Thursday, April 28, 2016

ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው ወይስ ለእኛም ጭምር?

Read in PDF

ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፥ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። (ዮሐንስ 19፥26-27)
የዘንድሮው በዓለ ስቅለት ከበዓለ ማርያም ጋር ስለገጠመ ወይም በ21ኛው ቀን ስለዋለ በየማኅበራዊ ድረ ገጹ አንዳንድ ሰዎች በዕለቱ ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም? በሚል ጥያቄ እያቀረቡ አንዳንድ ግለሰቦችም ምላሽ ሲሰጡ ነው የሰነበቱት፡፡ ጥያቄው ሊነሣ የቻለው በበዓላት እንደሚደረገው ሁሉ በበዓለ ማርያም በብዛት አይሰገድም የሚለው ወግ ተይዞ ነው፡፡ የእኔ ጥያቄ ግን ከበዓለ ማርያም በዓለ እግዚእ አይበልጥም ወይ? ከበዓል መንፈስ እንውጣና ከማርያምስ የተሰቀለው ኢየሱስ አይበልጥም ወይ? ታዲያ ምነው እርሱንና ለእኛ መዳን የሆነውን ስቅለቱን የምናስብበትን በዓል ዝቅ በማድረግ እርሷንና የእርሷን ወርኃዊ በዓል ከፍ ለማድረግ እንሞክራን? እንዲህ ለማለት የደፈርኩት ጥያቄው ውስጥ ከበዓሉ በስተጀርባ የተሰቀለው ኢየሱስና እናቱ ማርያም ስላሉ ነው፡፡ በበዓላቱ የሚታሰቡት እነርሱ ናቸውና፡፡ ጥያቄ አቅራቢዎቹ በዓለ ማርያምን ለማክበር በሚል በዓለ መስቀልን መሠዋት እንዳለባቸው እያሰቡ ይመስላል፡፡  
ይህን ሁኔታ የፈጠረው ምንድነው? በዋናነት በማርያም ዙሪያ እየተሰጠ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ትምህርት ነው፡፡ ከእነዚህ ትምህርቶች መካከል ከላይ በመግቢያው ላይ የተጠቀሰውና “ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፥ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፥ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።” (ዮሐንስ 19፥26-27) የሚለው ጥቅስ የተተረጎመበት መንገድ አንዱ ነው፡፡     

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታቸው ተዛብቶ ከቀረበው ጥቅሶች መካከል አንዱ ይህ ነው ቢባል የተጋነነ አይደለም፡፡ ይህ የወንጌል መልእክት የማያሻማና ግልጽ ቢሆንም አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ወገን እንዲረዳው የተደረገው በተዛባና በተሳሳተ መንገድ ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ እናቱንና ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ዮሐንስን በአጠገቡ ቆሞ ባየው ጊዜ ለእናቱ፥ “አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ” ሲላት ዮሐንስን ደግሞ “እናትህ እነኋት” አለው። ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ወደ ቤቱ ወሰዳት፡፡
ጌታ እንዲህ ያደረገው ለምንድነው? የሚል ጠያቂ ቢኖር መልሱ አሻሚ ያልሆነና ብዙ ምርምር የማይጠይቅ ግልጽ ነው፡፡ እናቱ ስለሆነች በልጇ መሰቀል ካገኛት በላይ ሞቱን ስታይ ደግሞ የበለጠ ሐዘን እንዳያገኛት በማሰብ ይህን እንዳደረገ አያጠራጥርም፡፡ እናቱን ለዮሐንስ የሰጠውም በጊዜው አጠገቡ የተገኘው የሚወደው ደቀ መዝሙር እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተለየ ምንም ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ወይም ለብዙዎች ዛሬ እንደሚመስላቸው በዮሐንስ ወክልና እናቱን ለእኛ እናት ትሆነን ዘንድ ለመስጠት አይደለም፡፡
በመንፈስ ቅዱስ አሠራር በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ለተጠራነው ለእኛ አባት ብቻ እንጂ እናት የለንም፡፡ በዚህ መንገድ በተገኘው ልደት መጽሐፍ ቅዱስ ደጋግሞ የሚነግረን የእግዚአብሔር ልጆች ብቻ መሆናችንን ነው፡፡ በተለይም እነኋት እናትህ ተብሎ ማርያምን ወደቤቱ የወሰዳት የጌታ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ በጻፈው መልእክት ውስጥ “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።” ሲል እንደ መሰከረው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ብቻ እንጂ የማርያምም ልጆች አይደለንም (1ዮሐ. 3፥1-2)፡፡ ይህም ዮሐንስ ማርያምን ውሰዳት የተባለው ለእኛ ጭምር እናት አንድትሆን ነው የተባለው ነገር መሠረት የሌለውና ሰዎች የፈጠሩት ትምህርት መሆኑንም የሚያስረዳ ነው፡፡
ሰው በክርስቶስ የማዳን ሥራ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ይሆናል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር “በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና። እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።” ብሏል (ኤፌ.2፥18-19)፡፡ እግዚአብሔር የሁሉ አባት በሆነበት በዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ማርያምም ልጅ እንጂ ለእግዚአብሔር ልጆች እናት አይደለችም፡፡ ይህ የማርያምን ክብር መቀነስ መስሎ እንዳይሰማ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ምክንያቱም እኛ በጸጋ እና በእምነት በኩል የተወለድነው ከእግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” (ዮሐ. 1፥12-13)፡፡ “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤” (ገላ. 3፥26)፡፡ በሌላ በኩል ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአንድም ስፍራ የማርያም ልጆች ስለመሆናችን አልተጻፈም፡፡
ነገር ግን ጌታ ለደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ማርያምን እነኋት እናትህ፣ ለማርያምም ዮሐንስን እነሆ ልጅሽ ብሎ መስጠቱን መነሻ በማድረግ፣ ከተጻፈው ውጪ በመሄድና ከንባቡ ጋር ያልተስማማ ትርጉም በመስጠት የማርያምን እናትነት በተሳሳተ መንገድ ለመስበክ የሚሞክሩ በርካቶች ናቸው፡፡ ይህም ኢየሱስን እስከ መሸፈን እየደረሰ ነው፡፡ ለምሳሌ በቀራንዮ ላይ ተሰቅሎ ሳለ ሊታይ የሚገባው ኢየሱስ ነው፤ ወደ መስቀሉ መመልከት ያስፈለገንም ኢየሱስን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ ወደ መስቀሉ ስናይ የተሰቀለውን ኢየሱስን ነው የምናየው፣ ልናይም የሚገባን እርሱን ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የዛሬ 2008 ዓመት የተፈጸመውን የቀራንዮ ትእይንት መሠረት አድርገው ወንጌልን እንሰብካለን ሲሉ ወደ መስቀሉ ስናይ በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ትተው መስቀሉ አጠገብ የቆመችውን ማርያምን ነው የምናየው የሚሉ በርክተዋል፡፡ ከተሰቀለው ላይ ዓይኖቹን አንሥቶ መስቀሉ አጠገብ የቆመችውን የሚያይ ምን ዓይነት ሰው ይሆን? እንዲህ ያለው ሰው፣ አንድን አስደናቂ ትእይንት ሊመለከት ሄዶ ትእይንቱን በመተው ትእይንቱን ሊመለከቱ ከቆሙት መካከል አንዱን እንደሚመለከት ዓላማ ቢስ ሰው ነው የሚቆጠረው፡፡ ይህ ሰው በእውነት ከስሯል!  “የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” (ገላ. 3፥1) የሚለው እንዲህ ያለውን ስለ መስቀል እያወራ ኢየሱስን ማየት ያልቻለውንና ዓይኖቹ ሌላው ላይ ያረፉትን ምስኪን ወገን ነው፡፡
ይህ በቃሉ ላይ ያልተመሠረተ ሐሰተኛና እኛን በተዘዋዋሪ ከእግዚአብሔር ልጅነት የሚያወጣ ትምህርት ኢየሱስንና ማርያምን በማነጻጸርና በማወዳደር፣ ብዙዎች፣ ሌሎችን የኢየሱስ ደጋፊ ራሳቸውን ደግሞ የማርያም ደጋፊ አድርገው እያቀረቡ ነው፡፡ እኛ እናት አለን፣ እነርሱ ግን እናት የላቸውም እያሉም “እንቁልልጮ” ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ትምህርት አጉል መራቀቅ የወለደውና የቃሉ መሠረት የሌለው እንዲያውም ቃሉን የሚቃረን ሐሰተኛ ትምህርት ነው፡፡ መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ከሌላ ጋር ተነጻጽሮና ተወዳድሮ ሳይሆን ብቻውን ያለ አማራጭ ወደውና ፈቅደው የሚያምኑት፣ የሚቀበሉትና የሚከተሉት የሕይወት ራስ ነው፡፡ ዛሬ በእልክ ተይዘው ማርያምን ከኢየሱስ በላይ እየሰበኩ ያሉ ክፍሎች ቢያስተውሉት በሐዋርያት ቃል ውጉዛን ናቸው (ገላ. 1፥6-9)፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት የሰበኩትና ሊሰበክ ይገባል ብለው የነገሩን ኢየሱስን ብቻ ነው፡፡
·        “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥” (1ቆሮ. 1፥22-23)
·        “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።” (2ቆሮ. 4፥5)
እግዚአብሔር አብ ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር የገለጠው ሌላ ማንንም ሳይሆን አንድያ ልጁን በመስጠት ነው፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፥16)፡፡ እንዲሁም “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥” (ኤፌ. 2፥5) ይላል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስም ከላይ በተገለጸው ምክንያት ማርያምን ለዮሐንስ፣ ዮሐንስን ደግሞ ለማርያም መስጠቱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ በመስቀል ላይ ለሁላችን የሰጠው ግን ራሱን እንጂ እናቱን አይደለም፡፡ ትልቁና የመጨረሻ የፍቅር መግለጫ ራስን መስጠት ነው፡፡ ነፍስን ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር እንደሌለም ከመሰቀሉ በፊት በዚህ ምድር ላይ እየተመላለሰ ሲያስተምር ራሱ ጌታችን ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጌታ ለሁላችን እናት ትሁናችሁ ብሎ ማርያምን በዮሐንስ በኩል ሰጠ የሚለው ትምህርት በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ ሳይሆን ሰዎች ስለማርያም ያስፋፉት የስሕተት ትምህርት አካል ነውና ሊታረሙ ከሚገባቸው የተሳሳቱ ትምህርቶች መካከል አንዱና ዋናው ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “አንተ አቡነ ወአንተ እምነ . . .” ማለትም “አንተ አባታችን እናታችንም ነህ. . . ” (ዘደብረ ዘይት ዘሠኑይ ገጽ 103) በማለት ያቀረበው ምስጋና ለእኛ አባትም እናትም እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ብቻ እንደ ሆነ ያመለክታል፡፡ ዛሬ ግን አቡነ ዘበሰማያትን ሲደግሙ ካልሆነ በቀር የእግዚአብሔር አባትነት ትዝ የማይላቸውና ስለማርያም እናትነት ደግሞ በተሳሳተ መንገድ የሚያምኑና ያልተጻፈውን የሚያነቡ በርካቶች ናቸው፡፡ ምናለ ቃሉን እንዲሁም “አንተ አቡነ ወአንተ እምነ” የሚለውን የአበው ምስክርነት ቢቀበሉና የእግዚአብሔር ልጆች ቢሆኑ? ደግሞስ የእግዚአብሔር ልጅ ከመባል የበለጠና በእርሱ ላይ ሊጨመር የሚችል ምን ክብር አለና ነው እነዚህ ክፍሎች ከእግዚአብሔር የልጅነት ከፍታ በእግዚአብሔር ወዳልተሰጠን ወደ ማርያም ልጅነት መውረድን የመረጡት?
“የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።”


