Sunday, April 10, 2016

በመላው ዓለም በስደት ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን፥“የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ነገር ነው።”
2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 11 ቁጥር 28
እኛ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰደደበትን ዓላማ ሳያዛባ ተጠናክሮና ጎልብቶ አንድ ወጥ አመራር ይዞ እንዲያመራ በስደት የሚገኘውን ምዕመናን ይዘን በየቤተክርስቲያናችን እየጠፋ ያለውን ፍቅር፥ ሰላምና አንድነት እንዲመጣ እግዚአብሔር የሰጠንን እድሜ፣ ትምህርትና የሥራ ልምድ እየተጠቀምን ለዚህ ላበቃን አምላክ ወረታውን ለመመለስ የምንጥር እና የምናገለግል የቤተክርስቲያን ልጆች ነን።
የእምነታችን፥ የቤተክርስቲያናችን እና የአንድነታችን ጉዳይ የሁላችንም በመሆኑ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የቀድሞው ፍቅር፥ መደማመጥ፥ መተሳሰብ ጠፍቶ ፖለቲካ ዘረኝነትና የጥቅማጥቅም ወረርሽኝ በሽታ እየተዛመተ ጨርሶ ሁላችንንም እንዳያጠፋን ዝም ብለን ማየት ስላልቻልን ያየነውን እና የተመለከትነውን ለመመስከር ተገደናል።
በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ለተሰባሰቡት ቤተክርስቲያናት የተጠናከረ ግልፅ እና ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር አለመቀረፁ በዚህ ምክንያት የተከሰቱ የአስተዳደር እና ድክመቶች እና የተፈጠሩ ችግሮች፥
ሀ. ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር እና የአስተዳደር ደንብ ለአንድ ድርጅት አላማውንና ተግባሩ የማስፈጸሚያ መሳሪያ መሆኑ እየታወቀ “ሕገ ቤተክርስቲያን” በሚል ተዘጋጅቶ የተበተነው ደንብ ምዕመናኑ ያልመከረበት እና ያልዘከረበት ሲሆን ተሻሽሎ የተዘጋጀ መተዳደሪያ ደንብ በማለት “የጠቅላይ ቤተክህነቱ ስራ አስኪያጅ” አባ ጽጌ ድንግል ደግፈው አለሙ የቅዱስ ሲኖዶሱን የቋሚ ኮሚቴና የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ በማሳሳት አቅርበው፣ አጽድቀው ለየቤተክርስቲያኑ እንዲበተን አድርገዋል። የቀረበው ደንብ ደካማና ብቁ ባለመሆኑ ምክንያትም የጠቅላይ ቤተክህነቱ ስራ አስኪያጅ የበተኑትን ደንብ እራሳቸው የሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን የስራ አመራር አለመቀበሉን በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ለምዕመናኑ ከማሳወቁ ባሻገር በአከባቢያቸው የሚገኘው ካቴድራል ተመሳሳይ መግለጫ በመስጠጥ ለምዕመናኑ ደንቡን አለመቀበሉን አሳውቋል።
ለዚህም ዋቢ የሚሆነው፡-
1.     የተዘጋጀው የመተዳደሪያው ደንብ በኢትዮጵያ ካለው ሲኖዶስ የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ አወቃቀር በቀጥታ የተገለበጠ ሲሆን ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ ሲኖዶስ ጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያለው የእዝ ሰንሰለት የኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ ሚኒስቴር አሰራር ተከትሎ በስዕለት፣ በሙዳየ ምጽዋት፥ በሌላም በልማት ስም ከተሰበሰበ ገንዘብ ከታች ወደ ላይ ወደ ቤተክህነት አስተዳደር ጽ/ቤት ገቢ ሆኖ በአገልግሎት ስም የተወካዮች ስልጣን ታክሎበት ትዕዛዝ እና መቀጫዎች ተጨምረውበት ከላይ ወደታች የሚወርድ ሰንሰለት እንዳለ ሆኖ የተዋቀረ መሆኑን፤

