Tuesday, April 19, 2016

የሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመተላለፍ ህገ ወጥ ሰባኪያንን የጋበዙ የስብከተ ወንጌል ኃላፊ ከስራና ከደሞዝ ታገዱበደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊ የነበሩት መምህር ግሩም በለጠ እና የደብሩ ሰባኪ የሆኑት መምህር አምደሐይማኖት ያለ ሐገረ ስብከቱ ፈቃድ የላብቶብ አገልጋዮችን በመጋባዛቸው ከስራና ከደሞዝ ታገዱ።
የእጉዱን ምክንያት የሚያብራራው ደብዳቤ እንደ አብራራው እነዚህ ሰዎች ከስራና ከደሞዝ የታገዱት “---የማኅበረ ቅዱሳን አቀንቃኝ ያረጋል አበጋዝን ጠርተው ካህናቱን መነኮሳቱን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያንን ወሯታል…” በማስባልና እንዲሁም “…ህዝቡ እንዲደናገር በካህናቱና በመነኮሳቱ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት…” በማድረጋቸው እና “…የቤተክርስቲያኒቱን መሪዎች አሰድበው ለተሳዳቢ የሰጡ ስለሆነ…” መሆኑን ገልጿል።
በተለይ መምህር አምደሀይማኖት ለማኅበረ ቅዱሳን ምግብ ቤት እንጀራ አቅራቢ እንደመሆኑ መጠን የእንጀራ ገመዱን የሚያራዝምበት አማራጭ እንደ አገኘ በደስታ የቆጠረ ቢሆንም ያገኘው ምላሽ ግን ከጠበቀው በላይ ሆኗል።
ከቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከቅዱስ ሲኖዶስ በተላለፈው ጥብቅ መመሪያ መሰረት በተለይ ሁከትንና ፓለቲካን እያጣቃሱ የሚሰብኩ ዘወትር አውደ ምህረቶችን በላብቶብና በፕሮጀክተር አሳብጠው የነበሩት ሁሉ ለቤተክርስቲያኒቱ የዳር አገር ሰዎች በመሆቸው ህጋዊ የመግቢያ በር በማጣት ጋራ ተጋብተው እንዳሉ ይታወቃል። 

በዚህም ምክንያት አውደ ምህረቶች ጤናማ ወንጌል እየተሰበከባቸው አንጻራዊ ሰላም እየተነፈሰባቸው ይገኛሉ። ከዚህ የተነሳ የአ.አ ሀገረ ስብከት ይህን የቅዱስነታቸውንና የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በተገቢው መንገድ በማስተላለፉ፥ የወረዳ ሥራ ኃላፊዎች አጥቢያዎችን በሚገባ በመቆጣጠር ሕገ ወጥ ሰባኪዎችን ተከላክለዋል። እንደ ጎፋ ገብርኤልና ግቢ ገብርኤል የመሳሰሉ ደብሮች ደግሞ መመሪያዎችን በመጣሳቸው  ማስጠንቀቂያ ተላላፎባቸዋል።
ይህ መመሪያ በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል መመሪያ ኃላፊ ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት በመሆኑ ውልፍት የሚለው ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እያገኘ ይገኛል። ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ፈለገ ለመወራጨት መንገድ በማጣት ተጨንቆ ሳላ የሥራ አስኪያጆችን ልውውጥ ምክንያት በማድረግ ይህን መመሪያ የግለሰብ መመሪያ በማድረግ የተላለፉት የራማ ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች ተገቢውን ቅጣት ተከናንበዋል። ያረጋል አበጋዝን በ19/07/2008 በደብሩ ስብከተ ወንጌል በተጋበዘ ጊዜ ከላይ እስከታች ያሉትን አባቶች በተሃድሶነት ፈርጆ ተሳድቦ በእግዚአብሔር ቃል ሊያርፍ የመጣውን ህዝብ በነገር አባክኖ የጨለማ ጩኸቱን አሰምቶ ሄዷል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ከቤተክርስቲያን እየጎረሱ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን የሚውጡ የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኃላፊና አንድ ሌላ አገልጋይ እንደማስቆም ዝም ብለዋቸዋል።
ሁል ግዜ ከቤተክርስቲያን ጋር የሚወግኑት እና በአላማቸውና በቆራጥነታቸው ወገናዊነት እና አድልዎ የማይታይባቸው የኮልፌ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እነዚህን ህገ ወጥ ሰባኪያንን ደብሩ አግዶ ሲልክላቸው ክፍለ ከተማውም እገዳወን ተቀብሎ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አስታውቋል። እንዲህ አይነቱን ተግባር የሀገረ ስብከቱ አዲስ ሥራ አስኪያጅም በቸልታ እንደማያልፉት አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ  በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአዲስ አንባ ኪዳነ ምህረት አለቃ በቀለ ዘውዴ ባለፈው እሁድ ዕለት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጋር በመሞዳሞድ በፕሮጀክተር የሃይማኖት አባቶችን ሲያሰድቡ ውለዋል። ይህን የሚያመቻቸው ነጋዴው የሺጥላ ሞገስ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። የሺጥላ ዲቁናውን ይሁን ቅስናው ከየት እንደተቀበለው የማይታወቅ ሲሆን ባለበት ደብር የሚካሄደውን ጻረ ወንጌል እንቅስቃሴ ፊታውራሪ ሆኖ እየመራው ይገኛል። የሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌል መምሪያ እንዲህ አይነት ግለሰቦች አሰራር ላይ እየፈጠሩት ያለውን ችግር በጥልቀት አጥንቶ ዘለቄታዊ መፍትሔ ሊያበጅለት ይገባል።
  

