Saturday, April 30, 2016

ትንሣኤ አንድ ነው፣ ሕይወትም እሱ ነው!ምንጭ፡-http://dejebirhan.blogspot.com/
Read in PDF
ቀልጣፋ ሬስቶራንቶች በቀላሉ የሚስቡን የፈለግነውን ምግብ በምንወደው መንገድ እንድናዝ መንገድ ስለሚከፍቱልን ነው። ጥቂት ካፌዎች ደግሞ ከመቶ በላይ የተለያዩ የቡና ጣዕም እንደሚያቀርቡ በጉራ ይናገራሉ። መኖሪያ ቤቶችና መኪናዎችን ስንገዛ እንኳ የምንፈልገው ምርጫ እንዲያሟላ እንሻለን። በቼኮላት፣ በቫኒላና በእንጆሪ ዓለም ታጥረን መኖር አንፈልግም። ፍላጎት ንጉሥ ነው! እንደግላዊ ፍላጎትህና ምርጫህ የምታገኝበት ሁሉ የተሟላበት ዘመን ነው። የዓይን አምሮትና ፍላጎትን የሚያሟላው ዓለም የእምነት መንገድንም ለዘላለማዊ ሕይወት ይበጃል ያለውን በአማራጭ አቅርቧል።

ታዲያ ለአንተ /ለአንቺ/ ትክክለኛ እምነት የማግኘቱ ሁኔታስ ምን ይመስላል?
ወቀሳ አልባ፣ ብዙ ጫና የሌለውና ይህንን አድርግ አታድርግ እያለ የማያስቸግር ሐይማኖት ብታገኝስ? ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ያውና እዚያ አለ እንደሚሉት ነገር፣ ሃይማኖት እንደሚወዱት አይስክሬም የሚመረጥ ነው እንዴ? እድሜው፣ ሥርዓቱና ደንቡ ስለሚስብህ ይሆን? ወይስ በባለብዙ መንገድ የሕይወትህ ቤዛ ቃል ስለተገባልህ በአንዱ ላይ ተስፋህን ለማኖር?
ትኩረታችንን ለመሳብ የሚሻሙ በርካታ ድምፆች ስላሉ ለምን? ብሎ ነው አንድ ሰው ኢየሱስን ከሌሎች ማለትም ከመሐመድ ወይም ከኮንፊሸየስ፣ ከቡድሐ ወይም ቻርለስ ቴዝ ራስል ወይም ከጆሴፍ እስሚዝ አስበልጦ የሚመርጠው? ዞሮ ዞሮ ሁሉም መንገዶች የሚያደርሱት ወደ መንግስተ ሰማይ አይደለም እንዴ?
 “በኢየሱስ እናምናለንየሚሉቱ ራሳቸው የማዳኑን ተስፋ የሚገልጡበት መንገድ የተለያየ ስለሆነ እንደገበያ ላይ ሸቀጥ ገብተን ድነትን የምንሸምትባቸው አይደሉም።

Thursday, April 28, 2016

ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው ወይስ ለእኛም ጭምር?

Read in PDF

ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፥ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። (ዮሐንስ 19፥26-27)
የዘንድሮው በዓለ ስቅለት ከበዓለ ማርያም ጋር ስለገጠመ ወይም በ21ኛው ቀን ስለዋለ በየማኅበራዊ ድረ ገጹ አንዳንድ ሰዎች በዕለቱ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም? በሚል ጥያቄ እያቀረቡ አንዳንድ ግለሰቦችም ምላሽ ሲሰጡ ነው የሰነበቱት፡፡ ጥያቄው ሊነሣ የቻለው በበዓላት እንደሚደረገው ሁሉ በበዓለ ማርያም በብዛት አይሰገድም የሚለው ወግ ተይዞ ነው፡፡ የእኔ ጥያቄ ግን ከበዓለ ማርያም በዓለ እግዚእ አይበልጥም ወይ? ከበዓል መንፈስ እንውጣና ከማርያምስ የተሰቀለው ኢየሱስ አይበልጥም ወይ? ታዲያ ምነው እርሱንና ለእኛ መዳን የሆነውን ስቅለቱን የምናስብበትን በዓል ዝቅ በማድረግ እርሷንና የእርሷን ወርኃዊ በዓል ከፍ ለማድረግ እንሞክራን? እንዲህ ለማለት የደፈርኩት ጥያቄው ውስጥ ከበዓሉ በስተጀርባ የተሰቀለው ኢየሱስና እናቱ ማርያም ስላሉ ነው፡፡ በበዓላቱ የሚታሰቡት እነርሱ ናቸውና፡፡ ጥያቄ አቅራቢዎቹ በዓለ ማርያምን ለማክበር በሚል በዓለ መስቀልን መሠዋት እንዳለባቸው እያሰቡ ይመስላል፡፡  
ይህን ሁኔታ የፈጠረው ምንድነው? በዋናነት በማርያም ዙሪያ እየተሰጠ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ትምህርት ነው፡፡ ከእነዚህ ትምህርቶች መካከል ከላይ በመግቢያው ላይ የተጠቀሰውና “ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፥ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።” (ዮሐንስ 19፥26-27) የሚለው ጥቅስ የተተረጎመበት መንገድ አንዱ ነው፡፡     

