ተሐድሶ እንባላለን፣ እንከሰሳለን በሚል ስጋት ከወንጌል ጋር ወንጌል ያልሆነ ነገር እየቀላቀሉ ይሰብካሉ፡፡ እንዲህም ሆኖ ከመከሰስና በተሐድሶነት ከመጠርጠር አልዳኑም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አንድ ጊዜ የመረዘው ሰው ምንም ቢያደርግ ተሐድሶ መባሉን ማስቀረት አይችልም፡፡ አንዳንዶችም በተሐድሶነት ላለመታማት የማያምኑበትንና ወንጌል ያልሆነውን ነገር ሁሉ ለመኖር ብለው ይሰብካሉ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ግን ተሐድሶ ከመባል አያመልጡም፡፡

ቅዱስነታቸው በማስከተልም “ውሉደ ካህናት በአጠቃላይ ማለትም ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ንፍቀ ዲያቆን ያሉት ሁሉ ሊያጤኑት የሚገባ ዓቢይ ነገር ከሁሉ በፊት ተቀዳሚ የቤተ ክርስቲያን ሥራ ስብከተ ወንጌል መሆኑን ነው፤ ስብከተ ወንጌልን መደበኛና ቀዋሚ ተግባር አድርጋ የማትንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋ አስተማማኝ አይሆንም፡፡ ቤተክርስቲያናችን ለሁለት ሺህ ዘመናት ያህል በየዘመኑ በልዩ ልዩ ኃይሎች የተጋረጡባትን እንቅፋቶች ሁሉ በመቋቋም እዚህ ልትደርስ የቻለችው በስብከት ወንጌል ኃይል ነው፤ ስብከተ ወንጌል ለቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል መተኪያ የሌለው ኃይል ነውና፤ ስብከተ ወንጌልን መደበኛና ቀዋሚ ተግባር አድርጋ የማትንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋ አስተማማኝ አይሆንም፡፡” ሲሉ ስብከተ ወንጌል ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ዋና ነገር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በእርግጥም ስብከተ ወንጌል ለቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠል መተኪያ የሌለው ኃይል ነውና፤ ስብከተ ወንጌልን መደበኛና ቀዋሚ ተግባር አድርጋ የማትንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋ አስተማማኝ አይሆንም፡፡”

ይህ ደግሞ እውን መሆን የሚችለው መንፈሳዊ ተቋማት በሥርዓተ ትምህርታቸው ውስጥ ለስብከተ ወንጌል ትኩረት ሲሰጡ መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፡፡ “የስብከተ ወንጌል ዕውቀት ማእከላት የሆኑት በየገዳማቱ፣ በየአድባራቱና በየቤተ ክርስቲያኑ ለዘመናት ተጠብቀው የኖሩት የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን፣ በየሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ማሰልጠኛዎቻችንና መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ሁሉ ስብከተ ወንጌልን ተኮር ያደረገና ሁሉንም ተማሪዎች ለመልእክተ ወንጌል ዝግጁ የሚያደርግ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ የቤተ ክርስቲያናችንን ህልውና ለማስጠበቅ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡”

