Wednesday, April 13, 2016

“ሊቃናተ ኢታመጕጽ ተአዘዝ ከመ ዘለአቡከ” “ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት . . . ለምነው።” (፩ጢሞ. ፭፥፩-፪) -ክፍል ሁለት

Read in PDF
ክፍል ሁለት       
ከዘሩባቤል
በመጀመሪያው ጽሑፌ ዳንኤል በጻፈው ጽሑፍ ዙሪያ አጠቃላይ ነገሮችንና የጽሑፍን የመጀመሪያን አንቀጽ መሠረት በማድረግ ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ ይህን ጽሑፍ ለመላክ በዝግጅት ላይ እንዳለሁ አንዳንድ ያልተጠበቁ ለውጦች ተደርገዋል፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከኃላፊነታቸው ተነሥተው በሌላ ሥራ አስኪያጅ ተተክተዋል፡፡ በዳንኤል ጽሑፍ ውስጥ ከተነሡት ጉዳዮች አንዱ የቀድሞውን ሥራ አስኪያጅ የተመለከተ ሐሳብም ይገኝበታል፡፡ ይህንና በመጀመሪያው ጽሑፍ ያልተነሡትን አንዳንድ ነጥቦች በዚህ ጽሑፍ አነሣለሁ፡፡ መሠረት የማደርገውም የዳንኤልን ጽሑፍ ሁለተኛና ሦስተኛ አንቀጾችን ይሆናል፡፡

ዳንኤል በሁለተኛው አንቀጽ ፓትርያርኩን ዘልፎ የጻፈበት የጽሑፉ ማጠንጠኛ “ይተኛሉ” የሚል ነው፡፡ቅዱስነታቸው በተሾሙበት ዓመት፣ ባለጉዳይ ሊያነጋግራቸው ሲመጣ ወይም ስልክ ሲደውል “ተኝተዋል” እየተባለ መልስ እየተሰጠ ነው የሚል ወሬ በሰፊው የሚያስወሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ማንነታቸው ግን እስከ ዛሬ ድረስ ግልጽ አልነበረም፡፡ “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል” እንደሚባለው ዳንኤል በዚህ ወቅት ያወጣው አንድ ምስጢር ብዬ የማስበው ይህ ወሬ የተነሣውና ይወራ የነበረው ከማኅበሩና በማኅበሩ ሰዎች መካከል መሆኑን ነው፡፡ ይህም ሆነ ተብሎና የፓትርያርኩን ሥራ ገና ከመነሻው ለማጠልሸት በማሰብ የተወራ ወሬ እንጂ ፓትርያርኩን የሚገልጽ እንዳልሆነ በቅዱስነታቸው ላይ ሲወራ የነበረውና ቅዱስነታቸው እየሠሩ ያለው ሥራ ለየቅል መሆናቸው በገሃድ ታይቷል፣ በተለይ ለማቅ እኩይ ሥራ እንዳልተኙ በተግባር አሳይተዋልና፡፡

ዳንኤል በማኅበሩ ውስጥ ሲወራ የነበረውን ይህን ወሬ በአዝማች መልክ ያወረደውና የአንባቢዎቹን ትኩረት እንዲስብለት ያደረገው ፓትርያርኩ የማኅበሩን ጥቅም አላስጠበቁም በሚል ነው፡፡ ይህን ጊዜ ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በመጉዳት የማቅ ዓላማ አስፈጻሚ ቢሆኑ ኖሮ፣ “ኖላዊ ትጉሕ ዘኢይነውም” ብሎ ውዳሴ ከንቱ ይደግምላቸው ነበር፡፡ ሰው የሚለካው በማንነቱ፣ በያዘው እውነትና በዓላማው መሆኑ ቀርቶ ማኅበሩን በመደገፉ ወይም በመቃወሙ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አባቶችን ብፁዕ ቅዱስ የሚላቸው የእርሱን ጥቅም ሲያስከብሩለት ብቻ ነው፡፡ እንደሚፈልገው ካልሆኑለት ግን አሁን በፓትርያርኩ ላይ እንዳደረገው ማድረጉ አይቀሬ ነው፡፡ የማኅበሩ ፍሬ ዳንኤል በፓትርያርኩ ላይ የፈጸመውም ከዚህ የመነጨ ነው፡፡

ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደ ዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤” ሲል ዳንኤል የጻፈውን ሳነብ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም “ክሽፈት እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የተሰኘ መጽሐፋቸውን ያለ ዕውቀቱና ያለ አቅሙ እርሳቸውን በድፍረት ለመተቸት በመውተርተሩ ስለ እርሱ ከዓመት በፊት ያቀረቡት ሂስ ትዝ አለኝ፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት “[ዳንኤል ክብረት] ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው ዕውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ እንጂ ዐውቆ የሚጽፍ አይመስልም” (አዳፍኔ - ፍርሀትና መክሸፍ ገጽ 222)፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ የፈጠነው ዳንኤል ትክክለኛው መረጃ የለውም፤ መረጃ አድርጎ ያቀረበው በቅርቡ በሐራ ዘተዋሕዶ ላይ የወጣው የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አስተዳደር ኮሚቴ ቃለ ጉባኤና ደብዳቤ የያዘውን መረጃ ነው፡፡ እነዚህ ሰነዶች በተጠየቀው መሠረት ለሊቀ ማእምራን የማነ 500 ሺሕ ብር እንዲሰጥ መወሰኑን ይናገራሉ፡፡ ይኸው ዘገባ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን በመሆን እያገለገለ ባለው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይም እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ለዳንኤል መረጃ የሆነው እንግዲህ ይህ ነው፡፡

እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ልጅ ስለታመመና ወደ ውጪ ሄዶ መታከም ስላለበት ሥራ አስኪያጁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ እየሠሩ የነበረውን ውጤታማ ሥራ ከግምት ያስገቡ አንዳንድ በጎ ፈቃደኞች እርሳቸው እንዲህ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ እኛ ደግሞ ልጃቸው የሚታከምበትን ገንዘብ ብናዋጣ መልካም ነው ብለው በኢትዮጵያዊ ደንብ የጀመሩት እንቅስቃሴ ነበረ፡፡ በማንኛውም ድርጅት ወይም አካባቢ ተመሳሳይ ችግር የገጠመው ሰው ካለ እንዲህ መደረጉ የተለመደ ነው፡፡ ለሥራ አስኪያጁ የተደረገው እርሳቸው ከነበሩበት ስፍራ አንጻር የተደረገ መሆኑን ከግምት ማስገባት ከተቻለ ይህ ተግባር ተገቢ እንጂ ስሕተት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሥራ አስኪያጅ ስለሆኑ ለልጃቸው ማሳከሚያ ድጋፍ የተጠየቀው በየደብሩ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ሠራተኞች ላይ መሆኑ የተለየ መስሎ መታየት የለበትም፡፡ ጥያቄው ደግሞ በፈቃደኛነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነና ሥራ አስኪያጁ በደብዳቤም ሆነ በቃል ትእዛዝ አስተላልፈው ሳይሆን በፈቃደኛነት የተሰባሰቡ ሌሎች አስተባባሪዎች ያደረጉት ነው፡፡ ስለዚህ ሰብአዊ ጥያቄውን ተቀብለው ድጋፍ የሰጡ አሉ ያልሰጡም አሉ፡፡ በዚህ ውስጥ ከእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት የወጣው ደብዳቤም ሆነ ቃለ ጉባኤ  ዓላማው ሌላ ነው፡፡

ሁለቱም ከገዳሙ ቢወጡም እውነትን ፈላጊና አጥብቆ ጠያቂ ቢኖር ሕጋዊነታቸው ላይ ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም፡፡ የሚነሣው ጥያቄ የገንዘብ ድጋፉ እንዲደረግ የጠየቀው ማነው? እንዲሁም በየትኛው ቁጥርና ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ነው የተጠየቀው ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የለውም፡፡ የደብዳቤን ፕሮቶኮል ያልጠበቀ ደብዳቤ ነው፡፡ ስለዚህ ሰነዶቹ ምንም እንኳን ከደብሩ የወጡ ቢሆንም ከሊቀ ማእምራን የማነ በስተጀርባ የተጎነጎነ ሴራ መኖሩን ይጠቁሟሉ፡፡ ይህም ወሬ በቤተ ክህነቱና በሀገረ ስብከቱ እንዲሁም በየአድባራቱና በየገዳማቱ ሲወራ ነበር፡፡

ከዚህ ሴራ በስተጀርባ  የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እጅ መኖሩ ቤተ ክህነት፣ አገረ ስብከትና በየደብሩ ሰራተኞች ዘንድ በሰፊው ሲወራ ነበር፡፡  ሊቀ ማእምራን የማነ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑ ወዲህ ንቡረ እድ ኤልያስ ከአንዳንድ የደብር አለቆች ወደምትፈልጉት ደብር እንድትዛወሩ አደርጋለሁ በሚል የጀመሩትን ነገር ማሳካት አልቻሉም ነበር፡፡ በዚህ የተነሣም ከአለቆቹ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተዋል የሚባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ በአንድ በኩል፣ አዲስ አበባ ላይ በሕገ ወጥ መንገድ እንዳይንቀሳቀስ እየተደረገ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በሌላ በኩል ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነን ከሥራ አስኪያጅነት ለማስነሣት የሸረቡት ሴራ መሆኑ በስፋት ሲወራ ቆይቷል፡፡ በዚህ መንገድ ደብዳቤውና ቃለጉባኤው ከእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እንዲወጣና ሰዎች በተዛባ መንገድ እንዲረዱት ተደረገ፡፡ ሥራ አስኪያጁንም ለማስነሣት ንቡረ እዱ ይህን የሴራቸውን ፍሬ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅመውበታል ነው የሚባለው፡፡ ሴራውን ለማጠናከርም በጲላጦሳዊና በሄሮድሳዊ ፍቅር ከአቡነ ማቴዎስ ገጥመው እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረቱ ደብዳቤ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የተባለው 500 ሺሕ ብር ከደብሩ ካዝና ስለመውጣቱ እና ለሥራ አስኪያጁ ስለመሰጠቱ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ፕሮቶኮል ያላሟላውን ደብዳቤ እየጠቀሱ ብሩ ተዘረፈ ብሎ ከማውራት ውጪ ማስረጃውን ያቀረበ አካል ግን የለም፡፡ ታዲያ ዳንኤል ከየት አምጥቶ ነው በዚህ መንገድ የተቀነባበረውን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ብሩ ተዘረፈ ሲል የጻፈው? ፕሮፌሰር መስፍን “[ዳንኤል ክብረት] ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው ዕውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ እንጂ ዐውቆ የሚጽፍ አይመስልም” ያሉት ምንም ሐሰት እንደሌለበት በዚህ ታውቋል፡፡ ሆኖም ሴራው ጠንክሮና እውነትን የሚያፈላለግ ጠፍቶ ግንቦት ከመምጣቱ በፊት ሥራ አስኪያጁ ሊነሡ ችለዋል፡፡ ይህንን ስል ሊቀ ማዕምራን የማነ ከችግሮች ሁሉ የነጹ ፍ  ጹም ናቸው እያልኩ እንዳልሆነ ግን ግንዛቤ ይወሰድልኝ።

