Saturday, April 2, 2016

ቢገድልህም እግዚአብሔርን ጠብቅ!ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

የጽሑፉ ዓላማ
ረሃብ ከሆነ ልብህን የከፈለው ረሃብ እንደማይገድልህ፤ መጠለያ ማጣትህ ከሆነ አንገት ያስደፋህ ጎዳና ላይ መውደቅህ የህይወትህ ፍጻሜ እንዳይደለ፤ ወንጌል ያድናል! ወንጌል ያድናል! ስትል ጓዶኞችህ ጥለውህ የሄዱና ወደኋላ የቀረህ መስሎህ የተሰማህ የዛሬ ማጣትህም ያሳሰበህ እንደሆነ የበረከት ጌታ የያዕቆብ አምላክ አንተን እየጠበቀ እንደሆነ፤ በሰው ፊት ጎድለህ መታየትህ ከሆነ ያሳፈረህ ደግሞ ገና የከፋ ነገር ከፊትህ እንዳለና እንደሚጠብቅህ አስታውስህ ዘንድ ፃፍኩልህ።  
መሪ ጥቅስ
 ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው (2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 69 10)
በክርስቶስ ኢየሱስ ወንድሜ ለሆንከው
በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል” እንዲል መጽሐፍ ብዬ አልሰብክህም። አንድ ነገር ግን እመሰክርልሃለሁ። “ክፉ ቀን” ማለፉ አይቅርምና በአገልግሎት ዘመንህ፤ እግዚአብሔር ባገለገልክባቸው ቀናቶች “አደረግኩለት/አደረግኩላት” የሚል ሥጋ ለባሽ እንዳይገኝ በአጽንዖት ወንድማዊ ምክሬን እለግስልህ ዘንድ እወዳለሁ። ሰው ዕዳ ነው። ዛሬ በግራ እጁ የሰጠህ እንደሆነ ነገ በቀኙ ይቀበልሃል። አንተ ደግሞ - እግዚአብሔር ይመስገን! የማንም ባለዕዳ፣ አሽከር፣ ወይም አሰላፊ አይደለህም። ስለ ባለሀብቶች የእግዚአብሔር ስም ለዘላአለም ይባረክ! ቢሆንም ራሳችንን በባለ ሃብቶች አንከብም። ከባለ ሃብቶች ጋር መተሻሸት ለእኔና ለአንተ አልተሰጠም። ታዳጊያችን የተኛ ቢመስልም መርከብዋ ላይ ያለ የጠራህ ጌታ ኢየሱስ ነው። መጠጊያችን አንድ እግዚአብሔር ነው! ወላጅ አልባ ልጆች አይደለንም። ቢከፋም ቢለማም ሮጠን አቤት! የምንልበት ከልብ የሚራራልን አባት አለን።  