ዛሬ በመንፈሳዊ ተቋማት ላይ በተለይም ማኅበረ ቅዱሳን እየቀረበ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ስንመለከት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ይህን የተቀደሰ ዓላማ በመቃወም ላይ የተመሠረተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጆች ጥረት እያደረጉ ያለው ዘመኑን በዋጀ መንገድ ስብከተ ወንጌል ተጠናክሮ ይቀጥል የምእመናን ፍልሰት ይቁም በሚል ዓላማ እያስተማሩና የተማሩትም ሁሉ ተመርቀው ሲወጡ ይህን ዓላማ ለማስፈጸም ነው የሚተጉት፡፡ ሆኖም ዘመኑን በዋጀ መንገድ ሳይሆን በኋላቀርና በባህላዊ መንገድ ሃይማኖትን አስጠብቃለሁ ከሚለው በዱሮ በሬ የማረስ አካሄድን ከሚከተለው ማቅ ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ማቅ የእነርሱን አገልግሎት ተሐድሶአዊ ነው የሚል ታርጋ ይለጥፍበትና እነርሱ እንዲጠረጠሩና እንዲሰደዱ ያደርጋል፡፡ ለመሆኑ ባለፈው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ሥርዓተ ትምህርታቸው እንዲፈተሽ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔና የሰየመው ኮሚቴ በየትኛው አቅጣጫ ሊሄዱ እንደሚችሉ መታሰብ አለበት፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲሁም ሥራ አስኪያጁ ከተናገሩት አንጻር ሥርዓተ ትምህርታቸው ዘመኑን የዋጀ መፍትሔ አምጪ መሆን እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎት ወይም ውሳኔውን የተረዳበትና የተረጎመበት መንገድ ደግሞ ከራሱ አካሄድ አንጻር የተቃኘና ባህላዊውንና ኋላ ቀሩን መንገድ እንዲሁም ለወንጌል ትኩረት የማይሰጠውን ይከተል ባይ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ውሳኔውን በመረዳትና በመተርጎም ላይ የተፈጠረውን ልዩነት ማስታረቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

በበዓለ ሲመቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስም ከፍ ብሎ የተገለጸውን ያንኑ ሐሳብ በመጋራት ቤተክርስቲያኗ በምእመናን ፍልሰት አደጋ ላይ መሆኗን ጠቅሰው “ምናልባት በሰሜኑ ሀገራችን ትንሽ ልንቆይ እንችል ይሆናል፡፡ አሁን ከዚህ በፊት ምንም በማናይባቸው አካባቢ ትልልቅ አዳራሾች እየታዩ ነው፡፡ ይህም በምሥራቁ በደቡብ በምእራቡ በእጅጉ እየሮጡ ሳይሆን እየተበረሩ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ይሄንንም ትንሽ ለማቆየት የአህጉረ ስብከትና የወረዳ ሊቃነ ካህናትን አድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎችን የሰበካ ጉባኤ ኣባላትን በማሰባሰብ ስለ ችግሩ አሳሳቢነት መመካከር ያስፈልጋል፡፡ ሕዝባችን ጠንካራ ነበር፤ ሥራ ሲሉት ይሠራል ስጥ ሲሉት ይሰጣል፡፡ ትልቁ ችግር ግን ጠላት ሲመጣ የሚመልስበት ትጥቅ ሳይዝ አገኙት፤ በምን ይከላከላል ከዚህ በፊት ማህሌት ይቆምለታል ቅዳሴ ይቀደስለታል እሰየው በቃ ክርስቲያን ነው፡፡ ግን ስለ እምነቱና ስለ ማንነቱ አልተማረም፡፡ በዚህ መሠረት የተዘጋጀና አውላላ ሜዳ ላይ የተገኘ ምርጥ ሆነላቸው፡፡ ማርከው ከበረታቸው አስገቡት፤ ሆኖም መፍትሄው መንቃት ብቻ ነው፡፡ … ከመላው ዓለም አስቀድማ በአምልኮተ እግዚአብሔር ያፀናችው ጥንታዊትዋ፤ ታሪካዊትዋና ብሔራዊትዋ ብሎም ዓለም አቀፋዊትዋ ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ጊዜ ትጥቋ ላልቶ ባእዳን ሊያስታጥቋት ሲዳዳቸው ይስተዋላል፡፡ … በአሁኑ ጊዜ የተሾምነው በቁጥር የበዛን ስንሆን ትጥቃችን በመላላቱ በቁጥር ያነሱት ያለፉት አባቶቻችን ህልውናውን ጠብቀው መብትዋን ሳያስደፍሩ ያስረከቡንን ቤተ ክርስቲያን እኛ ብናስደፍራት ባለውም በሚመጣውም ትውልድ ዘንድ የታሪክ ተወቃሾች እንዳንሆን የላላውን ትጥቃችንን አጥብቀን ልንነሣ ይገባናል፡፡” ብለዋል፡፡ 

