Sunday, April 24, 2016

ይድረስ ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና ለኢትዮጲያ ሊቃነ ጳጳሳት!


Read in PDF

ከዲያቆን አናኒ
      ይህን ደብዳቤ የምጽፍልዎ በቅዱስ መጽሐፍ “የሕዝብን አለቃ አክብረው ፤ ተገዛለትም” የሚለውን አምላካዊ ቃል በማሰብና የአገራችንን የአክብሮት ትውፊት ከልቤ እያመላለስኩ ፍጹም ዝግ ባለ መንፈስ ውስጥ እርሶንና ሊቃነ ጳጳሳቱን በክርስቶስ እንደ አባት በማሰብ ስለአንዲት ቤተ ክርስቲያን የተጨነቅሁባትንና ከሁሉ ይልቅ ታላቅ የሆነች መልዕክት በልጅነት አንደበት እንዲህ ልልክልዎ ወደድሁ፡፡
    ብጹዕ አባታችንና ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ከመቼውም ጊዜ በላይ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የምዕመናን ፍልሰት እጅግ ያሳሰበን ጊዜ ላይ እንዳለን በተደጋጋሚ ሲያነሱ ሰምተናል ፤ እውነታውንም እኛም አስተውለናል፡፡ ለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ “ታላላቅ” ከተባሉቱ ዘንድ ሳይቀር የተለያዩ አስተያየቶችና ከቃለ ወንጌሉ ጋር የማይዛመዱ ግምታዊ የሆኑ መላምቶች  ሲሰጡ እስኪሰለቸን ሰምተናል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት አስተያየቶችና መፍትሔ ተብለው የቀረቡት ግምቶች ፍልሰቱን ከመግታት ይልቅ አባሱት ፤ ይልቁን እንዲጨምር ያደረጉት ይመስላል፡፡

     ትላንት ሙሉ መንደሩና ከተማው ኦርቶዶክስ የነበረበት ሥፍራ ዛሬ በብዙ ቤተ ሃይማኖት የተወረሰ መሆኑንና እንዲያውም በዚሁ ከቀጠለ፥ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴዎስ እንደተናገሩት “ኦርቶዶክሳዊነት በሰሜን ብቻ ተወስኖ ሊቀር እንደሚችል” ከፍ ያለ ሥጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ አዎን አባታችን! ስጋቱ ግን ሥጋት ብቻ ሆኖ እንዲቀር ሁላችን አንፈልግም፡፡  ሁለት ጥያቄዎችን በልጅነት መንፈስ ለውይይት ማንሳት እፈልጋለሁ፥ ይኸውም፦
1.      ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለምን ይፈልሳሉ? የሚለውንና፥
2.     ከኦርቶዶክሰዊት ቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሲፈልሱ በብዛት ወደየትኛውም የሃይማኖት ተቋም ይሄዳሉ? ሚለውን ደጋግሜ ለራሴ በማንሳት አሰላስያለሁ ፤ ብዙዎችንም በዚህ ዙርያ ጠይቄያለሁ፡፡
    አንደኛውን ጥያቄ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መጠየቃቸውንና፥ “ሰዎች የሚፈልሱት ወንጌል ፍለጋ ነው፥ ባሏቸው ጊዜ ታዲያ ወንጌሉን ለእነርሱ እንዲገባና እንዲመጥን አድርጋችሁ ስጧቸው እንጂ” (በትክክል ካልጻፍኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ) ብለው መመለሳቸውን ሰምቼ ነበር፡፡ በእርግጥ ሰዎች በብዛት የሚፈልሱባቸውን የሃይማኖት ተቋማት ካስተዋልን የመጀመርያውን ጥያቄ ለመመለስ ይረዳናል፡፡
    ከተወሰነ አሥርት ዓመታት በፊት በመቶ ሺህዎች የነበረው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኝ ብዛት በአሁን ሰዓት ከአሥር ሚሊዮናት መካከል መሆኑን ስንሰማ ከአሥር ሚሊዮናት በላይ የሆኑት አማኞቻችን በአብዛኛው ወዴት እንደነጎዱ ማስተዋል ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ወደወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለምን እንደሄዱ በተለያየ ዘመን ይሰጥ የነበረው ምክንያት በአብዛኛው አሳፋሪ ነው ብንል ግነት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ስንፍናችንን አጉልቶታል ፤ ለሚፈጠረው ችግርና ፍልሰት ምክንያታዊ የሆነ ከወንጌል የተቀዳ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ አስታበየን እንጂ የሚፈልሰውን ምዕመን ቁጥር ዛሬም እንኳ አልገታነውም፡፡