Tuesday, April 26, 2016

የሆሳዕና ስብከት በቆሞስ አባ መዓዛክርስቶስ በየነ
ለዳዊት ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይሁን
ሆሳዕና ለእርሱ
እልልታ ለእርሱ
ጭብጨባ ለእርሱ ይገባዋል።
ጠላት የተሸበረበት ዝማሬ
ጌታ የከበረበት ዝማሬ ነው።
ቆሞስ አባ መዓዛክርስቶስ በየነ የሆሳዕና እለት የሰበኩትን ይህንን ድንቅ ስብከት አዳምጡ።
ክብር ሁሉ ለታረደው በግ
ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን።

Sunday, April 24, 2016

ይድረስ ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና ለኢትዮጲያ ሊቃነ ጳጳሳት!


Read in PDF

ከዲያቆን አናኒ
      ይህን ደብዳቤ የምጽፍልዎ በቅዱስ መጽሐፍ “የሕዝብን አለቃ አክብረው ፤ ተገዛለትም” የሚለውን አምላካዊ ቃል በማሰብና የአገራችንን የአክብሮት ትውፊት ከልቤ እያመላለስኩ ፍጹም ዝግ ባለ መንፈስ ውስጥ እርሶንና ሊቃነ ጳጳሳቱን በክርስቶስ እንደ አባት በማሰብ ስለአንዲት ቤተ ክርስቲያን የተጨነቅሁባትንና ከሁሉ ይልቅ ታላቅ የሆነች መልዕክት በልጅነት አንደበት እንዲህ ልልክልዎ ወደድሁ፡፡
    ብጹዕ አባታችንና ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ከመቼውም ጊዜ በላይ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የምዕመናን ፍልሰት እጅግ ያሳሰበን ጊዜ ላይ እንዳለን በተደጋጋሚ ሲያነሱ ሰምተናል ፤ እውነታውንም እኛም አስተውለናል፡፡ ለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ “ታላላቅ” ከተባሉቱ ዘንድ ሳይቀር የተለያዩ አስተያየቶችና ከቃለ ወንጌሉ ጋር የማይዛመዱ ግምታዊ የሆኑ መላምቶች  ሲሰጡ እስኪሰለቸን ሰምተናል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት አስተያየቶችና መፍትሔ ተብለው የቀረቡት ግምቶች ፍልሰቱን ከመግታት ይልቅ አባሱት ፤ ይልቁን እንዲጨምር ያደረጉት ይመስላል፡፡

     ትላንት ሙሉ መንደሩና ከተማው ኦርቶዶክስ የነበረበት ሥፍራ ዛሬ በብዙ ቤተ ሃይማኖት የተወረሰ መሆኑንና እንዲያውም በዚሁ ከቀጠለ፥ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ እንደተናገሩት “ኦርቶዶክሳዊነት በሰሜን ብቻ ተወስኖ ሊቀር እንደሚችል” ከፍ ያለ ሥጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ አዎን አባታችን! ስጋቱ ግን ሥጋት ብቻ ሆኖ እንዲቀር ሁላችን አንፈልግም፡፡  ሁለት ጥያቄዎችን በልጅነት መንፈስ ለውይይት ማንሳት እፈልጋለሁ፥ ይኸውም፦
1.      ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለምን ይፈልሳሉ? የሚለውንና፥
2.     ከኦርቶዶክሰዊት ቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሲፈልሱ በብዛት ወደየትኛውም የሃይማኖት ተቋም ይሄዳሉ? ሚለውን ደጋግሜ ለራሴ በማንሳት አሰላስያለሁ ፤ ብዙዎችንም በዚህ ዙርያ ጠይቄያለሁ፡፡
    አንደኛውን ጥያቄ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መጠየቃቸውንና፥ “ሰዎች የሚፈልሱት ወንጌል ፍለጋ ነው፥ ባሏቸው ጊዜ ታዲያ ወንጌሉን ለእነርሱ እንዲገባና እንዲመጥን አድርጋችሁ ስጧቸው እንጂ” (በትክክል ካልጻፍኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ) ብለው መመለሳቸውን ሰምቼ ነበር፡፡ በእርግጥ ሰዎች በብዛት የሚፈልሱባቸውን የሃይማኖት ተቋማት ካስተዋልን የመጀመርያውን ጥያቄ ለመመለስ ይረዳናል፡፡
    ከተወሰነ አሥርት ዓመታት በፊት በመቶ ሺህዎች የነበረው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኝ ብዛት በአሁን ሰዓት ከአሥር ሚሊዮናት መካከል መሆኑን ስንሰማ ከአሥር ሚሊዮናት በላይ የሆኑት አማኞቻችን በአብዛኛው ወዴት እንደነጎዱ ማስተዋል ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ወደወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለምን እንደሄዱ በተለያየ ዘመን ይሰጥ የነበረው ምክንያት በአብዛኛው አሳፋሪ ነው ብንል ግነት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ስንፍናችንን አጉልቶታል ፤ ለሚፈጠረው ችግርና ፍልሰት ምክንያታዊ የሆነ ከወንጌል የተቀዳ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ አስታበየን እንጂ የሚፈልሰውን ምዕመን ቁጥር ዛሬም እንኳ አልገታነውም፡፡