ሙስና የቤተ ክርስቲያኒቱ የኖረ ችግር መሆኑን ማንም አይክድም፡፡ አቡነ ማትያስ ሲሾሙ በዋናነት እዋጋለሁ ያሉት ሙስናን ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ሥር የሰደደው ሙስና እንዲህ በቀላሉ ሊወገድ የሚችል ሆኖ አልተገኘም፡፡ ችግሮቹ እንዳሉ ቢሆንም በአንጻራዊነት ሲታይ ግን በሊቀ ማእምራን የማነ የሥራ አስኪያጅነት ዘመን አንዳንድ መሻሻሎች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ የገንዘብ መጠን ተወስኖላቸው ጉቦ ይበላባቸው የነበሩ የሥራ መደቦች ያለ ጉቦ ሠራተኞች ተቀጥረውባቸዋል፣ ዝውውርም እንደዚሁ ያለ ጉቦ መከናወን ችሏል፡፡ እንዲህ ሲባል የተገኘውን አጋጣሚ የሚጠቀሙበት አንዳንድ የበታች ሃላፊዎች የሉም ማለት ግን አይደለም፡፡ ሊቀ ማእምራን የማነ ያለ ሊቀ ጳጳስ ሥራ አስኪያጅነቱን ሲያካሂዱ በከፍተኛ ደረጃ ጉቦ የሚበላባቸውን የአለቆችን ዝውውር ዝግ በማድረግ ቆይተዋል፡፡ ዒላማ ውስጥ ያስገባቸውም ይኸው እርምጃቸው እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ በአጠቃላይ ከሙስናው ሥር መስደድ የተነሳ በአንድ ጊዜ ሙሉ ሙሉ መለወጥ ባይቻል እንኳን ከተሰራበት ሙስናን መዋጋት እንደሚቻል ምሳሌ የሚሆን ሥራ የታየበት ወቅት ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡

ዳንኤል ግን አቡነ ማትያስ ሙስና ሲፈጸም ተኝተዋል ብሎ ሊዘልፋቸው ሞከረ እንጂ በዚህ አንጻር የተኙት እሳቸው ሳይሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ሙስና አለ እገሌ ሙሰኛ ነው የሚለው ሙስናን በሙስናነቱ ተጸይፎና መወገድ አለበት በሚል እምነት አይደለም፡፡ ያ ሰው የማኅበሩን ጥቅም የሚነካ ወይም የማያስከብር ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸው ንቡረ እድ ኤልያስና እርሳቸውን የተኳቸው ቀሲስ በላይ ከሙስና ጋር ተያይዞ ስማቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ ነበር፡፡ ሐራ ላይ ስለ ንቡረ እድ ኤልያስ ሙሰኛነት በተደጋጋሚ ሲጻፍ ስለ ቀሲስ በላይ ግን አንድም ቀን የተባለ ነገር አላስታውስም፡፡ በሁለቱም ዘመን ሙስና በእጅጉ የተስፋፋ መሆኑ ቢታወቅም ንቡረ እድ ለማኅበሩ የሚመቹ ሰው ባለመሆናቸው ብቻ ሙሰኛነታቸው በስፋት ተነገረ፡፡ ቀሲስ በላይ ግን ሙስናቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ በጩኸት ብዛት እንዲነሡ እስኪደረግ ድረስና ከዚያም በኋላ ባለው ጊዜ ማቅ ተኝቶ ነው ያለው፡፡ ሐራ ላይ ስለሙስናቸው ምንም አልተጻፈም፣ ለማህበሩ የተመቹ ሰው ነበሩና፡፡ ማህበሩ እስካልተነካ ድረስ የቤተ ክህነት ባለሥልጣን የፈለገውን ያህል ሙስና ቢፈጸም ማቅ ይተኛል፡፡ ሲነካ ግን የነካውን ሰው ወይ አማሳኝ ወይም ተሐድሶ ይለዋል፡፡ ስለዚህ ብዙዎች እነዚህ ስሞች እንዳይለጠፉባቸውና ለሙስና ሽፋን አግኝተው እንዲዘርፉ ማህበሩን ይጠጋሉ፡፡ ታዲያ እውነት እንነጋገር ከተባለ ለሙስና የተኛው ማነው? ፓትርያርኩ ወይስ ማኅበረ ቅዱሳን?

በዚሁ አንቀጽ ውስጥ ዳንኤል ያነሣው ሌላው ነጥብ በሕዝብ ጥያቄ ሽፋን ጽንፈኛ አቋምን በሚያራምዱ ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ይተኛሉ፤ የስልጤ ዞን ምእመናን በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ እየተቀበልን ነው ሲሉ ይተኛሉ፤ ብሎ ያቀረበው ነው፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ለአገር የማይበጅ በመሆኑ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ይፈጽመው ድርጊቱ መወገዝ ያለበት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ፓትርያርኩ ሊያደርጉ የሚገባው ምንድን ነው? ድርጊቱን ከማውገዝና ከማስተማር በቀር የአጸፋ እርምጃ ይውሰዱ ነው? ወይስ ምን ያድርጉ? እንዲህ ያለ ነገር በሚያጋጥም ጊዜ ድርጊቱ በሲኖዶስ ጭምር የሚወገዝና ተቻችሎ ስለ መኖር ትምህርት የሚሰጥበት አጋጣሚ አለ፡፡

ደቡብ እና ምዕራብ ላይ እንዲህ ሲደረግ ወደ ሰሜኑ ክፍል ብንሄድ ደግሞ ይህን ድርጊት የሚፈጽመው ጽንፈኛው ማህበረ ቅዱሳን ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በአንዳንድ የሰሜኑ አካባቢዎች ተሐድሶ ተብለው በማቅ የተፈረጁ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከሥራቸው በመፈናቀል ልዩ ልዩ ስደት ይታወጅባቸዋል፡፡ በዚያ ከተማ ቤት እንዳይከራዩ፣ ከሱቅ ዕቃ እንዳይገዙ እሳት እንዳይጭሩ አገር ሰላም እንዳይላቸው ወዘተ አድማ ይታደምባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ቤት ላይ የድንጋይ ናዳ ይወርዳል፡፡ በእሳት የሚቃጠልባቸው፣ የሚፈርስባቸውም አሉ፡፡ እንዲህ ዐይነቱ ግፍ በራስ ላይ ሲደርስ ግን ያማል፡፡ በሌላው ላይ ሲያደርሱት ግን እግዚአብሔርን እንደ ማገልገል ነው የሚቆጠረው፡፡ ስለዚህ ሰሜን ላይ የተዘራው ደቡብ ላይ ቢበቅልና ቢታጨድ ምን ይደንቃል?

በተጨማሪ ሌላ የመክሰሻ ነጥብ በማንሣት ፓትርያርኩንቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ሲሆን ይተኛሉ፤ ይላል፡፡ በዚህ አነጋገሩ ፓትርያርኩን ብቻ ሳይሆን ከማኅበረ ቅዱሳን በቀር ቤተ ክርስቲያኗ የኑፋቄ ማኅደር ሆናለች እያለ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሷን የሚመራው ቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ከሆነ ቤተ ክርስቲያኗም የኑፋቄ ማኅደር ናት ማለት ነው፡፡ ይህ አነጋገር የዳንኤልን የትዕቢት ልክ የሚያሳይ ነው፡፡ አሁን ማን ይሙት ዳንኤልና ማኅበሩ ሃይማኖትን ለመመዘን ብቁዎች ናቸው ወይ? የሚያምኑትን ለተመለከተ ሰው እኮ ሃይማኖትን ኑፋቄ ኑፋቄን ደግሞ ሃይማኖት የሚያደርጉ ግብዞች ናቸው፡፡ እነርሱ ከተነሡ ወዲህ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በተረት እየተተካ መጥቷል፡፡ ስለዚህ ዛሬ እውነተኛው የሃይማኖት ትምህርት ኑፋቄ እየተባለ ሰዎች የሚወገዙበት ሆኗል፡፡ ተረታ ተረቱ ደግሞ ሃይማኖተኛ አሰኝቶ ያስከብራል፡፡

ዳንኤል መች በዚህ ያበቃና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሲዘጉ፣ ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲበተኑ ይተኛሉ፤ በማለት አሁንም ፓትርያርኩን ይዘልፋል፡፡ ይህ ፓትርያርኩ የፈጠሩት ችግር ሳይሆን ከጊዜው ጋር አለመራመድ ያመጣው ጣጣ ነው፡፡ ማኅበሩስ ይህን ችግር እቀርፋለሁ ብሎ በሚያደርገው እንቅስቃሴ መች መፍትሔ አመጣ? በገዳማትና በአብነት ት/ቤቶች ስም ከመነገድና ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በሚሰበስበው ከፍተኛ ገንዘብ ኢኮኖሚያዊ ጡንቻውን ከማጠንከር ውጪ መች መፍትሔ አመጣ? ለዚህ መፍትሔው ለውጥ የማይቀር ሂደት መሆኑን ተገንዝቦ ራስን ለለውጥ ማዘጋጀትና አብነታዊውን ትምህርት ባለበት እንዲረግጥ ከማድረግ ይልቅ በዘመናዊ መንገድ እንዲራመድ መሥራት ይጠበቃል፡፡ እንዲህ ባለመደረጉና ዘመኑ ስላልተዋጀላቸው ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች ባሉበት መቀጠል አልቻሉም፡፡ አሁንም ለውጥን ለማስተናገድ የተዘጋጀ አመራርና ትውልድ ከሌለ ከዚህ የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር እንደማይመጣ ለመናገር ነቢይ መሆን አይጠበቅም፡፡

እስካሁን ባየነው አንቀጽ ውስጥ ከተናገረው በተቃራኒ ዳንኤል በጽሑፉ 3ኛ አንቀጽ ላይ ፓትርያርኩ “ይነቃሉ” ብሎ ያቀረበው ማኅበሩ የሚሠራውን ሥራ ለማፍረስ እንደሆነ ያትታል፡፡ ማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያን ባስወጣቸውና በራሳቸው ጊዜ በአብዛኛው እውነትን ፍለጋ ወጥተው የቀሩትን ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ኮሌጆች የተሐድሶ መፍለቂያ ናቸው ብሎ መጻፉና ውዝግብ ውስጥ መገኘቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ፓትርያርኩ ታዲያ መንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ የተጻፈውን ስም አጥፊ ጽሑፍ እንዴት መናፍቃንን የሚተች ጽሑፍ ነው ብለው ይቀበሉ?