ማኅበረ ቅዱሳንና የዓላማው ደጋፊዎች ግን ይህን የቤተክርስቲያኗን መሠረታዊ ችግርና ሥጋት ከሌላ አቅጣቻ የመጣ ነው እንጂ የወንጌልን ተልእኮ አለመወጣት ነው ብለው አያምኑም፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ እንደሚሰማው ችግሯ በዋናነት የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እንዲህ ሲባል ግን ሌሎች አስተዳደራዊ ችግሮች የሉባትም ይላሉ ማለት እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እነርሱ ለህልውናቸው መቀጠል ተሐድሶ ተሐድሶ ማለት ግድ ሆኖባቸው እንጂ ተሐድሶ እነርሱ እንደሚሉት ቤተክርስቲያን የዘነጋችውንና እነሆ በመሪዎቿ አንደበት መፍትሄ ነው ብላ ያወጀችውን የወንጌልን ተልእኮ ማፋጠን እንጂ ሌላ ተልእኮ የለውም፡፡ ይህም ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚናገረው ቃለ ብሥራት ነው፡፡ “… ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” (ሮሜ 1፡3-4)፡፡ የእርሱ አዳኝነት የማይሰበክበት ወንጌል ለስሙ ወንጌል ተብሎ ቢጠራም ወንጌል ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ለወንጌል ተልእኮ መፋጠን አለባት ሲባል ስለኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት በመስበክ እየተቅበዘበዘ ያለውን ምዕመን በእርሱ አዳኝነት ማሳረፍ መቻል አለባት፡፡ እርሱ ጌታችን እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማለቱ ከቶም ሊዘነጋ አይገባውም፡፡ (ማቴ. 11፡28)፡፡

ሌሎቹ በእጅጉ እየሮጡ ሳይሆን እየተበረሩ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡” የተባለው አሳሳቢ ሳይሆን መንፈሳዊ ቅንአትን የሚያሳድር መሆን ነው ያለበት፡፡ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መጠናከር ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀደም በስፋት አድርጋው የማታውቀውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንድታጠናክር ነው ያደረጋት፡፡ በየቤተክርስቲያኑ የሰርክ መርሐግብር የተጀመረው ከዚህ የተነሣ መሆኑ የቅርብ ዓመታት ትውስታ ነው፡፡ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ እንዲሆኑ ያደረገው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን እንደሚገባት አለመስበኳ ወይም መጽሔቱ እንዳለው “ፍዘቷ” ነው፡፡ እርሷ ዘንድ ይህ ክፍተት ባይኖር እነርሱ እንዲህ አይሆኑም ነበር፡፡ ዛሬም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ህልውናዋን ማስጠበቅ የምትችለው ወንጌልን በተገቢው መንገድና በጥራት መስበክ ስትችል ነው፡፡ የሆነው ሆኗል ሁሉም በተለያየ ባህልና ትውፊት ቢሆንም የሚሰብከው ክርስቶስን ስለሆነ እንደጠላት መተያየቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ክርስቶሳዊም አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ፀረክርስትና የሆነውንና ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ትልቅ ስጋት የሆነውን እስልምናን በስብከተ ወንጌል መቋቋምና ብዙዎችን ለቤዛ ዓለም በተሰቀለው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው የዘላለም ሕይወት ማምጣት ይገባል፡፡

የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እርስ በርስ በጠላትነት ከመተያየትና ከመወነጃጀል የኢኩሜኒዝምን መንፈስ በመጠበቅ በወንጌል ዓላማ ተስማምተው ክርስቶስን ለዓለም መስበክ ይገባቸዋል፡፡ በቅርቡ የታተመ “አውሎግሶን” የተባለ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተመሠረተ መጽሐፍ አዘጋጅ በመግቢያው ላይ ወንጌላውያን ከኢኩሜኒዝም መንፈስ ውጪ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንደ በደሉ ገልጾ “ሥራችሁ በኢኩሜኒዝም መንፈስ ከሆነ ግን፣ በወንጌል ዓላማ ተስማምተን፣ ክርስቶስን ለዓለም እንስበክ፡፡ ሌላ ተቃውሞ ግን እኛን ብቻ ሳይሆን እናንተንም ይጎዳችኋል፡፡ በፍጻሜው እንዲያውም የእናንተ ጉዳት ያመዝናል፡፡ ተጨባጩን ሁኔታ ገምግሙት፡፡” ብሏል፡፡ እንደ ግለሰቡ ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱም ነገሮችን በዚህ መንገድ መመልከት ብትጀምር መልካም ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡   

