Wednesday, March 23, 2016

ሰበር ዜና - ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም ሊነግድበትና ሊያትርፍበት አስቦ ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ በ11ኛው ሰዓት ላይ ታገደበትበሕገ ወጥ መንገድ መጓዙን የቀጠለውና ቤተክርስቲያንንና ዕሴቶቿን ማትረፊያ አድርጎ እየተጠቀመባት ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማኅበሩና ለግል ጥቅማቸው በቆሙ አንዳንድ ጥቅመኛ ጳጳሳት በመደገፍ ፈቃድ ጠይቆበት የነበረው ዐውደ ርእይ በ11ኛው ሰዓት ላይ ዛሬ መታገዱ ተሰማ፡፡ ማኅበሩ የቅዱስ ፓትርያርኩን መመሪያ ላለመቀበል ወስኖ በትዕቢትና በማንአለብኝነት እየተንቀሳቀሰ ባለበት በዚህ ወቅት ዓውደ ርእዩ ሊታገድ እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነበር፡፡ እንደተጠበቀውም አውደ ርእዩን ማካሄድ እንደማይችል ከኤግዚቢሽን ማእከል የተጻፈለት ደብዳቤ ጠቁሟል፡፡ የደብዳቤው ሙሉ ቃል እነሆ

                                                                                          ቁጥር ኤማ/ 1089-520-21/08 
                                                                                          ቀን 14/08/2008
በኢ//// የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለማኅበረ ቅዱሳን /ቤት
ጉዳዩ፣ በነገው ዕለት የሚከፈተው ኤግዚቢሽን መሰረዙን ስለ ማሳወቅ
በኢግዚቢሽን ማዕከልና በማኅበረ ቅዱሳን /ቤት መካከል በተፈጸመው ውለታ መሠረት የጽ/ቤቱ ኤግዚቢሽን በነገው ዕለት እንደሚከፈት ይታወቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ያልተሟላ በመኾኑ በታሰበው መልኩ ዝግጅቱን ለማካሄድ አስቸጋሪ ኾኖ ተገኝቷል፡፡ ለተፈጠረው ክፍተትም ኤግዚቢሽን ማዕከሉ አዘጋጆቹንና ተሳታፊዎችን ከፍተኛ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ 

በቀጣይ አስፈላጊ የኾኑ ፈቃዶች ሁሉ ሲሟሉ ተለዋጭ ፕሮግራም በማዘጋጀት አስፈላጊውን አገልግሎት ሁሉ እንደምንሰጥም በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

(
የማይነበብ ፊርማ)
ታምራት አድማስ
ዋና ሥራ አስኪያጅ
ማኅበረ ቅዱሳን በሌለው ሥልጣንና ውክልና የቤተ ክህነት መምሪያዎችን የሥራ ድርሻ በመንጠቅ ሲያዘጋጃቸውና ዳጎስ ያለ ገቢ ሊሰበስብባቸው ዐቅዷቸው የነበሩ መሰል ዝግጅቶች ሲታገዱበት የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ሆኖም እስካሁን ማኅበሩ ቆም ብሎ ራሱን ከማየትና አካሄዱን ከማስተካከል ይልቅ ጡንቻዬ ፈርጥሟል ማንም አያስቆመኝም በሚል በሕገወጥ አካሄዱ ገፍቶበት ይገኛል፡፡ የአውደ ርእዩ መታገድ ቅዱስ ፓትርያርኩ በማኅበሩ ላይ የያዙት አቋም የማይለወጥና ጠንካራ መሆኑን፣ እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ፣ መንፈሳውያን ኮሌጆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት ሃላፊዎች ሁሉ የያዙት ተመሳሳይ አቋም መሆኑን ያሳያል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗን ከማኅበሩ ስውር አመራሮችና ከቤተክህነቱ እየጎረሱ ወደማህበሩ የሚውጡ ከተባሉት የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣትና በቅንነት የማኅበሩ አባል ሆነው እያገለገሉ ያሉትን የዋሃን አባላቱን በትክክለኛው መስመር በማስኬድ ለአንድ ማኅበር ሳይሆን ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙበትን መንገድ ለመፈለግ እየተደረገ ያለውን ጥረት መደገፍ ከሁሉም የሚጠበቅ ነው፡፡

55 comments:

 1. ቅድሙንም ማህበሩ ቅዱስ ፓትርያርኩን ሽቅብ ማየት ሲጀምር እና ከእግራቸው ስር ቁጭ ብዬ እያለ የሚሸቅልባቸውን አባቶች ይቅርታ ለመጠየቅ ጉሮሮውን ሲያንቀው ከዚህ ያነሰ ነገር ምን ይጠበቅ ነበር። አሁንም ቢማርበት ይሻለዋል።