ቤተ ክርስቲያንን ከወንጌል ወደ ተረት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ምእመናንን ሲበትንና ከቤተ ክርስቲያን እንዲሸሹ ሲያደርግ የኖረው ማኅበር ያለፈው ሳያንሰው አውደ ምሕረቷ ላይ ወጥቶ “ተሐድሶ ጉድ ሊያፈላባችሁ ነውና እኔን ብቻ ስሙኝ” የሚለውን የማኅበሩን ዕድሜ መቀጠያ ስልት “ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ” ብለውስ እንዴት ይቀበሉ?

በሰንበት ት/ቤትና በሌላውም አደረጃጀት የማኅበሩን ጥቅም ለማስከበርና ጥቅሙ የተነካ ሲመስለው ደግሞ ዐመፅ ለማስነሣት በተጠንቀቅ እንዲቆም ተደርጎና አንዳንድ ሙከራዎችን አድርጎ በወጣቱ ትውልድ ስም እየተጠራ ቤተ ክርስቲያንን በመበጥበጥ ሥራ ተሰማርቶ የተገኘውን የወሮበላ ስብስብ እንዴት “ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው” ብለው ይቀበሉ?

በማኅበረ ቅዱሳን ሃይማኖት ያመነውና የተጠመቀው በውጭ ያለው ዲያስጶራ ቤተ ክርስቲያንን የመገንጠልና ራስን በማኅበረ ቅዱሳን ሥር በማደራጀት ሥራ ተጠምዶ ባለበት ሁኔታ “ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ” ሲባሉ እንዴት ይመኑ?

ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያንን ቅርስ ሀብትና ንብረት በመጠቀም በስሟ ለራሱ ብዙ ተከታይ ለማፍራት አልሞ ያዘጋጀውንና በቅርቡ ከገባበት ቀውስ ለመውጣት በብዙ አቅጣጫ ሊጠቀምበት የጓጓለትን ዐውደ ርእይ “ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው” በሚል እንዴት ይቀበሉ?

በመንፈሳዊ ፕሮግራም ስም እንቶ ፈንቶው ሲቀርብበት የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ፕሮግራም በሌሎቹ ወንጌልን በሚሰብኩ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እየተዋጠ ስለሄደ ሊኖር የሚገባው የቴሌቪዥን ፕሮግራም የእኔ ብቻ ነው በሚል ሥጋዊ ቅናትና ምቀኝነት መንፈስ ተነሣሥቶ ሌሎቹ እንዲዘጉ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቶ በውጤቱ ራሱን ጨምሮ ሁሉም እንዲዘጉ መደረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ከሆነስ በመዘጋቱ ከሚስማሙት አንዱ እኔ ነኝ፡፡ ሆኖም ወንጌልን የሚሰብኩት በማኅበረ ቅዱሳን ዳፋ መዘጋታቸው የወንጌልን ቃል ተርቦና ተጠምቶ ላለው ምእመን አለማሰብ ነው፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ይህን የወንጌልን እውነት የቀመሰውን ትውልድ ተረት ተጋት ቢሉት በጄ አይልም፣ ወደኋላ መመለስም አይፈልግም፡፡ ሆኖም ዳንኤል እንደ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም የቆጠረውን የማኅበረ ቅዱሳንን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ማገዳቸው እኔ የማየው ትውልድን ከተሳሳተ ትምህርት ለመታደግ የተወሰደ እርምጃ አድርጌ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ላይ መንቃታቸው የፓትርያርኩን ትጋት የሚያሳይ ነው፡፡

በዚህ በሦስተኛው አንቀጽ መጨረሻ ላይ የፓትርያርኩን ብእር የተቸበት መንገድ ግን በጣም ጸያፍ ነው፡፡ ገና ለገና ማቅ ስላጠፋው ጥፋት አደራቸውን ለመወጣት የማቅን መንደር ያሸበረውን ደብዳቤ መጻፋቸው የሚያስመሰግናቸው መሆን ሲገባውና ብዙዎችን ያስደነቀ ደብዳቤ ሆኖ ሳለ ማቅ ላይ ከፈጠረው ድንዛዜና ድንጋዜ አንጻር አፍዝ አደንግዝ ማለቱ አይገርምም፡፡ ነገር ግን ተራ ስድብ ነው፡፡ “የፓትርያርኩ ብእር ግን ምእመናንን የሚያጽናና ጦማር ለመጻፍ … የሚጨበጥ አይደለም” ሲል የገለጸው ግን ምእመናንንና ማኅበረ ቅዱሳንን ያደበላለቀ ገለጻ ነው፡፡ “የሚያጽናና ጦማር” በግልባጩ ሲነበብ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ያዘነ ክፍል አለ የሚል አንድምታ አለው፡፡ ያዘነ እንደሚኖር ሁሉ የተደሰተ ክፍልም እንደሚኖር የሚጠበቅ ነው፡፡ በዋናነት ያዘነው የማኅበረ ቅዱሳን አባልና ደጋፊ ነው፡፡ በሌላ አንጻር የተደሰተ ኦርቶዶክሳዊ ወገንም አለ፡፡ ነገር ግን ዳንኤል የማቅን አባላትና ደጋፊዎችን ብቻ ሊወክል የሚችለውን ሐዘን የምእመናን ሁሉ ሐዘን ማድረጉ ተገቢ አይደለም፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትም በረጋ መንፈስ ቢያጤኑትና ማቅ በቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት መመዘን ቢችሉ በፓትርያርኩ ደብዳቤ ሐዘናቸው ወደ ደስታ መለወጡ አይቀርም፡፡  
ይቀጥላል

34 comments:

 1. ተራ ናችሁ እናንተ ወንጀል እንጂ ወንጌል አታውቁም "ውሉደ አሬዎስ ትመስሉ ምስለ ኩሉ ግብሩ"

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ተራራ ነህ ማለት ነው? የክህደት እና የሸፍጥ የማስመስልና የጭፍንነት ተራራ። ደግሞ ወንጌል የሚለውን ቃል መጥራት ባንተ አያምርም። ወንጌል ከምታመልካቸው እና ከምትሰግድላቸው የተረት መጽሀፍት አይደመርምና

   Delete
  2. @ AnonymousApril 14, 2016 at 9:42 PM
   አንተ ተራራ ኮ ደብር(የተቀደሰ ከፍታ ቦታ) ማለት ነው ለሁሉም የሚታይ ለቤተክርስትያን የተገባ ቦታ.....የናንተው ባማ ይባላል(ለጣኦት የሚሰዋበት ከፍተኛ ስፍራ) ወዳጃችሁ እንደዘፈነችላችሁ:: አነተ የአሬዎስ የልጅ ልጅ የሉተር ልጅ ገና በ16 ኛው ክፍለ ዘመን የተፈለሰፈ ፍልስፍና ይዘህ ታቅራራለህ.....ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች አሉ አንተ ና ዘመዶችህ ስለ ወንጌል ለእኛ ልትነግሩን???....ኧረ ተው ልቤን አታፍርሰው በናትህ!!!!

   Delete
 2. Asama neh behiwiteh lemin endalkuh libeh yawkewal entewawekalen.Yezarew degimo andimta mehonu new andem eyalk yerasehin gimet askemetik gin andimita kemenfes kidus galachinet yemimeta enji keseytan lehon aychilim bante mikinyat lemahiberu lijoch yalegn kibir chemere min aynet tagashotch nachew? Yeafachihu difret mak bebetcristyan lay eyaderese yalew chigir bilachihu Sitaweru aygermim defar hatyategna matewos 25-14-31 yalew haketegna barya ayenet sechiwin endesedebew aynet nachihu batawetut minim aymeslegn alamaye lenante meger silehone chigir yelewim.

  ReplyDelete
 3. በእርግጥ ዳንኤል ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቢቆረቆር አይደንቅም፡፡ ምክንያቱም ድኅረ ወሊድ ማንም ባልተገኘበት ጭር ባለ ቀን በተክሊል የተዳረባት ቦታ ናትና፡፡ እንደሚታወቀው ዳንኤል ከአሁኑ ጋብቻው በፊት ከጋብቻ ውጪ ባሕር ዳር ላይ አንዲት ትንቢተ የተባለች ሴት ልጅ ወልዷል፡፡ ከዚህ አንጻር እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ልጅ እያለው በተክሊል ስላጋባችው ለዚህ ውለታዋ “እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ” ተዘረፈ ብሎ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ላይ ከሰሞኑ ማቅና አባቶቹ በከፈቱት ዘመቻ ላይ ጋዝ ቢያርከፈክፍ አይደንቅም፡፡ ነገር ግን መረጃው የተሳሳተ ነው፡፡
  እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ልጅ ስለታመመና ወደ ውጪ ሄዶ መታከም ስላለበት ሥራ አስኪያጁ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ እየሠራ ያለውን ውጤታማ ሥራ ከግምት ያስገቡ አንዳንድ በጎ ፈቃደኞች እርሱ እንዲህ እያደረገ ባለበት ሁኔታ እኛ ደግሞ ልጁ የሚታከምበትን ገንዘብ ብናዋጣ መልካም ነው ብለው በኢትዮጵያዊ ደንብ የጀመሩት እንቅስቃሴ አለ፡፡ በማንኛውም ድርጅት ወይም አካባቢ ተመሳሳይ ችግር የገጠመው ሰው ካለ እንዲህ መደረጉ የተለመደ ነው፡፡ ለሥራ አስኪያጁ እየተደረገ ያለውን በዚህ መልክ ማየት የሚከብድ አይደለም፡፡ ምናልባት ሥራ አስኪያጅ ስለሆነ ለልጁ ማሳከሚያ ድጋፍ የተጠየቀው በየደብሩ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ሠራተኞች ላይ መሆኑ የተለየ መስሎ መታየት የለበትም፡፡ ጥያቄው ደግሞ በፈቃደኛነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነና ሥራ አስኪያጁ በደብዳቤም ሆነ በቃል ትእዛዝ አስተላልፎ ሳይሆን በፈቃደኛነት የተሰባሰቡ አስተባባሪዎች ያደረጉት ነው፡፡ ስለዚህ ሰብአዊ ጥያቄውን ተቀብለው ድጋፍ የሰጡ አሉ ያልሰጡም አሉ፡፡ በዚህ ውስጠ ከእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት የወጣው ደብዳቤ ግን ዓላማው ሌላ ነው፡፡ በሥራ አስኪያጁ ላይ ክስ በማብዛት ጫና ለመፍጠርና ከሥራ አስኪያጅነቱ እንዲነሣ ለማድረግ የተጀመረ ጥረት ነው፡፡ ይህን ሴራ ሥራ አስኪያጁን ለማስነሣት በጲላጦሳዊ ወሄሮድሳዊ ፍቅር የተዋደዱት አባ ማቴዎስና ንቡረ እድ ኤልያስ እንደሸረቡት የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ሰዉም ይህ ሳያጣራ የማቅ ልሳን በሆነው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ጭምር እስከ ማውጣት የተደረሰበት ሁኔታ አለ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. hahahahahahahahhahaha አይ ዳኒኤል ማፈሪያ

