Saturday, April 30, 2016

ትንሣኤ አንድ ነው፣ ሕይወትም እሱ ነው!ምንጭ፡-http://dejebirhan.blogspot.com/
Read in PDF
ቀልጣፋ ሬስቶራንቶች በቀላሉ የሚስቡን የፈለግነውን ምግብ በምንወደው መንገድ እንድናዝ መንገድ ስለሚከፍቱልን ነው። ጥቂት ካፌዎች ደግሞ ከመቶ በላይ የተለያዩ የቡና ጣዕም እንደሚያቀርቡ በጉራ ይናገራሉ። መኖሪያ ቤቶችና መኪናዎችን ስንገዛ እንኳ የምንፈልገው ምርጫ እንዲያሟላ እንሻለን። በቼኮላት፣ በቫኒላና በእንጆሪ ዓለም ታጥረን መኖር አንፈልግም። ፍላጎት ንጉሥ ነው! እንደግላዊ ፍላጎትህና ምርጫህ የምታገኝበት ሁሉ የተሟላበት ዘመን ነው። የዓይን አምሮትና ፍላጎትን የሚያሟላው ዓለም የእምነት መንገድንም ለዘላለማዊ ሕይወት ይበጃል ያለውን በአማራጭ አቅርቧል።

ታዲያ ለአንተ /ለአንቺ/ ትክክለኛ እምነት የማግኘቱ ሁኔታስ ምን ይመስላል?
ወቀሳ አልባ፣ ብዙ ጫና የሌለውና ይህንን አድርግ አታድርግ እያለ የማያስቸግር ሐይማኖት ብታገኝስ? ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ያውና እዚያ አለ እንደሚሉት ነገር፣ ሃይማኖት እንደሚወዱት አይስክሬም የሚመረጥ ነው እንዴ? እድሜው፣ ሥርዓቱና ደንቡ ስለሚስብህ ይሆን? ወይስ በባለብዙ መንገድ የሕይወትህ ቤዛ ቃል ስለተገባልህ በአንዱ ላይ ተስፋህን ለማኖር?
ትኩረታችንን ለመሳብ የሚሻሙ በርካታ ድምፆች ስላሉ ለምን? ብሎ ነው አንድ ሰው ኢየሱስን ከሌሎች ማለትም ከመሐመድ ወይም ከኮንፊሸየስ፣ ከቡድሐ ወይም ቻርለስ ቴዝ ራስል ወይም ከጆሴፍ እስሚዝ አስበልጦ የሚመርጠው? ዞሮ ዞሮ ሁሉም መንገዶች የሚያደርሱት ወደ መንግስተ ሰማይ አይደለም እንዴ?
 “በኢየሱስ እናምናለንየሚሉቱ ራሳቸው የማዳኑን ተስፋ የሚገልጡበት መንገድ የተለያየ ስለሆነ እንደገበያ ላይ ሸቀጥ ገብተን ድነትን የምንሸምትባቸው አይደሉም።

 በመሰረቱ ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ አይደሉምና። እንደ እውነቱ ከሆነ ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ መንግስተ ሰማይ አያመሩም። ሁሉም መንገዶች ወደ ኢንዲያና መቼም አያደርሱም። የእምነት ድርጅቶች ሳይሆኑ ወደመንግሥቱ የሚያስገባው ላመኑበት ሁሉኢየሱስ ብቻ ነውየምንለው ማለት ስለፈለግን ሳይሆን እንድንል የሚያስገድደን እውነት ያለው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለተፈፀመ ነው።
1/ ኢየሱስ ብቻውን በእግዚአብሔር ሥልጣን ይናገራል።

ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻ ነው ሞትን ያሸነፈው። እስካሁን ድረስ መሐመድ፣ ኮንፊሸየስና ሌሎች በመቃብር በስብሰው ይገኛሉ። ነገር ግን ኢየሱስ በራሱ ስልጣን በጨካኙ የሮማውያን መስቀል ከሞተና ከተቀበረ ከሦስት ቀን በኋለ መቃብሩን ፈንቅሎ ተነስቶአል። በሞት ላይ ስልጣን ያለው ማንኛውም ሰው ትኩረታችን ሊስብ ግድ ይላል። ማንም በሞት ላይ ስልጣን ያለው ግለሰብ ሲናገር ልናደምጠው አስፈላጊ ነው። ሞትን ማሸነፍ የቻለ ከፍጥረታት መካከል ማንም የለም። ከሰማይ የመጣው ብቻ ሞትን አሸንፎ ወደሰማይ ወጥቷል።ስለዚህ እንዲህ ያለው አሸናፊ የተናገረው የእምነት መሠረት መሆን አለበት። ሰው ሟች መሆኑን ያውቃል። ሟች ደግሞ ከሞት ለማምለጥ የሚችለው በሞት ላይ ባለሙሉ ሥልጣን በሆነ ክንድ ላይ ሲያርፍ ነውና ኢየሱስን ማመን የግድ ይለዋል። በሞት ላይ ሥልጣን ያለው፣ ለሞታችን ብቸኛ ዋስትና የመሆን ብቃት አለው። ሌላ መንገድ፣ ሌላ ቃል ኪዳን፣ ሌላ አዳኝ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም የለም። ይህንን እውነት ያለምንም ድርድር ማወጅ ያልቻለ እምነት፣ ምድራዊ የሃይማኖት ድርጅት እንጂ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ምስክር አይደለም።
2/ የኢየሱስ ሕይወትና ትንሣዔ ምስክር ያለውና እውነት ነው።
የኢየሱስን ትንሣዔ የሚደግፈው መረጃ የሚያጥለቀልቅ ነው። ሮማውያንና ሰቃልያኑ ካህናት የኢየሱስን መቃብር ማስጠበቅ ያስፈለጋቸው «በሦስተኛው ቀን እነሳለሁ» ያለውን ቃሉን ይዘው እንጂ የሞተ ሰው መቃብር ስለሚጠበቅ አልነበረም። አዎ ትንሣኤውን ለመከላከል ወታደሮች ከመቃብሩ ማንም እንዳይወጣ፤ ወደመቃብሩም ማንም እንዳይደርስ አድርገው አስጠብቀው ነበር። ነገር ግን የመቃብሩ ቦታ ባዶ ሆኗል! እንደተናገረው አልተነሳም እንዳይሉ የኢየሱስ ጠላቶች ያን ሁሉ ስለትንሣኤው የተነዛውን ወሬ ለማክሸፍ የበሰበሰውን አካሉን በማቅረብ በቀላሉ ያስታግሱት ነበር። ግን አልቻሉም፤ መላው ሲጠፋባቸው ደቀመዛሙርቱ ሬሳውን ሰርቀውት ይሆን? አሉ። ከሐዋርያቱ መካከል ከዮሐንስ በስተቀር ሌሎቹ የሸሹት በጊዜ ነው። የሸሹ ሰዎች ተመልሰው ከሮማ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ሰረቁት ማለት የማይመስል ነገር ነው። የመቃብሩ ባዶ መሆን ሳያንስ ሞቶ የተቀበረ ሰው ዳግም ተነስቶ በሰዎች ፊት ራሱን በመግለጥ ያረጋገጠ በታሪክ ማንም የለም። ኢየሱስ ብቻ ይህን ማድረግ ችሏል። ትንሣዔውን ያለምስክር ያልተወ ኢየሱስ ግን በአንድና በሁለት ሰዎች ፊት ብቻ ሳይሆን በአምስት መቶ ሰዎች ፊት ትንሣዔውን አስመስክሯል።
«መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ» 1 ቆሮ 154-8
ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስን ለማመን የሚያስችላቸው በቂ የእምነት ማስረጃ ስላላቸው ነው። በዚህ ምድር ላይ ካሉ ሃይማኖቶች ውስጥ እንደኢየሱስ ሞትን ያሸነፈ፤ ትንሣኤውን በምስክር ያረጋገጠ ማንም የለም። ስለዚህ በሞት ላይ ሥልጣን ያለው ማንም ሰው ሊደመጥ ይገባል። ኢየሱስ በሞት ላይ ያለውን ሥልጣን አረጋግጧል። ስለዚህ የሚናገረውን መስማት ይገባናል። ለድነት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ መሆኑን ራሱ ይናገራል።(ዮሐንስ 14 6) ኢየሱስ ክርስቶስ ካሉትም ብዙ መንገዶች አንዱ አይደለም። ኢየሱስ ብቸኛ የድነት መንገድ ነው። ሌላ መንገድ ሁሉ በትንሣኤና በሕይወት ላይ ሥልጣን የሌለው የሞት መንገድ ነው። በሞትና በትንሣኤ ላይ ሥልጣን በሌለው ማንኛውም የመዳን ተስፋ ቃል ላይ አትታመኑ። እውነት የምትመስል ነገር ግን የጥፋት መንገድ ናት።በዚህና በዚያም ትድናላችሁየሚሉ ድምጾች መጨረሻቸው ሞት ነው። ሟች ለሟች የተስፋ መንገድ መሆን አይችልም።