40 comments:

 1. leke newe leke newe leke newe

  ReplyDelete
 2. “አንተ አቡነ ወአንተ እምነ . . .” ማለትም “አንተ አባታችን እናታችንም ነህ. . . ” (ዘደብረ ዘይት ዘሠኑይ ገጽ 103)

  ReplyDelete
 3. ምነው እንዲህ ስንጥቅ ውስጥ እየገባህ በመጣበቅ መከራህን አየህ፤እምንት እኮ ምርጫ ነው ዝም ብለህ የራስህን ስብከት ስበክ፣ ምዕመን የራሱ የሆነ መመዘኛ አለው አንተ ስንጥቅ ለማስፋት ጣርክም አልጣርክም፤ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መቼ መች አትፈታም፣ በየጊዜው የሚነሱ ሹሞችና ምናምንቴዎች ሊያዳክሟት በትራቸውን ቢያወርዱባትም የተዋቀረችው በራሱ በጌታችን ደም የተሠራችውም የተቆለፈችውም/ ሥርዓት የተበጀላት/ እንደአንተ ባሉት ዓይነት ለሆዳቸው ባደሩ ሰባክያን ሳይሆን በሃዋርያት ጾም ጸሎት እና መስዋዕትነት ነው፡፡ እንደው ደከምክ ታዲያ እግዚአብሄርም ቤቱን የሚጠብቁ ሃዋርያት በየጊዜው ያስነሳል አስቀድሞም ያዘጋጀል፡፡
  አንተ ማስተዋል ያቀተህ ፣ እሰቲ አስተውል አቡነ ጎርጎሪዮስ በነበሩበት በዚያ ወቅት ወደፊት ከ20 እና 23 ዓመታት በኋላ አንተና መሰሎችህ ተነስታችሁ ይህችን እውነትና አውነት የሆነች ቤተክርስቲያናችንን እንደምታውኳት በማወቃቸው ይኸው ዛሬ አንተ እንደሾህ የምትፈራው የቤተክርስቲያን ጠበቃ የሆነውን ማህበረ ቅዱሳን ለመመስረት ምክንት ሆኑ፣ እና ምን ትላለህ ሁል ጊዜም እውነት አውንት ነው አይቀለበስ አይታደስ ፤የአንተ ተሀድሶ ፕሮቴስታንቲዝም ቅራቅንቦ በጥቅማጥቅምና በውሸት ላይ የተገነባ በመሆኑ በየጊዜው እራስህ በምትፈጥራት ውሸት እራስህ እየታመስክ ትኖራለህ እንጂ ፡ ቤተክርስቲያን አንተና መሰሎቿ በምትፈጥሩት ስንጥቅ ውስጥ እየገባህ መከራህን አትብላ፡፡

  ReplyDelete
 4. Here it is Bible fact Mat.16 13-20. He is the son of God or God reveled himself as human being for our sake. so yes he was born by Mary but not the same thing like our human nature. please let us see remember he is the son of God as written in the bible so many times. SO consider his Divine nature that can not be ignored. Please ;et us concentrate about him and the Cross. May God Bless you.

  ReplyDelete
 5. ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው However your explanation ... እናቱ ስለሆነች በልጇ መሰቀል ካገኛት በላይ ሞቱን ስታይ ደግሞ የበለጠ ሐዘን እንዳያገኛት በማሰብ ይህን እንዳደረገ አያጠራጥርም፡፡ እናቱን ለዮሐንስ የሰጠውም በጊዜው አጠገቡ የተገኘው የሚወደው ደቀ መዝሙር እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተለየ ምንም ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ is very simplistic. I personally think the reason he did that is because his time on earth was almost over and he did not want to abandon his beloved mother and told John to take care of her as his own mother for the rest of her life. More than that I think it also shows that Mary did not have other children unlike what some protestants say. But for the future, please try to be fair in your writing and let the truth shine. God bless!

  ReplyDelete
 6. ከመናፍቅ ድሮስ ምን ይገኛል

  ReplyDelete
 7. ይህ ቅጥፈት ነው፡፡ እውነቱን ግን አይቀይረውም፡፡ ለእኛም እናታችን ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ፡፡

  ReplyDelete
 8. Berayi Yohanis yetenegeriwun alastewlkewumin? "zendowu sititun asadede kewalawa bahir yemiyakilin wuha defa midiritum wuhawun watechi" yelal ayeh yih yetebalewu lantina lemeselochu newu. Dabilos mechem yihun meche beakal tayito ayakim bante wusit hono gin yisadebal yemeriz wuhawun yirechal yesan kiber ayikenisim mechereshal siol newu. egna kirston newu yeminayewu yeminsebkewum neger gin sine meskelu sinesa bezina gize yalut negeroch hulu yinesalu yitawesalu melkamim yaderegewu kifatim yaderegewu biyibelit gin kemeskelu sir inatu kidist inat lehulachin inat adirgo bedekemezimuru sim yeseten alech. ante ifer tedebek yesiol lij egna gin anafirim kirsitos kena gar newu.

  ReplyDelete
 9. Le ante enate ayidelechem , lante ayidelechem.le egna gen lek endeyohannes enatachen nat, yihenen tsega lemagegnet eske Qeraniyo deres mehed yasfelegal.krestos rasu eneho enateh eyale, ante demo beteqarani enatu ayidelechem telaleh, Amlakachen yalewun new yemenamew enji yanten yehasset mabraria ansemam. eweq

  ReplyDelete
 10. Esu yesebekelenen eko eyetekawemachihu new, rasu "eneho enateh" nat bilo yesetewun enante gen krestos ene enatehehm abatehm ene negn malet neberebet, eneho enateh malet alneberebetem eyalachihu eko new, tegermalachihu

  ReplyDelete
 11. በሕማማት ደግሞ በዐላት ይከበራሉ ማለት ሐሳበ ግትርነት ሲነግሩት አለመስማት ነው።
  ኢሳ ፴.፩ ቤ/ክርስቲያን ከሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ጥምቀተ ሕፃናት፤ከብካበ ወራዙትና
  የሙታን ፍትሐት የለም በማለት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት ብቻ በጾም በጸሎት በስግደትና በከፍተኛ ትጋት እንዲታሰብ ታውጃለች እነ ሠርጎ ገብ ደግሞ አስተብርኮ እንጂ ስግደት አይገባም በማለት ያደናግራሉ የራቸውን አዋጅም ያሰማሉ ይህ ሁሉ ሐሳበ ግትርነት ክፋትና ጥመት እንጂ ነገሩን ስተውት አይዶለም እናም በአካላዊ ቃል ለማመን እና እርሱ የተናገረውን ለመቀበል እንዲችሉ የክፋታቸውን ሥር ይንቀሉ!

  ReplyDelete
 12. በሕማማት ደግሞ በዐላት ይከበራሉ ማለት ሐሳበ ግትርነት ሲነግሩት አለመስማት ነው።
  ኢሳ ፴.፩ ቤ/ክርስቲያን ከሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ጥምቀተ ሕፃናት፤ከብካበ ወራዙትና
  የሙታን ፍትሐት የለም በማለት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት ብቻ በጾም በጸሎት በስግደትና በከፍተኛ ትጋት እንዲታሰብ ታውጃለች እነ ሠርጎ ገብ ደግሞ አስተብርኮ እንጂ ስግደት አይገባም በማለት ያደናግራሉ የራቸውን አዋጅም ያሰማሉ ይህ ሁሉ ሐሳበ ግትርነት ክፋትና ጥመት እንጂ ነገሩን ስተውት አይዶለም እናም በአካላዊ ቃል ለማመን እና እርሱ የተናገረውን ለመቀበል እንዲችሉ የክፋታቸውን ሥር ይንቀሉ!

  ReplyDelete
 13. እናንተ ቁጥር ማስላት ያልቻለ መቀነስና መደመር የሕፃናት ትምህርት ያቃተው እንዴት ይህ ይገባዋል? 2008 ዓመት አንተ የቀራንዮው ትእይንት ያልከው የጌታ ማዳን ከተፈጸመ ሳይሆን ከተወለደ ነው። 33ዓመት ቀንስበት ለዚያ። እንዲህ ዓይነቱን ምስጢር (የድንግል ማርያምን እናትነት ቅድስና ክብርና አማላጅነት) ለመረዳት እንደ ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ መተኛት አልያም እንደ ዮሐንስ መከራውን ታግሶ ስድቡን ችሎና ሐዘኑን ተቋቁሞ ቀራንዮ መገኘት ይጠይቃል። ምርጫው ያንተ ነው። ይህ ቢያቅትህ እንኳ ደጋጎቹ እናቶቻችን በየገዳማቱ ሲገኙ በእሰይ ስለቴ ሰመረ ዜማ የጸለዩት ጸሎት ይደርስህ ዘንድ ምኞቴ ነው። እንዲህ እያሉ "እዚያው ማርልኝ ያን ግትቻ እዚያው ማርልኝ ያን ግትቻ ይዤው እንዳልመጣ አጣሁኝ ማንገቻ" ማንገቻውን ያብጅላችሁ!

  ReplyDelete
 14. ጸረ ማርያም መናፍቅ ነህ

  ReplyDelete
 15. lemin erasihin chileh atinikesakesim. ante bemejemeriya orthodox tewahido silalonik yefelekewn malet tichilalek. tadiya lemin sew bet gebiteh tikelawitaleh. mariam enatachin nati binil legna new enji ante lemidinew yekenekenh.

  ReplyDelete
 16. ማርያምማ እናቴ ናት አዛኝቱ ሩህሩህ።እናታችን ብንላት ምን ክፋት አለው ለጌታየም እናት ናት እንኳን ለኛ ስትበዛብን ነው።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

  ReplyDelete
 17. በጣም ይገርማል የቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን የዘመናችን አገልጋዮች አስተምህሮ። ምክንያቱም የጌታችን ስቅለት በስግደት እንዳናስበው የእመቤታችን በዓል ስለሆነ ግዝት ነው አይሰገድም መባሉ እጅግ አሳፋር አሳዛኝ እና አምላክንና ፍጡርን ማነጻጸር በራሱ ሞት ነው።ገና የወንጌል ቃል ጠልቆ ያልገባንና በስም ብቻ በልማድ ተመላላሾች ሆን መገኘታች መኖራችን ነው።ለመሆነ እንደት ተደርጎ ነው ስቅለት ያለስግደት የምታሰበው? የመቤታቸን በዓል ከአምላኳ በላይ እንደት አደርጎ ከፍ ተደርጎ ልታይና ልከበር ይችላል? ምንስ ይባላል። አንድ ሰባኪ ስያስተም እመቤታችን ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል ናት ምክንያቱም ቅድመ ዓለም አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ተውልዶዋል ድህረ ዓለም ደግም ከድንግል ማርያም ስለተውለደ እርሷም እንደ አምላክ መታየት አለባት በማለት ኑፋቀ ያዘለ ማቅ ስያሰብክ ሰምተን እጅግ አዘን። አሁን ደግም ስግደት በስቅለት እለት አይገባም ግዝት ነው ብለው የምያስተምሩ አንዳንድ ሆዳሞችና ለነዋይ ብቻ ያደሩት ስናገሩ እየተሰሙ ናቸው። ለመሆኑ እነ ዶክተር ቀሲስ ዘበነ ለማ በገለልተኛ ቤተ ከርስቲያን እየኖሩ ሥርዓተ ቅዳሴ አፍርሶ የፓትራርኩ ስም ሳይጠራ እያገለገለ ስርአቱዋን እየሻረ ያለ ሰው ሥርዓተ ቤተ ከርስቲያን አስተምራለሁ እየለ ይነግዳል። መጀመሪያ እራሱ ስርዓተ ቤተ ከርስቲያን ሳይጠብቅ እንደት አድርጎ ነው ስለ ስርዓተ ቤተ ከርስቲያን የምናረው። ይህ ሰው በእለተ ስቅለቱ ስግደት የለም ግዝት ነው ብሎ በአደባባይ የሰበከ አባል ነው። እሬ ወንድሞቼ ጉድ ነው።የባሰውን የመናፍቃን መሳቅይ ሆነን ቀረን። እስከ መቼ ነው ከኢየሱስ ከርስቶስ ርቀን የምን ጓዘው? ይህ ዓይነቱ ጉዞ የእመቤታችን ፍቅር መግለጫ አይደለም። ይበቃል በማታለል መኖር ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ግን ሰግደሃል እነሱ የፈለጉትን ይበሉ....ትችት ብቻ እንደውም የሰገድክ አይመስለኝም ጫፍ ይዞ መሮጥ ብቻ!!!!

   Delete
 18. ጅል መናፍቅ፣እንዲሁ እንደለፈለፍክ እድሜህን ጨረስክ፣የሰይጣን አሽከር

  ReplyDelete
  Replies
  1. We are never ever slave for satan. Brother you have to know the difference between Lord Jesuse and his mother Vergin Mary position. God is God never compare with other things. You need open the bible and read it before giving any comment.

   Delete
  2. ጅላጅል አንተ ነህ ምክንያቱም አምላክና ፍጡርን ለይተህ ያላወቅህ። በመጅመሪያ ሰይጣን ብለህ ከአንደበትህ ከማወጣህ በፊት ማወቅ የምገባህ ነገር ነበር እርሱም በመስቀል ላይ የሞተልህን አምላክ ባለማወቅህና እመቤታችንን የፈጠራት አምላክ ለይተህ ባለማቅህ በነፍስ በጣም የተጎሳቆልክ ነህ። ደሙን በመስቀል ላይ የፈሰሰልህን አምላክና ጌታ እስካሁን አለመረዳትህ በስጋ ብቻ ነጣላ እየለበሰክ ባዶህን መመላለስ በጣም ያሳዝናል። ሰጣይጣን እውነቱን እዳታውቅ ልቦናህ ጋርዶታል ደጅህን ዘግተህ ጸልይ የነፍስን አዳኝ ታውቀዋለህ።

   Delete
 19. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዳልተለየች ወንጌላዊው ዮሐንስ እንዲህ ብሎ ጻፈልን
  በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ከኢየሱስ ክርስቶስ በስደቱ በሰርጉ ከተዓምራቱ ያልተየች እናት ድንግል ማርያም ለከመከራው ከስቃዩ ከሞቱ በአጠቃላይ ከማዳን ጉዞው ውስጥ ያልተለየች ሰማዕት የሰማዕታት እናት ምክኒያተ ድኂን ናት፡፡
  ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ እናቱ ከመናገር ዝም አላለም ሀዘኗ ብዙ ነበርና ያጸናት ልጇ የሚጽናናት የሚያረጋጋት የሚወደውን ሐዋርያ ዮሐንስን እነሆ ልጅሽ አላት፡፡

  ለሰው ልጆችም ሁሉ እናት ታስፈልገናለችና የአዳም ዘር በሙሉ እንዲድን ምክንያት ሆናናለችና ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽህናዋን ቅድስናዋን ወዶ ተወልዶባታልና ስለ እርሱም ብዙ ሀዘን ደርሶባታልና የሚወዳት እናቱን ለሚወደው ሐዋርያ የሚወዳት እናቱን ለሚወደን እስከሞት ድረስ ላፈቀረን ለእኛ እናት ታስፈልገናለችና በዮሐንስ በኩል እናት ትሆነን ዘንድ ተሰጠችን
  ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት።
  ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።ዮሐ 19፡26-27
  አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያውን ተዓምር በቃና ዘገሊላ ሲያደርግ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም በዚያ ነበረች ዮሐ 2፡1-3
  አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀላይ ተፈጸመ ሲል የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም በዚያ ነበረች ዮሐ 19፡26-27 ፡፡የመስቀል ስጦታችን እናትነቷም ፍጹም በሆነ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ለሚያምኑ ቀራንዮ ለሚገኙ ሁሉ ናት በእውነትም የጌታየ እናት እናቴ ነሽ፡፡

  የእመቤታችን ማርያም ፍቅሯ በልባችን ጣዕሟ ከአንደበታችን ይኑር
  አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር
  ወለወላዲቱ ድንግል
  ወለመስቀሉ ክቡር
  አሜን
  ተፈጸመ ዮሐ 19 ፡30

  ReplyDelete
 20. እነኋት እናትህ ዮሐ 19፡27
  በኢዮብ ቀናው
  ሚያዝያ 21/2008 ዓ.ም
  ጌታችን ወዶ ና ፈቅዶ እናት ትሆነው ዘንድ የመረጣት እናቱን እነኃት ብሎ ለሰውልጆች በሚወደው ሐዋርያ በኩል ሰጠን፡፡የነብያት ትንቢት ተፈጸመ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧ ሰው የሆነ ተወልዷልና መዝ 87፡5፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀላይ ከተናገራቸው 7 መልእክቶች መካከል አንዱ ስለ እናቱ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እናቱ መናገር ዝም አላለም ታዲየ ስለ እመቤታችን ክብር ለመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም፡፡
  ነብያት ሐዋርያት ጻድቃን ስለ እመቤታችን እናትነት ምን አሉ
  ዳዊት
  ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል መዝ 87፡5
  ሐዋርያት
  የኢየሱስ እናት ዮሐ 2፡1 ዮሐ 2፡3
  ቅዱሳት አንስት
  የጌታየ እናት ሉቃ 1፡43
  ኢየሱስ ክርስቶስ
  ዳዊት ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ብሎ በትንቢቱ የተናገረውን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነኃት እናትህ ብሎ በዮሐንስ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጠን ዮሐ 19፡27
  ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም -የፈጣሪም የሰው ልጆችም ሁሉ እናት ናት
  ለሙሴ የተሰጠ አስርቱ ትዕዛዛት ለእርሱ ብቻ እንዳልሆነ ኦሪ ዘሌ 4፡2 ኦሪ ዘሌ 27፡34
  ለደቀመዛሙርቱ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ክቡር ደሜ ነው ስለ እናንተ የሚቆረስ ቅዱስ ሥጋየ ነው ተብሎ የተነገረው ለእነርሱ ብቻ እንዳልሆነ ማቴ 26 :28 ማር 14፡24
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳምራዊቷ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል ሲላት ለእርሷ ብቻ እንዳልሆነ
  በቀኙ ለተሰቀለው ወንበዴ ገነትን ሲያወርሰው ለእርሱ ብቻ እንዳለሆነ ሉቃ23:42
  ለወንጌላዊያን /ለሉቃስ ዮሐንስ ማቴዎስ ማርቆስ/ የተገለጠ ወንጌል ለዓለም ሁሉ እንደሆነ
  ለዮሐንስ ወንጌላዊው የተሰጠችው እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ለእርሱ ብቻ ሳትሆን ለሰው ልጆች በሙሉ ነው፡፡ ዮሐ 19፡27

  ReplyDelete
 21. ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት ውስጥ አምስቱ ዐዋድያት በዓላት (Movable feasts) ስለኾኑ ዕለት ይጠብቃሉ፡፡ እነዚኽም ሆሣዕና፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ እሑድን ሳይለቁ ሲውሉ፤ ስቅለት ዐርብን ዕርገት ደግሞ ኃሙስን ባለመልቀቅ ይውላሉ፡፡ የቀሩት አራቱ ማለትም ፅንሰት ወይም ትስብእት፣ ልደት፣ ጥምቀት እና ደብረ ታቦር ደግሞ ዐዋድያት ስላልኾኑ(Immovable) ወር እና ቀን ሳይለዋውጡ በተለያዩ ዕለታት ይውላሉ፡፡

  አኹንም ግን ከእነዚኽ ከዘጠኙ ደግሞ አራቱ እጅግ የተለየ ክብር አላቸው፡፡ እነዚኽም ልደት፣ ጥምቀት፣ ስቅለት እና ትንሣኤ ናቸው፡፡ ልደት፣ ጥምቀት እና ትንሣኤ ታላላቅ የደስታ በዓላት ስለኾኑ ደስታው መብልንና መጠጥን በማካተትና ሌሊት በመቀደስ የሚከበሩ ናቸው፡፡ ከዚኽ ታላቅነታቸው የተነሣም ሦስቱም የዐርብንና የረቡዕን ጾሞች ሳይቀር የመሻር ሥልጣን አላቸው፡፡

  ልደት እና ጥምቀት ዐርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላሉ፡፡ ትንሣኤ ምንም እሑድን ባይለቅም በሚቀጥሉት 50 ቀናት ውስጥ ያሉትን ረቡዕ እና ዐርብ በሙሉ ያሽራቸዋል፡፡ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ትውፊት ደግሞ ከልደት ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ባለው የዘመነ አስተርእዮ ጊዜ ውስጥ ያሉትም ረቡዕ እና ዐርብ ቀናት በሙሉ በልደቱ እና በጥምቀቱ (በአስተርእዮው) ታላቅነት ይሻራሉ፡፡ ከዚኽም በላይ በትክክል ቀኖናውንና ትውፊቱን ጠብቀን የምናከብር ቢኾን በእነዚኽ ዕለታት ሰው ቢሞት አይለቀስም፤ በአንፃሩ ሰርግ እና ሌላ ሥጋዊ ተድላ ደስታ ማድረግም የተከለከለ ነው፡፡ በዓላተ ቅዱሳን ቢገጥምም ማዘከር ይደረግለታል እንጂ በዐቢይነት የሚከበረው የጌታችን በዓል ነው፡፡ ለምሳሌ፥ በዚህ ዓመት በዓለ ትንሣኤው የሚውለው የዐቢይ ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት ዕለት፣ ሚያዚያ 23 ቀን ነው፡፡ ኾኖም በዚኽ ዕለት የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ወጥቶ እንደሌላው ጊዜ ክብረ በዓል(ንግሥ) ተደርጎ ሊከበር አይችልም፡፡ ይህም ስለማያመች ብቻ ሳይኾን ስለማይገባም ነው፡፡ በመኾኑም በዓሉ ከትንሣኤ በኋላ ባሉት ቀናት በአንዱ ይከበራል እንጂ የትንሣኤ ዕለት የሚከበረው የጌታችን የትንሣኤው በዓል ብቻ ነው፡፡ ስለዚኽ እነዚኽ በዓላት ማንኛውንም ጾም፣ ሐዘንና ደስታንም ይሽራሉ ማለት ነው፡፡

  crucifixion-ethiopianልክ እንደነዚኽ ደግሞ በዓለ ስቅለት ዐርብን ሳይለቅ ቢውልም ይህም ከዐቢይነቱ የተነሣ እንደ ቀደሙት እንደ ሦስቱ ራሱን ችሎ የሚሽራቸው ነገሮች አሉት፡፡ እነዚያ ጾምን እንደሚሽሩት ስቅለት ደግሞ በምንም ምክንያት ጾም ተጹሞባት የማያውቀውንና ከዐሥርቱ ትእዛዛት አንዷ የኾነችውን ቀዳሚት ሰንበትን ሽሮ ከሰንበትነት አውጥቶ የራሱን ጾምነት አውርሶ ያስጾማታል፤ ስሟንም አስለውጦ ቀዳሚት ስዑር(የተሻረች ሰንበት) አሰኝቶ ያስገብራታል፡፡ ስለዚህ ስቅለት በፍትሐ ነገሥቱ የበዓላት ክብር ቅደም ተከተል መሠረት ከጌታችን ዓበይት በዓላት ቀጥላ የምትከበረውን ሰንበትን ከሻረ የማይሽረው ሌላ ምንም በዓል ሊኖረው አይችልም ማለት ነው፡፡

  የቀደሙት ሦስቱ ከታላቅነታቸውና ከታሪካዊ ዳራቸው የተነሣ ሌሊት እንደሚቀደሱት፣ ስቅለት ደግሞ በተቃራኒው ምንም ቀን ቢገጥመው ቅዳሴ አይቀደስበትም፡፡ ለምሳሌ፥ የዚኽ ዓመት ስቅለት የእመቤታችን ወርኃዊ በዓል ጋር ስለገጠመ ይቀደስ አይባልም፤ የሚከበረው በሚበልጠው በጌታችን በዓል ስለኾነ፡፡ እንኳን በወርኃዊ የእመቤታችን በዓል ቀርቶ ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ከኾነውና መጋቢት 29 ቀን ከሚከበረው ከትስብእት ጋር ቢደረብ እንኳ በዓሉ ትስብእትን አስቀድሞ በቅዳሴ አይከበርም፤ ይልቁንም ስቅለትን አስበልጦ በጾም በሰጊድ ይከበራል እንጅ፡፡ ስለዚኽ ስቅለት ከዘጠኙ ዓበይት በዓላትም እንደ ልደት፣ ጥምቀት እና ትንሣኤ ሌላውን ይሽራል እንጂ በሌላ በዓል አይሻርም፤ እንኳን ራሱን ሊያስደፍር ሰንበትንም ሽሯልና ፡፡

  እንኳን በዓለ ስቅለት ሰሙነ ሕማማትም እነዚኽን በዓላት ይሽራቸዋል፡፡ ኾኖም ከሰሙነ ሕማማት ኀሙስ በቅዳሴ ትሻራለች፡፡ ይህም እንኳ ራሱ ጌታ ሐዲሱን ሥርዓት ስለመሠረተባት ቢኾንም ስግደቱ እና ሌላው ሥርዓት በሙሉ በሕማማቱ ሥርዓት የሚሔድ ስለኾነ እንደተሻረ የሚቆጠር አይደለም፡፡ ልክ ቀደም ብለን ልደት፣ ጥምቀት እና ትንሣኤ ሐዘንን ይሽራሉ እንዳልነው ስቅለትም ማንኛውንም ደስታ ትሽራለች፤ ዕለቱ በሐዘን (ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን፣ መከራ መስቀሉን በማሰብ)፣ በልቅሶ፣ በጾም፣ በስግደት የሚከበር ስለኾነ የሌላ በዓል ጠባይን በፍጹም ሊወርስ አይችልም፡፡ እንደ ትውፊታችንማ ቢኾን፣ እንኳን የራሱ የስቅለት ዕለት የሚውል በዓል ቀርቶ በዐቢይ ጾም የሚውሉ ዓመታዊ በዓላት እንኳ በንግሥ፣ በማሕሌት እና በከበሮ በሌላ ወቅት እንዲከበሩ ነበር የተወሰነው፡፡ ምክንያቱም ልክ በዓለ ኃምሳን እንደ አንዲት ዕለተ ሰንበት ቆጥረን እንደምናከብረው ዐቢይ ጾምም እንደ አንድ ዕለት ጾም በአንድ ሥርዓት ብቻ እንዲጾም የተወሰነ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ መሻር አላመሻር አደለም ዋነው ቁም ነገር። የአምላካችን በዓል በምንም ምክንያት ለሰዎች ፍላጎት ተብሎ ለሻር አይቸልም ነው። የእምነታችን ችግሩ እዚህ ላይ ነው። እኛ ያደነን አምላክ ፈጣር እርሱ ብቻ ነው በማለት እናምናለን። መልሰን ደግሞ እርሱ በጠራቸው ፍጥራታቱ ክብር ተብሎ ይሻራል። የአምላክ ክብርና የእናቱን ቅድስት ድንግል ማርያም በምንም መልኩ ማነጻጸር አንችልም። እግዚአብሔር እርሱ እርሷን ፈጠራት ለክብሩም ማደርያ መረጣት ይህንን በትክክል ማመንና መከተለል አለብን። የእናቱ ፍቅር አለን በለን ከፈጣርዋ ጋር መወዳደር እስካለቆምን ግዜ ድረስ ለኦርቶዶክስ ቤተ ከርስትያናችን ትልቅ አደጋና አድስ ሃይማኖትን የበለጠውን እየፈጠርን መሆናችን ጠንቅቀን ልንረዳ ይገባናል።በዓላት እንድ ሻሩ እያደረግን ያለን እኛ ለግል ፍላቶታችን እንድመች እያደረግን በመፈጸማችን ለስተቶች እየተዳረግን ነው። በሌላ በኩል የበዓላት መሻሻር ካመጣ እኮ በተዘዋዋር እመነቱን ተሐድሶ እየተደረገበት ነው። ለምን ተሐድሶ አያስፈልግም ብለን እንናገራለን። ከላይ ወንድማችን የበዓላትን ተሐድሶ የተደረገበትን በትክክል አስቀምጦታል። እምነት አይታደስም ብለን ለምንናገር ሰዎች መልሱ ቁልጭ ብሎ ተቀምጦዋል። በስቅለት ቀን ስግደትን በእመቤታችን በዓል መሻር ከተቻለ ተሐድሶ እያስፈልገንም ማለት አንችልም። እምነቱ ብልጽ ተሐድሶ እየተደረገበት ነው።

   Delete
 22. ለእኛ አባት ብቻ እንጂ እናት የለንም ያልከው ትክክል ነው ድሮም እናት የላችሁምና፡፡ እናንተ እናት ቤተክርስቲያናችሁን የካዳችሁ፤ እናት ድንግል ማርያምን የካዳችሁ እናት መጽሐፍ ቅዱስን የካዳችሁ እናንተ እንዴት እናት ሊኖራችሁ ይችላል? ለእኛ ለምናምን ለክርስቶሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን ሰብእሰ ይብል እምነ ጽዮን ( ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ) ተብሎ በመዝሙር 86 እንደተነገረ ድንግል ማርያምን እናታችን ጽዮን እንላታለን እሷም ልጆቼ ትለናለች፡፡ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ አቅፋ ሰብስባ ከነጣቂ ጭልፊትና ከተኩላ እንድትጠብቅ በትምህርቷ፣ በምሥጢራቷ፣ በወንጌል ብርሀኗ እቅፍ አድርጋ ከአጋንንት ንጥቂያ ጠብቃ ለሰማያዊ መንግሥት የምታበቃ እናት ቤተክርስቲያን አለችንና እኛ እናታችን ስንላት እሷም ልጆቼ ትለናለች፡፡ ከብሉይና ከሐዲስ ይዘቷ ለነፍሳችን ማርና ወተት እያፈለቀች የምትመግበን የጌታ ቃል የሆነች፤ መንገድንም የምታያሳየን እናት ወንጌል አለችንና እኛ እናታችን ስንላት እሷም ልጆቼ ብላ ትክክለኛውን መንገድ ታሳየናለች፤ ወንጌል ባሳየችን መንገድም በመጓዝ የወንጌል ባለቤት ጌታ ካለበት እንደርሳለን፡፡ እናንተ ግን ወንጌልን በራሳችን ትርጉም እንምራሽ እንጂ በአንቺ እንመራ የማትሉ ከሀድያን ስለሆናችሁ እናት የምትሆን ወንጌል የለቻችሁም፡፡ ስለዚህ ለእኛ አባት ብቻ እንጂ እናት የለንም ያልከው ትክክል ነው ፡፡ አባታችሁም እኮ አእምሯችሁን በትዕቢት፣ በማን አለብኝነት፣ በዘረኝነት፣ በራስ ወዳድነት አደንዝዞባችሁ አላወቃችሁትም እንጂ ጥፋትን የምታስተምሩለት የጠበጎ ነገር ሁሉ ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ እባካችሁ ወደ ልባችሁ ተመለሱና በነፍሳችሁ ከመጎዳት ዳኑ፡፡