27 comments:

 1. Sele Dr yaregal Abegaz enikuan anite tehadisow menafikan kerito lelawum menager aychilim.Awe yeegiziabherin sew menager lemenafikan kelal new gin waga yasekefilal. enide Dr yaregal Abegaz aynet 5 sew ye Ethiopia Orthodox betekiristiyan binorat betekirstiyanachin bicha satihon agerachin yet bederesech. Zirzir alinagerim wudase kentu enidayhon gin yaregal bekalu saihon betegibar yemiyastemir ejig menifesawi sew new eskezare dires lalefut 24 ametat yegiziabher sew hono sai sintoch demas honew sikeru bersu tsenat des yilegnal.geta yiketahal sele yaregal atawura, please

  ReplyDelete
 2. እንዲህ እየታተሉ እርምጃ መውሰድ ጥሩ ነው። ከያረጋል ጋር አብረን ተምረናል። ተማሪው ሁሉ የሚያውቀው እንደ አእምሮ በሽተኛ ነው። የፈዘዘ የደነዘዘ ግራ የገባው ሰው ነው። እሱ አስገንዝቦት ሰው ምን እንደሚገባው አላውቅም። ግንዛቤ ሳይሆን ድንግዝጋዜ ቢሉት ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እሺ የኔ ቱልቱላ እሱ ዶክተር/በቅድስት ሃይማኖት ውስጥ ሆኖ/ ሆኖ በ ዓለማዊው ትውልድ በ መንፈሣዊውም እየቀረፅ ሲሆን አንተ ግን ምንፍቅናና ድድብናን እስከዛሬ ይዘህ ቀጥለሃል

   Delete
  2. አብረህ ከተማርክ ለምን ስምህን አልገለጽክም የጭለማዉ አርበኛ : ደግሞ ከእናንተ ምን ይጠበቃል:: ውሸት እንጂ ታድያ እርሱን ለማወቅ እና ለመረዳት ያለመቻልህ የአንተን ደካማነት እና ትዕቢት ነው የሚያሳየዉ :: ምክንያቱም በመምህራኖቹ ብቃት እንዳለው ተረጋግጦለት መሰለኝ በኮሌጅ መምህርነት እንዲሰራ ያስቀሩት::አንተስ የት ነህ?