2.    አንድ የመተዳደሪያ ደንብ በሚዘጋጅበት ጊዜ አላማው፣ ተግባሩ የዕዝ ሰንሰለቱ በማያሻማ ሁኔታ ተገልፆ መመልከት ይኖርበታል፤ በተጨማሪም የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡ ከውስጠ ደንቡ ተለይቶ አስተዳደርን በተመለከተ የአገልጋዮች፥ የጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ቅጥር፣ ዝውውር፣ ሕክምና፣ የጡረታ መብት፣ የትምህርት ማሻሻል፣ የፋይናንስ እና በጀትን በተመለከተ፣ የሂሳብ አያያዝ እና አዘገጃጀትን፣ የንብረት አያያዝና ቁጥጥርን በተመለከተ የቋሚና አላቂ ንብረት አገባብ እና አሰረጫጨት በውል መመልከት አለበት። የተዘጋጀው የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ከላይ የተመለከተውን ስርዓት ያልተከተለ መሆኑን፣
3.    በተዘጋጀው የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ውስጥ እንደተመለከተው የአስተዳደሩ ተግባር በአንድ ኃላፊ፣ “በጠቅላይ ቤተክህነቱ ስራ አስኪያጅ” አመራር ሥር ሆኖ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች የአስተዳደር ለውጥ በሚያደርጉበት ጊዜ ካለ ቤተክህነቱ ስራ አስኪያጅ ፈቃድና ፊርማ በስተቀር የባንክ ሂሳብ፣ የፊርማ ልውውጥ ማድረግ የማይችሉበት አንቀፅ የተመለከተበት የአጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ህልውና የሚፈታተን ብሎም ከማሰባሰብ ይልቅ በታኝ ሆኖ የተስተዋለበት መሆኑን፤
4.    በዚህ የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ውስጥ የሥራ ድርብርቦሽ የሚፈጥሩ አንቀፆች ጎልተው የተመለከቱበት፤ አንዱ የሥራ ክፍል ሌላውን የሚቆጣጠርበት፤ የሚያግዝበት፣ ብሎም ችግር ቢፈጥር በውል ችግሩን የሚፈታበት ስልት ያልተነደፈበት ያልተመለከተበት በአጠቃላይ “አመራር በጋራ ኃላፊነት በነፍስ ወከፍ” የሚለውን መርሕ ያልተከተለበት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በስደት ላይ ያለችው ቤተክርስቲያናችን በሌሎች ቦታዎች የተዛመተው በሽታ “የሥልጣን መባለግና ምዝበራ” የመከላከያና የመቆጣጠርያ አውታር ያልዘረጋ መሆኑን ተመልክተናል።
በስደት ላይ ባለው ሕጋዊው ሲኖዶስ ስር የተደራጁ ቤተክርስቲያኖች፣ በምዕመናኑ ታታሪነት ተደራጅተውና ተጠናክረው የሚተዳደሩት በእየራሣቸው ቤተክርስቲያን በምዕመናን ጠቅላላ ጉባኤ የበላይነት በተደራጀ ድርጅታዊ መዋቅር ሲሆን፤ እነዚህ ከኪራይ እስከ ካቴድራል የደረሱ አብያተ ክርስቲያናት ከታች ተሰብስቦ ወደ ቤተክህነት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ገቢ ሆኖ ወደታች በሚወርድ በጀት/ገንዘብ የሚተዳደሩ ሳይሆን እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ባዘጋጀው የቤተክርስቲያን ደንብና ስርዓት መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፤ በቅዱስ ሲኖዶስ የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ላይ አፍራሽ ሳይሆን ገንቢ ሃሳቦች በማከል የተዘጋጀ ደንብ ረቂቅ ቢቀርብም “የጠቅላይ ቤተክህቱ ሥራ አስኪያጅ” እና አብረዋቸው ሆነው “የሚሰሩ” ኃላፊዎች ሥልጣን የሚያሳጣቸው መስሏቸው አልተቀበሉትም። ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል እንዲሉ የተዘጋጀውን ድርጅታዊ መዋቅርና የአስተዳደር ደንብ ረቂቅ በተዘዋዋሪ በወያኔ እጅ እንዲገባ ተደርጎ የሚገለገሉበት መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ለ) እንደ ጨው ተበትኖ በዓለም ዙሪያ የሚገኘው ምዕመናን ከአባት ከእናቱ የወረሰውን ሃይማኖቱን ጠብቆና ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ ከሚያገኘው ጉርሱ ቤተክርስቲያን ሰርቶ የእግዚአብሔር አገልጋይ አባቶችን አሳድሮ ለሕዝቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ሆኖም በሚከተሉት አብያተክርስርቲያናት ምዕመናን ላይ የአስተዳደርና የፍትሕ ጉድለት የተፈጸመባቸው የሚከተሉት ናቸው። 1) የሲያትል ቅዱስ ገብርኤል፣ 2) የዳላስ ኢየሱስ፣ 3) የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሚካኤል፣ 4) የኖርዝ ካሮላይና ሥላሴ እንዲሁም 5) የሙኒክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያናት ሲሆኑ ችግራቸውንም በማስመልከት ጥቅምት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ከነአባሪ ሠነዱ 116 ገጽ ተያይዞ በ40ኛው የቅዱሰው ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ቢቀርብም ሰሚ በማጣት ችግሩ ይበልጥ እየተባባሰ ይገኛል።
“የጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ” “ከፀሓፊው” ከቀሲስ አንዱዓለም ዳግማዊ ጎበና የዳላሱ ካህን ጋር በመሆን ከላይ እንደተጠቀሰው ሲኖዶሱን በውል የሚደራጅበትንና የሚጠናከርበትን አቅም እንዲኖረው ከማድረግ ይልቅ ቀስ በቀስ ስርዓት ጠፍቶ ጠንካራ አመራር እንዳይኖር ጥረት እያደረጉ ናቸው።
ለዚህም ዋቢ የሚሆነው፡-
1)     የቅዱስ ሲኖዶሱን ውግዘት በመሻር ከአዲስ አበባ የመጡ ሊቀ ጳጳስ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወስደው በቅዳሴ በስማቸውን ከመጥራት በላይ አውደ ምህረት አስቀምጠው ሊቀ ጳጳሱን ሲያወድሱ ተሰውምተዋል።
2)    ለዳላስ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የቴክሳሱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና ሲሰጡ እኝሁ ቀሲስ አንዱዓለም የሚካኤልን ካህናት በሊቀ ጳጳሱ ላይ አድማ እንዲያደርጉ በማስተባበር የተቃዉሞ ደብዳቤ በ40ኛው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲነበብ አድርገዋል። በተጨማሪም በሕጋዊው ሲኖዶስ ስር ጳጳስ እንደሌለ በማሰብ በውግዘት ላይ ያሉ ጳጳስ ከኢትዮጵያ ለሠርጋቸው በማስመጣት ውግዘቱ እንዲሻር አድርገዋል። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የእዝ ሰንሰለት ይጠበቅ፣ አንድ ካህን ገደቡን አውቆ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ጠብቆ የእግዚአብሔርን ቤት ያገልግል እንጂ ተማርኩ አወቅሁ በማለት ከሥርዓት ውጭ የሚደረገውን ድርጊት አሳዛኝ የሆነው። የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት አባቶች ይከበሩ የተሰጣቸው ማዕረግ ሞገሳችን ነውና ትዕዛዛቸው ይከበር ትዕዛዙ ከታች ወደ ላይ ሆኖ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰደደበትን ዓላማ እንዳይስት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች ምዕመናን በትህትና ለማሳሰብ የተገደድነው።
3)   ቅዱስ ፓትርያርኩ ስለ እንደራሴያቸው ውክልና ስለመስጠት ጉዳይ ለፃፉት ደብዳቤ ምላሽ በጠቅላይ የቤተክህነት ሥራ አስኪያጁ ተዘጋጅቶ የቅዱስ ሲኖዶሱን የቋሚ ኮሜቲውን በማስተባበርና የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ በማሳሳት አስፈርመው ለቅዱስንነታቸው የተላከው ደብዳቤ በአሁኑ ጊዜ የአደባባይ ሚስጢር በመሆኑ የቤተክርስቲያናችን ጉዳይና የቅዱስ ሲኖዶሱ ጥንካሬ ያገባኛል የሚል በስደት ላይ የሚገኘው ምዕመናን በሙሉ ሰምቶቷል፤ አንብቦታል፤ ለታሪክም ኮፒውን አስቀምጧል። ታሪካዊ የሚያሰኘውም የፍትሐ ነገሥቱን አንቀጽ 54 በመተላለፍ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክ መሾምና ሥልጣን መስጠት ከተጀመረበት እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከ1951 ዓ.ም ጀምሮ ተደርጎና ተሰምቶ የማይታወቅ የቤተክርስቲያን የደብዳቤ አፃፃፍና ሥርዓት ያልተከተለ ብሎም “ሕገ ቤተክርስቲያን” በሚል ስያሜ የሥራ አስኪያጁ የሚያገለግሉበትን ቤተክርስቲያን ጨምሮ ሌሎች በስደት የሚገኙ ቤተክርስቲያናት ያልተወያዩበት፣ ያልደገፉትና ተቀባይነት ካላገኘው ደንብ በመጀመሪያውም ሆነ በሁለተኛው ረቂቅ ደንብ ውስጥ ያልነበረ አንቀጽ 10 ቁጥር 10 ተጠቅሶ ከታች ወደላይ ቅዱስነታቸው ይህን ዉሉ ያልታወቀ ደንብ ተላልፈዋል ተብሎ ያአስተዳደር ተዋረድ ያልተመለከተበት በማን አለብኝነት የተፃፈ አሳዛኝ ደብዳቤ በመሆኑ ነው።
4)   የጠቅላይ የቤተክህነት ሥራ አስኪያጁ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪና አሳቢ መሳይ ቅጥረኛ ጋዜጠኛ ተብዬ ከአበሮቻቸው ጋር ሆነው በማዘጋጀት ወንድሞቻቸውን አባቶች በአደባባይ ሲያሰድቡ የቱን ያህል የህሊና እርካታ እንደሚያገኙ ባይገባንም፤ ቤተክርስቲያናት ከማስተባበር ይልቅ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚበተንበትን የሚሹ መሆናቸውን ለመረዳት ይቻላል።
5)   ከአምስት የሚያንሱ ሊቀጳጳስት ከተመደቡበት ሀገረስብከት በልዩ ልዩ ምክንያት ከቦታቸው ተነስተው በየቤተክርስቲያኑ በጥገኝነት ይገኛሉ። ጥፋት ከአደረሱና በምዕመናኑ ላይ ችግር ከፈጠሩ አባቶች ናቸውና አስመክሮና አዘክሮ ወደሌላ ቦታ ማዛወር፣ የጤና መታወክ ደርሶባቸው እንደሆነ ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኙ በመርዳት ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ሲገባ አለአግባብ ካለሥራ አስቀምጦ ከእጅ ወደ አፍ ከሚኖረው ስደተኛ ክርስቲያን ከሚሰበሰበው ገንዘብ እንዲወጣ ማድረጉ የቅዱስ ሲኖዶሰዉን ቋሚ ኮሚቴ በጋራ ኃላፊነት ከመጠየቅ አያድነውም። በዚህ አንፃር “የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጁ” የከፍተኛ የሰው ኃይል ጉልበትና የገንዘብ መባከን፣ ከቦታቸው በተፈናቀሉት አባቶች ላይ ለደረሰባቸው የሞራል ውድቀት በኃላፊነት እንደሚያጠይቃቸው ከወዲሁ ለመገንዘብ ይቻላል።
በአሁኑ ጊዜ በየቤተክርስቲያኑ አነጋጋሪና አስገራሚ ዜና ሆኖ የሚነገረው በአቡነ ኤልያስ የአውሮፓና የአፍሪቃ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ የሚመራ ስድስት አባላት ያሉት የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ መቋቋምና በታህሣስ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. (12/12/2015) በአስመራጩ ሊቀጳጳስ ፊርማ ለጳጳሳት፣ ለየቤተክርስቲያናቱ ካህናትና ለአመራር አባላት ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እጩዎችን እንዲያቀርቡ ስለሚጋብዘው የጥሪ ደብዳቤ ነው። እኝህን ሊቀጳጳስ የተዛባ መተዳደሪያ ደንብ ተይዞ ምርጫው መካሂድ እንደሌለበት በስልክ አነጋግረናቸው በጉዳዩ በማመን ምርጫው መዘግየት እንዳለበት የሚገልጽ ደብዳቤ ጻፉልኝ ብለው ወደ አውሮፓ ሄደዋል። እኛም ጉዳዩኝ በማስመልከት ጥር 13 ቀን 2008 በአድራሻቸው ደብዳቤ ልከንላቸው፣ ደብዳቤው መድረሱን አረጋግጠን በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልላቸውም ለማነጋገር ፈቃደኛ አልሆኑም። ከዚህም ሌላ ከአስመራጩ ኮሜቲ አባል መካከል በአደባባይና በሚዲያ መድረክ እንደሚወራውና እንደሚዘከረው በክህነታቸው ላይ ችግር ስላለባቸው የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ሆነው ለመሥራት እንደማይበቁ፣ በአጠቃላይ የሚከናወነውም ምርጫ የተዛባ፣ አድሏዊና ከዕውነት የራቀ እንደሚሆን ይወሳል።
ከላይ እንደተጠቀሰው ከአምስት ያላነሱ ሊቀጳጳስት ምድብ ቦታ ሳይኖራቸው ሌላ ተጨማሪ የኤጲስ ቆጶስ ሹመት መስጠት ለምን አስፈለገ? ወይስ በአደባባይ ሊሾሙ ነው እየተባለ ለሚነገርላቸውን “አባቶች” ለመጥቀም? ወይስ ከሌሎች አባቶች ለየት ለማድረግ ይሆንን? እነዚህስ ይሾማሉ የሚባሉት ሁለት “አባቶች በስደተኛው ሲኖዶስ ስር በተሰባሰቡት ቤተክርስቲያኖች ምን አይነት ተግባር የፈጸሙ እና እየፈጸሙ ያሉ ናቸው? “አባት” ተብለው በተመደቡበት ቤተክርስቲያኖች ምን ሲያከናውኑ እንደነበር ይታወቃሉ? አሁንስ ምን እያደረጉ ነው? ምዕመናኑን ፍቅር፣ አንድነት፣ እድገት፣ የሚጠብቁ፣ የሚንከባከቡና የሚያከብሩ ናቸውን ምዕመናኑ ለሚያደርግላቸው እንክብካቤ ጥቂቱ እንኳን ምላሽ የሚሰጡ ናቸው?
እግዚአብሔር የዕድሜ ጸጋ ሰጥቶ እዚህ ያደረሳቸውን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን የማያከብሩ፥ ትዕዛዛቸውን የማይቀበሉ፣ ከየቤተክርስቲያናቸው በራፍ ላይ አብረዋቸው ካሉ የሥራ አመራር ጋር በመሆን ቅዱስነታቸው እንዳይገቡ የሚከለክሉ ናቸው። ከዚህም ተጨማሪ ይህ ድርጊታቸው በሃይማኖትን ላይ ደባ የሚያደርሱና የሚፈጽሙ፣ ከአድማና ከሴራ ያራቁ፣ ከዕድሜ ባለጸጋ አባቶች ጋር በመጠጋት ለጊዜው እውነት የሚመስል በማር የተለወሰ የሀሰት መርዝ እያቀረቡና እያሰወሩ የስደተኛውን ሲኖዶስ እድገት የሚያቀጭጩ ናቸው። ታድያ እነዚህን ነው በሌሎች ካባ ስር አሾልኮ ለመሾም ውጣ ውረዱ?
የተወደዳችሁ ምዕመናን፣
እነዚህ የንጹሃን አባቶች ካባ የሚመስል ለብሰው እምነታችንን እና ሃይማኖታችን የሚፈታተኑትን “አባት” ነን የሚሉትን ለሹመት ማቅረቡ በቤተክርስቲያናችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱ በፊትና ከታሪክ ተወቃሽኑት የሚዳንበትን ጥንቃቄ ከወዲሁ እንዲወሰድ በትህትና እናሳስባለን።
ከዚህ በላይ በዝርዝር ካነሳናቸው ውስጥ፡-
1)     የቅዱስ ፓትርያርኩን ክብርና ማዕረግ ያላገናዘበና በምዕመናኑ አስተያየት ያልሰጠበት የሲኖዶሱ የመተባበሪያ ደንብና ድርጅታዊ መዋቅር በአግባቡ ተስተካክሎ ምዕመናኑ አስተያየት ሰጥቶበት በጠቅላላው የሲኖዶስ ጉባኤ ሳይጸድቅ፣
2)    የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይ ምላሽ ሳያገኝ፡
3)   አንዳንድ አባቶች በአደባባይ ለይስሙላ በካህናቱ መካከል ምንም አይነት መከፋፈልና አለመግባባት እንደሌለ በማስመሰል ምዕመናኑን የሚሸነግሉት ቀርቶ እየጠፋ ያለው ፍቅርና ሠላም ሳይወርድ
የቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እርምጃ ለመውሰድ ቢሞክሩ፣ ከላይ በዝርዝር የተመለከተውን ድርጊታቸውን ስም በመጥቀስ ከተጨባጭ መረጃ ጋር ለእናንተ ለእግዚአብሔር ተገዢ ለሆናችሁትና ጎንበስ ቀና እያላችሁ ቤተክርስቲያናችንን በጉልበታችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ ለምታገለግሉ ምዕመናን የምናቀርብ መሆናችንን በትህትና እየገለፅን አስተያየታችሁንም ሆነ ሃሳባችሁን ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ እንድትልኩን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ሁሉን አድራጊና ፈጻሚው ኃይል እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ!
ግልባጭ
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳሳት ዘኢትዮጵያ
ለቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ኮሚቴ
መጋቢት 22 ቀን 2008