ባለ ሀብት ሲያደርግልህ መዘዙ ብዙ ነው። ምላሱ ትከተልሃለች እጁም ወደ ወደደችው ትመራሃለች። ያን ጊዜ የሰው ፊት አይቶ የማያዳላ፣ ለፍትሕና ለጽድቅ የቆመ፣ እውነቱን ተናግሮ ፍርዱን ለመስማት የሚቆም የእግዚአብሔር ባሪያ መሆንህ ይቀርና “ይህን ባስተምር እትዬን/ጋሼን ያስቆጣል ስለዚህ ይቅርብኝ” እያልክ ጋሼንና እትዬን ደስ የሚያሰኝ ስብከትና መዝሙር እየመረጠ አፉን የሚከፍት፣ ለሆዱ ያደረ - ልበ ድንጉጥ ፍሬ አላባ የጋሼና የእትዬ አፍ/ባሪያ ሆነህ ትቀራለህ።
የነጻነት መንገድ ሰው እንደሚያስበው ውስብስብ አይደለም። በእነዚህ ጥቂት ዓመታት የመጣ ሥር ነቀል የባህል ለውጥ ከሌለ በስተቀር እኔ እስከማቀው ድረስ የኢትዮጵያ ባለሀብት ድሃ ለመርዳት ድሃው የሚገኝበት ስፍራ ድረስ ሄዶ ሊጎበኘው ቀርቶ ድንገት መንገድ ላይ የተገናኙ እንደሆነ የባለሀብቱ ፊት ምን ያህል እንደሚጠቁር ለሁላችን ግልፅ ነው። ካልፈለግከው አይፈልግህም። ምን በወጣው?! ለመጻፍ ራሱ አያመችም። ኢትዮጵያዊ ድሃና ባለሀብት ድንገት መንገድ ላይ የተገናኙ እንደሆነ ፈጥኖ በእግዚአብሔር ፊት የሚሰማው ድምጽ “መድሃኔዓለም! ገንዘብ እንዳይጠይቀኝ አፉን ያዝልኝ - እንደው አደራ” የሚል የባለ ሀብቱ ጸሎት ለመሆኑ ሁላችን የምናውቀው እውነታ ነው። ወንድሜ! አንድም ይሁኑ ሁለት ቀደም ብለህ የምታውቃቸው (ከአገልግሎት የተያያዘ ይሁን የሥጋ ዘመድ) ባለ ሃብቶች ያሉ እንደሆነ በመከራህ ጊዜ ተሰወርባቸው። ፈልገውም አያግኙህ። ለሚያልፈው ቀን የሰው ፊት የምታይ ሰው አይደለህም። አንተ ለፍጥረት ሁሉ መድሃኒት የሆነው የጌታን ስም የተሸከምክ የእግዚአብሔር ባሪያ እንጅ ለማኝ አይደለህም።
ወንድሜ ሆይ! ለራስህ ተዋርደህ የእግዚአብሔርን ሥም እንዳታዋርድ ደግሜ እማጸንሃለሁ። ባለ አመል ካልሆኑ በቀር ሰዎች ስለ አንተ የሚሉት ነውር አይኑራቸው። ስለ አንተ በእግዚአብሔር ፊት የምጸልየው ጸሎትም ይህ ነው፣ ምህረተ ብዙ እግዚአብሔር አይኖችህን ይከፍት ዘንድ፣ ጉልበትህን ያጸና ዘንድ፣ ስለ አንተ ዘወትር በጌታ ፊት እተጋለሁ። ወንድሜ ሆይ! ለሚያልፍ ቀን ራስህን እንዳትታዘብ አደራ። ቢፈራረቅብህም ማለፉ አይቀርም። የቤተ ልሔም ራብ ካለፈ ያንተም የማያልፍበት ምክንያት የለውም። ያልፋል ነው እያልኩህ ያለሁት፡፡ ማለፉ ለማይቀር ነገር ግን እጅ እንዳትሰጥ፣  ቢገድልህም ጌታ አምላክህን እግዚአብሔርን ጠብቅ!
አደራ!
Ø ወንጌል ብለህ ወጥተህ ስታበቃ - በመከራህ ጊዜ ከሰው እጅ የምትጠብቃት ሰባራ ሳንቲም እንዳትኖር፤
Ø ረሃቡም ሆነ ጥማቱ ጠልፎ ቢጥልህም እርዳታ ፍለጋ የሰው ደጅ እንዳታንኳኳ፤
Ø ማጣት ቢያዳፋህም ወዳጅ ዘመድ ፍለጋ እግሮችህን እንዳታነሳ፤
Ø እራት ይገዛልህ ዘንድ የቀድሞ ጓደኛህን አድራሻ ፍለጋ እንዳትገባ፤
Ø ለመሆኑ በህይወትህ ለተነሳው ማዕበል መንስኤው ምንድነው? መልስህ “የጌታ ስም” ከሆነ እንግዲያውስ የተነሳው ማዕበል ሰው የሚመልሰው አይደለምና እግሮችህን መልስ።
