Sunday, April 3, 2016

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መልካም ሥራዎች እና ተግዳሮቶቹ

Read in PDF


የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መልካም ሥራዎች ስንል መልካም ያልሆነውን መልካም ለማለት፣ በቲፎዞ ለመመስከር፣ ሊቀ ማዕምራን የማነ መንፈስ ቅዱስን ለማሞገስ ፈልገን ሳይሆን፣ ያየነውን እውነትና ቤተ ክርስቲያናችን ያገኘችውን ነፃነት፣ ያተረፈችውን መልካም እሴት መመስከር ስላለብን ነው፡፡ ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያን አትራፊ ሆናለች፡፡
በውድ ልጇ በሊቀ ማዕምራን የማነ ያተረፈችውን አንዳንድ ነገር እንኳን ብንመለከት ለምሳሌ ማህበረ ቅዱሳን የተባለውን የአመፀኞች ስብስብ ብናይ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ካለው ንቀት የተነሣ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ሰዎች እያሉዋት ለቤተ ክርስቲያን እንደ ወረርሽኝ ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ (ዲግሪ) እያስታጠቀ ቤተ ክርቲያን እንድትዋረድ አድርጓል፡፡ መንግሥትም ይሁን ሌላ ገለልተኛ አካል ይህን የመሰለውን የሃፍረት ካባ እዚህች የሊቃውንት መገኛ የመናንያን መፍለቂያ ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ይህ ዲቃላ ማህበር ሰርጎ በመግባት አንገት የሚያስደፋ ተግባር እንዲፈጸም አድርጓል፡፡