  ReplyDelete
 2. የአምበሳ ልጅ ሞቶ የጅብ ልጅ ገነነ…
  አባ ሰላማዎች ክስና ተንኮል ጥልቅ ከሆነው መዝገቡ ክፉው መንፈስ ያጎናጸፋችሁ መሆኑን እናንትም ቢሆን የምታጡት አይመስለኝም፡፡
  ዐውደ ርእዩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ድርሻቸውን ዐውቀው በተሰጣቸው ጸጋ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የማነቃቃት ዓላማ ነበረው፡፡ በተለይ በሰፊው ማሳ ላይ እንደ አረም የበቀላችሁ እንደ እንክርዳድ የተሰገሰጋችሁ እናንተንና መሰሎቻችሁን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ነቅሎ ለማውጣት ምንያህል ሊያግዝ እንደሚችል ከማንም በላይ ታውቁታላችሁ፡፡
  የአምበሳ ልጅ ሞቶ የጅብ ልጅ ገነነ እንደተባለው
  ኦርቶዶክሳውያንን መግፋት ባዕዳንን ማንሰራፋት በግራና በቀኝ ዙፋን ላይ ያሉት የሁለቱም ቁልፍ ዓላማ ይመስላል፡፡
  ይህ የማይታሠረውን ቃለ እግዚአብሔር ለማሠር መሞከር ግን ትርፉ ከንቱ ድካም ብቻ ይሆናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን "የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሠርም" ፪ጢሞ ፪፥፱። ለዚህ ደግሞ ምንም ዓይነት ቦታ የለንም፡፡ በዚህ ቢታገድ እግዚአብሔር በወጀብ እና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው እና በሚከፍትበት ይከፍተዋል፡፡ ቅስማችንን ለመስበር ታስቦ ከኾነ ያበረታናል እንጂ አንገታችንን እንደማንደፋ እልፍ ጊዜ እልፍ ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ "ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝ" ያለውን እያሰብን ከድካም ወደብርታት ከምንሸጋገር በቀር ከዓላማችን ዝንፍ አንልም፡፡ ፪ቆሮ ፲፪፥፲።

  የሚኾነውን ባናውቅም የታሰበውን እናውቃለንና አንደነግጥም፡፡ አሁንም ግን ሥራችንን በቅንነት እንቀጥላለን፡፡ በዚህ ጉዳይ ሀዘን የሚሰማችሁ ወንድሞች እና እኅቶች በማዘን ሰይጣንን እና ተልእኮ አስፈጻሚውን ከማስደሰት ይልቅ በተሻለ ሥራ እና መንፈሳዊ ቆራጥነት ወደፊት እንጋደል፡፡ ከዚህም የሚበልጥ መከራ ቢመጣ ወደ ኋላ አንመለስምና፡፡ እንባችንን የሚያብሰውን እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ እንደበረታን እንቁም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አምበሳ ልጅ ሞቶ የጅብ ልጅ ገነነ that is perfect example
   but the problem is who is የአምበሳ ልጅ and who is የጅብ ልጅ
   as far as i know MK is የጅብ ልጅ
   let alone our holy fathers who died to save EOTC even when we compare the holy synod they deserve to be የአምበሳ ልጅ but you consider them as if they don't exist. When you call all those believers to tell them that their holy fathers are not doing good for the church and trying to mobilize them against their fathers. Please stop and think clearly and respect the authority of the church

   Delete
 3. Mk anchi yebetekeretiyan lijoche gubae eyasagedesh yemeteserwe betebeta ena huket meleso anchin segerfe semetun ewwkiwe

  ReplyDelete
 4. ለናንተማ ትልቅ የምስራች ነዉ ደስ ይበላችሁ//// ሠይጣንን ማስደሰት ቀላል ነዉ ነገር ግን ምድራዊ ደስታ ከወሬ አያልፍም ///

  ReplyDelete
 5. ደስስስስስስስስስስ ሲል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተንሥእ ፡ እግዚኦ ፡ አፅምእ ፡ ፍትሕየ፤
   አምላኪየ ፡ ወእግዚእየ ፡ ውስተ ፡ ቅሥትየ ።
   ".....
   ወኢይበሉ ፡ በልቦሙ ፡ እንቋዕ ፡ እንቋዕ ፡ ላዕለ ፡ ነፍስየ፤
   ወኢይበሉ ፡ ውኅጥናሁ:: ....
   በልባቸው፦ እሰይ እሰይ፥ ነፍሳችንን ደስ አላት አይበሉ፤
   ደግሞም፦ ዋጥነው አይበሉ::"
   መዝሙረ ዳዊት(34/35፥25)

   Delete
 6. mechem melikam neger yemayasidesitew man lihon indemichil yitaweqal

  ReplyDelete
 7. yewengel telat mehon ye egziyabiher telat mehon new , yeh degmo lezi yedaregal

  ReplyDelete
 8. አባቶች ዲያብሎስ በነበረበት ጊዜ የነረውን ሁኔታ በምሳሌ ሲነግሩን ወደ መቀመቅ እየወረደ እግዚአብሔር ሰማዩን ጠቅለሎ ሸሸ ይል ነበር ይላሉ፡፡ የዚህ የቦታ መከልከልን ከቅዱስነታቸው ጋር የምታገናኙ ከሆነ እና በመቅረቱ ደስታችሁን እየገለፃችሁ ከሆነ ሽንፈቱ የማኅበሩ ሳይሆን መልካም ነገርን የምትቃወሙ የእናንተ ነው፡፡ ምክንያቱም እውነቱ የት እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ቅዱስነታቸውንም ከእናንተ ጋር አታካቱ፡፡
  ስለዚህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ ከእውነት እትታገሉ፡፡ እውነት አንድ ቀን ማሸነፏ ስለማይቀር ብትስተካከሉ ይሻላችኋል፡፡ ያን ቀን በምድርም በሰማይም ራሳችሁን መውቀሳችሁ አይቀርም፡፡
  እግዚአብሔር በእውነት መንገድ ይምራችሁ፡፡