   Delete
 4. ዳንኤል ክብረት አንተ ከአባትህ ከዲያብሎስ ነህ
  ማኅበረ ቅዱሳን የድኅነት ሥጋት ነው፤ የደኅንነት ሥጋት ሊሆን ግን አይችልም
  ዳንኤል ክብረት “ለመናገርና ለመጻፍ ያለው ፍጥነት በሚናገርባቸው ጉዳዮች ላይ ካለው ዕውቀት ጋር አይመጣጠንም፤ እንዲያውም ያውቃል እንዲባል የሚጽፍ እንጂ ዐውቆ የሚጽፍ አይመስልም” (አዳፍኔ - ፍርሀትና መክሸፍ ገጽ 222)፡፡ በዳንኤል ክብረት ላይ ይህን አስተያየት የሰጡት ታላቁ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ናቸው፡፡ “ክሽፈት እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የተሰኘ መጽሐፋቸውን ያለ ዕውቀቱ ያለ አቅሙ በድፍረት ለመተቸት በመሞከሩ የሰጡት ምላሽ ነው፡፡ እኔም ይህን ጽሑፍ በእርሳቸው አስተያየት የጀመርኩት ዳንኤልን በሚገባ ስለሚገልጸው ነው፡፡
  “ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል ርእስ፣ ኀሙስ ማታ መታገዱ በይፋ ለታወቀው የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ በስሜት ተገፋፍቶ የጻፈውንና በተራ ዘለፋና ስድብ የተሞላውን ጽሑፉን ለተመለከተ ሰው ዳንኤል “ያውቃል እንዲባል እንጂ ዐውቆ የሚጽፍ” አለመሆኑን በሚገባ ያሳየበት ነው፡፡ ጽሑፉ የዳንኤልን ትክክለኛ ማንነትና ባዶነት ያጋለጠ ነው፡፡ በማቅ መንደር የሚወራውን ይዞ እንጂ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ የጻፈው ጽሑፍ አይደለም፡፡
  ዳንኤል ከአሁኑም ሆነ ቀደም ካለው የማኅበሩ ግልጽ አመራር ጋር እንደማይዋደድና ጠበኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በተለይ አሁን ያለው አመራር ዳንኤልን እንደ ሥጋት ያየዋል፡፡ ከስውር አመራሩ ጋርማ ጠብ ውስጥ ከገባ ቆየ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ዳንኤል ራሱን በልዩ ልዩ መንገድ በማስተዋወቅ ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ዳንኤል ክብረት እስኪመስል ድረስ ማኅበሩን ሸፍኗል የሚል ነው፡፡ ከማኅበሩ ሰዎች ገንኖ የወጣው እርሱ ስለሆነም ነው፡፡ ዳንኤልም አመራሩን ባይወድም ለማኅበሩ ያለውን ፍቅር ግን እንዲህ ባለው ክፉ ቀን በተቆርቋሪነት መንፈስ መግለጹ አልቀረም፡፡ ማኅበሩን በተሳሳተ አቋሙና አካሄዱ ሲተች ይቆይና ማኅበሩ ላይ ክፉ ቀን ሲመጣ ግን ማኅበሩን የመከላከል ሥራ ይሠራል፡፡ ይህም በአንድ ወገን ለእርሱ ሳያውቅ አዋቂ ያሰኘውና ዝናን ያተረፈለት በማኅበሩ ውስጥ ጎልቶ መውጣቱ ስለሆነ ድንገት ማኅበሩ አንድ ነገር ቢሆን የእርሱም ዝና አብሮ ሊከስም እንደሚችል ስለሚያስብ ይመስለኛል፡፡ እስኪ እርሱ የጻፈውን የስድብና የዘለፋ ጽሑፍ ለመዳሰስ እንሞክር፡፡
  የጽሑፉ ርእስ “ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” የሚል ነው፡፡ ይህ ርእስ ፓትርያርኩ ባለባቸው ኀላፊነትና አደራ ማኅበረ ቅዱሳንን አደብ ለማስገዛትና መሥመር ለማስያዝ፣ ቤተክርስቲያንንም ከእርሱ ቅኝ ግዛትና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የጀመሩትን ትክክለኛና ተገቢ እርምጃ ሌላ መልክ ለመስጠት የሚሞክር ሲሆን በሌላ በኩል ለማኅበረ ቅዱሳን የሌለውን ማንነት ለማላበስ የታሰበበት ነው፡፡ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን በመንካታቸው ለኢትዮጵያ ደኅንነት ስጋት ሆነዋል ማለት ምን ማለት ነው? ተገልብጦ ሲታይ ማኅበረ ቅዱሳንን መንካት ለኢትዮጵያ ደኅንነት ያሰጋል የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው፡፡
  በእኔ እምነት ማኅበሩ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ማንነት አው ብዬ አላምንም፡፡ ስሙ አለቅጥ የገነነ፣ እንደሚወራለት ያልሆነ፣ ይልቁንም የተሐድሶ እንቅስቃሴን ለማደናቀፍ ከሚያደርገው አፍራሽ ሥራ የተነሣ በተደጋጋሚ ስለእርሱ ስለተወራ የሌለውን ማንነት የተላበሰ ቡድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስጋት ቢሆን ዐውደ ርእዩ ሲታገድ ስጋትነቱን ለምን አላሳየም? መመሪያ እስኪተላለፍለት እየጠበቀ ነው እንዳይባል በማኅበራዊ ሚዲያው የነበረው ቅስቀሳ፣ ጫጫታና ሁካታ ቀላል አልነበረም፡፡ ያ ሁሉ ግን በአየር ላይ በተገነባ የሌለ ሰብእና ከማስፈራራት ያለፈና ለአገር ደኅንነት ሥጋት የሚሆን ነገር መፍጠር የሚችል አቅም የሌለው ስብስብ እንደሆ ያሳያል፡፡ እዚህ ላይ መጠየቅ የምፈልገው አንድ ጥያቄ ግን አለ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ያፈራው አባልና ጀሌ ሃይማኖተኛ ነው ወይስ ፖለቲከኛ? እነዳንኤል ለማስፈራራት ከሚሞክሩበት ሁኔታ አንጻር ካየነው ፖለቲከኛ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ እንዲህ የሚያደርግ ፖለቲከኛ ወይም ሌላ ዐላማ ያለው እንጂ ሃይማኖተኛ ይልቁንም በክርስትና ስም የሚጠራ ሃይማኖተኛ ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ የክርስትና ትምህርት ክርስትና በስደትና በመከራ ውስጥ የሚያልፉበት መንገድ ቢሆንም ያንን ሁኔታ በኃይልና በዐመፅ መቀልበስን የሚያስተምር ሳይሆን በመሸነፍ ማሸነፍን ነው የሚያስተምረው፡፡
  ለምእመናን የድኅነት ሥጋት የሆነው ማነው? ዳንኤል አሁንም ተጠያቂ የሚያደርገው ፓትርያርኩን ነው፡፡ድኅነት የሚገኘው በወንጌል በተገለጠው እውነት መሠረት በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የአድኅኖት ሥራ በማመን ነው፡፡ በዚያ ላይ ተመሥርቶ በሕያው እምነት ያገኙትን መዳን በበጎ ሥራ እየገለጡና እግዚአብሔርን እየመሰሉ በመኖር ድኅነትን መፈጸም ይገባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምእመናንን ወደዚህ የወንጌል እውነት ለማድረስ እየተጋ ያለው ማነው? በየተገኙበት መድረክ ሁሉ ቤተክርስቲያን ላይ የተጋረጠውን የምእመናን ፍልሰት ለማቆም ወንጌል መሰበክ አለበት በማለት የምእመናንን ድኅነት ለማረጋገጥ በቃልም በተግባርም እየተጉ ያሉት ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ማኅበሩ ግን ከዚህ በተቃራኒ እየተንቀሳቀሰ ለምእመናን የድኅነት ስጋት ሆኗል፡፡ ከወንጌል ይልቅ ተረትን፣ ከወንጌል ይልቅ ገድልን፣ ከሚያንጽ ይልቅ የሚያፈርስን ነገር በመናገር የተካነውና ምእመናንን ከድኅነት መንገድ ያወጣው ማነው?
  ዳንኤል እንኳን በዚህ ጽሑፉ ቅዱስነታቸውን ምእመናንን ከድኅነት መንገድ የሚያወጡ ብሎ ሲዘልፋቸው እርሱ ግን አሁንም ከተረት እንደልወጣ “ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡” ሲል መስክሯል፡፡ እውን እንዲህ ይሆናል? ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማነጋገርም ሆነ ማስታረቅ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ነው? ይህ በፍጹም የሚታሰብም ሆነ የሚቻል አይደለም፡፡ የታዘዝነውም ዲያብሎስን እንድንቃወመው ነው እንጂ እንድናስታርቀው ወይም ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ ውጪ ነው፡፡ እንዲህ አድርጋለች የተባለችው ክርስቶስ ሠምራ ወይም በስሟ ይህን የደረሰው ደብተራ ተሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብም ርቀዋል፡፡ ይህ ድርጊት በየዋሃን ምእመናን ዘንድ እንደ ትልቅ መገለጥ እንደ ትልቅ ሐሳብ እንደ መስሎ ቢታሰብም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ይቃረናል፡፡ እስኪ ከቅዱሳን ነቢያትም ሆነ ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ይህ የሞከረ ማነው? እንዲህ እንዲሆንስ ያስተማረ ማነው? ሁሉም በአንድ አፍ ዲያብሎስን እንድንቃወመው ነው ያስተማሩን፤ በተግባርም ገሥጸው ነው ያባረሩት እንጂ ስለማይታረቅና እርሱን የማስታረቅ ሐሳብም ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ከእግዚአብሔር ጋር እናስታርቅ የሚል ሐሳብ ከቶም አላሰቡም፤ እንዲህ አይታሰብምም፡፡ ታዲያ ሊሆን ቀርቶ የማይታሰበውን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ የሚለው ሐሳብ ተረት እንጂ ወንጌል ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ እንዲህ ባለው የአሮጊቶች ተረት የተሞላው የማኅበረ ቅዱሳን መድረክ ሰውን ከክርስቶስ የማዳን መንገድ የሚያወጣ በመሆኑ የድኅነት ሥጋት ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. ዳንኤል ክብረት ወልደ አቡሃ ለሐሰት
  መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግብር የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆኑ በስም የእግዚአብሔር ልጅ ነን ለሚሉትና በግብር ግን የዲያብሎስ ልጆች ለሆኑት አይሁድ፣ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ሲል ተናገረ (ዮሐ. 8፥44)፡፡ ዳንኤል ክብረት ሰሞኑን በስሜት ተገፋፍቶ በጻፈው አባት አዋራጅ ጽሑፉ እንደነርሱ ሆኖ ስላገኘሁት ነው የጽሑፌን ርእስ “ዳንኤል ክብረት ወልደ አቡሃ ለሐሰት” ለማለት የደፈርኩት፡፡ እናንተም በመጨረሻ በርእሱ እንደምትስማሙ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ለጽሑፉ ከሰጠው ርእስ ልጀምር፣
  የዳንኤል ክብረት የጽሑፍ ርእስ “ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” የሚል ነው፡፡ ይህ ርእስ ፓትርያርኩ ባለባቸው ኀላፊነትና አደራ ማኅበረ ቅዱሳንን አደብ ለማስገዛትና መሥመር ለማስያዝ፣ ቤተክርስቲያንንም ከእርሱ ቅኝ ግዛትና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (በልዩ ልዩ መንገድ ባስገበራቸው ጳጳሳትና የቤተክህነት ሰዎች በኩል) ነጻ ለማውጣት የጀመሩትን ትክክለኛና ተገቢ እርምጃ ሌላ መልክ ለመስጠት የሚሞክር ሲሆን በሌላ በኩል ለማኅበረ ቅዱሳን የሌለውን ማንነት ለማላበስ የታሰበበት ነው፡፡ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳንን በመንካታቸው ለኢትዮጵያ ደኅንነት ስጋት ሆነዋል ማለት ምን ማለት ነው? ተገልብጦ ሲታይ ማኅበረ ቅዱሳንን መንካት ለኢትዮጵያ ደኅንነት ያሰጋል የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠው፡፡
  በእኔ እምነት ማኅበሩ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ማንነት አው ብዬ አላምንም፡፡ ስሙ አለቅጥ የገነነ፣ ውስጣዊ ክፍፍል ያለበት፣ ዳንኤልና አመራሩ እንኳን ዐይንና ናጫ የሆኑበት፣ እንደሚወራለት ያልሆነ፣ ይልቁንም የተሐድሶ እንቅስቃሴን ለማደናቀፍ ከሚያደርገው አፍራሽ ሥራ የተነሣ በተደጋጋሚ ስለእርሱ ስለተወራ የሌለውን ማንነት የተላበሰ የማፍያ ቡድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስጋት ቢሆን ዐውደ ርእዩ ሲታገድ ስጋትነቱን ያሳይ ነበር፡፡ አባላቱና ጀሌዎቹ የፌስቡክ አንበሶች ከመሆን ያለፈ ያወሩትንና የሚያስወሩትን አላደረጉትም፤ ሊያደርጉትም አይችሉም፡፡ ወይም ደግሞ ከስውሩ አመራር መመሪያ እስኪተላለፍለት እየተጠበቀ ነው እንዳይባል ከላይ እንደጠቀስሁት በየፌስቡኩ የነበረው ቅስቀሳ፣ ጫጫታና ሁካታ ቀላል አልነበረም፡፡ ያ ሁሉ ግን በአየር ላይ በተገነባ የሌለ ሰብእና ከማስፈራራት ያለፈና ለአገር ደኅንነት ሥጋት የሚሆን ነገር መፍጠር የሚችል አቅም የሌለው ስብስብ እንደሆነ ያሳያል፡፡
  እዚህ ላይ መጠየቅ የምፈልገው አንድ ጥያቄ ግን አለ፣ ማኅበረ ቅዱሳን እስከ ዛሬ ያፈራው አባልና ጀሌ ሃይማኖተኛ ነው ወይስ ፖለቲከኛ? ወይስ ሁለቱን እያጣቀሰ የሚጓዝ? እነዳንኤል ለማስፈራራት ከሚሞክሩበት ሁኔታ አንጻር ካየነው ፖለቲከኛ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደ ታደሰ ወርቁ ያሉት ሃይማኖትንና ፖለቲካን በጣምራ የሚያራምዱ የማኅበሩ “ፖቲከኛ ሃይማኖተኞች” እንደገለጡት ማኅበሩ ለክፉ ቀን ያስቀመጠው ቅምጥ ኀይል መኖሩን የጥምቀት ተመላሾች በስም በመጥቀስ ግልጽ አድርጓል፡፡ መቼም እንዲህ የሚያደርግ ፖለቲከኛ ወይም ሌላ ዐላማ ያለው እንጂ ሃይማኖተኛ ይልቁንም በክርስትና ስም የሚጠራ ሃይማኖተኛ ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ የክርስትና ትምህርት ክርስትና በስደትና በመከራ ውስጥ የሚያልፉበት መንገድ ቢሆንም ያንን ሁኔታ በኃይልና በዐመፅ መቀልበስን የሚያስተምር ሳይሆን በመሸነፍ ማሸነፍን ነው የሚያስተምረው፡፡
  ለምእመናን የድኅነት ሥጋት የሆነው ማነው? ዳንኤል በጽሑፉ ርእስ አሁንም ተጠያቂ የሚያደርገው ፓትርያርኩን ነው፡፡ ድኅነት የሚገኘው በወንጌል በተገለጠው እውነት መሠረት በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የአድኅኖት ሥራ በማመን ነው፡፡ በዚያ ላይ ተመሥርቶ በሕያው እምነት ያገኙትን መዳን በበጎ ሥራ እየገለጡና እግዚአብሔርን እየመሰሉ በመኖር ድኅነትን መፈጸም ይገባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምእመናንን ወደዚህ የወንጌል እውነት ለማድረስ እየተጋ ያለው ታዲያ ማነው? በየተገኙበት መድረክ ሁሉ ቤተክርስቲያን ላይ የተጋረጠውን የምእመናን ፍልሰት ለማቆም ወንጌል መሰበክ አለበት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መጠናከር አለበት በማለት የምእመናንን ድኅነት ለማረጋገጥ በቃልም በተግባርም እየተጉ ያሉት ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ማኅበሩ ግን ከዚህ በተቃራኒ እየተንቀሳቀሰ ለምእመናን የድኅነት ስጋት ነው የሆነው፡፡ ከወንጌል ይልቅ ተረትን፣ ከወንጌል ይልቅ ገድልን፣ ከሚያንጽ ይልቅ የሚያፈርስን ነገር በመናገር የተካነውና ምእመናንን ከድኅነት መንገድ ያወጣው ማነው? ቢባል ዳንኤልና በአካል የተለየው ከልቡ ግን ያልወጣው ማኅበሩ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
  ዳንኤል እንኳን በዚህ ጽሑፉ ቅዱስነታቸውን ምእመናንን ከድኅነት መንገድ የሚያወጡ ብሎ ሲዘልፋቸው እርሱ ግን አሁንም ከተረት እንደልወጣ “ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡” ሲል በልቡ የሞላውንና ከወንጌል ቃል ጋር የሚጣላውን ገድልን ነው የጠቀሰው፡፡ እውን እንዲህ ይሆናል? ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማነጋገርም ሆነ ማስታረቅ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ነው? ይህ በፍጹም የሚታሰብም ሆነ የሚቻል አይደለም፡፡ የታዘዝነውም ዲያብሎስን እንድንቃወመውና ከእኛ እንድናርቀው ነው እንጂ ወደእግዚአብሔር ቀርበን እንድናስታርቀው ወይም ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ቃል፣ ፈቃድና ሐሳብ ውጪ ነው፡፡ እንዲህ አድርጋለች የተባለችው ክርስቶስ ሠምራ ወይም በስሟ ይህን የደረሰው ደብተራ ተሳስተዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብም ርቀዋል፡፡ ይህ ድርጊት በየዋሃን ምእመናን ዘንድ እንደ ትልቅ መገለጥ ወይም እንደ ትልቅ ሐሳብ ቢታሰብም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ግን ይቃረናል፡፡ እስኪ ከቅዱሳን ነቢያትም ሆነ ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ይህን የሞከረ ማነው? እንዲህ እንዲሆንስ ያስተማረ ማነው? ሁሉም በአንድ አፍ ዲያብሎስን እንድንቃወመው በቃል አስተማሩን፣ በተግባርም ገሥጸው እንድናባርረው አሳዩን፡፡ እርሱ ከቶም ስለማይታረቅና እርሱን የማስታረቅ ሐሳብም ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ከእግዚአብሔር ጋር እናስታርቅ የሚል ሐሳብ ከቶም አላሰቡም፤ እንዲህም አይታሰብም፡፡ ታዲያ ሊሆን ቀርቶ የማይታሰበውን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ የሚለው ሐሳብ ተረት እንጂ ወንጌል ሊሆን በፍጹም አይችልም፡፡ እንዲህ ባለው የአሮጊቶች ተረት የተሞላው የማኅበረ ቅዱሳን መድረክ ሰውን ከክርስቶስ የማዳን መንገድ የሚያወጣ በመሆኑ የድኅነት ሥጋት ነው፡፡
  ዳንኤል ግን ክርስቶስ ሠምራ በዚህ ረገድ አብነት ስለሆነችው ከዚህ ቀደም ብዙ ተቃውሞ የገጠመውና “ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ” በሚል በተከታታይ ሐመር መጽሔት ላይ ያወጣቸው የነበሩና በኋላም በመጽሐፍ መልክ ያሳተማቸው መጣጥፎቹ እርሱ በምናቡ ሰይጣንን በማነጋገር ሥራ ተጠምዶ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሰይጣንን ለማናገር የክርሰቶስ ሠምራ ገድል ተጽዕኖ ሳያደርግበት አይቀርም፡፡ በዚህ ምናባዊ ሥራ ላይ ዋናው ተቃውሞ ሰው እንዴት ከሰይጣን ጋር ቃለ ምልልስ ያደርጋል? የሚል ነበር፡፡