P.O.Box 111852
Campbell, CA 95011-1852

32 comments:

 1. Thank you Aba Selama for posting something this grave and important for the Diaspora Christian community. This really is an eye opener. Also thank you to those of you concerned Christians that had written the article, as you had stated after trying for so long to correct the problem. It is the hopeful that contributes his/her hard earned money toward buying a church building and funding every expense the church incurs including salaries for the clergy. But after years of selfless contributions of funds, expertise, time, etc. the building is paid off and debt is no more. Members start relaxing from the burden of paying off debts, then almost instantly trouble hits, disagreements break out, divisions, confusions are thrown into the mix by none other than the slimy Woyane and Mahibere Kidsuan. They want to take over, confiscate and rob the monies and the church away from the straggling members that paid debts for many years to secure a house of worship. As shown in this article they have gone beyond the robbery and now they have infiltrated the Legal Synod and are in the process of dismantling it and replacing it with their own cronies. This warning might have come a few years too late, but may be just may be there might be a chance to redeem this Synod if the hopeful heeds to the warning and wakes up from a long sleep and says enough is enough and throw out these robbers from its churches as well as from the Synod. We urge this committee to keep its promise to post the names and disgraceful historical biographies of the infiltrators that are creating turmoil and sucking the blood of the Diaspora Christians so that everyone at every church knows to purge them before they suck him/her out dry.
  God is Great! Jesus is Lord!

  ReplyDelete
 2. ለተሃድሶ ኑፋቄ አልመች ሲል የአዞ እንባ ታነባላችሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለተሃድሶ ኑፋቄ አልመች ሲል የአዞ እንባ ታነባላችሁ።
   አዞውማ አንተ እኮ ነህ ማህበረ ሰይጣን! እንደለመድከው አንተው አልቅስ እንጂ! እነዚህ አባቶችማ ማንነታቸውን በመጀመሪያው አምስት መስመሮች ገልጹልህ። ሳታነቡ ዝም ብላችሁ እንዴት ትኮንናላቸሁ። ሰይጣን እንኳን ብልህ ነበር ውነት ተናግሮ ውሸት እየቀላቀለ ነበር የሚያሳስት፤ ምነው ተከታዮቹ ደነዛችሁ? የሰጠህን ስራ እንደሚፈልገው ካልሰራህለት ሰይጣን ቀልድ አያውቅ ፤ ይቅርታ አያውቅ አስፈንጥሮ ነው ወደ ሲኦል የሚወረውርህ። ጥጋብህ ሲበርድልህ ከስድብ ስትቆጠብና ወደ ልብህ ስትመለስ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው በይቅርታ እጁን ዘርግቶ የሚቀበልህ። ለመሆኑ እነዚህን የተራራ ያህል ግዙፍ የሆኑ ቃላቶች በምን አገኘሃቸው? ሲሉ ሰምተህ አላዋቂ እንዳትባል ዝም ብለህ እንደለጠፍከው ያስታውቅብሃል። ተሃድሶ፤ ኑፋቄ። እስቲ መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጥልህ የበራለት መምህር ፈልግና ምን ማለት እንደሆነ ያስረዳህ። ከተረዳህ ወደዚች መድረክ ብቅ በልና ስለተማርከው ምስክርነት ስጥ። የያዘህ አለቅ ብሎህ እጭለማህ መቆየት ከፈልግህ ደግሞ መብትህ ነውና ተጠቅምበት። ወደ ጥልቁ ከመውረድህ በፊት ግን ግድየለህም እግዚአብሔርን ከልብህ ፈልገው። በዮሐንስ ወንጌል ም፫ ቁ ፫-፭ ኢየሱስ ክርስቶስ ኒቆዲሞስን ሲያስተምር ሰው ከውሃና ከመንፈስ እንደገና ካልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገባም ነው ያለው። ተሃድሶ ይልሃል ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ከውሃና ከመንፈስ ስእንደገና መወለድ ማለት ነው። ሌላው ደግሞ “ኑፋቄ” ብለሃል ገላትያ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፮-፱ ጳውሎስ ሲያስተምር ሃዋሪያት ካስተማሩት ልዩ ወንጌል የሚያስተምር መልአክም ቢሆን የተረገመ ይሁን ብሏል። ታዲያ ይሄን የሚያክሉ ቃላቶች እንዴት ብትጠግብ በእነዚህ አባቶች ላይ ትሰነዝራለህ?? ጌታ ይገስጽህ ከጭለማም ያወጣህ ዘንድ ጨርቅህን ቀደህ አመድ ነስነሰህ ወደ እግዚአብሔር አልቅስ።