Thursday, April 21, 2016

በጋምቤላ ፤ በሜድትራኒያን ዳርቻ … የሆነው፥ ለእኛ የ“ንስሐ ግቡ” ደወል ይሆን?


“አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፥ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቍጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ። አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነውና፥ ወደ እርሱም ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ አያዞርምና ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኩአቸው ፊት ምሕረትን ያገኛሉ፥ ደግሞም ወደዚህች ምድር ይመለሳሉ።” (2ዜና.30፥8-9)
    ከወደጋምቤላ እናት እስካዘለችው ልጇ ድረስ ተቀልታ በጠቅላላ ከ148 ሰዎች መታረዳቸውን ሰምተን ጆሮዋችን ሳያባራ፥ ከወደሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ ደግሞ ትውልደ ኢትዮጲያውንና ኤርትራውያን ይበዙበታል በተባለ የስደተኞች የባሕር ጉዞ ጀልባ ተገልብጦ ከ400 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተረዳን፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ኢትዮጲያውያን በዚሁ በሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ በሰው በላው አይ ኤስ አይ ኤስ ዜጎቻችን እንደዋዛ እንደበግ ታርደው ደማቸው በከንቱ ከባሕር ጋር ተቀላቀለ፡፡

    ለመሆኑ የዚህች አገር የሰቆቃ ድግስ መች ነው የሚያበቃው? የኢትዮጲያችን ዕልቂትና እንግልት የት ነው የሚገደበው? ለሰቆቃችን ፍጻሜ የሚያበጅለት የትኛው ብርቱ ክንድ ይሆን? ሞት ዕጣ ፈንታችን ፣ መታረድ ጽዋ ተርታችን ፣ በስደት ወጥቶ የባሕር እራት መሆን “የአርባና የሰማንያ” ቀን ዕድላችን ከመሆን የሚያከትመው መችና በማን ነው? ከውጋጋን ይልቅ ጨለማው ምነው ከበደ? የሕይወታችንና የኑሮአችን የጧፍ ክር ተስለምልሞ ከመብራት ወደመጤስ ምነው ቸኰለ? ያለፈውን ሃዘን አንደኛውን ዓመት “መታሰቢያውን ሳናከብር” ሌላ ምርር ያለው ሐዘን ምነው ሊያገኘን ፈጠነ? 