   Delete
  3. keyaregal ketemarikima yaregal yemitawekew bemenifesawinetuna lelawun yemitawekibetin anite tawukewaleh lelawum temari yawukewal wudase yemifelig sew selalihone ena wudasen atibiko yemitela selehone alinagerim. Aemiro beshetegn setil tinish aysemahem azinalehu banite anegager

   Delete
  4. ሰይጣን በፍጹም እውነት ይመሰክራል ተብሎ አይጠበቅም አንተም ልታውቀው የሚገባው ሥለደነዘዘ ሳይሆን ሥለደነዘዝክ አልገባህም ዓይነ ልቦናህን ያብራል እኛ ግን በደንብ ገብቶናል አንተና መሰሎችህ ምናልባትም ደብዳቤውን የጻፉት በጥቅም ታውራችሁ ደንዝዛችሁ ይሆናል አዲሰ አበባ ሀገረ ስብከት በዚህ በሰፊው ይታመል እና ስለዚህ እውነት የተናገረ ከደነዘዘ ልክነህ ያረጋል ደንዝዟል ለአንተና ለመሰሎች ግን በእግዚአብሔር ተመርጧል እናም እፈር እግዚአብሔር ይመስገን !

   Delete
  5. My dear, it you that is foolish, not Yaregal. Read the book << Medlote Tsidik>> he wrote on Tehadeso menafikan like you.

   Delete
  6. please tell me about yourself if u studied with yaregal. I studied with him and I know him very well.He is not like other the so called christians and who pretend, but Yaregal is quite different,If you criticize other preachers I don't mind because yaregal is especial persons. I myself don't listen others because I know their activities but Yaregal speaks not by his words but by his deeds.

   Delete
 3. መጽሐፍስ ወይፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ አይደል የሚል? እርምጃው መቀጠል አለበት ቤተ ክርስቲያናችን የማንም ጋጠ ወጥ መጫወቻ መሆን የለባትም እርምጃው ተገቢና ወቅታዊ ነው።

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር በግዜው መልስ አለው ለዚህም ግን አትቸኩሉ አናንተ እና መሰሎቻችሁ በተናገራችሁት የምትጠፉበት ግዜ ሩቅ አይሆንም ስለዚህ በሚያልፍ አለም ለዘለአለም የተባረከውን እግዚአብሔርን አታሳዝኑ ልብ ይስጣችሁ ??

  ReplyDelete
 5. Kift afe kesenef aemiro diros min yitebekal sidib enji?????? enakachihualen