“ከመላው ዓለም አስቀድማ በአምልኮተ እግዚአብሔር ያፀናችው ጥንታዊትዋ፤ ታሪካዊትዋና ብሔራዊትዋ ብሎም ዓለም አቀፋዊትዋ ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ጊዜ ትጥቋ ላልቶ ባእዳን ሊያስታጥቋት ሲዳዳቸው ይስተዋላል፡፡” ትጥቋ ምን ይሆን? ወንጌል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ወንጌልን ማለትም አዳኙን ክርስቶስን ብትሰብክ ኖሮ ሌሎች ወንጌልን አልሰበከችም ብለው ባልከሰሷት፣ ምእመናኖቿንም ወንጌልን እየሰበኩ ባልወሰዷቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ወንጌልን በተገቢውና የሰውን ሕይወት ሊለውጥ በሚችል መንገድ መስበክ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ትጥቋን ካላጠበቀች በቀር ከገባችብት ምእመናንን የማጣት ችግር አትወጣም፡፡ ከወንጌል ውጪ ሌላ ትጥቅ በማስታጠቅም የምእመናንን ፍልሰት መግታት እንዳልተቻለ ማኅበረ ቅዱሳን ከተከተለው ስልት መረዳት ይቻላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከተረት እስከ ኃይል እርምጃ ድረስ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ምእመናንን ከፍልሰት መታደግ አልቻለም፡፡ እንዲያውም ፍልሰቱን አባብሶታል፡፡ ፍልሰት የበዛው እርሱ ለቤተክርስቲያን እኔ ብቻ አለሁላት እያለ ከላይ በተጠቀሰው ስልት በተንቀሳቀሰባቸው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ተረት ስፍራውን ለወንጌል መልቀቅ አለበት፡፡ ያን ጊዜ ነው ቤተክርስቲያን ትጥቋን ጠበቅ አደረገች የሚባለው፡፡
     
17 comments:

 1. አዛኝ ቂቤ አንጓች፡፡ ቅጥረኝነትህ አልሰራም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱሳን የእግር እሳት ሆነባችሁ መቼም፡፡ እሱንማ ፈጣሬ ዓለማት ባያስነሳልን፡፡ መጫወቻ በሆንን ነበር ግን እግዚአብሔር ይመስገን ዓላማ አለው፡፡ የምዕመናን ፍልሰት ትላለህ እርግጥ በምትፈልገው ፍጥነት እና መጠን አልፈለሰምና ደስታህ ቀንሷል፡፡ ሆኖም አምላከ ቅዱሳን የአባቶችን መንፈስና እምነት ዛሬም በእኛ በልጆቹ ስላሳደረ ለሐይማኖታችን ከመጋደል ወደኋላ አንልም፡፡ የቤዠን በደሙም ያሳረፈን ፈጣሪያችንን ሳንሸቃቅጥ ፍጹም እምነት እናመልከዋለን ስናመልከውም ኖረናል፡፡ አንተ የምትለው የተንሸዋረረ የትዕቢት ወንጌል ግን በአፍንጫችን ይውጣ፡፡ የሉተር ዓላማ ለተኮላሹት እንጂ ሰማያዊት የእግዚአብሔርን መንግስት በእምነት እና በተስፋ ለምንጠባበቅ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ አማኞች አይሰራም፡፡ አምላክ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን፡፡

  ReplyDelete
 2. Let MK= Mahibere kidusan , 'AB'= 'Aba selama'/Tehadiso and x=Multiplication sign Then the relation ship b/n Mk & 'AB' is given by MK(100%)x 0='AB'(0%) 'AB' always multiplies the fruitful tasks of MK by zero.Long Live Mk!!!!!!