     አባታችንና ኦርቶዶክሳውያን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ከእኛ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ምዕመናን ለመፍለሳቸው ምክንያቱ አንድና አንድ፥ እናንተም እንደተናገራችሁት የኢየሱስ ወንጌል ልቆና ገኖ አለመሰበኩ ነው፡፡ ብዙዎች ይህን እውነት በመሸሽ የቤታችንን ችግር የአስተዳደርና የቀኖና ብቻ አድርገው ያቀርቡታል፡፡  እውነት ለመነጋገር ግን ብዙ ነገራችን አደባባይ ላይ የተሰጣው ፤ ዘፋኙም ፣ ሰካራሙም ፣ ጠንቋዩም ፣ ሙሰኛውም ፣ ታቦት ሰርቆ ሻጭ ሌባውም ፣ አጭበርባሪ ነጋዴውም ፣ ሴሰኛውና አመንዝራውም ... በታወቀ ነውር ተይዞ ሳለ ኦርቶዶክስ ነኝ እያለ እውነተኞችን ሲያሳድድ የኖረው የሕይወቱን ሚዛን ከኢየሱስ ወንጌል አውርዶ በሰው ትምህርት ላይ ስለመሠረተ ነው፡፡
    የዛሬው ኦርቶዶክሳዊ መልክ ከላይ የተጠቀሰውንና ሌላውንም ሁሉ አይደለም፡፡ የትምህርታችንና የሕይወታችን መርሕ ከቅዱስ ወንጌሉ ቢቀዳም ፤ እጅግ በጣም ተበርዟል፡፡ አውደ ነገሥትን የመሳሰሉ የጥንቆላ መጻሕፍትና ሌሎች አደገኛ የኑፋቄና ከወንጌሉ ጋር ምንም ስምምነት የሌላቸው መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያኒቱ ስምና አርማ ሲታተሙ ማንም ምንም አላላቸውም ፤ አስተዳደራችን በዘረኝነትና በሙስና የተተበተበው ፣ የብዙ ቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች የግል ሕይወታቸው በኃጢአት የተጨመላለቀውና የአደባባይ ገመና የሆነው ከወንጌሉ ሙሉ ለሙሉ ፍቺ ስለፈጸመ ነው፡፡ ይህ ግን ቶሎ መፍትሔ ካላገኘ ውጤቱ ፈጽሞ መራራ ሊሆን ይችላል፡፡
   እስኪ አንድ ምሳሌ ላንሳ፦ “መነኩሴው” ማርቲን ሉተር በሮማ ካቶሊክ የነበረውን ልማዳዊ ትምህርት ወደወንጌል እውነት ለመመለስ ሲነሳ፥ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም በእልህ ፕሮቴስታንትን የሚቃወሙና “የሚሰብኩ ማኅበረ ጀስዊትን መሠረተች”፡፡ ማርቲን ሉተርን ለመቃወም የተመሠረተው ማኅበር ቅንነት የጎደለው ቢሆንም ሳያስቡት ግን ላቲን አሜሪካ ድረስ አብያተ ክርስቲያኖቻቸውን እስከማስፋትና ሥፍራ እስከማግኘት ደረሱ፡፡ ይህ ሥራቸው ግን ለመሥራት አስበው ያደረጉት ሳይሆን ለተነሳባቸው “ሉተራዊ አስተምኅሮ” ምላሽ ለመስጠት በተነሱበት ጊዜ ነው፡፡ እውነት ለመናገር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሉተርን ከመቃወም በፊት አስባ ፤ ተልማ ቀድማ ሠርታ ቢሆን ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመከፈል አድና ብዙ ነፍሳትንም ማትረፍ በቻለች ነበር፡፡
   ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን! ከዚህ ታሪክ መማር እንዳለብን ይሠማኛል፡፡ ዛሬ ኦርቶዶክሳዊውን ተሃድሶ ለመቃወም የተነሳ አንድ ሌላ ቡድን “ኢየሱስን እሰብካለሁ” ብሎ ተነስቷል፡፡ ነገር ግን ለሠላሳ ዓመታት ያህል ሠርተው ምንም እንዳላመጡ ፤ የምዕመናኑን ፍልሰት ፈጽመው ሊገቱ እንዳልቻሉ እኛም እናንተም የሚያየው ሁሉ ምስክር ነው፡፡ ይልቁን ቤተ ክርስቲያንን በማወክ ፤ በመረበሽ ሥራ ተጠመዱ እንጂ፡፡ የተለያየ ትርጉም እንስጠው እንጂ ቤተ ክርስቲያን ጭምር በአንደበቷ ኦርቶዶክሳዊ ተሃድሶ እንደሚያስፈልግ አምናበታለች ፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ ተሃድሶው የግድ ነው በሚሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምርጥ ልጆች ላይ፥ እንደካቶሊካዊው ያለው “ጀስዊታዊው ቡድን” ስደት ፣ ጥላቻ ፣ ስም ማጥፋት ፣ ዛቻ ፣ ከባድ ተቃውሞ በግልጥ አስነስቷል፡፡ እንደእኔ አመለካከት ይህ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እጅግ ከባድ አደጋ ነው፡፡ ምክንያቱም ኦርቶክሳዊ ተሃድሶ ያስፈልገናል የሚሉ ውድ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተነሳው ተቃውሞ በሚገባ ተጠንቶ መንፈስ ቅዱሳዊ መፍትሔ ካልተበጀለት ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት ሊከፍላት ይችላልና፡፡ እኔን ጨምሮ ኦርቶክሳዊ ተሃድሶ ያስፈልገናል የምንል ፈጽሞ ቤተ ክርስቲያናችን እንድትከፈል አንሻም ፤ አዎ! ኦርቶዶክሳዊው አንድነታችን እንዲነካብን አንሻም፡፡ ይህ የሁልጊዜም አቋማችን ነው፡፡
      ሌላ ምሳሌ ልጨምር ፦ በአገራችን ኢትዮጲያ በደቡቡ ፣ በምዕራቡ ፣ አልፎ አልፎ በመካከለኛው ክፍልና አንዳንድ በምሥራቁ ክፍል ያሉት አብዛኛው አማኞቻችን ወደፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የፈለሱት ወንጌልን ፍለጋ እንደሆነ ከማመን በቀር ምንም አመክንዮታዊ መከራከርያ ማንሳት አንችልም፡፡ አሁን ግን ታሪክ ሊያስተምረን ይገባል፡፡ ኦርቶዶክሰዊው ተሃድሶ እጅግ በበሰለ አዕምሮ እንዲጤን ፤ እንዲታሰብበት እንሻለን ፤ ይህን የምንለው ፍልሰቱ እንዲቆም ፤ ምዕመናን ወደፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ከመሄድ ይልቅ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ እንዲቀሩ ከመሻት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ከማጠንከሩ ባሻገር ጥራት ያላቸውን አማኞች ለማፍራት መንፈሳዊ መሠረት ይሆነናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ሲሆን ማንም የማያቆመን የአፍሪካና የምድር ሁሉ ሕያዋን የወንጌል ምስክር ከመሆን ማንም አይመልሰንም፡፡
    የኢየሱስ ወንጌል ቢሰበክ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እጆቻቸውን ዘርግተው በእንባ ወደ“እናት ቤታቸው” የማይመለሱበት ምንም ምክንያት የለም ፤ ደግሜ እላለሁ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የኢየሱስ ወንጌልን በትክክል ብትሰብክ ያለምንም ጥርጥር ምዕመናን ምንም የሚፈልሱበት ምክንያት የላቸውም፡፡ ሕዝባችን በቀደሙት ዘመናትና አሁንም ፍጡር እስከማምለክና የጠንቋይ እግር እጣቢ እስከመጠጣት የደረሰው የአምልኮ ጥማትና የወንጌሉን እውነት በትክክል ካለመረዳት የተነሳ ነው፡፡
  ወንጌል የሁሉ ነገር መሠረትና የአዲስ ነገር ሁሉ ጅማሬ ነው፡፡ በወንጌል ሕይወት አርፋጅ የለም፡፡ እግዚአብሔር የእንደገና አምላክ ነውና ዛሬም ገለል ያደረግነውን ወይም የጣልነውን ወንጌል ንስሐ በመግባት በአዲስ ኃይልና መንፈስ ብናነሳው አይረፍድብንም ፤ አልረፈደብንም፡፡ አባታችንና ኦርቶዶክሳውያን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ለብዙ ወንድሞቻችን ፤ እህቶቻችን ፤ እናቶቻችንና አባቶቻችን መፍለስ ምክንያቱ ወንጌሉን ፍጹም አለመግለጣችን እንደሆነው ሁሉ፥ የትንሣኤውና የአዲስ ነፍሳት መጨመርና መመለስም ምክንያቱ የቅዱስ ወንጌል ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መሰበክን ነውና እባክዎ! በዚህ እውነት ላይ እንስማማና ወንጌሉን አድምቀን እንስበከው ፤ እናውጀው፡፡      

41 comments:

 1. ዲያቆን፤ ይህንን ሁሉ ከመዘብዘብህ በፊት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወንጌልን እንዴት ነው የምተሰብከው፣ እንዴትስ ስትሰብክ ኖረች፣ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፣ የነገረ ድህነት ምስጢሩ የት ጋ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለጌታችን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርቶስ ምን ያስተምራል፣ የሚለውን በሚገባ ተረዳ፡፡ በኔ እምነት እንተ እና ብጤዎችህ ነገረ ድህነትን በሚገባ ባለማወቅ እና የኦርቶዶስ ተዋህዶን አስተምሮ ባለማወቅ የተነሳ ምዕመናን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ሌሎች በየዕለቱ ከሚወለዱ እብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት ለይተው ሊረዱ በሚችበት ደረጃ ባለማስተማራችሁ ምዕመናን ሊሄዱ ችለዋል፡፡ ሌላው ሰዎች ለሥጋ ተገዥ የመሆን ሁኔታ እየሰፋ መሄድ ነው፣ ይህም አባቶች በፆምና በጸሎት ፀንተው ያስተምሩ የነበረበት ጊዜ አልፎ ዛሬ ራሱን ለመንፈሳዊ ሕይተው ሳያስገዛ እንደ ባለ ዛር በድፍረት ወንጌሉን እየጮኸ የሚሰብክ በመብዛቱ እና አረያ የሚሆን እየቀነሰ በመምጣቱ ነው፣ አንተ ለምዕምናን መፍለስ የምትጨነቀ ከሆነ ወደ ሌሎች ለማቀራረብ ከመትጋት ይልቅ የኦርቶዶክስን ነገረ ትምህርት በሚገባ እወቅና ልዩነቱን አስረዳቸው፣ ምዕመኑ ልዩነቱን ካወቅ ወደ እናት ቤተክርስቲያኑ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ በእውነት የምትቀና ከሆነ ጣትህን ወደ ሌላ መቀሰርህን እና መቀላቀልህ ትተህ እውነተኛ የመዳን ትምህርትን፣ መጽሐፍ ቅዱስን ጌታን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ጭምር ለዚያውም ከባለቤቱ እንደተማረ ነገር ግን ለድህነት እንዳልተቀበለ፣ በአምላክ ሰው መሆኑ የተሰናከሉ ሰዎች የተናገሩትን ቃል መርጠህ እንደ አውነተኛ የመዳን ትምህርት በመውሰድ ምዕመናን ከማደናገር በመቆጠብ አውነቱን ለተከታዮችን አሳውቅ፣ ያን ጊዜ በመጸጸት ይመለሳሉ፡፡ የቤቱ ቅናት ካቃጠለህ አሁን አውነቱን ወደ መገንዘብ የምትመጣበት ደረጃ ላይ እየደረስክ ስለሆነ ዓለም ይድን ዘነድ ምን ላድርግ ብለህ፣ ሰሞነ ሕመማትን በጨመለማ ውስጥ የነበርንበትን ጊዜ እያሰብክ ጌታ ለሰው ልጆች የዋለውን ውለታ በማሰብ ራስህን ምርምር፡፡ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 2. እውነት ነው የባረከህ ይባረክ ብዙ እህትና ወንድሞቻችን ወደሌላ ቤተ እምነት ለምን ይሄዳሉ ሲባል ድክመትን ላለመቀበል ብዙ ምክንያት ይነሳሉ like ለገንዘብ ነው ለስንዴ .... ሀብታም ሆኖ እኮ የሚወጡ አሉ ቤተክርስትያን ግዴታ አለባት ለሚወጣው ምመን ማነው ተጠያቂው? ለምን ስለነሱ ግድ አይላትም? 1ድ ሰው መውጣት እኮ ምን ያህል ያሳዝናል አንድ ምስክርነት አለኝ በምማርበት ጊቢ ውስጥ ኦርቶዶክስ አንድ እህት ወደ ፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ገባች ያገኘዋት ዘግይቼ ነው ጎደኞቻችን ስሞአን አብጠልጥለው ጨርሰው የስድብ ጋጋታን አውርደው መናፍቅ .... ይሉአታል የማቅ አባል አንዱ ወንድማችን ላናግርሽ ብሎ እንደጠራትና የስድብ መአት እንዳወረደባት ነግራኝ ነበር እኔም ለምን ወደዛ እንደሄደች እንደቀልድ ስጠይቃት በወንጌል ለማረፍ እንደሆነ ኦርቶዶስ ውስጥ ያለው አምልኮ ድብልቅልቅ ያለ መሆኑን መርጨ እንኮን እንዳልሰማ "ሁሉን በጊዜው ዉብ አርጎ ሰራው አምላክን ለወለደች ምስጋና ይገባል" ይባላል የሰራው እሱ የሚመሰገነው ሌላ ምነው እሱን ብናመሰግንበት በመጨረሻም ብዙ ካወራን በሆላ የቀደሙት አባቶች ምን ይሉ እንደ ነበር የኑፋቄው ትምህርት ሲቆይ እውነት መስሎ እንደተቀመጠ ኢየሱስን ማወቅ የተቆም ለውጥ ማድረግ አለመሆኑን ባለችበት ቤተ እምነት ውስጥ ሆላ ማምለክ እንደምችል ተማምነን መፅሀፍ ላይ መወያየት ጀመርን ተመልሳም መጣች ችግሩ ደም ፕሮቴስታንት ስትሆን የሰደብአት አሁን ከበፊቱ አይለው የስድብ የግልምጫ ዶፋቸውን ያዘንባሉ ቆይ ስትሄድ ሄደች ስትመጣ ለምን መጣች አያስመስልም የቱ ጋር ነው ለቤተክርስትያን መቆርቆር? ምመን እያስወጡ እየገፋ ነው ቤተክርስትያንን ማገልገል? ድንቄም አለው ባይነት ቤተክርስትያን ያለምመን ምንድናት? ሰው ሁሉ ወቶ ካለቀ ጌታ ልብ ይስጠን ምክንያት ከመደርደር ተኝቶ ከማለም ከማሳደድ የበለጠ ጠላትነት የለም እያየን እንዳላየን መአት የወጡ እስኪደንቀን ላለማመን መጣር ጅልነት ነው ይልቅ መፍትሄ ሊበጅ ያስፈልጋል አንድ ሰው በግሌ እንዲወጣ አልፈልግም የወጡትም እንዲመለሱ የእውነትን ወንጌል ይሰበክ እራሱ ወንጌል ያሸንፋልና<! ኢየሱስ ጌታ ነው አሜን አሜን

  ReplyDelete
 3. ሲጀመር ቤተከርስትያንን ጭራሽ ወንጌል እንዳልሰበከች መግለጽህ ትክክል አለመሆኑን ልገልፅል እወዳለሁ፡፡ ሲቀጥል አሁንም ቢሆን ቤተክርስትያን እንዳንተ ያለውን የናት ጡት ነካሽ ቢቻል በቀኖና መመለስ ካልተችለ ደግሞ በውግዘት አሰናብታ ራስዋን ማፅዳት አለባት፡፡ ባንተ ቤት አባቶቻችንን ያከበርክ መስለህ መዘርጠጥህ ነው፡፡ በነዳንኤል ክብረት እውነታው ሲነገር አባቶችን አዋረደ ምናምን እያላችሁ ትጮ ሃላችሁ እናንተ ግን አባቶችን ወንጌል መስበክ አልቻላችሁም ብላችሁ ስትከሱ ምርቃት ይመስላችኃል፡፡ ለማንኛውም ማስተዋሉን ይስጣችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አልሰሜን ግባ በለው