   Delete
 3. የሚገርመኝ የአባ ሰላማዎች የምትሰብኩት ሰላምን ሳይሆን እረብሻን ወነጌልን ሳይሆን ወንጀልን ስድብን ይገርማል የምታወሩት ስለ ማህበረ ቅዱሳን ነው እስኪ ተዉቱ ድናይ አትወርውሩ ማህበረቅዱሳን እንደሆነ ጠበቂው እግዚአብሔር ነው ለቤተክርስቲያናችን ቅን አገልጋዮች ናቸው ና ተውት ማህበሩ ችግር ሲገጥመው የሚደክም አይመሰላችሁ ይበረታል እንጂ ስድብ አገልግሎቱን አያደናቅፈውም

  ReplyDelete
 4. እናመሰግናለን ስለ መረጃው

  ReplyDelete
 5. ድርሳነ ሚካኤል ደጋሚዉ ባለ ንቅሳቱ(tatto),እና ባለ መቁጠሪያው አንዷአለም ዳግማዊ በሂደበት ሁሉ እንደበጠበጠ ነው ሰፋኒት ነኝ ከዳላስ ሚካኤል

  ReplyDelete
 6. ድቅምቄ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ።አይመለከታችሁም???

  ReplyDelete
  Replies
  1. If you were a christian you would not say that. The church is every christian's concern and business to take care of it. As Paul put bluntly in simple language in 2 Cor. 11:27-28 ("27 I have been in labor and hardship, through many sleepless nights, in hunger and thirst, often without food, in cold and exposure. 28 Apart from such external things, there is the daily pressure on me of concern for all the churches". Ask your self if you have any concern at all about your christian brothers and sisters. This one sentence says a lot about you. You sound like part of the clergy that is enjoying the American life who cares nothing about the flock
   that you are given the responsibility to shepheard. This people have reported what concerened them most and instead of your insults you should give you response or opinion and if you are part of the problem that is stated in the article, here is your chance to explain yourself to the sheep you might be leading astray.

   Delete
  2. አይ አያ እንቶኔ! ክርስትናው በመስኮት ተወረወረና ፤ ተቆርቋሪዎች አባቶችን ማንጓጠጥ ተጀመረ? ይቺ ናት ክርስትና እንግዲህ፤ ስንት ዘመን ስትለመኑ እንደከረማችሁ በግልጽ አስቀምጠዋል። መልስ ከመስጠት ይልቅ ሹመት ሊቀርብኝ ነው፤ ጉዴ ሊወጣ ነው እያሉ ድረገጽ ለማዘጋት ከመሯሯጥ ይልቅ። ዘላቂ መፍትሄ መፈለጉ ይሻል ነበር። እነዚህን አባቶች እድሜያቸውን እግዚአብሔር ያርዝምልን እንደምእመናንነታችን የቀረብልንን ጽሁፍ አንብበን ጉዳዩን ተረድተናል። የሚቀጥለውንም በጉጉት እንጠብቃለን።

   Delete
 7. ለአባ ጽጌ፣ ለዲያቆን አንዱአለም እና ለመሰሎቻቸው ወዮላቸው! እነርሱ ምናልባት ሰውን የጎዱ መስሏቸው ይሆናል ይህን ፀረ ክርስቲያን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉት፤ ነገር ግን ክርስቶስን እየተቃወሙ መሆናቸውን የተገነዘቡት አይመስልም። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9 ቁጥር 5 ላይ የሚገኘውን "የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ብሎ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳውል የነገረውን ቃል ቢረዱት ይህን ሰይጣናዊ ሥራቸውን በገቱ ነበር። የሥልጣን ጥማት እና ጥቅም ከክርስትና ሕይወት ጋር አይሄድም፤ ይህ ሁሉ ሩጫ የወያኔን ዓላማ ለመፈጸምም ከሆነ ቅስናቸውን አፍርሰው የፖለቲካውን ጎራ ይዘው ከጨለማው መሪ ከአለቃቸው ከሰይጣን ጋር የያዙትን ሂደት ይቀጥሉ፤ በሰላም እና በእውነት እግዚአብሔርን አምልኮ መኖር የሚፈልገውን ሕዝብ በደፉት ቆብ እና በሃይማኖት ሥር ተደብቀው ይዘውት ገደል አይግቡ። ኢየሱስ የሞተው ለሁሉም ነው ለእነርሱም ጭምር። የወንጌልን መስፋፋት መቃወምና ወንጌላውያኖችን ለመኮነን እና ለማሳደድ እንቅልፍ ማጣት ማለት ክርስቶስን እራሱን መቃወም ነው። እርሱን ተቃውሞ ደግሞ ራስን ክርስቲያን አድርጎ መመጻደቅ የመጨረሻ ክህደት ነው። የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ እንዳስቀመጠው "ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው" ይላል፤ እና እነርሱም ነፍሰ ገዳዮች ናቸው። እውነተኛ ክርስቲያኖች ወንድሞቻቸውን አይጠሉም ሰይጣናዊ ተግባራቸውን እንጂ፤ ስለዚህም ለእነዚህ የሰይጣን መልእክተኞች እግዚአብሔር አእምሮአቸውን ከፍቶላቸው ማንነታቸውን ተረድተውና ተጸጽተው ንስሐ የሚገቡበትን እድል እንዲሰጣቸው እንጸልይላቸዋለን። ይህንንም አንገብጋቢ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለሕዝብ በዚህ ጽሑፍ እንዲደርስ ላደረጉት ክርስቲያኖች እና አገልጋዮች እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንዲቆም፣ እንዲያበረታቸው፣ እና አብሯቸው ለውጊያ እንዲወጣ ያለማቋረጥ እንጸልይላቸዋለን። እውነት ትመነምናለች እንጂ አትጠፋም። ቤተክርስቲያንም በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተች ስለሆነች አትጠፋም። ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው! የቤተክርስቲያን ራስ ነው!!

  ReplyDelete
 8. Egziabhere yebarkachehu! endih legta leyesus kerstos yekomachehu yeorthodox lejoch bemenorachehu Egziabhere mesgana yegebaw!!

  ReplyDelete
 9. May God bless all. Thanks for the info, I appreciate. I am really bothered and angry about what is going on in the Synodos. Please get together and take the weed out, from the healthy plant. Dear our Synodos, you heard or seen a deacon now a priest, insulted his Papas, treaed him badly but nobody did anything. He is dividing everybody and created groups, like weyane. If you don't stop this person, then it is up to you. God bless all.

  ReplyDelete
 10. ስራ ፈት ጡረተኞች የጻፊት ነው። በሀገር ውስጥም ጡረተኛች እየተመረጡ ነው የሚያመሳቅሉት። ህጋዊ ሲኖዶስ ከምንም በላይ አንድ የሆነበት ወቅት ነው። ራሳቸውን የሽምግልና ኮሚቲ ብለው የሚጠሩት ሰዎች ስራ ስላጡ የተደሰቱ አይመስልም። ለማንኛውም እነ አቶ ዘውገ የቅንጅት ሽምግልና አበላሽተው እዚህ ደግሞ እኛ ያላቦካነው ዳቦ አይጋገርም እያሉን ነው። ሲኖዶሱ ለምን አንድ ሆነ እያሉ ነው። ወረቀቱ 95% ውሸት ነው። አባ ሰላማ ለምን እንዳስተናገደው አልገባኝም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why don't you understand that Abaselama Blog entertain this paper? It is simply, the blog is from and to the Protestants.!!!!!!!!