  ReplyDelete
 3. Tehadiso Menafik!!!

  ReplyDelete
 4. Zare min nekachihu Mak satilu restachihut mehon alebet bezi yemitiketilu kehone lene bigermegnim addis zena new yilmedibachihu...............

  ReplyDelete
 5. JESUS IS THE ONLY WAY BROTHERS AND SISTERS. READ BIBLE, NOT GEDEL, READ BIBLE AND KNOW THE TRUTH. JESUS CHRIST IS THE ONLY WAY. PERIOD!!!!!!! EGZIABHER HASABUM HONE ALAMAW BE LEJU BE EYESUS KRISTOS AMNEN YEZELALEM HYWOT ENDENAGEGN BECHA NAW. LELAW HAYMANOT, SERAT, WEG NAW. BELIEVE IN JESUS CHRIST AND BE SAVED MY BROTHERS AND SISTERS. JESUS CHRIST AJABIE AYFELEGIM BECHAWN BEKI NAW, BECHAWN AMLAK, BECHAWN ADAGN, BECHAWN, BECHAWN. FEKERENA SELAM YEBZALACHEHU, TESMAMU TEWADEDU, TEKEBABERU, SEDEBENA TELACHAN AREKU. JESUS CHRIST IS LOVE AND LOVE OTHERS. ENANTE MANACEHU LELAWN YEMTSEDBUT KIRSTINA ALGEBACHEHUM, BIGEBACHEHU ATESADEBUM, TASTEMERALACHEHU ENJI. ESTI BEGO NEGER ENESMA KENANTE KE ORTHODOX CHRISTIANS. ENEZIA HULU YEMTAMNUACHEW AMLAKOCHACHEHU YEMTANEGSUACHEW, YEMTAKEBRUACHEW MEN ASTEMARUACHEHU, SEDEBENA TELACHA!!!! ESTI ASAYU KIRSTINACHEHUN YALE SEDEB YALE TELACHA YALE ALEMAWINET..........

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ye-Hawariat sera eko Gedle hawareyat newu(GEDEL), Metsehafe sosena is Gedle sosena (GEDEL). Ye-gedel tirgumu eskigebah tegna!!!!

   Delete
 6. kIDASE ERASO SEBEKETE MEWENO SELELEMATAWEK NEW AHYEFEREDEBEM ... KE KIDASE KEFELOC ANDO EKO TIMERETE KIDASE NEW MEZEMERE DAWETE KE BILOYATE ,YE KIDOUS PAWOULOSE MELEKET,KE 5 YE ADISATE METSEAFET ANDO ,YE HAWAREYATE SERA , KE 4 WEGELAWEYANE ANDO ,,, EYEWELO SEBEKETE AHYEDELEM MAHLETE NEW “ከእንግዲህ ወዲህ በራስ ሩጫ እንጂ እንደ ቀድሞው በመንግሥት ትእዛዝ የሚስፋፋና የሚጠበቅ ሃይማኖት ስለሌለ በትምህርተ ወንጌል እንጂ በዝማሬና በቅዳሴ ብቻም ተከታዮችን ማፍራት” እንደማይቻል ገልጾ “ወደፊት ምእመናን አልባ ቤተክርስቲያን እንዳትሆን ክፍት በሆኑትና ተደርበው በተያዙት አህጉረ ስብከት ወቅቱን ሊዋጁ የሚችሉ ሁለገብ ዕውቀትን ከቅድስና ጋር አዋሕደው የያዙ ዓለምን የሚገዙት እንጂ ዓለም የማይገዛቸውን ኤጲስ ቆጶሳት መርጦ መሾም ይዋል ይደር የማይባል ዐቢይ ጉዳይ ነው፡፡” LENEGERO EYEN TSAFEWE KIDASE ASEKEDISO SELEMAYAWEK AHYEFEREDEBETEM