   Delete
 4. ጥሩ ሞክረሀል፤ግን አልተሳካልህም፡፡የደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ ለፕሮቴስታንቶች (ወንጌላውያን ማለቱን እርሳውና) መጋለጥ ከጣሊያን ወረራ በኋላ በነበረረው አገርን መልሶ የማቋቋም እንቅስቃሴ እገዛ እንዲያደርጉ የገቡ ሚሲዮናውያን ሕዝቡን ያለማንም ተቀናቃኝ ስላገኙት ነው፡፡በአብዛኛው ኦርቶዶክስ የነበረ ሳይሆን የባሕላዊ እምነት ተከታይ ነበር፡፡ደርግ ሲመጣ ሁሉንም ሃይማኖት ደመሰሰ፡፡ኢህአዴግ ሲመጣ መድረኩ ለውድድር ክፍት ሆነ፤የወጡት ሚሲዮናውያን በኤንጂኦ ሥም ተመልሰው ገቡ፡፡ኦርቶዶክስንና ነፍጠኝነትን ሆን ብለው አመሳስለው በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ ሰበኩ፡፡ለፌ ወለፌ የሆኑና በሥማ ተሐድሶ በግብር ፕሮቴስታንት የሆኑ ገላግልት ወገበ ነጭ ቀሳውስትን መልምለው በሰሜን በኩል ሞከሩ፡፡በሰሜን የተካሄደው ሙከራ ከምዕራቡና ደቡብ በተለየ ነው፡፡ምክንያቱም ሰሜን ሄደህ ነፍጠኛ ሃይማኖት ብትል ስለማያዋጣ ትውፊቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እነሱን ተረታተረት እያልክ ሸማውን አስጥለህና አገራዊና ብሔራዊ ማንነቱን ጭምር ከትውፊቱ ጋር ኋላቀር ስትል ነድፎ አባረረህ፡፡
  የወንጌላውያን ተብዬዎች ቁጥር አንድ ኢላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናት፡፡ኤንጂኦው፣ፖለቲከኛው፣ብሄርተኛው፣ሙስሊሙ፣ጴንጤው፣ፓጋኑ ሁሉ ያለፈው ዘመኑን ድክመት በቤተክርስቲያኗ ላይ ለማወራረድ እንቅልፍ የለውም፡፡ሕማሙን፣ስቅለቱን፣ትንሣኤውን በብሔራዊ ደረጃ የምትዘክረውንና የጌታና ሥጋና ደም ያልበላ እግዚአብሄርን መንግሥት አይወርስም በምትል ከሺህ በላይ ያለማንም ረዳት በምሥራቅ አፍሪካ መከራዋን ስታይ ለኖረች ቤተክርስቲያን መዳከም ድንጋይ ያልወረወረ የለም፡፡ብዙ ነውረኛ ንግግር ሰምተናል፡፡ቤተክርስቲያኗ የተረት ቤት እንደሆነች ለማስመሰል በቤቷ ፍርፋሪ ቀምሰው ያደጉት ርኁባን ተሐድሶ ነን ባይ ወገበ ነጮች የሚሉትን ስንሰማ ኖረናል፡፡ወንጌል ተሰበከባቸው፣ሉተር በተሐድሶ አደሳቸው፣የበራላቸው እየተባሉ የሚወደሱት የተሐድሶዎች አያት የፕሮቴስታንቶች ወላጅ የሆኑ ምዕራባውያን አገራት ያሉበትና ዘቀጡበት የሞራል ደረጃ ምን ላይ እንደሆነ እያየነው ነው፡፡በአገራችን የሚንፈላሰሱ የውጭ ፓስተሮች ቀን ትንቢትና ኮንፈንስ ሲሉ ውለው ማታ በየሆቴሉ ጠያይም ቆነጃጅትን ሲያሞናድሉ ነው የምናያቸው፡፡የነተከስተና የነፓስተር ዳዊት ዝቅጠት በገሀድ የሚታይ ነው፡፡
  የወንጀል ሪከርድ ማነጻጸር ካስፈለገ የፈለጋችሁትን ፕሮቴስታንት የበዛበት የደቡብ ከተማ የወንጀል ሪከርድ ከአክሱም ወይም ከላሊበላ ጋር አነጻጽሩና አስገርሙን፡፡ከሰማኒያ በመቶ በላይ ነዋሪዎቿ ኦርቶዶክሳውያን በሆኑባት አዲስ አበባ ያለውን ሪከርድ ወስደህ ጠቅላላውን ሃይማኖት መበየን ጥሬ መሆን ነው፡፡ዐይንህ በፕሮቴስታንታዊ የፈንድ ሳሙና ስለታጠበ ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት በጎ ተግባር አይታይህም፡፡የቤተክርስቲያኗ ልጆችና ቤተክርስቲያኗ ያለማንም ውጫዊ እርዳታ ባገር ልጆች ብቻ ተደግፈው መቆማቸው ላንተ ኋላቀርነት ነው፡፡እኛ 50ሺህ ቤተክርስቲየሣን ቢኖረን መቶ በመቶ ባገር ልጆች የላብ ውጤትና አስራት የተገኘ ነው፡፡በፈንድ እስክንፈነዳ በፓስተርነት ሥም ኢንተርፕርነርሺፕ እና የውጭ ተመጽዋችነት አላስፋፋንም፡፡
  ወንጌል ወንጌል ትላላችሁ፡፡በለፈለፈ አይደለም፡፡አብያተ ክርስቲያናቷ የነግህና የሠርክ ጉባኤያት ምን እየተሰበከባቸው እንደሆነ ማንም ማየት ይችላል፡፡የመምህራኑ ሥም በራሱ ሰባኬ ወንጌል ነው፡፡ማዕረጋቸውም መጋቤ ሐዲስና መጋቤ ብሉይ ነው፡፡ከድሮ ጀምሮ ልጆች ፊደል ሲቆጥሩ የዮሐንስ መጀመሪያ መልእክት የሆነውን መልእክት ዮሐንስና ኋላም የዮሐኝስ ወንጌል፣ቀጥሎም መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ቅዳሴው፣ሃይማኖተ አበው፣ድጓው፣ጾመድጓው ስለክርስቶስ አንስቶ አይጠግብም፡፡ይሄን ሳያጣሩ በአቋራጭና በትውውቅ ዲቁና እየተቀበሉ ልባቸው በተሐድሶ ምውት ቀረርቶ ያበጠ ንዑሳን ዲያቆናት ግን በየብሎጉ እየተሸለከለኩ ጎበዝ ለመባል ኦርቶዶክሳዊ የሆነን ነገር ሁሉ ‹‹ተረት›› እያሉ ቀጣሪዎቻቸውን ለማስደሰት ይደክማሉ፡፡ቀጣሪዎቻችሁ የመጡበት ሀገር እንዲሁ በወንጌል ሲምልና ሲገዘት ኖሮ ዛሬ ቸርቾቹን ወደ ሙዚየምነት ቀይሮ በአደባባይ ወንድና ወንድ ያልሞሸረ ሁሉ የተረታተረት አገር ነው ማለት ጀምሯል፡፡ከየት ጀምሮ ወዴት እንደሆነ መዳረሻው የመይታወቅ ቃልን ‹‹ተሐድሶ›› እያሉ መለፋደድ ትርፉ ይኸው ነው፡፡የክርስቶስ ቤዛነት አንድ ጊዜ ነው፡፡ሃይማኖት፣ጥምቀት፣ጌታ ሁሉም አንድ ናቸው፡፡አይታደሱም፤አይከለሱም፡፡ራሳህን በንስሐ አጥበህ መታደስ ሲያቅትህ እዚህና እዚያ እያሉ መንቦጫረቅ ፍጻሜው የምዕራባውያን ማኅበራዊ ቀውስና በስተመጨረሻም ባዶነትና እምነት አልባነት ነው፡፡በፕሮቴስታንት እምነት ተመርቶ የሞራል ተምሳሌት ሊሰኝ የሚችል ማኅበረሰብ የገነባ አገር የለም፡፡በእኛ አገር መጀመሪያ አካባቢ ለመምሰልና ለመመሳሰል ፕሮቴስታንቶች በየፌርማታው ሲቅለሰለሱ ቢታዩም ኋላ ግማሹ በኒኬል ውስኪ የሚጨልጥ፣ግማሹ በትንቢትና ልሳን የሚያምታታ፣ግማሹ ልጃገረዶችንና ባለትዳሮችን የሚያማግጥ ነው የሆነው፡፡ በሙስናውም ቢሆን ፕሮቴስታንት ባለሥልጣናት ከቁራቸው በላይ የተዘፈቁ ናቸው፡፡በሙስና ከሰሜኑ ሕዝብ በላይ የሚታማው ፕሮቴስታንት ይበዛበታል የሚባለው ክፍል ነው፡፡እነታምራት ላይኔ፣አባዱላ ገመዳ፣ያረጋል አይሸሹም በሕዝብ ንበረት የተጨማለቁ ጴንጤዎች ናቸው፡፡ንዑሱና ወገበ ነጩ ዲያቆን በየብሎጉ ከመለፋደድ ራስህን ዝቅ አድርገህ ቢያንስ የማታ ጉባኤ ተማር፡፡ላሁኑ አልተሳካልህም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔር ይስጥህ የልቤን ነው የተናገርክልኝ!!! ምድረ መናፍቅ ወንጀል እንጂ ወንጌል የማያውቁ፣ሆዳቸው አምላካቸው፣ክብራቸው በነውራቸው የሆነላቸው ርትዕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያንን ለማጥፋት ደጅ የሚጠኑ 'በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ አሉ ወንጌል ወንጌል: በማለት ጌታ ጌታ በማለት አይደለም" ማቴ 7፣21 "ጌታ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም"