  ReplyDelete
 6. በጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ7 አመት በላይ ታላቅ ወርሀዊ የቅዱስ ገብርኤል ጉባዬ ይካሄድ ነበርና ቤተክርስቲያኗ ከበባእድ አምላኪ ፣ እስልምና ፣ የፖሮቴስታንት ፣ አምላኪዎች የተከበበች ናት በመሆኑም ጉባዬው የሚካሄድ የነበረው ይሄ ቁጭት በነበረባቸው ምእመናን ወንጌል እንዲሰበክ የተጀመረ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ ቤተክርስቲያኗ በረከትና ጸጋ ያላቸው አባቶች ያሉባት ቦታ ናት ለቤተክርስቲያኗ ጉባዬውን ለማወክ የማህበሩ ሰዎች ከጥቂት ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ጋር ግንባር በመፍጠር እየተጠራሩ እየመጡ ያልታገዱትን አገልጋዬች ታግደዋል ይህ መሰሪ ማህበሩ ራሱን እነደ አለቃ በመቁጠር የቤተክህነት ሀላፊነት ወደኋላ በመተው ላለመታዘዝ በበሬ ወለደ ውንጀላ በየቤቱ በየለቅሶቤቱ እየዞሩ ፒቲሽን እያስፈረሙ ጉባዬው እንዲታገድ ሲጥሩ አዲስ የቤተክርስቲያን ሀላፊዎች ተሾመው ሲመጡ አለቆችንም ለማሳመን ሲጥሩ ሀላፊዎችም ገባዬውን በመገምግም ምንም ከሚሉት ጋር የማይገኛኝ አገልጋዮችም የቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆናቸው በመረጋገጡ ጉባዬው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን አሁን ግን ማንኛውም ማህበር እንዲሁም ግለሰቦች የቤተክህነቱን ህጋዊነትን እንዲከተሉ ሲባል ያለፈቃድ እንዳያስተምሩ የሚል መመሪያ ሲወጣ ይህ ማህበሩን ጨምሮ ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አካል በዚህ ትዛዝ ስር መተዳደርና ማክበር ነበረበት ግን ይህ ማህበር ጊዜው አሁን ነው በማለት የዋህና ምንም ያልጠረጠሩ የስበከተ ወንጌል አገልጋዮች መታዘዝ ያለባቸው ለቤተክህነቱ መሆኑንና የቤተክህነቱን ትእዛዝ በማህበረ ቅዱሳን መሰሪዎች ከስርስር እየተከታተሉ መምህር እኛ እናመጣለን ጉባው ለአንድ ቀንም አይስተጓጎልም እያለ ወሬ ለሚያበዛ ምቀኛ ወጥመዱ ገቡለት የእለት ጉርስ የሚያገኙ ምስኪን ድሆች ታገዱ ማህበሩ ስርአት ሳይኖረው የቤተክርስቲያንን ጊቢና መድረኮች የረበረሻና የጭቅጭቅ ቦታ እንድትሆን እንደፈለገው ሰንበት ተማሪዎች ነን በማለት ልጆቹን በማባበል እድሜያቸው ከ30 አመት በላይ የሆኑ የማህበሩን ጉዳይ ለማስፈጸም ሰርገው በመግባት ልጆቹ ወንጌል ሳሆን ከአዲሳባ ከተማ አድባራት ውስጥ በረብሻ ጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል እንዲጠራና ህዝቡን እርስ በእርሱ እነዲከፋፈልና እንዲጠራጠር ሲያደርጉ ቆይተው የሰንበት ተማሪዎቹ ልጆች በማን አለብኝነት እንዲበረታቱ በማድረግ ነባሩን ጉባዬ አፍርሶ ራሱን ታላቅነት ለማሳየት ሲጥር በፖሮጀክተር ሲላምጡት የኖሩትን ወሬ ቤተክርስቲንንና አባቶችን የሚያወርድ ሲዲ ሊያስተላልፉ ሲሞክሩ አስዳዳሪው ሀላፊነት ስለነበረባቸው በህግ ለማስከበር አስቆመዋቸዋል፡፡
  ያካባቢው ምእመናን ስንከላከል የኖርነው ይህ እንዳሆን ነበር ልጅ የቦካው ሆነና አረፈው፡
  ለማንናውም ቤተክርስቲያንን የሚጠብቃት አያንቀላፋም!!!
  እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅልን!!!!!