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማንን ለማለት ነው? አባ ማቴዎስን ነው? ለነገሩ እሳቸው ስድስት ኪሎ አዲሷ ሚስታቸው ጋር አርብ ሄደው ሰኞ ስለሚመለሱ ቅዳሴ አያስቀድሱም ማለትህ ልክ ነው፡፡

   Delete
 7. ቤተ ክርስቲያኒቱ በ57 ዓመታት ታሪኳ ውስጥ እንደዚህ ጊዜ በብዙ የቤት ሥራዎች የተወጠረችበት ወቅት የለም፡፡ በአንጻሩም እንደዚህ በከንቱ የባከኑ ሦስት ዓመታትም አጋጥሟት አያውቅም፡፡
  ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ በሦስት ዓመታት የፕትርክና ጊዜ ውስጥ የስብከተ ወንጌል ድርጅት አቋቁመዋል፤ 17 ሊቃነ ጳጳሳትን ሾመዋል፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ የልማት ኮሚሽንን መሥርተዋል፤ ሰበካ ጉባኤን አቋቁመዋል፤ 7 ሊቃነ ጰጳሳትን ሾመዋል፡፡ መናኙ አባት ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 28 ጳጳሳትን ሾመዋል፤ ተዘግቶ የነበረውን ሰዋስወ ብርሃን ኮሌጅ አስከፍተዋል፤ ለአብነት መምህራን ደመወዝ እንዲከፈላቸው አድርገዋል፡፡ በአስቸጋሪ ወቅት የነበሩት ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ (አባ ዘሊባኖስ) ቢያንስ 6 ጳጳሳትን ሾመዋል፡፡ በበርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች የሚታወቁት ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ እንኳ በሦስት ዓመት ውስጥ በርካታ ጳጳሳትን በመሾም አህጉረ ስብከትን አስፋፍተዋል፡፡ አገልግሎት አቁሞ የነበረውን ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን አስከፍተዋል፡፡ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ሲኖዶሳዊ የሕግ ማሕቀፍ በማበጀት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡ የቀደሙት ፓትርያርኮች ይህንና ሌሎች መልካም ተግባራትን በተሾሙ በሦስት ዓመታት ውስጥ ሲፈጽሙ፤ ስ ድስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ግን ከወረቀት ያለፈ ይህ ነው የሚባል ተግባር የፈጸሙ አይመስለኝም፡፡
  የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የሦስት ዓመታት የሥራ ፍሬዎች ከብፁዓን አባቶች ጋር በስምምነት አለመሥራት፣ ያለምንም መንፈሳዊ ፋይዳ አሜሪካ መመላለስ (በሦስት ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ሂደዋል)፣ የማኅበረ ቅዱሳንን ጉባኤያት፣ የውይይት መድረኮችና የቴሌቭዥን ፕሮግራምን ማገድ፣ ማኅበሩን ማዕከል ያደረጉ ደንቦችና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከአገልግሎት ማደናቀፍ ወዘተ ናቸው የሚል ግምት አለኝ፡፡
  ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት፣ ፓትርያርኩ ያሳለፏቸውን ሦስት ዓመታት በማስተዋል መገምገምና መጭውን የመንፈሳዊ የአገልግሎት ዘመናቸውን ቢያጤኑት እላለሁ፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አምላክም ይርዳቸው፡፡
  ምንጮች ተጠቅሰዋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከተሾሙበት ዘመን ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር እንደ አቡነ ማትያስ ትልቅ ሥራ የሠራ የለም፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ተወልዶ የፋፋውንና ለቤተክርስቲያን የጎን ውጋት የሆነውን ማቅን መስመር ለማስያዝ የጀመሩት ትግል አቡነ ጳውሎስ እንኳን ሞክረው ያልቻሉት ነው፡፡ አቡነ ማትያስ ግን እስካሁን የተሳካ ስራ ሰርተዋል፡፡ ሌላውንማ የሚሰሩት ማቅ መሥመር ከያዘ ነው ካልሆነ ግን እንደተለመደው ጳጳሳቱን በጥቅምና በነውር እየከፋፈለ አያሰራቸውም፡፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የያዙት ሥራ ትልቅ ነውና ይበርቱንል፡፡

   Delete
  2. From > 45 Papasat how 1 Aba Matias could be right???????? This is true in Catholic church where the Pop is KIDUS alone. In Orthodox the top kidus is the Synodos. Yigbachu!!!!!!

   Delete
 8. በውቤ የደነቆረ ውቤ ውቤ እንዳለ ሞተ ተብሎ እንደሚነገረው ሆኖ ማኅበረ ቅዱሳን ዕኩይ ዓላማህን አውቆ ከአሁን በፊት በቤተክረስቲያን ላይ ከሠራኸው ክፉ ድርጊት በተጨማሪ ዛሬ እንዳታደርግ እንቅፋት ሆኖብህ በህልምም በእውንም ያህንን ያደረገብኝ ማኅበረ ቅዱሳን ነው እያልክ ከማሰብህ የመጣብህ ችግር ካልሆነ ባነሳኸው ነጥብ ዙሪያ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ ነገር የለም፡፡ እውነትን መደበቅ አይቻልም፡፡ ለእውነት ጠላት የሚሆን አካል የበለጠ ይጎዳል፡፡ ስለዚህ ራህን አስተካከል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ኑር፡፡
  እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 9. ኧረ ገና፤ ገና ምን ታየና የሰው ልጆች ኩነኔን ሳይረዱ ጽድቅን እናውቃለን እያሉ
  በማያገባቸው ጥልቅ እያሉ ስም እየተሰጣጡ እንደ እሥሥት ሲለዋዎጡ እንዳሳ ሲገላበጡ ለነፍስ ይቅርና ለሥጋ ሰላምን እንዳጡ እስከዘመናችን ደርሰዋል።ከዚህ የከፋ
  አያምጣ ምክንያቱም ይህ መከፋፈልና ራስን ማጽደቅ ባለንጀራን መናቅ በፊትም የነበረ
  ነውና በነገር ደረጃ ካራ ቅባት ጸጋ ባካል ደረጃ ደቂቀ እስጢፋኖስ ደቂቀ ኤዎስጣቴዎስ ደቂቀ ተክለ ሀይማኖት እየተባባሉ በመሠየምና በመሠያየም ደም እንደ ወሀ ሲፋሰሱ ኖረዋል። አሁንም ትውልዱ እኔ እበልጥ እኔ እሻል እያለ በነገር መዳማቱን ቀጥሎበታል። ይህ ምንም አይደል፤ የባሰ አያምጣ ማለት ተራራው ተንዶ በተጫነን መሬቱ ተከፍቶ በዋጠን ከሚባልበት ጊዜ እንዳንደርስ ክፋትን መቀንስ መልካም ይሆናል ያውም ለመዋል ለማደር ለመሰንበት ነው።ከዚህ ውጭ ማንም ተመጻዳቂ ከምንም አይደርስም።

  ReplyDelete
 10. አይ አባ ሠላማዎች ይቅርታ እናንተ መጠሪያ አደረጋችሁት እንጂ ሲጀመር የተጠቀሱት አባት አባ ሠላማ እንደናንተ ላለዉ አዲስ የክህደት ወንጌል ለመስበክ ህይወታቸዉን የሠጡ አልነበሩም፡፡ አንድ እዉነት እንነጋገር እና አቡነ ማትያስንም ጠጋ ማለታችሁ በድክመታቸዉ ገብታችሁ አላማ ለማሳት መሆኑን ስጋችሁ ታዉሮ ባይመሰክርባችሁም እዉነታዉን ግን አታዉቁትም ማለት አልችልም፡፡ትእቢተኞች እና ተንኮለኞች ናችሁ ይህንንም ከፍሬያችሁ እያየነዉ ነዉ፡፡ እዉነት ምእመናን ከቤተክርስቲያን መኮብለላቸዉ እናንተን ያሳሰበ ጉዳይ ነዉ?እናንተ የመኮብለሉን መንገድ ያሳያችሁ ኮብላዬች አይደላችሁ እንዴ?ይብላኝ ለናንተ አሁንስ የትንቢት ጊዜ ሆኖ ልቦናችሁ እንደፈርኦን ደንድኖ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ላሰናከላችሁ ለእናንተ አዝናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 11. የከለባት ስብስብ ሁሉ! በየ ብሎጉ ተደብቀህ ጨፍር! የማትታወቁ ከመሰላችሁ ደግሞ ተሳስታችኋል፡፡ ለቤተ ክርስቲያኖቷ በምንም መልኩ የማትጠቅሟት መሆናችሁን በጊዜ ሂደት ታወቀባችሁ፡፡ ነቄው ማኅበረ ቅዱሳን በጊዜው ማንነታችሁን እያጋለጠ መሯሯጫ ሜዳችሁን አጠበባችሁ፡፡ የቤተ ክርስቲያን መድረክ ለሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ እንደማይመች በሂደት ስትረዱ ወደብሎግ ላይ ጽሑፍ ገባችሁ፡፡ ገጽ ለገጽ መድረክ ላይ ሆኖ ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ አጀንዳ አራምዳለሁ ማለት እየነደደ ያለን እሳት በምላስ ለመላስ ሙከራ እደማድረግ ነው፡፡
  የቤተ ክርስቲያን መድረክ ከአሁን በኋላ ለናንተ ለሐራ ጥቃውያን ተላልፎ እንደማይሰጥ ከዚህ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይሆን እኛ ምዕመናን እንፋረዳችኋላን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ማፍረስ አይደለም፤ ጫፉን ንኩና የዛን ጊዜ መውደቂያህ ከወዴት እንኳ እንደሆነ ሳታውቅ ላታንሰራራ ትወድቃለ፡፡ የምትወድቀው ደግሞ ብቻህን ከመሰለህ ተሳስተሃል፡፡ ሜዳውን ካመቻቸልህ ከዚህ ሙሰኛና ተው ሲባል ከማይሰማ ፓርቲህ ጋር ይሆናል፡፡ ሀገሪቷን እኔ ብቻ ልምራትና ልቦጥቡጣት እንዲሁም ቤተክርስቲያኒቷን እያለ ነው፡፡ የእነሱ ጀሌዎች እንደሆናችሁና ጊዜ አልፎ ተራው ለሌላው እንደሚደርስ እንኳን ለአፍታ አታስቡም፡፡
  ይሄ ገዢ ፓርቲ እራሱ የተነካ ቢሆን ኖሮ “ሀገርን በመክዳትና በማሴር” በሚል ሰበብና አስባብ ፈልጎ ይቀፈድድህ ነበር፡፡ ግን የሚፈልገውን እያደረጋችሁለት ስለሆነ በየመድረኩ ቤተክርስቲያኒቷን የሚያጥላላ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደብ እንደናንተ ሐራ ጥቃ/ተሐድሶ/ ሳይውል ሳያድር ሹመት ያገኛል፡፡ ዋናው ምሳሌዬ የማነ ብርሃን ከጋዜጠኝነት እያክለፈለፈ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት እንደመጣ ሳይ ይገርመኛል፡፡ ሁሌም ይደንቀኛል፡፡ አሁንም “የማኅበረ ቅዱሳን አባል ነህ” በሉኛ፡፡ አይገርመኝም፡፡ ስም መለጠፍ የግብር ስለሆነ፡፡
  ንሰሐ ግቡ፣ ተመለሱ፣ ቤተክርስቲያኒቷ ጥሩ የንሰሐና የቀኖና ስርዓት ባለቤት ነች፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለበዪ አመቻችታችሁ አትስጧት፡፡ በርካታ ሥራ ያለባት ነች! “ካፈርኩኝ አይመልሰኝ” ዓይነት ነገር በክርስትና አይሰራም፡፡ ጊዜ የለም መመለስ ነው! ለዛ ደግሞ እንዲያበቃችሁ አባሰላማዎች የሁል ጊዜ ጸሎቴ ነው፡፡

  ReplyDelete