   Delete

  2. ደካማ አተያይ ማለት ይህ ነው፡፡ እኔ የትኛውም ሃይማኖት እንዲሰደብ አልሻም ፤ ድንጋይ የሚያመልኩትን ቢሆን እንኳ፡፡ ግን እንደመጽሐፍ ቅዱስ በሙያዊ ቋንቋ ቢተች ደስተኛ ነኝ፡፡ ዛሬም ለምን ደካማ ጎናችንን እንደምንሸፋፍን አይገባኝም፡፡ እኔ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነኝ፡፡ እንዳንተ ግን ግትርና ግብዝ አይደለሁም፡፡ የፕሮቴስታንትን ሃይማኖት የሰይጣን ቁርጭ አድርገን ብዙ ከምናወራ (በማያገባን ገብተን ከምንፈተፍት) የእኛ ቤት ምን ይመስላል? አንተ በጣም የተኩራራህበት ሰሜን መልኩ ምን ይመስላል? እውነት ከሁሉ የተሻለ ነው? ጥንቁልና ፣ ሥራውና ከነትምህርቱ የት ነው ያለው? ንጹሐን ቀሳውስትና መሪጌቶች የሚፈልቁበትን ያህል ጠንቋዩ ፣ መስተፋቅር አሳሪው ፣ ደጋሚው ፣ ሰብስቤው ፣ አዶ ከበሬው ፣ አሻራ አንባቢው ፣ ዓውደ ነገስት ፈቺው ፣ አብሾ አጠጪውና ጠጪው ፣ … ከየት ነው የመጣው(የሚመጣው) ቄስና መሪ ጌታው ከሰሜን አይደለም? ዛሬም ድረስ ገድሎ ፎካሪው ፣ ደመኛን ቆጥሮ ተበቃዩ ፣ የሰኞ የማክሰኞ ገዳይ ነኝ ባዩ ፣ ከሌላ ብሔር ጋር መጋባትን እንደርኩስ ቆጣሪው ፣ ከቤተ እስራኤል ጋር ራሱን ቆጥሮ ሌላውንብሔር በንቀት ገላማጩ ማን ነው? … የሰሜን ሰው ብዙ ምርጥ ያሉትን ያህል ብዙ እጅግ ብዙ አስነዋሪም አሉት፡፡ ይልቅ ራስን ማየቱ ጥሩ አይመስልህም? እናውራ ከተባለ ብዙ የምንለው አለን፡፡ ግን አይረባንም፡፡ ደቡቡንስ ቢሆን ምነው ገድለ ሃይማኖቱ የተክለ ሃይማኖት አገር ፤ ሐዋርያዊ ሥራ የሠራበት እያለስ የሚያነሳው አይደለም? እኔ ኦርቶዶክስ እንደመሆኔ ኦርቶዶክስን በዘመን ሁሉ ያልተሳሳተች ብዬ አልቀበልም፡፡ ስንት ጉድ የተሸከምን መሰለህ፡፡ እኛ ብንደብቀው አሁን ታግሶ የማያልፈው ትውልድ መጥቶብናል፡፡ ይልቅ ቤታችንን ማስተካከል ያለብን እኛ መሰለኝ፡፡
   አንተና ብዙ ሰዎች ስለፓስተሮች ብዙ ብላችኋል፡፡ ስለጥቁሩ ቆብ (መነኩሴም በለው ቄስም በለው) ባለሃብቶችስ ምነው ዝም አልክ? አየህ እዚህም ቤት ሆነ እዛም ቤት እሳት መኖሩን መካካድ አይረባንም፡፡ ሁላችን እጅ ሰጥተን ንስሐ መግባቱንና መሸነፉን በአምላክ እጅ መውደቁን ብንመርጥ እጅግ ይሻለናል፡፡ (ከዚህ ጽሁፍ በኋላ ስድብ ብጠብቅ አልደነቅም፡፡)

   Delete
  3. እራሰእህን አኔ ኦርቶዶክስ ነኝ በማለት የዋሃንን ለማደናገር ከሆነ በጣም ታሳዝናለህ ብቻ ሳይሆን በጣም ተሳስተሃል ለምን መሰለህ ንቁ ስለሚል እንኳን ያንተን የተንሻፈፈ አካሄድ ቀርቶ ሌላም ይታወቃልና አትልፋ ??????????

   Delete
  4. ንቃ ወንድም ተረት እየተቻወተብህ ነው በግብዝነት የዘላለም ህይወትህን ለሞት አጋብዛት ወንጌል ተረት ለሆነብህ እና ተረት ወንጌል ለሆነብህ ንቃ ንቃ ንቃ የተሰቀለውን እየው በሱ ከታመንክ አታፍርም አምላክ ለፈጠረው ለእጆቹ ስራ ቃሉ ታማኝ ነውና

   Delete
 5. አሳቢ መሰይ ሓሳዊ ላላወቀህ ታጠን አዛኝ ቅቤ አንጓአች ምናለ እራስእን ገልጠህ ብትቃወም ደግሞ ለቀባሪው አረዱት አይሆንብህም ከኦርቶዶክስ በላይ ወንጌሉን በቃልም ሆነ በተግባር የሚያስተምር አለ?? በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ሁሉ እኮ የሚሰብከው እግዚአብሔርን ነው ታዲያ ምንታደርግ እናንተ የገላትያ ሰዎች ክርስቶስ በፊታችሁ እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሏል ይህን እንዳታስተውሉ ማን አዚም አደረገባችሁ?? ይላልና አልፈረድባችሁም እናንተም በግበረሰዶማዊነት የሚገኝ ገንዘብ አዚም አድረጎባችሃል ለምን የምትናፈቁት የፐሮቴስታነቱን አለም ስለሆነ እነሱን መሆን ስለምትፈልጉ ልብ ይስጣችሁ ዛሬ እኮ የፕሮቴስታንቱ አለም ሰባኪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው ግበረሰዶማዊነት በየምለሀገራቸው ህግ እንዲጸድቅላቸው ታግለው አታገሉ ተሳካላቸው ተጋቡ እናም አንተና መሰሎችህም ለዚሁ ትደክማላችሁ፡፡ ሌላው የፕሮቴስታንቱ አለም የሚስብከው የጌቶችጌታ የአማልክት አምላክ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው እናንተ ፕሮቴስታንተአውያን የምትሰብኩት ግን በመጨረሻው ሰዓት ክርስቶስ ነኝ ብሎ የሚነሳውን የአውሬወን መንፈስነው በደንብ አንተና መሰሎችህ ታውቁታላችሁ ለዚህም
  እኛ ኢየሱስ ስንል መድሐኒት
  ›› ›› የጌቶች ጌታ
  ›› ›› የአማልክት አምላክ
  ›› ›› የዘላለም አባት
  ›› ›› የሰላም አለቃ
  ›› ›› ሁሉ በእርሱ የሆነ ብለን ነው ለእናንተ ልብ ይስጣችሁ ከማለት የተለየ ምንም አይባልም ለምን በዳያቢሎስ ቁራኝነት ስለታሰራችሁ ሰላም ሳይሆን ሁከትን ፡ ህይወትን ሳይሆን ሞትን የሰውልጅ እንዲወርስ ስለምትሰሩ የዲያቢሎስ መልክተኞች ውሎአችሁ ጭፈራ ቤት ለስሙ ቸርች ትላላችሁ ጭፈራና ዳንኪራ ከሞላበት ጎሬኣችሁ ሆናችሁ ዲያቢሎስ ለከፈላችሁ የሰውን ደም ለማፍሰስ ስለተዘጋጃችሁ ልብ ይስጣችሁ; እኛግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን

  ReplyDelete
  Replies

  1. ኛግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ?????????????

   እኛ ግን ተረትና ኑፋቄ እንጅ ክርሰቶስን በቃልና በተግባር ስትሰበኩ አልሰማንም፡፡እንዲያወም ክርሰቶስን የሰበከ ፤መናፍቅ፡ ታሀድሶ ጴነጤ..የሚል ስም አየተለጠፈበት አይደለም እንዴ ከፍ ብለህ ካንገቱ ዝቅ ብለህ ከቁርጭምጭቱ ቁረጥ እያላቸሁ ከፍቀር ይልቅ ያባታችሁ የዲያቢሎስ የሆነውን መግደልና ማረድ የምታደርጉ????