  ReplyDelete
 9. እኔ በበኩል የሄ የሚሳየኝ የማኅበረ ቅዱሳን ብርሃናችሁን ለመጋረድ አጋንንት ምን ያህል እየተጋ እንደሆነ ነው
  ስለዚህ ደስ ይበላችሁ እንጂ አትዘኑ፡ ሁሌም ቢሆን እውነት ሳትፈተን የቀረችበት ጊዜ የለም

  ReplyDelete
 10. SEYXAN DESS BILEWUM LEGIZEW NEW, HUALA LEZELALEM MAZENU AYQER; YE EGZI'ABHER LIJOCH BIYAZIMUN LEGIZEW NEW, HUALA LEZELALEM MEDDESSETACHEW AYQERIM!

  ReplyDelete
 11. Yetehadiso sera serana teleko megaletu selemayker awdereyu yketilal lehizb kift yhonal!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 12. ለመሆኑ ቤተክርስቲያን ትላንት ማን ናት ዛሬስ?? ሀሳቡ በራሱ ልክ አልነበረም፡፡
  ማህበረ ቅዱሳን በሸገር ስፖርት 102 አበበ ግዴይ ላይ ፣ በብስራት ስፖርት 101 መንሱር አብዱል ቀኒ ላይ መሰለ መንግስቱ ላይ ...ብቻ ምን አለፋችሁ በሚችሉት ሁሉ ማስታወቂያ ቢነገርም ታገደ፡፡
  የቤተክርስቲያኗን ስርዓት ማክበር ግድ ነው፡፡
  አንድ ቤተክርስቲያን እንጂ ሌላ ማህበር ሊኖር አይገባም፡፡
  ለሚመሩን አባቶች መታዘዝ ግድ ነው ፡፡ በመመርያ መመራት ግድ ነው

  ReplyDelete
 13. ትዕቢትና ኩራት ውሎ አድሮ አንዲ ይከፍላል፤ አዉንም አልተማራችዉም????? ህዝቡን በማታዉቁት ትምህረት ለማዶንቆር ስትተጉ እግዚኣብሔር ጣልቃ ገባ ሓይማኖት ጠንቅቁ …….. ምናምን አቤት አቤት አቤት ወጉስ መረጉስ፤ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ቂሮስ ናቸዉ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ መዉጫዉ ደርሷል…… ለውጥ፣ ለውጥ፣ ለውጥ፣ ተሓድሶ፣ ተሓድሶ ፣ ተሓድሶ ፣ ተሓድሶ ፣ ተሓድሶ እንፈልጋለን፤ ተረት ይብቃ ሰዉ አይለውጥም፤ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን ቢቻዉን ማዳን የበጉ ነዉና፣  ReplyDelete
  Replies
  1. ቅዱስነታቸው ተሃዲሶ…ተሃድሶ … ተሃድሶ እያሉ ነው እያልክ ነው

   Delete
  2. ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/ታሃድሶ/ፔንቴኮስቴ/…….. ብትል አይሻልህም ቤተክርስቲያናችን የተሀድሶና ፔንቴኮስቴ ዓለማዊ ዝተት የመሸከም ጫንቃ የላትም፤ ዛሬ ያጎነበሰች ብትመስልም ምርጥ ልጆቿ እንደምንግዚው ይታደጓታል እንጂ እናንተ ከነዝትታችሁ (ስግብግብነት፤ዝሙት ገንዘብ እና ራስ ወዳድነታችሁ…) ወደ ቤተክርስቲያንችን እንድትገቡ ማን ይፈቅድላችኋል፡፡ ያማትታወቁበት ሀገር ሄዳችሁ ቁርበት አስነጥፉ፡፡ እሺ

   Delete
 14. "Addisu Mulugeta" ነኝ ያልከው አንተ ደግሞ ማነህ ራስን ኦርቶዶክስ ሌላውን ባዕድ፣ ራስህን የአንበሳ ልጅ፡ ሌላውን የጅብ ልጅ እያልክ የምትሳደበው? በእናንተና በመንበረ ፓትርያርኩ መካከል የሚካሄደውን ሁሉ እየተከታተልን ነው፡፡ አንተና መሰሎችህ በየትኛውም መለኪያ ኦርቶዶክስ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ ይህ ማቅ የምትሉት የንግድ ድርጅት በብሎጉ ቅዱስ ፓትርያርኩን "ካድሬ" ብሎ በድፍረት ተሳድቧል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ መሳደብና ማዋረድ ቤተ ክርስቲያኒቱን ማዋረድ ነው፡ ምእመናንዋን መናቅ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ የመሰለ ብልሹ ምግባር ያላቸውን ልጆች አልወለደችም፡ እናታችሁን ሌላ ቦታ ፈልጉ፡፡

  አሁን ለእኩይ ዓላማችሁ ያቀነባበራችሁት "ዓውደ ርእይ" ታገደ ብላችሁ ትንጨረጨራላችሁ፡፡ እንዲያውም ለእናንተ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለማትገዙ ሕገ ወጥ ትዕቢተኞች ጠቅላይ ቤተ ክህነቱና የቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት እጅግ ታግሠዋል፡፡ ከዚህ የጠነከረ ርምጃ መውሰድ ይችሉ ነበር፡፡ መብቱም ሥልጣኑም አላቸው፡፡ እናንተን በቅንነትና በየውሃት የሚከተሉ ወደ ጥፋት የምትመሩአቸው ብዙኃን አሉና ለእነርሱ እግዚአብሔር የሚያስተውል ልቦና ይስጣቸው፡፡

  ከታዛቢ ምእመናን አንዱ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Egziabher Endate yalutin yemenafist agelgayouch yabirdialachihu!