ሌላው ስለ ሙስና ተቆርቋሪ መስሎ መቅረቡ ነው፡፡ አሁን ተቆርቋሪ ቢመስልም ሲጀመር የሚያበረታታ ነበር እኮ፣ ምክንያቱም ሙስናን፣ ሌብነትን፣ ዝሙትን የፈፀመ ሰው ተጠያቂ ሳይሆን መኖር እንዲችል የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ቀደም እነ አባ እስጢፋኖስ አድባራቱን በኮታ ሲዘርፉ ሊቃውንቱን ሲያሳድዱ ተቆርቋሪነቱ የት ነበረ? ቀሲስ በላይ በመጀመሪያ መልካም ሰብእና እያላቸው መናፍቅ ሲባሉ፣ በመጨረሻ ግን ቀሲስ በላይ የሙስናን እስኬል ሲሰቅሉ፣ ሊቃውንቱን ሲያሳድዱ በዘረኝነት ሲጠለፉ፣ የማታ ማታ ብቸኝነት ሲሰማቸው ሰዎች ኃጢአት ሠርተው በሚጠመቁበት በዚህ ማህበር ተጠመቁና ኃጢአታቸው ተሰረየላቸው፡፡
በመሠረቱ ማቅ ትናንትና የሰደበውንና ያዋረደውን ሰው ያለ ቀኖና ይቅር እንደሚል በቅርቡ በካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፍ አይተናል፡፡ ከዚህ በፊት ካሕሣይ ገ/እግዚአብሔር መጽሐፍ ሲያሳትም ማህበረ ቅዱሳን በምርቃቱ ላይ ማንም ሰው እንዳይገኝ ብሎ አሳድሞበት ምርቃቱ ሳይሳካ ቀርቶ ነበር፡፡ አሁን ግን ካሕሣይና ማቅ ጋብቻ ፈጽመው ትናንትና ያወገዘውን ሰው ያለ ቀኖና ተቀብሎ መጽሐፍ አሳትሞለታል ያሳፍራል፡፡
ወደ ዋናው ነገር ስንመጣ ማቅ በአሁኑ ጊዜ ሊቀ ምእምራን የማነ ዘመንፈስን ጥላሸት የመቀባቱ ምስጢር፦
1.     ማቅ ቤተ ክርስቲያን ላይ የፈፀመውን ውርደት በመረዳት የአንዳንድ ግለሰዎችን ወንጀል ማክሸፉ ነው፡፡ እስከ አሁን በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃና በፎርጅድ ቅጥር፣ ፅላት በመሸጥ ለዘመናት ሲበለፅጉበት የነበረ ወንጀል በሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ አማካይነት ክሸፏል፡፡
2.     ሊቀ ምዕምራን ከተሾመ ወዲህ ማህበረ ቅዱሳን በየአድባራቱና ገዳማቱ የተማሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አሳድዶ በተገላቢጦሽ ፎርጅድ ሠርተፍኬትና ዲግሪ እያሰራ አባላቱን ቦታ ማስያዙ እንዲቀር በማድረግ የቤተክርስቲያን ልጆች እፎይታ ያገኙበት፣ የማቅ ሊቃውንቱን ያሳደደበትና “መናፍቃንን አሳደድኩ” ብሎ የገቢ መሰብሰቢያ ጎተራው እና የአሳዳጅነትና የከሳሽነት መንፈሱ በሊቀ ማዕምራን የማነ መክሸፉ ነው፡፡
ወደ ሌላው ነጥብ ስናልፍ አቤሴሎም በአባቱ በዳዊት ላይ እኔ ብሾም ኑሮ ፍትህ አሰፍን ነበር እያለ የእስራኤልን ልብ ይሰርቅ እንደነበር (2ሳሙ. 15፥2) ንቡረ እድ ኤልያስም እንደ አቤሴሎም ያገኙትን አለቃና ፀሐፊ መፈንቅለ የማነ ለማድረግ ያለ መታከት ሴራ መጎንጎን አሳፋሪው ተግባር ነው፡፡
እውነት እነ ንቡረ እድ ኤልያስ ለቤተ ክርቲያን ከመቆርቆር ወይስ ሌላ ዓላማ አላቸው? ትናንትና እኮ በየ አድባራቱ ሲዞሩ ከሄዱበት ደብር ከ15 ሺሕ እስከ 20 ሺህ ድረስ የኮቴ እንዳላስከፈሉ ዛሬ ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው ለጥቅማቸው እንጂ ለቤተክርስቲያን አስበው እንዳልሆነ የምናውቅ እናውቃለን፡፡ ያን ጊዜ የተዘረፈው ገንዘብ በአንዳንድ ደብሮች እስከ አሁን ሂሳቡ ያልተወራረደባቸው አድባራት አሉ፡፡ አሁን ደግሞ ለዝውውር ብለው ትልልቅ ገቢ ወዳላቸው ካቴድራል ለመግባት ቀብድ የከፈሉአቸው አለቆች ወጣጥረው ስለያዙዋቸውና ገንዘባችን ይመለስልን ሲሉአቸው “የማነ ሲወርድ ይስተካከልላችኋል፤ ብቻ የማነን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለማውረድ ተባበሩ” እያሉ ማሳደም ስራዬ ብለው ይዘዋል፡፡
እውነት ሊቀ ምዕምራን የማነ ሙስናን አልተዋጋም? ዘረኝነትን አላስቀረም? ከከተማ እስከ አቃቂ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለማሰከበር አልደከመም? ያለ ሊቀ ጳጳስ በታማኝነት ያለአድልዎ ያለሙስና የሰራና እየሠራ ያለ ብቸኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ ለእግዚአብሔርና ሹመቱን ለሰጠው አካል በታማኝነት እየሠራ ያለ ልጅ ነው፡፡ ለመሆኑ ሰው የሚመሰገነው መቼ ይሆን?
በአስተዳደር በኩል ግን በሊቀ ስዩማን ወ/ሰንበት አለነ በኩል እጅግ አስፀያፊ የሆነ ዘረኝነትና ሙስና እየተፈፀመ ስለሆነ አስቸኳይ እርምት ያስፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት

30 comments:

 1. Replies
  1. The witness of rat is Dinbit/
   "Ye Ayit Misikrua Dinbit"
   le Missa/lunch/ Siasibun le kursi/breakfast/ Aderegnachu.long leave MK. Yihe ne Yeaba liji.