   Delete
  2. ያንተ አይገርመኝም ምክንያቱም ልክ እንዳንተው ዲያቢሎስም ክርስቶስን አንተ አምላክ ከሆንክ ይህን ድንጋይ ዳበ አደርግ እያለ ተፈታትኖታል ዛሬም አንተና መሰሎችህ ለዲያቢሎስ ፈረሶች የስጋችሁ ባሮች ስለሆናችሁ እንጂ አረቶዶክስማ ክርሰቶስን ስተጠራው የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ የንጉሶች ንጉስ ብላ ነው ይህንን ደግሞ አንተ የዲያቢሎስ ፈረስ ውስጥህ ካለው ተከራከር ያንግዜ እንዲህ ያለ ጥያቄ አተጠይቀኝ እያለህ እንደነበረ ሁሉ አሁንም ይልሀል ምንታደርግ ሉሲፈር ሰፍሮብህ እግዚአበሔር ይፈታህ በስጋ ገመድ በዲያቢሎስ ታስረህ ???? ልብ ይስጥህ ደግሞ አልሰማንም ትላለህ ድሮም እኮ ዲያቢሎስ የእግዚአብሀር ቃል ሲነገር እንዲት ብሎ ይሰማል ቃሉ ሰይፍ ስለሆነ ይቆራርጣል አሁንም ጆሮህ ካልሰማ አትድንም የሚዳነው በመስማት ብቻ አይደለም በስራም እንጂ መች ስራ ትወዳላችሁ አንተና መሰሎች ህዘቡን በማመን እንጂ የሚጸደቀው እያላችሁ የሰራውን እያፈረሳቸሁበት ለሲሆል ዳረጋችሁት እግዚአብሄር ይገሰጻችሁ

   Delete
  3. አቤት አቤት አሁንም ግትር እንዳልህ ነህ አንዴ?ለነገሩ ክህደትን ሙጥኝ ብሎ ጆሮውን አደንቁር ልቡንም አደንድን ከያዘው ሰው ጋር መመላለስ አላወቂነት ነው. በጸሎት አስራቱ ካለተፈታስአይሰማምና!!!ነገር ግን ባይስሙ የግራችሁን አቧራ አረግፍችሁ ውጡ አንደሚል ቃሉ ለመጨረሻ ጊዜ ግትር የሆንህበት ትክክል አንዳልሆነ ደግሜ ላስረዳህ፡፡ በእጅጉ ከበዙት ክርሰቶስን ከሚያስክዱ ትምህርቶች አባይን በጭልፋ እንዲሉ አንድ ማሰረጃ ልሰጥህ
   በክርሰቶስ ሞትና ትንሳየኤ ያገኘነውን የዘላለም ድህነት ወደ ጎን በማለት ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አየድንም?? የሚልን የድንቁርናና የክህድት ትምህረት ነው እንዴ ‘’አኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ‘’ አያልክ አፍህን ሞለተህ ልብህን በትቢት ወጥረህ የምትናገር???አሰኪ ስድቡን ተዉና በእግዜአብሄር ቃል አጣቅስህ ከላይ ያሰቀመጥሁትን ክሀደት ከዚህ በታቸ ካለው አወነተኛ ከሆነው የክርሰቶስ ቃል ጋር አስማምተህ አስረዳኝ፡
   • ዮሐ 14፡ 6 ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።ንፃፅር ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም??ውውውውው!!

   • መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ንፃፅር ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም??

   • እኛ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለየውን ወንጌል ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን (ገላትያ 1፡6-9) ታዲያ የትኛው ሃዋርያ ነው ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም??ያለው???ይህ ትምሀርት ያጋንንት ነው! የስጋ ነው!! የክሀደት ነው!በንስሃ ካለተመለስህ ፍርድን ያመጣል

   • “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (1ጢሞ. 2፡5) ንጽጽር ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም?? በአርግጥ ይህ ትምሀርት ያጋንንት ነው! የስጋ ነው!! የክሀደት ነው! በንስሃ ካለተመለስህ ፍርድን ያመጣል

   • ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።ዮሐ፤3፤17

   • በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።።ዮሐ፤3፤18 ንፃፅር ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም??

   • በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሐ፤3፤136 ንፃፅር ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አየድንም??

   • ዮሐ 4፡ 24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
   ከዚህ በላይ መጽሃፍ ቅዱስ አስረግጦ የሚነግረንን በክርሰቶስ የሆነውን ትመህርት አንያዝ እንክርዳዱን አራግፈን ከፍርድ ለመዳን ንስሃ እንግባ፡፡ብዞች እንዲያሰረዱኝ ስጠይቃቸው ካፋቸው ስድበ ይቀድማል፡፡ያለተፃፈን አንክረዳድ ሊዘሩብኝ ይሞክራሉ፤የክርስቶስ ቃል ያለሆንውን ተረተና ድሪቶ ጠቀልለው በማዋጥ ለሞት ሊያበቁኝ ሞከረዋል፡፡አባክህ የክርሰቶስን አዳኘነት ቸል አተበል!ማርን ከሬት ህይወትን ከሞት ጨለማን ከብርሃን ጋር አተቀላቅል!!!!!!!!   Delete
 6. ተሐድሶ
  ይቀራል ፈርሶ
  አንተ ዳግማይ ሉተር በማያገባህ ገብተህ አትዘባርቅ መጀመሪያ አንተ በንስሃ ታደስ .....ኦርትዶክስን ልታድስ የህልም እንጀራ ነው "ንህነሰ ንተልው አበዊነ ቀደምት" እኛስ አባቶቻችንን እንከተላለን!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ማቅ! አልሞት ባይ ተጋዳይ!! "እኛስ አባቶቻችንን እንከተላለን!!!!!" ማናቸው አባቶቻችሁ??? ጽሁፉን ተመለስና አንብብ እናንተ አባቶችን ስለናቃችሁ ስለተሳደባችሁ አይደለም እንዴ ይህ ሁሉ ጽሁፍ በተከታታይ የሚጻፈው። ድንቁርናችሁን እንደያዛችሁ አፋችሁን ሸብባችሁ ቁጭ ብትሉ በተሻላችሁ ነበር። ነገር ግን የተጫናችሁት ይዟችሁ ሲኦል እስትትወርዱ ድረስ ቤተክርስቲያንን መበጥበጣችሁን ቀጥሉ። ሰይጣን እግዚአብሔርን ሊፈታተን ሞክሮ አንስቶ ቢወረውረው ተገጣጥቦ ጠባሳው ይኸው ዛሬ በእናንተ ላይ ጎልቶ ይታያል። የአባታችሁን የዲያብሎስን ስራ ለማስፈጸም ስትሉ አባቶችን ትሰድባላችሁ፤ ክርስቲያኖችን ታሳድዳላችሁ፤ የቋንቋችሁ ክርፋት በየድረ ገጹ ጠንብቷል። እስቲ ኃይለየሱስ ለጌቶቻችሁ ለዳንኤልና ለዘበነ እግዚአብሔር የቀባውን ፓትራያርክ ስለሰደቡ የሰጠውን መልስ ወደ ዩቱብ ብቅ በሉና አዳምጡ አጓርታችሁም ቢሆን ተንደፋድፋችሁ ምናልባት እግዚአብሔር ይቅር ቢላችሁ ከዚህ መቅበዝበዛችሁ እረፍት ታገኙ ይሆናል። እውነት ለመናገር ያብቃችሁ!! እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

   Delete
 7. Good civilized advice, I hope our church leaders ,Mahbere Kidusan preachers pay attention to your simple advice.Unfortunately they are busy killing each other and dying to make more money.
  The church need complete overhaul and revival to survive.