Ø ወንድሜ ሆይ! እግዚአብሔር ይስማህና - ስማኝ! ረሃብ የሚገድልህ ዓይነት መስሎህ ከተሰማህ ቤትህን ቆልፍና በክብር በተኛህበት የሰላም እንቅልፍ ይውሰድህ። ያን ጊዜ “ጉድ! ጉድ! አንተ፣ ያ ጌታ ጌታ፣ ወንጌል ወንጌል የሚለው ልጅ እኮ የሚበላው አጥቶ ከረሃብ የተነሳ ወዳሰበው ሳይደርስ ሞት ቀደመው አሉ … አቤት! ከዚህ በላይ ምን ውርደት አለ?” እየተባለ የሚሣለቅበት፣ የባልቴት የቡና መጣጫ የወሬ ማጣፈጫ የሚሆነው አንተ ሳትሆን፣ ሰውም ሰይጣንም የሚያውቀው የታመንከውና የተደገፍከው እግዚአብሔር ይሆናል። መልዕክቴ ግልፅ ነው። ቢገድልህም እግዚአብሔርን ጠብቅ። እስቲ አሁን ለዚህ ምን አንድምታ ያስፈልገዋል? ይህን ሐቅ አሁን አንተ አጥተኸው ነው?
Ø “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! ደክሜአለሁና በፊትህም ሞገስ ያገኘሁ እንደ ሆነ የባሪያህን ነፍስ …” እስከ ማለት የደረስክ እንደሆነ እንዲያውም “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን” የሚለውን የጌታን ጸሎት ዝለለው። ስለ መብል ብለህ በእግዚአብሔር ፊት ወድቀህ እንዳትገኝ አደራ። ለምን የምድር ባንኮች ሁሉ በናስ ብረት ጥርቅም ብለው አይዘጉም! መታመኛችን የዘላለም አባት እግዚአብሔር ነው። አንተ በሆድህ አትገመትም! እግዚአብሔር ይመግብህ ዘንድም ስለ መብል ለመጸለይ ጊዜህንና ጉልበትህን በከንቱ እንዳታባክን። እውነቱን ልንገርህ - እግዚአብሔር የአንተን ነገር የረሳው የመሰለህ ያህል አንተ ደግሞ የመብሉን ነገር እንዲሁ የዚያኑ ያህል እርሳው። እስቲ እግዚአብሔር አንተን ጦም ያሳድርና ያን ጊዜ ታየዋለህ፡፡  
Ø ከአባትህ ቤት ያስኮበለለህ ወንጌል ከሆነ፤ ለዚህ ሁሉ ጉስቁልና የዳረገህ ወንጌል ከሆነ አሁን ላይ ደርሰህ የሰው እጅ የምታይበትና የምትጠብቅበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። ሰማያትን የዘረጋ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር አንተን አንዱን ግለሰብ መመገብ ያቅተዋልን? ምንም ይሁን ምን ከዚህ ቀደም በእግዚአብሔር ባሪያዎች ያልሆነና ያላለፈ ሰይፍ በአንተ ህይወት አያልፍምና የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል ብትሆንም ሰው ላይ የጣልካት እምነት ያለችህ እንደሆነ እስዋንም ጭምር አሁንኑ ትጥላት ዘንድ በጌታ ስም እጠይቃሃለሁ። እግዚአብሔርን መታመን ዛሬ ካልተማርክ ነገ የእግዚአብሔርን ስራ ለመስራት ብቁ አይደለህም።
Ø ድርጅቱ አሁንም ድረስ ይኑር አይኑር ባላውቅም፣ ራሱን የቅዱሳን ማኅበር በማለት የሚጠራ የአጋንንትና የምናምንቴ ስብስብ “ማኅበረ ቅዱሳን” ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እርግማንን (የበለዓም ትምህርት) ማለትም በመንፈሳዊ አገልግሎት ስም የምእመናንን ኪስ እንዴት አድርጎ ማራቆት እንደሚቻል በሚገባ አስተምሮአል። “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን። ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ! ‘ምርቃቱ ትደርስልህ ዘንድ ቢጠራህ አቤት ቢልክህ ወዴት ብለህ አባትህን አክብረው’ ሲራ. ፫፥፱” የሚል ፖስተር ለጥፈህና አስለጥፈህ በአገልግሎት አሳብበህ ወደ ምእመናን ኪስ ለመግባት እንዳትሞክር፤ በእንዲህ ዓይነቱ የሌብነት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ሰይጣን የተነፈሰባቸው ምናምንቴዎች ጋር ህብረት እንዳይኖርህም አደራ እልሃለሁ። ሌባ በእግዚአብሔር መንግሥት እድል ፈንታ የለውምና።
በጌታ ወንድሜ ለሆነከው
v ከወንጌል የተነሳ ለሌላው ሸክም ሆነህ የተሰማራህ እንደሆነ - እነግርሃለሁ አንተ የማንም ሸክም አይደለህም። እንደማንኛውም ሰው ድንጋይም ቢሆን ተሸክመህ ኑሮህን መምራት፣ ሰርተህ መኖር፣ መውጣትና መግባት የምትችል ጎበዝ/ሙሉ ሰው ነህ። ዳሩ ግን እግዚአብሔር ለመንግሥቱ ሥራ አጭቶሃልና በህይወትህ መሆን ያለበት ይሆን ዘንድ ግድ ይላል።
v ለአገልግሎት ያለህ ፍቅርና ትጋትህ ሰዎች ሲተረጉሙት ለማኝ ሆነህ የታየህ እንደሆነም አንተ ለማኝ አይደለህም። ሰው አለኝ የሚለው ሀብት፣ ብርና ወርቅም ቢሆን ምንጩ የአንተ አምላክ እግዚአብሔር ነው።
v ከሰው በታች ሆነህ የተሰማህ እንደሆነም አንተ ያ ሰው አይደለህም። እንደውም ከነድካምህ የሺሕ ሰው ግምት ነህ። ዝቅ ያልከው በህይወትህ ከፍ ብሎ መታየት ያለበትና የሚገባው አምላክህን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ለማድረግ እንጂ ዝቅታ ቦታህ ስለሆነ አይደለም።
v ከአንደበትህ የማይታጣ የወንጌል ቃል - ከጌታ ስምም የተነሳ ሰዎች “ይሄ ደግሞ - እንደው ምናለበት - ሰርቶ አይበላም እንዴ?” ቢሉም አንተ ስራ ፊት አይደለህም። አንተ ከራስህ ያለፈ አጀንዳ የተሸከምክ - ትርጉም ያለህ፣ መረዳትህ የላቀ፣ ዓይነ ልቡናው የበራ፣ ለአማኞች ወይም ለቤተ ክርስቲያን - ለአገርና ለትውልድ ሸክም ያለውና የሚሰማው ባለ መድሃኒት ባለ ራዕይ ሰው ነህምድሪቱ ያጣችው እንደ አንተ ያለ - ያልዘራውን የማያጭድ፣ የራሱ ያልሆነውን የማይፈልግ፣ በወገኖቹ ደስታ ሐሴትን የሚያደርግ፣ የጽድቅ ልብስ የለበሰ፣ ታማኝ አገልጋይ ነው። ጥያቄው ነገ የሚፈለገው ዓይነት ሰው አንተ ነህ ወይ? ስደቱ መከራውና ረሃቡ እንዴት ይዞሃል? ወንድሜ! ለማየት ያብቃህ - ሰዓቱ ሲደርስ የጨዋታውን ህግ እንቀይረዋለን። የጊዜ ጉዳይ ነው። አብረን የጌታን ማዕድ የምንቆርስበት ዘመንም ሩቅ አይሆንም።
ስለ አንተ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን!