Tuesday, April 19, 2016

የሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመተላለፍ ህገ ወጥ ሰባኪያንን የጋበዙ የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ከስራና ከደሞዝ ታገዱበደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ የነበሩት መምህር ግሩም በለጠ እና የደብሩ ሰባኪ የሆኑት መምህር አምደሐይማኖት ያለ ሐገረ ስብከቱ ፈቃድ የላብቶብ አገልጋዮችን በመጋባዛቸው ከስራና ከደሞዝ ታገዱ።
የእጉዱን ምክንያት የሚያብራራው ደብዳቤ እንደ አብራራው እነዚህ ሰዎች ከስራና ከደሞዝ የታገዱት “---የማኅበረ ቅዱሳን አቀንቃኝ ያረጋል አበጋዝን ጠርተው ካህናቱን መነኮሳቱን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያንን ወሯታል…” በማስባልና እንዲሁም “…ህዝቡ እንዲደናገር በካህናቱና በመነኮሳቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት…” በማድረጋቸው እና “…የቤተክርስቲያኒቱን መሪዎች አሰድበው ለተሳዳቢ የሰጡ ስለሆነ…” መሆኑን ገልጿል።
በተለይ መምህር አምደሀይማኖት ለማኅበረ ቅዱሳን ምግብ ቤት እንጀራ አቅራቢ እንደመሆኑ መጠን የእንጀራ ገመዱን የሚያራዝምበት አማራጭ እንደ አገኘ በደስታ የቆጠረ ቢሆንም ያገኘው ምላሽ ግን ከጠበቀው በላይ ሆኗል።
ከቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ በተላለፈው ጥብቅ መመሪያ መሰረት በተለይ ሁከትንና ፓለቲካን እያጣቃሱ የሚሰብኩ ዘወትር አውደ ምህረቶችን በላብቶብና በፕሮጀክተር አሳብጠው የነበሩት ሁሉ ለቤተክርስቲያኒቱ የዳር አገር ሰዎች በመሆቸው ህጋዊ የመግቢያ በር በማጣት ጋራ ተጋብተው እንዳሉ ይታወቃል። 

Monday, April 18, 2016

ስድቡ ተዛውሯልና ወደ ቦታው እንመልሰው.ከመሪጌታ አለኸኝ 

አንድ   አዛንት   ወደ   ቤተ   ክርስቲያን   ቅጽረ   ግቢ   ሳለም   ሲገቡ   አንድ   ጎበዝ  ይገፈትራቸዋል።   ዘወር   ብለ   ለከቱ     በቀ   ጊዜ   ልዩ    ሰጠ  (ባርያ)    ባርያ  እንዳይሉ  ያስቀጣ  ሆነባቸ ትኩር  ብለ  
አይተ   «አጓ»   አሉት።   እርሱ   ግን   ልሶ   እርሳቸ   ሊሉት    ያሰቡትን  
«ባርያ»   አላቸ!!!!   በዚህ    ክንያት   ስታረቅ   የተቀመጡ   ግሌ   «  
ተዛውሯል  ወደ  ቦታ   እንልሰ»  አሉ   ይባላል።  

ያሳለፍነ   ንት   አስተዋዮችና   ባለአእሮዎች   እጅግ   ያዘኑበት   ባላጌዎ  የስድ   ቀስታቸ   በየ   ቡኩ   የተወራወሩበት   ነበረ።   ለዚህም   ነሻ   የሆ  ጋጠወ   ዳንኤል   ያደገበትን   ብልግናና   ደዴነቱን   እንደ   ወረደ   ከተቡ    በእርግጥ   በዚህ      ክቡር   የሰ   ሕይወት   ላስ     ሰዎ  ተሳድበ  እንጀራ  በሉበት  ስለሆነ  ይኽን   ያህል  ያስ  ሊባል   ይችላል።  ይሁን   እንጂ   ታናሹ    በታላቁ   ዓለዊው   ንፈሳዊ   ርኩሱ   በቅዱሱ   ላይ  የስድ   አፉን   ሲከፍት   ስማት   ለአዋቂዎ   ኃዘን      በተሳሳይ    ለተያዙ   ወገኖ   ግን   የገበጣ   ወታ     ብልሆች   ወይም   የእ  ሰዎች   ስለሌ   አት   ያለቅሳሉ።   በክፋትና   በኃሰት   የታወሩ   ሰዎች   ግን  የሌላ   አት   ሊያስለቅሳቸ   ቀርቶ   የራሳቸ   እንኳ   የት   እድ  የላቸ   ,   ካብ   ሲናድ   ብልህ   ያለቅስ     ይስ.   እንዲሉ።   የአንድ  ትውልድ   ርዓተ   አልበ   ራላዊና   ባህላዊ   ረት   ሥሜትን    ለባለአእሮዎ   ብቻ     ይልቁንም   የአንድ   የሃይማኖት   ተቋም   ወይም   ቤተ  
እምነት    /ቀኖና    ሲጣስ    ሃይማኖቱ    ሲነካ    አማኙን    ያስቆጣል  
ያሳዝናል   ንደኛ   እንጄራን   ብላት   ብቻ   ሃይማኖትን   ተገን   አድርጎ  ኖር   ግን   ንም   ሥሜ   አይሰጠም።   ይኽንን     ኑን   ያየ  ብዙዎች   አማኞች   ተሳዳቢውን   ሲያወግዙ   ጥቂት   ግብረ    አበሮቹ   ደግሞ   ሲያወድሱ  ተስተውሏል።  እግ በስ !!!!!