   Delete
 2. .....ለእግዚአብሔርና ሹመቱን ለሰጠው አካል በታማኝነት እየሠራ ያለ ልጅ ነው፡፡ kkkkkkkk

  ReplyDelete
 3. የዲያብሎስ የስስት ልጆች ከናንተ ድሮውንስ ምንይጠበቃል!!! በሬ ወለደ ወሬ!!!

  ReplyDelete
 4. ስድብ ከኃጥያት ስራዎች አንዱ እንደሆነ ተቀምጧል እናንተም ብዙ ጊዜ የምታወጡት ስድብ ያዘለ ነው፡፡ ይህን ከማን ተማራችሁት መቼም ከእግዚአብሔር አይደለም ከአባታችሁ ከዲያብሎስ እንጅ ይህ ያልሁትም መፅሐፍ ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ ብሏልና እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል እንደተባለው ከመሆን ይልቅ ንስሃ ገብቶ መመለስ ይሻላል፡፡ የሚከተለን አለ ብላችሁ ከሆነ ግብራችሁ ታውቋልና አትድከሙ፡፡

  ReplyDelete
 5. Zare degimo mahibere kidusan forjid asere hone yetemare haile silanesew bforgid yetemaru eyaderege betkihnet wist asgeba eyalachihu new girum new mahibere kidusanen lemesdeb yemanen mamesgen endet tayito yemitebk gignet new jal? tsehufachihun lemanbeb search lay gebche mak beye etsefalehu andim ken atichew alwkim esti andken mulich adirgachihu sidebuachewna yilefilachihuna yetewesen gize situachew yemigermew tibebe amlak setuachew lezeh laltegereze milas mells alemestetachew gizeachew besira yeteyaze new yenante betekaraniw. Esti bemin hisab en yemane bego yedergalu yetefa simachewn madesha andi tesfachew enante bitcha silehonachihu new.

  ReplyDelete
 6. hiwetachihu forged yehonew enante eyalachihu silewereket atawiru ewket timihert lenante yeras mitat new

  ReplyDelete
 7. ከብሎጋችሁ እንድም እውነት የማይነብበት እግዚያብሔርን ሣይሆን የማነዘመንፈስቅዱስን የምትሰብኩ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንን ትወቅሳላችሁ ቅዱሳንን አምልኩ ይላሉ ብላችሁ እናንተማ ምንም ስራ የሌለውን በሙስናና በዘረኝነት አባዜ የተወጠረውን ግለሰብ በስልጣኑ እንዲቆይ ያላደረጋችሁት ነገር ልነበረም ግን እውነተኛ የሆነው አምላክ ሥራቸሁን መና ከንቱ መሆኑን ሲያጋልጥባችሁ በምትኩ ሌላ ሰው መሾሙን ሰማን እስኪ ደግሞ ለአዲሱ አጎብድዱ ስለእግዚአብሔር ሳይሆን ስለእርሱ ስበኩን ሣናውቃችሁ ከማህበሩ ጋር ተጋጨን እውነት መስሎን ለካስ ቅዱሳንን ያከበር ያከበራቸው እግዚአብሔር ያከብረዋል አሁን እውነቱን ተረዳን ከማህበሩጋር ሆነን ቅዱሳንን እናከብራለን እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተ የተዋህዶልጆች ሁላችሁ መልእክት አለኝ ይሀ የምናየው እና የምንሰማው ሁሉ ያልፋል እውነት ግን ከእውነተኞች ጋር ናትና በተዋህዶ እንጽና
  አባ ሰላመዎች ይብቃችሁ በእግዚአብሄር ስም የከፈታችሁትን ብሎግ አትዋሹበት

  ReplyDelete
 8. ye tehadiso megagnaApril 4, 2016 at 1:49 PM

  Yekebir le mut meshegna yettsafe metsinagna new. Mutan lemutan.
  Beje

  ReplyDelete
 9. ውይ ተባረረኮ 500 000 ብር ሙስና ሲቀበል ተይዞ ኪኪኪ የናተ ታማኝ።ቱልቱላ ቆምጬ

  ReplyDelete
 10. አቤት ድሮም ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል ይባላል፡፡ ሌባን ማመገስ ልማዳችሁ ነው

  ReplyDelete
 11. I was expecting you guys are from Orthodox but truly spiking your not. labanena musegnan yemidegef christian ????? betam azegnabachewalehu...Yemanen medegef malet serkoten musenan kemdegef ga ande new..Im so sorry...