  ReplyDelete
 23. ድንግል ማርያም የመናፍቃን እናታቸው አይደለችም አይወዷትምና ለኛ ለኦርቶዶክሶች ግን የምንዳት: ዘወትር ካፋችን የማትወጣ: ፍቅሯ የበዛልን :ድንግል ማርያምን የጌታ እናት ወይም የእግዚአብሔር እናት(ወላዲተ አምላክ) እንላታለን:: ቤተክርስቲያኗ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም አምላክ ፣ ወልደ አምላክ ፣ ወልደ ማርያም ፣ ወልድ፣ ቃል ብላ ትጠራዋለች:: ድንግል ማርያምን ደግሞ እመቤት ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ፣ እግዝእትነ ማርያም ፣ የጌታ እናት ፣ ወላዲተ አምላክ ፣ ቅድስት፣እመ ብርሃን ፣ እመ አምላክ፣ንጽሕተ ንጹሃን ቅድስተ ቅዱሳን፣ጽዮን ወዘተ በማለት ትጠራታለች::ቅድስት ድንግል ማርያምን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአዳም በደል ወይም ከጥንተ አብሶ ነጻ ሆና በአዳም ባህርይ እንደ እንቁ ስታበራ የኖረች አደፍ ጉድፍ የሌለባት ፣ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ የነጻች ፣ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነች፣ የሰማይ የምድር ንግስት ፣ እንደሆነች እናምናለን::

  ReplyDelete
 24. ይብላኝ እናት ለሌለው እኛስ ንግስተ ሰማይ ወምድር ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን እናት አለችልን!!!

  ReplyDelete
 25. አባቶቻችን ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው በአምላክ ዘንድ ተወድዳ እናቱ ትኾን ዘንድ ስለተመረጠችው ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ውበት ጻፉ አመሰገኑ፤ በረከትን አፈሱ፤ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አላት ፡- “የዚኽችን ብጽዕት ገጽታ መሳል እንዴት ኾኖ ይቻለኛል፣ እኔ የምቀምመው ቀለም ተራ እና ለርሷ የማይመጥን አይደለምን? የርሷ ውብ መልክ እኔ ከምቀኘው ቅኔ እጅግ የላቀና የከበረ ነው፤ ውበቷን (ገጽታዋን) ይስል (ይገልጽ) ዘንድ አእምሮዬም አይሞክረውም፡፡ የእመቤታችን የማርያምን ታሪክ (ዝና) በምላቱ ከመንገር ይልቅ፣ ፀሓይን ከነብርሃኗና ከነሙቀቷ መግለጽ ይቀላል፡፡ ምናልባት የጠፈርን ብርሃናት በሰማይ ላይ መያዝ ይቻል ይኾናል፣ የርሷ ዜና ግን በሰባክያን ኹሉ እንኳ ቢነገር በፍጹም አያልቅም) እንዳለ፤ ሃይማኖታችኊ የቀና ኦርቶዶክሳውያን አንባብያን ብቻ እንደ ቀደሙቱ አበው ስለ ውበቷ የተሰማችኹን ጻፉላት እስቲ፤ እምነተ ጐዶሎዎችን ግን አይመለከትም!!!

  ReplyDelete
 26. ለእኛ አባት ብቻ እንጂ እናት የለንም ያልከው ትክክል ነው ድሮም እናት የላችሁምና፡፡ እናንተ እናት ቤተክርስቲያናችሁን የካዳችሁ፤ እናት ድንግል ማርያምን የካዳችሁ እናት መጽሐፍ ቅዱስን የካዳችሁ እናንተ እንዴት እናት ሊኖራችሁ ይችላል? ለእኛ ለምናምን ለክርስቶሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን ሰብእሰ ይብል እምነ ጽዮን ( ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ) ተብሎ በመዝሙር 86 እንደተነገረ ድንግል ማርያምን እናታችን ጽዮን እንላታለን እሷም ልጆቼ ትለናለች፡፡ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ አቅፋ ሰብስባ ከነጣቂ ጭልፊትና ከተኩላ እንድትጠብቅ በትምህርቷ፣ በምሥጢራቷ፣ በወንጌል ብርሀኗ እቅፍ አድርጋ ከአጋንንት ንጥቂያ ጠብቃ ለሰማያዊ መንግሥት የምታበቃ እናት ቤተክርስቲያን አለችንና እኛ እናታችን ስንላት እሷም ልጆቼ ትለናለች፡፡ ከብሉይና ከሐዲስ ይዘቷ ለነፍሳችን ማርና ወተት እያፈለቀች የምትመግበን የጌታ ቃል የሆነች፤ መንገድንም የምታያሳየን እናት ወንጌል አለችንና እኛ እናታችን ስንላት እሷም ልጆቼ ብላ ትክክለኛውን መንገድ ታሳየናለች፤ ወንጌል ባሳየችን መንገድም በመጓዝ የወንጌል ባለቤት ጌታ ካለበት እንደርሳለን፡፡ እናንተ ግን ወንጌልን በራሳችን ትርጉም እንምራሽ እንጂ በአንቺ እንመራ የማትሉ ከሀድያን ስለሆናችሁ እናት የምትሆን ወንጌል የለቻችሁም፡፡ ስለዚህ ለእኛ አባት ብቻ እንጂ እናት የለንም ያልከው ትክክል ነው ፡፡ አባታችሁም እኮ አእምሯችሁን በትዕቢት፣ በማን አለብኝነት፣ በዘረኝነት፣ በራስ ወዳድነት አደንዝዞባችሁ አላወቃችሁትም እንጂ ጥፋትን የምታስተምሩለት የጠበጎ ነገር ሁሉ ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ እባካችሁ ወደ ልባችሁ ተመለሱና በነፍሳችሁ ከመጎዳት ዳኑ፡

  ReplyDelete
 27. "ዮሐንስ ማርያምን ውሰዳት የተባለው ለእኛ ጭምር እናት አንድትሆን ነው የተባለው ነገር መሠረት የሌለውና ሰዎች የፈጠሩት ትምህርት መሆኑንም የሚያስረዳ ነው፡፡" yalkew betam tilik kihidet newu kehadi!!!! neger gin emnet yegil new mebtih newu. sewun gin atasasit enat kal;felegih begid enat athonhim, wededikm telahim Legna gin ENATACHIN nat!!!!!!

  ReplyDelete
 28. please First if you believe that you are son of Jusus, you will believe you are the son of Mary.....

  ReplyDelete
 29. ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው ወይስ ለእኛም ጭምር?aye ...... chirash ledirdir?????? Ager sitefa jart yabekilal?