  ReplyDelete
 7. በጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ7 አመት በላይ ታላቅ ወርሀዊ የቅዱስ ገብርኤል ጉባዬ ይካሄድ ነበርና ቤተክርስቲያኗ ከበባእድ አምላኪ ፣ እስልምና ፣ የፖሮቴስታንት ፣ አምላኪዎች የተከበበች ናት በመሆኑም ጉባዬው የሚካሄድ የነበረው ይሄ ቁጭት በነበረባቸው ምእመናን ወንጌል እንዲሰበክ የተጀመረ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ ቤተክርስቲያኗ በረከትና ጸጋ ያላቸው አባቶች ያሉባት ቦታ ናት ለቤተክርስቲያኗ ጉባዬውን ለማወክ የማህበሩ ሰዎች ከጥቂት ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ጋር ግንባር በመፍጠር እየተጠራሩ እየመጡ ያልታገዱትን አገልጋዬች ታግደዋል ይህ መሰሪ ማህበሩ ራሱን እነደ አለቃ በመቁጠር የቤተክህነት ሀላፊነት ወደኋላ በመተው ላለመታዘዝ በበሬ ወለደ ውንጀላ በየቤቱ በየለቅሶቤቱ እየዞሩ ፒቲሽን እያስፈረሙ ጉባዬው እንዲታገድ ሲጥሩ አዲስ የቤተክርስቲያን ሀላፊዎች ተሾመው ሲመጡ አለቆችንም ለማሳመን ሲጥሩ ሀላፊዎችም ገባዬውን በመገምግም ምንም ከሚሉት ጋር የማይገኛኝ አገልጋዮችም የቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆናቸው በመረጋገጡ ጉባዬው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን አሁን ግን ማንኛውም ማህበር እንዲሁም ግለሰቦች የቤተክህነቱን ህጋዊነትን እንዲከተሉ ሲባል ያለፈቃድ እንዳያስተምሩ የሚል መመሪያ ሲወጣ ይህ ማህበሩን ጨምሮ ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አካል በዚህ ትዛዝ ስር መተዳደርና ማክበር ነበረበት ግን ይህ ማህበር ጊዜው አሁን ነው በማለት የዋህና ምንም ያልጠረጠሩ የስበከተ ወንጌል አገልጋዮች መታዘዝ ያለባቸው ለቤተክህነቱ መሆኑንና የቤተክህነቱን ትእዛዝ በማህበረ ቅዱሳን መሰሪዎች ከስርስር እየተከታተሉ መምህር እኛ እናመጣለን ጉባው ለአንድ ቀንም አይስተጓጎልም እያለ ወሬ ለሚያበዛ ምቀኛ ወጥመዱ ገቡለት የእለት ጉርስ የሚያገኙ ምስኪን ድሆች ታገዱ ማህበሩ ስርአት ሳይኖረው የቤተክርስቲያንን ጊቢና መድረኮች የረበረሻና የጭቅጭቅ ቦታ እንድትሆን እንደፈለገው ሰንበት ተማሪዎች ነን በማለት ልጆቹን በማባበል እድሜያቸው ከ30 አመት በላይ የሆኑ የማህበሩን ጉዳይ ለማስፈጸም ሰርገው በመግባት ልጆቹ ወንጌል ሳሆን ከአዲሳባ ከተማ አድባራት ውስጥ በረብሻ ጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል እንዲጠራና ህዝቡን እርስ በእርሱ እነዲከፋፈልና እንዲጠራጠር ሲያደርጉ ቆይተው የሰንበት ተማሪዎቹ ልጆች በማን አለብኝነት እንዲበረታቱ በማድረግ ነባሩን ጉባዬ አፍርሶ ራሱን ታላቅነት ለማሳየት ሲጥር በፖሮጀክተር ሲላምጡት የኖሩትን ወሬ ቤተክርስቲንንና አባቶችን የሚያወርድ ሲዲ ሊያስተላልፉ ሲሞክሩ አስዳዳሪው ሀላፊነት ስለነበረባቸው በህግ ለማስከበር አስቆመዋቸዋል፡፡
  ያካባቢው ምእመናን ስንከላከል የኖርነው ይህ እንዳሆን ነበር ልጅ የቦካው ሆነና አረፈው፡
  ለማንናውም ቤተክርስቲያንን የሚጠብቃት አያንቀላፋም!!!
  እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅልን!!!!!

  ReplyDelete
 8. ታግዶ የነበረውና ማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 15-21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ለ5ኛ ጊዜ ሊያካሔደው የነበረው ዐውደ ርእይ ተፈቀደ፡፡

  ReplyDelete
 9. Anchim sewu honesh D/n Yaregalin titechalish minyadergal keahiya yewalech gider ..... endemibalewu antena gibaberochachiwu bemulu yimetawukut chuhitina yemenafikan chifera yihi kehone yisemal bileh yimitasib irasihin ina abaselamawochin shewudi ewunetignochuma dimitsachewu yitawekal yisemal. be D/n yaregal kenteh kehone kitil bel yedabilos lij mingizem bihon shi gizi bitikebatir yetewahidon lij atidersibetim izawu yemenafikan gedel giba