  ReplyDelete
 6. ዳንኤል ቅዱስ ፓትርያርኩን የዘለፈበት አንዱ ነጥብ ቅዱስነታቸውን ቤተ ክርስቲያንን ከማቅ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የጀመሩትን ሥርዐት የማስያዝ ሥራ ከሰይጣን ሥራ ጋር በማነጻጸር ማቅረቡ ነው፡፡ እጅግ ያሳዝናል፤ እጅግም ያሳፍራል፡፡ ፓትርያርክ “ታላቅ አባት” ማለት ነው ብሎ ትርጉሙን የተናገረው ዳንኤል ታላቁን የአባት ማክበር ተስኖትና ትልቅነታቸውን ከተሰጣቸው ማዕርግና ካላቸው ሥልጣን አኳያ ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም ከማስከበራቸው ጋር አያይዞ ነው ያቀረበው፡፡ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያንን ይጎዳል ያሉትን የማኅበሩን አደገኛ አካሄድ መሥመር ለማስያዝ መንቀሳቀሳቸው በዳንኤል አስተሳሰብ የሰይጣን ሥራ ተደርጎ ተቆጠረ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ መሆን እንዳልነበረበት ዳንኤል ራሱ ከዚህ ቀደም በማኅበሩ ላይ በጻፈው ትችት ገልጾ ነበር፡፡ እንዲያውም ሌላው ቤተ ክህነት ወደመሆን መሸጋገሩ ትክክለኛ አለመሆኑንም አስረድቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጽሑፍ ይህን ጉዳይ ባነሣበት አንቀጽ ውስጥ ፓትርያርኩን አራት ቦታ ላይ ከሰይጣን ጋር በማነጻጸር ነው ያቀረባቸው፡፡ እርሳቸው የሠሩትን ሁሉ የሰይጣን ሥራ አድርጎ ማቅረብ እጅግ አሳፋሪና የዳንኤልን ባዶነት የሚያሳይ ተግባር ነው፡፡