   Delete
  2. You are right! there is no way you would understand this! This is beyond your knowing capacity! Ato Zewge might be a retiree but at least everyone knows he stands for his Orthodox religion and fight as much as he can to bring peace and order to this Synod that you and your crony friends are trying to destroy for your almighty dollar that you worship. As a woyane you should know better than to stick your finger on retirees that are worshiping The One God and fighting the likes of you from destroying this Synod by transplanting your aba Taddesse, aba Andualem and aba Tsige as Patriarch, Secretary of the Synod etc....You need to leave these elders alone, whom you insult by calling them retirees! Then again you are born and raised to speak this way! No manners, ignorant and arrogant! They are beyond your pay grade. You tried to denigrate them by calling them retirees, their article 95% lie, have nothing to do, etc... You need to look at yourself in the mirror, a miracle may happen if your horns fall off. This ugly stench smells like Merchaw and associates (the devil's alternatives). It is time to sober up. They (the elders) have stated that everything in this article is 99.9999% true, we would rather trust them who would benefit nothing by putting themselves and their reputation out there than a bunch of crooks and bullies that are out there robbing churches and creating havoc amongst believers. Don't cry yet!, you will have ample time for that, when like they say they put out your names and the evidence to support your crimes posted on websites for the whole Christian world to see and prove who is telling the truth. Aba Selama had put out the evidence (divorce certificate) for one of you who has no shame to do the liturgy every Sunday against the rules of the Orthodox religion, you call that a lie too?????????

   Delete
  3. You said you don't know why Aba Selama posted it? What do you know? Nothing! Nothing at all! You must be a member of the famous group known as the walking dead! You live to eat and rob churches blind!! This was your Job in Ethiopia, you come here what do you do? The same old thing, you are addicted to your evil self you can't see straight!! From the one paragraph you wrote you are scared......your story is going to come out!! Every so often you all need to check your pants. I hope they post all of your stories and everybody knows the scum of the earth you all are. Read the article at least 10 times, you may have a revelation of the Satanic evil you were doing to the Orthodox faith and its leaders. You deny the Patriarch’s authority, insult and throw out Bishops from churches, put Aba Woldetensae in jail and kick out church members and clergy from their own churches and you say these people write a story that is 95% false? You have been lying so much, you would not know the truth if it slaps you upside down. How dare you insult our intelligence! Read Genesis 3:14 you should find yourself somewhere in that verse. RIP

   Delete
 11. Thank you abaselama for posting this you my run but you can' hide Adualm {MK} you hide for this long .it is time to put your true face

  ReplyDelete
 12. ይገርማል፡ እጅግም ያሳዝናል፡፡ እዚህ በአገር ቤት ቤተ ክርስቲያንን የሚበጠብጠው ቀንዳሙ ሰይጣን፡ እስከ ምዕራብ አገሮችም የፀላዔ ሰናያት ክንፉን መዘርጋቱ፡ ምን ያህል መንፈስ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን እንደራቀ ያሳያል፡፡ ኧረ ምእመናን እንንቃ፡ ወደ እግዚአብሔር እንጩኸ እናልቅስ፡ መፍትሒው ከእርሱ ዘንድ ነውና፡፡

  ReplyDelete
 13. በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 9 ቁጥር 5 ላይ የሚገኘውን "የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ብሎ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳውል የነገረውን ቃል FOR ALL JESUS CHRIST TEKAWAMIWOCH -

  ReplyDelete
 14. The migrated synod? Then the legal synode?

  ReplyDelete
 15. መልካም ሰላማዎች ጥሩውን ስም ይዛችሁታል አፋጂዎች ብትሉት ይሻላችሁ ነበር ለአባቶቼ ለአባ ጽጌ እና ለቀሲስ አንዱአለም የአገልግሎት ዘመናችሁን እግዚያብሄር ይባርክ። እውነት እውነት ነው መስክሩ ብሏል የያዛችሁት አቋም በጣም ጥሩ ነው እነዚህ አሁን ፓፓስ ለመሁን የሚመረጡ አባቶች የተሃድሶ ምልምሎች ናቸውቭእና በዚህ በውጩ ሲኖዶስ ስር የሚደረገው ሽኩቻ በጣም የምእመናኑን ህይዎት እያበላሽ ነው ድብልቅልቁ ወጥቷል እውነት የሚናገር የሚያወጣ ዎይም ታልቅ የሚገስጽ አባት ስለጠፋ የማንም ፕሮቴስታንት ማላገጫ አደረጋችሁት አሁን አብዛኛው መእመን አውቆባችኋል የሚደርገው ስራ ያሳፍራል ቤተክርስቲያንን ለማደስ ዘመናዊ ለማድረግ እረ ለኛ አስቡ አረ የስውን ልብ እንዲያድስቨድርጉ ስውን እያጠፋችሁ አብሶ ልጆቻችን እውነተኛዋን ኦርቶዶክስ አውቀው እንዳያድጉ የምታደርጉት ሁሉ የውጩን ሲኖዶስ ለመቃወም ትጥቁን እየታጠቀ ይገኛል።እናንተም እራሳችሁን ፓፓስ ለማድረግ የምትቋምጡ በሙሉ እራሳችሁን መጀመሪያ ከመፍቅና ስራ አስወጡ።አለዚያቭቤተክርስቲያንን እያሸሹቭ ፓፓስ መሁን ሃጢያት ይመስለኛል ጥሩ ምሳሌዎች ሁኑን እባካችሁ ስለፈጣሪ አታሰድቡን። እግዚያብሄር አይነልቢናችሁን ይክፈት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድማችን “ሰላማዎች፤ አፋጂዎች” የሚሉ ሁለት ተቃራኒ ቃላቶች በመጠቀም ትችት ይሁን ዘለፋ ባለየለት አረፍተ ነገር ጀምሮ አባቶቹን ካመሰገነና ከመረቀ በኋላ ስለያዙት አቋም ጥሩነት መስክሮ ሲያበቃ ወዲያው የአእምሮ ቀውስ የደረሰበት ይመስላል ሲባርካቸው የቆየውን አባቶች መልሶ ሲያወግዝ፤ ሲረግም፤ ሲማጸን ወዘተርፈ ይታያል። ይህ ሰው ምናልባት እየዘለፈ ያለው የሚያመሰግናቸውን አባቶቹን እንደሆነ የተረዳ አይመስልም። አርቲክሉንም እንዳላነበበው ግልጽ ነው። ምከንያቱም የአርቲክሉ ጸኃፊዎች ለጠቆሟቸው ችግሮች ቀንደኛ ባለቤት ያደረጓቸው እነዚህን ሁለቱን አባቶች ሲሆን የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም አብያተ ክርስቲያናቱንም ሆነ ሲንዶሱን አሁን ካለበት ምስቅልቅል ያደረሱት በዋናነት እነዚሁ አባቶችና ግብረ አበሮቻቸው እንደሆኑ በተደጋጋሚ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል።
   አስተያየት ከሰጡት አንባቢዎች ውስጥ አንድ ሁለቱ እባካችሁ አስተያየት ከመስጠት በፊት አንብቡ ማለታቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን ጽሁፉን ባያነብም ያሰፈራቸው ነጥቦች ከልብ የመነጩና የሃይማኖቱና የምእመናኑ ችግር በተለይም የነገ ተረካቢዎች እንዳይኖሩ የሚሰራ ሴራ እንዳለ የገባው ይመስላል። ያልገባው ግን ይሄን ሴራ ጠንሰሰው ከወያኔ ጋር በማበር ለስልጣንና ለገንዘብ የሚሯሯጡት አባቶቼ የሚላቸው በተደጋጋሚ ስማቸው በአርቲክሉ መሃል የተርከፈከፈው ካህናትና ግብረ አበሮቻቸው እንደሆኑ ነው። ሰውን ማታለል ይቻል ይሆናል እግዚአብሔርን ግን ማታለል አይቻልም። ነገ የነሱ እንዳልሆነች የዘነጉት ካህናትም ሆኑ ምእመናን እግዚአብሔርን ሳይፈሩ አይናቸውን ጨፍነው ምን ያደርገናል በማለት ምእመናኑንም በመናቅ ለጥቅምና ለስልጣን ሲሯሯጡና እፊታቸው የቆመውን ሁሉ እየዳጡ አሁን ካለንበት ችግር ላይ አድርሰውናል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በአውድ ምህረት ቆመው የእግዚአብሔርን ስም ጠርተው እነርሱ እውነተኞች የሚሉትን የማይደግፍ ሁሉ ግን ውሸታም እንደሆነ በጽሁፍ ሳይቀር በአደባባይ እንዲሁም በድህረ ገጽ ሳይቀር ሲያወግዙ ኖረዋል። ወንድማችን ይኸን ሳይረዳ ከምስጋናው በኋላ የሚከተለውን ጽፏል።
   “እነዚህ አሁን ፓፓስ ለመሁን የሚመረጡ አባቶች የተሃድሶ ምልምሎች ናቸውቭእና በዚህ በውጩ ሲኖዶስ ስር የሚደረገው ሽኩቻ በጣም የምእመናኑን ህይዎት እያበላሽ ነው ድብልቅልቁ ወጥቷል እውነት የሚናገር የሚያወጣ ዎይም ታልቅ የሚገስጽ አባት ስለጠፋ የማንም ፕሮቴስታንት ማላገጫ አደረጋችሁት አሁን አብዛኛው መእመን አውቆባችኋል የሚደርገው ስራ ያሳፍራል ቤተክርስቲያንን ለማደስ ዘመናዊ ለማድረግ እረ ለኛ አስቡ አረ የስውን ልብ እንዲያድስቨድርጉ ስውን እያጠፋችሁ አብሶ ልጆቻችን እውነተኛዋን ኦርቶዶክስ አውቀው እንዳያድጉ የምታደርጉት ሁሉ የውጩን ሲኖዶስ ለመቃወም ትጥቁን እየታጠቀ ይገኛል።እናንተም እራሳችሁን ፓፓስ ለማድረግ የምትቋምጡ በሙሉ እራሳችሁን መጀመሪያ ከመፍቅና ስራ አስወጡ።አለዚያቭቤተክርስቲያንን እያሸሹቭ ፓፓስ መሁን ሃጢያት ይመስለኛል ጥሩ ምሳሌዎች ሁኑን እባካችሁ ስለፈጣሪ አታሰድቡን። እግዚያብሄር አይነልቢናችሁን ይክፈት”
   ከልቡ ከሆነ ከእግዚአብሔር የሚደበቅ ወይም የሚያመልጥ ስለሌለ የማያዳላው እውነተኛና ትክክለኛው ዳኛ ፍርድ በእርሱ ሰዓት ይፈጸማል።
   አንድ አዛውንት ሲናገሩ “ወያኔ ከሃያ አምስት አመት በፊት ቅዱስ ፓትራያርክ መርቆሬዎስን ከስልጣን አውርዶ አቡነ ጳውሎስን በቦታቸው ሲያስቀምጥ የሰጠው የሀሰት ምክንያት በጠና ስለታመሙ አገልግሎት መስጠት አይችሉም የሚል እንደነበር ይታወሳል። ነገር ግን አሁን ከሃያ አምስት አመት በኋላ የእግዚአብሔር ቀን ሲሞላና ፍርድ ሲፈጸም ሁለቱ የወያኔ ባልስልጣናት የሉም አቡነ መርቆሬዎስ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት እዚህ ደርሰዋል። የወደፊቱም በእግዚአብሔር እጅ ነው።”
   እብራውያን ምእራፍ 4 ቁጥር 11-13
   “እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።”

