Wednesday, April 6, 2016

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከሃላፊነት መነሳትና በምትካቸው መ/ር ጎይትኦም የመሾማቸው ጉዳይ

Read In PDF

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስከያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ከሃላፊነታቸው መነሳት ወደ ከረመ ዜናነት ተሸጋግሯል፡፡ ሥራ አስኪያጁ እንደማንኛውም ሰው ደካማ ጎን ቢኖርባቸውም የፈጸሟቸው ስሕተቶች ቢኖሩም በሃላፊነት በቆዩባቸው ጊዜያት እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ሥራዎችን መሥራታቸው ይታወቃል፡፡ የሀገረ ስብከቱን የፐርሰንት ገቢ ከፍ ከማለቱ የተነሳ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሕንጻ ግንባታ 6 ሚሊየን ብር፣ ለትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግ የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ሥራ እንዲውል በማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል፡፡


የቅጥር ሁኔታን በተመለከተ በመስፈርት በሙያ ብቃትና በውድድር እንዲፈጸም በማድረግ ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል፡፡ አጥቢያ የሌላቸው ሰባክያን ማስረጃቸውን አቅርበውና ተፈትነው ሰባት ሰባክያን ፈተናውን አልፈው ወደ 30 የሚጠጉት ደግሞ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተጠባባቂ ሆነዋል፡፡ በሚገኘው ክፍት ቦታም ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ሰባክያነ ወንጌል መብትና ነጻነት አስከብረዋል፡፡ መድረኩን ከስብከተ ወንጌል ውጪ ይፈነጩበት የነበሩ፣ ሃይማኖትና ፖለቲካን እያጣቀሱ ይዘሉበት የነበሩ ሰዎች ተገቢ ቦታቸውን እንዲይዙ አድርገዋል፡፡ ይህም ቅጥር ያልሆነ ማንኛውም ሰባኪ እንዳይሰብክ ጥብቅ መመሪያ በማስተላለፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በዚህም ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች እና ሌሎችም ሰባኪዎች በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ውስጥ ከአውደ ምሕረት ውጪ በማድረግ አውደ ምሕረቱ በአብዛኛው ጤናማ ወንጌል የሚሰበክበት እንዲሆን ለማድረግ ተችሏል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለይ ስብከተ ወንጌልን በሚመለከት ተገቢ ትኩረት በመስጠት የጽንፈኝነት አዝማሚያ የሚታይባቸውን እንደ ማቅ ያሉትን ቡድኖች በተመለከተ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት አቋም እንዲወሰድ አድርገዋል፡፡ በቅርቡም ለፓትርያርኩ ደብዳቤ ምላሽ በጻፈው ማቅ ላይ በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት አለቆችና ሌሎችም ሃላፊዎች ዘንድ አቋም እንዲያዝና የማቅ አውደ ርእይ ይታገድ ዘንድ የአቋም መግለጫ እንዲወጣ በማድረግ ማቅን ታግለዋል፡፡ ከእዚህ የተነሣ የማቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ በሀገረ ስብከቱ እየተገታ የሚገኝ መሆኑን መታዘብ የሚቻል ሲሆን በላፕቶፕና በፕሮጀክተር ዲስኩር ያበጡ  አውደ ምሕረቶች እንዲተነፍሱ ተደርጓል፡፡ ሌላው በቅርቡ በሀገረ ስብከቱ ድረ ገጽ ላይ እንደ ተገለጸው በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ሳይቀር መምሪያ እስከ መያዝ የደረሱ እንዲሁም በየአጥቢያው ማቅ የሰገሰጋቸው በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ መቀጠራቸው ተደርሶበት የታሠሩ ነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በሦስት የፖሊስ መምሪያዎች በፎርጅድ የታሠሩ የቤ/ክ አገልጋዮች ቁጥራቸው 14 ደርሶአል፡፡ በአጠቃላይ ሀገረ ስብከቱ የሄደባቸው መልካም ነገሮች በርካታ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ቢሆንም ካለው ገቢና ጠቀሜታ እንጻር የብዙዎች ዓይን የሚያርፍበት ሀገረ ስብከት ስለሆነ ብዙ ውጥረት ያለበት ቦታ ነው፡፡ የራሳቸውን ሀገረ ስብከት እርግፍ አድርገው በመተው የፓትርያርኩ ሀገረ ስብከት በሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚያገኙትን ልዩ ልዩ ጥቅም ከግምት በማስገባት ከጀርባ ሆነው በመረበሽና በማስረበሽ፣ ጣልቃ በመግባትና ሴራ በማስጎንጎን በሊቀ ማእምራን የሥራ አስኪያጅነት በዚህ ወቅት ከሚጠቀሱት መካከል የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አባ ማቴዎስ አንዱ ናቸው፡፡ በጣም የሚገርመው በዚህ ወር አባ ማቴዎስ ከሀገረ ስብከታቸው ከወላይታ የመጡ የአስተዳደር ሰዎችንና የአገር ሽማግሌዎችን ያነጋገሩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የተወሰኑ ሰዎችን ወደ ወላይታ ልከዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ 28 አብያተ ክርስቲያናት በወላይታ ዳውሮ ሀገረ ስብከት በመዘጋታቸው ነው፡፡ እርሳቸው ሀገረ ስብከታቸውን እርግፍ አድርገው በመተው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ስፍራ ያጣውን ማቅን እንዴት ቦታ እንደሚያስዙ በማሰብና በመሥራት ነው ጊዜያቸውን የሚያጠፉት፡፡   