  ፓትርያርኩ እያፈረሱ ያሉት የማቅን እኩይ ሥራ ነው፡፡ “የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” ተብሎ ተጽፏል (1ዮሐ. 3፥9)፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እያደረገ ያለውንና ለቤተ ክርስቲያን የማይበጀውን ክፉ ሥራውን ቢያፈርሱ ምስጋና እንጂ ዘለፋ ሊሰነዘርባቸው አይገባም ነበር፡፡ ማኅበሩን ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ለማኅበሩ መጠቀሚያ የሚያደርግ አካሄድ ይብቃ! ሁሉም ነገር እዚህ ላይ መቆም አለበት ባሉ አእምሮ የጎደለው ዳንኤል ግን በድፍረት ፓትርያርኩንና የተቀደሰ ሥራቸውን ከግብር አባቱ ከዲያብሎስና ከክፉ ሥራው ጋር ለማመሳሰል ሞከረ፡፡ ዛሬ ረስቶት እንደሁ እንጂ በተለይ የማኅበሩ አመራር እርሱን ክፉኛ አስቆጥቶት በነበረ ጊዜ “ደጀ ሰላም” ሰቅሎ በሰዓታት ውስጥ እንዲወርድ በተደረገው ጽሑፉ ውስጥ “አመራሩ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን የተመሠረተ መሆኑን ዘንግቶታል፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያን ለማኅበሩ ወደሚል አመለካከትም ዞሯል፡፡ ይህ ፍርሃት ማኅበሩ የሚጠበቅበትን ከመሥራት ይልቅ ራሱን ለመከላከል ከፍተኛ ወጭ እንዲያወጣ አድርጎታል” ብሎ ነበር፡፡ በተለይ “ቤተ ክርስቲያን ለማኅበሩ” የሚለው አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ የዚህን አካሄድ አደገኛነት የተረዱት ፓትርያርኩ ለማስተካከል ሲነሡ ዳንኤል የእኔን አቋም ደግፈውልኛል ብሎ ለእውነት በመቆም ፈንታ ምነው የሰይጣን ሥራ አለው? ታዲያ ይህ አስመሳይነትና እውነትን የመሸጥ አካሄድ እርሱን “ወልደ አቡሃ ለሐሰት” አያሰኘውም ትላላችሁ?
  ዳንኤል ፓትርያርኩን እንደ አባት የማኅበሩን አባላት እንደ ልጆች ያቀረበ ሲሆን፣ ፓትርያርኩ የአባትነት ሚናቸውን እንዳልተወጡ ብቻ አድርጎ ነው የጻፈው፡፡ ጉዳዩን እርሱ በጻፈው መንገድ እንኳን ብናየው አባት ለልጆቹ የሚያደርገው ብቻ ሳይሆን ልጆች ለአባታቸው ማድረግ የሚገባቸውን ተወጥተዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ የሚነሳበትን ሐሣብ ነው ያቀረበው፡፡ ሩቅ ሳንሄድ ፓትርያርኩ ማኅበሩ ስሕተት መፈጸሙን ማስረጃ ጠቅሰው ለስሕተቱ ይቅርታ ይጠይቅ ብለው ለጻፉት ደብዳቤ፣ አላጠፋሁም ብሎ ከሚከራከር ይቅርታ ቢጠይቅ ምን ይሆን ነበር? ልጅ ከሆነ አባቱን ይቀርታ ለመጠየቅ አይቸገርም ነበር፡፡ ነገሩ እንዲያ ስላልሆነ ግን ለይቀርታ ልቡ አልነበረውም፡፡ ይህ ለፓትርያርኩ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ልጅ የራስን ኀላፊነት ሳይወጡ አባትን መውቀስ ሚዛናዊ አይደለም፡፡ እስካሁን እንደታየው ማኅበረ ቅዱሳን ተመክሮ ተዘክሮ ሊመለስ የማይችልና በጀመረው የጥፋት መንገድ ወደፊት ከመቀጠል በቀር የሚስተካከል ማንነት እንደሌለው ታውቋል፡፡ ዳንኤል እንኳ በዚሁ ጽሑፉ አመራሩ እርሱ የነገረውን የማይሰማና ከመለወጥ ይልቅ አንድ ቦታ ላይ “የተቸከለ” መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ ራሱን ፍጹማዊ አድርጎ ለሚቆጥር ማኅበር በር መክፈት በጥፋቱ እንዲበረታ ከማድረግ ያለፈ አንዳች ፋይዳ ስለሌለው ፓትርያርኩ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በር ተከፍቶ የመንግሥት ተወካዮች ባሉበት በተደረገው ውይይት መቼ ለውጥ መጣ? አሁንም በዚህ መንገድ የሚለወጥ ነገር ስለሌለ ለማኅበረ ቅዱሳን የሚከፈት በር አዋጭ አይደለም

  ReplyDelete
 7. ሙስናን በሚመለከት ፓትርያርኩ “እንደተኙ” የጻፈው ዳንኤል እርሳቸው ከተሾሙ ወዲህ የሙስናን ወንጀልነት አጉልቶ ለማሳየት ያደረጉትን እንቅስቃሴና በሙስና ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ያቀረበው ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለው ነው፡፡ ሙስና ከጥንት ጀምሮ የነበረና በተለይ ግን በአቡነ ጳውሎስ ዘመን እጅግ የተንሰራፋ የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ነው፡፡ ስለሆነም ፓትርያርኩ ይህን ችግር ለመዋጋት ገና ከመነሽ ነው ታጥቀው የተነሡት፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተንሰራፈውን ሙስና ለማስወገድ በወሰዷቸወ እርምጃዎች ከፍተኛ ውጠየቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት፣ ሥር መስደድም አንጻር ገና ብዙ መሠራት ያለበት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ያለጉቦ መቅጠርና የሰራተኛ ዝውውር መድረግ ተችሏል፡፡ ይህ አጠናክሮ መቀጠልና ሙስናን ከቤተክርስቲያን ለሙስና እንደማቅ የተኛ ማን አለ፡

  ReplyDelete
 8. ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ የሚለን ይሄ ነው፡፡ የተምታታ፣ እውነትን በሀሰት የሚያደበዝዝ ጽሑፍ ነው፡፡ ታዲያ አሁን ከእናንተ ሌላ ምን ይጠበቃል? እውነት ከእውነተኞች እንጂ ከሀሰተኞች ለመፈለግ የሚጓጓ ሞኝ ነው፡፡ ታሳዝኑኛላችሁ፤ እግዚአብሔር ከሚመጣው መከራ ትድኑ ዘንድ ማስተዋሉን ይስጣችሁ እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 9. yizelfal kemitil yimekral lemin alalkim? Daniel yanten 7 chikilat yizual

  ReplyDelete
  Replies
  1. መስሎሽ ነው ቆማጢት አለ ያገሬ ሰው

   Delete
 10. ይቀልሽ እንደሆን እየዞርሽ አውሪ አሉ!"ለሥራ አስኪያጁ የተደረገው እርሳቸው ከነበሩበት ስፍራ አንጻር የተደረገ መሆኑን ከግምት ማስገባት ከተቻለ ይህ ተግባር ተገቢ እንጂ ስሕተት አይደለም"፡፡
  ስንት ምስኪን የሚልሰው የሚቀምሰው የሚወድቅበት አጥቶ በሚሰቃይበት አገር አንተ ለአንድ ሙሰኛ ባለሥልጣን የሚደረግ ነገር የሰብአዊነትና የክርስቲያናዊ ምግባር አድርገህ ልትሰብክ ትሞክራለህ፣ ማፈሪያ።
  በተረፈ ስላንተ ማንነት ለመናገር ብዙ መድከም አያስፈልግም አፍ ሲከፈት ማንነት ይታያልና። እራስህ ማንነትህን ገልፀኸዋል።

  ReplyDelete
 11. አይ ዳንኤል ፓትርያርኩ እንደተኙ ፅፈሀል አንተ ጉዳም ከጒጃም እሰከ አሜሪካ ያልተኛሀት ሴት አለች ወይ የማሀበሩ ቀሚስ ለባሽ ሴቶች ሳይቆጠሩ

  ReplyDelete
 12. በእርግጥ ዳንኤል ለእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ቢቆረቆር አይደንቅም፡፡ ምክንያቱም ድኅረ ወሊድ ማንም ባልተገኘበት ጭር ባለ ቀን በተክሊል የተዳረባት ቦታ ናትና፡፡ እንደሚታወቀው ዳንኤል ከአሁኑ ጋብቻው በፊት ከጋብቻ ውጪ ባሕር ዳር ላይ አንዲት ትንቢተ የተባለች ሴት ልጅ ወልዷል፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰይጣን ሑሌ ሰውን በሐሰት እንደከሰሰ ነው

   Delete
 13. endete new menafekane 50,000 yemenafeka church legenebo new eyetebale new zime ahlacho min new ?? new enanetenem selememelekete new esyewe yegeneba mahletacho new .... ahwene mewerate yalebeten tetacho ..zibazeke yemitenegeron Dacon Daniael Kibereten yemeaweke ye Beat Kiresetane Lijoche Enawekewalen negare ahyasefelegenem .....Ye Dabilosen le Dabilose Lijoche Negerachewe egna ye Egizahber Lijoche neh ye Egizahber Kale new yeminesemawe.... sele 50,000 church yegenebale enanetem ye enanete ....Abate Pateraleko minem yalachewete yelem alamacho min enedewene enawekalen...Tadiso Menafekane