  ReplyDelete
 12. እውነት ሊቀ ምዕምራን የማነ ሙስናን አልተዋጋም?¡¡¡

  ReplyDelete
 13. you guy are you crazy? you raised very paradox issue within a single issue?

  ReplyDelete
 14. የአይጥ ምስክር ድንቢጥ አሉ የሌባ እና የተሐድሶ ዘብ የሆናችሁ እውሮች ሆይ ምን ያክል የሀሳብ ዝቅጠት ውስጥ እንዳላችሁ ታስታውቃላች፡፡ ጥላቻን ብቻ የምታወሩ የክፉ ተግባር ማሳያዎች መሆን እንደምትችሉ ታሳያላችሁ እርግጠኛ ነኛ ይህ ብሎግ ሰው ካላወቀ የድቁርና ጥግ እስከየት እንደሚወርድ የዚህ ዘመን ማሳያ ናሙና ናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 15. yihew tebarere men telu???

  ReplyDelete
 16. ሊቀ ምዕምራን ከተሾመ ወዲህ ማህበረ ቅዱሳን በየአድባራቱና ገዳማቱ የተማሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አሳድዶ በተገላቢጦሽ ፎርጅድ ሠርተፍኬትና ዲግሪ እያሰራ አባላቱን ቦታ ማስያዙ እንዲቀር በማድረግ የቤተክርስቲያን ልጆች እፎይታ ያገኙበት፣ የማቅ ሊቃውንቱን ያሳደደበትና “መናፍቃንን አሳደድኩ” ብሎ የገቢ መሰብሰቢያ ጎተራው እና የአሳዳጅነትና የከሳሽነት መንፈሱ በሊቀ ማዕምራን የማነ መክሸፉ ነው፡፡

  ReplyDelete
 17. Abet firehat sintun tsihufen alaweta alachihu maninetachihun yeminager tsihuf bsansur sim endayweta tadergalachihu netsa kehonachihu lemin atakerbutim.Bilogu endayzega kebetekiristyan yezerefutin yakamisuachihual endet bilachihu ewnet yiwtachihu ? gileseb weginachihu yet tidersu endehon enayalen betkirstyanin bitweginu yishalachihual.Niseha gibu

  ReplyDelete
 18. ምክንያቱም ሙስናን፣ ሌብነትን፣ ዝሙትን የፈፀመ ሰው ተጠያቂ ሳይሆን መኖር እንዲችል የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆን ይጠበቅበታል፡

  ReplyDelete
 19. የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ካህናት አባቶቼ ለመሆኑ ለተፃፈው ጽሑፍ የተሰጠውን ርዕስ እና ይዘቱን አስተውላችኋል የማኅበረ ቅዱሳንን ስም በማይመለከተው ጉዳይ ለመውቀስ ለምን ያልሆነውን በሬ ጥጃ ወለደ የፈጠራ ውሸት ውስጥ ለመግባት ለምን ይህን ያህል ደከማችሁ፣ ልባችሁ እውነቱን እያወቀ ለምን ከራሳችሁ ጋር ትጣላላችሁ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት መቼ ከሙስና ነፃ ወጣ፣ ለሊቀመአምራን መነሳትስ ምክንያቱ ይኼው አይደል፣ ሙስናን ሲዋጉ የነበሩ የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ምዕመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሲያሳስር አልነበረም፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ችግር ያለባቸውን አብያተ ክርስቲያናት አጥንተው ባቀረቡ ኮሚቴዎች መሰረት የተወሰነውን ውሳኔ እንዳይፈፀም ያደረገ እርሱ አይደለም፣ ዱሮ በገጠር ኮሶ ሲጠጣ እናቶች ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ይሉ ነበር፣ እኛም ዶሮ አንደማይታረድልን እያወቅን እንዘል ነበር፡፡ በሙስና ውስጥ አብራችሁ ተሳታፊ የነበራችሁ ካላችሁም የምትሰጡት ምስክር ከሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ያለፈ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ምዕመኑ እውነትን ያውቃል፡፡ ይልቀኑ እኔ አሁን አንድ ሥጋት አለኝ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ያለው ሙስና ከምን ጊዜውም በላይ እየበዛ እና በሐቅ ለቤተክርስቲያን የሚታገሉትን የመግፋት ሁኔታ እየጨመረ ስለሆነ፤ ምዕመኑም ይህንን እየተረዳ ስለመጣ ለቤተክርስቲያ የሚያስገባውን ሙዳይ ምፅዋት እንዳይቀንስ ነው፣ ይህንን በመሥጋት የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ብዙ ሥራ መሥራት አለበት፡፡ የአዲስ አበባ ምዕመን አሥራት በኩራቱን ለአዲስ አበባ መስጠት በላተኛን እና የቤተክርስቲያ ጠላቶች ማፈርጠም እንደሆ እየተገነዘበ ስለሆነ ገንቡን በተለያዩ ምክንያቶች ከአዲስ አበባ ሲወጣ ለሚያገኛቸው አድባራት የመስጠት ሁኔታ እያደገ እየመጣ ነው፤ ከማኅበረ ቅዱሳንም ጋር የሚሰሩ በጎ አድራጊዎች ገንዘባቸው የት እንደዋለ በትክክል ስለሚያውቁ እንጂ የማኅበር ፍቅር ይዞአቸው አይደለም፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ራሱን ካላስተካከል፣ ቤተክርስቲያንም አዲስ አበባ ላይ የሚገኘውን ገቢ ለገጠር አድባራት የሚሰርስበትን ሁኔታ ካለመቻቸች የአዲስ አበባ ገቢ በዚሁ ላይቀጥል ይችላል የሚል ሥጋት አለኝ፡፡
  እግዚአብሔር አምላክ ሙሰኞችን ያስታግስልን፡፡

  ReplyDelete
 20. "በውድ ልጇ በሊቀ ማዕምራን የማነ ያተረፈችውን" ኪኪኪ

  ReplyDelete
 21. Sorry for your biased support. I can see that yemane is the leader of robbers. But you support him. Are you on the side of the church or his relatives! Anyway yemane is sent out. He is no longer the manager. Aba selama tazebinish.lekas yewoyane neshi.

  ReplyDelete
 22. the owner of this blog is Yemnezemenfeskidus that why he keep silent he was removed from his post .you are the devil not from our church.