   Hebrews 4:11-13
   “Because of this, let us have a strong desire to come into that rest, and let no one go after the example of those who went against God's orders.
   For the word of God is living and full of power, and is sharper than any two-edged sword, cutting through and making a division even of the soul and the spirit, the bones and the muscles, and quick to see the thoughts and purposes of the heart. And there is nothing made which is not completely clear to him; there is nothing covered, but all things are open to the eyes of him with whom we have to do.”

   Delete
  2. ወንድማችን “ሰላማዎች፤ አፋጂዎች” የሚሉ ሁለት ተቃራኒ ቃላቶች በመጠቀም ትችት ይሁን ዘለፋ ባለየለት አረፍተ ነገር ጀምሮ አባቶቹን ካመሰገነና ከመረቀ በኋላ ስለያዙት አቋም ጥሩነት መስክሮ ሲያበቃ ወዲያው የአእምሮ ቀውስ የደረሰበት ይመስላል ሲባርካቸው የቆየውን አባቶች መልሶ ሲያወግዝ፤ ሲረግም፤ ሲማጸን ወዘተርፈ ይታያል። ይህ ሰው ምናልባት እየዘለፈ ያለው የሚያመሰግናቸውን አባቶቹን እንደሆነ የተረዳ አይመስልም። አርቲክሉንም እንዳላነበበው ግልጽ ነው። ምከንያቱም አርቲክሉን የጻፉት አዛውንቶች ለጠቆሟቸው ችግሮች ቀንደኛ ባለቤት ያደረጓቸው እነዚህን ሁለቱን አባቶች ሲሆን የተሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም አብያተ ክርስቲያናቱንም ሆነ ሲኖዶሱን አሁን ካለበት ምስቅልቅል ያደረሱት በዋናነት እነዚሁ አባቶችና ግብረ አበሮቻቸው እንደሆኑ በተደጋጋሚ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል።
   አስተያየት ከሰጡት አንባቢዎች ውስጥ አንድ ሁለቱ እባካችሁ አስተያየት ከመስጠት በፊት አንብቡ ማለታቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን ጽሁፉን ባያነብም ያሰፈራቸው ነጥቦች ከልብ የመነጩና የሃይማኖቱና የምእመናኑ ችግር በተለይም የነገ ተረካቢዎች እንዳይኖሩ የሚሰራ ሴራ እንዳለ የገባው ይመስላል። ያልገባው ግን ይሄን ሴራ ጠንሰሰው ከወያኔ ጋር በማበር ለስልጣንና ለገንዘብ የሚሯሯጡት አባቶቼ የሚላቸው በተደጋጋሚ ስማቸው በአርቲክሉ መሃል የተርከፈከፈው ካህናትና ግብረ አበሮቻቸው እንደሆኑ ነው። ሰውን ማታለል ይቻል ይሆናል እግዚአብሔርን ግን ማታለል አይቻልም። ነገ የነሱ እንዳልሆነች የዘነጉት ካህናትም ሆኑ ምእመናን እግዚአብሔርን ሳይፈሩ አይናቸውን ጨፍነው ምን ያደርገናል በማለት ምእመናኑን በመናቅ ለጥቅምና ለስልጣን ሲሯሯጡና እፊታቸው የቆመውን ሁሉ እየዳጡ አሁን ካለንበት ችግር ላይ አድርሰውናል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በአውደ ምህረት ቆመው የእግዚአብሔርን ስም ጠርተው እነርሱ እውነተኞች የሚሉትን የማይደግፍ ሁሉ ግን ውሸታም እንደሆነ በጽሁፍ ሳይቀር በአደባባይ እንዲሁም በድህረ ገጽ ሳይቀር ሲያወግዙ ኖረዋል። ወንድማችን ይኸን ሳይረዳ ከምስጋናው በኋላ የሚከተለውን ጽፏል።
   “እነዚህ አሁን ፓፓስ ለመሁን የሚመረጡ አባቶች የተሃድሶ ምልምሎች ናቸውቭእና በዚህ በውጩ ሲኖዶስ ስር የሚደረገው ሽኩቻ በጣም የምእመናኑን ህይዎት እያበላሽ ነው ድብልቅልቁ ወጥቷል እውነት የሚናገር የሚያወጣ ዎይም ታልቅ የሚገስጽ አባት ስለጠፋ የማንም ፕሮቴስታንት ማላገጫ አደረጋችሁት አሁን አብዛኛው መእመን አውቆባችኋል የሚደርገው ስራ ያሳፍራል ቤተክርስቲያንን ለማደስ ዘመናዊ ለማድረግ እረ ለኛ አስቡ አረ የስውን ልብ እንዲያድስቨድርጉ ስውን እያጠፋችሁ አብሶ ልጆቻችን እውነተኛዋን ኦርቶዶክስ አውቀው እንዳያድጉ የምታደርጉት ሁሉ የውጩን ሲኖዶስ ለመቃወም ትጥቁን እየታጠቀ ይገኛል።እናንተም እራሳችሁን ፓፓስ ለማድረግ የምትቋምጡ በሙሉ እራሳችሁን መጀመሪያ ከመፍቅና ስራ አስወጡ።አለዚያቭቤተክርስቲያንን እያሸሹቭ ፓፓስ መሁን ሃጢያት ይመስለኛል ጥሩ ምሳሌዎች ሁኑን እባካችሁ ስለፈጣሪ አታሰድቡን። እግዚያብሄር አይነልቢናችሁን ይክፈት”
   ከልቡ ከሆነ ከእግዚአብሔር የሚደበቅ ወይም የሚያመልጥ ስለሌለ የማያዳላው እውነተኛና ትክክለኛው ዳኛ ፍርዱ በእርሱ ሰዓት ይፈጸማል።
   አንድ አዛውንት ሲናገሩ “ወያኔ ከሃያ አምስት አመት በፊት ቅዱስ ፓትራያርክ መርቆሬዎስን ከስልጣን አውርዶ አቡነ ጳውሎስን በቦታቸው ሲያስቀምጥ የሰጠው የሀሰት ምክንያት በጠና ስለታመሙ አገልግሎት መስጠት አይችሉም የሚል እንደነበር ይታወሳል። ነገር ግን አሁን ከሃያ አምስት አመት በኋላ የእግዚአብሔር ቀን ሲሞላና ፍርድ ሲፈጸም ሁለቱ የወያኔ ባልስልጣናት የሉም አቡነ መርቆሬዎስ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት እዚህ ደርሰዋል። የወደፊቱም በእግዚአብሔር እጅ ነው።”
   እብራውያን ምእራፍ 4 ቁጥር 11-13
   “እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።”

   Hebrews 4:11-13
   “Because of this, let us have a strong desire to come into that rest, and let no one go after the example of those who went against God's orders.
   For the word of God is living and full of power, and is sharper than any two-edged sword, cutting through and making a division even of the soul and the spirit, the bones and the muscles, and quick to see the thoughts and purposes of the heart. And there is nothing made which is not completely clear to him; there is nothing covered, but all things are open to the eyes of him with whom we have to do.”

   Delete
 16. ይአየነዉን እንናገራለን የሰማነዉን እንመሰክራለን
  ዮሐ ፫፡ ፲፩
  የዉጩ ሲኖዶስ እንደ ዘንድሮ ሰላም ሁኖ አያዉቅም ጸሕፊዉ ሊያደናግረዉ የፈለገዉ ነገር ያለ ይመስለኛል በእርግጥም ነዉ።
  አባ ሰላማዎችም የማያንጽ ጽሑፍ ባታወጡ መልካም ነዉ ብየ አምናለሁ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስቲ ተጠየቅ፤ ማነህ? ምንአልክ? ወይ ማንበብ ሳትችል በጭፍን የመጻፍ አመል የፊጥኝ ይዞሃል! አለበለዚያ ደግሞ ምን ተባለ እያልክ ከሰማኸው የሚሰማህን የምትለጥፍ ነህ። ከአንባቢዎች አንዱ በሰጡት አስተያየት ላይ “ለዚህ አርቲክል መልስ ከመስጠት በፊት ፲ ጊዜ ይነበብ” የሚለው እንዳአንተ ላለው የሚለውን ለማያውቅ ስለሆነ ጊዜህን ወስደህ ፲ ጊዜ አንብበህ ብታጤነውና ብትጫጭር ድንገት ምናልባት ይረዳህ ይሆን?
   ስላላነበብከው እንጂ ጸኃፊዎቹ በዝርዝር በጽሁፋቸው እንደገለጹት ከሆነ ሲኖዶሱ ከመቼውም ጊዜ የባሰ ችግር ላይ ነው። ከጻፍከው አደናግር መረዳት የሚቻለው ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከትህ መሆኑን ነው። ምናልባትም ታሪካቸውን ከነስማቸው በማስርጃ አስደግፈን እናወጣቸዋለን ከሚባሉት አንዱ ሳትሆን እንዳልቀረህ መረዳት አስቸጋሪ አይሆንም። እነዚህ ሰዎች ጉዳዩን በጥሞና አጢነው ከመጻፋቸው በፊት የሚመለከተውን ባለሥልጣን ከታች እስከላይ እስከ ፓትራያርኩ በቃልም በጽሁፍም ያሳሰቧቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ማቅረባቸውን አትተው ማንም ምንም እንዳላደረገ ጨምረው ገልጸዋል።
   1. እግዚአብሔር የቀባቸውን የቅዱስ ፓትራያርክ ስልጣን በመጋፋት የኦርቶድክስ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት በማታውቀው ህግ በደብዳቤ አንቀጽ ፲ ቁጥር ፲ ተጠቅሶ እንደራሴ የመሾም ስልጣን የለዎትም ተብለው ከታች ወደ ላይ ስልጣናቸው ተሽሯል።
   2. ከ፭ የማያንሱ ጳጳሳት ከቦታቸው ተባረው በየቦታው ተጠልለው እያሉ እነአባ ታደሰን የመሳሰሉ ቅዱስ ፓትራያርኩን ቤተክርስቲያን መግባት አይችሉም ብለው ያገዱ እና እንደ አባ ጽጌድንግል ያሉ መነኮሳት ካልተሾሙ ያውም የቀድሞው አባ ታደስ፤ የዛሬው አባ ገብረስላሴ፤ የነገው በሟች ስም አቡነ ዜና ማርቆስ መባል አለብኝ የሚሉ አመጸኛ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።
   3. በጽሁፋቸው ላይ በተራ ቁጥር ፩ ያስቀመጡት ህገ ደንብ ሲነበብ የፓትራያርኩን ስልጣን ለመሻር የተጠቀሰው የነአባ ጽጌድንግል የስራ ውጤት ሲሆን ቅዱስ ፓትራያርኩም ሆኑ አብዛኛው ጳጳሳትና እንዲሁም ምእመናኑ የማያውቁት እንደሆነ በዝርዝር ተቀምጧል።
   ታዲያ ይኸ ነው ሲኖዶሱ “እንደዘንድሮ ሰላም ሆኖ አያውቅም” የተባለውና የሚያስብለው? ይኸ ሰላም ክሆነ ከዚህ በፊት ምን ይመስል ነበር የሚለውን ጥያቄ ያስከትላል። አንባቢ ይመርምር። ጸኃፊዎቹ አዛውንቶች ምንም የሚያገኙት ጥቅም ኖሮ ሳይሆን፤ ከፍተኛ ችግር አይተናል፤ ይታረም ብንል ሰሚ አጣን፤ ሃይማኖታችን ስለሆነ ይገደናል፤ ክርስቲያን የሆንክ ሁሉ ይግደደህ ነው የሚሉት ከጽሁፋቸው እንደምንረዳው። በተለይ የኦርቶድክስ ሃይማኖት ልጆች ክሆን ሊገደን ይገባል።
   ሳናነብ ባልተገራ አንደበት ደርሶ አዋቂ ለመምሰል “ጸሕፊዉ ሊያደናግረዉ የፈለገዉ ነገር ያለ ይመስለኛል በእርግጥም ነዉ።” ብሎ በሕዝብ ሚድያ ላይ ወጥቶ ከመዘባረቅ ይልቅ፤ በጥሞና አንብቦ አስተያየትን በጨዋነት መስጠት የክርስቲያን ተግባር ነው።

   Delete
 17. hahah Leba dirom sizerff enji sikafel aysmamam. Leba hula, gudu siweta, ewnet sigelet - mechereshaw yihew new. Ayy fetariye sirah dinkk new eko! Gena bizu gudd ale.