  ReplyDelete
 14. ahle negere ahle ye ahgere sew ኢሕአዴግ ለምን ማኅበረ ቅዱሳንን ማፍረስ ፈለገ? –
  enqu-magazine-megabit-cover
  (ዕንቊ፤ ቅጽ ፮ ቁጥር ፻፲፬፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)
  ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይስማማሉ፡፡
  በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ሃይማኖታዊና ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎት ያላቸው የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናትና ጥቂት አማሳኝ የደኅንነቱ ሰዎች ተቋሙን አፍርሶና ቤተ ክርስቲያንን በሒደት አዳክሞ በመቆጣጠር አልያም በታትኖ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ማስረከብ ቀላል እንደኾነ ያስባሉ፡፡ በአንጻሩ ‹‹በምድር ላይ ሊሳኩ ከማይችሉ ነገሮች አንዱ ይኼ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ምኞት ነው፤››የሚለው አንድ የቀድሞው የማኅበሩ ሥራ አመራር አባል እንደሚያሳስበው፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች፣ ማኅበሩ በግቢ ጉባኤያት አንፆ መስቀል በአንገታቸው አስሮ የሸኛቸው በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ምሩቃን፣ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራንና በማኅበሩ ስኬታማና ተጨባጭ አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ያደረባቸው ምእመናን ኹሉ ለዘመናት እየመነዘሩ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ተግዳሮቶች የሚመክቱበት መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው በቅጡ መረዳት ያሻል፡፡
  በርካታ አገራዊ አጀንዳዎች አሉኝ በማለት ሕዝቡን ለሕዳሴ የሚያነሣሣው መንግሥት፣ በተለይም የፀረ አክራሪነቱን ትግል በቅድመ ግንባር እንዲመራ ፖሊቲካዊ ተልእኮ የተሰጠው አካልና ሓላፊዎቹ፣ መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራታቸውና እጃቸውን ወደ ብልሽት ከመዘርጋታቸው በፊት ነገሮችን በርጋታ ማጤንና በግልጽ ውይይት ማመን ይበጃቸዋል፡፡

  ከሰሞኑ ኢሕአዴግ መራሹ ግብረ ኃይል ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ እንቅስቃሴውን ከየትኛውም ጊዜ በባሰ አጠናከሮ መቀጠሉ እየተደመጠ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐቀኛና ዓይናማ አበው ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ዘንድ ዐቃቤ ሃይማኖት ኾኖ የሚታየውና በብዙዎች ምሁራን ዘንድ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምሁራን ክንፍ (academic wing) መኾኑ የሚታመነው ማኅበረ ቅዱሳን የገዥው ፓርቲ ጥቃት ሰላባ መኾኑ አይቀሬነት እውን እየኾነ መምጣቱ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው፡፡
  በተለይ ጥቃቱ የማኅበሩ የአስተሳሰብ፣ የመርሕና የስትራተጂ ርትዓተ አእምሮ የኾኑ አመራርና አባላቱ ላይ ማነጣጠሩ ርምጃው ደጅ ላይ ስለመኾኑ ማረጋገጫ ተደርጎ እየተወሰደ ነው፡፡ በኢ.ቴቪ ይዘጋጃል ተብሎ የተነገረውም ዶኩመንተሪ የዚሁ ጥቃት መንገድ ጥርጊያ ተደርጐ መታየት አለበት ይላሉ፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር፡፡
  ያልተሳካው ሙከራ!
  እኚህ ምሁር ለዕንቁ መጽሔት እንደገለጹት፣ ሥርዐቱ ማኅበረ ቅዱሳን የማፍረስ አዝማሚያ ማሳየት ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ በንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ፣ በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም የውንጀላ ጽሑፍ አቅራቢነት፤ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ በነበሩት አቶ ኣባይ ፀሐዬና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስተር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያምአቅጣጫ ሰጪነትና ተሳታፊነት መስከረም 12 ቀን 2002 ዓ.ም የተካሔደው የውንጀላ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ እንቅስቃሴ ይፋዊ ጅማሮ እንደነበረ የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው፡፡
  በአምስተኛው ዘመነ ፕትርክና መገባደጃ መንግሥታዊ ሥርዐቱ ይኹን ቤተ ክህነቱ የጥፋት እጁ ኾነው ያገለግላሉ የሚባሉት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃና አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ማኅበሩን እንዲዘጉ ግፊት ቢያደርጉባቸውም ‹‹ፓትርያርኩ የእነርሱን የመጨረሻ ሕልም እውን ለማድረግ ሳይፈቅዱ ላይመለሱ ሔዱ፤›› የሚሉት አንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባል፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ግን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በኻያ ዓመታት ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያልፈጸሙትን ግፍ አንደኛ ዘመነ ፕትርከናቸውን እንኳ ሳያከብሩ ፈጸሙ ይላሉ፡፡
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የገዥው ፓርቲና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የዘወትር የጥፋት ግንባር አባላትን ግፊት እያለ ማኅበሩን ለመዝጋት ያልደፈሩት፣ ለማኅበሩ በጎ አመለካከት ስላላቸው ወይም በማኅበሩ አገልግሎት ፍቅር ስለወደቁ ሳይኾን ‹‹ማኅበሩን መንካት የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ስላሰሉት ነው፤›› ይላሉ አንድ ሊቀ ጳጳስ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሥርዐቱን ተልእኮ ለማስፈጸም በሚል የጀመሩት ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ እንቀስቃሴ መተባበር፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ውስጥ ከመክተቱም በላይ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው በቅጡ የተረዱ አይመስሉም፤›› ሲሉ እኚኹ ሊቀ ጳጳስ ለዕንቁ መጽሔት ገልጸዋል፡፡

  ReplyDelete
 15. mechem yey commete post ataderegotemአዲሱ መግፍኤ ነገር
  ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቅዱስ ፓትርያርኩን ይኹን በዙሪያቸው የተሰበሰቡትን አማሳኞች ተጠቅሞ ማኅበሩን ለማፍረስ ለምን ፈለገ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ የሰጡ አንድ ምሁር፣ ማኅበረ ቅዱሳን ብዙኃን ጳጳሳትን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ምሁራን፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችንና ምእመናንን በዙሪያው ለማሰለፍ የሚያስችለው ርእይ፣ ዓላማና አቅም እንዳለው በተግባርም እያሰለፈ ያለ ማኅበር መኾኑን በማስገንዘብ ይጀምራሉ፡፡
  እኚህ ምሁር ማኅበረ ቅዱሳን የቆመለት የአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልማትና ዕድገት አቅጣጫ ጥቅማቸውን በላቀ ደረጃ የሚያስጠብቅላቸው የመኖራቸውን ያህል የኘሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ፣ ብልሹ አሠራርና ተቋማዊ ቀውስ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸው መኖራቸውንም ይጠቅሳሉ፤ በትይዩም ሥርዐቱ የእነዚህ ተጠቃሚ በመኾኑ የማኅበረ ቅዱሳንን መኖር አይፈልግም ይላሉ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማዳከም ወይም ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት ያልተሳካለት ኢሕአዴግ ማኅበሩን ለማፍረስ የመምረጡ አንድ መንሥኤ ይህ ሊኾን እንደሚችልም ያስረዳሉ፡፡
  ዘመናዊ ትምህርት የቀሰሙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሁራዊ መለዮ የኾነው የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የጎሳ ይኹን የቤተ ሰብእ ማንነት ሳይለያያቸው ኹሉም በቤተ ክርስቲያንና በሀገር ፍቅር እሳት የሚቃጠሉ፣ አገራቸውና ቤተ ክርስቲያናቸው ሌሎች አገሮችና አኀት አብያተ ክርስቲያናት ከደረሱበት የሥልጣኔ ደረጃ ላይ ለማድረስ በጎ ፍላጎትና ምኞት የሞላባቸው ናቸው የሚሉት እኚህ ምሁር፣ ገዥው ፓርቲ ማኅበሩን ለማፍረስ ቆርጦ የተነሣበት ሁለተኛው ምክንያት ማኅበሩና መላው አባላቱ ሀገራዊ ብሔርተኝነትን ማቀንቀናቸው ነው ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሥርዐቱ በአቋም ከሚያራምደው የዘውግ ብሔርተኝነት ጋር በእጅጉ ይቃረናል፡፡ በዚህ የተነሣ ማኅበሩ የሥርዐቱ የፕሮፓጋንዳ ጥቃት ሰለባ ኾኗል ይላሉ፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፈቃድና ጥበቃ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ላለፉት ኻያ ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ተጠብቆ እንዲቆይ፤ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ መምህራንና ደቀ መዘሙርቱ ያሉበት አስከፊ የድህነት ኹኔታ በማጥናት ህልውናቸውን ከሚፈታተነው ችግር ተላቀው፣ በራሳቸው በመተማመን የቤተ ክርስቲያኒቱ የዕውቀት ማእከልነታቸው ጠብቀው ዘመን እንዲሻገሩ፤ ገዳማትና አድባራት በዘላቂ ልማት ተጠቃሚ ኾነው በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉና በአገሪቱ ልማት ተሳታፊና በቅድመ ግንባር አርኣያ እንዲኾኑ በሞያ፣ በገንዘብና በጉልበት ተግባራዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንድ የቤተ ክህነቱ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ ያስረዳሉ፡፡
  እኚኹ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ ሦስተኛው ምክንያት፣ በመንግሥት የፀረ አክራሪነት ትግል ሽፋን መንግሥታዊ ሥልጣናቸው ተጠቅመው ሃይማኖታዊ ፍላጎታቸውን ማኅበረ ቅዱሳንን በመቅበር ለማሳካት ደፋ ቀና የሚሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከቤተ ክህነቱ አማሳኞች ጋር ጥብቅ የዓላማና የጥቅም ቁርኝት የፈጠሩ የደኅንነት ሰዎች በጋራ መንግሥትን በማሳሳትና የፕሮፓጋንዳ አቅጣጫውን በመቃኘት የፈጠሩት የሐስት ክሥ ውጤት ነው፤ ብለዋል፡፡
  የሥርዐቱ ስውር እጆች
  የማኅበሩን ተቋማዊ እንቅስቃሴ እንዲገደብና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት የምሁራን ንቁ ተሳትፎ እንዳይኖር የሚፈልጉት እኒኹ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና አማሳኝ የደኅንነት ሰዎች ብቻ አይደሉም የሚሉት የቤተ ክህነቱ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ በራሷ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅሮች ውስጥ ሓላፊነት ይዘው በስውር ቤተ ክርስቲያኒቱን ለሚያጠፉ አካላት የማይታይ እጅ ኾነው በመሥራት ላይ ያሉ ግለሰቦችንና ቡድኖችንም እንደሚጨምር ገልጸዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን መቅበር፣ በመቃብሩም ላይ እያላገጡ መቆም፣ ከዚያም የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነትና ህልውና ለአደጋ አጋልጦ የማትሰማ የማትለማ የእነርሱ ጥገኛና የርካሽ ዓላማቸው መሣርያ ማድረግ ዋነኛ ተልእኳቸው ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ለዕንቁ መጽሔት ሰጥተዋል፡፡
  ቅዱስ ሲኖዶስ በመተዳደርያ ደንብ ቆጥሩና ስፍሮ በሰጠው ተልእኮ መሠረት ማኅበሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ፣ በሥነ ምግባር እንዲታነጹ፣ በተሰማሩበት ሓላፊነት ኹሉ ሀገራዊ ሓላፊነት እንዲሰማቸው፣ የብዙ ታሪክና ቅርስ ባለቤት የኾነችውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ምቹ ጊዜ ጠብቀው ሊያጠፏት ካሰፈሰፉ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንድትጠበቅ የሚሰጠውን አገልግሎት በበጎ የማይመለከቱት እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ፓትርያርኩን ጨምሮ የሥርዐቱ ቋሚ ጉዳይ አስፈጻሚ የኾኑ ጥቂት ጳጳሳትም ማኅበሩን በማፍረስ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳሉ ይገለጻል፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳን በኻያ አንድ ዓመታት ታሪኩ የሠራው ሥራ ምሁራን አባላቱ በመዋቅራዊ አሠራር ብቻ ሳይወሰኑ በተናጠልም አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን ለመቋቋም፣ በስውርና በግልጽ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚፈጸሙ ደባዎችን በማጋለጥ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑንም በአስተውሎትና በመረጃ በታገዘ መንገድ በማንቃት ሰፊ መሠረት ያለው ማኅበራዊ – መንፈሳዊ አቅምና እሴት ፈጥሯል፡፡
  በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ሃይማኖታዊና ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎት ያላቸው የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ የዓላማና ጥቅም ቁርኝት የፈጠሩ ጥቂት የደኅንነቱ ሰዎች ተቋሙን በማፍረስ ቤተ ክርስቲያንን በሒደት አዳክሞ በመቆጣጠር አልያም በታትኖ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ማስረከብ ቀላል እንደኾነ ያስባሉ፡፡
  ይኹን እንጂ ‹‹በምድር ላይ ሊኾኑ ከማይችሉ ነገሮች አንዱ ይኼ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ምኞት ነው፤›› የሚለው አንድ የቀድሞው የማኅበሩ ሥራ አመራር አባል እንደሚያሳስበው፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች፣ ማኅበሩ በግቢ ጉባኤያት አንፆ መስቀል በአንገታቸው አስሮ የሸኛቸው በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ምሩቃን፣ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራንና በማኅበሩ ስኬታማና ተጨባጭ አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ያደረባቸው ምእመናን ኹሉ ለዘመናት እየመነዘሩ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ተግዳሮቶች የሚመክቱበት መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው በቅጡ መረዳት ያሻል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አላወቁማ ምን ይደረግ ይሞክሩን