  ReplyDelete
 10. የመሓበር ቅዱሳን አወደ ርእይ ተፈቀደ ደስ አይልም፡፡ ሓራ ጥቃዎች አሁንስ ምን ትሉ አለነበባችሁትም እንዳይባል አፍራችሁ ነው አይደል

  ReplyDelete
 11. Mahibere Satan really has no religion, no faith, no belief whatsoever; they worship the almighty dollar and whatever it takes to get they will do it. They really! Really! do not belong in any church. They are a plague that have been unleashed on the Ethiopian Orthodox church!! The sower (Abune Gorgorios) with no mal-intention sown them among the flock to do good work, but the devil was sown among them and deceived them all to do his evil deed. They ruined the religion by persecuting its clergy, teachers, and its good work. Now it seems like God had enough and has raised this Patriarch to bring things to order. Every devout Christian has to fervently pray for him to have the strength and the stamina to stay the course. The devil has never been working this hard and strong in the Global Ethiopian Orthodox churches. There is not one congregation that this group somehow, someway negatively affected. Let us all put our hopes in God Almighty and pray to Him to drive Sataniel and his demons out of the Ethiopian orthodox churches. Glory be to God in the highest!!

  ReplyDelete
 12. God is doing his work, the head of coruption network in AA hagere sibket exposed it self. The exhibition is allowed. The Tehadiso guyexposed himself in Chiro. In Christianity, the permanent enemy is only satan. Hence, those people who made this anti Christian decision should ask forgiveness from God and the meme her and the Mememehran they persecuted. The sentimental Dn Daniel who did no have to wait for God judgement should also ask forgiveness of hi Holiness Abba Mathias

  ReplyDelete
 13. ከግንቦት 17- 22 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ይካሔዳል፡

  ታግዶ የነበረውና ማኅበረ ቅዱሳን €œኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ€ በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 15-21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ለ5ኛ ጊዜ ሊያካሔደው የነበረው ዐውደ ርእይ ተፈቀደ፡፡
  ዐውደ ርእዩ ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ የነበረ ቢሆንም ማኅበሩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ባደረግው ውይይት ስምምነት ላይ ተደርሶ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት መፈቀዱን የሚገልጽ ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑን የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ አቶ ተስፋዬ ቢሆነኝ ገልጸዋል፡፡

  ማኅበሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማካሔድ ዐውደ ርእዩ እንዲፈቀድ ጥረት እንደሚያደረግና ጊዜውና ቦታውንም እንደሚያሳውቅ ከዚህ በፊት ገልጦ እንደነበር አስታውሰው ውይይቱ ውጤታማ ሆኖ መፈቀዱ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት የራሱ የሆነ በጎ ጎን እንደሚኖረው አስገንዝበዋል፡፡

  ዐውደ ርእዩ ከታገደ በኋላ በቶሎ ለማሳየት ያልተቻለውም ኤግዚቢሽን ማእከል ዓመቱን ሙሉ የተያዘ በመሆኑ ቦታ ባለመገኘቱ እንደሆነ የገለጹት ዋና ጸሐፊው ከኤግዚቢሽን ማእከሉ ጋር ውይይት በማድረግ አመራጭ ቀናትን በማፈላለግ ማእከሉ ከፍተኛ ትብበር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

  የተካሔዱት ውይይቶች ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና ለኤግዚቢሽን ማእከል አቶ ተስፋዬ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

  ኤግዙቢሽን ማእከሉ ያሉትን መርሐ ግብሮች በማጣበብ ጥያቄያችንን በድጋሚ በመቀበል ዐውደ ርእዩ እንዲታይ ከፍተኛ ጥረት ያደረገ በመሆኑ ወደፊትም በሚደረገው ዝግጅት እስከመጨረሻው ትብብሩ አይለየንም ብለዋል፡፡