  ReplyDelete
 8. አባታችንና ኦርቶዶክሳውያን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ለብዙ ወንድሞቻችን ፤ እህቶቻችን ፤ እናቶቻችንና አባቶቻችን መፍለስ ምክንያቱ ወንጌሉን ፍጹም አለመግለጣችን እንደሆነው ሁሉ፥ የትንሣኤውና የአዲስ ነፍሳት መጨመርና መመለስም ምክንያቱ የቅዱስ ወንጌል ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መሰበክን ነውና እባክዎ! በዚህ እውነት ላይ እንስማማና ወንጌሉን አድምቀን እንስበከው ፤ እናውጀው፡፡ GOD BLESS YOU ALL!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ላንተ ማድመቅ መጨፈር ከሆነ በለመድከው በስመ ቸርች ጭፈራቤት የደረከወ ላይ እንደለመድከው ቀጥል ውጤቱን ትነግረናለህ ባትነግረንም እናውቀዋለን ብዙዎቹ የአውሮፓውያን ዘመዶችህ ወደ ጭፈራ ቤትነት ተቀይረዋል እናም የኛዎቹም አይቀርም

   Delete
 9. Leba lamelu dabo yilisal alu. ayeh lebawu kemagnawu tekula mechem yichin tsafiku bele papasun lemedelel kehone tesasitehal mikiniyatum ante litisebken yasebekewuna yebeg lemid lebeseh yawerahewu sele menafikinet inji seletewahido ayidelem. tehadiso betekerisitiyanuwa yasifeligatal bibal endate zeregnana musegnawun lemenikel, begosa tederajito betekerisitayanuwan lematifat yetenesawun lemenikel fitawina menifesawit hiwot yemesebekibat lemadireg begeterina beketema iqul yehone astedaderawi mewakir indinorat inji wedeminifikina inditigeba ayidelem. beyebelit anten yemeselu yewusit yemenafikan arbegna ketewegedelat yetefut lijochawa yimelesalu bekenifochawa sir yitakefalu. yanten tehadiso lemenafikan abatochi nigirachewu

  ReplyDelete
 10. You are rigt. please teach gosple we are back.

  ReplyDelete
 11. hi ጰንጤ ይጥፋ ማቅም ይጥፋ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ብቻ ለዘላለም ትኑር

  ReplyDelete
 12. ሃኣኣኣኣሃኣኣአአአአአአአአአ

  ReplyDelete
 13. የአቶ አናኒ ክስረት !!

  ReplyDelete
 14. ድፍረት!!!ለመሆኑ ሰዎች ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚኮበልሉት ወንጌል ፍለጋ ነዉ ማለትህ ማንነትህን በሚገባ ያሳያል፡፡ ድፍረትህ አልኩ እንጂ ያዉ ይሆን ዘንድ ግድ ነዉ እንዳንተ አይነቶቹ እንደአሸን የሚፈሉበት እና እዉነተኛ የክርስቶስ ወንጌል እንዳይሰበክ በመበረዝ እና በማጣመም እንደገዛ ፍላጎታቸዉ በመተርጎም የትንቢት መፈፀሚያ ከመሆን የዘለለ ስላልሆነ ብዙም አይገርመኝም፡፡ምክንያቱም ይህ እንዳንተ አይነቱ ይመጣ ዘንድ ግድ ነዉና፡፡
  አሁንም ባይገባህም ባታስተዉልም ልንገርህ አዉቆ ያንቀላፋን ቢቀሰቅሱት አይሰማም አይደል የተባለዉ አይኑን ጨፍኖ ሊዋጋ ወደፊት እንደሚንደረደር በሬ አይነት እንቅስቃሴህን ብታቆም በስጋ የሚጠይቅህ ባይኖርም በነፍስ ከመቀጣት ያድንሃልና አስተዉል አስተዉል፡፡
  እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስር በክርስቶስ ክርስቲያን የሆንኩ አማኝ ነኝ፡፡ነገር ግን ቤተክርስያን የእዉነት ጌታ የሆነ ኢየሱስን ያልሰበከችበት እኔም ያልተማርኩበት ዘመን የለም፡፡
  አንተ ግን ..... ብቻ ይብቃኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው ስለፍፃሜ ክፋት ብቻ ታወራላችው ድል አድራጊው እኮ ኢየሱስ ነው አላማውም ሰውን ሁሉ መጠቅለል ነው ለምን ስለተሸናፊው እያወራህ ጠላትህን ታገናለህ ይሄኮ ማለት እራስህን በደንብ አታውቀውም ማለት ነው ኢየሱስ ጌታ ነው ለማለት ለምን ከበደህ? ጠላት እንዳትል ተረት ከቦህ እውነትን ውሸት ኡርጎ አንተ ውስጥ ቀርፃታል እኛኮ የጌቶች ጌታ ነው እንላለን የምትለው ይህን ካልክ ጌታ ነው የሚለው ለምን ማለት አቃተህ አስተውል ፍርድ እዚው ነው የሚፈፀመው ማመንና ኡለማመን

   Delete
 15. ሃይል ፤ ሃላፊነት መዉሰድ ፤ መቀነባበር ...ቋንቋችሁ ጠቅላላ ፖለቲካ ነዉ የሚመስለዉ :: ያነተ ከፍታ የት ደርሶ ነዉ እንዲህ አቧራ የምታስነሳዉ?

  ReplyDelete
 16. በመተከል ሀገረ ስብከት ግልገል በለስ 8620 አዳዲስ አማንያን ተጠመቁ
  እስከዚህ ዕድሜያችን ድረስ ስንጠብቃችሁ ነበር ተጠማቂያኑ፡፡

  02gilgel 2በመተከል ሀገረ ስብከት በግልገል በለስ ማእከል ሥር በሚገኙ 3 ወረዳዎች 8620 አዳዲስ አማንያንን ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2008 ዓ.ም መጠመቃቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ገለጸ፡፡


  በማንዱራ፣ ድባጤ እና ዳንጉር ወረዳዎች የሚገኙት እነዚህ አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ከሀገረ ስብከቱ፣ ከወረዳ ቤተ ክህነቶች እና ከግልገል በለስ ማእከል ጋር በመተባበር የቅድሰት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማሩ መቆየታቸውን ከማኅበሩ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


  ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ፍቅር እንዳላቸው የገለጹት ተጠማቂያኑ እስከዚህ ዕድሜያችን ድረስ ስንጠብቃችሁ ነበርÂ በማለት ሲናፍቁት የነበረው ጊዜ በመድረሱና ፍላጎታቸው በመሳካቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

  ReplyDelete
 17. 4. ብዙ ተሐድሶ ነን የሚሉ ሰዎች በስነ ምግባራቸው የዘቀጡ( ዝሙት ፣ገንዘብ መዝረፍ፣….በጾም መብላት..) ወዘተ ሆነው ሳለ እንዴት ነው ተሐድሶ መንፈሳዊ ለውጥ የሚያመጣው…..በእርግጥ ሥጋዊ ለውጥ ያመጣል …ምክኒያቱም ሰዎች ተሀድሶ ሲሆኑ ያልነበራቸውን ቤት መኪና…..ወዘተ ኖሯቸዋል…..ስለዚህ አባባላችሁ ውሸት ነው…..ቤተክርስቲያን አለም አቀፋዊት እንጅ አብዮታዊት አይደለችም…ልትሆንም አይገባም

  ReplyDelete
 18. menafikan anite doma chinikilat orthodox tehadso setil orthodox atitadesim hidina elemedikibet keandu adarash wedelela eyekeyayerik ebed aganinit yediyabilos lij

  ReplyDelete
 19. Wuhibe aganentes ante. taot yemtamelk lekeskes.