  ReplyDelete
 18. ምን ዓይነት አሳዛኝ ዘመን ላይ ደረስን፤ ቤተክርስቲያኗን የከበባት የበግ ለምድ የለበሰ የተኩላ መንጋ እና ከሥር ደግሞ መሠረቷን ገዘግዞ ለመጣል ቀን ከሌት የሚጥር የምስጥ መንጋ (termite) ነው። ቀሲስ ተብዬው የዳላሱ አንዱዓለም እና የስም መነኩሴው አባ ጽጌ እንዲሁም ማነው ያ ደግሞ አቡነ መርቆርዮስን ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ የከለከለው? ኧ... የሲያትሉ የትናንቱ ዲያቆን ታደሰ የዛሬው “አባ” ዲያብሎስ የነገው ማን ይሆን? እግዚአብሔር ይርዳቸው እንጂ መጨረሻቸው አያምርም ከነምርጫው ጋር ወያኔን በቡችላነት እያገለገሉ ስለሆነ የአሜሪካስ ውሻ ማእረግ አለው እነሱ ግን እንደኢትዮጵያ ውሻ ክፉ ስራቸው መርዝ ሆኖ ሳያጠፋቸው አይቀርም። እኔን ተሁሉም በላይ የሚደንቀኝ ነገር ቢኖር የአቡነ መልከጼዴቅ እንደዚህ ዓይነቱ አሳፋሪ እና ክርስቲያናዊ ያልሆነ ነገር ውስጥ ራሳቸውን መጨመራቸውና ማቅለላቸው ነው። እግዚአብሔርን እና መንጋውን አገለግላለሁ ብለው የተቀበሉትን አደራ በጎጠኝነት እና ምናልባትም በወያኔ ተዘዋዋሪ ድጎማ መተካታቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። ይህንን እንድል ያስገደደኝ ይሄ ሁሉ ሕገ ወጥ የሆነን ድርጊት ከማስቆምና እንዲታረም ከማድረግ ይልቅ ጭራሽ የፓትርያርኩን ሥልጣን እሚቃረን ደብዳቤ ላይ መፈረማቸው ነው። ጽሑፉን ያወጡት ሰዎች ምን ያህል ቀና እንደሆኑ ልረዳ የቻልኩት “የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ በማሳሳት አስፈርመው” ብለው ነው ጽሁፉ ላይ ያሰፈሩት እውነቱን ሳይረዱ ቀርተው አይመስለኝም ግን እርሳቸውን በማክበር ይሆናል የሚል ግምት አለኝ። አክብሮት አይከፋም ግን እሳቸው ከነአንዱአለምና ከሲያትሉ አባ ጋር ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ፓትርያርኩ ላይና ሲኖዶሱ ላይ ለሚፈጸመው እኩይ ሴራ ተባባሪ እና ብሎም በፊርማቸው አስፈጻሚ መሆንን ሲመርጡ ክብራቸውን በመስኮት አሽቀንጥረው እንደጣሉት ነው የምረዳው። በዕድሜ ያበለጸጋቸውን እግዚአብሔርን እንዲህ መፈታተናቸው ከሕሊና በላይ ነው። እግዚአብሔር በሐሰት የተመረዘውን አእምሮአቸውን ምናልባትም በጥቅም የተከለለውን ዓይናቸውን በጎጠኝነት የደነደነውን ልቦናቸውን እንዲያስተካክልላቸውና ለንስሃ እንዲያበቃቸው የሁላችንም ጸሎት ነው። የክህነትን ሥልጣን መጫወቻ ያደረጉትንም ካህናት ተብዬዎች በተንኮል በጥቅምና በስልጣን ጥማት እንደፊኛ የተነፋውን ልባቸውን የአምላክ ምህረት አፈንድቶት በኢየሱስ ጸጋ በንስሐ እንዲጠገን እንጸልይላቸዋለን፤ ኢየሱስም ምንም እንኳን አሳዳጆቹ ቢሆኑም ስህተታቸውን አምነው በጸጸት ቢመለሱ እጁን ዘርግቶ ከነቆሻሻቸው ተቀብሎ ለማንጻት ዝግጁ ስለሆነ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቸም እግዚአብሔርን የካደና በስም ክርስቲያን እየተባለ በየእሁዱ የኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያን የሚያጣብበው በነጠላ ታንቆና በመቋሚያ ተደግፎ የኢየሱስን ስም እየጠራ ተሰጥኦውን ሲመልስ፤ ስርአቱን፤ ወጉን ሲጠብቅ ለተመለከተው በተመስጦ ከራሱ ውጭ ካለ መንፈስ ጋር ግንኙነት የሚያደርግ ይመስላል። ቅዳሴው አልቆ መምህሩ በተለያየ አርእስት በማስተማር ክርስትና፤ ክርስቲያንነት፤ መዳን በሌላ በማንም የለም በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንጂ ሲሉ አሜን ሲል የዋለው የነጠላ ክርስቲያን በርዋን ሲወጣ እሱን ስም አትጥራብኝ አንተ ጴንጤ መሰልከኝ አስሬ ኢየሱስ ትላለህ ይላል። እንዴ እውስጥ ሆነህ በቅዳሴውም ሆነ በትምህርቱ አሜን ስትል አልዋልክም እንዴ? ሲባል ያ ሌላ ይኸ ሌላ ይላል። ይኸ ነው እንግዲህ የዘመኑ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በስም ክርስቲያን። እንዲህ ያለውን በጨለማ ውስጥ ያለ ህዝብ ነው ከዚህ በላይ ያለው ጸሃፊ ሊገልጽ እንደሞከረው የጠቀሳቸው ካህናትና በነሱ ተገን የሚነግዱ እኩያት ሃይማኖታችንን፤ ባህላችንን፤ ስርአታችንን ውድም አድርገው አጥፍተው ከአለማውያን የባሰ ቅሌት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ በማምጣትና በአማኞቹ ላይ ለመንገስ ምድር ሳይኖራቸው በአየር ላይ የስልጣንና የጥቅም ጥማታቸውን ለማርካት ሲሯሯጡ የሚታዩት። የጸኃፊዎቹ ዋነኛ ጥያቄ ካሉት ጳጳሳት ከአምስት በላይ የሚሆኑት ከምድብ ቦታቸው ተፈናቅለው በስደት አገር በየምእመኑ ተጠግተው እያሉ እነሱ ቦታ ሳይዙ ምርጫ ለምን አስፈለገ? ምርጫ ያስፈልጋል ከተባለም መጀመሪያ አስመርጭ ኮሚቴ ያሉ የወያኔ ወኪሎች ይወገዱ ከተመራጮቹም የሃይማኖቱ ቀንደኛ ጠላቶች የሆኑት የሲያትሉ ከይሲና የሎስአንጀለሱ የሳጥናኤል ደቀመዝሙር በፍጹም ለምርጫ መቅረብ የለባቸውም የሚል ነበር። ነገር ግን ከአንዳንድ የዜና ምንጮች እንደሚሰማው ያለ ህገ ደንብና ያለሕዝብ ድምጽ ምርጫውን በራሳቸው አጠናቀው በሲኖዶሱ ጸድቋል አስብለው ሊበተኑ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ይነገራል።
   ስለዚህ እነዚህን የሃይማኖቱ እውቀትም ሆነ የስርአቱ ግንዛቤ የሌላቸው አጉራዘለል ቢጽሃሳውያን እንደሳጥናኤል የታበዩና በምእመናኑ ላይ የሰለጠኑ ስለሆኑ ከፍ ወዳለ ስልጣን ሳይሆን እንደአባታቸው እንደሳጥናኤል ወደ ጥልቁ መውረድ ይገባቸዋል። እግዚአብሔርን ከማገልገልና ለሱ ክብር ከመቆም ይልቅ የራሳቸውን ክብርና ጥቅም አስቀድመዋልና ቤተክህነትን አፍርሰው ምእመናኑን ከመበተናቸው በፊት በውርደት ሊባረሩ ይገባቸዋል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በታሪኳና በሃይማኖቷ የትኛው ዲያቆን ነው ካህኑን ወይም ካህኑ ጳጳሱን ሽቅብ የሚተቸውና የሚሰድበው? በዚህ ዘመን በዚህ በውጭ ሲኖዶስ ጉድ እየታየና የኢትዮጵያ ሕዝብ እርግማን በሙሉ እየደረሰ በግልጽ እያየነው ነው። በሲያትል የሚገኝ ካህን ተብዬ የጵጵስና እጩ ፓትራያርኩን ከቤተክርስትያን እንዳይገቡ ሲያግድ፤ የሎሳንጀለሱ የቤተክህነት አስተዳዳሪ ተብዬው ሌላው የጵጵስና እጩ የፓትራያርኩን እንደራሴ ሹመት ሲያሽር፤ የዳላሱ ዲያቆን ቄስ አስተዳዳሪ ተብዬው ደግሞ የሃገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ሲያባርር እያየን ሲኖዶስ አለ ብለን አፋችንን ሞልተን ለመናገር አንችልም። ይኸ ሁሉ ሲሆን ግን አንድ ሁለት ሶስት እንኳን ለእውነት የቆሙ ጳጳሳት መጥፋታቸው የሚያሳዝን ነው። እንዴ የሉም ????????? ወይስ እግዚአብሔር የሚፈራ የለም ማለት ነው። ሃይማኖተኛ ነን ባይ ሚዲያውስ ይኸ ሁሉ ጽሁፍ ሲጻፍ የት አለ? ከአሜሪካ ሚድያ አይማሩም እንዴ? በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የደረሰውን ግብርሰዶም በምን አይነት ተከታትለው እንዳስቆሙት፤ አያዩም አያነቡም ማለት ነው ወይስ ምን አገባኝ ምን ቸገረኝ አይመለከትኝም ነው።
   የሌላውን ሃይማኖት ከማውገዝና ስም ከማጥፋት በፊት ቤትን ማጽዳት ያስፈልጋል። በጭፍን አማኙን ሕዝብ በተኩላ መሃል የበተናችሁ እረኞች ወዮላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ በእናንተ ላይ ይነዳል። ከእግዚአብሔር መደበቅ እንደማትችሉ አለመረዳታችሁ ከስራችሁ በግልጽ ይታወቃል ምክንያቱም የምታገለግሉት እግዚአብሔርን ሳይሆን ዲያብሎስን ስለሆነ ነው። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እናንተ ግን እግዚአብሔርን ሳትፈሩ የእረኝነት ስራችሁን ትታችሁ ለስልጣንና ለጥቅም ስትሯሯጡ ምእመኑ ክስና ጭቅጭቅ ሸሽቶ ወደ ጴንጤና ወደ ፕሮቴስታንቱ አለም እየፈለሰ ይገኛል። እግዚአብሔር ብድራታችሁን ይክፈላችሁ።

   Delete