  ReplyDelete
 23. በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምትክ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡትለልዩ ጸሓፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን መ/ር ጎይቶኦም ያዩኒ!!
  እንኳን ስራ አስኪያጅ ይቅርና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ተቀባዮች ስለት ገንዘብ ቆጣሪዎች እነ አብረኸት ብቻ ሆነዋል፡፡ እነሱ እኮ ሌላው ካላጎነበሰላቸው በቀር እንኳን የሀላፊነት ወይንም የገንዘብ ቦታ ይቅርና ተራ ሥራም አይሰጡት፡፡ እኔ የማደንቀው ግን የእነ ያማነ ሌብነት አላምር ሲለው በጊዜ በራሱ ፈቃድ ም/ሥራ አስኪያጅነቱን የለቀቀውን መምህር አእመረን ነው፡፡ አሁን ዘረኝነት ባይኖር ኖሮ እሱ በሐቀኝነቱ የዋና ሥረ አስኪያጅነቱን ቦታ መያዝ ነበረበት ግን ሌላ (ጎዣሜ) ነዋ!!
  ሪዛቸውን ያረዘሙ እድሜን የጠገቡ በገጻቸው መንፈሳዊነት ያለባቸው የሚመስሉ ውስጣቸው በጎጠኝነት የተሞላ አባቶች ተብዬዎች እጃችሁን ለእግዚአብሔር ሳትሰጡ መንፈሳዊ ሥራ የሰራችሁበት ሳይሆን የሳታችሁበት እድሜአችሁ ወደ ፍርድ እየነዳችሁ ነው ነው፡፡ ተው!! በቀሪ ዘመናችሁ ለእውነት ሥሩ፡፡ አናንተ ዘረኞች፣ የደብሩ አስተዳዳሪ እና ቢሮ ሰራተኛው ሙዳየ ምጽዋት ቀማኛ፣ ወጣቱ ሱሰኛ፣ ባለሥልጣኑ ቀማኛ፣ባለትዳሩ ሴሰኛ፣የእኛ የምትሉት ሥነ ምግባር አልባ ሆነ፡፡ ሁሉ ተበላሽቶ አይከብዳችሁም ቀሚስ እየጎተታቸሁ አባቶች ነን ስትሉ ልጆቻችሁ እነማን ነን…. እስቲ በእናንተ ወንበር የነበሩትን ቀደምት አባቶች አንብቧቸው፡፡ ማን ከማን ተምሮ ጥሩ ምግባር ይኑረው፡፡ ሌላው ቀርቶ ቅርባችሁ ያለው ማህበር እንኳን በአግባቡ ልትይዙት ስላልቻላችሁ እና ስላልመራችሁት ዛሬ አጉራ ዘለል ሆኖ ሽቅብ ገልብጦ እየጋለባችሁ ነው፡፡ እበቶች ሆናችሁ እኮ!!! እበት በእርጥበቱም ሆነ ሲደርቅ ያው ነው! ክብር የለውም!! አፍንጫ ይሰረስራል፣ ጥሩ መኣዛ የለውም ፡፡
  እና ወዳጃችን አቅም እና ሙሉ እውቀት ያለው ሰው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥልጣን ይይዛል ብለህ ባታልም ጥሩ ነው፡፡ የጎጠኝነቱ ደመና ሲገለጥ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የፍቅርና የሰላምን ሐር ግምጃ ያለብሳታል ፡፡ ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

  ReplyDelete
 24. lemen rasachehun atatefum....kkkkkk.... tanko megelagel eyale... yasadegachehut leba agul honebachehu... kesemonu demo beregetegnenet patriariku lay tezoralachehu.... dn. Daniel lay bekefetachehubet afachu... Ayezon MUTAN.

  ReplyDelete
 25. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካህናት አሉ¡
  ስም የለሽ ካህናት ¡¡¡

  ReplyDelete
 26. በውድ ልጇ በሊቀ ማዕምራን የማነ ያተረፈችውን አንዳንድ ነገር....kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk. Ere saku gedelegne. በሌባ ቤ/ያን ስታተርፍ ታየኝ. ጉድ ነው! ትንሽ ቆይታችሁ በተሀሃድሶው አባ ሰላማም ቤ/ያን አተረፈች ልትሉን ነዋ!

  ReplyDelete
 27. የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት ካህናት አባቶቼ ለመሆኑ ለተፃፈው ጽሑፍ የተሰጠውን ርዕስ እና ይዘቱን አስተውላችኋል የማኅበረ ቅዱሳንን ስም በማይመለከተው ጉዳይ ለመውቀስ ለምን ያልሆነውን በሬ ጥጃ ወለደ የፈጠራ ውሸት ውስጥ ለመግባት ለምን ይህን ያህል ደከማችሁ፣ ልባችሁ እውነቱን እያወቀ ለምን ከራሳችሁ ጋር ትጣላላችሁ፣

  ReplyDelete
 28. በሌባ ቤ/ያን ስታተርፍ ታየኝ. ጉድ ነው! ትንሽ ቆይታችሁ በተሀሃድሶው አባ ሰላማም ቤ/ያን አተረፈች ልትሉን ነዋ!

  ReplyDelete