   Delete
  2. የታገደችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን አይደለም!
   ኤግዚቢሽን ማዕከሉን የጠየቀው ማን ነው? ቅድስት ቤተክርስቲያን አይደለችም?
   ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም በቁጥር 4944/8613/07 ጠቅላይ ቤተክህነት እንደጠየቀ አልሰማችሁ ይሆን? በእርግጥ "ዐውቆ የተኛን…" እንደሚባለው ጆሯችሁ ዕውነትን ለማስተናገድ የሚሆን ለምልክት እንኳን ምንም ጭላንጭል እንደሌለው እናውቃለን፡፡ ደብዳቤው ግን እንዲህ ይነበባል፡፡
   ". . . ከዚህ በፊት እንደተለመደው ሁሉ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እየጠየቅን ለሚደረግልን መልካም ትብብርም በቅድሚያ ምስጋና እናቀርባለን፡፡"
   ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ይህን ደብዳቤ መጻፉ የማኅበሩን ሕጋዊ አካሄድ ያመለክታል፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ጉዳዩን ተቀብሎ እና አምኖበት የማኅበሩ ጉዳይ ብቻ ሳይኾን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጉዳይ ነው ብሎ ጥያቄውን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም አቅርቧል፡፡ የማኅበሩን ዐቅድ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከማጽደቁም በላይ ይሁንታውን እና ፈቃዱን አክሎበት ለሦስተኛ ወገን ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ተገብቶ ፈቃድ ጠያቂ ኾኖ ደብዳቤ መጻፉ ሊሠመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ጉዳዩ የአንድ ማኅበር ብቻ ሳይኾን ኩላዊት፣ ሐዋርያዊት የኾነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደተደረገ ከዚህ እንረዳለን፡፡
   ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በጻፈው ደብዳቤ መነሻነት ምንም ይደረግ ምን የውጤቱ ተቀባይ እና ባለቤት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ነው፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሥራ ይመራል ተብሎ ተደንግጓልና፡፡
   ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለቤትነቱን ወስዳ በተገቢው መንገድ የተጓዘችለት ዐውደ ርእይ ሲታገድ ለእኔ የታገደችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይኽንን ታሪካዊ ስህተት በእርሷ ላይ መሥራት ከጤናማነት አይቀዳም፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ሁለመናዋ ናትና፡፡ አንድ ማኅበርን ያጠቃን የመሰላችሁ ሁሉ እየተጋቻችሁ ያላችሁት ከታላቋ ከብሔራዊትም በላይ ዓለማቀፋዊት ከኾነቸው ቤተ ክርስቲያን ጋር እንደኾነ ካልተረዳችሁት ብትረዱት መልካም ነው፡፡ እርሷን ማገድስ ይቻላል ወይ?

   Delete
  3. You 'Aba Selama's are always against Mahibere Kidusan b/s you assume that you rejected by the Ethiopian Orthodox Tewahido (During 2004 E.c Synod assembly)due to Mahibere kidusan.so,you are doing a kind of revenge for that matter.But don't you know that your preaching is like protestants!Please first be Orthodox to talk about the Ethiopian orthodox Tewahido church.Mahibere kidusan didn't say "ካድሬ" for the patriarch but I read a kind of comment on Hara Tewahido.Any Way God Bless Mahibere kidusan!!!!!

   Delete
  4. በብሎጉ ቅዱስ ፓትርያርኩን "ካድሬ" ብሎ በድፍረት ተሳድቧል፡፡ Yalikew sew esti Bezih ken Bezih Gareta kutir woyim Bezih Yehamer etim lay yigegnal bileh tikikilegnawun Minch Nigeregnina Limenih. Zim Bilo Ekele Yihen Ale Yanin ale eyalu mawurat kekentu Hamet ayiwetam.

   Delete
 15. ማቅ መታገድ እንዴት እንደሆነ እዩት ጉድ ነው ዘንድሮ ምንም አልሆነላቸውም።የምታሳድዱት ኢየሱስን እመኑት ግድ ይላችውም

  ReplyDelete
 16. yeshiro dinfata enjera eskineka dires new. Truth lives fore ever.Mahibere kidusan ayizuachihu we are beside you.The difference is visible...between paid and unpaid(MK).
  We will support MK forever as Truth is with Them.