3/ ኢየሱስ ከሸክም ያሳርፋል።
በዚህ ምድር ላይ ከሸክም አሳርፋችኋለሁ ብሎ ቃል የገባ አንድም ሥጋ ለባሽ የለም። ይህ ብቸኛ ኢየሱስ እንዲህ ይላልእናንተ ደካሞች፤ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደእኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” (ማቴዎስ 11 28) ሕይወትም አስቸጋሪ ነው። ብዙዎቻችን ደምተናል፣ ቆስለናል፣ ጦርነትንም እንፈራለን። ዓለምም አስጨናቂ እየሆነች ነው። ስለዚህ የሚያሳርፈንን ብንፈልግ ተገቢ ነው። ነገር ግን ከኢየሱስ በቀር ሸክም የከበዳችሁ ወደእኔ እኔም አሳርፋችኋለሁ ያለ ማንም ሌላ የለም። በትንሣኤውና በሕይወቱ የታመነ ኢየሱስ ይህንን የማለት ብቃት ስላለው በእርሱ ላይ ማረፍ ከአስጨናቂው ዓለም ለመዳናችን ዋስትናችን ነው። ከድካማችሁ በማያሳርፉ በማንም ላይ አትታመኑ። ትድኑበት ዘንድ ብቸኛው ቃል ኪዳን ኢየሱስ ለመሆኑወደእኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁየሚል ቃል ነግሮናልና ነው። በዚህ ተራራ ወይም በዚያ ሸለቆ የሚያሳርፍ ቃል የለም። ቃል፣ ቀራንዮ ላይ ስለእኛ አንድ ጊዜ ተሰጥቷል። በሞቱ ሞታችንን ሽሮ፣ በትንሣኤው ሕይወት በሰጠን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ብቻ እንድንታመን የሚያስፈልገን የሚያስተማምን ምስክርነት ስለተወልን ነው።
ስለዚህ ምን ትፈልጋላችሁ? ከኃጢአት፤ ከድካም፤ ከተስፋ መቁረጥ በንስሐ መታደስ ወይስ የአንዱ ሃይማኖት አባል በመሆን ብቻ መኖር? ሕያው የሆነ አዳኝ ወይስከሞቱት በርካታ ነቢያት ወይም ጻድቅአንዱን ተስፋ ማድረግ? ትርጉም ያለው ግንኙነት ወይስ ተራ የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት መከተል?
4/ ኢየሱስ አማራጭ ሳይሆን ምርጫ ነው!
ሃይማኖት ማለት አንድ መንፈሳዊ ድርጅት ወይም የአንዱ ተቋም ስያሜና የዚያ አባል ሆኖ መኖር ማለት አይደለም። ከእግዚአብሔር አብ ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት ትፈልግ እንደሆን ሃይማኖትህ ኢየሱስን ማመን ነው። «በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው» ይላል መጽሐፍ። (ዮሐንስ 3 36) አንዳንዶች ይህንንማ እናምናለን ነገር ግን ትክክለኛው እምነት ያለው በኛ ሃይማኖት ውስጥ ስለሆነ አባል ሁነን ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ በማኅበር ስለመጸለይ ይነግረናል እንጂ ኢየሱስን ለማመን የዚህ ወይም የዚያ ሃይማኖት ተቋም አባል የመሆን ትዕዛዝ የለውም። ኢየሱስ በሱ የሚያምኑ ሁሉ እንዲድኑ እንጂ የሃይማኖት ድርጅት ሊመሠረት አልመጣም። ለጸሎት በኅብረት መሆን ቢያስፈልግ መጀመሪያውም መጨረሻውም የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ የሚከብርበት እንጂ ሰው፣ ሰው የሚሸትበት፣ ብቃትና የሰዎች ማንነት የሚደሰኮርበት ከሆነ ድርጅትን ማምለክ ይሆናል። በዚህ ዘመን ብዙዎች ተሰነካክለዋል።
 በራሱ ሥልጣን ከሙታን የተነሳ ማን አለ? ወይም በዓለም ላይ ካሉ የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶች መካከል ለሰው ልጆች ዘላለማዊ የሕይወት ተስፋ ለመስጠት አስተማማኝ ማን አለ? መሐመድ፣ ኮንፊሽየስ፣ ራስል፣ ስሚዝ፣ ሉተር፣ ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት ወዘተ ማንም ቢሆን ይህን ማድረግ አይችሉም።
እምነት ከሞት በላይ በሆነ በትንሣኤው ምስክርነት ላይ ይታመናል። ሕይወት ከድርጅት ሥልጣንም ባለፈ ብቸኛ የድነት መንገድ በሆነው ኢየሱስ ላይ ይጸናል።
እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለውዮሐ 6:47 ያለን ኢየሱስ ብቻ ነው።

17 comments:

 1. አሜን አሜን ኢየሱስ ጌታ ነዉ

  ReplyDelete
 2. ”ከርሞ የሚያብድ ሰው ዘንድሮ ልብሱን ከፍ ከፍ በማድረግ ይሰናዳል“ እንዲል ተረት፡፡ ለነገሩ አንተ እንኳን ዘንድሮም አብደሃል፡፡ ምንአልባትም እብደትን በደረጃ ሳይሆን በአንድ ጊዜ ካሳኩት መካከል ነህ ማለት ይቻላል፡፡ አሁን የቀረህ ነገር ቢኖር ይህ ለተራና እርካሽ ለሆነ ፍልስፍናህ የምትጠቅሰውን መጽሐፍ ቅዱስ ወርውረህ ግብረ ሰዶማዊ መሆን ብቻ ነው፡፡ ለነገሩ እዛም ደርሰህ ሊሆን ይችላል!ይህ የቀባጠርከውን ፍልስፍና ያራመዱ ብዞዎች መጨረሻቸው እንዲሁ ሰለሆነ !

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ ምነው ተናገሩ አሰኘህ። በተሃድሶ እንቅስቃሴ ሰዶማዊነቱ የታወቀ ሰው ቢኖር አንድ አሸናፊ መኮንን ነው። እሱንም ቢሆን ማቅ ደርሶበት ሳይሆን በቅድስና የማይደራደረው የተሀድሶ አገልግሎት ራሱ ነው ያጋለጠው። ምነው ንገሩኝ ባይ ሆንክ የአንተው ማቆቹ እነ ያረጋል ሰዶማዊ መሆናቸውን ረሳኸው እንዴ? እነ ዳንኤል ልጃቸውን ክደው አይናቸውን በጨው አጥበው እንደገና በደናግል ሥርዓት በተክሊል ማግባታቸውን አባይነህ ካሴ ከሚስቱ የተለያየው ከሰራተናው ጋር ይዛው መስሎኝ። የእናንተ ቅዱሳን እነ ደጀኔስ ቢሆኑ ጅማ ያስለዳትን ልጅ ትረሳለህ እንዴ? ቀጥሉ ካልክ ይቀጠልልሀል። አንድ አሸናፊ መኮንን ሰዶማዊ ሆነና አፍህን ሰላሳ ጊዜ ለአንድ ዘፈን አትክፈት

   Delete
  2. በሬ ወለደ ወሬማ ታውቁበታላችሁ ያባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች አሁን እነ ዲ/ን ያረጋልን ለመስደብ በቃህ እርጉም.....ጌታ ይገስጽህ!!!!