   Delete
  2. አላወቁማ ምን ይደረግ ይሞክሩን

   Delete
 16. መካሪ የሌለው መንግሥት?
  ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይስማማሉ፡፡
  ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ በሃይማኖታዊ ዕውቀት የታጠቀ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ያወቀ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የተገነዘበና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ብቁ ዜጋ እንዲኾን የተጫወተውን በጎ ሚና የሚገነዘበው ዜጋ ‹‹መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፤›› የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ ከእስልምናው የተቃውሞ ጎራ ጋር ትይዩ የኾነና ከቁጥጥር ውጭ የኾነ መቧደን የሚፈጥር ቀውስ ሊቀሰቅስ ይችላል ይላሉ፡፡
  ስለዚህም በርካታ አገራዊ አጀንዳዎች አሉኝ በማለት ሕዝቡን ለሕዳሴ የሚያነሣሣው መንግሥት፣ በተለይም የፀረ አክራሪነቱን ትግል በቅድመ ግንባር እንዲመራ ፖሊቲካዊ ተልእኮ የተሰጠው አካልና ሓላፊዎቹ፣ መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራታቸውና እጃቸውን ወደ ብልሽት ከመዘርጋታቸው በፊት ነገሮችን በርጋታ ማጤንና በግልጽ ውይይት ማመን ይበጃቸዋል የሚለውን ምክር የሚጋሩ ብዙዎች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 17. ለመሰረት ስብሃት/አሬዎስ/ሉተር ለአብ ልጆቸና መሰሎቹ ሁሉ እንደምንአላችሁ??

  የሚገርም ነው የሰፈር ስራፈቶች ተራ የሮጊቶች ወሬ ይዛችኋል ካዋጣችሁ በርቱ!! እኔ ግን እላለሁ ዳንኤል እንደናንተ ስራ ፈት አይደለም ለዚህም ጊዜ የለውም እናንተ ግን ቁጭ ብላችሁ ወሬ ትፈተፍታላችሁ ትሳደባላችሁ "እስመ ናሁ አነ ተናገርኩ አንትሙ ትሜስሉ በኩል ግብሩ ለዲያብሎስ"

  እመቤቴ ማርያም ልባችሁን ትመልስ የእውነቱ ጌታ ይገለጥላችሁ!!!

  ReplyDelete
 18. Denkorowoch yejoro aydelem yelib enante yesidib blog kefetachihuna yesidib amrotachihun tewetachihu fernjoch tinanish aymirowoch silesew yaweralu yalut enanten lemenager new esti yesew hatyat titachihu siletsidik sileniseha awiru ene daniel yesew hiwot yemegeneba yitsifalu enante yesew hiwot yemibekil Daniel bedel binoribet eyastemaren yalew endezi bedilu bilo aydelem kebedel eraku bilo enji silesu metfo neger yemitawerun endintelaw new kehone yewededinew btsidk mengedu silehone atdkemu egziabher yewededewin lemin egna entelalen bintelam yetim anders hatyat benoribet esu yetagesewin enante mindinachihu wey hiwetachihu wey tshufachihu ayastemir. esti kifatachihun temelketu ewnet yemselelachihu mesloachihu yetetsafewin wered eyalachihu tidegmutalachihu kentu kentu nachihu atidinum

  ReplyDelete
 19. ተረት መሆኑን ለዲ/ን ያረጋል መጽሀፍ መልስ ሰጥታችሁ ለምን አላሳያችሁንም ወሬ እና ብቻ

  ReplyDelete
 20. በእውነት ላይ ምንም ልንጨምር አንችል!

  ዳኒ የተናገረው ውሸት የሆነው የቱ እንደሆነ በጽሁፉችሁ ላይ አላየሁም::
  እናንተም ማስረዳት አልቻላችሁም! አባት እንዲህ ባይባል ጥሩ ነው ልንል እንችላለን ::
  ግን ውሸት አይደለም :: ወይ እርሳቸው ወይም በዙሪያቸው ያሉ አካላት /ግን እኔ አይደለሁም በዙራዬ ያሉ ናቸው :: በማለት ከተጠያቂነት መዳን ይቻላል?/ የሚሰሩት ተግባራት ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚነው ብላችሁ ታምናላቸሁ? ወይስ የዚች ቤ/ክ አባል አደላቸሁም ? አገር ያወቀውና ጸሐይ በሞቀው የዛሬዋ ቤተ ክርሰቲያን ጉዳይ አንድ ሰው ተሳደበ አልተሳደበም የሚለው ጉዳይ ነው ካላችሁ …. አላወቃችኃትም ማለት ነው:: ወይም እናተም ሌላ ዓለማ አንዳለባችሁ ያስመስላል:: ስለዚህ በእውነት ላይ ምንም ልንጨምር አንችል!

  ReplyDelete
 21. Ante seytan yeweledkew aleh aydel minyigermal?

  ReplyDelete
 22. It is so sad to see most of the comments that are written on this page are out of mere ignorance and caustic insults to those that post articles which are based on important church issues and deserve a thorough discussion. It is one thing to give pointed and critiqued opinions, it is another to be obnoxious, hateful and spew childish remarks by insulting writers and/or those commenting on the issue. Ethiopia was known among other things for the etiquette of its people, mannerism and its culture. The woyane generation has totally lost a three-thousand-year history of respecting elders, opinions of others, measured conversations, etc. This is why most of the elders and educated Ethiopians resigned from participating in any meaningful discussions on issues that would make or break the future of Ethiopia.
  The Orthodox religion used to be at the forefront of the religion and culture, but since it allowed to be dictated by woyane it had lost its credibility and no one pays attention to what it says. To top that off, it recruited a cult which names itself Mahibere Kidusan which is at the verge of taking it over and replace all of its clergy, teaching and a 3000-year history with its own.
  This cult had ruined the country’s youth by teaching it a different gospel from what the apostles taught, as Paul explained in his writing to the Galatian church. They claim to be Ethiopians but they have nothing that even resembles Ethiopian, tradition, culture, etiquette, etc. They claim to be a Christian, but they have never practiced what Christ taught, they are the ones you see on this and other pages that shamelessly throw around insults against people for writing their opinions. The follow up story on this page is about their famous leader Deacon Danielle Keibret, who pretends to be a Christian by preaching a different good news, and publicly insulting and writing lies about the Patriarch whom he supposedly was to respect as he is at the bottom of the hierarchy. The writer of Hebrews tells us it would be impossible to bring back to Christ those that has already condemn and rejected Him and has gone astray.
  Hebrews 6:4-6
  4 For it is impossible to bring back to repentance those who were once enlightened—those who have experienced the good things of heaven and shared in the Holy Spirit, 5 who have tasted the goodness of the word of God and the power of the age to come— 6 and who then turn away from God. It is impossible to bring such people back to repentance; by rejecting the Son of God, they themselves are nailing him to the cross once again and holding him up to public shame.
  God help them!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hey Pastor, What the hell do you have in our Tewahido Church? Mind your own business only and leave our church to the followers only.

   Delete
 23. "Hell" is where you belong not in the Orthodox Church! You sound like you are part of the ISIS group. Christians don't talk like that.

  ReplyDelete
 24. አሁን እንደዚህ የምትጮሁት በሰሞኑ ዳንኤል ክብረትና ቁርጠኛ የተዋህዶ ልጆች በተሐድሶና መናፍቅ በሆናችሁት ለእናንተ በኢትዮጵያ አና በአለም ለጀመሩት የሃሰት ተምህርታቹ መልስ ስለሰጡ ነው እነርሱ ግን አገልግሎት ላይናችው ባትለፉ ይሻላል ?? መስሚያ የለንም

  ReplyDelete