  ReplyDelete
 30. ጌታ በመስቀል ላይ እናቱን የሰጠው ለዮሐንስ ነው ወይስ ለእኛም ጭምር? Ende eminetih yhun.... MENAFIK

  ReplyDelete
 31. “….እናቱ ስለሆነች በልጇ መሰቀል ካገኛት በላይ ሞቱን ስታይ ደግሞ የበለጠ ሐዘን እንዳያገኛት በማሰብ ይህን እንዳደረገ አያጠራጥርም፡፡” ከታች በመልእክትህ የተዘበዘቡት በሙሉ ይህንን ያንተን ጭፍን ድምዳሜ የሚያስረዳልህ ስለመሰለህ ነዉ:: ሃዘንማ እስከ ሞት ድረስ ጌታ ሲጎተት አብሯት አለ:: “የበለጠ ሃዘን” የምትለዉ ልጅን የሚያህል ነገር በመስቀል ተንጠልጥሎ እያየች ከዚህ በላይ ምን አይነት ልብ ሰባሪ ሃዘን እንዲኖራት አስበህ ነዉ? ስለ እናት አንስተህ አባት ስላለን የሚል መከራከሪያ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” አስመሰለብህ:: በDEBATE ህግም ከአጀንዳ በመዉጣህ ብዙ አዉርተህ ምንም ሳትል ቀርተሃል:: “ለቅዱስ ዮሃንስስ “እንኋት እናትህ ያለው ለምንድን ነዉ?” ቢሉህም መልስ አታገኝም::

  ReplyDelete
 32. ሄዋን የህዝብ እናት ተብላለች እመቤታቸን እናታችን ማለት ምኑ ነው ሀጥያቱ?ያለመታደል ነው።

  ReplyDelete
 33. Revelation
  የዮሐንስ ራእይ

  And when the dragon saw that he was cast unto the earth, he persecuted the woman which brought forth the man child.
  ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።

  And the dragon was wroth with the woman, and went to make war with the remnant of her seed, which keep the commandments of God, and have the testimony of Jesus Christ.
  ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።

  And there was given unto him a mouth speaking great things and blasphemies; and power was given unto him to continue forty and two months.
  ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

  And he opened his mouth in blasphemy against God, to blaspheme his name, and his tabernacle, and them that dwell in heaven.
  እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።

  And it was given unto him to make war with the saints, and to overcome them: and power was given him over all kindreds, and tongues, and nations.
  ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።

  I know thy works, that thou art neither cold nor hot: I would thou wert cold or hot.
  በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።

  So then because thou art lukewarm, and neither cold nor hot, I will spue thee out of my mouth.
  እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።

  If any man have an ear, let him hear
  ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።


  ReplyDelete
 34. እንኳዋን ደስአላችሁ ተቃጥላ የነበረችው በስልጢ ወረዳ ልዩ ስሙ ጉሮሬ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ከቡታጂራ በ16 ኪሎ ሜተር ርቀት ላይ የተሰራቺው ቤተክርስቲያን በቀን 6-7/09/2008 ዓ.ም ይመረቃል በወቅቱ ልባችሁ ያዘነ ሁላችሁ በዕለቱ መጥታችሁ እግዚአብሔርን እንድታመሰግኑ የበረከቱ ተካፋይ እንድት ሆኑ ተጋብዛችኃል
  እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቹአን ይባርክ !

  ReplyDelete
 35. ለዮሐንስ የተሰጠች እናት ድንግል ማርያም ለሁላችን እናት ናት፡፡ ዮሐ 19፡26-27
  እነሆ በቂ ና ከበቂ በላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
  በኢዮብ ቀናው
  ሚያዚያ 23/2008 ዓ.ም
  1. አብርሃምን አባታችን ሣራን እናታችን ብለን እየጠራን ይህም ፍጡር የተባረከ ይስሐቅን ስለወለዱ በእምነታቸው በምግባራቸው ስለጸኑ ነው እነሆ እግዚእብሔር ከሣራ የበለጠች በአጠቃላይ በቅድስናዋ በንጽህናዋ የሚወዳደራት የሌለ እርሱ እግዚአብሔር እናት እንድትሆነው የወደዳትን ደግሞም እነኃት ተብለን የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱሰ ክርስቶስን አምላኬ ብሎ ላመነ ሁሉ በእውነት እናት ናት፡፡

  ፥ ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ ኢሳይያስ 51፡ ፡2

  2. አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና። ኦሪዘፍ 3፡20 ሞት የወለደችውንና ያመጣችውን ሔዋንን እናታችን እያልን ህይዎት የወለደችውንና ያስገኘችውን እናት ድንግል ማርያምን የሕያዋን ሁሉ እናት እናታችን አይደለችም ማለት ክህደት እና እግዚአብሔርን መቃወም ነው ፡፡

  3. ዳዊት ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል ብሎ በትንቢቱ የተናገረውን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት ሊፈጽም ነውና እነኃት እናትህ ብሎ በሚወደው ሐዋርያ በዮሐንስ በኩል እስከ ሞት ድረስ ለወደደን ለእኛ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጠን ዮሐ 19፡27
  4. ለሙሴ የተሰጠ አስርቱ ትዕዛዛት ለእርሱ ብቻ እንዳልሆነ ኦሪ ዘሌ 4፡2 ኦሪ ዘሌ 27፡34
  5. ለደቀመዛሙርቱ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ክቡር ደሜ ነው ስለ እናንተ የሚቆረስ ቅዱስ ሥጋየ ነው ተብሎ የተነገረው ለእነርሱ ብቻ እንዳልሆነ ማቴ 26 :28 ማር 14፡24
  6. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳምራዊቷ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል ሲላት ለእርሷ ብቻ እንዳልሆነ
  7. በቀኙ ለተሰቀለው ወንበዴ ገነትን ሲያወርሰው ለእርሱ ብቻ እንዳለሆነ ሉቃ23:42
  8. ለወንጌላዊያን /ለሉቃስ ዮሐንስ ማቴዎስ ማርቆስ/ የተገለጠ ወንጌል ለእነርሱ ብቻ እንዳልሆነ ይልቁንስ ለዓለም ሁሉ እንደሆነ
  9. ለዮሐንስ ወንጌላዊው የተሰጠችው እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ለእርሱ ብቻ ሳትሆን ለሰው ልጆች በሙሉ ነው፡፡ ዮሐ 19፡27
  10. ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም -የፈጣሪም የሰው ልጆችም ሁሉ እናት ናት
  11. ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀላይ ሲሞት ደሙን ያፈሰሰው በዘመኑ ለነበሩ ፍጥረቱ ብቻ አይደለም ነገር ግን ከመጀመሪያው አዳም እስከመጨረሻው ሰው ድረስ ነው
  ነገር ግን
  ይህን ዕወቁ
  መናፍቃን እስቀድ መው ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ፈራጅ ሳለ አማላጅ በማለት ሃይሉን ከደዋል እናቱንም መጥላታቸው የሚገርመን አይደለም ስለሆነ ምንም የእምነት መልክ የሌላው ናቸው ንቁ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ
  እነሆ ድምጼ ከምድር እስከ ሰማይ ይሰማ በጥልቁ ውስጥም ይድረስ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም እናታችን ናት፡፡አሜን ፡፡

  ReplyDelete
 36. መጀመርያ ጌታ ጋር ከዚያም ከዮሐንስ ጋር ሳትግባባ ደረቅ ጩኸት አጩህ እሺ።

  ReplyDelete