አዲሱ ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይትኦም ያዩኒ መሾሙ እንደ ተሰማ ሖራ “የተሃድሶ ተላላኪ” በማለት ነገር ጀምራለች፡፡ የሚገርመው ነገር አዲሱን ሥራ አስኪያጅ ለምን ቀድሞ እንዲህ አላለችም? የዚህ ምክንያቱ ሌላ ሳይሆን መ/ር ጐይቶም የማቅን ህገወጥ አሠራር የሚቃወም በመሆኑ ነው፡፡ ማቅ ህልውናው የቆመው ስለ ተሃድሶ በማውራት ስለሆነ በመ/ር ጐይትኦም ሹመት በጣም ደንግጧል፡፡ መ/ር ጎይትኦም መሾሙ እንደተሰማ ከሰዓት በኋላ የማቅ ጉዳይ አስፈጻሚዎች ሹመቱ እንዳይጸድቅ ጫና ያሳድሩ ዘንድ በየጳጳሳቱ ቤት ደጅ ሲጠኑ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንዲህ ባለ አጋጣሚ እንዲህ ዓይነቱን ሥራ የሚሠሩና ለዚሁ ተብለው የተመደቡ የማቅ ጉዳይ አስፈጻሚዎች እንዳሉ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ጾም ሲሆን ፍራፍሬ ይዘው በፍስክ ደግሞ ሙክት ውስኪ ይዘው ጳጳሳቱ የማቅን አቋም እንዲያራምዱ ሎቢ የማድረግ ሥራ እንደሚሰሩ ምንጮች አክለው ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ የታሰበው ሳይሆን ስለቀረና ሹመቱ ስለጸና በማህበረ ቅዱሳን ሰፈር በሊቀ ማእምራን የማነ መነሣት የተፈጠረው ደስታ ሙሉ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

መ/ር ጎይትኦም በሀገረ ስብከቱ የተጀመረውን መልካም ሥራ እንደሚቀጥልበትና ለማቅ ህገወጥ አሠራር ፊት እንደማይሰጥ ማቅ የተገነዘበ ይመስላል፡፡ ለዚህ ነው አስቀድሞ እንዳይመረጥ ሲሯሯጥ የነበረውና የተለመደ ፍረጃ ውስጥ የገባው፡፡ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ከቤተክርስቲያኒቱ ኮሌጅ ተምሮ የወጣ ኮሌጆቹን በመምራትና በማስተዳደር የሚታወቅና በማቅ ስማቸው ለጠፋው ኮሌጆች ከሚቆሙት አንዱ ስለሆነ አሁንም የተጣለበትን ሃላፊነት ይወጣል የሚል ትልቅ እምነት አለ፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ካሁኑ በመምህር ጎይቶምና በሊቀ ማእምራን የማነ መካከል ጠላትነት እንዲመሰረት ለጥላቻ የሚያነሳሳቸውን ዘገባ መስራት ጀምሯል። ሆነ ብሎም መምህር ጎይቶምን ከንቡረ እድ ኤልያስ ጋር በማገናኘት በሊቀ ማእምራን የማነ እና በንቡረ እድ ኤልያስ መካከል አለ የሚባለውን አለመግባባት በማነሳሳት ሊቀ ማእምራን የማነ ለመምህር ጎይቶም በጎ አመለካከት እንዳይኖረው ለማድረግ እየሞከረ ነው። ተሰናባቹም ሆነ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሳያስቡት በማኅበረ ቅዱሳን ወጥመድ ውስጥ እንዳይገቡ ሊጠነቀቁ ይገባል።12 comments:

 1. yemane yewedaj meker bisema noro manim ainekawem neber gin...betam tibi yazew

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yetehadiso MegagnaApril 7, 2016 at 8:27 AM

   "Afincha(nose) simeta ayin (eye) yalekisal" just it is starting KUBA. MK the hero le missa sitasibu le kurisi Aderegachihu. Now we started on the head of corrupters & next will continue to others trush the so called hartikan (tehadiso). We will pull out like a spil from each structure of the church with help of the almighty of God yhr great.it is a matter of time.wait KUBA.....

   Delete
 2. Dingaye bewekitut enboch yetebalew neger new esti sira askiaju yeserut sihetet endinmaribet awitut beras metemamen yelelachihu silehone new ende lemedachihut neger mesirat jemerachihu emtsifew lesew lemenger silehone batwetut gid yelegnim mechem satanebut ataswegidutim min aynet tefetiro endalachihu ligebagn alchalem yediro yebete mengist sir betoch weyim ef ef colledge mirukan nachihu ef ef colledge buna abetariwoch malet new lenante niseha kemelemen wuchi min yibalal timehrt yemaysetibet blog bealem binor yihe new.

  ReplyDelete
 3. You are object is. Only opposite Ing Mk not speaking the truth. Is gathering 0.5 million burr from poor people contribution is correct?

  ReplyDelete
 4. የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል እነዚህ ሰዎች ካለፈው ታሪክ መማር አለባቸው የእርስ በእርስ ሽኩቻ ለማን እንደሚጠቅም ከቀደሙት የአባቶቻችን ታሪክ መገንዘብ ይቻላል ሁለት ወንድማማቾችን በማደባደብ ለማትረፍ የሚሮጡ እኩያን ተስፋ ቢሶች ስላሉ ከወዲሁ የሃሳብ ልዩነት በማጥበብ ለጠላት በር ከመክፈት በመታቀብ ያለውን ችግር መፍታት ያስፈልጋል አለበለዚያ እንደከዚህ ቀደሙ ተያይዞ መጥፋት ይመጣል ።

  ReplyDelete

 5. በተጨማሪም ለራሱ የሕንጻ ግንባታ፤እንጨት ከሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር ፤ከምስኪን ምእመናን ኪስ የተሰበሰበዉን ከየአድባራቱ በጥቂቱ 3 ሚሊየን ብር፣ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች ኪራይ፤ ከመንበረ ፕትርክናቸው ሥር ባለች አጥቢያ የቤተ ክርስቲንን ገንዘብ አናስበላም ያሉ ካህናትና ምእመናን በማባረር…..አረ ስንቱ..ስንቱ …ይነገር