12 comments:

 1. ሙሉጌታ አመሰግናለሁ አላማችን እንጀራ ፍለጋ አይደለም የእግዚአብሔር ልጅ በምድራችን አሸንፎ ማየት ነው። በዚህ ዓለም ምኞት ተጠላልፈን ሳንወድቅ ወደ ራእያችን እንገሰግሳለን። አንተ ዳቦና ሙዝ እየበላህ ያሳለፍከውን ጊዜ አይቼአለሁ ይህ ያስተላለፍከው መልክት የህይወትህ ታሪክ ሰለሆነ አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ። መኪና ለመቀያየር ከሚታገሉ ሰባኪዎች እንዳዱ ስላልሆንህ የፃፍከው እውነት ነው። ስለዚህ ከግብዝነት ራሳችንን እንጠብቅ በጣታችን የማንነካውን ለሰው ማስተማር የለብንም። እኔ በስደቴ እመካለሁ እንዲህ አይነት ምክር ደግሞ ያፅናናኛል። ራእያችን ባገራችን መፈፀሙ ስለማይቀር ክብር ለጌታ ይሁን!

  ReplyDelete
 2. ወይ ዲ።ሙሉጌታ እንዲህ የጠፋኸዉ ጨምርህ ለመምጣት ነዉ ተባረክ

  ReplyDelete
 3. Abet abet...Tsifehi motehal...
  Ere bakachiew degifut bemetsaf dekmual....

  ReplyDelete
 4. ጅብ የማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆዳ አንጥፉልኝ አለ ብለው አባቶቻችን የተረቱትን ተረት ሙሉጌታ በተግባር አሳየን………. አንተ መናፍቅ የማትታወቅ መስለሆን ደግሞ ብቅ አልክ ይገርማል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሐዋ 24:14 አንብብ ብትል አይደንቅም ከኢየሱስ ውጪ ወደውጪ

   Delete
 5. ሙለር!!!

  በወንጌል ለሚኖሩ፤ ነገር ግን ለወንጌል ለማይኖሩ ሰዎች ቢሰሙና ቢያስተውሉ ጥሩ የማሳሰቢያ ደወል ነው!!!
  'እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም' የሚለው ቃል በእያንዳንዳችን ላይ ተግባራዊ እንዳይሆንብን አለማስተዋልን በማስተዋል ይሙላን እያልኩ ኑሮ ማለት ለመብላትና ለመጠጣት ገንዘብን ማካባት የመሰላችሁ ወይም የማያልፈውን በሚያልፍ ከንቱ ነገር ተክታችሁ ወንድሞቻችሁን የምትገድሉና ለስደት የምትዳርጉ እናንተ የሥጋ ዘመዶቻችን ሆይ! ቢያንስ ለራሳችሁ ሕይዎት ስትሉ ቆም ብላችሁ ጌታ የሰጣችሁን አእምሮ እደሚገባ ተጠቀሙበት ለሌላው ወገናችሁም ትንሽ አስቡ ለራሱ ብቻ የሚኖር የማያስብ እንስሳ ተደርገን የተፈጠርን ሳንሆን ለክብሩ በምሳሌው ውብ ተደርገን የተፈጠርን የፍጥረት ቆንጮ እንጂ ከዚህ በላይ በእግሊዘኛ ፊደል አማርኛ አቤት አቤት ጽፈህ ሞተሃል ብሎ እንደ ጻፈው ሰው ተራ ነገር በማቅረብ ትዝብት ላይ አንውደቅ!!!አንተ ወንድሜ ለመሆኑ ስነ-ጽሁፍ ላንተ ምንድነው??? ሎሚ ተራ ተራ? ብዙ የሚናገሩትንና የሚሠሩትን የማያውቁ አላዋቂ የእለት እንጀራ ተቀጣሪዎች በምድራችን ላይ ብዙ ስለሆኑ ነው የብዙ ወገናችንን ሃብት በእጃቸው ውስጥ ያስገቡ ክፉ ሰዎች በቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ጭካኔ ተዝናንተው እንደነ ሙሉጌታን ለማስገደል ሲሞክሩ በስደት ያጣናቸው። እረ እባካችሁ ነፍሰ ገዳይ ቀጣሪዎችም ሆናችሁና እንዲሁም ለእለት እንጀራ ብላችሁም በቅጥር ገዳይነትና በስም አጥፊነት ሥራ የተሠማራችሁ ወገኖች ማስተዋላችሁን ተጠቅማችሁ ከዚህ ሥራ ተቆጥቡና ቤተ ክርስቲያናችንን የወላድ መካን አታድርጓት ወይም የአጋንንት አገልጋይ ክፉና አሳዳጅ ሰዎች ዋሻ አታደርጓት? ማስተዋል ይብዛላችሁ!!!

  በእውነት ወንድማችሁ
  እውነቱ ነኝ
  ሰላም ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን
  ብሎም ለምድራችን/ለሕዝባችን በሙሉ!!!

  ReplyDelete
 6. Thanks Mulugata you are right every thi g is pass.

  ReplyDelete
 7. ሙሌ የመታመልከው አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ይባርክህ፣፣፣፣ ደስ ኢያለኝ ነዉ ያነበብኩት፤ ባከህን አተጥፋ ስላአንተ ከወንድሞች ሰምቻለዉ እንጂ በአካል አላዉቅህም፡፡ሆኖም ሃስብህን ምኞትህን ሁሉ ከወንወድሞች ሰምቼ ባንተ ሁኔታ እግዚአብሔረን አመስግኛለዉ ወደ ፊትም ቢሆን ጌታን ስላንተ አከብረዋለዉ፡፡ በአገራችን በእጅጉን ወንጌል ኢየሰፋ ነዉ ደስ ይበልህ……. ከፍተኛ የወንጌል ሥራ አለ ተቀዋሚዎችም ቢኖሩ እንኳ እንዳለከዉ ጨዋታዉ ኢየተቀየረ ነዉ፡፡ በየ አጥቢያዉ፣በየገዳማቱ፣በትምህርት ተቋማት፣ በየቤቱ(ቤት ለቤት ሰዉ የሚያውቀዉ የዓደባባዩን ነዉ)፣በማህበራት ፣በዓውደ ምህረት ፣በሰ/ት ቤት በሶሻል ሚዲያ ወንጌል ኢየተቀጣጠለ ነዉ፡፡ ለተቀዋሚሆች ከማዘን ያለፈ ምንም ማድረግ አልችልም፤ አንድ ቀን እነርሱም አንደሚለወጡ ተስፋ አለን፡፡ ሆኖም እነርሱ ነህሚያ እንዳለዉ ቀላል አድርጎ ተመልክቶናል ፡፡ ነገሩ ከሰማይ የታዘዘ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አላወቁትም መሰለኝ፡፡ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነዉ፤ በርታ፣ በርታ፣ በርታ፣ በርታ፣በርታ፣ በርታ…….እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 8. ተባረክ ወንድም ኢየሱስን አምኖ መሞት በኢየሱስ መነቀፍ መታደል ነው

  ReplyDelete
 9. Mr. Ewnetu,
  I feel your profound and sincere concern and heartfelt pain for those with sight but blind. I have been in this struggle for the best part of 10 years, but I have seen Satan's kingdom flourishing and his disciples ever increasing. His followers are mute, deaf and blind. They only see what he sees and wants them to destroy. They are possessed and have sold their soul for riches and comfort. They will do whatever it is he wants them to do. They are destroying our country, religion and the Christian community at large as much as they can. Their day is coming to an end, as you thoughtfully stated as Christians we should pray for our enemies for that is the commandment from our Lord "Love your Enemies".
  It is good to hear from Mulugeta again after a long silence!!

  ReplyDelete
 10. yegermalu mulugeta eskahun beyefa protestant adarash sayegeb yekoyal beye altebekem neber bemayawekuh bota ehedeh eskahun eyasastek new.

  ReplyDelete
 11. God bless the writer. May the Lord Jesus bless him . It is so wonderful please give us more to learn.

  ReplyDelete