  ReplyDelete
 17. ማህበረ ቅድሳን በቅኖና ቤተክርስቲያን ስርዓት ውስጥ ለአንድም ቅን ትጉዞ የማያውቅ ሲኖዶሳዊ ስርዓትን የሚንድና ሚፈተን ስራ የሚሰራ መዋቅራዊ ጥሰትን የሚፋጽም እራሱን አቅቤ እምነት ዘኦርቶዶክስ አድርጎ ንግድ ላይ የተሰማራ ማህበር ነው።ለማሳየነት ከተሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ማስተማር በዘለለ እራሱን ሲኖዶስ አድርጒ ቤተክርስቲያኒቱን በሚመለከት ገለጻ ይሰጣል ያወግዛል ያጸድቃል።ሲፖዚየም ያዘጋጃል ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ምእመን ከቦታ ቦታ ያንቀሳቅሳል።በቤተክርሰቲያኒቱ ስም አስራት ይሰበስባል በቤተክርስቲያኒቱ ትዩና አቻ ሆኖ የልማት ተቊማትን መምሪያዎችንና ክፍሎችን አቊቁሞ በአቻነት ይንቀሳቀሳል ።ይህ ፍጹም ህገወጥ ተግባርና ኢቀኖናዊ ነው የፓትሪያሪኩ ውሳኔ ፍታዊ ነው።

  ReplyDelete
 18. "በናንተ ላይ ቢደረግባችሁ የማትወዱትን በሌላዉ ላይ አታድርጉ"ማቴ ፯ ፲፪
  ማቆች ኣረ አስተዉሉ ?
  የተባላሁት" ስራት ያዙ ነዉ" ሌላ አይደለም ምክንያት አታብዙ።
  እናንተ የሰዎችን ጉባኤ ስትረብሹና ስትበጠብጡ ስታሳግዱ ነዉ የኖራችሁ ።
  ያንም በማድረጋሽሁ እጅግ እንደምትደሰቱ በብሎጎቻችሁ ስትገልጹ ነዉ የኖራችሁት .አወ እስኪ መቆጥቆጡን ወይም ስሜቱን ቅመሱት ምናልባት የሚያዝን ልብ ቢኖራችሁ "ሀዘነ ዘፈተነ የአምር ሀዘነ" ነዉና ።
  ማቆች ወይ ንስሀ ገብታችሁ ወደ ልባችሁ ተመለሱ
  ቤተ ክርስቲያናን ግራ አታጋᎄት ፤ስለዚህ ተገፋን ለማለት ስበብ አታብዙ "የገፋችሁት እንጂ የገፋችሁ የለም "ለመገንጠል ፈልጋችሁ ከሆነ ስበብ አታብዙ ዝም ብላችሁ ዉጡ።
  እንዴ ሁሉንም ፓትርያርኮች ኮነናችሁ ኮነናችሁ ኮነናችሁ ለናንተ ፓትርያርክ ከሰማይ ሊወርድላችሁ ነዉ?
  አበዛችሁት ይቅርታ አንጠይቅም ያላችሁ ጀግኖች ናችሁ
  ክርስትና እንዲህ ነዉ??

  ReplyDelete
 19. ብዙ ምርምር የሚያስፈልገው አይደለም የአማሳኞቹና የሃራጥቃዎቹ የሠረቀ ብርሃን፣የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስና መሰሎቻቸው ሴራ ነው።ከዘላለማዊው ይልቅ ነገ ጠፊ በሆነው ወያኔ የተመኩ ለወያኔም ጠላት እያበዙለት ያሉ።

  ReplyDelete

 20. (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 3)

  እነዚህ በጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3 ትንቢት የተነገረባቸው አና ማን
  እንደሆኑ የሚያውቅ ካለ ቢነግረኝ ደስ ይለኛል።

  ----------
  1፤ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።

  2፤ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥

  3፤ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
  (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 3)
  ----------
  4፤ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤

  5፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

  6-7፤ ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።

  ReplyDelete
 21. አባ ሰላማዎች

  እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ለረጅም ጊዜ ስትመኙት የኖራችሁት እና በየቦታው ያሉ ተከታዮቻችሁን አውደርእዩ በሚቻለው ሁሉ የሚታገድበትን መንገድ ስታፈላልጉ ነበር። ይኸው ሆነላችሁ። ደስ ይበላችሁ!!!

  ብሎጋችሁን ከከፈታችሁ ጅምሮ ማቅ እያላችሁ የምትጠሩትን ማኅበር አቅማችሁ በፈቀደላችሁ መጠን ስታወግዙ፣ ስትሳደቡ ፣ ማህበሩ የሚሰራውን ሁሉ የስይጣን ስራ እንደሆነ ስትለፍፉ ቆይታችሗል።

  ብሎጋችሁ ላይ

  "እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።"

  ይላል።


  ማቅ ብላችሁ የምትጠሩት ማህበር በተመለከተ የሚወጡ ጽሁፎች እና አስተያየቶች ላይ ግን ይህ መመሪያችሁ ለምን አልሰራ አለ? እባካችሁ ስለ አባ ሰላማ ብሎግ ብላችሁ የጻፋችሁን ጽሁፍ ከአላማችሁ እና ድርጊታችሁን በትክክል ስለማይገልጽ ቀይሩት።

  እስከዛሬ ካነበብኳችው ጽሁፎቻችሁ እንደተረዳሁት አላማችሁ ማቅ ብላችሁ የምትጠሩትን ማህበር ማውገዝ ማብጠልጠል መሳደብ ወዘተ እና በተቻለ መጠን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖችን ሃሳብ መደገፍ ማበረታታት ነው። ጽሁፎቹ ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩት ብሎጓ የተቁቋመችው "ሚዛናዊ" አመለካከት ለማንጸባረቅ ሳይሆን ለስድብ ነው። ስድብ እና በውሸት ሌላውን ለመክሰስ መሯሯጥ የክርስትና ጸባይ ሆነው አያውቁም። ሊሆኑም አይችሉም።

  ReplyDelete
 22. MK has a theory of isolation. It tries to isolate the patriarch from the holy synod. If there is not unity in the holy synod including the patriarch it will be lifeless. God only participates in love and unity. Then Mk will have the power to do as it wishes to take the church to the next level. God knows if that level is upward or downward.