  ዐውደ ርእዩን ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ ምእመናን ይመለከቱታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከግንቦት 17- 22 ቀን 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

  ReplyDelete
 14. ኦ አምላክ!!! አንተ ናሁሰናይ የተሀድሶ ጭራ… የራስህ አልበቃ ብሎ የሌላውን ወጥ የምታማስል ተኩላ!!! በአዲስ አምባ ቅ/ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 09 የደብሩ አለቃ ከሰ/ት ቤት አባላት ጋር በመሞዳሞድ አባቶችን ሲያሰድቡ አልክ!!! እስቲ ምን ይጠቅምሀል የአባቶችን ቆብ ደፍተህ እንዲህ ርካሽ ቦታ ለመገኘት መራራጥ!!! በደብራችን ሰ/ት/ቤት አዳራሽ በቀኑ የነበረው መርሐ ግብር በሳሪስ አካባቢ ያሉ ወጣቶች በቅድስት ኪዳነ ምህረት ስም ተሰብስበው በወር በወር እየተሰበሰቡ ወንጌል የሚማሩበት፣አብያተ ክርስቲያናትን የሚደግበት ማህበር አላቸው፡፡ ይህን ማህበር ሰ/ት/ቤቱም ሆነ አንተ የምትለው ቀሲስ የሺጥላ የመሰረተው ሳይሆን ራሳቸውን አደራጅተው ለቤ/ክርስቲያን የሚገባንን እናድርግ፣ወንጌል እንማር ብለው ተሰበሰቡ ወጣቶች ናቸው!!! በቀኑም 10ኛ አመታቸውን ለማክበር በሰ/ት/ቤቱ አዳረሽ በዓላቸውን ወንጌል በመማር፣የንስሐ መዝሙር በመዘመር ነበር ያሳለፉት!!! የተሐድሶ ምንፍቅና ካልተሰበከ ወንጌል አልተሰበከም ለናንተ!!! ለቀቅ ደሞ አባታችንን…አባታችን መላከ ገነት በቀለ ዘውዴ…የወንጌል አርበኛ፣ያባቶቻቸውን ቀለም የሚያቁ ሊቅ እንጂ አንተ በአፍህ ልትጠራቸው እንኳን የማይገቡ ተወዳጅ አባታችን ናቸው!!! ባጠቃላይ ደብራችን ሰላማዊ፣ወንጌላዊት ደብር መሆኑአ አንገብግቦህ የተሀድሶ መርዝህን ከተባባሪዎችህ ጋር ለመጋት አልሆን ሲልህ የሀሰት አባትህን የዲያቢሎስን ስራ ይዘህ ብቅ አልክ….ጌታ ልቡና ይስጥህ…

  ReplyDelete
 15. "አባ ሰለማዎች" በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን ዘንድ የሚቀጥለው ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርቶስ ሰዎችን ከድያብሎስ ተገዥነት ለማዳን የተቀበለቀው መከራ የሚታሰብበት ነው፡፡
  እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ! ሰይጣንን ከመጸሐፍ ቅዱስ ሳትወጣ ስለ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናገር ወይም ጻፍ ቢባል ምን ሊናገር ወይም ሊጽፍ ይችላል? ሰይጣንን ሊናገር ወይም ሊጽፍ ከሚችለው አንፃር ራሳችሁን መርምሩ፡፡ ያን ጊዜ እውነት የት ነው ያለው የሚለውን ትረዳላችሁ፣ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና እውነተኛ አገልጋዮቿ ላይ የጥፋት፣ ውሻት፣ ማንም በገሀድ የሚያውቀውን በውሸት ቃል ለማጠልሸት የምትተጉለት ነገር ከየት እንደሚመነጭ ትረዱታላችሁ፡፡ እግዚአብሔር ንፁህ ልብ ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 16. enie yemigermegn andken ye egziabher kal sitastemru aytayim, enante yesidb blogoch bilenachuhal.kemtsdbut mahber wongel sisbk enji sisadeb semten anawkm.

  ReplyDelete