  አቤት አባ ሰላማዎች ምን ሰላም ላችሁ እናንተ

  ReplyDelete
 6. ቀጣፊዎች መቼም አይሳካላችሁም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Who said this is it Mahber kidusan or Aba selama ......"እውነት እነ ንቡረ እድ ኤልያስ ለቤተ ክርቲያን ከመቆርቆር ወይስ ሌላ ዓላማ አላቸው? ትናንትና እኮ በየ አድባራቱ ሲዞሩ ከሄዱበት ደብር ከ15 ሺሕ እስከ 20 ሺህ ድረስ የኮቴ እንዳላስከፈሉ ዛሬ ተቆርቋሪ መስለው መቅረባቸው ለጥቅማቸው እንጂ ለቤተክርስቲያን አስበው እንዳልሆነ የምናውቅ እናውቃለን፡፡ .............." The king of the lair, aba selam blog

   Delete
 7. አባ ሰላማዎች በጣም እናመሰግናለን በ AnonymousApril 5, 2016 at 11:13 PM የሰጠነውን አስተያየት ሳይቆራረጥ አውጥታችሁታል የማ/ቅ ልሳን የሆነው ሐራ ብሎግ ‹‹ሰበር ዜና -አማሳኙ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ተወገደ! የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪው ጎይቶኦም ያዩኒ ተተካ፤ 3 ተጨማሪ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችም ተነሥተዋል››› በሚለው ዜናው ሥር fesha negash April 5, 2016 at 10:32 am በሚል አድራሻ ይህንኑ አስተየየት ልከነው ነበር፤ ነገር ግን ማ/ቅን የሚመለከተውን የሚከተለውን አረፍተ ነገር ‹‹‹ሌላው ቀርቶ ቅርባችሁ ያለው ማህበር እንኳን በአግባቡ ልትይዙት ስላልቻላችሁ እና ስላልመራችሁት ዛሬ አጉራ ዘለል ሆኖ ሽቅብ ገልብጦ እየጋለባችሁ ነው፡፡››› በመቁረጥ አውጥተውታል፡፡ ማቆች(ማህበር ቅዱሳን) አውነት እስከ መቼ እየመረረው ይኖራል!!!!!!

  ReplyDelete
 8. ጎይቶም እንኳን ደስ ያለህ….. ለምን ቢባል አንተ እንደሌሎች በዘር፣በገንዘብ አልታማህም፤መልካም ሥራ ሰርተ እግዚአብሔርን ደስ እንደምታሰኝ ተስፋ አለኝ፡፡ በርትተ ወንጌል እንዲሰበክ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተጠብቆ ምእመናን እንዲገለገሉ አድርግ፤ በምትችለዉ መጠን የአስተዳደር ሥራዉ እንዲቃና እንድትተጋ በጌታ ሥም አሳስብሓለዉ፡፡ ቅዱስ ፓትርያሪካችንንም ኢያደመጥክ ኢየታዘዝካቸዉ የጀመሩትን ነገር ከግብ እንዲያደርሱ እርዳቸዉ አንተም ታሪክ ሥራ፣ ለቡድን የሚታገሉትን ወገኖች ተዋቸዉ፤ በርታ፣ጸልይ በንቃት የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት ትጋ፤ በር የሚከፍት የሚዘጋ አንድዬ ቢቻ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 9. yetewedaderut betemelekete ergetegna nachu musna yelem?

  ReplyDelete
 10. Aba selamawoch ene ewunetegnoch honachihu alagegnehuachihum. Ahun ahun yazagadgun maninet tereterhu . Yemane yekefekew leba meselegn . Benante zend sew mahiberekidusan kalhone tifatu aygaletim? Lemin mk adluawi tebale? Tea zebra.

  ReplyDelete