  ReplyDelete
  Replies
  1. How insightful view, my friend!

   Delete
 23. This theory of isolation does not stop in the holy synod. This particular gathering was intended to isolate members of the church from the patriarch. Only in ethiopian orthodox such a thing can happen. An organization can call upon all believers and tell them what they should do about their church. It is like children revolting against their parents and take over over all administration of the family. That is a disaster unfolding.

  ReplyDelete
 24. ግድ የለም ጎልያድ ተሃድሶ መናፍቅ ብትፎክርም ልበአምላክ ዳዊት ይነሳል በአንድ ጠጠር ድራሻቹህ ይጠፋል ደግሞ እወቁት የፈለገ ያህል ብትቋምጡ ምንም አታመጡም መንጋ የአሪዎስ ርዝራዥ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳን ገና ለዘመናት ያንቀጠቅጣቹሃል ።

  ReplyDelete
 25. YEFUCHET MEMHIRU EBDU ABAMATEWOS 3 AMETATIN YALEMENFESAWI SIRA BETEKHNETUN SIREBESH KEBETEKIHNETU DEMEWZ EYEBELA LEMAHBERE Monky DIGAF BICHA SIYADERGNA KEAKMU BELAY SINTERARA WIRDETU EYETESHEKEME KOYTEWAL ABAMATEWO BEYETIGNAW KRISTINAH AZAGN HONKINA YEMETSIHAF LEBAWIN YEMAK MK MELIEKTEGNAWN LEBAWIN DESTA ENDAYKESES YELIJOCH ABAT SILEHONE AYKESESIM ALK ENDIH BEMALET HAFRET TILEBSALEH INJI LEBA TEYIZO DULA AYTEYEKM YIH METFO SIRA BEGOJAM LIJOCH TESRTO BIHON ABAMATEWOS ERASIH TEBEKA HONEH TIKES NEBER MATEWOS TEKLAY SIRA ASKIYAJ LANTENEW ANBIBEW KKĶK

  ReplyDelete
 26. enanet yebatea krestyne telate dase ayebalachu egezabeher mengede alwe tenshe tabeku

  ReplyDelete
 27. አንተም ክፉ ነበርክ ክፉ አዘዘብህ ቤተክርስቲያን ከማቅ ነጻ ትውጣ ዞር በል ከመንግድዋ ደንቃራ ማህበር ትንሽ ህፍረትና ቅንነት የሌለህ አጉል ቤተክርስቲን ተቆርቋሪ መሳይ ጥቅመኛ ቤተክርስቲንን እንኳን አንተ 25 አመት ፍንዳታ ሌላም ሌላም አላሸነፋትም 3000ሺ ዘመናትን ዘልቃለች ወደፊትም እስከ አለም መጨረሻ ተከብራ ትኖራለች በፍንዳታና በምቀኞች ተፈትና አትቀርም ታሸንፋለች ውረድላት ከጫንቃዋ አባቶችን አትስደብ የተሸሙት ከእግዚብያሄር ነውና የአባቶች በረከት ይደርብን አሜን !!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  2. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  3. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  4. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  5. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  6. ጽፈህ ሞተሀል ርካሽ ባንዳ፡፡ ተሐድሶ መቀበሪያህ ይሆናል፡፡

   Delete
  7. አንተ መፈክር አደረከው እኮ ለካ እንዲህ ያናድዳል አሁን የተጻፈው ምኑ ተሀድሶ ይመስላል ቀዠት ሆነብህ ይሄ ተሃድሶ የሚሉት አንተ በፈጠርከው ሰለቤተክርስቲያን እናስብ ማህበሩ ራሱን ይመርምር ስርአት ይያዝ አባቶችን አይሳደብ አሉባልታ የሚነዙ አባላቱን አደብ ያስገዛ ንግግራቸው ሁሉ መስመር የለቀቀ ነው አባላቱን መክሮ መመለስ የቻለ አልመሰለኝም በጉልበት በማን አለብኝነት እንዲጓዙ መፍቀድ ለበትም አሉ ወሬ አባቶች ከሀዋርያት ተቀብለው ያቆዩአትን በትርምስ አትክተቱአት ህዝቡ ሀኪሙ ፈዋሹ ቤተክርስቲን ናት እባካችሁ በምትወዱት ሁሉ ተለመኑ በወሬና በምቀኝነት ፈተና አትሁኑ አግዚቤሄር ቤተክርቲየንን ኢትዮጵንና ህዘቧን የባርክ አሜን!!!!!

   Delete
 28. What goes around comes around.
  Beseferut kuna mesefer aykerim .yemit mejemeriya new mechem gif endeseru aynoru.yeseytan mahber.sewachewo moltowal.

  ReplyDelete
 29. በቅድሚያ ማህበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያንን ልእልና ደፍቆ በላይዋ ላይ ሌላ መዋቅር የዘረጋ ሰይጣናዊ ማህበር መሆኑን ብዙ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን ያልተረዱት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ማህበሩ በቤተ ክርስተያን ውስጥ ሊይዝ የሚገባውን ህጋዊ እና መንፈሳዊ መሰረት ምን ምን ሊሆን እንደሚገባው ለተከታዮቿ ማስተማር ማሳወቅ የቤተ ክርስቲያኒቱ ግዴታ ነበር አልተደረገም፡፡ ይህም የማህበሩ ጥቅም እንዲጠበቅ በሚሰሩ የሲኖዶስ አባለት ትብብር የተደረገ ፤አነርሱም አብዝተው ለማህበሩ በሚሰጡት ድጋፍ የተነሳ ነው፡፡ በእውነቱ እነዚህ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ያልገባቸው፣ በገቡት ቃል ኪዳን መሰረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ እና መንጋው ጠበቃ መሆንና መሥራት ያልቻሉ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ሳይሆን በግብታዊነት የጵጵስና ሹመት የተቀበሉ ናቸው፡፡ ያሳዝናል!!!!
  የማህበሩ አመራሮች ዛሬም የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ነን እያሉ ከማዕከላዊ አሰራር ውጭ ተሀድሶ ወረረን ፣ ገዳማት ተቃጠሉ፣ መምህራን ተሰደዱ ወዘተ.. በሚል ማደናገሪያ የዋሑን ምእመን ይነዱታል፣ ገንዘቡን ይዘርፉታል፣ለአመጽም ያነሳሱታል፡፡ እነርሱ የሚነዱት ምእመን በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች በእውነትና በፍቅር ተይዞ ቢሆን ቤተ ክርሲቲያን የት በደረሰች ነበር ፡፡
  አሁን ፓትርያርክ ማትያስ ማህበሩን ሕጋዊ እና መንፈሳዊ መሰረት ለማስያዝ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ ትክክል ቢሆንም በሚመሯት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና እና ሰይጣናዊ አሰራር ሊነኩት ስላልፈለጉ ግን ዘረኝነታቸው ከፓትያርክ ጳውሎስ የከፋ ነው፡፡ እስቲበእውነት ለቤተ ክርስቲያን ከተቆረቆሩ የማህበሩን ኤግዚቪሽን እንዳሳገዱት በታማሚ ልጁ ስም ከየአድባራቱ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚዘርፈውን የአ/አ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከያዘው ከሁለቱም ሥልጣኑ ያግዱት፡፡
  እስቲ በዘረፋና በዝሙት ሥራ ተጠምደው ካሉት በመቶዎች ከሚቆጠሩ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች…… ቢያንስ በተጨባጭ ማስረጃ የርኩሰት ሥቸውን ከሚያውቁት መካከል ሁለት ሶሰቱ ላይ እርምጃ ይውሰዱ እና ምእመኑን ያስደስቱ፡፡ አያደርጉትም እንጂ!! ኔትወርኩ አይነኬ ነውና፡፡
  በአንድ ወቅት የደርግ ባለሥልጣን የነበሩ ኮሎኔል ኢሀዲግ አ/አ ሳይገባ ከድተው ከውጭ ጋዤጠኛ ሲጠይቃቸው የመለሱት መልስ ለዚህ አስተያየቴ መደምደሚያ ይሁን ፡፡ የተጠየቁት ስለ ደርግም ስለ ኢሀዴግም የተሸለው ነገር እንዲናገሩ ነበር ፡- እሳቸው ሲናገሩ ግን ‹ሁለቱንም በሁለት እጆቼ እዋጋቸዋለሁ› ነበር ያሉት ፡፡ አሁንም ማህበር ቅዱሳንም ሆነ የፓትርያርኩ አመራር ከበደል ርቀው እና ሁሉም ከጥፋቱ ተመልሶ ለእውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመሥራት ካልተስማሙ ለቤተ ክርስቲያን አይጠቅሙም ሁለቱም በርኩሰት ሥራ የተጠምዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ናቸው፡፡ ለእኛ ለምእመናን የሚያዋጣን ግን የእነርሱን በደል እለት እለት መስማት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍርድ በጸሎት መጠባበቅ ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 30. ጫካን የሚያርም ከዚያው የሚከርም
  አባ ሰላማዎች የ'ዐዋቂ' አጥፊነታችሁ ልክና መልክ ስለሌለው ልብ ይስጣችሁ እንጅ ከእናንተ ጋር መዳረቁ ከንቱ ድካም ሆናል፡፡
  "ደን አይታረምም… ጫካን የሚርም ከዚው ሚከርም" እንዲሉ አበው፡፡

  ReplyDelete
 31. Endew lemin tilefalachihu mahiberu kedmo beyesewu libona awderey keftual adarash mezgat yechalut yesewin lib mezgat aychalachewm yeh blog gin yale tiriter yeprotestant new yeorthodox behon yihe yasazinal enji ayasdesitim.Were animarim wengel enji wengel degimo man zend endale yeadebabay mistir new wey lib yistachihu weyim yedatana yeaberonen ken yistachihu.

  ReplyDelete
 32. We don't miss our mission due to the evil mind ...... Please Mk continues your spiritual services we orthodox are with you

  ReplyDelete
 33. We don't miss our mission due to the evil mind ...... Please Mk continues your spiritual services we orthodox are with you

  ReplyDelete
 34. wey mk mindinachu gin? mk yebetekerestian telat new.

  ReplyDelete
 35. ርዕሳችሁ
  "ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም ሊነግድበትና ሊያትርፍበት………"

  ከዚህ በፊት የፃፋችሁት
  "በመርሐ ግብሩ ላይ ራሱ እንደ ገለፀው አውደ ርእዩን ከ100 ሺህ ሰው በላይ ይጎበኛዋል ብሎ ገምቷል፡፡ ከወዲሁ የቲኬት ሽያጩንም በየንግድ ተቋሞቹ ውስጥና ከቤተክህነት እየጎረሱ ወደማኅበሩ በሚወጡ እንደ ሰአሊተ ምሕረቱ አለቃ ያሉ አንዳንድ ጥቅመኛ የደብር አለቆች አማካይነት አጧጡፎታል፡፡ አውደ ርእዩ ተካሄደም ታገደም ቀደም ብሎ ከወዲሁ መሸጥ ከጀመረው ቲኬት ዳጎስ ያለ ገቢ መሰብሰቡ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ በገቢው በኩል ማኅበሩ ብዙም ሥጋት የለበትም፡፡ ቢያንስ እንደ ነጋዴ የሚያወጣውን ወጪ መሸፈኑ አይቀርም፡፡"

  በአንድ ራስ ሁለት ምላስ። እንደ መርዛም እባብ። ውሸታሞች።

  ReplyDelete
 36. † ማኅበረ ቅዱሳን †
  ጠላት ተራወጠ ተሸበረ ልቡ፣
  አልገናኝ አለው አዕምሮና ቀልቡ።
  ሚይዝ ሚጨብጠው ሚሆነውን አጣ፣
  ማህበረ ቅዱሳን ታጥቆበት ሲመጣ።
  ጠላት መስሎት ነበር ተራ ተርታ ማህበር፣
  መች አወቀውና ማበሩን እንደ ድር።
  ባልተማረ አእምሮ በጭካኔ ስልቱ፣
  በዘቀጠ ሃሳብ በክፉ አንደበቱ።
  በባዶነት ወኔ ባልሰራው ጀግንነት፣
  ትዕቢትን እንደክብር ጫንቃው ተጎናጽፎት፣
  አቤት..አቤት ጠላት ከረመ ሲዶልት ።
  የሃሰት ደብዳቤ በመጻፍ ደከመ፣
  ከዐይኑ እንቅልፍጠፋ ጨጓራው ታመመ።
  ቢጤዎችን ጠራ በዝግ ቤት መከሩ፣
  ፈሪሳውያኑ ተንኮልን አሴሩ።
  የጻሃፍቶች ምክር ያ የሃሰት ሸንጎ፣
  በቀያፋ መንደር በአምስት ኪሎ አድርጎ።
  ጱላጦስ ፊት ሲደርስ መስቀል አደባባይ፣
  ለፍርድ ተሰጠ "አውደ-እርእይ"።
  መርካቶ አክሲዎን ፩ ህንጻ ማስሏቸው፣
  እናፍርሰው አሉ..እንገርስሰው አሉ፣
  ዉሉደ ይሁዳ....... ከሃዲያን ሁሉ፣
  ደቂቀ አርዮስ ሸርን የተሞሉ።
  መች አወቁትና..መች ተረዱትና፣
  ማህበረ ቅዱሳእንክርዳዱን በሰዎች ልቦና፣
  እንደ እሳት መንደዱን ደምቆ እንደፋና።
  እንዴት ያጠፉ ይሆን ከሰው ልብ ከተማ
  "ማህበረ ቅዱሳን ያበራውን ሻማ"
  ሰንበት ተማሪዎች ዛሬ ተነስተናል፣
  ፍሬና እንክርዳዱን ለይተእንክርዳዱን አውቀናል።
  በበጎች በር ተኩላ ከፍተው ለሚያስገቡት፣
  በዝምታ አናልፍም እንደ ቤተ-ክህነት።
  በአባቶቿ ፈንታ ልጆች ተወልደናል፣
  ቅጥሯን ልናስከብር ቃልኪዳን ገብተናል።
  አደራ አለብን የነ አትናቲዎስ፣
  አደራ አለብን የነ ዴዮስቆሮስ።
  በአንደበት ያይደለ በተግባር አይተናል፣
  ማህበረ ቅዱሳን ብዙ አስተምሮናል።


  ××××ምድረ ተሃድሶ ሃራ ጥቃ ሁሉ፣
  አንድ መልክት አለኝ አሁን ልብ በሉ።
  ከደጀ ሰላም ላይ ሁሌም የማንጠፋው፣
  ብንወድቅ ብንነሳም ትተን የማንወጣው።
  የነገው ተተኪ ከስራቸው ያለን ፣
  ማህበረ ቅዱሳን ሰንበት ተማሪ ነን።
  መታሰቢያነቱ - ለኤግዚቢሽን ማዕከሉ ! By Maheder

  ReplyDelete