   Delete
  3. ወንድሜ የክርስቶስን የማዳን ስራ ጥሩ ገልጸሃል፡፡እግዚያብሄር ይባርክህ፡፡ሰለኔ የሚመሰክር ባባቴና በመላክት ፊት እመሰክርለታለሁ በኔ የሚያፍር አፍርበታለሁ ይላልና ቃሉ፡፡ አዎ ትነሳኤ አንድ ነው ህይወትም እሱ ነው፡፡፡፡፡፡፡፡፡የክርሰቶስን የማዳን ስራ መመስከር የክርስተናችን አመድ የማናፍርበትም ተግባር ነውና፡፡ ይህንን አወነት ተቃርናችሁ የቆማችሁ አሰተያት ሰጭዎች የቀረበወን ትምህርት በመጽሃፍ ቅዱስ ቃል መዝኖ ስህተትም ካለበት ከእገዚያብሄር ቃል ጋር አመዛዝኖ ስህተት የሆነውን ለምን አታስረዱንም??? አኔ ግበረሰዶም ሰለ እረኩሰት እንጅ ክርሰቶስን ሲሰብኩት አላየሁምና ከላይ የቀረበውን ቃል ግበረሰዶሞች ናቸው የሚለው አስተያይት ከድንቁርና የመነጨ መሰረትና ማሰረጃም የሌለው ጭፍን የጥላቻ አመለካክት መሆኑን መረዳት በፈጹም ቀላል ነው፡፡የጻህፍት ፈሪሳዊያን መንፈስ መንፈሳችሁንና ነፍሳችሁን አደንዝዞ እወነቱን በመረዳት ከመከተል ይልቅ እኛ ብቻ አዋቂ ብላችሁ በትቢት ራሳችሁን አግዝፋችና ኮፍሳችሁ ነፍስና መንፈሳችሁ ታስራለችና እግዚያብሄር ይፍታችሁ፡፡
   ለነገሩ ያባታችሁ የዲያቢሎስ የሆነውን ስደብ በየቀኑ ስተልጥፉ ማየት የተለመና የሰለቸን ጉዳይ ነው ፡፡እወነቱን ለመናገር ሰለክርሰትና ከገለባ የቀለለ መረዳት እንዳላችሁ ብቻ ሳይሆን በስማ በለው የምትነዱ ግብዞች መሆናችሁን ያሳያል፡፡
   ከላይ አንዳለሁት አሰኪ ስሀተቱን ከበሬ ወለድ ተረታችሁ ሳየሆን ከቃሉ ጋር አጣቀሳችሁ ብስለት ባለበት አገላለጽ ንገሩኝ???በእርግጠኝነት አትችሉም፡፡ካፋችሁ ስድብ ነው ያለውና፡፡ስለሆነም ከዚህ በኋላ የናነተን ተረተና ኢመጻህፍ ቅዱሳዊ የሆነ የሞትና የክህደት ትምሀረት አራግፈናል፡፡ ክርሰቶስ ብቸኛው የድህነት መንገድ ነው፡ የሃ.ስራ 4፡12 እባካችሁ አናነተም አራግፉ፡፡ፊታችሁን ወደ ክርሰቶስ ወንጌል አዙሩ፡፡ሰላምንና ፍቅርን ስበኩ፡፡የሳተም አለ ብላችሁ ካመናችሁ በፍቅርና በጸሎት ቀርባችሁ ስህተቱና በቃሉ አሳዩ ፡፡ ይህ ነው የመነፈስም የአምሮም ብስለተና እድገት፡፡
   አባሰላማዎች በርቱ የክርሰቶስ ወንጌል ያሸንፋል፡፡እናነተ አወነትን ይዛችሁ የክርሰቶስን ቤዛነትና አዳኘነት ንገሩ ፡፡ መከሩ በዙ ሰራተኞች ግን ጥቂት ናቸው እንዳናለ ጌታችን ፡፡ ክርሰቶስ የሞተበትን የህይት መንገድ ባ10 ሳንቲም ክር ለውጦ የ10 ሳንቲም ክር ባነገቱ ቋጥር ነፈሱን ለነፍስ አባቱ አደራ ሰጥቶ ቃሉን እንዳያወቅ ተደርጎ በሞት መንገድ ለሚሄደው መከር በክርሰቶስ የማዳን ወንጌል ወደአረፍቱ ሊሰበሰብ ይገባዋልና፡፡ጊዜውም አሁን ነውና፡፡

   Delete
  4. ልጅ ግርማ ፎቶግራፉ ያንተ ከሆነ ገና ጡት ያልጣልክ ውርንጭላ ትመስላለህ። ምላስህ ግን አርባ ክንድ ተዘረጋ። ይህ ደግሞ የዚህ አለም ገዥ አሰራር ነው። ታዲያ ስም አላዘዋወርክም የዲያብሎስ ልጅ ስለክርሰቶስ የሚናገረው ሳይሆን እንዳንተ ያለ የተጠናወተው አንደበተ ተውሳክ የሳጥናኤል ደቀመዝሙር ነው። ጌታህም እሱ ስለሆነ መገሰጽ ስለማያውቅ አስፈንጥሮ ወደ ጥልቁ ይወረውርሃል። ጡት እስክትጥል እንኳ አደብ ብትገዛ ምን ነበረበት? ጡጦ አጉርሰው የማቅን ቱልቱላ መንፋትና ማጓራትን ስላስተማሩህ ምን ታደርግ የንጉስህን የጌታህን የዲያብሎስን አዋጅ ትለፍፍ ወጣህ። የያዘህ አባዜ እንዲለቅህ እግዚአብሔር ይርዳህ።

   Delete
 3. Amen!!! Great article.

  ReplyDelete
 4. በሬ ወለደ ወሬማ ታውቁበታላችሁ ያባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች አሁን እነ ዲ/ን ያረጋልን ለመስደብ በቃህ እርጉም.....ጌታ ይገስጽህ!!!!

  ReplyDelete
 5. የተፃፈው ቃል እውነት ነው አይደለም? ማየትና መረዳት ከሚገባችሁ ውጪ ከፅሁፉ ጋር ግንኙነት በሌለው ጉዳይ ላይ መነታረክ አግባብ አይደለም። ኦርቶዎች እውነት ሲያግጥማቸው ይወራጫሉ። ግን ለምንድነው?

  ReplyDelete
 6. እናንተም አበዛችሁት ሰይጣን በገዛ ግዛቱ አይንገስ ነው እንዴ? ጀሌዎቹ ነግደው፤ ዘርፈው፤ ቀጥፈው፤ ዘሙተው፤ ወዠንብረው አይኑሩ እያላችሁ እኮ ነው። እኮ በማን ግዛት? አካይስትን ስራ ማስፈታት እኮ ነው የፈለጋችሁት። መጽሀፍ እንደሚለው ሳጥናኤል ገብርኤልን ሃያ አንድ ቀን በአየር ላይ ገትሮ ከተልእኮው ቢያዘገየው ሚካኤል መጥቶ ረዳው። ኢየሱስ ክርሰቶስስ? ክርስቶስማ ሞቶ በመነሳቱ ድል ነሳው። እኮ እኛስ? እኛማ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛችን አድርገን የተቀበልነው ይኸው ትክክለኛውን ወንጌል እየሰበክን ጌታ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ የዲያብሎስን ጎራ እናተራምሰዋለን። ምክንያቱም ገብርኤልን የታገለበት ኃይሉ በክርስቶስ ስለተመታ በኛ ላይ ምንም ኃይል የለውም። ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ እነማቅና መሰሎቻቸው የዲያብሎስ ልጆች የተካኑትን ጫጫታ፤ ሁከትና ስድብ ባልተገራ አንደበታቸው እንደ አይጥ በየስርቻው እየተሽሎኮሎኩ መርዛቸውን ይረጫሉ። እግዚአብሔር መሃሪ ነውና ይቅር ይበላቸው። አባ ሰላማ ሳታዳሉ ሁሉንም ማቅን ጨምሮ ማለት ነው እንዲተነፍስ ሃሳቡንም እንዲገልጽ ስላደረጋቸሁ ልትመሰገኑ ይገባል። እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 7. ተሳዳቢ ትውልድ በጣም ያሳዝናል ያለ ስድብ ሌላ ስራ የለም ለነገሩ ።በህዝቡ ተሳዳቢነት ምክንያት ሀገሪቷ በረከት አጠች።የተረገመች ሆነች።ስድብ አቁሙ የአጥያተኞዘች መገለጫ ነው ።መፍረድ አቁሙ ስራችሁ አይደለም የፈጣሪ ስረሰ እንጂ ።ሰው ከመሳደባችሁ በፊት ስለ እራሳችሁ ሀጢያት አስቡ።የሚሰለች የሚያሰለች ትዉልድ።

  ReplyDelete
 8. ወንድሞች የስቅለትን በዓል በእመቤታቸን በዓል መሻር ከተቻለ በኦርቶዶስ ቤተ ከርስትያናችን ውስጥ ተሐድሶን በትክክል ተቀብለናል ማለት ነው። እልልልል..............እግዚአብሔር እኛ በክነ ጥበቡ ተሐድሶ ማለት ምን ማለት እንደሆን እያስተማረን ነው። የጌታን ስቅለቱ ስግደት መሻር ከቻልን ሌላ ምን ለሆን እንፈልጋለን።አምላክንና እናቱን ማነጻጻር በቤተ ከርስቲያናችን ውስጥ አድስ ትምህርት ተጀምሮዋል። ስሙ ላልሰሙት አሰሙ ..........

  ReplyDelete
 9. ተው ማነህ? እንዴት እንዴት? ስቅለትን ሻርከው ቤልዚበብ?? እንዴት ሰነበትክ፤ የኛ ጌታ በመስቀል ላይ ሆኖ እኮ ነው "ተፈጸመ" ያለው ያኔ እኮ ነው ድባቅ የተመታኸው። ሲኦል እኮ ጥርስ ማፋጨት ነው ያለው። የምን እልልታ ነው የምታወራው። ጌታ ገስጾ ዝም በል አላለህም እንዴ? የሚሰማህ የለም አንተው ቱልቱላህን ንፋ። ይኸ ተሐድሶ የምትለው ቃል በጣም ከባድ ነው እኮ። ሲሉ ሰምተህ እሱ አዋቂ እንዲሉህ መልሰህ ታናፋለፍ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነት የማይዋጥልህ በመንፈስህ ደካማ ነግር በክፉ አንደበትህ ጠንካራ የሆነክ ወንድሜ ሆይ ስማ ተረዳ እውነት እውነት ነውና። በቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን አዲስ አስተምህሮ መጀመሩ ነው። ጌታችንና አምላካችን ለሰው ልጆች ሁሉ ራሱ በመስቅል ላይ በፍቅሩ ነፍሱን ሰጥቶ ድያብሎስን ድል በማድረግ ያዳነን አምላክ ብቻ ነው በማለት እውነቱን እንናገራለን እንጅ እመቤታችንን ከፈጣሪዋ በማስበለጥ የጌታን ስለት እለት ስግደትን መከልከል አዲስ አስተምህሮ በዚህ ክፉ ዘመናችን በቅድስት ቤተ ከርስቲያናችን መጀመሩ አሳዛኝና አሳፋር ነው። ለምን ተሐድሶን እን ቃወማለን እየተባለ በማቅ አውደ ምህርቶችን ከፉ ትምህረቶች ይበተናሉ። ራሱ ማቅ አባለትና መሪ ጳጳሳት በራሳቸው ግዜ እምነቱዋን እየሻሩ እያየን ነው። ለዚህም ነው ጌታችን ለኒቆዲሞስ በግልጽ እንድህ በማለት በዮሐ ወንጌል ም 3 ቁ ጥር 11 ላይ የተናገረው በቅ ትምህርት ይሆንሃል " እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን የያነውንም እንመሰክራለን ምስክርነታችን አትቀበሉም" በማለት ግልጽ ትምህርት ሰጥቶናል ክብር ይግባው ለስም አጠራሩ ለአምላካችን ።

   Delete