  ReplyDelete
 20. ሰው ለራሱ ተጎዳ እንጂ ቤተክርስትያናቺን እማ የገሃነም ደጆች ኣያናውፅዋትም ሰው ለራሱ ይታደስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የቤተ ክርስቲያን ትርጉም ያልገባህ ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ማደሪያ የሆነ ሰዉ ማለት ነዉ፡፡ ህንጻዉንማ በቅርቡ ለጭፈራ ቤት ታከራየዋለህ/ሽ/ አይፈርስም፡፡

   Delete
  2. ርጉም እንደናንተ አዳራሽ መሰለህ እንዴ ቤተክርስትያኗ ጭፈራ ቤት ምትሆነው ....ርካሽ ነህ!! 2000 ዓመት ኖራ ምንም ያልተለወጠች ቤተክርስትያን ናት ያለችን ....በ 16ኛው ክ.ዘ የተመሰረተ ፍልስፍና ይዛችሁ አይደል እንዴ በሺዎች የተከፋፈላችሁት.....ያንተ ሃሳብ ገብቶኛል አውሮፓ ያለውን ጭፈራ ቤታችሁን ነው ምታወራው!!! ነገሩ እዚሁም ያለው ያው ነው!!!

   Delete
 21. ግን የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እውነት የሰዎች ወደ ተለያየ እምነት መሄድ አንገብግቦክ ነው ወይስ አንተ ከዛ የምታገኘው ጥቅም ስላለ ነው መቼም ለነፍሴ ነው እንደማትለኝ ሙሉ እምነቴ ነው

  ReplyDelete
 22. ያሳዝናል በተቃዉሞ ከተሰነዘሩት ሃሳቦች ዉሰጥ አንድም አማራጭ ምክንያት ወይም መፍትሄ የሰጠ የለም፡፡ ዝም ብሎ መሳደብ ብቻ፡፡ ወንጌልን ከሚፈልጉ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ፡፡ ለብዙ ጊዚ ወደ ፕሮቴስታንት ለመሄድ ግፊት አድሮብኝ ነበር ግን ላለመሄድ ወሰንኩ አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያኔ ልብ ትገዛ ይሆናል ብየ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የተከተለችዉ ዕቅበተ ዕምነት/apology/ ማለትም ከተለመደዉ ኢየሱስን ከማያስቀድም አስተሳሰብ ወጣ ያሉ ምዕመናንን ማሸማቀቅ ብሎም ማሳደድ እራስን እንደ መብላት ነዉ፡፡ እጇን፣ እግሯን፣ ጆሮዋን በልታ አይኗን አጥፍታ ወደ ምንምነት ስትቀየር ይተየኛል፡፡ አንድ ቀን ትዉልዱ ትቷት ሲሄድ ይታየኛል፡፡ አሁን አብዛኛዉ ምዕመን የገጠሩ ህዝብ እና ጠያቂ ያልሆነ በመሆኑ ሊያኩራራን ይችላል፡፡ ግን እኔም ባንድ ወቅት እዲህ ነበርኩ፡፡ ዘመኑን ካልወጀን ዘመኑ ይበላናል በበኩሌ ክብሩ ይስፋ ወንጌል ወንጌሉን እየመረጥኩ እበላለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውን ወንጌል የለም ኦርቶዶክስ ውስጥ አንተ ታስታውቃለህ ወንጀል ነው ምትፈልገው እንጂማ ስንዱዋ እመቤት ሙሉ ናት እንኳን ወንጌል አንተን ከንደገና ታድስሃለች!!!!

   Delete
 23. ስለወንጌል እያሉ ፕሮትሰታንትን መጥቀስ ርካሽነት ነው፡፡ ባይሆን ምእመናን ለምን ይፈልሳሉ ብትል ኖሮ ትንሽ ተጨባጭ ይመስል ነበር፡፡ ለማንኛውም ጥሩ አድርጎ መልሶልሀል፡፡ ሩጫው ለግብረሰዶማዊነት ከሆነ ከንቱ ምኞት ነው አይሳካላችሁም፡፡
  ይሄ ሁሉ ጫጫታ ለምን እንደነ ፓስተር ከሚስቶቻችን በተጨማሪ እንደፈለግነው አላማገጥንም ከሆነ ቀጥልበት፡፡

  ReplyDelete
 24. AND TYAKE ALEGN????????

  YE MERABU ALEM(WESTERN WORLD) PROTESTANT BEGHAD ENDEMITAYEW SHIFANACHEW "eyesus huno'
  amlkotachew gn yaw "LUCIFERISM" ENDEHONE YTAWOKAL.SWEEDEN HAGER SEMONUN YETAZEBKUT YEHNINU NEW.

  YEGNA WOGENOCH(ETHIOPIANS)YEHN YAHL YEMITADEFULET ENDENECHOCHU AWUREWUN LEMEKEBEL NEW WOYS.............???????

  ReplyDelete
 25. ዲያቆን፤ ይህንን ሁሉ ከመዘብዘብህ በፊት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ወንጌልን እንዴት ነው የምተሰብከው፣ እንዴትስ ስትሰብክ ኖረች፣ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፣ የነገረ ድህነት ምስጢሩ የት ጋ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለጌታችን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርቶስ ምን ያስተምራል፣ የሚለውን በሚገባ ተረዳ፡፡ በኔ እምነት እንተ እና ብጤዎችህ ነገረ ድህነትን በሚገባ ባለማወቅ እና የኦርቶዶስ ተዋህዶን አስተምሮ ባለማወቅ የተነሳ ምዕመናን በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ሌሎች በየዕለቱ ከሚወለዱ እብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት ለይተው ሊረዱ በሚችበት ደረጃ ባለማስተማራችሁ ምዕመናን ሊሄዱ ችለዋል፡፡ ሌላው ሰዎች ለሥጋ ተገዥ የመሆን ሁኔታ እየሰፋ መሄድ ነው፣ ይህም አባቶች በፆምና በጸሎት ፀንተው ያስተምሩ የነበረበት ጊዜ አልፎ ዛሬ ራሱን ለመንፈሳዊ ሕይተው ሳያስገዛ እንደ ባለ ዛር በድፍረት ወንጌሉን እየጮኸ የሚሰብክ በመብዛቱ እና አረያ የሚሆን እየቀነሰ በመምጣቱ ነው፣ አንተ ለምዕምናን መፍለስ የምትጨነቀ ከሆነ ወደ ሌሎች ለማቀራረብ ከመትጋት ይልቅ የኦርቶዶክስን ነገረ ትምህርት በሚገባ እወቅና ልዩነቱን አስረዳቸው፣ ምዕመኑ ልዩነቱን ካወቅ ወደ እናት ቤተክርስቲያኑ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ በእውነት የምትቀና ከሆነ ጣትህን ወደ ሌላ መቀሰርህን እና መቀላቀልህ ትተህ እውነተኛ የመዳን ትምህርትን፣ መጽሐፍ ቅዱስን ጌታን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ጭምር ለዚያውም ከባለቤቱ እንደተማረ ነገር ግን ለድህነት እንዳልተቀበለ፣ በአምላክ ሰው መሆኑ የተሰናከሉ ሰዎች የተናገሩትን ቃል መርጠህ እንደ አውነተኛ የመዳን ትምህርት በመውሰድ ምዕመናን ከማደናገር በመቆጠብ አውነቱን ለተከታዮችን አሳውቅ፣ ያን ጊዜ በመጸጸት ይመለሳሉ፡፡ የቤቱ ቅናት ካቃጠለህ አሁን አውነቱን ወደ መገንዘብ የምትመጣበት ደረጃ ላይ እየደረስክ ስለሆነ ዓለም ይድን ዘነድ ምን ላድርግ ብለህ፣ ሰሞነ ሕመማትን በጨመለማ ውስጥ የነበርንበትን ጊዜ እያሰብክ ጌታ ለሰው ልጆች የዋለውን ውለታ በማሰብ ራስህን ምርምር፡፡ እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete